torsdag 26. februar 2015

ለዲያቆን ዳንኤል ክብረት ፣ ከኤርሚያስ ለጋሲ


ከአንድ ሰአት በላይ የፈጀውን ጥናታዊ ጵሁፍህን ሰማሁት። ሰምቼ ስጨርስ ደነገጥኩ። ከራሴም ጋር ለሰአታት ሙግት ገጠምኩ ። ኢህአዴግን ለቅቄ የወጣሁት ልቤ የፈቀደውን በነጳነት ለመናገር ነውና የማውቀውን እና የሚሰማኝን መናገር እንዳለብኝ ተሰማኝ ። ርግጥ በሐይማኖት ጉዳዬች ላይ መናገር ከባድ እንደሆነና ዋጋ እንደሚያስከፍል ጠንቅቄ አውቃለሁ ። በሌላ በኩል የሚያውቁትን አለመግለጵም የፀፀት ዋጋ አለው። በመሆኑም ባለመናገሬ ከሚሰማኝ ሙግት መናገሩን ስለመረጥኩ የሚከተለውን አጭር አስተያየት ለመስጠት ተገደድኩ።

1• ያቀረብከውን መረጃዎች እንዴት እንዳሰባሰብካቸው የተገለፀ ነገር የለም። በተለይም በድህረና ቅድመ ምርጫ 97 ባሉት ሶስት አመታት( ከኃላም ከፊትም) ያቀረብካቸውን መረጃዎች ምንጭ ማወቅ እፈልጋለሁ ። ይህን ጥያቄ የማነሳበት መሰረታዊ ምክንያቶች ስላሉኝ ነው።
1•1• በኢትዮጵያ አቆጣጠር 2001 አ• ም• ኢሕአዴግ ለሕዝቡ ይዞለት የመጣው እቅድ " በአክራሪነት " ስም ሀይማኖቶችን ማዳከም ነበር። ይህንንም ለማቀጣጠል እንዲረዳው በኢህአዴግ ቢሮ፣ በኮሙዩኒኬሽን ጵ/ ቤት፣ ፌደራል ጉዳዬች እና ፌደራል ፓሊስ መረጃ እንዲሰባሰቡ ተደረገ። የእስልምና ጉዳዬች ላይ ዝርዝር ጥናቱን እንዲሰራ የቤትስራ የተሰጠው ሽመልስ ከማል ነበር። ዛሬ አንተ ካቀረብክልን ውስጥ ግማሹ የቃላት ለውጥ እንኳን ሳይደረግለት በሽመልስ ከማል ጥናታዊ ፅሁፍ የቀረበ ነበር። በወቅቱ እጅግ ከመደንገጤ የተነሳ ሽመልስ እንዴት እንዲህ አይነት ጥናት እንደሰራ ለማወቅ ከጀርባው መጓዝ ነበረብኝ ። መጓዜ ያልጠበኩትን ውጤት አመጣ። ሽመልስ በእስልምና ላይ ከፍተኛ ጥላቻ የያዘው በቤተሰቡ ውስጥ በተፈጠረው ምስቅልቅል እድገት መሆኑን ተገነዘብኩ። አባቱ በአንድ ወቅት የመስኪድ አስተዳደር ነበሩ። በኃላ የሳውዲ ጉዞ አድርገው ሲመለሱ አስተዳደሩን በመነጠቃቸው ከሀይማኖቱ በተቃራኒ ተሰለፋ ። " ከመካ መዲና ደርሶ መልስ" የሚል መጵሀፍ አሳትመው ክርስትና ተነሱ። ስማቸውም ወደ ሀይለየሱስ ተቀየረ። ባስታወቀው እርምጃ ቤታቸው ተመሰቃቀለ። ወንድማማች እና እህታማቾች የሚጠሩበት የአባት ስም እስከ መለያየት ደረሰ። ባጭሩ የሽመልስ ፀረ -እስላም የመሆን ምንጩ ይሄ ነው። በመሆኑም በሽመልስ ሲቀርቡ የነበሩ ዳታዎችና ትንታኔዎች እንደወረዱ ከአንተ ሲቀርቡ ስሰማ የመረጃ ምንጭህን ተጠራጠርኩ። በተለይ ቴኳንዶ ፣አክሱም፣ መያዶች …ወዘተ ብለህ የገለጵከው የካርቦን ግልባጭ ሆኖ አግኝቸዋለሁ።
1•2• ሌላኛው ዳታ የሰበሰበው የፌደራል ጉዳዬች ሚኒስተር የነበረው ዶክተር ሽፈራው ከፓሊስ ጋር በመሆን ነበር። ዶክተሩ ያጠናቀረው መረጃ ተመሳሳይ ሲሆን በማጠቃለያው " የኦርቶዶክስ አክራሪነት አለ" የሚል ነበር። የአክራሪነቱ አስኳል ማህበረ ቅዱሳን እንደሆነ አፅንኦት ሰጥቶበት ነበር። ይህ የዶክተሩ መረጃ በአንተ ጥናታዊ ፅሁፍ ላይ አልቀረበም ።
( ግምቴን አስቀምጬ ለማለፍ ይህን የዶክተር ሽፈራው ዳታና ትንታኔ ለሌላ የእስልምና መምህር እንዲደርሰው ይደረግና እንደአንተ እንዲያቀርብ ይደረጋል ። ርዕሱንም " የኦርቶዶክስ አክራሪነት " ብሎ እንዲጠራው ይደረጋል ።)
2• የመረጃዎቹ ምንጭ እንደተጠበቀ ሆኖ ኩነቶቹ ሲፈጠሩ ሀገሪቷ የነበረችበትን ፓለቲካዊ ሁኔታ ከግምት አላስገባህም። ለምሳሌ ከምርጫ 97 በኃላ በኦሮሚያ የተከሰቱት የሐይማኖት ግጭቶች የተጠነሰሱት በአቶ መለስና ደህንነት ጵ/ ቤት ሲሆን ዋነኛ አሰፈጳሚዎቹ እነ አባዱላና የኦህዴድ ካድሬዎች ነበሩ። " ቅንጅት የክርስቲያን ጠበቃ ነው" የሚለው መልእክት የተቀረፀው አንተ በጥናታዊ ጵሁፍህ ላይ " ውሸት ሲደጋገም እውነት ይሆናል" የሚለው መርሆ አቀንቃኝ የሆነው አቶ በረከት ነው። በየጉራንጉሩ መልእክቱን ያሰራጩት ደግሞ " እኔ ከሞትኩ… " በሚለው ብሂል እነ አባዱላና ጁነዲን ናቸው። በተለይ በድሬደዋ የጠነሰሱት ሴራ ባይከሽፍ ኖሮ ዘግናኝ እልቂት ይከሰት ነበር። በመሆኑም ከምርጫ 97 በኃላ የተከሰቱት ግጭቶች ( በተለይ በኦሮሚያ) ጠንሳሾቹ አሁን እየመሩን ያሉት ፓለቲከኞች ሲሆኑ መንስኤውም ፓለቲካው የፈጠረው ነበር። አንተ ግን በየትኛው ቦታ ላይ የፓለቲከኞቹን ሚና ማንሳት አልፈለክም ። ይልቁንስ መንግስት አበረደው፣ መከላከያ አረገበው ማለትን መርጠሀል። ጥናትህን ሰፋ ብታደርገው ኢትየጵያ ውስጥ አክራሪነት በዋነኛነት እየሰፋ የሄደው በፓለቲካው መበላሸት ምክንያት የተፈጠረ መሆኑን ትደርስበት ነበር። አሁንማ በድጋሚ ለማየት ጊዜው አልረፈደም።
3• በጥናታዊ ጵሁፍህ ላይ በአሁን ሰአት ያለውን የኢትየጵያ ሙስሊሞች " ኢትዬጲያዊነት የተላበሰ፣ ሰላማዊና ፍትሐዊ ጥያቄ" ማንሳት አልፈለክም ። እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የተቃወሙት የመንግስት ጣልቃ ገብነት ነው።ኢህአዴግ ከሀይማኖቱ ላይ እጁን እንዲያነሳ ነው በሰላማዊ መንገድ እየጠየቁ ያሉት። አመራራችን በእኛ ይመረጡ፣ ተቋማችንን ራሳችን እናስተዳድር የሚል ነው። ለዚህ ደግሞ እኔ በየትኛውም ቦታና ሰአት ምስክር መሆን እችላለሁ። ታዲያ አክራሪን፣ አክራሪ ካልሆነው ለይቶ የማስረዳት አላማ ካነገብክ ለምን ፍትሐዊ የሆነውን ይህን ጥያቄ ሳታነሳ ቀረህ? እንደ ገዥዎቻችን " የሙስሊሙ ጥያቄ አክራሪነት የወለደው ነው" የምትለን ከሆነም ወደ መድረክ አውጣውና እንነጋገርበት ።
4• አጀንዳህ ስለ " ሙስሊም አክራሪነት " ሆኖ ወደ ማጠቃለያህ ላይ በውጭ ሀገር ያለውን ሲኖዶስ ወደ መዝለፍ ለምን ተሸጋገርክ። ከአንደበትህ የወጣው ቃል " የሐሰት ሲኖዶስ ተቋቁሞ መንጋ የማይጠብቅ ጳጳሳት ይሾማል " የሚል ነው። ይህ ንግግር በራሱ አንድነት የሚያመጣ ነው? ውጭ ያለው ሲኖዶስ የሐሰት ነው / አይደለም ከሚለው ትርክት በፊት ይህ እንዲፈጠር ያደረገው ምክንያት ምንድነው የሚለውን ብታነሳ የተሻለ መልስ ታገኝ እንደነበር እገምታለሁ። ሐገር ቤት ያለውን ሲኖዶስ ማን ከጀርባ ሆኖ እንደሚያሽከረክረው ካላወክ በኢትዮጵያ ምህዳር ላይ መኖርህን እንድጠራጠር ያደርገኛል።
4• ሌላኛው " ለምን አሁን?፣ ምን አዲስ ነገር አለ?" የሚል ጥያቄ እንዳነሳ አድርጐኛል ። የሙስሊሞች ሰላማዊ ትግል በተጠናከረበት፣ መንግስት በጅምላ ማሰር በጀመረበት ፣ ማህበረ ቅዱሳን ላይ በተዛተበት ወቅት ለምን የሚከፋፍል አጀንዳ ይዞ ብቅ ማለት ተፈለገ? የማን አጀንዳ ነው እየተራመደ ያለው የሚለውን ማየት ተገቢ ይሆናል ።
ለዲያቆን ዳንኤል ክብረት ፣

ከአንድ ሰአት በላይ የፈጀውን ጥናታዊ ጵሁፍህን ሰማሁት ። ሰምቼ ስጨርስ ደነገጥኩ ። ከራሴም ጋር ለሰአታት ሙግት ገጠምኩ ። ኢህአዴግን ለቅቄ የወጣሁት ልቤ የፈቀደውን በነጳነት ለመናገር ነውና የማውቀውን እና የሚሰማኝን መናገር እንዳለብኝ ተሰማኝ ። ርግጥ በሐይማኖት ጉዳዬች ላይ መናገር ከባድ እንደሆነና ዋጋ እንደሚያስከፍል ጠንቅቄ አውቃለሁ ። በሌላ በኩል የሚያውቁትን አለመግለጵም የፀፀት ዋጋ አለው ። በመሆኑም ባለመናገሬ ከሚሰማኝ ሙግት መናገሩን ስለመረጥኩ የሚከተለውን አጭር አስተያየት ለመስጠት ተገደድኩ ።

1 • ያቀረብከውን መረጃዎች እንዴት እንዳሰባሰብካቸው የተገለፀ ነገር የለም ። በተለይም በድህረና ቅድመ ምርጫ 97 ባሉት ሶስት አመታት ( ከኃላም ከፊትም ) ያቀረብካቸውን መረጃዎች ምንጭ ማወቅ እፈልጋለሁ ። ይህን ጥያቄ የማነሳበት መሰረታዊ ምክንያቶች ስላሉኝ ነው ።
1•1 • በኢትዮጵያ አቆጣጠር 2001 አ • ም • ኢሕአዴግ ለሕዝቡ ይዞለት የመጣው እቅድ ' በአክራሪነት ' ስም ሀይማኖቶችን ማዳከም ነበር ። ይህንንም ለማቀጣጠል እንዲረዳው በኢህአዴግ ቢሮ ፣ በኮሙዩኒኬሽን ጵ / ቤት ፣ ፌደራል ጉዳዬች እና ፌደራል ፓሊስ መረጃ እንዲሰባሰቡ ተደረገ ። የእስልምና ጉዳዬች ላይ ዝርዝር ጥናቱን እንዲሰራ የቤትስራ የተሰጠው ሽመልስ ከማል ነበር ። ዛሬ አንተ ካቀረብክልን ውስጥ ግማሹ የቃላት ለውጥ እንኳን ሳይደረግለት በሽመልስ ከማል ጥናታዊ ፅሁፍ የቀረበ ነበር ። በወቅቱ እጅግ ከመደንገጤ የተነሳ ሽመልስ እንዴት እንዲህ አይነት ጥናት እንደሰራ ለማወቅ ከጀርባው መጓዝ ነበረብኝ ። መጓዜ ያልጠበኩትን ውጤት አመጣ ። ሽመልስ በእስልምና ላይ ከፍተኛ ጥላቻ የያዘው በቤተሰቡ ውስጥ በተፈጠረው ምስቅልቅል እድገት መሆኑን ተገነዘብኩ ። አባቱ በአንድ ወቅት የመስኪድ አስተዳደር ነበሩ ። በኃላ የሳውዲ ጉዞ አድርገው ሲመለሱ አስተዳደሩን በመነጠቃቸው ከሀይማኖቱ በተቃራኒ ተሰለፋ ። ' ከመካ መዲና ደርሶ መልስ ' የሚል መጵሀፍ አሳትመው ክርስትና ተነሱ ። ስማቸውም ወደ ሀይለየሱስ ተቀየረ ። ባስታወቀው እርምጃ ቤታቸው ተመሰቃቀለ ። ወንድማማች እና እህታማቾች የሚጠሩበት የአባት ስም እስከ መለያየት ደረሰ ። ባጭሩ የሽመልስ ፀረ - እስላም የመሆን ምንጩ ይሄ ነው ። በመሆኑም በሽመልስ ሲቀርቡ የነበሩ ዳታዎችና ትንታኔዎች እንደወረዱ ከአንተ ሲቀርቡ ስሰማ የመረጃ ምንጭህን ተጠራጠርኩ ። በተለይ ቴኳንዶ ፣ አክሱም ፣ መያዶች... ወዘተ ብለህ የገለጵከው የካርቦን ግልባጭ ሆኖ አግኝቸዋለሁ ።

1•2 • ሌላኛው ዳታ የሰበሰበው የፌደራል ጉዳዬች ሚኒስተር የነበረው ዶክተር ሽፈራው ከፓሊስ ጋር በመሆን ነበር ። ዶክተሩ ያጠናቀረው መረጃ ተመሳሳይ ሲሆን በማጠቃለያው ' የኦርቶዶክስ አክራሪነት አለ ' የሚል ነበር ። የአክራሪነቱ አስኳል ማህበረ ቅዱሳን እንደሆነ አፅንኦት ሰጥቶበት ነበር ። ይህ የዶክተሩ መረጃ በአንተ ጥናታዊ ፅሁፍ ላይ አልቀረበም ።
( ግምቴን አስቀምጬ ለማለፍ ይህን የዶክተር ሽፈራው ዳታና ትንታኔ ለሌላ የእስልምና መምህር እንዲደርሰው ይደረግና እንደአንተ እንዲያቀርብ ይደረጋል ። ርዕሱንም " የኦርቶዶክስ አክራሪነት " ብሎ እንዲጠራው ይደረጋል ።)

2 • የመረጃዎቹ ምንጭ እንደተጠበቀ ሆኖ ኩነቶቹ ሲፈጠሩ ሀገሪቷ የነበረችበትን ፓለቲካዊ ሁኔታ ከግምት አላስገባህም ። ለምሳሌ ከምርጫ 97 በኃላ በኦሮሚያ የተከሰቱት የሐይማኖት ግጭቶች የተጠነሰሱት በአቶ መለስና ደህንነት ጵ / ቤት ሲሆን ዋነኛ አሰፈጳሚዎቹ እነ አባዱላና የኦህዴድ ካድሬዎች ነበሩ ። ' ቅንጅት የክርስቲያን ጠበቃ ነው ' የሚለው መልእክት የተቀረፀው አንተ በጥናታዊ ጵሁፍህ ላይ ' ውሸት ሲደጋገም እውነት ይሆናል ' የሚለው መርሆ አቀንቃኝ የሆነው አቶ በረከት ነው ። በየጉራንጉሩ መልእክቱን ያሰራጩት ደግሞ ' እኔ ከሞትኩ... ' በሚለው ብሂል እነ አባዱላና ጁነዲን ናቸው ። በተለይ በድሬደዋ የጠነሰሱት ሴራ ባይከሽፍ ኖሮ ዘግናኝ እልቂት ይከሰት ነበር ። በመሆኑም ከምርጫ 97 በኃላ የተከሰቱት ግጭቶች ( በተለይ በኦሮሚያ ) ጠንሳሾቹ አሁን እየመሩን ያሉት ፓለቲከኞች ሲሆኑ መንስኤውም ፓለቲካው የፈጠረው ነበር ። አንተ ግን በየትኛው ቦታ ላይ የፓለቲከኞቹን ሚና ማንሳት አልፈለክም ። ይልቁንስ መንግስት አበረደው ፣ መከላከያ አረገበው ማለትን መርጠሀል ። ጥናትህን ሰፋ ብታደርገው ኢትየጵያ ውስጥ አክራሪነት በዋነኛነት እየሰፋ የሄደው በፓለቲካው መበላሸት ምክንያት የተፈጠረ መሆኑን ትደርስበት ነበር ። አሁንማ በድጋሚ ለማየት ጊዜው አልረፈደም ።

3 • በጥናታዊ ጵሁፍህ ላይ በአሁን ሰአት ያለውን የኢትየጵያ ሙስሊሞች ' ኢትዬጲያዊነት የተላበሰ ፣ ሰላማዊና ፍትሐዊ ጥያቄ ' ማንሳት አልፈለክም ። እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የተቃወሙት የመንግስት ጣልቃ ገብነት ነው ። ኢህአዴግ ከሀይማኖቱ ላይ እጁን እንዲያነሳ ነው በሰላማዊ መንገድ እየጠየቁ ያሉት ። አመራራችን በእኛ ይመረጡ ፣ ተቋማችንን ራሳችን እናስተዳድር የሚል ነው ። ለዚህ ደግሞ እኔ በየትኛውም ቦታና ሰአት ምስክር መሆን እችላለሁ ። ታዲያ አክራሪን ፣ አክራሪ ካልሆነው ለይቶ የማስረዳት አላማ ካነገብክ ለምን ፍትሐዊ የሆነውን ይህን ጥያቄ ሳታነሳ ቀረህ? እንደ ገዥዎቻችን ' የሙስሊሙ ጥያቄ አክራሪነት የወለደው ነው ' የምትለን ከሆነም ወደ መድረክ አውጣውና እንነጋገርበት ።

4 • አጀንዳህ ስለ ' ሙስሊም አክራሪነት ' ሆኖ ወደ ማጠቃለያህ ላይ በውጭ ሀገር ያለውን ሲኖዶስ ወደ መዝለፍ ለምን ተሸጋገርክ ። ከአንደበትህ የወጣው ቃል ' የሐሰት ሲኖዶስ ተቋቁሞ መንጋ የማይጠብቅ ጳጳሳት ይሾማል ' የሚል ነው ። ይህ ንግግር በራሱ አንድነት የሚያመጣ ነው? ውጭ ያለው ሲኖዶስ የሐሰት ነው / አይደለም ከሚለው ትርክት በፊት ይህ እንዲፈጠር ያደረገው ምክንያት ምንድነው የሚለውን ብታነሳ የተሻለ መልስ ታገኝ እንደነበር እገምታለሁ ። ሐገር ቤት ያለውን ሲኖዶስ ማን ከጀርባ ሆኖ እንደሚያሽከረክረው ካላወክ በኢትዮጵያ ምህዳር ላይ መኖርህን እንድጠራጠር ያደርገኛል ።

4 • ሌላኛው ' ለምን አሁን?፣ ምን አዲስ ነገር አለ?' የሚል ጥያቄ እንዳነሳ አድርጐኛል ። የሙስሊሞች ሰላማዊ ትግል በተጠናከረበት ፣ መንግስት በጅምላ ማሰር በጀመረበት ፣ ማህበረ ቅዱሳን ላይ በተዛተበት ወቅት ለምን የሚከፋፍል አጀንዳ ይዞ ብቅ ማለት ተፈለገ? የማን አጀንዳ ነው እየተራመደ ያለው የሚለውን ማየት ተገቢ ይሆናል ።

mandag 23. februar 2015

ኢህአዴግ በደንብ አላገለገሉኝም ያላቸውን የመጅሊስ አመራሮችን አባረረ



ከሕዝበ ሙስሊሙ ፍላጎት ውጪ በ2005 ዓ.ም የተመረጡት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) አመራሮች የመንግስትን ፍላጎት ማርካት ባለመቻላቸውና በአመራሮቹ ላይ እምነት በመጥፋቱ በአስቸኩዋይ ስልጣናቸውን እንዲያስረክቡ በማድረግ በምትካቸው ሌሎች ተመርጠዋል።
በአሁኑ ወቅት በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ሼህ ኪያር መሐመድ ኢማንን ወደ ስልጣን ያመጣውን የመጅሊስ ምርጫ ሕገወጥ ነው በማለት እንዲታገድ ለከፍተኛው ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ሰባተኛ ፍትሐ ብሄር ችሎት በወቅቱ ክስ አቅርበው የነበረ ቢሆንም ክሱ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቶአል፡፡
11 አባላት ያሉት የቀድሞ መጅሊስ አባላት ለኢህአዴግ የሚጠበቅባቸውን አገልግሎት አልሰጡም በሚል የሥራ አስፈጻሚ አባላትን በማስፈራራትና የኡላማዎች ም/ቤትን አንዳንድ ተለጣፊ የኢህአዴግ አባላትና ደጋፊዎችን በማስተባበር በፍጥነት ምርጫ እንዲካሄድ በተወሰነው መሰረት አስቸኳይ ጉባዔው ተካሂዷል።
አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔውም ሐጂ መሀመድ አሚን ጀማልን ፣ ከኦሮሚያ ክልል፣ ፕሬዝዳንት አድርጎ የመረጠ ሲሆን የአማራ ክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ተወካይ ሼህ ዑመር ይማም የጠቅላይ ምክር ቤቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ፣ የአዲስ አበባው ተወካይ ሐጂ ከድር ሁሴን ዋና ፀሃፊ ሆነው እንዲሰሩ ተመርጠዋል። ጠቅላላ ጉባዔው ቀደም ሲል የነበሩትን አመራሮችን ሙሉ በሙሉ በማንሳት በአዲስ እንዲተኩ አድርጎአል፡፡
የቀድሞ አመራሮች መጀመሪያውኑም የሕዝበ ሙስሊሙን ፍላጎት መሰረት አድርጎ በተካሄደ ነጻና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ወደሃላፊነት እንዳልመጡ የሚታወቅ ቢሆንም በእሁዱ ምርጫ ወቅት አመራሮቹ ከሃላፊነታቸው የተነሱት “የህዝበ ሙስሊሙን የልማት ጥያቄ አልመለሱም፣ አክራሪነትና ጽንፈኝነትን የመታገል ቁርጠኝነት አላሳዩም” በሚል መሆኑን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ኢሳት አሁን የተሾሙት የመጅሊስ አመራር አባላት ከመንግስት የደህንነት ሃይሎች ጋር በጋራ እንደሚሰሩ የሚያሳይ ከስብሰባ ላይ በድብቅ የተቀረጸ ድምጽ መልቀቁ ይታወቃል። ገዢው ፓርቲ ሙስሊም ወጣቶችን እንዳዲስ በመያዝ እያሰረ መሆኑን የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። የፌደራል ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም በቅርቡ በባህርዳር ባደረጉት የክልሎች የጸጥታ ግምገማ ላይ ፣ መንግስት በመጅሊስ አመራሮች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ፍንጭ ሰጥተው ነበር።

አዋራጅ ሰልፎችና ድግሶች እንዲያበቁ ህወሓት ይወገድ!


pg7-logoድግሶችን፣ ወታደራዊ ሰልፎችንና ሀውልቶችን ማብዛት የአባገነኖች ሁሉ የጋራ ባህርይ ነው። ዘረኛውና ፋሽስቱ የህወሓት አገዛዝም በሕዝብ እየተጠላ፣ እያረጀና እየወላለቀ በሄደ መጠን በየተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ደግሶ መብላት፤ ወታደራዊ ሰልፍና የመሣሪያ ጋጋታ ማሳየት እና በየመንደሩ ሀውልት መመረቅ ሙያው አድርጎት ቆይቷል።
የህወሓት ድግሶችና ፌሽታዎች የአገራችን ሀብት ከማሟጠጣቸውም በላይ የመንግሥት ሠራተኞችን፣ የአርሶ አደሮችንና የአነስተኛ ነጋዴዎችን ኪስ እያራቆቱ ናቸው። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጆች በእስር ቤቶች እየማቀቁ በሚገኙበት ሁኔታ፤ በመቶ ሺዎች የሚገመቱ የአማራ አርሶአደሮች ተፈናቅለው እያለ፤ በጋምቤላና በኦጋዴን ወገኖቻችን ላይ ዘግናኝ የጅምላ ጭፍጨፋዎች እየተደረጉ፤ በአፋር፣ በሲዳማ፣ በቦረና፣ በወልቃይት እና በመላው ኢትዮጵያ ግጭቶች በበዙበት፤ ሕዝብ እያለቀሰ ባለበት በአሁኑ ሰዓት “የብሔር፣ ብሔረሰቦች መብት ተከበረ” እያሉ እነዚህኑ በደል እየደረሰባቸው ያሉ ዜጎችን ማስጨፈር እና ለእነዚህ ጭፈራዎች በርካታ ሚሊዮኖች ብር ማውጣት በእጅጉ ያስቆጫል። እነዚህ ጭፈራዎች ለህወሓት ሰዎች የገቢ ምንጮች መሆናቸው ጥርጥር የለውም፤ ለድሀው ኢትዮጵያዊ ግን መራቆቻዎች ናቸው። ከዚህም አልፎ በዘረኝነት እየተበደለ ያለ ሕዝብ ስለእኩልነት ዝፈን ማለት ክብረ ነክ ተግባር ነው። ዘንድሮ በአሶሳ የተደረገው አገር አቀፍ ድግስ ካለቀ ጥቂት ወራት በኋላ አገራችን በሌላ ዙር የህወሓቶች ድግስ ተወጥራለች።
ሰሞኑን በባህር ዳር በተደረገው የጦር ሠራዊት ሰልፍ እና ሰልፉን ተከትሎ በነበረው የድግሶች ግርግር ከሁሉም በላይ የተሰደበውና የተዋረደው የሠራዊቱ አባል ነው። አዛዦቹ መቶ በመቶ የህወሓት አባላት የሆኑበትን ሠራዊት “የኢትዮጵያ መከላከያ” ተብሎ መጠራቱ ራሱ የሚያሳፍረው ኢትዮጵያዊ ወኔ በልባቸው ውስጥ እየተንቀለቀለና እልህ እየተናነቃቸው ያሉ የሠራዊቱን አባላት ነው። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እንዴት የኢትዮጵያ ጠላቶች በሆኑ የህወሓት ካድሬዎች ይመራል? እንዴት የአስር አለቃ እንኳን ሊሆን የማይገባው የህወሓት ካድሬ “ጄኔራል” ተብሎ ኢትዮጵያዊያን ወታደሮችን እንደ ሎሌው ያዛል? እንዴት አንድ የህወሓት ሎሌ ሹመት ተሰጥቶት እየፏለለ በልምድ፣ በትምህርትና በእውቀት የሚበልጠውን ኢትዮጵያዊ ተንቆ ይዋረዳል? ይህ ቁጭትና እልህ ሠራዊቱ የዘረኛውን ህወሓት ሰልፍ አድማቂ መሆኑ የሚያከትምበት ጊዜ ይበልጥ እንዲናፍቅ የሚደረገው ነው። አልያማ ሰልፍ ያሳመረ ሠራዊት ሁሉ አሸናፊ እንዳልሆነ የታወቀ ነው። በሰልፍ ብዛትና በመሣሪያ ትዕይንት ማሸነፍ ቢቻል ኖሮ የትም አገር አምባገነኖች ባልወደቁም፤ ህወሓት ራሱን ስልጣን ላይ ባልወጣም ነበር።
የህወሓት ምሥረታ 40ኛ ዓመት ድግስም ሌላው የታሪክና የሀብት ውድመት የሚያስከትል ክስተት ነው። የካቲት 11 ቀን 1967፣ ጥቂት ኢትዮጵያዊያን እናታቸውን ኢትዮጵያን ለመግደል ያሴሩበት እና ልጆች በእናታቸው ላይ ቢላዋ የሳሉበት ዕለት በመሆኑ በሀዘንና በሱባኤ እንጂ በድግስና በጭፈራ የሚታሰብ ዕለት አይደለም። ሲነሳ ምንም ይሁን ምን ዛሬ በደረስንበት ሁኔታ ሲገመገም፣ ኢትዮጵያ በታሪኳ ውስጥ ህወሓትን የመሰለ መሠሪና አድርባይ ድርጅት ገጥሟት አያውቅም። እነሆ ዘንድሮም ይኸው አድርባይ ድርጅት የመሪዎቹን የሀብትና ዝና ረሀብ ለማስታገስ ሲል ያልነበረ ታሪክ እየፈጠረ በድግስ ስም ከድሀው ገንዘብ እየሰበሰበ ለሀብታም የህወሓት አባላትና ደጋፊዎች ያሸጋግራል። የድግሶቹ ሁሉ አዘጋጆች፣ እቃ አቅራቢዎችና ተጠቃሚዎች ራሳቸው የህወሓት መሪዎችና አሽቃባጮቻቸው ሲሆኑ ከፋዩ ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው። በህወሓት ድግስ የሚባክነው የሕዝብ ሀብት ስንት ሆስፒታል ይገነባ እንደነበር ስናስብ እና ይህ ሀብት በተገቢው ቦታ ውሎ ቢሆን ኖሮ ዛሬ ስም ብቻ የያዙ ዩንቨርስቲዎቻችንን ትምህርት መቅሰሚያ ማድረግ እንችል እንደነበር ስናሰላ ሀዘናችን ጥልቅ ነው። ህወሓት ለልጅ ልጆቻችን የሚተርፍ ዕዳ እየቆለለ ዳንኪራ ሲረግጥና ሲያስረግጥ ማየትና መስማት ህሊና ሊሸከመው ከሚችል በላይ ነው።
አርበኞች ግንቦት 7፡ የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በህወሓት ወታደራዊ ሰልፍ እና የመሣሪያዎች ትዕይንት የሚረበሽ ድርጅት አይደለም። ይልቁንም በሰልፉ ጨኸት የታፈነው የኢትዮጵያዊ ወታደር ጩኸት ይሰማዋል። ኢትዮጵያዊ ወታደር በአዛዦቹ ላይ ጥርሱን ነክሶ፣ ቂም አርግዞ ሰልፋቸውን እንደሚሰለፍ አርበኞች ግንቦት 7 ያውቃል። አርበኞች ግንቦት 7፣ የሠራዊቱ አባላት ውስጥ ውስጡን እየተሰቃዩ የታዘዙትን መፈፀማቸው መብቃት አለበት ይላል፤ ወይ ተቀላቀሉን፣ አሊያም እውስጡ ሆናችሁ ሥርዓቱን የማዳከም ሥራዎችን ሥሩ። በእናንተ ውርደት የዘራፊዎች፣ ሙሰኖች፣ ጎጠኞችና ዘረኞች ደረት አብጦ መታየት የለበትም።
አርበኞች ግንቦት 7፣ የዘንድሮው የህወሓት 40ኛ ዓመት በዓል የጨረሻው በዓል እንዲሆን፤ ከርሞም ተመሳሳይ አዋራጅ በዓል እንዳናከብር፤ ሠራዊቱ በዘራፊዎች ታዞ የሚሰለፍበት ውርደት እንዲያበቃ ተባብረን ህወሓትን እንቅበር ይላል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

lørdag 21. februar 2015

ህወሃት ምንድን ነው? ገለታው ዘለቀ

TPLF inflation
በቅርቡ የህወሃት ኣርባኛ ዓመት ለየት ባለ መንገድ መከበሩ ገርሞኛል። በየዓመቱ እንደሚከበር ሁላችን እናውቃለን። ይሁን እንጂ የዓርባኛ ዓመቱ በዓል እንዲህ ለምን እንደተወራለት ለምን የሌላ ኣገር መሪ ሳይቀር እንደተጋበዘበት ኣልገባኝም። ብዙ ጊዜ እንዲህ ዓይነት ለየት ያለ ድግስ የሚደረገው የኢዮቤልዩ በዓል ሲከበር ነው። የሆነው ሆኖ የመነሻ ኣሳቤ ይሄ ኣይደለም። ህወሃት ኣርባኛ ዓመት በዓሉን ሲያከብር እኔ በህወሃት ተፈጥሮ ስደመም ነበር።
በርግጥ ኢትዮጵያ ኣሁን ላለችበት የተመሰቃቀለ ህይወት ሲንከባለሉ የመጡ ኣንዳንድ ችግሮች ኣስተዋጾ ቢያደርጉም የችግሩ ከፍተኛ ኣስተዋጾ ኣድራጊ ግን ህወሃት ነው። በየክልሉ የህወሃት ተከታዮች ኣስተዋጾኣቸው እንዳለ ሆኖ የህወሃት ድርሻ ግን በጣም ገዝፎ ይታያል። ግን …ግን ለምንድነው በህወሃት መራሹ መንግስት ጊዜ ኢትዮጵያ እንዲህ ዓይነት ኣስከፊ ችግር ውስጥ የገባችው? ብለን መጠየቅ ካማረን የህወሃትን ተፈጥሮና ኣነሳስ በሚገባ መረዳትን ይጠይቀናል። ብዙ ሰው ህወሃትን የሚገልጸው ዘረኛ…… ኣምባገነን በሚል ነው። እውነት ነው ህወሃት ጎጠኛና ኣምባገነን ነው::ከዚህ በተሻለና በጠራ ሁኔታ የህወሃትን ስርና መሰረት መመርመሩ የበለጠ የህወሃትን ተፈጥሮ እንድንረዳው ያደርገናል። ኢትዮጵያ በየጊዜው የሚገጥማት ችግር በርግጥ እንዴት ከዚህ ከህወሃት ተፈጥሮ ጋር እንደሚመጋገብ አብርቶ ያሳየናል። ከዚህም በተጨማሪ የሃገሪቱን ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ጉዳይ የበለጠ እንድንረዳው ያደርጋል።
ህወሃት ምንድን ነው?  ምን ዓይነት ጉዳይ ኣንገብግቦት ነው የዛሬ ኣርባ ዓመት ወደ በረሃ የገባው? ብለን ከጠየቅን የህወሃት ኣባላት እንደሚሉት የነጻነት (Liberty) ጥያቄ ጉዳይ ኣይደለም። የነጻነት ጥያቄ ስል ትግራይንም ማለቴ ነው። ህወሃት የታገለው ለትግራይ ነጻነትም ኣይደለም ማለቴ ነው።
ህወሃት ወደ ጫካ ሲገባ በርግጥ በወቅቱ የነበረው የፖለቲካ ድባብ ማለትም “የብሄር ብሄረሰብ ጥያቄ” የሚባለው ነገር ኣስተዋጾ ቢያደርግም ዋናው የዚህ ቡድን ጥያቄ የነጻነት ጥያቄ፣ የእኩልነት ጥያቄ፣ ወይም የዴሞክራሲ ጥያቄ ሳይሆን  በወቅቱ ያበሸቀውና ወደ ጫካ የሰደደው ጉዳይ የኢኮኖሚ ጉዳይ፣ የከፋ ድህነት ጉዳይ ነው። የህወሃት መስራቾች በወቅቱ ስርዓት ኣኩርፈው ወደ ጫካ ሲገቡ በነበራቸው ግምገማ መሰረት ትግራይ በጣም የተጎዳች፣ ረሃብ ያጠቃት ናት። ሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ህይወት ከትግራይ የማይለይ፣ የሃብት ክፍፍሉ በኣጠቃላይ ህዝብ ደረጃ ኣብዛኛውን የጎዳ መሆኑን ለማወቅም ሆነ ይህንን ለመመርመር ኣልፈቀዱም። በጠባቡ የትግራይን የኢኮኖሚ ህይወት፣ የገበሬውን ህይወት ኣይተው የትግራይ ሃርነት ትግል ጀመሩ። የዚህ ህዝብ ችግር በሃገር ጥላ ስር ኣብሮ ይፈታል የሚለው ነገር ያበሽቃቸው ነበር። የኣንድነትን ሃይሎች እንደነ ኢህዓፓ ኣይነቶችን እንደጠላት ያዩትም ለዚህ ነው። ትግራይን ነጥለው ሲያዩ ችግሩን ለመረዳት በጣም የቀለላቸው ይመስላል። ለመጡበት ቀየ የራራው ልባቸው ለኦሮሞው ለኣማራው ለሌላው ድሃ ህዝብ ኣልራራም ኣላቸው። እንዴውም ይህንን ስሜት ሳይንሳዊ ይዘት እንዲኖረው ለማድረግ ሲጥሩ ታዩ። በመጀምሪያ ኣካባቢህን ከዚያ ሃገር ምናምን… እያሉ  በዚያ ስሜታቸው ከማፈር ይልቅ ለማስተማመን (justify ለማድረግ) ብዙ ጣሩ።
ከፍ ሲል እንዳልነው ህወሃቶች “ትግራይ ሃርነት” ይበሉት እንጂ መራራው ጥያቄ ትግራይን ከሆነ ጨቋኝ ስርዓት ኣላቆ ኣንድ ነጻ ኣገር ለማድረግ ኣልነበረም። ጥያቄው የፖለቲካና የኣስተዳደር ነክ የነጻነት ጥያቄ ስላልሆነ በትግላቸው የመጀመሪያ ወራት ኣንዳንድ ኣባላት የመገንጠል ጥያቄ ኣንስተው የነበረ ቢሆንም ገና በማለዳ ይህ ኣሳብ ተቀጨ። ከፍ ሲል እንዳልኩት መራራው ጥያቄ የኢኮኖሚ ኦፖርቹኒቲ እንዴት ለኛ ሰፈር ይሰፋል? የሚል በመሆኑ ለዚህ ጥያቄ ብዙ መስዋእትነት ተከፈለ። ሌላው ኢትዮጵያዊ በደርግ ስርዓት ተጨቁኖ ስለነበረና ለውጥ ሽቶ ስለነበር የህወሃትን ተፈጥሮ መመራመር ኣልፈለገም። የኣንድ ኣካባቢ ኣርማ ለጥፈው ቢመጡም በኣንድያ የሃገር ስሜት ስር ያደገው ሰፊ ህዝብ ይህ ኣስተዳደጉ ስለ ህወሃት እንዳይመራመር ትኩረቱን ጋረደው። ኣንዳንዱ ሰው ደግሞ ከጅምሩ ብሄርተኞች መሆናቸው ባይዋጥለትም እስቲ ይሁን፣ ወንድሞቻችን ናቸው፣ ማእከላዊውን ስልጣን ሲይዙት፣ ኢትዮጵያ የምትባለውን ኣገር ሲያዩ፣ የሌላውን ህዝብ የከፋ ችግር ጠጋ ብለው ሲያዩ፣ ኣለማቀፋዊ መጋለጥ ሲኖራቸው ይተውታል ብሎ በልበ ሰፊነት ሲጠብቅ እነሆ ህወሃት ኣርባ ኣመቱን ትናንትና ሲያከብር ወይ ፍንክች ኣልተለወጠም።
ወያኔ የዛሬ ሃያ ሶስት ዓመት የኢኮኖሚ ጥያቄ ዋና ጥያቄው ኣድርጎ ስልጣን ላይ ሲወጣ የኦፖርቹኒስቲክ ባህርይ (Opportunistic behavior) በሃጋሪቱ ፖለቲካ ኣካባቢ በሰፊው  ሰፈነ። ይህ ባህርይ የፖለቲካውን ጨዋታ ሁሉ እንዳይሆን እንዳይሆን ኣድርጎ ኣበላሸው:: ማህበራዊ ሃብታችንን በተለይም የመተማመን (የ trust) ሀብታችንን በጣም ጎዳብን።
ህወሃት ትግራይ ትግራይ ይበል እንጂ በትግሉ ጊዜ ለትግራይ የገባውን ቃል መፈጸም ኣልቻለም። ከሁሉ በላይ የትግራይ ህዝብም በወያኔ ጎጠኛ ስሜት ተከፋ። ኣብዛኛውን የትግራይን ህዝብ ወደማይፈልገው ስሜት ውስጥ ከተተው። ስለዚህም ህወሃት ከትግራይም ሌላ ክብ ሰርቶ የዚያን ክብ እርሻ ለወጠ። የዚያን ጠባብ ክብ ኣባላት ነጋዴዎች ኪስ በገንዘብ ጠቀጠቀ።ስልጣኑን ለማቆየት ይረዳኛል በሚል በየክልሉ ጥቂት ጥቂት ክቦችን እየሰራ እነሱን የከፍተኛ የኢኮኖሚ ኦፖርቹኒቲ ተጠቃሚ እያደረገ እልፉን ህዝብ ሜዳ ላይ ጣለው።
ቶሎ እንድናድግ ሃብት በኣንድ ኣካባቢ ይደልብልን በሚል ማታለያ ኣንዳንዴም የልማታዊ መንግስትን ስም ለጠፍ እያደረገ የኢኮኖሚውን ኦፖርቹኒቲ ሁሉ በጣም በጠበበ የህብረተሰብ ክብ ውስጥ ጠቀጠቀው። ይህ ቡድን መነሻው የኢኮኖሚ ችግር በመሆኑና የታገለውም ለዚህ በመሆኑ ነው ይህን የሚያደርገው። ይህ ቡድን ለኢኮኖሚ ጉዳቱ ማገገሚያ ኣድርጎ የወሰደው የፖለቲካ ስልጣንን መሳሪያ በማድረግ በመሆኑ በሃገሪቱ ፍትህ ኣድሮ ሲቀጭጭ ይታይ ጀመር። ያሳዝናል።
ህወሃት ገና ከመነሻው የዚህ የኢኮኖሚ ጥቅም ጉዳይ ኣናዶት ጫካ መግባቱ ብቻ ሳይሆን የጎዳን ይህንን ጠባብ የሆነ የኢኮኖሚ እድል ለማስፋት ኢትዮጵያ የምትከፍለው ዋጋ እጅግ ከፍተኛ መሆኑ ነው። የጥቂት የህወሃት ደጋፊዎችን እርሻ ለመለወጥ፣ የጥቂት የሰርዓቱ ደጋፊ ነጋዴዎችን ኪስ ለመሙላት ኢትዮጵያ የባህር በር እስክታጣ፣ ኢትዮጵያ ድንበሩዋ ተቆርጦ እስክታንስ፣ በዘር ፖለቲካ ማህበራዊ ሃብታችን እስኪፈርስ ድረስ ዋጋ ትከፍላለች።እስከዚህ ጥግ የሄደ መስዋእትነት ይከፈላል። ይሄ ነው እጅግ ኣሳዛኙ ነገር። እነዚህን ኣላፊ ወይም ኣነስተኛ የኢኮኖሚ ድጋፎችን ለማድረግ ስለምን ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቱዋ እስኪደፈር ዋጋ ትከፍላለች? ብለን ስናስብ እስከ ሃቹ ያስደምመናል። ህወሃት ቢገነዘብ ኖሮ ይህን በዙሪያው የኮለኮለውን ጠባብ ቡድን ኣሁን የጠቀመውን ያህል ለመጥቀም ኢትዮጵያ ይሄን ያህል ዋጋ መክፈል ኣልነበረባትም። በኣምባ ገነን ኣገሮች ሙስና እንዳለ ሁሉ በሙስና የተለያዩ ጥቅሞችን ማደረግ ቢቻል የህወሃት ክፋት እስከዚህ ጥግ ይባል ነበር። ይህ ግን ኣልሆነም። ስርዓቱን ለመጠበቅ ሲባል፣ የነዚህን ጠባብ ቡድኖች ጥቅም ለመጠበቅ ሲባል በሱዳን በኩል ተቃዋሚ እንዳይነሳ የጠገበ መሬት ቆርሶ እስከ መስጠት መድረሱ በጣም ያስገርማል። ኢትዮጵያን የሚያህል ትልቅ ኣገር የባህር በር ጥያቄን ኣምርራ ከመጠየቅ ይልቅ ዝምታን መርጣ የነዚህን ጠባብ ጉጅሌዎች ኪስ መሙላት ይሻላል ለወያኔ።
ይህ ስርዓት ከቀደሙት የሚለየው በዚህ ነው። የቀደሙት ስርዓቶች ኣምባገነን ሆነው የሆነ ክብን እየጠቀሙ ብዙውን ኣግልለው ይኖሩ ነበር። እነዚህ መንግስታት ይህን ቡድናቸውን ወይም ጉጅሌዎቻቸውን የሚጠቅሙት ግን የድሃውን ጉልበት እስከመበዝበዝ በሚደርስ ጭካኔ ነው። ህወሃት ግን ድሃውን ከመበዝበዝ ኣልፎ ኢትዮጵያን ራሱዋን ሉዓላዊነቱዋን ታሪካዊ ማንነቷን ሁሉ ሸጦ ነው ቡድኑን የሚጠቅመው።
ደርግ ለዚህ ምሳሌ ነው። ሁሉ እንደሚያስታውሰው ጨካኝ በመሆኑ ኢትዮጵያ ብዙ ዋጋ ከፈለች። ነገር ግን ለስልጣኑ ሲል የሃገሩን ሉዓላዊነት ኣላስደፈረም። ደርግ ለስልጣኑ ሲል በሉዓላዊነት ላይ ቢነሳ ኤርትራን እንድትገነጠል ማድረግ ብቻ ይበቃው ነበር። ኤርትራን በሰላማዊ መንገድ እንድትገነጠል ቢስማማ ወይም ቀደም ብሎ በኮንፌደሬሽን ኣስተዳደር ችግሩን ቢፈታ ሃይሉን ኣሰባስቦ ወያኔን ያጠፋ ነበር። ህወሃት ወደ ስልጣን እንዲመጣ የሻእቢያ ኣስተዋጾ እጅግ የጎላ እንደነበር ይታወቃል። በመሆኑም ያለፉት መንግስታት በስልጣን ለመቆየትና ለግል ጥቅም ልክ የነበራቸው ሲሆን ያሁኑ መንግስት ግን ኢትዮጵያን መስዋእት እያደረገ ኣላፊ የሆነ ጥቅማጥቅም የሚቃርም በመሆኑ በታሪካችን ኣይነተው የማናውቀው ጉደኛ መንግስት ያደረዋል።
በቅርቡ ኣርባ ኣመቱን ያከበረው ህወሃት በኣርባ ኣመት ቆይታው ምንም ኣልተማረም። ከጥፋት ወደ ጥፋት ሲያዘግም ነው የምናየው። መሪዎቹ የዛሬ ሃያ ኣመት ካሳዩት ትህትና ያሁኑ ያንሳል፣ የዛሬ ሃያ ኣመት ካሳዩት የፕሬስ ነጻነት የዛሬው ያንሳል። ወያኔ ኣንዱ እንዳይማር ያደረገው ነገር ከመነሻው ትግሉ የኢኮኖሚ እድልን መጠቀም በመሆኑ እንዲሁ ሃብቱን እንደነከሰ መኖርን ስለሚመርጥ ነው።የህወሃት ተፈጥሮ እንደዚህ ነው። ይህ ስርዓት ካልተለወጠ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ኣጠቃላይ የኣካባቢውን ኣገራት ጂኦ ፖለቲክስ በመቀየር በኣፍሪካ ቀንድ ችግር ሊፈጥር እንደሚችል መገመት ኣያዳግትም። የዘር ፖለቲካውና የመሬት ነጠቃው የኣካባቢውን ጂዖ ፖለቲክስ ወደ ኣልተፈለገ ኣቅጣጫ ሊወስዱ የሚችሉ እምቅ ችግሮች ናቸው። የመሬት ነጠቃ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚና የኦፖርቹኒቲ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን ፖለቲካዊ እንድምታውና ተጽእኖው በሚገባ መታወቅ ኣለበት። እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ በኣፍሪካ ቀንድ ካላት ግዝፈት የተነሳ ኣለመረጋጋት ቢፈጠር በጅቡቲ፣በሶማሊያና በኤርትራ ላይ የሚፈጥረው ተጽእኖ እጅግ ጉልህ ነው።  የኣፍሪካ ቀንድ ሰላም ሲታሰብ ከኢትዮጵያ ሰላምነት ውጭ ማሰብ ኣይቻልም። ወያኔ ትልቅ ውስጣዊ ችግር በውስጡ ደብቆ ይዞ በኣካባቢው ኣገራት ዘንድና በኣለም ኣቀፍ ተቋማት ዘንድ ሰላም እንደሆነ፣ ሃላፊነት ሊሸከም እንደሚችል ለማሳየት ይሞክራል። ይህ ግን እውነት ሳይሆን በርግጥ ኢትዮጵያ በኣሁኑ ሰዓት ማህበራዊ ሃብቱዋ ያለ ልክ ተጎድቶ በከፍተኛ ውጥረት ላይ ያለች ኣገር ናት። ለኣፍሪካ ቀንድ ዋና ስጋት የሆነው የኣክራሪነት ችግር በህወሃት ኣይፈታም ብቻ ሳይሆን ራሱ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ድባብ ኣክራሪነት የሚታይበት በመሆኑ እምቅ ኣሸባሪነት በህወሃት ኣገዛዝ ውስጥ ተቀብሮ ይኖራል።ህወሃት በተፈጥሮው የኣሸባሪነት ጠላትም ሊሆን የሚያስችል ነገር የለውም። ኣክራሪነት የሚገለጸው ከሃይማኖት ጋር በተያያዘ ብቻ ሳይሆን ከማንነት ፖለቲካ ጋር የተያያዘ በመሆኑ ኢትዮጵያ በኣህኑ ሰዓት ይህን ችግር በውስጡዋ ይዛ ያለች ኣገር ናት። በየትኛውም ጊዜ ሊፈነዳ የሚችል የጎሳ ኣመጽን እያፈራች ያለች ኣገር ናት። ከፍ ሲል እንዳልነው የህወሃትን ተፈጥሮ ተከትሎ የመጣው  የኦፖርቹኒስቲክ ጸባይ ብዙዎችን ኣብሽቆ ይታያል። እኛ ኢትዮጵያዊያን የወያኔን ተፈጥሮ ተረድተን የጋራ የሆነችውን ኣገራችንን በጋራ እንደገና ለማነጽ ሳንከፋፈል በጋራ ታግለን ይህን ስርዓት መለወጥ ይኖርብናል። በኣንድም በሌላም መንገድ ለወያኔ የጎሳ ፖለቲካ ሰለባ ሳንሆን ኣንድነትን ኣጥብቀን ልንይዝ በፍቅር ላይ የተመሰረተ የለውጥ እንቅስቃሴ ልናደርግ ይገባናል።

እግዚኣብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ

torsdag 19. februar 2015

“ዘመቻው በከፊል ተሳክቷል፤ ከጋዜጠኛ ተመስገን ጋር ተገናኝተናል”




(ኢ.ኤም.ኤፍ) ጋዜጠኛ ተመስገን የኢህአዴግን አሰራር በመቃወም ሃሳቡን ስለገለጸ “አሸባሪ” ተብሎ አሁን በእስር ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል። ነገሮችን የበለጠ ያከፋው ደግሞ ከቅርብ ግዜ ወዲህ፤ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በቤተሰቡም ሆነ በጓደኞቹ እንዳይጎበኝ መደረጉ ነበር። ከአንድ ወር በፊት ስንቅ ሊያቀብል የሄደው ወንድሙን ደብድበው፤ ምግቡን መሬት ላይ ደፍተው ገንዘቡን ጭምር ወስደው ከቃሊቲ እስር ቤት ያባረሩት መሆኑ የሚዘነጋ አይደለም።
ጋዜጠኛውን በፈጠራ ወንጀል ማሰር ሳያንስ እንዲህ ያለ ግፍ መፈጸም ኢሰብአዊነት መሆኑን በመግለጽ በርካታ ውትወታዎች ተደርገው ነበር። በቅርቡም የህገ መንግስቱ አንቀጽ 21 እንዲከበር እና የእስረኛ ሰብአዊ መብት እንዲከበር የሚጠይቅ የበይነ መረብ ዘመቻ ተካሂዷል። ይህ ዘመቻ በከፊልም ቢሆን ውጤት ያሳየ ይመስላል። ለመጀመሪያ ግዜ የተመስገን ወንድም እስር ቤት ሄዶ እንዲጎበኝ ተፈቅዶለታል። ሆኖም ጋዜጠኛ ተመስገን አሁንም በከፍተኛ የህመም ዝቃይ ውስጥ ነው። ህክምና እንዳያገኝ ተደርጓል። ይህም ሁኔታ የበይነ መረቡ ዘመቻ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አመላካች ነው። ለማንኛውም የዘመቻው አስተባባሪዎች የሰጡትን አጭር መግለጫ ከዚህ ቀጥሎ አቅርበናል።

በቅድሚያ ያለፈውን ሳምንት አብራችሁን ለነበራችሁ የበይነ-መረብ ዘማቾችና ወዳጆች ምስጋና ይድረስ፡፡
በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ የምግብ የህክምናና የጎብኚ እግድ የተጣለው ከአንድ ወር በፊት ነበር፡፡ በዚህ የተቆጡ ቤተሰብና ወዳጆች ይህን መንግስታዊ ወንጀል ለማስቆም ይበጃል ያሉትን ሙከራ አድርገዋል፡፡ ለአምስት ተከታታይ ቀናት በበይነ-መረብና በተቋማት ቢሮዎች ላይ የተደረገው አስጨናቂ ህግን የማስከበር ውትወታ የመጀመሪያውን ውጤት አይቷል፡፡ ተመስገንንም በአካል ለማየት ተችሏል፡፡
የሰብአዊ መብት ኮሚሽን መርማሪዎችና በርከት ያሉ አጃቢ ወታደሮች ባሉበት፣ ከወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ ጋር ዛሬ የተገናኘው ጋዜጠኛ ተመስገን ጤንነቱ አደጋ ላይ እንዳለ መረዳት ተችሏል፡፡ ከዚህ ቀደም የነበረው የጀርባ ህመም አላስተኛ ወዳለው እብጠት መቀየሩንና የግራ ጆሮውም መስማት ወደማይችልበት ደረጃ መድረሱ ታውቋል፡፡ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኝ ለዝዋይ ማረሚያ ቤት ያቀረበው ጥያቄም እስካሁን ምላሽ እንዳላገኘ በቦታው ለነበረው ወንድሙ ገልጾለታል፡፡ አያይዞም ያለቀናት በቆየው ያላቋረጠ ዘመቻ ልባዊ ወዳጅነትን፣ ስስትንና ወንድማዊነትን ላሳያችሁ ወገኖች ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ምስጋና አቅርቧል፡፡
መጎብኘት እንደተፈቀደላቸው ከኮሚሽኑ መርማሪዎች በስልክ ማረጋገጫ ያገኙት ወንድሙና አንድ ወዳጁ ቢሆንም ሁለቱም ለመግባት የሚያስፈልገውን ምዝገባ ካሟሉ በኋላ የተመስገን ወዳጅ ተከልክሎ ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ እንዲገባ መደረጉ ለማወቅ ተችሏል፡፡

mandag 16. februar 2015

የ2007ቱን ሀገራዊ ምርጫ ሂደት እና ከምርጫዉ ዉጭ ያሉ አዋጭ አማራጮችን በተመለከተ የአርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ የአቋም መግለጫ


  

pg7-headerአርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሰላማዊ፣ ተዓማኒና ፍትሀዊ በሆነ ምርጫ የማይፈልጋቸውን መሪዎች መሻር፤ የሚፈልጋቸውን ደግሞ መሾም የሚያስችሉትን መሠረቶች ለመጣል የሚታገል ንቅናቄ ነው። እንደሚታወቀው የሕዝብ እውነተኛ ፍላጎት የሚገለጽበት እውነተኛ ምርጫ እንዲኖር ገለልተኛና ቀልጣፋ የፍትህ ሥርዓት፣ የጦርና የፓሊስ ሠራዊት ሊኖሩ ይገባል። ነፃ የሚዲያ ተቋማትና በነፃነት የሚንቀሳቀሱ የሲቪክ ማኅበራት መኖርም መታለፍ የሌለባቸው አቢይ ጉዳዮች ናቸው። አማራጭ ፓሊሲዎችን ማቅረብ የሚችሉ በነፃነት የሚንቀሳቀሱ የፓለቲካ ፓርቲዎች ከሌሉም አማራጮች የሉምና ምርጫ ትርጉም የለውም። ይህ ሁሉ ቢሟላ እንኳን ምርጫውን የሚያስፈጽመው አካል ገለልተኛ፣ ሀቀኛና ተዓማኒ ካልሆነ የሚደረገው ምርጫ የመራጩን ሕዝብ ፍላጎት የሚያንፀባርቅ ሊሆን አይችልም።

ከላይ የተዘረዘሩትን የምርጫ እሴቶች ሙሉ በሙሉ ባይሆንም እንኳን የተወሰኑትን በመጠኑም ቢሆን ያካተተ ምርጫ እንዲኖር መጣርና በሂደት የምርጫውን አፈፃፀም ማሻሻል ይቻል ይሆናል በሚል እምነት የዲሞክራሲ ኃይሎች በህወሓት የሴራ ምርጫዎች ሲሳተፉ ቆይተዋል። ሆኖም በህወሓትና በእውነተኛ ምርጫ መካከል ያለው ተቃርኖ እያደር እየሰፋ ሲሄድ እንጂ ሲጠብ አልታየም። በህወሓት ሙሉ ቁጥጥር ስር በሚካሄድ ምርጫ ኢትዮጵያን የሚጠቅም ለውጥ ሊመጣ ይችላል የሚለው እምነት ለአርበኞች ግንቦት 7 ፈጽሞ የተሟጠጠው ከምርጫ 97 ማግስት ጀምሮ ነው። በግንቦት 7 ቀን 1997 ዓም የኢትዮጵያ ሕዝብ በታላቅ የለውጥ ተስፋ የሰጠው ድምጽ በህወሓት የተዘረፈው ከላይ የተዘረዘሩት ተቋማት ያልነበሩ በመሆናቸው፤ ስለዚህም ከምርጫ በፊት ተቋማቱን መገንባት፤ ተቋማቱን ለመገንባት ደግሞ ህወሓትን ከስልጣን ማስወገድ ይገባል ብሎ በማመኑ ነው አርበኞች ግንቦት 7 በሁለገብ የትግል ስልት በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኘው።

ያም ሆኖ ግን በምርጫ ላይ ያላቸው ተስፋ ፈጽሞ ያልተሟጠጠ ፓርቲዎችን በማክበርና ሥራቸውንም አስቸጋሪ ላለማድረግ ሲባል ከምርጫ 97 ወዲህ የነበሩ ብሄራዊም ሆነ ክልላዊ ምርጫዎችን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከምርጫ ዉጭ ያሉ ሌሎች አማራጮችን ብቻ እንዲመለከት አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪ አድርጎ አያውቅም ነበር። አሁን ግን የአገራችን ኢትዮጵያ የፓለቲካ ሁኔታዎች ይህንን የቆየ አቋም በሚያስቀይር መንገድ፤ የአገራችንን የወደፊት ዕድል ብቻ ሳይሆን ባጠቃላይ ያካባቢውን ሰላም በሚጎዳ መልኩ ተቀይሯል። የሰሞኑ የወያኔ እርምጃዎች ትንሽ ተስፋ ያደርግ የነበረውን የዴሞክራሲ ወገንተኛ ተስፋም እምሽክ አድርጎ በልቶታል:: እየተቃረበ ያለው ዓይነት የፌዝ ምርጫ ወያኔ እንደ እንጄራ የራበውን የተቀባይነት እጦት ለአጭር ጊዜ ያስታግስለት ይሆናል እንጂ የሀገሪቱን እያደር እየተወሳሰበ የመጣ ችግር ለጊዜውም እንኳን የሚያስታግስ አይሆንም፤ ይልቁንም ጊዜው በገፋ ቁጥር ችግሩ መቋጠሪያ የጠፋው እየሆነ ይሄዳል::

የሁኔታውን አሳሳቢነት ከግምት ውስጥ በማስገባት የአርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ አመራር የወቅቱን የአገራችን የፓለቲካ ሁኔታ በጥንቃቄ መርምሮ የሚከተሉት ግንዛቤዎች ላይ ደርሷል።

1. ህወሓት ብዙዎች እትዮጵያዊያን የተሰውላቸውን አንድነት ፓርቲንና መኢአድን በመበተን የድርጅቶቹን ስምና ንብረት ለአገልጋዮቹ መስጠቱ፤ ከዚህ በፊት ሲያደርግ እንደነበረው የመራጭን ድምጽ መስረቅ ሳይበቃው የምርጫ ተወዳዳሪንም መዝረፍ መጀመሩን አመላካች ነው። ይህ ተግባር ህወሓት የምርጫ ውጤትን ብቻ ሳይሆን ተወዳዳሪዎችንም እሱ ራሱ ለመምረጥ መወሰኑን ያሳያል፤ ከዚህ በተጨማሪ የሴራ ምርጫውን ከጅምሩ ጀምሮ አስቀድሞ እስከተወሰነለት መዳረሻው ድረስ ለምንም ዓይነት ያልተጠበቀ አጋጣሚ (በምርጫው ወቅት የሚደረጉትን ክርክር ተብዬዎች ጨምሮ) እድል ላለመስጠት ወስኖ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን በግልጽ ያሳያል፤

2. ይህ እኩይ ውሳኔ በምርጫ ቦርድ ፊርማና አንደበት ቢነገርም ምንጩ የህወሓት ፓሊት ቢሮ መሆኑን የሚከተሉት ተግባራት ይጠቁማሉ፤
2.1. በምርጫ ቦርድ በኩል እንዲገለጽ የተወሰነው እርምጃ ለማስመሰል ያክልም ቢሆን የህጋዊነት ሽፋን እንዲኖረው አለመደረጉ ውሳኔው ፍጹም እብሪተኛ በሆነ አካል መወሰኑን ያመለክታል። እንዲህ ዓይነቱ እብሪተኛ አካል ደግሞ የህወሓት ፓሊት ቢሮ ነው። ውሳኔውን ለማስፈፀም የነበረው ጥድፊያም ይህንኑ ያጠናክራል።
2.2. ለማስመሰያ ያክል እንኳን ምንም አይነት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሳይኖር ፓሊስ የአንድነትና የመኢአድ ቢሮዎችን መውረሩ፤ ህወሓት አንድነትንና መኢአድን አጥፍቶ የድርጅቶቹን ስሞችና ንብረቶች ለሚፈልጋቸው ሰዎች ሰጥቶ በአስቸኳይ ለምርጫ ድራማው በፊት መስመር ሊያሰልፋቸው መወሰኑን አመላካች ነው። እንዲህ ዓይነት ከባድ ውሳኔ የሚሰጠው ደግሞ የህወሓት ፓሊት ቢሮ ብቻ ነው::

2.3. ወደ ፈቃድ መንጠቅ ከመደረሱ በፊትም በሰማያዊ ፓርቲ፣ በአንድነትና በመኢአድ አባላት የደረሰው አረመኔያዊ ድብደባ፤ ንቁ የፓለቲካ ተሳትፎ የሚያደርጉ ዜጎች ላይ የሚደርሰው እስር፣ መሰወርና እና ባልታወቁ ሰዎች ተገድሎ መገኘት መብዛት እነዚህን አገራዊ ፓርቲዎች የመበተን የፓለቲካ ውሳኔ መሰጠቱን አመላካቾች ናቸው።

3. ለጊዜው የፈቃድ ነጠቃና የንብረት ዘረፋ የተፈፀመው በአንድነትና በመኢአድ ላይ ቢሆንም በሰማያዊ ፓርቲ ላይ በየእለቱ እየጠነከረ የመጣው የአፈና እርምጃም በተመሳሳይ ፓርቲውን ወደማገድ አለዚያም ፈጽሞ መንቀሳቀስ ወደማይችልበት ደረጃ ሊያደርሰው ይችላል የሚል እምነት አሳድሯል። ሌሎች ፓርቲዎችም ከዚህ ህወሓት ካሰመረው የውሸት ጫወታ መስመር የመውጣት ዝንባሌ ቢያሳዩ ተመሳሳይ እርምጃ አይቀርላቸውም።
4. የህወሓት የወቅቱ የጥፋት ዒላማ ያነጣጠረው አንፃራዊ በሆነ መንገድ የተሻለ መዋቅርና ማኅበራዊ መሠረት ባላቸው እና በአገራዊ አጀንዳዎቻቸው በሚታወቁ ፓርቲዎች ላይ መሆኑ፤ የወቅቱ የጥፋት ዘመቻ የኢትዮጵያ አንድነትን የማዳከምና ከፋፍሎ የመግዛት የህወሓት ትልቁ አጀንዳ አካል መሆኑን ያሳያል።
5. እራሱን በዘር ያደራጀዉና ኢትዮጰያ ዉስጥ ያለዉ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ አደረጃጀት ከዚሁ እሱ ከተደራጀበት የዘር አደረጃጀት ዉጭ እንዲሆን በፍጹም የማይፈቅደዉ የወያኔ አገዛዝ፤ መጣፊያው ሲያጥረውና ወደ ማይቀረው ውድቀቱ ሲያመራ፤ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል እንዳለችው አህያ አገራችን ኢትዮጵያን በቀላሉ ወደማትወጣዉ የዘዉግ ግጭት ዉስጥ አስገብቶ ዘመናት ያስቆጠረዉ አንድነቷ እንዲፈረስ በትጋት እየሠራ መሆኑን ያሳያል።

6. ከመለስ ዜናዊ ሞት ወዲህ ህወሓት ከሁሉን ጠቅላይ (totalitarian) አገዛዝ ወደ ፋሽስታዊ ቡድንነት ያሽቆለቆለ መሆኑን አርበኞች ግንቦት 7 ተገንዝቧል። ህወሓት ዘረኛ፣ ጠቅላይና ፈላጭ ቆራጭ ጨቌኝ በመሆኑ ፋሽስት ብለነዋል። ሆኖም በታሪክ የሚታወቁ ፋሺስታዊ አገዛዞች ከፍተኛ ብሄራዊ ስሜት የነበራቸው ሲሆን የህወሓት ፋሽስታዊ አገዛዝ ግን ብሔራው ስሜት አልባ መሆኑ ልዩ እና የበለጠ አደገኛ ያደርገዋል። ይህ ፋሽስታዊ ቡድን የህወሓት መሪዎችንና ጥቂት ሌሎች አጫፋሪዎቻቸውን የያዘ ለጊዜው አስተባባሪ መሪ የሌለው ሆኖም ግን የጦር ሠራዊትን፣ የስለላ መዋቅሩንና ፓሊስን ተቆጣጥሮ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያን እየገዛ ያለው ይህ አስኳል የለሽ ፋሽስታዊ ቡድን መሆኑ እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን አርበኞች ግንቦት 7 ተገንዝቧል።

 ይህ ፋሽስታዊ ቡድን ተደላድሎ መሪ እንዲፈጥር ከተፈቀደለት አገራችንን የከፋ መከራ ውስጥ ሊከታት እንደሚችል ግንዛቤ ተወስዷል።
ከላይ በአጭሩ ከተራ ቁጥ 1 እስከ 6 የተዘረዘሩትን በማገናዘብ በግንቦት 2007 ሊደረግ የታቀደውን አምስተኛው ዙር ሀገር አቀፍ የሴራ ምርጫን በተመለከተ የአርበኞች ግንቦት 7 አመራር ውሳኔዎችን አስተላልፎ ከዚህ የሚከተሉት ጥሪዎችን ለኢትዮጵያ ሕዝብ አቅርቧል።

1. በምርጫ 2007 መሳተፍ ለዲሞክራሲያዊ ለውጥ ሁኔታዎችን ከማመቻቸት ይልቅ ፋሽስታዊውን ቡድን የሚያጠናክርና የኢትዮጵያን ሕዝብ የወደፊት ዕድል የሚገድል በመሆኑ፣ ለፍትህ፣ ለነፃነት፤ ለዲሞክራሲና ለአገር አንድነት ግድ ያላቸው ወገኖች ሁሉ ከአሁኑ ከዚህ የይስሙላ ምርጫ ዉጭ ዓይኖቻቸውንና ሙሉ ጉልበታቸዉን በሌሎች የኢትዮጵያን ሕዝብ ነፃነት በሚያፋጥኑ አማራጮች ላይ እንዲያሳርፉ ጥሪ ያደርጋል። አርበኞች ግንቦት 7 የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዚህ ዓይን ያወጣ የሴራ ምርጫ ይልቅ መብቱን፤ ነፃነቱንና እኩልነቱን በሚያፋጥኑለት በሕዝባዊ እምቢተኝነትና በሕዝባዊ አመፅ የትግል አመራጮች ላይ እንዲሳትፍ ለመላው ያገሪቱ ሕዝብ ጥሪ ያስተላልፋል። ህወሓት ማኅበረሰባችንን ለመከፋፈልና ለማባላት የሚያደርገውን እኩይ ሴራ በጋራ እንድናከሽፈው ወገናዊ ጥሪ ያስተላልፋል፤ “አንከፋፈልም፤ ተከፋፍለንም አንጠቃም“ እንበል ይላል::

2. ህወሓትን ማስወገድ የሚቻለው በሕዝባዊ እምቢተኝነትና በሕዝባዊ አመጽ በመሆኑ፤ ከሁለቱ አንዱንም አለመያዝ ሌላ ሰው ታግሎ ነፃነቴን ያቀዳጀኝ እንደማለት የሚቆጠር በመሆኑ፤ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በአፋጣኝ ከእነዚህ ሁለት የትግል ዘርፎች ዉስጥ የተሻለ አስተዋጽኦ አበረክታለሁ በሚለው የትግል ዘርፍ ውስጥ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ ያቀርባል።

3. አርበኞች ግንቦት 7፣ በሁለቱም የትግል ዘርፎች ድርጅታዊ መዋቅሩን እያሰፋና ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በመተባበር በሕዝባዊ እምቢተኝነትና በሕዝባዊ አመጽ ህወሓትን ከስልጣን ለማስወገድ አቅዶ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ኢትዮጵያዊያን በስፋት እንዲቀላቀሉት፤ በኅብረት እንድንቆም እና የህወሓትን ውድቀትና የኢትዮጵያን ትንሳኤ እንድናፋጥን ጥሪ ያደርጋል::

4. ያለንን አቅም በሙሉ ህወሓትን በማስወገድ ላይ ካዋልነው አንድ ጠንክር ያለ ሕዝባዊ አመጽ አገዛዙን ሊያፍረክርክው የሚችል በመሆኑ፤ በአንድ ወይም በሌላ መንገድ ከምርጫ ጋር ለተያያዙ ሥራዎች ሊውል ታስቦ የነበረው የሰው ኃይል፣ ጊዜ፣ ገንዘብና እውቀት ለሕዝባዊ አብዮት መቀስቀሻነት እንዲውል ጥሪ ያደርጋል።

5. በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንም በ2007 ምርጫ ላይ ጊዜና ንብረት ከማባከን ይልቅ በአንድ ልብ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሕዝባዊ አብዮት መቀስቀስ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪ ያደርጋል። ከሁሉም ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች የተውጣጣ አካል የዚህን ጥሪ ተፈፃሚነት እንዲከታተል ቢደረግ ይበልጥ ውጤታማ ይሆናል ብሎ ያምናል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!
አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ
ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ

ኣቶ ገብሩ ኣስራት የምርጫ ካርድ ተከለከሉ..!


ዓረና-መድረክ ወክለው በመቐለ ምርጫ ክልል ለፌደራል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ የሆኑት ኣቶ ገብሩ ኣስራት “የመራጭነት ካርድ ጨርሰናል” በሚል ምክንያት ተከልክለዋል።

ይህ የሆነው እሁድ የካቲት 06 / 2007 ዓ/ም ከቀኑ 10 ስዓት በመቐለ ኣስራ 15 ቀበሌ እንዳባ ኣነንያ ምርጫ ጣብያ በኣካል ተገኝተው በጠየቁበት ወቅት ነው።

የምርጫ ካርድ በመቐለ ምርጫ ጣብያዎች ከሓሙስ 28 / 05 / 2007 ዓ/ም ጀምሮ ሲሆን ከዚህ ቀን በሗላ የመራጭነት ካርድ ማግኘት ኣልተቻለም።

የትግራይ ምርጫ ፅህፈት ቤት ችግሩ እንዳጋጠመ ያመነ ሲሆን ለችግሩ መፍትሄ ግን ሊያበጅ ኣልቻለው።

 ይህ ችግር ያጋጠመው በየምርጫ ጣብያው “ከእቅድ በላይ በመቶዎች ካርድ በመወሰዳቸው መሆኑ” ያስረዳሉ የጣብያዎቹ ሰዎች።
ይህ የህወሓት ወጣትና ሴቶች ሊግ ኣባላት እስከ ሰዎስት የመራጭነት ካርድች በተለያዩ ቦታዎች እያውጡ መሆኑ ታውቋል።

 የህወሓት መንግስት የትግራይ ሰዎች A.B.C.D ብሎ በመመደብ ካርዱ ለ A.B ቅድምያ በመስጠት እንዳስፈላጊነቱ ደግሞ C ለተሰጣቸው ሰዎች ካርዱ ይሰጣቸዋል።

Dየተመደበው ዜጋ የተለያዩ ምክንያቶች በመስጠት ካርድ እንዳይ ደርቸው እየተደረገ ነው።
በዚህ ለሚመርጥህ ሰው ለይተህ ካርድ በመስጠትና ለታማኝ የሊግ ኣባላት ከ3 በላይ ካርድ በማደል ከወዲሁ የምርጫው ውጤት ለመወሰን ጥረት እየተደረገ ነው ያለው።

ማንኛውም ሰው በኣቅራብያው ያለው የምርጫ ጣብያ ጠይቆ ካርድ መኖሩ ኣለመነሩ ማረጋግጥ ይችላል።

 ይህ ማጭበርበርያ ዘዴ ለማውጣት የተፈለገበት ዋነኛ ምክንያት የትግራይ ህዝብ እንደማይመርጣቸው በማረጋገጣቸው ነው።
ኣሁንም ምርጫ ቦርድ የመራጭነት ካርድ እንዲልክና የህዝቡን ፍላጎት እንዲያከብር እንመክራለን።
ኣቶ ገብሩ ኣስርትም የመራጭነት ካርድ ሊሰጣቸው ይገባል።

tirsdag 10. februar 2015

ጓዶች ሆይ፦ ምርጫውን እርሱት! (ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ -ዝዋይ እስር ቤት )

ባለወር ተተካ
ተቀበለኝ ትግሌን እንካ”
(ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን)
temesgen-desalegn
…ሲያሻው እየጋመ፤ ሲያሻው እንደበረዶ እየቀዘቀዘ በመካሄድ ላይ ያለው የፀረ-ጭቆና ትግል እንደዋዛ ግማሽ ክፍለ ዘመን አስቆጠረ፡፡ የሂደቱ ክፉ ጎን ደግሞ የአያሌ ብርቱ ወንድም-እህቶቻችንን የህይወት ግብር እየጠየቀ ዛሬ ድረስ ተጉዟል፡፡ በተለይም ሁለቱ ቀደምት አብዮቶች (የ1966ቱ እና የ1983ቱ) ብረት-ነከስ ናቸውና የትውልድ ክፍተት እስከመፍጠር የደረሰ ዕልቂት ስለመሸከማቸው በደም የተፃፉት ድርሳናት ያወሳሉ፡፡ ከመዓቱ የተረፉት የዓይን እማኞችም ለወቅቱ መከራ ምስክሮች ናቸው፡፡ እነዚህ አብዮቶች፣ አነሰም በዛም፣ የየራሳቸውን በጎ አበርክቶ ትተውልን ማለፋቸው ባይካድም፤ የተከፈለው መራራ ዋጋ ግን ለውጤታቸው በዝቶባቸዋል፡፡ ህይወት የተማገደላቸው እኒህ የለውጥ ንቅናቄዎች፣ የተነሱለትን ምክኒያት የዘነጉ ዋጋ-ቢስ አገዛዞችን በማዋለድ ተጠናቀዋል፡፡ እኔና የትውልድ ተጋሪዎቼም ቀሪውን የለውጥ ጥያቄ በድል ለማጀብ የቀለም አብዮትን ወደ መምረጡ ጠርዝ የመጣንበት መግፍኤ ይኅው ነው ብዬ አምናለሁ፡፡
የ1983ቱ የኮ/ል መንግስቱ ኃ/ማርያም ውድቀትን ተከትሎ የስልጣን ባለቤት የሆኑት የማሌሊት ጓዶች ናቸው፡፡ ተረኞቹ ባነበሩት ሥርዓት የዲሞክራሲና የሰብአዊ መብቶች ልዕልናን በህገ-መንግስት ሳይቀር መደንገጋቸው የሚስተባበል ባይሆንም፤ ይህንኑ መብት ለመጠቀም በሞከሩ የተቃውሞ ስብስቦች ላይ የወሰዱት ተከታታይ የኃይል ጭፍለቃዎች ግን የ“አዋጁን በጆሮ”ነት ይመሰክራሉ፡፡ በዚህ መሰሉ ግብ-ግብም ህልቆ-መሳፍርት የአገሬ ልጆች የህይወት መስዋዕትነት መክፈላቸውን፤ እስር ቤቶችን ማጨናነቃቸውንና በስደት መላውን ዓለም ማዳረሳቸውን አንዘነጋውም፡፡ በርግጥም ይህን መዘንጋት ለደመ-ቀዛቃዛ ገዢዎቻችን ተጨማሪ ድል ነውና መቼም ቢሆን አናደርገውም፡፡
ሥርዓቱ በየዕለቱ የሚፈጥረውን መሰል ሰቆቃዎች አስተውለው በዝምታ ሊያልፉ ያልቻሉት፤ የወደቁትን እየተራመዱ፤ የደከሙትን እየተኩ፤ “ፋኖ-ተሰማራ”ን እያንጎራጎሩ ስለመሆናቸው ጠርቶ ከሚሰማው ድምፃቸው መረዳት አይገድም፡፡ የግብፃዊያንን፤ የቱኒዚያዊያንን፤ የዩክሬናዊያንን….አብዮታዊ ድል እያወደሱ ወደፊት የሚያገሰግሱ፤ አደባባዩን በንቃት የሚያማትሩ…. የለውጥ ጥያቄ ያነገቡ አዳዲስ ከዋክብት መፈንጠቃቸውን ጆሮዬ እየሰማ፤ ዓይኔም እያየ በመሆኑ ልቤ በደስታ ሙቀት መሞላቱን ስመሰክር በኩራት ነው፡፡
ጓዶች ሆይ፦ ገዥው-ግንባር ዛሬም እንደትላንቱ በ“ምርጫ” ስም የጭቆና ዘመናችንን ለማራዘም የማይፈነቅለው ቋጥኝ፣ የማይንደው ጋራ፣ የማይገባባት ጉድጓድ እንደሌለ በትዝብት እየተመለከትን ነው፡፡ በድርጅታዊ መዋቅሩ ሙሉ በሙሉ በተቆጣጠረው ምርጫ ቦርድ ፊት-አውራሪነት፤ በካድሬዎቹ ታዛቢነት፤ በጭፍራ “ተቃዋሚ“ ድርጅት አጃቢነት ለአምስተኛው ክሹፍ ምርጫ ነጋሪት እየጎሰመ መሆኑንም እያስተዋልን ነው፡፡ አልቃሻ የፖለቲካ አቋም የተጠናውታቸውን ጨምሮ ራስ-ወዳዶችና ለዘብተኞችን ከጎኑ ማሰለፉ ፍንትው ብሎ የሚታይ ኩነት ሆኗል፡፡ ይህ ሽር-ጉድ በፍፁም ልባችን የምንታመንለትን የ“ህዳሴ (ሦስተኛው) አብዬት”ን ለመቀልበስ ቀን ከሌት እያሴሩ ስለመሆኑ ይነግረናል፡፡
ርግጥ ነው፣ ሥርዓቱ ከሁለት አስርታት በላይ ያለመንገራገጭ መሰንበት የቻለው እንዳሻው በማሰሩና በዘፈቀደ በመግደሉ ብቻ አይደለም፤ መስዋዕትነትን ከሚጠይቅ ትግል ይልቅ አፋዊነትን በሚመርጡ የተቃውሞ ስብስብ ስሁት ስልትም ጭምር እንጂ፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ ይህ የትላንት ታሪክ ዛሬም ሊደገም ከደጅ ያለ መስሏል፡፡ በሃሳውያን የአመራር አባላት ቁጥጥር ስር የዋሉት ፓርቲዎችም የአገዛዙን የፖለቲካ ንቅዘት መተቸት ስለቻሉ ብቻ በ“ብርቱ” እየሰሩ መስሏቸዋል፡፡ ዘመኑን የሚመጥን አማራጭ የትግል መንገድ ከመከተል፤ ከቤተ-መንግስት የሚወረወርላቸውን ጥቂት የ“ምክር ቤት” ወንበርን በተስፋ መጠበቅ አብዝተው መርጠዋል፡፡ ለወይኑ ዛፍም የእጅ ስንዝር ያህል ርቀት የቀራቸው በማስመሰል ደጋግመው አታለውናል፤ ያለአንዳች ድርጅታዊ ስራ በምርጫ ለመሳተፍ ተዋክበው አዋክበውናል፤ ስተው አስተውናል፡፡ በ“ውድድሩ”ም ቀደሞውኑ የተገመተውን ሽንፈት ሲከናነቡ፤ በ“ተጭበርብረናል” የጓዳ መግለጫ ከመቃወም የዘለለ ሳይራመዱና ከታሪካዊው ስህተታቸው ሳይማሩ በቀጣዩም ለመሳተፍ ቅንጣት ሲያንገራግሩ አይስተዋሉም፡፡ ስለምን ቢሉ? “ምርጫ“ የምትለውን ቃል ነክሰው ከተከተሩ ሀያ አራት አመታትን አስቆጥረዋልና ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ፣ የአውሮፓ ህብረት የዘንድሮውን ምርጫ እንደማይታዘብ ይፋ ባደረገበት አቋሙ ያስተላለፈውን መልዕክት ወርቁን-ከሰሙ ለይተው መረዳት ተስኗቸዋል፡፡ መቼም ኃይለማርያም ደሳለኝ “በበጀት እጥረት ነው” ሲል ማሾፉን ከቁም-ነገር ከወሰዱት የክ/ዘመኑ ታላቅ ስላቅ መሆኑ አይቀሬ ነው፡፡ ከዚህ ባለፈም አንድን ምርጫ ዲሞክራሲያዊ የሚያሰኘው በነፃ ውድድር ላይ ሲመሰረት፣ ዜጎች ሁሉ ያለ ተፅዕኖ በፖለቲካው ላይ መሳተፍም ሆነ የሚምኑትን ያለፍርሀት መናገር ሲችሉ፤ እንዲሁም ከምርጫው በኋላ የህዝብን አለቃነት የሚቀበል መንግስት መመስረቱ ሲሳካ መሆኑን ለመረዳት ከፖለቲካ ሀሁ የዘለለ እውቀት አለመጠየቁ ከማንም የሚሰወር አይደለም፡፡ ይህን ለመረዳት ያልተዘጋጀ ግን በመጪው “ዲሞክራሲያዊና ፍትሀዊ” ምርጫ ላይ ይሳተፋል፡፡
የሆነው ሆኖ ወደር በማይገኝለት ጥልቅ ብሶት የሰመጠ እና የሥርዓታዊ ምሬትን የመጨረሻ ፅዋ አንጠፍጥፎ የጨለጠ ህዝብ ከእሳተ-ጎመራ የሚልቅ፤ አንደዕቶን የሚንቀለቀል የቁጣ ስሜት ስለማርገዙ ለመመስከር ኮኮብ ቆጣሪ ማፈላለግን አይጠይቅም፡፡ በየግንባራችን ላይ የተቸከቸከው ብሶት-ወለድ ጉርምርምታ የአመፁ ቀናት በቅርብ ስለመሆናቸው ያስረግጥልናል፡፡ ዘመን ተጋሪዎቼም ርቱዕ ፍትህንም ሆነ የዜግነት ክብርን ከህዝባዊ እምቢ-ተኝነት እንጂ ከኮሮጆ ሊያገኙት እንደማይችሉ ካለፉበት የታሪክ ምዕራፍ ከተረዱ ሰነባብተዋል፡፡ ቅዱስ መፅሀፉም “ህግ ከሌለ ህግን የመተላለፍ በደል አይኖርም” እንዲል፤ ሥርዓቱ ከጭቆና ማራዘሚያነት በዘለለ ዋጋ በማያወጡት ቅምጥ ፍርድ ቤቶቹ በኩል እንደፈለገው የሚመነዝራቸውንና ንፁሃንን ለግፍ እስር ወህኒ የሚወረውርባቸውን የህግ አንቀፆች በእንዲህ አይነቱ ንቅናቄ ወቅት በግላጭ መጣሱ የትግሉ ቅዱስ ግዴታ መሆኑን ለማስታወስ እወዳለሁ፡፡ በርግጥ ከለውጡ ቀድሞ በሚኖረው ነውጥ ጥቂቶችን ማሰር ይቻል ይሆናል፡፡ ይህ ግን ትግሉንም ሆነ ድሉን አያቆመውም፡፡ በ1960ዎቹ አጋማሽ ታዋቂው የጥቁሮች መብት ተሟጋች አሜሪካዊው ማርቲን ሉተር ኪንግ በመኖሪያ ቤቱ ላይ የተቃጣበትን የግድያ ሙከራ ተከትሎ በደጁ ለተሰበሰቡት እንዲህ ሲል መናገሩን ታሪክ መዝግቦልናል፦ “እኔን ብታስሩኝ እንኳን ትግላችንን ማቆም አትችሉም፡፡ ምክኒያቱም የምንሰራው ትክክል የሆነ ሥራ ነውና አምላክም ቢሆን ከእኛ ጋር ነው”
ጓዶች ሆይ፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ! ጥቂት ወራት የቀረውን የይስሙላ ምርጫ ረስተን፤ እጅ ለእጅ ተያይዘን በባንዲራችን ሕብረ-ቀለማት አሸብርቀን ይህን የተጠላና በክፋቱ ወደር የማይገኝለትን ጨቋኝ-ሥርዓት በሰላማዊ አመፅ ለማስወገድ፤ እሳት በሚተፉ አንደበቶቻችን አደባባዩን ከማንቀጥቀጥ የተሻለ አማራጭ የለንም፡፡ በጩኸት የፈረሰችው ኢያሪኮ ብቻ ሳትሆን የዛሬውም አገዛዝ ስለመሆኑ ለዓለም የምናውጅባቸው ቀናት እጅግ ቅርብ ናቸው፡፡ ከነማርቲን ጋር የነበረው አምላክም ከተበደለው ህዝብ ጎን ይሰለፋል፡፡ ያኔም የሞትንላቸውና የታሰርንላቸው ጥያቄዎቻችን ጥያቄ መሆናቸው ያበቃለታል፡፡ በድላችን ማግስት ምላሽ አግኝተው ታሪክ ይሆናሉ፡
እስከዚያው ግን የነካኩትን ሁሉ በልቶ የጨረሰ ሥርዓት ቀጣይ ባለተራ የሚያደርገው ለዘብተኞችን እና “ምን አገባኝ” ባዮችን መሆኑን ልብ ልንል ይገባል፡፡ ይህን ሁኔታም ከእኔ ደካማ ቃላት ይልቅ የባለቅኔው ሥንኞች የበለጠ አብራርተውታልና ጥቂት ቀንጭቤ ላብቃ፦
“ዝም ኣልኳቸው ዝም ይበሉኝ
ትቻቸዋለሁ ይተውኝ
አልነካቸውም አይንኩኝ
ብለህ ተገልለህ ርቀህ
እውነት ይተውኛል ብለህ
እንዴት ተስፋ ታደርጋለህ?!….
….የህሊናህ ሚዛን ረግቶ…
ጉዳዩ ሁሉ ኩልል ሲል
የደፈረሰው ሲያጠልል
እግዜር ያሳያችሁ ብለህ ፍረዱኝ እንዳትል
ከናካቴው ሳይጨርስህ
ምንም ቢሆን ሰላም አይሰጥህ”

mandag 9. februar 2015

ይኸውና! ኤርትራ ሞተች ትግል ለሀገር ትንሳኤ! – ተስፋጽዮን መድሃኔ (ፕሮፈሰር

ERITREAN SOLDIERS BEGIN WITHDRAWL FROM FRONT LINES.


… ይህ ጥናታዊ ጽሁፍ እኔ እንደ ግለሰብ በራሴ ተነሳሽነትና ፍላጎት ያዘጋጀሁት ነው። በስተጀርባዬ ሆኖ የገፋፋኝ ማንም ኃይል ወይም የፓለቲካ ድርጅት የለም። በመሆኑም፡ በጽሑፉ ላይ የሰፈረውን ይዘትም ሆነ ስርጭት በሚመለከት ኃላፊነት የምወስደው እኔ ራሴ ብቻ መሆኔን በቅድሚያ ለማሳሰብ እወዳለሁ። ይህ መልእክት በስእለ ድምጽ፡ ማለት በአውዲዮ ቪዲዮ፡ የተቀረጸ ሲሆን በጽሁፍ ደረጃም በትግርኛና በAማርኛ ይኸው ተሰራጭቷል።
ይህንን ጽሑፍ መጀመርያ በትግርኛ አዘጋጅቼ ለመጨረስ፡ ሀገራዊና ህዝባዊ ፍቅር ያላቸው ኤርትራውያን ወገኖቼ በተለያየ መንገድ ድጋፋቸውን ሰጥተውኛል። አንዳንዶቹ መረጃ በማቀበል ሲሳተፉ ሌሎች ደግሞ ጽሑፉን ገና በግርድፉ እያለ ወስደው በማንበብና ጥያቄዎችን ከማቅረብ ባሻጋር ጠቃሚ የሆኑ አስተያየቶችንም ጭምር ለግሰውልኛል። ሌሎቹም እንደዚሁ መልእክቱን በኮምፒዩተር ተጽፎ ከተጠናቀቀ በኋላ፡ ከመሰራጨቱ በፊት ወስደው በጥንቃቄ በማንበብ የፊደላት ግድፈቶችን አርሟል። … ተስፋጽዮን መድሃኔ (ፕሮፈሰር)… ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

onsdag 4. februar 2015

መቶ አለቃ ተሰማ ወንድሙ እስር ቤት ውስጥ በደረሰባቸው ችግር ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የህዳር 27/28 የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የጠራው የአዳር ሰልፍ ወቅት ተይዘው በደረሰባቸው ከፍተኛ ድብደባ እና ለሶስት ቀን የስኳር በሽታ መድሃኒት እንዳይገባላቸው በመከልከላቸው ለህመም የተዳረጉት የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት (መአሕድ) ምክትል ፀኃፊ መቶ አለቃ ተሰማ ወንድሙ ከእስር ከተፈቱበት ጊዜ ጀምሮ ለሁለት ወር ሆስፒታል ከቆዩ በኋላ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
መቶ አለቃ ተሰማ ወንድሙ እኚህ ነበሩ
መቶ አለቃ ተሰማ ወንድሙ እኚህ ነበሩ
መቶ አለቃ ተሰማ ወንድሙ በአዳሩ ሰላማዊ ሰልፍ ወቅት ተይዘው ከፍተኛ ድብደባ የደረሰባቸው ሲሆን ለአምስት ቀናት ቀዝቃዛና ጨለማ ቤት ውስጥ ታስረው ቆይተዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ከታሰሩበት ጊዜ ጀምሮ ይዘውት የነበረውን የስኳር በሽታ መድሃኒታቸውን በመቀማታቸው፣ እንዳይገባላቸው በመከልከላቸውና በወቅቱም ህክምናም ባለማግኘታቸው ለከፍተኛ ህመም በመዳረጋቸው ለሁለት ወር ያህል ዘውዲቱ ሆስፒታል ቆይተዋል፡፡
መቶ አለቃ ተሰማ ወንድሙ እስር ቤት እያሉ በደረሰባቸው ችግር ምክንያት ዘውዲቱ ሆስፒታል ከገቡበት ታህሳስ 4/2007 ዓ.ም ጀምሮ ከፍተኛ ህመም እየተሰቃዩ እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የመቶ አለቃ ተሰማ ወንድሙ የቀብር ስነስርዓት ዛሬ ጥር 27/2007 ዓ.ም በቦሌ ሚካኤል እንደሚፈጸም ለማወቅ ተችሏል፡፡

tirsdag 3. februar 2015

የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ አባላት በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን ተቀላቀሉ

ብሄራዊ ምርጫ ቦርድና ኢህአዴግ በወሰኑብን ፖለቲካዊ ውሳኔ ምክንያት አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ተነጥቀናል>> ያሉ የአንድነት ፓርቲ አባላት› በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸውን ሰማያዊ ፓርቲ አስታውቋል፡፡ በእነ በላይ ፍቃዱ አመራርነት አንድነት ፓርቲን በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ሲመሩ የነበሩ አመራሮች ዛሬ ጥር 26 ቀን 2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ፤ ከቀድሞ ፓርቲያቸው አንድነት ጋር የፕሮግራምም ሆነ የስትራቴጂ ተመሳሳይነት ወዳለው ሰማያዊ ፓርቲ ተቀላቅለው ሰላማዊ ትግላቸውን ለመቀጠል መወሰናቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡
ሌሎችን የ አንድነት አባላትን በመወከል  መግለጫውን የሰጡት፦ የቀድሞው አንድነት ፓርቲ አፈ ጉባዔ  አቶ አበበ አካሉ፣ ምክትል አፈ ጉባዔ አቶ ፀጋዬ አላምረው፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ነገሰ ተፋረደኝ እና የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል ናቸው፡፡
‹‹የምናምነው በሰላማዊ ትግል ብቻ ነው፡፡ ይህን ሰላማዊ ትግል ለመምራት ደግሞ ሰማያዊ ፓርቲ ብቁ ነው ብለን በማመን ፓርቲውን ተቀላቅለናል›› ብለዋል የቀድሞዎቹ የአንድነት አመራሮች።  በዚህም መሰረት በርከት ያሉ  የአንድነት አመራሮችና አባላት በይፋ የሰማያዊ ፓርቲን የአባልነት ፎርም መሙላታቸው ተመልክቷል፡፡
በሌላ በኩል የአንድነት አባላት ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸውን አስመልክቶ መግለጫ ለመስጠት ወደ ሰማያዊ ቢሮ ባቀኑበት ወቅት ፖሊስ ሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ ድረስ በመግባት፦ ‹‹በሰማያዊ ስም መግለጫ የሚሰጡ አካላት እንዳሉ ሰለሰማን ነው›› በሚል ለፓርቲው አመራሮች ጥያቄዎችን ማቅረባቸውን ከሰማያዊ ፓርቲ ጽህፈት ቤት የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።፡፡ ይህ  በእንዲህ እንዳለ-“በመድብለ ፓርቲ ስርዓት ስልጣን ይያዛል ብሎ ማመን ህዝቡን ማታለል ነው” ሲል አንድነት ፓርቲ አስታወቀ

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ባወጣው መግለጫ  ስርዓቱ ለመድብለ ፓርቲ ፖለቲካ የሚመች የአስተሳሰብ ለውጥ እስካላመጣ ድረስ ፣ በመድብለ ፓርቲ ስርዓት ስልጣን ይያዛል ብሎ ማመን ህዝቡን ማታለል ነው ብሎአል።

የምርጫ ቦርድ ፓርቲውን ለማፍረስ የወሰደውን እርምጃ አጥብቆ የኮነነው አንድነት፣ አሁን ባለው ሁኔታ የመድብለ ፓርቲ ፖለቲካ ተቀበረዋል የሚል ድምዳሜ ላይ  መድረሱን አስታውቋል።

አባሎቹ ይህን ህገወጥ እርምጃ በፅኑ እየተቃወሙ ለነፃነትና ለኢትዮጵያዊነት የሚከፈለውን መስዋዕትነት ለመከፍል ዝግጁ መሆን እንደሚኖርባቸው አሳስቧል፡፡

ምርጫን በተመለከተ ፓርቲው አቋሙን ሲገልጽ፣ በአምስት ዓመት የሚደረግ ክብረ በዓል አድርጎ ለማድመቅ እና የህዝብ ሀብት ለማባከን በሚደረግ ሂደት ተሳታፊ ለመሆን አዲስ ፓርቲ መመስረትም ሆነ አሁን ካሉት ፓርቲዎች ጋር ተቀላቅሎ መታገል የሚያመጣው ለውጥ የለም ብሎአል፡፡

በመድብለ ፓርቲ ሰርዓት ስልጣን ይያዛል ብሎ ማመን ህዝቡን ማታለል ነው የሚል ፅኑ እምነት መያዙን የሚገልጸው አንድነት፣   የፓርቲ ፖለቲካ አላበቃም ብለው የሚያምኑ የአንድነት አባላት ካሉ በራሳቸው ነፃ ውሳኔ ወደ ፈለጉት ፓርቲ ተቀላቅለው የመታግል መብታቸው መጠበቁንም አስታውሷል።

ህዝቡ የትግሉ ባለቤት ሆኖ የስርዓት ለውጥ እንዲመጣ  የፓርቲው አባላት ሀገራዊ ግዴታቸውን ለመወጣት ቁርጠኞች መሆናቸውንም መግለጫው ጠቅሷል። አንድነት ፓርቲ በምርጫ ቦርድ ውሳኔ እንዲፈርስ መደረጉ ብዙ ኢትዮጵያውያንን አበሳጭቷል።

mandag 2. februar 2015

አንድነቶች በምርጫ ጨዋታዉ ግጥሚያዉ ሳይጀመር አሸንፈናቸዋል፤በሰላማዊ ትግሉም የመጨሻዉን ሽንፈት ይጎነጫሉ!! – ተክሌ በቀለ

ምርጫ 2007 ለለዉጥ ብለን ተነሳን፡፡በሙሉ ልብና ዝግጅት ለህዝቡ አማረጭ ለመሆን ለምርጫ የሚየስፈልገዉን ግብኣት ይዘን ተሰለፍን፡፡ አጥቂዎችን ከተከላካዮች ለይተን ደጀኖችን ከኃላ አሰልፈን በትምህርት ዝግጅትና በአባላት ጥራት እንዲሁም በሃሳብ የበላይነት ከኢህአዴግ የሚበልለጡ እጩዎችን አዘጋጀን፡፡ ከሃቀኛ ፓርቲዎች ጋር ላለመወዳደር በሰጥቶ መቀበል መርህ ለመዳረደርና ለህዝቡ ብቁ ተመራጭ ይዞ ለመቅረብ ተደራዳሪ ኮሚቲም አቋቋምን፡፡ህወሓት ሃሳብ የለዉም፡፡ቢኖረዉም ያረጀ ነዉ፡፡ለዚህ ትዉልድ አይመጥንም፡፡የሚጮኸዉን ያህል ቀርቶ ከኣባለቱ ሩብ ያህል እንኳን አድማጭ የለዉም፡፡እኛ ብዙ ተምረናል፡፡ከወደቁትና ዛሬም በጽናት ከሚታገሉቱ ቡድኖችና ግለሰቦች ትምህርት ቀስመናል፡፡ከአሮጌዉ ህወሓትም ይሁን ከወጣቱ ሰማያዊ ፓርቲ የምንቀስመዉን ቀስመናል፤ለመማር ዝግ አይደለንም፡፡ለዉህደትና ለትብብርም እንዲሁ፡፡እደሉም ስላልነበራቸዉ እነሱ የብሄረሰብን ጥያቄ ከነስታሊን መጽሃፍት የቃረሙት ሲሆን እኛ በተግባር አብርን ኖረን የምናዉቀዉ፤በብሄረሰብ መሰረት ከተደራጁ ሃይሎች ጋር ግንባር ፈጥረን ችግረቸዉን ተረድተን የህዝብን ጥያቄ በተግባር ለመመለስ የቆረጥን በህዝብና በሃገር ሉኣለዊነት የማንደራደር የዘመኑ አስተሳሰብ ዉጤት ነን፡፡በመሳሪያና በገንዘብ ሳይሆን በሃሳብ የበላይነት ኮርተን፤ ዳኛዉን ሳይሆን ህዝቡን ተማምነን ለምርጫ ጨዋታዉ ዝግጁ ሆነን ነበር፡፡
ሽንፈቱ ከወዲሁ የገባዉ ህወሓት መጋረጃ ዉስጥ ሆኖ ጨዋታዉን ከወዲሁ አበላሸዉ፤አንድነት ፓርቲን ቢያሸዉ ቢደፈጥጠዉ ጎማ ሆነበት፡፡አልፈርጥለት ሲል የመጨረሻዉን አደረገ፡፡በጠራራ ጸሃይ ከህግ በላይ በጉልበት ዋናዉን ቢሮ ወረረዉ፡፡ምን እንደወሰዱ ምንስ እንዳስገቡብን አናቅም፡፡እርጉዝ ሴት በዱላ መትተዉ የወርቅ ሃብል የወሰዱ፤ጽ/ቤት ገብተዉ ምን እንደሚያደርጉ መገመት ይቻላል፡፡ያለ ህግዊና በእማኝ ፊት ርክክብ እንደልማዳቸዉ የህዝብ ሃብት ነጥቀዋል፡፡በሂደቱም ግለሰቦችና የህወሓትን ተግባር ለመፈጸም የተቋቋሙ ተቋማት ጥቁር ታሪካቸዉን ሲያኖሩ በእስር እየማቀቁ ያሉቱ የለዉጥ ሃይሎችና በዚህ ሂደት የለዉጥ ሃይሉን ከሚመራዉ ጋር የቆሙ የእንድነት አባላትና ደጋፊዎች ታሪካቸዉን በወርቅ ቀለም ጽፈዉ አኑረዋል፡፡እንዲሆም ድርጊቱን በማዉገዝ ከጎናችን የቆማችሁ ሁሉ በነጻነት ትግሉ የክብር ቦታ አላችሁ፡፡
አንድነቶች በበምርጫ ጨዋታዉ ግጥሚያዉ ሳይጀመር አሸንፈናቸዋል፤በሰላማዊ ትግሉም የመጨሻዉን ሽንፈት ይጎነጫሉ፡፡ ዛሬም የነጻ አዉጪን ስም የተሸከመዉ ህወሓት የሚያስበዉ እንደራሱ ነዉ፡፡የፓርቲ ስም፤አርማና ማህተም በዚህ ትዉልድ ቦታ እንደሌላቸዉ አልተረዳዉም፡፡የትዉልዱ ጥያቄ በእኩልነት ላይ መሰረትዋን ያኖረች ጠንካራ ሃገር እንጂ እወክለዋለሁ የሚለዉን ህዝብ እንኳን በበለጠ የሚያፍን የፓርቲ ስም አይነት አይደለም፡፡የአንድነት ፓርቲ ፕሮግራምና የኛ ራእይና በኛና በህዝብ ልብ እንዲሁም በሌሎች ፓርቲዎች ዉስጥ እንደሚገኝ አልገባቸዉምና ፓርቲን ሲነጥቁ ሰላማዊ ትግሉን የገደሉ፤እኛንም የበተኑ መስሎአችዋል፡፡የለዉጥና የአንድነት ሃይል ይበልጥ ይጠናከራል እንጂ አይበተንም፡፡እርግጥ ነዉ የመድበለ ፓርቲ ስርኣትን አደጋ ላይ ጥለዉታል፡፡ህዝባዊ ሰላማዊ ትግሉ ላይ ግን ጉልበትና ተጨማሪ እድል ጨምረዉለታል፡፡ የአንድነትና የለዉጥ ሃይሎች ዛሬም ይበልጥ ቁርኝነታችንን በማጠንከር ለሰላማዊ ትግሉ መጎልበት ያለንን አቅም ልናበረክት ይገባል፡፡ሁላችንም እድሉን እንጠቀምበት፤የጠበቡ ቤቶችንም ለሁሉም እንዲሆኑ ባፋጣኝ እናስፋቸዉ !
ይህ ተዉልድ የቃል እዳ አለበት፤እነአንዷለምም እነ አሞራዉም የሚሉቱና እያሉ ያሉቱ ይህን ነዉ፤ ፍትህና ነጻነት በኢትዮጵያችን በትግላችን ይሰፍናሉ!!10933980_997756040251782_3805022157732763333_n
10559726_435976746552563_1734583492566496101_n
10153833_587630041337455_4078181881316786241_n
10846215_387439034753787_52815730277175743_n