torsdag 10. juli 2014

አቶ አንዳርጋቸውን መታሰር ተከትሎ ኢትዮጵያውያን ቁጣቸውን መግለጽ ቀጥለዋል

ሰሞኑን ከአገር ቤት በሚደወሉ ስለኮች የተጨናነቀ ሲሆን፣ አብዛኞቹ ደዋዮች የኢህአዴግን
ስርአት በሃይል ለመፋለም መቁረጣቸውን የሚገልጹ ናቸው።
እንደሰሞኑ ሁሉ ” መንገዱን አሳዩን እና አቶ አንዳርጋቸው ይዘውት የተነሱትን ራእይ እውን እናድርገው ” የሚሉ ወጣቶች እየተበራከቱ ሲሆን፣ አንዳንዶች ደግሞ ህዝቡ
ራሱን እያደራጀ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባው እያሳሰቡ ነው።
አንድ አስተያየት ሰጪ መንግስት ህዝቡን ለማረጋጋት በሚል አቶ አንዳርጋቸውን በቴሌቪዥን ማሳየቱን ገልጸው፤ ህዝቡ በዚህ ሳይዘናጋ ፣
ባርነትን ከራሱ ለማውረድ ከፈለገ የራሱን እርምጃ መውሰድ መጀመር አለበት ብለዋል።
ሌላ አስተያየት ሰጪ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ በየትና እንዴት እንደሚታገል ፍንጭ ነው ያጣው ካሉ በሁዋላ፣ ስራውን መጀመር አማራጭ የሌለው ነገር ሲሉ አክለዋል።
“አንድ ቀን ቀን ይወጣል ብለን” ስንጠብቅ ከርመናል ያሉት አንድ አስተያየት ሰጪ፣ ከእንግዲህ የምንጠብቀው ምንም ነገር የለም፣ ሁሉም ደምቷል ብለዋል።
“እኛም ሴቶች ብንሆን ለትግሉ ብዙ የምናግዘው ነገር ይኖራል” ያለችው አንዲት የራያ ቆቦ ነዋሪ፣ ለነጻነት የሚደረገው ትግል ወደፊት መቀጠል እንዳለበት ገልጻለች።
በሌላ በኩል ደግሞ የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች መግለጫዎችን ማውጣት የቀጠሉ ሲሆን፣ የተቃውሞ ሰልፎችም በተለያዩ አካባቢዎች እየተደረጉ ነው።
የአፋር አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ህብረት ግንባር ወይም በእንግሊዝኛው አርዱፍ በአቶ አንዳርጋቸው መያዝ ቁጣውን ገልጿል።
የመን ህገወጥ በሆነ መንገድ አቶ አንዳርጋቸውን አሳልፋ መስጠቷን በጽኑ ያወገዘው አርዱፍ፣ የመን በፈጸመቸው ህገወጥ ተግባር ተጠያቂ መሆን አለባት ብሎአል።
አቶ አንዳርጋቸውን የመሰሉ የነጻነት ታጋዮችን በማሰር የነጻነት ትግሉ እንደማይቋረጥ የገለፀው አርዱፍ ፣ እንዲያውም ትግሉን የበለጠ እንድናጠናክር ያደርገናል ሲል አክሏል።
የአለማቀፍ ማህበረሰቡ፣ የእንግሊዝ መንግስትና  የኢትዮጵያ ሃይሎች በሙሉ ለአቶ አንዳርጋቸው መለቀቅ አበክረው እንዲሰሩ አርዱፍ በመግለጫው ጠይቋል።
በብሪዝበን አውስትራሊያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ደግሞ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸውን ጋዜጠኛ ኤልሳ ይመኑ ከስፍራው ዘግባለች።
በፊንላንድየሚገኙኢትዮዽያውያንእናትውልደኢትዮዽያውያን ደግሞ ሄልሲንኪ  በሚገኘው የ እንግሊዝ
ኤምባሲ በመገኘት ያዘጋጁትን ደብዳቤ አስረክበዋል። ኢትዮጵያውያኑ በደብዳቤው የየመን መንግስት የፈፀመውን ታሪካዊና ይቅርታ  የማያሰጥ ተግባር በጽኑ አውግዘው
የየመን መንግሥት አለም አቀፍን ሕግ ጥሶ ለፈፀመው ሕገወጥ ተግባር በተለያዩ መንገዶች እና  ግዜያት ዋጋ እንደሚያስከፍለው አስታውቀዋል ።
የእንግሊዝ  መንግስትም  አቶ አንዳርጋቸው  ጽጌ ዜጋው  ስለሆኑ ፣ ሰብአዊ   መብታቸው  ስለተገፈፈ እንዲሁም የህወሓት አገዛዝ በቶርቸር እና ሰብአዊ መብት ረገጣ  አለም አቀፍ
ድርጅቶች ባረጋገጡት መሠረት የታወቀ በመሆኑ ባስቸኳይ ተለቀው እንግሊዝ ሀገር ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲቀላቀሉ የእንግሊዝ  መንግስት ቅድሚያ ሰጥቶ ባፋጣኝ እንዲሰሩ ጠይቀዋል ።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን አምባገነን አገዛዝ፣የሰብአዊ መብት ረገጣ ፣ግድያ የሚዲያ አፈና፣ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት አለመከበር የእንግሊዝ መንግሥት ዝም
ብሎ ማየቱን ከቀጠለ ወይንም ጠንካራ አቋም የማይወስድ ከሆነ ለጊዜያዊ ጥቅም ብሎ ዘለቄታዊ
የሆነውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትና የእንግሊዝ ብሔራዊ ጥቅም ስለሚጎዳ እንግሊዝ በኢትዮጵያ ላይ የምትከተለውን የውጭ ጉዳይ ፓሊስ እንደገና ባትክሮት እንድትመረምረው ጠይቀዋል ።

የአቶ አንዳርጋቸው ይዞታና የሂዩመንራይትስ ዋች ጥሪ

የመን ለኢትዮጵያ መንግሥት አሳልፋ የሰጠቻቸው የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዴሞክራሲ ፓርቲ ዋና ፀሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በኢትዮጵያ እሥር ቤት ውስጥ ይበደላሉ ብሎ እንደሚፈራ ዓለም ዓቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሂዩመን ራይትስ ዋች አስታወቀ ።
Human Rights Watch Logo
የድርጅቱ የአፍሪቃ ጉዳዮች ምክትል ሃላፊ ሚስ ሌስሊ ሌፍኮው ድርጅታቸዉ ሥለ ኢትዮጵያ የእስረኞች ይዞታ ያለዉን ልምድ ጠቅሰዉ እንዳሉት አቶ አንዳርጋቸው በኢትዮጵያ እሥር ቤት ይንገላታሉ የሚል ስጋት አለው ። ሌፍኮው የብሪታኒያ መንግሥት የአቶ አንዳርጋቸው መብት እንዲከበር አስፈላጊውን ጫና እንዲያደርግም ጠይቀዋል ።የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዴሞክራሲ ፓርቲ ዋና ፀሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ኢትዮጵያ እስር ቤት ዉስጥ በደል-ይደርስባቸዋል ለማለት ሑዩማን ራይትስ ዋች የመጀመሪያዉ አይደለም።ሌላዉ አለም አቀፍ የመብት ተሟጋች ድርጅት አምንስቲ ኢንተርናሽንልም ባወጣዉ መግለጫ ተመሳሳይ ሥጋቱን አስታዉቋል።
የሑዩማን ራይትስ ዋች የአፍሪቃ ጉዳዮች ምክትል ሃላፊ ሚስ ሌስሊ ሌፍኮው  እንደተናገሩት ድርጅታቸው መዝግቦ በያዘው መረጃ መሠረት የኢትዮጵያ መንግሥት ከዚህ ቀደም በእስረኞች ላይ ግፍ በመፈፀም ይታወቃል ። የአቶ አንዳርጋቸው እጣም ከዚህ የተለየ አይሆንም የሚል ስጋት አለው ።
Symbolbild Amnesty International und Human Rights Watch gegen Hinrichtung von Jugendlichen
« አይንገላቱም የሚል ተስፋ አለኝ ። ሆኖም መንግሥት በዚህ ረገድ ከዚህ ቀደም የተመዘገባበት መረጃ ጥሩ አይደለም ። ሂዩመን ራይትስ ዋችና ሌሎች ድርጅቶች መንግሥት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከባድ በደሎች እንደሚፈፅም መዝግበዋል ። እንደ አቶ አንዳርጋቸው ከባድ በሚባሉ ወንጀሎች የሚከሰሱ ሰዎች በኢትዮጵያ ፖሊስና የፀጥታ ኃይሎች የሚፈፀሙባቸውን ከባድ በደሎች መዝግበናል ። ስለዚህ እርሳቸውም ተመሳሳይ በደል ይፈፀምባቸዋል የሚል በምክንያት የተደገፈ ስጋት አለን ።
የኢትዮጵያ መንግሥት አቶ አንዳርጋቸውን መያዙን ትናንት ነው ያረጋገጠው ። መንግሥት በሚቆጣጠረዉ ቴሌቪን በሰጠው መግለጫ መሠረት አቶ አንዳርጋቸው ሰኔ 16 2006 ዓም በሰንዓ በኩል ወደ ኤርትራ ሊጓዙ ሲሉ ተይዘው በዚያኑ እለት ነው ለኢትዮጵያ ተላልፈው የተሰጡት ። ሌፍኮ የመን አቶ አንዳርጋቸውን አሳልፋ መስጠቷ ዓለም ዓቀፍ ህግን የሚፃረር እርምጃ ነው ይላሉ ።
« አቶ አንዳርጋቸው ከየመን ወደ ኢትዮጵያ ተላልፈው መሰጠታቸው ያሳስበናል ። ምክንያቱም አሳልፎ መስጠት በራሱ ህገ ወጥ ነው ። የየመን መንግሥት ፀረ ቁም ስቅል ስምምነት ፈርሟል ። ለቁም ስቅል ውይም ደግሞ ለመንገላታት አደጋ ወደ ሚጋለጡበት አገር አሳልፎ ያለመስጠት ግዴታ አለባቸው።አቶ አንዳርጋቸውን በዚህ መንገድ ለኢትዮጵያ መስጠታቸው ዓለም ዓቀፍ ግዴታዎቻቸውን በግልፅ ጥሰዋል። »
Logo von Human Rights Watch der UNO
ሌፍኮ እንደሚሉት ኢትዮጵያ የያዘቻቸውን በትውልድ ኢትዮጵዊ በዜግነት ብሪታያዊ የሆኑትን የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌን መብቶች ማክበር ይኖርባታል ።አቶ አንዳርጋቸው ከጠበቆቻቸው፤ ከቤተሰቦቻቸውና ከብሪታኒያ ኤምባሲ ባለሥልጣናት ጋር በአስቸኳይ እንዲገናኙ ማደረግ ይገባዋል ያሉት ሌፍኮ ይህ ተግባራዊ እንዲሆን የብሪታኒያ መንግሥትም ግፊት እንዲያደርግ ጠይቀዋል ።
«የብሪታኒያ መንግሥት አንዳርጋቸውን ማየት እንዲቻል ና መብታቸውም እንዲጠበቅ የሚችለውን ሁሉ ጠንካራ እርምጃ ይወስዳል ብዮ እጠብቃለሁ ። ብሪታኒያም ለማንኛውም ዜጋዋ ይህን የማድረግ ግዴታ አለባት ። አቶ አንዳርጋቸው ባልተገኙበት የፍርድ ሂደት ሞት የተበየነባቸው ሰው ናቸው ። ሰዎች በሌሉበት የሚሰጡ ብይኖች የተለየ ስጋት ያሳድራሉ ። ስለዚህ የሞት ቅጣትን በመቃወም ጠንካራ አቋም ያለው የብሪታኒያ መንግሥት ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ ሊያሳስብና መብታቸው እንዲጠበቅም የሚችለውን ሁሉ ጫና ሊያደርግ ይገባል ።»

ከልባቸው ደፋር የሆኑ የሀገሬን ልጆች ማየት በመጀመሬ ደስ አለኝ – (ኤሊያስ ገብሩ)

የሰሞኑ የኢትዮጵያችን ሁኔታ ሀዘን፣ ቁጣ፣ ንዴት፣ እልህ፣ ብሎም የደስታ ስሜትን የቀላቀለ ነበር፡፡ የእሰሩ ሁኔታ ቀጥሏል፡፡ ዛሬ እንኳን ከአንድነት ፓርቲ አቶ ሀብታሙ አያሌው እና ከሰማያዊ ፓርቲ አቶ የሺዋስ አሰፋ መታሰራቸውን ሰምተናል፣ አውቀናል፡፡ የዚህ መሰል አካሄድ ግን መዘዝ የሚስከትል ይመስለኛል፡፡
አሁን አሁን ሰዎች እንደጥጃ ከቤታቸው፣ ከየመንገዱ፣ ከሚሰሩባቸው ቦታዎች …እየተወሰዱ መታሰራቸው በሀገራችን እየተለመደ የመጣ አዲስ ክስተት ሆኗል፡፡ ሥልጣን በጨበጡ ኃይሎች ለነገሮች የሚሰጡት ምላሾች የእስር እርምጃ መሆናቸው ከቀጠለ ከትርፉ ይልቅ ኪሳራቸው ማመዘኑ አይቀሬ ነው፡፡ አይንም ጆሮም ያለው መንግሥት ይስማ!
ኤልያስ ገብሩ
ኤልያስ ገብሩ
‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ሰዎች ለምን ይፈራሉ?›› በማለት ራሴን ደጋግሜ የምጠይቅበት ጊዜ ነበር፡፡ አሁንም እጠይቅና የራሴን ምላሽ ለራሴ እሰጣለሁ፡፡ የምቀርባቸውን ሰዎች ጠይቄም ምክንያቱን ለመረዳት ጥረት አደርጋለሁ፡፡ ‹‹ፈሪ ለእናቱ›› የሚል መልስ አስተናግጄም አውቃለሁ፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ ግን ‹‹እመኑ እንጂ አትፍሩ›› ነው የሚለን፡፡
ግን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከልባቸው ደፋር የሆኑ ወንድ እና ሴት ኢትዮጵያዊ ወገኖቼን በድፍረት ብቅ ብቅ እያሉ ማየት በመቻሌ ደስ ብሎኛል፡፡
አሁን፣ ሕግን አክብሮ በድፍረት መንቀሳቀስ እንጂ ያለተፈጥሯችን መፍራት በብዙ ችግሮች ለተተበተበችው ሀገራችን አይጠቅማትም፡፡ ‹‹ፍትሕ አጥተናል››፣ ‹‹ተርበናል››፣ ‹‹ነጻነት አጥተናል››፣ ‹‹በኑሮ ተማርረናል››፣ … እያሉ የዳር ተመልካች መሆን መፍትሄ አይደለም፡፡ ‹‹ኢትዮጵኖች የጀግና ሕዝቦች ነን›› እንል የለ? ታዲያ ሕግን ተከትለን በተግባር እናሳየዋ!
ምንጭ፡ ፍኖተ ነፃነት

tirsdag 8. juli 2014

የሰማያዊ ፓርቲው አቶ የሽዋስ አሰፋ በመኖሪያ ቤቱ ታገተ


ኢ.ኤም.ኤፍ) የሰማያዊ ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ የአቶ የሽዋስ አሰፋ መኖሪያ ቤት በፖሊሶች ተከቦ ብርበራ እየተደረገበት መሆኑ ታወቀ። አቶ የሽዋስም በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ እንደታገቱ ናቸው። ዮናታን አያሌው ከስፍራው እንደገለጸው ከሆነ፤ የሽዋስ አሰፋ በቤቱ እንዳለ ብዛት ያላቸው የፌደራል ፖሊሶች አከባቢዉን በመክበብ ጎረቤቶቹን ካራቁ በኋላ እሱን ብቻውን ቤቱ ውስጥ በማፈን እስካሁን ድረስ ቤቱን እየበረበሩ መሆኑን ባለቤቱ አሳውቃለች፡፡
Yeshwas Assefaባለቤቱ ከስራ በጓረቤቶቻቸው ተደውሎላት ወደ ቤቷ ሄደች ቢሆንም ወደ አካባቢው እንዳትቀርብ ታዛለች፡፡ በአሁኑ ሰዓት አካባቢው ላይ በርካታ ፌደራል ፖሊሶችና ደህንነቶች ውጥረት አንግሰውበታል፡፡ 

mandag 7. juli 2014

የግንቦት 7 ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለኢትዮጵያ ባለስልጣናት ተላልፈው መሰጠታቸውን ተከትሎ ግንቦት 7 የክተት አዋጅ አወጀ

ድርጅቱ ፣ ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓም ባወጣው መግለጫ ፣ “የየመን መንግሥት በህገወጥ መንገድ ያገተብንን የንቅናቀዓችንን አመራር በአስቸኳይ እንዲፈታ በተለያዩ መንገዶች ላለፈው አንድ ሣምንት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም ” ብሎአል።
“የአገሩን የረዥም ጊዜ ጥቅም ማየት የተሳነው የየመን መንግሥት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ይልቅ አምባገኑን ወያኔ መርጦ መሪያችንን ለእርድ አሳልፎ ሰጥቶብናል ፣በዚህም ሳቢያ የየመን መንግሥት ይቅርታ የማያሰጥ ፤ ዘመን የማይሽረው ታሪካዊ ስህተት ፈጽሟል” ሲል ግንቦት 7 አስታውቋል።
” የኢትዮጵያ ሕዝብ ለወዳጅ ጎረቤት ትሁትና ቀና ቢሆንም ጥቃት በሚያደርስበት የቅርብም ሆነ የሩቅ ጎረቤት ላይ ግን ቁጣውን የሚመጥን የአፀፋ እርምጃ መውሰድ ያውቅበታል።” በማለት የሚዘረዝረው የግንቦት 7 መግለጫ፣ “የወያኔ ፋሽስቶች አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በማሰቃየት ትግላችንን ማቀዝቀዝ እንደማይችሉ ልናረጋግጥላቸው እንወዳለን ።”ብሎአል።
“ወያኔ ፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በውንብድና ጠልፎ መውሰዱ የትግሉን ሜዳ አስፍቶታል ፤ የትግሉንም ዓይነት አብዝቶታል ። ይህ ደግሞ የወያኔ ፋሽስቶችን ከፍ ያለ ዋጋ ያስከፍላቸዋል ።” በማለት ድርጅቱ አጸፋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቋል።
“የፓለቲካ ልዩነት አጥር ሆኖ ሳይከልላችሁ ከገናችን ለቆማችሁት የሲቪክ ማኅበራትና ዜጎች ሁሉ በወገናዊ
ተግባራችሁ ልባችን ተነክቷ ልያለው ግንቦት 7 ፣ ከዚህ በላይ ደግሞ ለቀጣዩ ወሳኝ ፍልሚያም እንደምንቆም እና የወያኔን እድሜ እንደምናሳጥር እምነታችን አጠንክሮልናል” ሲል አክሎአል።
መግለጫው ” ከዛሬ ጀምሮ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ አንዳርጋቸውጽጌን ሆኗል” ካለ በሁዋላ፣በአቶ
አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ ለደረሰውና ለሚደርሰው ጥቃት እያንዳንዱ የወያኔ ሹም በግል ዋጋ እንደሚከፍል ፣ ሕዝብ ለሚወስደው እርምጃ ተጠያቂው ራሱ ወያኔ መሆኑን እንዲሁም በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እስር የክተት አዋጅ መታወጁን በመጥቀስ” ህዝቡ ለጥሪው መልስ እንዲሰጥ ጠይቋል።

አቶ አንዳርጋቸው ለኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች ተላልፈው መሰጠታቸውን ተከትሎ ኢትዮጵያውያን የሚያሰሙት ቁጣ እንደቀጠለ ነው

የየመን የጸጥታ ሃይሎች የግንቦት7 ዋና ጸሃፊ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን አሳልፈው በሰብአዊ መብት ጥሰትና ህዝብን በማሰቃየት በአለም የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ዘወትር ለሚወገዘው ለኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች አሳልፈው መስጠታቸው ያበሳጫቸው በአገር ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የነጻነት ትግሉን የምንቀላቀልበትን” መንገዱን ምሩን” በማለት ጥያቄ ሲያቀርቡ፣ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ደግሞ የተቃውሞ ሰልፎችን እያዘጋጁ ነው።
ለኢሳት ስልኮችን እየደወሉ ቁጣቸውን የሚገልጹት ኢትዮጵያውያኑ ፣ አንዳርጋቸው በነፍሳቸው የከፈሉትን  መስዋትነት እነሱም ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
አብዛኞቹ አስተያየት ሰጪዎች ትግሉን ለመቀላቀል መንገዱ እንደጠፈባቸው ሲናገሩ ሌሎች ደግሞ አመራሩን ምን አይነት እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው ይጠይቃሉ።
ግንቦት7 ሰኔ 29 ቀን 2006 ዓም ባወጣው መግለጫ  ትግሉ “ሁላችን አንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን” ወደ ተባለ አዲስ ምዕራፍ መሸጋገሩን ገልጿል።
አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ማለት ልክ እንደሱ ትሁት ሆኖ ግን ቆራጥ፤ ሆደ ሰፊ ሆኖ በዚያው ልክ ደግሞ መራር፤ አስተዋይና ብልህ ሆኖም ተግባር ተኮር መሆን ማለት ነው ብሎአል።
አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ማለት ወያኔን ለማስወገድ መደረግ የሚገባውን እርምጃ ለመውሰድ የተዘጋጀ ሰው እንዲሁም ለአገርና ለትውልድ ቤዛ መሆን ማለት ነው የሚለው የግንቦት 7 መግለጫ፣ አገዛዙ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ ካተኮረባቸው ምክንያቶች አንዱ የወያኔን የዘር ፓለቲካና ፕሮፖጋንዳ በሚያመክን መልኩ በተግባር ትግል ውስጥ ካሉ የኦሮሞ፣ የአፋር፣ የኦጋዴን፣ የጋምቤላ እና ሌሎች ዘውግ ተኮር ድርጅቶችና ንቅናቄዎች ጋር ተግባራዊ ትብብር ማድረግ የሚችሉበት ደረጃ ድረስ ማቀራረብ በመቻሉ መሆኑን ገልጿል።
ንቅናቄው  “አገዛዙን  ለመጣል ትልቁን ድርሻ የሚያበረክተው ሕይወታቸውን ለመስጠት የቆረጡ፡ ከቁም ውርደትና ባርነት ለነጻነትና ለፍትህ ከወያኔ ጋር ጉረሮ ለጉረሮ እየተናነቁ እየጣሉ ለመውደቅ ፤ መስዋእት ለመሆን በወሰኑ ኢትዮጵያዊያን  ወገኖቻችንና  የህዝብ ሃይሎች  የሚያደርጉት ተግባራዊ እንቅስቅሴ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ትግሉን እንዲቀላቀሉ ጠይቋል።
በመላው አለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ደግሞ የተቃውሞ ሰልፎችን እያዘጋጁ ነው። በካናዳ ኦታዋ ማክሰኞ  በብሪቲሽ ከፍተኛ ኮሚሽን መንገድ ከ1 ፒም ጀምሮ ይካሄዳል። በነገው እለት በተለያዩ ከቶሞች የሚደረጉት ሰልፎች ዋነኛ አላማቸው ምንድንነው በማለት ካስተባባሪዎቹ አንዱ የሆኑትን አቶ ውሂብ የሽጥላን አነጋገረናቸዋል
ከአሁን በሁዋላ እያንዳንዱ ፍትህ ወዳድ ኢትዮጵያዊ በዚህ ወሳኝ ወቅት ልዩነትን በማጥበብ በአንድነት ቆሞ የህግ የበላይነትን በሀገራችን ለማስፈን በመፋለም ታማኝነትን ማሳየት ይጠበቅበታል ሲልራዲዮ ነጃሽ አስታወቀ

tirsdag 1. juli 2014

የአቶ አንዳርጋቸውን ጽጌን በየመን መታፈን ተከትሎ ኢትዮጵያውያን የተለያዩ አስተያየቶችን እያሰጡ ነው



የየመን የጸጥታ ሃይሎች የግንቦት7 ንቅናቄ ዋና ጸሃፊ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸውን ማፈናቸውን ተከትሎ በፌስቡክ፣ በቲውቲርና በድረገጾች ላይ የተለያዩ አስተያየቶች ተሰጥተዋል።
አክቲቪስት አበበ ገላው በበኩሉ የመንአቶአንዳርጋቸውጽጌንማገቷሌላአደገኛናበጣምአሳሳቢክስተትነው።የአንባገነኑየህወሃትስርወመንግስትተቃዋሚዎችንማንምአገርበምንምአይነትሁኔታማፈን፣ማሰርናማንገገላታትአለምአቀፍህግንየሚጥስህገወጥድርጊትነው።የመንአቶአንዳርጋቸውንለወያኔአሳልፋእንዳትሰጥናያለምንምቅድመሁኔታእንድትለቅሁሉምነጻነትናፋቂኢትዮጵያዊሁሉበጋራጥረትሊያደርግይገባል።የየመንኤምባሲዎችንበያሉበትበተቃውሞማጨናነቅናእንቅልፍመንሳትእንዲሁምአለምአቀፍጫናማድረግያስፈልጋል።ግዜሳይረፍድይህንንየቁርጥቀንኢትዮጵያዊለመታደግበያለንበትበጋራእንረባረብ።” ሲል ጥሪ አቅርቧል።
ፕራይድ ዲ ባሰፈረው ጽሁፍ ደግሞ ” እውነተኛ ታጋይ ሊታሰር ሊሞት ይችላል፣ የተጀመረውን ትግል ግን ሊያስሩትም ሆነ ሊገሉት ከቶ አይቻላቸውም። ኢትዮጵያም አንድ አንዳርጋቸውን ብቻ ሳይሆን ሚሊዮን አንዳርጋቸውን ፈጥራለችና በከንቱ አትድከሙ፣ ወደዳችሁም ጠላችሁም ሁላችንም ግንቦት 7 ነን።” ብሎአል።
የአረና ፓርቲ አመራር አባል የሆነው ወጣቱ ፖለቲከኛና መምህር አብራሀ ደስታ ከመቀሌ ባሰፈረው ጽሁፍ ደግሞ ” በርካታኢትዮጵያውያንስደተኞችበየመንሲሰቃዩየኢህአዴግመንግስትዝምታመምረጡይገርመኝነበር።ኢትዮጵያውያንበየመንይታሰራሉ፣ይገረፋሉ፣ይገደላሉ።መንግስትናሀገርየሌላቸውይመስልማንምየሚደርስላቸውየለም።ይህንነገርእንቆቅልሽሆኖብኝነበር።ለካኢትዮጵያውያንስደተኞችበየመንሲሰቃዩየኢትዮጵያመንግስትሰምቶእንዳልሰማየሆነውየየመንመንግስትየግንቦት 7ንአመራርአባላትበመያዝእንዲተባበረውለማግባባትነው።ይሄውኢህአዴግለዜጎችደህንነትሳይሆንለስልጣኑየቆመየማፍያዎችድርጅትመሆኑአስመሰከረ።መንግስትየሚመሰረተውየህዝብናሀገርደህንነትለመጠበቅነው።ኢህአዴግግንየስደተኞችንደህንነትወደጎንትቶለስልጣኑየሚፈታተኑትንግለሰቦችበመያዝስራተጠምዷል።ለስልጣንጥበቃየሚውልንያህልለዜጎችደህንነትምየሚውልቢኖርመልካምነውእላለሁ።” ብሎአል።
ዘላለም ጸጋየ በበኩሉ ” በሀገራችንመኖርሲያቅተንእንሰደዳለን፡፡ተሰደንእንኳንእንታደናለን፡፡ኦአምላክሆይምነውእረሳኸን፡፡ኢትዮጵያውያንልጆችህእንደራሄልእንባቸውጸባዖትየሚደርሰውመቸነው፡፡ ጃያስተሰርያ” ያለ ሲሆን፣ ነጻነት ይበልጣል ደግሞ ” የመንበኢትዮጵያህዝብየነፃነትትግልላይጣልቃመግባቷንእንድታቆምለጫትናለርካሽለሆነጥቅምየወንበዴስብስብየሆነውወያኔኢህአዴግጋርበማበርታጋዮቿላይእየደረሰላለውአፍናመከራእንግልትተባበሪበመሆንየሀገራችንታሪካዊጠላትእየሆነችእንደምትገኝሊገነዘቡትይገባል:፡” ብሎአል።
የነፃነትትግልሁሉንምመራራመከራለመቀበልመፍቀድነው በሚል ርእስ ሥርጉተሥላሴ ባወጣችው ጽሁፍ ደግሞ ” የነፃነትትግልመከራንለመቀበልተፈቅዶናተወዶየሚወሰድእርምጃነው።የነፃነትትግልየጫጉላጊዜሽርሽርአይደለም።ሊሆንምከቶውንምአይችልም።ስለዚህዛሬበግንቦት 7 ጸሐፊበአቶአንዳርጋቸውጽጌየደረሰውእግታከትግልመስምርአንዱበመሆኑሊያደናግጥየሚገባውየዓለምፍጻሜአይደለም።ጀግኖችአባቶቻችንናእናቶቻችንእራሳቸውንሰጥተውነውኢትዮጵያሀገራችንከክብሯጋርያቆዩን።” ብላለች።
ሙላት ሃይሉ ለየመኑ ፕሬዚዳንት በጻፈው ደብዳቤ ደግሞ ” የየመን መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር የሚኖረውን የረጅም ጊዜ የጥቅም ግንኙነት በመመርመር አቶ አንዳርጋቸውን አሳልፎ እንዳይሰጥ ጠይቋል። ሙላት አቶ አንዳርጋቸው በኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲያዊ ስርአት እንዲሰፍን እራሱን አሳልፎ የሰጠ ሰው መሆኑን ገልጿል።
ለኢሳት በኢሜል ከደረሱት መልእከቶች መካከል ፣ አዱኛ የተባሉ ሰው “ለነጻነት በሚደረግ ትግል  ውስጥ መሪ ወይም ታጋይ ቢሞት፣ ቢታሰር ወይም ቢሰደድ ትግል አይቆምም፣ ትግል የሚቆመው ወይም ቅርጹ የሚቀየረው የተፈለገው ነጻነት ሲመጣ ብቻ ነው። አንድ መሪ በመታሰሩ ወይም በመሞቱ ትግል የሚቆም ቢሆን ኖሮ የጆን ጋራንግ ደቡብ ሱዳን ወይም የማንዴላዋ ደቡብ አፍሪካ እስከዛሬም አይወለዱም ነበር። አንዳርጋቸው ጽጌ ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ጀግና የነጻነት ታጋዮች መካካል በመጀመሪያው ረድፍ የሚሰለፍ ነው። አንድም ቀን ለልጆቹና ለኑሮው ሳያስብ በረሃ ለበረሃ የሚንከራተት፣ ለአገሩ ነጻነት ሲል ውድ ህይወቱን ለመስጠት ቆርጦ የተነሳ እውነተኛና ጀግና መሪ ነው።  አንዳርጋቸው ቆራጥና ጀግና ሰው ነው። የአገሩ ጉዳይ ሁሌም ስለሚያንገበግበው እረፍት የለውም። የየመን መንግስት አንዳርጋቸውን ለወያኔ ጅቦች አሳልፎ እንደማይሰጠው ተስፋ አደርጋለሁ፣  ቢያደርገው እንኳን ለነጻነት የሚደረገው ትግል መልኩን ቀይሮ፣ እስካሁን ከታየውም በበለጠ ቆራጥነትና አንዳንዴም ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ይካሄዳል እንጅ አይደበዝዝም።  ” ብሎአል።