onsdag 10. september 2014

የዓመቱ ምርጥ ሰው መምህር አብርሃ ደስታ ሆነ (የ36ቱን እጩዎች ዝርዝር ይዘናል)


  • 207
     
    Share
person of the year
እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን። የዘ-ሐበሻ አንባቢያን ከሦስት ዓመት በፊት መምህር የኔሰው ገብሬን የዓመቱ ምርጥ ሰው ሲሉ በ2004 ዓ.ም መርጠው ነበር። ቀጠሉና በ2005 ዓ.ም የዓመቱ ምርጥ ሰው አድርገው የሰየሙት እድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት የሚገኘውውን አንዷለም አራጌን ነበር። ዘንድሮም እንዲሁ ዘ-ሐበሻ ለአንባቢዎቿ የአመቱን ምርጥ ሰው ምረጡ በሚል ባቀረበችው መጠይቅ መሰረት የተለያዩ ምርጥ ታጋይ ኢትዮጵያዉያን የአንባቢዎቻችንን ድምጽ አግኝተዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ መራጮች በሰጡት ድምጽ መሰረት ለአመቱ ምርጥ ሰውነት የታጩት የሚከተሉት ናቸው።
1ኛ. ቴዲ አፍሮ
2ኛ. አበበ ገላው
3ኛ. ታማኝ በየነ
4ኛ. አብርሃ ደስታ
5ኛ. ጥሩነሽ ዲባባ
6ኛ. መሠረት ደፋር
7ኛ. ሔኖክ ዓለማየሁ
8ኛ. አንዷአለም አራጌ
9ኛ. እስክንድር ነጋ
10ኛ. አንዳርጋቸው ጽጌ
11ኛ. ሌንጮ ለታ
13ኛ. ጄነራል ከማል ገልቹ
14ኛ. ታጋይ ሞላ አስገዶም
15ኛ. ርዕዮት ዓለሙ
16ኛ. አቡበከር አህመድ
17ኛ. ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ
18ኛ. ኃይለማርያም ደሳለኝ
19ኛ. ካፒቴን ኃይለመድህን አበራ
20ኛ. ሊያ ከበደ
21ኛ. የሺዋስ አሰፋ
22ኛ. በቀለ ገርባ
23ና ኦልባና ሌሊሳ
24ኛ. ፕ/ር ተካልኝ ማሞ
25ኛ. ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
26ኛ. ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም
27ኛ. ኢንጂነር ተስፋሁን ጨመዳ (በወህኒ ቤት ያረፉ)
28ኛ. ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት
29ኛ. ዶ/ር መረራ ጉዲና
30ኛ. ሃብታሙ አያሌው
31ኛ. የሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ምዕመናን
32ኛ. ኦባንግ ሜቶ
33ኛ. ቴዎድሮስ አድሃኖም
34ኛ. በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵዮጵያውያን
35ኛ. ጃዋር መሐመድ
36ኛ. እና ሌሎችም
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ገልሰቦች ድምጽ ያግኙ ኢትዮጵያውያን ሲሆኖ ክነዚህ ውስጥ 624 ድምጾችን ያገኘው ታዋቂው ታጋይና በአሁኑ ወቅት በእስር ቤት የሚገኘው አብርሃ ደስታ ነው። ከሱ በመቀጠል ተቀራራቢ ድምጽ ያገኘው ታጋይ በወያኔ እስር ቤት የሚገኘው አንዳርጋቸው ጽጌ ነው። 601 ድምጾችን ያገኘው አንዳርጋቸው ጽጌ በቀጣይ ሲቀመጥ 534 የሚሆን ድምጽ ያገኘው ደግሞ ታጋይ ሃብታሙ አያሌው ነው። የዓመቱ ምርጥ ዘፋኝ የሚለውን የአንባቢዎቻችንን ክብር ያገኘው ቴዲ አፍሮ ሲሆን 369 ድምጾችን አግኝቶ ከሌሎች አርቲድቶች የተለየ ሆኗል።

tirsdag 9. september 2014

የቀድሞው የጋምቤላ መሪ በክልሉ ለደረሰው ጭፍጨፋ የህወሃት ባለስልጣናትን ተጠያቂ አደረጉ

አቶ ኦሞድ ኦባንግ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ 400
ሰዎች የተገደሉበት የጋምቤላወኢ ጭፍጨፋ እንዴት እንደተከናወነ በዝርዝር አስረድተዋል።
የህወሃት ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት አቶ አባይ ጸሃየ ግድያውን በተመለከተ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል።
በክልሉ ስለሚፈጸመው ሙስናና የመሬት ወረራ የቀድሞው ባለስልጣን በዝርዝር ገልጸዋል። አቶ አዲሱ ለገሰ
በቅርቡ ባወጡት ጽሁፍ በጋምቤላ ለኢህአዴግ ታማኝ የሆነ ሰው ለማግኘት እንዳልተቻለ ገልጸው ነበር።
አቶ ኦሞድ ውጭ አገርከወጡ በሁዋላ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ ይህ የመጀመሪያ ጊዜያቸው ነው። የቀድሞው ባለስልጣን ከክልል ፕሬዚዳንትነታቸው ከወረዱ በሁዋላ የፌደራል ጉዳዮች ም/ል ሚኒስትር ሆነው ሰርተዋል።

mandag 8. september 2014

በአዲስ አበባ በየሰፈሩ ዲሽ የሚገጥሙ ወጣቶች “ኢሳትን እየቀጠላችሁ ነው በሚል ወከባ ይደርስባናል” አሉ


  • 405
     
    Share
Dish addis ababaአዲስ አበባ ውስጥ በየ ቤቱ እየዞሩ ዲሽ የሚገጥሙ ወጣቶች ‹‹ኢሳትን እየቀጠላችሁ ነው›› በሚል ወከባ እንደሚደርስባቸው ገለጹ፡፡ ወጣቶቹ ከኢሳት ውጭ ያሉ ጣቢያዎች የሚተላለፉበት ዲሽ በሚገጥሙበት ወቅትም ‹‹ኢሳትን እየቀጠላችሁ ነው፡፡ ህዝቡ ኢሳትን እንዲያይ ታደርጋላችሁ›› በሚል በደህንነቶች ወከባ እንደሚደርስባቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡
በተመሳሳይ ከወራት በፊት መርካቶ አካባቢ ዲሽ የሚገጥሙ ወጣቶች ‹‹ኢሳትን ለህዝቡ እያሳያችሁ ነው›› ተብለው በፖሊስ ተይዘው እንደነበር ተጠቁሟል፡፡ ያም ሆኖ ግን በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች ኢሳትን እንደሚገጥሙ የሚያሳዩ የዲሽ ማስታወቂያዎች ይታያሉ፡፡ ምንጭ ነገረ ኢትዮጵያ

fredag 5. september 2014

የለገጣፎ ነዋሪዎች በ10 ቀን ውስጥ ቤታቸውን እንዲያፈርሱ መታዘዛቸውን ነገረ ኢትዮጵያ ዘገበ

ለገጣፎ ውስጥ በሶስት ጎጦች የሚኖሩ ዜጎች በ10 ቀን ውስጥ ቤታቸውን እንዲያፈርሱ መታዘዛቸውን ጋዜጣው
የትእዛዝ ወረቀቱን በማያያዝ ያሰፈረው ዜና ያማለክታል፡፡ጎራጎጭ፣ዳሌናድሬበተባሉትሶስትጎጦችእስከ 23 ሺህህዝብእንደሚኖርባቸው
ነዋሪዎቹ ለጋዜጣው ዘጋቢ ተናግረዋል። “የሰንዳፋወረዳሰራተኛናማህበራዊጉዳይጽ/ቤት ማህተም አስቀርጾ የመረዳጃ እድር ማቋቋሙን፣ ለመብራትኃይልአንድሚሊዮንያህልገንዘብከፍለውትራንስፎርመርለማስተከልእየተጠባበቁመሆናቸውንና፣የውሃናሌሎችተቋማት
ህጋዊለሆነአካልየሚሰጡትንአገልግሎትከፍለውእያገኙእንደቆዩበመግለጽየሚኖሩበትአካባቢህገወጥአለመሆኑንበመግለጽ እየተከራከሩ
ቆይተዋል። እንደጋዜጣው ዘገባ  ነሃሴ 26 ተጻፈየተባለናከፊንፊኔልዩዙሪያ  በረህወረዳ   የመሬትአስተዳደርጽ/ቤትእንደሆነ
የሚገልጽፊርማየሌለውደብዳቤ  ማምነታቸው በውል ያልተለየ ሰዎች ነሃሴ 30 ለጥፈውመሄዳቸውንነዋሪዎቹገልጸዋል፡፡
በደብዳቤውም ላይ ‹‹በዚህቦታየሰፈራችሁሰዎችቦታውየእርሻቦታስለሆነቤታችሁንአፍርሳችሁእንድትለቁ፡፡ይህንካላደረጋችሁአፍራሽ
ግብረሃይልልከንአስፈርሰንመሬቱንወደመሬትባንክእንዲገባእናደርጋለን ›› የሚልመሆኑንነዋሪዎች ገልጸዋል።
በሌላ ዜና ደግሞ  የቀድሞፕሬዚደንትግርማወ./ጊዮርጊስበዚህዓመት መጀመሪያየተኩትፕሬዚደንትዶ/ርሙላቱተሾመለሕዝብየገቡትንቃል
የአዲስአበባከተማአስተዳደርሳይፈጽም ቀረ፡፡ ዶ/ርሙላቱበገዥውፓርቲለፕሬዚደንትነትከተመረጡበኃላመስከረም 27 ቀን
2006 ዓ.ምለፓርላማውባደረጉት ንግግርመንግሥትበዚህዓመትሊያከናውንናሊያስፈጽምካሰባቸውፕሮጀክቶችአንዱበሆነው
የቤቶችግንባታ 74ሺህ
ያህልቤቶችለተጠቃሚዎችእንደሚተላለፉይፋቢያደርጉምዓመቱሊጠናቀቅከሳምንትያነሰዕድሜበቀረውበዚህ
ወቅትይህየፕሬዚደንቱቃልተግባራዊሊሆንእንዳልቻለከአስተዳደሩየተገኘመረጃጠቁሟል፡፡
ፕሬዚደንቱበወቅቱለኢትዮጵያሕዝብበቀጥታየቴሌቪዥንስርጭትየተላለፈውንየፓርላማንግግራቸው 95ሺህያህል
ቤቶችግንባታእየተካሄደመሆኑንከዚህውስጥ 21ሺህያህሉለተጠቃሚዎችመተላለፉንጠቅሰውቀሪው 74ሺህቤቶች
በዚህዓመትለተጠቃሚዎችእንደሚተላለፍይፋአድርገዋል፡፡
የአዲስአበባከተማአስተዳደርግንቤቶችመሠረተልማትአልተሟላላቸውምበሚልሰበብግንባታውንለምርጫድጋፍ
ማሰባሰቢያለማድረግዕጣውከመጪውዓመትታህሳስወርበሃላበተከታታይለማውጣትማቀዱታውቋል፡፡

አንጀሊና ጆሊ ኢትዮጵያ ውስጥ የሰራችው ”ድፍረት” ፊልም በፖሊሶች ታገደ (አቤ ቶኮቻው)

አቤ ቶኮቻው
አንጀሊና ጆሊ ኢትዮጵያ ውስጥ የሰራችው ”ድፍረት” ፊልም በፖሊሶች ድፈረት በርካታ ”ትላልቅ” እንግዶች በተገኙበት ሊመረቅ ሲል ታገደ፤ አርቲስቶች አዝነዋል እኛም የጥንቸሏን ተረት አስታውሰናል…
409864572-12ሜሮን ጌትነት በመሪ ተዋናይነት ሰርታበታለች የተባለው ይህ ፊልም የታገደው በፖሊሶች ቀጭን ትዛዝ ነው። በርካታ አርቲስቶች የዚህ አይነት ነገር ሲያጋጥማቸው ለመጀመሪያ ግዜ መሆኑን ተናግረዋል። እኛ ግን የነጻ ጋዜጠኞች ማህበር ስብሰባ ፖሊስ በትኑ ሲል ሰምተን እናውቃልን እና፣ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ሰብሰባዎች ከተሰበሰቡ በኋላ ብዙ ጊዜ አምቦውሃው መንግስታችን ሲበትነው አየተናልና፣ የባለራዕይ ወጣቶችን ሰላማዊ ስብሰባ በተደጋጋሚ ያለምንም ሀጋዊ ከለላ ሲያገደው አየተናልና… የዳዊት ጸጋዬ ቲያትር ማስመረቂያ አጥቶ ከሰማያዊ ፓርቲዎች ጋር ቦታ ፍለጋ ሲነከራተት መሰንበቱን እናውቃለነና ኧረ ስንቱ…
(በነገራችን ላይ ዘ ዲክታተር የተባለው አስቂኝ ፊልም እንኳ፤ ባንድ ወቅት ርሳቸው ሬሳ ከመሆናቸው በፊት…(ውይ እኔ ደግሞ አንዳንዴ አበዛዋለሁ አቶ መለስ ”ከመሰዋታቸው” በፊት ማለቴ ነው… እና ያኔ ታግዶ ነበር።) ይሄንን ሁሉ ያልሰሙ አርቲስቶች ዛሬ ተደነቁ እንጂ መንግስታችን ማገድ ብርቁ አይደለም።
የጥንቸሏ ተረት ምን መሰላችሁ…
ዝሆን እና ጥንቸል ሲኒማ ቤት ተገናኙ አሉ፤ ከዛ ዝሆን ሆዬ ከጥንቸል ፊት ሄዱ ቁጭ ብሎ ከለላት አይገልጸውም…(ከፊልም ቤት አስወጣት ብንል ይሻላል…ሃሃ) እና ታድያ ጥንⶨሊት ዝሆንን በቡጢ እየደበደበች በሹክሹክታ ”እረ በናትህ ዝሆን አይደብርህም እንዴ ከለልከኝ እኮ…” እያለች ብትወተውት ብትወተውት አለሰማ አላት… (ዝሆን እኮ ጆሮው ትልቅ ነው እንጂ በተልቁ አይሰማም… ) ከዛ ብዚህ የተበሳጨችው ጥንቸል ከፊት ለፊቱ ሄዳ ቁጭ አለች እና ፊልሟን ኮመኮመች በማብቂያው ላይ ዞር ብላ ”አየህ አይደል የመከለል ነገር እንዴት እንደሚያበሳጭ” አለችው አሉ…
አርቲስቶቻችን የመታገን ነገር አያችሁት አየደል እንዴት እንደሚያበሳጭ… በፊልም እና ድራማ ስራ ተወጥራችሁ ልብ አላላችሁትም እንጂ እናንተ ላይ ሀዝቡ ላይ የደረሰው እገታ ዝሆኑ ጥንቸሏን ሲከልላት የነበረው አይነት ነው…!
ይሄንን እና ሌሎች እገታዎችን ለመቃወም እና መጪው አመት ብሩህ እንዲሆን ለመስበክ ነው‪#‎Blackweek‬ ብለን እየዘከርን ያለነው፤
ለማንኛውም እንሆ ፊልሙ በፖሊስ ቀጭን ትዛዝ ሲታገድ የሚያሳይ ቪዲዮ!
Abe Tokichaw

በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ካድሬ ለማድረግ የተጠራው ስልጠና በማስፈራራት ተጠናቀቀ

በአፋር ክልል በረእሰ መዲናው በሰመራ የሚገኘው ብቸኛው ዩኒቨርሲቲ ለ10 ቀናት ሲሰጥ የቆየው የተማሪዎች ሰልጠና ባለፈው ሰኞ ተጠናቀቋል። በስልጠናው የክልሉ የፓለቲካ መሪዎች የተገኙ ሲሆን በአጣቃላይ ሰለ መጭው ምርጫ ቅስቀሳ እንደነበረ ምንጮችን ገልፆል።
afar univercity
እንደ ምንጮቻችን ዘገባ ከሆነ ለመጪውው ምርጫ ኢህአዴግን ምረጡ ካልመረጣቹሁ ግን ስራ አታገኙም በሚል ብዙ ማሰፈራራት የበዛበት ስልጠና እንደነበረ ታውቋል፡
በዚህ አመት ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲ የተመረቁ ተማሪዎች በሰልጠናው የተገኙ ሲሆን በተማሪዎች በኩል ለሚነሱ ወቅተዊ ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ማስፈራራትና ማስጠንቀቅ እንደነበረ ታይቷል።
በመጪው ምርጫ ኢህአዴግ እና የክልሉ ፓርቲ አብዴፓ በዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች ላይ ያላቸው ድፍራቻ በግልፅ በታየበት በዚህ ስልጠና በክልሉ በግልፅ ስለሚታዩ ችግሮች ላይ የሚናገሩ ተማሪዎች ስማቸው እየተመዘገበ እንደነበረ የአይን እማኞች ገልጸዋል።
በዘንድሮው ምርጫ በመላው ኢትዮጵያ ሊነሳ ስለሚችለው ሁከት ተማሪዎችን ከወዲሁ የማስጠንቀቅ ስልጣና ይመስላል ሲሉ አሰተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።

tirsdag 2. september 2014

ተማሪዎች ዘንድሮም ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በግዴታ እንዲከፍሉ ታዘዙ

መጪውን የትምህርት ዘመን ለመጀመር የሚያስችል ምዝገባ ለማካሄድ በትምህርት ቤቶች የተገኙ
ተማሪዎች ለአባይ ግድብ ገንዘብ የማያዋጡ ከሆነ እንደማይመዘገቡ ተገልጸላቸዋል።
ተማሪዎቹ በነፍስ ወከፍ 120 ብር የማይከፍሉ ከሆነ ምዝገባ እንደማያካሂዱ እንደተነገራቸው ለኢሳት እንደተነገራቸው ገልጸዋል።
ሁለት እና ከዚያ በላይ  ልጆች ያላቸው ወላጆች በቤተሰብ ደረጃ ሳይሆን በእያንዳንዱ ልጅ ስም የመክፈል ግዴታ ተጥሎባቸዋል።
አንዳንድ ተማሪዎች በእያመቱ ለአባይ ግድብ እየተባለ የምንከፍለው ክፍያ አግባብ አይደለም በማለት አስተያየታቸውን ለኢሳት ዘጋቢ ገልጸዋል።
መንግስት ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ከህዝብ እስበስበዋለሁ ብሎ ያሰበው እቅዱ አልተሳካለትም። በአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝና በአቶ በረከት ስምኦን
የሚመራው የገንዘብ አሰባሳቢ ኮሚቴም እንቅስቃሴዎችን ሲያደርግ አይታይም። በውጭ አገር ለግድቡ ማሰሪያ ይደረጉ የነበሩ ዝግጀቶችም በውጭ
አገር ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሚደርሰው ተቃውሞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቆመዋል።