lørdag 31. januar 2015

የሚሊዮኖች ድምጽ ጋዜጣ (ቁጥር 5)

የሚሊዮኖች ድምጽ ጋዜጣ በየሳምንቱ በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ እየታተመ ለህዝብ የሚቀርብ ጋዜጣ ነው። ጋዜጣው በዚህ ሳምንት እትሙ የሚከተሉትን አበይት ጉዳዮችን ይዟል።
-‹‹የፈሰሰው ደምና የተሰበረው አጥንት ለነጻነት የተከፈለ ዋጋ ነው›› -የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በላይ በፍቃዱ ፕሬዝዳንት
-መንግሥት መሸኛው ደርሷል!  – እሱም ይሄን ያውቃል!
“በውንብድና የሚቆም የነፃነት ትግል አይኖርም!” ነብዩ ሃይሉ
አቶ ኤርሚያስ ለገሠ/ የቀድሞ የመንግሥት ጉዳዮች ኮሙኑኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ/ ደግሞ ለሚሊዮኖች ድምጽ ልዩ ቃለ ምልልስ ሰጥተዋል። ከተናገሯቸው ዋና ዋና ነገሮች መካከል የሚከተሉት አንኳር ጉዳዮች ይገኙባቸዋል።
‹‹ሀገራችን መስቀለኛ መንገድ ላይ ቆማለች››
‹‹ለኢትዮጵያ ህዝብ፣ በተለይም ለአዲስ አበባ ህዝብ ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ››
‹‹ምርጫ ቦርድ በህወሃት ቁጥጥር ሥር ያለ ተቋም ነው። የሰው ኃይሉን ምደባና ቅጥር ያደረግነው እኛ ነን››
‹‹ወዳጄ ሽመልስ ከማል 90 በመቶ ጊዜውን የሚያጠፋው በጋዜጦች ላይ እንከን በመፈለግ ነበር››
‹‹አልፎ አልፎም ለፍትህ ሚኒስቴር የክስ ቻርጅ የሚያዘጋጀው ሽመልስ ከማል ነበር››
‹‹አንድነቶች በምንም መልኩ መደናገጥ የለባቸውም›› ይላሉ። ከአቶ ኤርሚያስ ጋር የተደረገውን ሙሉውን ቃለ ምልልስ በዚህ እትም ላይ ያገኛሉ።

fredag 30. januar 2015

ምርጫ ፣ የሀገሬ ፖለቲካና የህዝብ ድምጽ ! – ነቢዩ ሲራክ

tagel
* ” እናንተስ በምርጫ ትወርዱ ይሆን? ” አልኩ የምርጫ ቦርድን ውሳኔ ቢያስገርመኝ
ምርጫ በቀረበ ቁጥር የእኛ ሀገር የውስጥና የውጭ ፖለ ቲካ ምህዳር ይደማምቃል፣ ይተረማመሳል ። በዘመኔ በሀ ገሬ እውነተኛ ሆኖ ብዙሃን የተሳተፉበት ምርጫ አላየሁም ። ”  ያን የከፋ መስዋዕትነት የተከፈለበትን ትግል ጠረጴ ዛ ላይ ሆነህ ምርጫ በመቀስቀስ ልትወስደው ትፈልጋለህ?  ” የሚል ጋን ጩር ፖለቲከኛ በሞላባት ሀገር ምርጫ ለይስሙላ እንጅ የህ ዝብን ፍላጎት ለማክበር ተደርጓል ማለት አልችልም።   ምርጫ በእኛ ሀገር ጉልበተኞች ትላልቅ አሳዎች ፣ ትናንሾቹን አሳዎች እንደ ሚውጡት አይነት ነው ። አንዱ አውራ “ትልቅ ነኝ ” ባይ ፖርቲ ትንንሾቹን ተቃዋሚዎች ሲለው እየዳጠ ፣ እየሰለቅጠና በሌላ አምሳያ እየተካ መጓዙ በማን አለብኝነት ይጓዛል።  ይህ እየሆነ ተቸግረናል። ገና ምርጫ ቅስቀሳ ሲባል ትንሹ ትልቁን የሚያንኳስስበት ፣ ፖለቲከኞች በሰላማዊ ፉክክር ሳይሆን በሰይጣናዊ ፉክክር የሚጠመዱበት ፣ የመጠላለፊያ ወቅት ሆኖ ችግር ላይ ነን ።  ዛሬ ዛሬ ደግሞ ምርጫውን ነጻ ማድረ ግ ኋላፊነት የተሰጠው ምርጫ ቦርድ በዘባተሎው ፖለቲካ እጁን አስገብቶ ፖለቲካው የሚቦጫጨቅና የመዘራጠጥ የወ ረደ ምህዳር እያደረገው መሆኑን ዛሬ በሰጠው ውሳኔ እያሳየን ነው  !  በዚህ ፉክቻ ከሚጎዳው ሰላማዊ የፖለቲካ ሂደት ብቻ አይደለም ፣ በንትርክ ግብግቡ ፣ በሚፈሰው የሰው ደም ሀገር ትጎዳለች  !
የሃገሬው ብሶት ሲገለጥ ..
በምርጫ ማሸነፍ መሸናነፍ በወጉ በማይከወንባት ሃገር በኢትዮጵያ ድሮም ሆነ ዛሬ የሃገሬው እድገት በመንግስት ሲገ ለጽ ፣ የሃገሬው ድቀት ፣ ብሶትና ምሬት በሃገሬው በየጉራንጉ ሩ በጥብብ ተሸፋፍኖ ይገለጻል ። የሃገሬውን የውስጥ ነዲድ ወኔ ፣ ፍላጎትና  ምኞት ገላጮች ደግሞ የስነ ጽሁፍ ባለሙያ ዎችና አርቲስቶች ናቸው ። ላለፉት ሃያ አመታት በሃገራቸው ፖለቲካዊና ማህበራዊ ኩነቶች ዙሪያ ድምጻቸውን ባንድ ጎራ ያሰሙ የነበሩና ያልነበሩት የእኛ የጥበብ ሰዎች መናገር መተን ፈስ ጀምረዋል ።
የአርቲስት ሜሮን ጌትነት የተዋጣ የተጨበጨበለት “የአት ሂድ” መልስ “ሂድ ” ግጥም ጥልቅ ለመሆኑ ከእውነት ጋር ያለ ው ተዛማጅነት ብቻ ነውና በጥበብ እስትንፋሷ የህዝብ ብሶት ተገልጧል ባይ ነኝ ። ግጥሙ አሁን ድረስ ከጓዳ እሰከ አደባባ ይ የተለያዩ መድረኮችን ጠረጴዛ በመነጋገሪያነት  የማድመቁ ሚስጥር በግጥም የተገለጸው እውነት በመሆኑ ብቻ እንጂ ደልዳላዋ ቆንጆ ባማረ ቅላጼ ስላቀረበችው አይደለም። እውነቱን ዘርግፋ በመናገሯ እንጅ  !
ሌላዋ ተጠቃሸ የአርቲ ስት አስቴር በዳኔ በጥበብ የደመቀ ታላቅ መጽሃፍ እንደጻፈች ስሟ ከዳር አስከ ዳር የመግነኑ ሚስ ጥር በዳበረው ክህሎቷ ፖለቲካ ቀመስ ጥበብ ተቀኝታ ፣ አለያ ም ደርሳ አሳይታን አይደለም። ጋዜጠኞች ሀሞት አጥተን መ ጠየቅ ያልቻለነውን አስተያየትና ጥያቄ አርቲስት አስቴር በዳኔ በመጠየቋ እንጅ  !  …ቦታው ህወሃት የተመሰረተበትን 40ኛ ዓመት የተከበረበት ደደቢት ነው ። አስቴር በዚያ ቦታ በአብዛኛ ው ነዋሪ አዕምሮ የሚላወስ ጥያቄ  ” …አዲስ ታሪክ አዲስ አስተሳሰብ በዲሞክራሲያዊ ምርጫ ተለውጦ እናያለን? እናን ተስ በምርጫ ትወርዱ ይሆን? ”  አለቻቸው  የአባይ በዳኔ ልጅ በድፍረት ፊቷን ክችም አድርጋ  … አብረዋት የተጓዙት ጓደኞቿ በአብዛኛው ህወሃትን ሲያወድሱና ሲያሞካሹት አስቴ ር በታላላቅ የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት መካከል በተደረ ገ ውይይት ፈርጠም ብላ ለጀኔራል ሳሞራ ያቀረበችው ያልተ ጠበቀ ጥያቄ የተወደደ  ፣ የተወደሰበት ሚስጥሩ  አርቲስት አስቴር በዳኔ ስለተናገረችው ሳይሆን ጥያቄው የህዝብ በመሆኑ ነው  !
የነዋሪውን ቀልብ የሳበው የአርቲስት አስቴር በዳኔ ጠንካራ፣ ሞጋች አስየያየትና ጥያቄ ትዝ አለኝ  …እንዲህ ነበር ያለችው አስቴር ” ዛሬ ባልናገረው የሚቆጨኝ የተከፈለው መስዋዕትነት እጅግ በጣም ከባድ እንደ ነበር ግልጽ ነው፡፡ በጆሮ ስሰማው ደርግ ተደምስሶ ታጋይ እንዲህ ሆኖ ሲባል ከሁለቱም ወገን የተሰዉት በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው፡፡ የሞቱት፣ እግራቸው የተቆረጠ፣ ዓይናቸው የጠፋ ስላሉ ለሁለቱም ‹ጠላት› የሚለው ቃል ተገቢ አይመስለኝም፡፡ የወንድማማቾች ደም በመፍሰሱ ቤተሰቦቻቸው ዘንድ ሄደን ስናይ ልብ የሚሰብር ነው፡፡ ነገር ግን ይህ የጦርነትና የትግል ታሪክ ዘመኑ የፈጠረው ነው፡፡ በወቅቱ መንግሥታዊ ለውጥ ለማምጣት የትጥቅ ትግሉ አማራጭ አልነበረውም፡፡ አሁንስ ? የትግሉ ዋና ሐሳብ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት በአገሪቱ ለማምጣት ነው፡፡ የመንግሥትም ሆነ የሥርዓት ለውጥ በጦርነት ሳይሆን በዲሞክራሲ እንዲሆን ነበር ያ ሁሉ ከባድ መስዋዕትነት የተከፈለው፡፡ አሁን ላይ ሲታሰብ የሚመጣው ግንቦት ላይ 24 ዓመት የሚሆነው ሥልጣን ላይ ያለው አንድ ፓርቲ ነው፡፡ ዲሞክራሲያዊ ለውጥ ላይ ልባችሁ ምን ይላል? ያኔ ለሥልጣን ሳይሆን ለሕዝብ ስትታገሉ በጦርነት ሳይሆን በዲሞክራሲ ለውጥ እንዲደረግ ነበር፡፡ አይለደም? በእርግጥ የድሮን አስተሳሰብ መናፈቅ አዲስ አስተሳሰብ ለመቀበል ይከብዳል፡፡ አሁን ዝም ብዬ ሳስበው ራሱ ተቃዋሚ የሚለው ቃል ራሱ ጥሩ አይደለም፡፡ ተፎካካሪ ቢባል፡፡ አዲስ አስተሳሰብና ፍልስፍና ያለው ተተኪ መሪ ሊፈጠር አይችልም የሚል አቋም ነው ያላችሁ? እውነት መናገር እውዳለሁ ምክንያቱም እግዚአብሔር ምስክሬ ነው፡፡ ‘So, next time’ ምን ያህል አዲስ ታሪክ አዲስ አስተሳሰብ በዲሞክራሲያዊ ምርጫ ተለውጦ እናያለን? እናንተስ በምርጫ ትወርዱ ይሆን? ” ብላ አጠየቀች አርቲስት አስቴር  ፣ መልስ ተሰጥቷል  ! የጀኔራል ሳሞራ መልስ ግን በአርቲስቷ ውስጥ ያለፈውን የብዙሃን ዜጎች ጥያቄ የመለሰ ነው ለማለት ይከብዳል  ! ግራን ነፈሰ ቀኝ የሀገሬው ጥያቄ ግን በባለጥበቧ በኩል ተላልፏል  !
ሃሳቡን በሳልና በሰላ ቋንቋ ፣ ፍልስፍና ባልተለየው አቀራ ረብ ከምስልና ከማራኪ አቀራረብ ጋር እያዋሃደ የጥበብ በረከት ከሚቸረን የጥበብ ሰዎች መካከል አንዱ የሆነው ገጣሚ ታገል ሰይፉ ነው ። ገጣሚ ታገል ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ህልፈትን ተከትሎ ” ተከፍሎን አለቀስን ” በሚል ባቀረበው በምስል የተቀነባበረ መታሰቢያን ጨምሮ ለኢህአዴ ግን መንግስት በሚሰጠው ድጋፍ ይታወቃል። ታገል ለፖርቲ ውና ለግለሰቡ የሰጠው ድጋፍ የግል አቋሙና መብቱ በመሆ ኑ በግል ባከብርለትም በብዙሃን ዘንድ ግን የገጣሚውን  ተወ ዳጅነቱን ሳይሸረሽርበት እንዳልቀረ መናገር ይቻላል ። ብዙ አድናቂዎቹ አኩርፈውታል ። እሱም ይህን ያጣው አይመስልም …
ገጣሚ ታገል ሰው በእሱ ላይ የሚሰነዝረው አሉታዊ አስተ ያየትን ግልጽ ለማድረግ  ምላሽ ለመስጠትና ግልጽ ለማድረግ ይመስላል ፣ ያን ሰሞን በኤፍ ኤም 97 እድል አገኘ ። በዚሁ ፕሮግራም ተጋብዞ ” ሰው እንዲያውቅልኝ እንዲረዳኝ የምፈል ገው ” በሚል አንድምታ ከዚህ ቀደም ባልለመድነው መንገድ በሃገራችን ፖለቲላ ምህዳር ዙሪያ የሚሰማ የሚታየውን  አዲ ስ ሃሳቡን ገልጦታል ። “ሰዎች የማይረዱት ነገር አለ። ” ሲል ደደቢት ተጋብዞ ስለመቅረቱ ፣ በዘመነ ኢህአዴግ ስለወረደው ስነ ጽሁፍና እየተሸረሸረ ስላለው የትውልድ ሞራል ዝቅጠት እንዲህ ሲል ተናገረ …”ሰዎች የማይረዱት ነገር አለ። ለምሳሌ ባለፈው የመቀሌ ጉዞ ላይ እኔ አልሄድኩም። አርቲስቶች ሲሄዱ ጥሪ ተደርጎልኛል። ነገር ግን የደደቢቱን ጉዞ ስላላመ ንኩበት ቀርቻለሁ። ስለማልፈልገው ማለት ነው። …ለነሱም የምለው ነው። በተለይ ባለፉት 15 አመታት ብዙ ነገር አልተሰ ራም። ለስነ ጽሁፍ የሚመች ግዜ አይደለም። ስነጽሁፍን ትኩረት አልሰጡትም። እያየን ነው። ግድቡ ሲገነባ ደስ ይላል። ቤት ሲሰራ ደስ ይላል። ነገር ግን የሞራል ሃብታችን እየወደቀ ነው። በደርግ ግዜ ለስነ ጽሁፍ ትኩረት ተሰጥቶት አድጓል። ብዙ ትላልቅ ደራሲዎቻችን በሳንሱር ዘመን ነው የወጡት። እንደ እነ ጸጋዬ ገብረመኅን፣ እነ በአሉ ግርማ… አሁን ግን እንደነዚያ አይነት ትላልቅ ሰዎች አልወጡም። ምክ ንያቱም ለስነ ጽሁፍ ትኩረት አልተሰጠም። ይህ መንግስ ትን ዋጋ ያስከፍለዋል። እንዲያውም ጠቅላይ ሚንስትሩ የሞቱ ግዜ ለሳቸው የተሰማኝን ሃዘን የሚገልጽ ግጥም አቅርቤ ነበር። እና ከዝግጅቴ በኋላ አንድ ጋዜጠኛ ‘ጠቅላይ ሚንስ ትሩ ለኪነ ጥበቡ ማደግ ምን አድርገዋል?’ ሲለኝ ‘ምን ም’ ነበ ር ያልኩት። እርግጥ ይህ ያልኩትን ቆርጠው አውጥተው ታል ።…እናም ወደ ትግራይ ለጉብኝት ሲሄዱ ስላላ መንኩበት እኔ አልሄኩም። በሁለተኛ ደረጃ የግል አቋም አለኝ። ለምሳሌ በደር ግ እና ኢህአዴግ’ መካከል የተካሄደው ጦርነት የሁለት ወንድ ማማቾች ጸብ ነው። እዛ ጸብ ውስጥ አንዱን በሌላው ላይ ጀግና ማለት እምነቴ አይደለም። ለኔ የመንግስት ጀግንነት የሚጀምረው ጦርነቱን ጨርሶ አዲስ አበባ ከገባ በኋላ ባሳያ ቸው ለውጦች ነው የምለካው። እንጂ እዛ ጋር ገዳይም ወንድሜ ነው፤ ሟችም ወንድሜ ነው። አንዱን በአንዱ ላይ ጀግና ለማለት እዚያ አልሄድም። አስፈላጊም አልነበረም። አሁን እኔ እንደዚህ አይነት አቋም አለኝ። ሆኖም አንዳንድ ድረ ገጾች ላይ ስታይ፤ (ለአባይ ግድብ ያቀረበውን ግጥም አይተ ው፤ ሰዎች ”ባንዳ ባንዳ’ ብለው የሰደቡትን በማስታወስ ይመስላል… የንዴት ትንፋሽ አስማ) የአባይ ጉዳይ ሲሆን በዚህ ሁሉ ልዩነት መሃል አገሪቱን ዲያብሎስም ቢመራት የአባይን መገደብ እደግፈዋለሁ። ብዙ ሰዎች ይህንን በደንብ አይረዱትም። ….ወደኋላ ሄደህ ብትመለከት ወንድሙን ገድሎ ስለመጣው ኢህአዴግ ጀግንነት ጽፌ አላውቅም ።…ከመንግ ስት ጋር ብዙ ደስ የማይሉኝ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ።አባይ ሲባል ግን… ይህ የአገር ጉዳይ ነው። …ማንም የፈለገውን ትርጉም ቢሰጠው ይህ ለዘመናት አያት ቅድማያቶቻችን እንዲሆን ሲመኙት የነበረው ነገር ነው። ስለዚህ አባይን በተመለከተ ሰዎች በዚህ በኩል ቢረዱኝ ደስ ይለኛል፤ ለማለት ነው።” ሲል ደመደመ !  የገጣሚ ታገልም ድምጽ ለመጻኢዋ ክብርት ሀገር መልካምን የማሰብ የመቆርቆርና አዙራችሁ እዩነየሚል መልዕክት ያያዘ የህዝብ ድምጽ ነው  !
ዛሬ ከቀትር በኋላ ተሰይሞ በአንድነት ፖርቲ የውስጥ ጉዳይ ፍርደ ገምድል የሰጠው የምርጫና የምርጫ ኮሚሽኑ ነገር  አስገርሞኝ አመሸ። ከህዝብ ውስጥ የህዝብ ሆነው ስለህዝብ መብት ፣ ለሰላማዊ ውሎ አዳር ፣ ስለምንጓዝበት አደገኛ መንገድና ስለመጭው የእኛ ጉዞ አሳስቧቸው መንቀ ሳቀስ የጀመሩት ጥበበኞች ድምጽ የህዝቡን ድምጽ ነውና ሰሚ ያስፈልገዋል ። ጥበበኞች እንደ ቀድሞው ” ሊቀ መኳስ ” አዟዙረው ሳይሆን በቀጥታ የህዝቡን ሮሮ ማስተጋባት መጀ መራቸው የለውጥ ፈላጊውን ቁጥር መበራከት መግነን እኛ እንዳየነው ፖለቲከኛ ገዥዎቻችን ካሳያቸው መልካም ነው!  ይህ ካልሆነ አደጋ አለው  !
እየሆነ ያለው ቢያስደምመኝ ዝም አልኩና የአርቲስት አስቴርን ጥያቄ ደጋገኝኩና ጠየቅኩ ” ምን ያህል አዲስ ታሪክ አዲስ አስተሳሰብ በዲሞክራሲ ያዊ ምርጫ ተለውጦ እናያለን? እናንተስ በምርጫ ትወርዱ ይሆን? ” ብየ የአስቴርን ጥያቄ ላጠይቅ ግድ አለኝ ! አዎ እናንተስ በምርጫ ትወርዱ ይሆን? ” አልኩ የዛሬውን የምርጫ ቦርድን በአንድ ፖለቲካ ፖርቲ ላይ የወሰደውን ቅጥ ያጣ  እርምጃ  መግለጫ ቢያስደምመኝ  … !
እስኪ ቸር ያሰማን  !
ጥር 21 ቀን 2007 ዓም

fredag 23. januar 2015

በስዊድን የኢትዮጵያ አምባሳደር በተቃዎሟቸው ኢትዮጰያውያን ላይ የመሰረቱትን ክስ የስዊድን ፖሊስ ውድቅ አደረገው።

ቀደም ሲል የኢህአዴግ መንግስት ፤ በስዊድን-ስቶኮሆልም  አዘጋጅቶት የነበረው የቦንድ ሽያጭ ዝግጅት ላይ ኢትዮጰያውያን ከፍተኛ ተቃውሞ ማሰማታቸው ይታወቃል።
<<ከአባይ በፊት ዘረኝነት ይገደብ>> በሚል መርህ ተቃውሞውን ያደረጉት ኢትዮጰያውያን፤  ዜጎች ያለፍርድ እየታሰሩና እየተገደሉ ባለበት ሁኔታ  ገንዘብ ለመሰብሰብ መሯሯጥ፤ በሀገርና በህዝብ ላይ መቀለድ እንደሆነ በመናገር  ነበር- ተቃውሟቸውን  ጫማና እንቁላል በመወርወር የገለጹት።
ኢትዮጰያውያኑ -አምባሳደሯን መኪና ላይ የ እንቁላል መዓት በመወርወር ተቃውሟቸውን ሲገልጹ፤አምባሳደር ወይንሽት ከመኪናቸው መውጣት ተስኗቸው ተስተውለዋል። በኦትዮጰያውያኑ ጫማና እንቁላል የተወረወረባቸው በስዊድን የኢትዮጰያ አምባሳደር ወይንሸት ታደሰ፤ <<ስራዬን መስራት እስከማልችል ድረስ በደል ደርሶብኛል>> በማለት  ለስዊድን ፖሊስ ክስ ይመሰርታሉ።
የአምባሰደሯን ክስ ተከትሎ የስዊድን ፖሊስ  ባቀረበላቸው ጥሪ መሰረት ቃል ለመስጠት የሄዱት የኢትዮ-ስዊድን ግብረ-ሀይል አስተባባሪ አክቲቪስት መቅደስ ወርቁ እና የኢትዮጰያ ዲሞክራቲክ መድረክ ምክትል ሊቀ-መንበር አቶ ሞላ፤ ኢትዮጰያ ውስጥ ስላለው የመብት ረገጣና በስፋት ለስዊድን ፖሊስ በማብራራት፤ ተቃውሞው የተደረገው የሰብዓዊ መብት ጥሰትን፣ዘረኝነትን እና ሙስናን ለመቃወም እንደሆነ አስረድተዋል።
ጉዳዩን የተመለከተው የስዊድን ፖሊስም በስዊድን ህግ መሰረት የዚህ ዓይነት ተቃውሞ ማድረግ መብት እንጂ ወንጀል እንዳልሆነ በመጥቀስ እና ክሱ ውደ ፍርድ ቤት የሚያመራበት አንዳችም የህግ ምክንያት እንደሌለ በማብራራት የአምባሰደሯን ክስ ውድቅ እንዳደረገው አክቲቪስት መቅደስ ተናግረዋል። የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን ከወራት በፊት በዋሽንግተን ዲሲ የልብስ መደብር ውስጥተቃውሞ ባቀረቡባቸው አክቲቪስቶች ላይ የመሰረቱት ክስ ሰሞኑን በአሜሪካ ፍርድ ቤት ውድቅ መደረጉ ይታወቃል።

torsdag 22. januar 2015

የጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ የልደት በአል አገር ቤት በድምቀት ተከበረ (ርእዮት ለልደት ቀኗ ከእስር ቤት የላከችውን ደብዳቤ ይዘናል)

በውጭው አለም የታዋቂ ታጋዮችን የልደት በአል በማክበር አላማቸውን ህያው ማድረግ የተለመደ ነው። ኔልሰን ማንዴላ በእስር ላይ በነበሩበት ወቅት የልደት በአላቸውን በማክበር፤ አላማቸው ሁሌም በተከታዮቻቸው ህሊና ውስጥ እንዲቆይ ሲደረግ ነበር። ከሞቱም በኋላ ቢሆን ይኸው የልደት ማክበር ስርአት እንደቀጠለ ነው። በአሜሪካ ደግሞ መስሪያ ቤቶች እና ት/ቤት ጭምር ተዘግተው የጥቁሩ ታጋይ ማርቲን ሉተር ኪንግ የልደት በአል በየአመቱ በድምቀት ሲከበር እናያለን። በዚህም የልደት በአል አጋጣሚ… ማርቲን ሉተር ኪንግ የቆመለት የሰላማዊ ትግል አላማ ይዘከራል። ይህ አይነቱ መልካም ባህል ወደ ኢትዮጵያ ተሸጋግሮ የጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ የልደት በአል በየአመቱ በመከበር ላይ ነው።
በዚህ አመት የርዕዮት አለሙ የልደት ቀን ከመድረሱ በፊት በውጭ አገር በሚገኙ ደጋፊዎች ጭምር ነው መከበር የጀመረው። በአትላንታ የሚገኘው ማህደረ አንድነት የተባለው፤ አንጋፋ የሬድዮ ጣቢያ የርዕዮት አለሙን የልደት በአል ባለፈው የእሁድ ፕሮግራሙ ሰፊ የአየር ሽፋን ሰጥቶ ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ እንድትታወስ አድርጓል።
00:53
43:41

እሮብ ‘ለት የር ዕዮት አለሙ ልደት ሲከበር፤ በርካታ የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ተገኝተው ነበር። የመድረክ፣ የአንድነት፣ የሰማያዊ ፓርቲ መሪዎች ተገኝተዋል። እንደፕሮፌሰር መስፍን እና ዶ/ር ያዕቆብ አይነት ታዋቂ ሰዎች በልደት በአሏ ላይ ሲገኙ ልዩነታቸውን ወደጎን አድርገው ነበር። የልደት በአሏ ከተከበረ በኋላ ፍቅረኛዋ ጋዜጠኛ ስለሺ ሃጎስ እንደገለጸው ከሆነ፤ “ሁሉም ሰው ተገኝቶ ነበር።” በማለት ስሜቱን እንዲህ በማለት ነበር የገለጸው።
ልደቷን ሰብሰብ ብለን አክብረናል፡፡ የቀረ ሰው የለም፡፡ ቤተሰቦቿ፣ ጓደኞቿ፣ ጋዜጠኞች፣ አክቲቪስቶች፣ ፖለቲከኞች… ማንም አልቀረም፡፡ “ደስ ይል ነበር” የማልለው ርዕዮት ስላልነበረች ብቻ ነው፡፡ የልደት በዓሉ ሲከበር ርዕዮት በዚህ ሰዐት ምን እያሰበች ይሆን? በሚል ጥያቄ ስናጥ ነበር፡፡ አሁንም መልስ ባላኘሁላቸው በርካታ ጥያቄዎች እየተናጥኩ ነው፡፡ ለርዕዮት መስዋዕትነት እውቅና ለመስጠት የሚፈቅዱ ሰዎች ቁጥራቸው ብዙ ነው፡፡ ታዲያ ርዕዮት ይሄ ሁሉ ሰው እያላት ለምን ትሰቃያለች? ለምን እኛ እያለን የርዕዮትና የመሰሎቿ የመከራ ቀን ይረዝማል? እኛስ ተራበተራ እየተለቀምን መከራችንን የምናየው ለምንድነው? ለምን አንድ አልሆንም? ለምን? ለምን? ለምን? ለምን?… ጥያቄ ብቻ፤ መልስ የለም፡፡
በዚህ የልደት አከባበር ወቅት ርዕዮት አለሙ ከቃሊቲ እስር ቤት በጽሁፍ ያስተላለፈችው መልእክት በንባብ ተሰምቷል።  ይህንኑ ጽሁፍ ከዚህ በመቀጠል አቅርበነዋል።
ጥር 13/2007 ዓ.ም
==============================
በቅድሚያ የልደት በዓሌን ለማክበር እዚህ የተሰባሰባችሁትንና እዚህ ባትገኙም አላማዬን በመደገፍ ፍቅርና ከብር የሰጣችሁኝን ወገኖች ሁሉ ላመሰግን እወዳለሁ፡፡
በመቀጠል እኛም ራሳችን ሆንን ሌሎች ኢትዮጵያዉያን እንደሰዉ መኖር የሚችሉባትን ሀገር ለመፍጠር በየሙያ ዘርፎቻችሁ፣ በፓርቲ ተደራጅታችሁም ሆነ በሌላ በማንኛዉም መንገድ እየታገላችሁ ላላችሁ በሀገር ዉስጥና በዉጭ የምትኖሩ የማከብራችሁ ወገኖች በሙሉ ሶስት ዋና ነጥቦችን የያዘ አጭር መልዕክት ላስተላልፍላችሁ ፈልጋለሁ፡፡
ጊዜዉ የምንታገለው ስርአት ከመቼዉም በበለጠ ሁኔታ አምባገነንነቱ የበረታበት ወቅት እንደመሆኑ ከባድ የስራና የመስዕዋትነት ዘመን ከፊታችን እንደሚጠብቀን ግልፅ ነው፡፡ ተግባራዊነቱ ላይ ድክመት ቢኖርብንም ስራችንን ለማቅለልም ሆነ መስዕዋትነቱን ቀንሶ ባልረዘመ ጊዜ ዉስጥ ለድል ለመብቃት አንድነት ቁልፍ መሆኑን እኔን እናንተም አናጣዉም፡፡ የአንድነትን ተገቢነትና ጠቃሚነት እስካመንበት ጊዜ ድረስ ቆም ብለን ድክመቶቻችንን በመገምገም እና በተቻለ መጠን አላስፈላጊ ልዩነቶችን በማጥበብ ትግሉ የሚጠይቀውን ማንኛዉንም አይነት ህብረት ልንፈጥር ይገባል እስኪ አስቡበት፡፡
በተለያዩ እስር ቤቶች ዉስጥ የሚገኙ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎችና አባላት፣ የሃይማኖታቸዉን ነፃነት ለማስከበር የቆረጡ የእስልምና ሃይማኖት መሪዎችና ተከታዮች፣ የሀገርና የወገን ጉዳይ ያገባናል ያሉ በተለያዩ የትምህርትና የስራ መስኮች ላይ ተሰማርተዉ የነበሩ ግለሰቦች፣ እነዚህና የመሳሰሉትን እስረኞች ስታስቡ ምን ይሰማችኋል? ሁሉም በአንድ ወይም በሌላ መንገድ ለሀገራችን ብሩህ ቀን ለማምጣት ወይም እንደሰዉ መብታቸው ተከብሮ ለመኖር ሲ,ታትሩ የነበሩ ግን በተለያየ ስም ተጠርተው ወደ እስር ቤት የተወረወሩ የኢትዮጵያችን ምርጥ ልጆች መሆናቸዉ እነደሚሰማችሁ አልጠራጠርም፡፡ እኔም የሚሰማኝ እንዲሁ ነው፡፡ ታዲያ እንዲህ በተሰማኝ ቁጥር እቆጫለሁ፡፡
የሁላችንም አላማ ተመሳሳይ ወይም ተቀራራቢ ቢሆንም ተነሳሽነቱን ወስደን ወደ አንድነት ለመምጣት ባለመሞከራችን ወይም በሙከራችን ባለመግፋታችን ምክንያት መከራችንንም ሆነ የድሉን ቀን እንዳራዘምን መረዳቴ የቁጭቴ ምክንያት ነው፡፡ በመሆኑም እድሉ በእጃችሁ ያለ እናንተ ከእንዲህ አይነቱ ቁጭት ትድኑ ዘንድ ይህን አምባገነን ስርዐት ከልባቸዉ የሚቃወሙትን ሁሉ በሆነ መንገድ ወደ አንድነት ለማምጣት የሚቻላችሁን ሁሉ እንድታደርጉ አበረታታችኋለሁ፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር እንኳን ቢያንስ ቢያንስ አንዳችሁ ስለሌላችሁ አሉታዊ አስተያየት ከመስጠት መቆጠብ ግን ይኖርባችኋል፡፡
ስለ አንድነት ይህችን ያህል ካልኩ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ተገቢ የሆነ የትግል ስልትና አይነት ስለመጠቀም ጥቂት ለመተንፈስ ወደድኩ፡፡ ኔልሰን ማንዴላ Long walk to freedom በተሰኘ ግለ ታሪካቸዉ ላይ እንዳሰፈሩት የትግሉን ስልት የሚወስነዉ ጨቋኙ ነው፡፡ እኔም በዚህ አምናለሁ፡፡ አንድ ሰዉ ለሰደበዉ ሰውና ለተኮሰበት አንድ አይነት የአፀፋ ምላሽ የሚሰጥ ከሆነ ጤነኛነቱ ያጠራጥራል፡፡ አንድ ጤነኛ ሰዉ ለሁለቱም የሚሰጠው የአፀፋ ምላሽ የተለያየና ለድርጊታቸዉ የሚመጥን እንደሚሆን ይገመታል፡፡ በሌላ አነጋገር የተበዳዩን ሰዉዬ ምላሽ የወሰነው በዳዩ ነው ማለት ነው፡፡ እኛስ ምን እያደርግን ነው ያለው? መረጥነው የትግል ስልት የምንታገለውን አካል ለማሸነፍ የሚያዋጣ ነዉን? የሚያዋጣ ከሆነስ በሚገባ ተጠቅመንበታል? እነዚህንና የመሳሰሉት ጥያቄዎች መጠያየቅና በቂ ምላሽ ማዘጋጀት ይኖርብናል፡፡ አሁን እየተሸከረከርንበት ካለሁ ክብም መዉጣት አለብን “የቱ ክብ?” ካላችሁኝ መልሴ እነሆ!
ምርጫ በደረሰ ቁጥር ገዢዉ ፓርቲ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና አባሎች እንዲሁም የግሉን ፕሬስ ጋዜጠኞች ያስራል፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲዎቹ በቂ ቅስቀሳ እንዳያደርጉ የሚችለዉን ሁሉ ይፈፅማል፡፡ የግል የህትመት ዉጤቶችን ይዘጋል፡፡ በዚህ ሁሉ መሀል ምርጫዉ ይደረጋል፡፡ ገዢዉ ፓርቲ ድምጽ ያጭበረብራል፡፡ ምርጫዉ ተጭበርብሯል የሚሉ ወገኖች ካሉ ከመታሰር አንስቶ እስከመገደል ድረስ እርምጃ ይወሰድባቸዋል፡፡ ይህ እንዳይሆን ከተፈለገ ደግሞ ተቃዋሚ ፓርቲዎች “አሸንፋችኋል” የተባሉትን መቀመጫ በጸጋ ተቀብለዉ እስከሚቀጥለው አምስት አመት ድረስ ያደፍጣሉ፡፡
ታዋቂዉ ሳይንቲስት አልበርት አንስታይን “አንድ ነገር በተመሳሳይ መልኩ እያደረጉ የተለየ ዉጤት መጠበቅ ሞኝነት ነው” አለ ተብሎ የለ? እስካሁን የተሞኘነዉ ከበቂ በላይ በመሆኑ አካሄዳችንን ቆም ብለን ማየትና የትግል ስልቶቻችንን መፈተሸ ይኖርብናል፡፡ እንዲህ ማድረግ ካልተቻለ ግን ህዝቡ አካሄዳችን የትም እንደማይደርስ ይሰማዉና በትግሉ ዉጤታማነት ተስፋ ይቆርጣል፡፡ እንዲህ እንዲህ እያለ ተስፋ መቁረጡ ወደ ግሉ ፕሬስ አባላት፣ ወደ ተቃዋሚ ፓርቲ አባሎችና አመራሮች ጭምር እየተጋባ አንገት ደፍቶ መገዛት ይከተላል፡፡ ያቀን ከመምጣቱ በፊት የህዝቡን ተጠቃሚነትና ደህንነት ማዕከል ያደረጉ ነገር ግን አዋጪ ሊሆኑ የሚችሉ የመታገያ መንገዶችን በሙሉ መፈተሸና እንዳስፈላጊነቱ መጠቀም አማራጭ የሌለው መፍትሄ እንደሆነ ይሰማኛል ፡፡
በሶስተኛነት ልጠቅሰዉ የምፈልገዉ ጉዳይ ፅናት ነው፡፡ ፅናት የያዝነዉን አላማ ከዳር ለማድረስም ሆነ ለራሳችን የስነልቦና ደህንነት የሚጠቅመን ድንቅ ሀብት በመሆኑ አጥብቀን ልንይዘዉ ይገባናል፡፡ ላመንበት ነገር መቆም፣ ለሱው መኖርና ለሱው መሞት! ወደ ድል መድረሻ መንገዱ ሲረዝምባቸዉ ወይም አላዋጣ ሲላቸዉ አላማቸዉን የሚተዉ ወይም የሚቀይሩ ሰዎች አልገጠሟችሁም? ከእነሱ ስህተት ተምራችሁ አካሄዳችሁ ወደተስፋ መዉረጥ ሳይወስዳችሁ በፊት አስተካክሉት፡፡ አላማችሁን ግን በፅናት አጥብቃችሁ ያዙት፡፡ ከመጀመሪያው በያዝነዉ አላማ ምክንያት የሚደርስብንን ሁሉ ለመቀበል አስቦ መንቀሳቀስ እንጂ መከራ ሲመጣ “ጎመን በጤና” ብሎ ማፈግፈግም ተገቢ አይደለም፡፡ በመሆኑም የጀመርነውን ጉዞ በስኬት ለማጠናቀቅ ከፈለግን ፅናት ሊለየን እንደማይገባ እያስታወስኩ እሰናበታችኋለሁ፡፡ እወዳችኋለሁ፡፡
ርዕዮት አለሙ
ከቃሊቲ እስርቤት
ጥር 13/2007ዓ.ም

በምርጫ ቦርድና በአንድነት ፓርቲ መካከል የተፈጠረው ውዝግብ የመጨረሻው ጫፍ ላይ ደርሷል ። ፓርቲው -ጥር 17 ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ነው

ምርጫ ቦርድ የውስጥ ጠቅላላ ጉባዔ ጠርታችሁ የውስጥ ችግራችሁን ካልፈታችሁ በመጪው ምርጫ አትሳተፉም የሚል  ውሳኔ በ አንድነትና በመ ኢአድ ፓርቲዎች ላይ ማሳለፉን ተከትሎ አንድነት ፓርቲ  የቦርዱን ውሳኔ ለማሟላት ከሳምንት በፊት  በአስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ  ማካሄዱ ይታወሳል።
 ይሁንና በወቅቱ ድርጅቱ  በጠራው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ተጋብዞ  ተወካዩን ለመላክ ፈቃደኛ ያልሆነው ምርጫ ቦርድ፤ ፓርቲው በአቋም ተለይተው  ካፈነገጡ ጥቂት የቀድሞ አባላቱ ጋር ተስማምቶ ዳግም የጠቅላላ ጉባዔ እንዲያደርግ  በደብዳቤ ትእዛዝ አስተላልፏል።
ባለፈው ቅዳሜ የተሰበሰበው የአንድነት ብሄራዊ ምክር ቤትም፤ ምርጫ ቦርድ በፃፈው ድብዳቤ ከተወያየ በኋላ ደብዳቤው ህገወጥ ነው ሲል አወግዟል።
ምርጫ ቦርድ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ በተካሄደ ማግስት ሌላ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሩ ማለቱንና  ጉባ ዔው ሲጠራ ደግሞ አልታዘብም ማለቱን  ያስታወሱት የጠቅላላ ጉባኤው አባላት፤ አሁን ደግሞ  ለሶስተኛ ጊዜ ሌላ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሩ ማለቱ ህገወጥ ተግባር ነው >> በማለት  የቦርዱን አሰራር በ አንድ ድምጽ ኮንነዋል። ተሰብሳቢዎቹ አክለውም፦<< ከእንግዲህ ጠቅላላ ጉባኤ አንጠራም!   ከእንግዲህ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት እና ወደ ህዝቡ ነው የምንወስደው!>> በማለት ወስነዋል።
የአንድነት ፓርቲ  ስራ አስፈፃሚ በምርጫ ቦርድ እና በስርዓቱ የተደቀነበትን የማፍረስ ዘመቻ ለመመከት ግብረ ኃይል ማቋቋሙን የገለጸው ፓርቲው፤ ምርጫ ቦርድና ኢህአዴግ ፓርቲውን ለማስረስ የሚያደርጉትን በመቃወም  ለጥር 17 ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድርግ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ አስታውቋል።
የአንድነት አባለት፣ ደጋፊዎች በጠቅላላ በኢትዮጵያ የስርዓት ለውጥ እንዲመጣ የምንፈልግ ሁሉ በዚህ በአጭር ጊዜ ሰልፎቹ የተሳኩ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ርብርብ ያደርጉ ዘንድ ሀገራዊ ጥሪ አቅርቧል።
 <<በምንም ዓይነት ሁኔታ አንድነት -ለምርጫ ቦርድ ህገወጥ ተግባራት አይምበረከክም>> ያለው ፓርቲው፤  << ፓርቲያችን በምርጫው ይሳተፍም ፤አይሳተፍም፤የምፅዓት ቀን ቀርበዋልና ለንሰሀ ተዘጋጁ እንዲል መፅሐፉ –   ህዝቡን ጫፍ እስከ ጫፍ የማደራጀቱን ስራ ግን ጠንክሮ እንደሚቀጥልበት የማያወላውል ውሳኔ  ማሳለፉን አስታውቀል።
ህዝባዊ ትግሉን ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማሸጋገር ያለውን ታሪካዊ ሃላፊነት ለመወጣት ከመቸውም ጊዜ በላይ ዝግጁ መሆኑን ያሳወቀው አንድነት ፓርቲ፤  አባላቱ፤ ደጋፊዎቹና ህዝቡ አመራሩ ለሚያሳልፈው ውሳኔና እንቅስቃሴ በተጠንቀቅ እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርቧል።
ይህ በ እንዲህ እንዳለ ራዲዮ ፋና-ከምርጫ ቦርድ ጋር በመተባበር ዛሬ በሸራተን አዲስ ላሊበላ አዳራሽ ባዘጋጀው ኮንፈረንስ ተጋባዥ ከነበሩት ፓርቲዎች መካከል የአንድነት ፓርቲ ወኪል የነበሩት አቶ አስራትወ ጣሴ መድረኩን ጥለው ወጥተዋል።
ሚኒስትሮችና ከፍተኛ ባለስልጣናት በታደሙበት በዚህ ያዲዮ ፋና መድረክ የውይይት መነሻ ጽሁፍ ያቀረቡት ኢህ አዴግ፣ምርጫ ቦርድ፣ ኢዴፓ እና መድረክ ናቸው።
የአንድነቱ ተወካይ አቶ አስራት መድረኩን ጥለው የወጡት  ጽሁፎቹ ከቀረቡ በሁዋላ ለመናገር ሲዘጋጁ በመድረኩ መሪ በራዲዮ ፋናው ምክትል ስረታ አስኪያጅ በብሩክ ከበደ አማካይነት የተሰጣቸው 3 ደቂቃ ብቻ ነው በመባሉ፣ እንዲሁም ከአንድነት ከተለዩት ጥቂት ሰዎች መካከል አቶ ትእግስቱ የሚባሉት የቀድሞው የፓርቲው አመራር  የ አንድነት ፕሬዚዳንት በሚል ፕሮቶኮል በኮንፈረንሱ እንዲታደሙ በመደረጋቸው ነው።
አንድነት አንድ እንጂ ሁለት ፕሬዚዳንት የለውም ያሉት አቶ አስራት፤ ገዥው ፓርቲ አንድነትን ይበልጥ ውዝግብ ውስጥ ለማስገባትና ለማፍረስ ባሴረበት መድረክ መሳተፍ ፓርቲያቸውን የሚጠቅም ሆኖ እንዳላገኙት ተናግረዋል።  ከአቶ አስራት ጋር ያደረግነውን አጠር ያለ ቃለ ምልልስ በልዩ ፕሮግራም የምናቀርብ መሆኑን እናሳውቃለን

tirsdag 20. januar 2015

ኢትዮጰያ ውስጥ ያለው ችግር የዘር ፉክክር ነው>>ሲሉ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ተናገሩ።

ፕሮፌሰር መስፍን ይህን ያሉት ሰማያዊ ፓርቱ እና በሰሜን አሜሪካ የሰማያዊ ፓርቲ ድጋፍ ኮሚቴ በመተባበር ያዘጋጁትን ውይይት ሲከፍቱ ነው።
<<ሁላችንም ስንለወጥ ነው ለውጥ የሚመጣው ያሉት ፕሮፌሰር መስፍን፤ ከጣሊያን ጊዜ አንስቶ አሁን እስካለንበት ጊዜ ድረስ ባንዳው፣ፖሊሱ፣ባለስልጣኑ ሁሉ በመሸጦነት ማለፋቸውን በማውሳት፤ አንድ ትውልድ ይህን የመሸጦነት ባህል እየተባበረ ከሄደ ለውጥ እንደማይመጣ በአንጽንኦት ተናግረዋል።

ተከታዩ ተናጋሪ ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ ደግሞ፦‹ለህወሓቶች ፖለቲካ ማለት ወዳጅና ጠላት የሚለይበትና ፍልሚያ የሚደረግበት ነው ፡፡ አንድ የናዚ ሰውም ፦<<ፖለቲካ ማለት ወዳጅና ጠላት የሚለይበት ሜዳ ነው>> ነው የሚለው፡፡>>ብለዋል።
<<ህወሀቶች ያለ ጠላት መንቀሳቀስ አይችሉም፡፡>>ያሉት ዶክተር ዳኛቸው፤ <<ድህነትንም ጠላት ብለውታል፡፡

ሲጀመር እኛ እና እነሱ ይባልና- ጠላትና ወዳጅ ወደሚለው ያድጋል፡፡›› ብለዋል። ሁላችንም በሀገራችን የባለቤትነት መብት ቢገባንም የሀገሪቱ ፖለቲካ ዝግ ሆኗል ያሉት ዶክተር ዳኛቸው፤ <<ውድድር በሌለበት ቦታ ፍትሐዊ ምርጫ ማድረግ እንደማይቻል ገልፀዋል።
የአዲሲቷ ኢትዮጰያ የጋራ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ኦባንግ ሜቶ በበኩላቸው፤ <<በጎሳና በዘር ተከፋፈግለናል፤ ሀገራችንን ለመቀየር ከፈለግን ለውጡ ከራሳችን መጀመር አለበት ብለዋል።

<<እኛ ለሀገራችን ዋጋ ካልከፈልን፤ማንም ለኢትዮጰያ ዋጋ ሊከፍልልን አይችልም>>ብለዋል-አቶ ኦባንግ።
የዞን 9 ጦማርያን አባል የሆነችው ሶልያና ሽመልስ በበኩሏ ትንሽ የሚመስሉ ጥረቶችን ማድነቅ እንደሚያስፈልግ በመጥቀስ፤ ቀደም ሲል ጠቀሜታው ብዙም ግምት ያልተሰጠውንና በአሁኑ ወቅት ተጽእኖ እየፈጠረ ያለውን በኢንተርኔት መረጃ የመለዋወጥን  እና የመጻፍን ጉዳይ በተደራጀ መልኩ መጠቀም እንደሚያስፈልግ መክራለች።

በምርጫ 97 ወቅት የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ የተቋቋመው አጣሪ ኮሚቴ ሊቀ-መንበር የነበሩት ዳኛ ፍሬህይወት ሳሙኤል በበኩላቸው ኢትዮጰያ ውስጥ የህግ የበላይነት እንደሌለ ምሳሌዎችን በመጥቀስ ተናግረዋል።
ኢትዮጰያ ውስጥ ወደ እስር ቤት የተወረወሩት አንድም በፖለቲካ የተሳተፉ አለያም ድሆች ናቸው ያሉት ዳኛ ፍሬህይወት፤ “የሀብታም ክስ ከፖሊስ አልፎ ፍርድ ቤት አይደርስም>> ብለዋል።

“ለውጥ ይመጣል፡፡ ለውጥ ይሸተኛል”በማለት ንግግራቸውን የጀመሩት ደግሞ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ናቸው።

<< ለውጡ እንደስከዛሬው እንዳይከሽፍ ግን ፖለቲከኞችና የፖለቲካ ቡድኖችበራሳችን ላይ አብዮት ማምጣት አለብን፡፡>>ያሉት ኢንጂነር ይልቃል << ከእስካሁኑ የተለየ ለውጥ እንዲመጣ የኢትዮጵያ ህዝብ የስልጣን ባለቤት እንዲሆን ማድረግ አለብን›› ብለዋል።

ሰማያዊ ፓርቲ ያዘጋጀውን ይህን ውይይት በርካቶች  በአካል በስብሰባው ቦታ ተገኝተው ከተከታተሉት ታዳሚዎች ባሻገር በርካቶች ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች በስካይፒ የተከትሉት ሲሆን፤ ፓናሊስቶቹ ባቀረቧቸው ሀሳቦች ላይ ውይይት ተካሂዷል።

በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት ባለፉት ሁለት ዓመታት በእጅጉ ማሽቆልቆሉን <፣ያንግ ላይቭስ>> የተሰኘ ተቋም ይፋ አደረገ።




የፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት ልጅ በሆኑት  በዶክተር አሉላ ፓንክረስ የሚመራው  <፣ያንግ ላይቭስ>> ሰሞኑን ይፋ ባደረገው ጥናት  ኢትዮጵያ ውስጥ  የትምህርት ደረጃና ጥራት ከክልል-ክልል እንደሚለያይ ጠቁሟል።

ትምህርት ከጀመሩ ተማሪዎች መካከል  17 በመቶ ያህሉ በተለያዩ  ችግሮች እንደሚያቆሙ  ያመለከተው ጥናቱ፤ ከሚማሩት መካከልም 24 በመቶዎቹ  ወደተከታዩ ክፍል ማለፍ እየተሳናቸው እንደሚደግሙ  ይጠቁማል።

ዋና ጽህፈት ቤቱ በእንግሊዝ የሆነው<< ያንግ ላይቭስ>> የኢትዮጵያን  የትምህርት ጥራት አሰመልክቶ ያጠናውን  ይህን ጥናት ሰሞኑን  በአዲስ አበባ  ይፋ አድርጓል።

ባለፉት አመታት በኢትዮጵያ  የትምህርት ጥራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቀለ  እንደመጣ  በርካታ  ምሁራን  በተደጋጋሚ ሲናገሩ ቆይተዋል።

søndag 18. januar 2015

ትንሽ ልበል ዶር ቆስጠንጢኖስ በረሔ




መጀመሪያ ሀሰቱን ወደ እውነት ለአሰማን የኢዮያ ቁርጥ ልጅ አበበ ገላው ምስጋና እየቸርኩ::

ትንሽ ልበል ዶር ቆስጠንጢኖስ በረሔ በእውነቱ በጣም የሚሳዝን በባዶነት ሀገርን የመውረር አባዜ ሕወሀት ላይ ጥላውን ከጣለ  ይሓው  ሆነው ኢትዮጵያችን ከማጡ ወደ ጥዱ ካደርጋአት አንዱ ይሔ መሆኑ ነው ታድያ እንዴት ዘረኝነት አይነግስ ::

የባሕል የታሪክ የትውፊት መርዝ ወዘተ እረ ምኑ በፋሽስት ሕወሀት እየተደረገ ያለው ስሙን መፃፍ የማይችል ሁሉ ነው ዲግሪ ያገኘው በሕወሀት ዘመን ኢትዮጲያኖች ከገባቹ የሕወሐትን እድሜ ካረዘሙ ሰዎች መሀል የነዚ ሰዎች አሻራ አለ ።

 ባሪያ ለንጉሱ ልበለዉ ስለዚሕ ሁላችንም ወደቀድሞ ማንነታችን ለመመለስ ይሕንን ስረአት በቃ ልንለዉ ያገባል አልያ እንዳልኩት ከድጡ ወደ ማጡ ነው  እና ወገኔ እየኖርን ያለንው ሀገርን ለታሪክን ቋንቋን ለሀይማኖትን ወዘተ ምንም በማይመስላቸው ሰዎች አገራችን ወዴት እያመራች እንደሆነች መገመት አይከብድም ።

 እና ዋጋ ለመክፈል እምቢተኝነት በቂ ነው እላለው አንችም አንተም ሁላችንም በቃ እንበል፥ የሕዝብ እምቢተኝነት ዋጋ አለው። አበቃሁ

       by Emishaw

MPs seek release of British citizen on death row in Ethiopia

anuary 16, 2015 (LONDON) – A delegation of British parliamentarians will be in Ethiopia next month in an attempt to secure the release of a British citizen who is facing the death penalty in Ethiopia.
Andargachew Tsege, a British national who was born in Ethiopia, was the secretary-general of exiled Ethiopian opposition movement Ginbot 7, labelled by the Ethiopian government as terrorist entity in 2011.
Tsege was sentenced to death in absentia in 2009 on charges of planning to assassinate government officials and thereby to stage a coup, an allegation he denies.
He was arrested by Yemeni authorities at Sana’a airport on 23 June while he was in transit to Eritrea and was subsequently extradited to Ethiopia under a security arrangement Yemen has with Ethiopia.
The Independent newspaper, reported that the delegation of British legislators will be headed by Jeremy Corbyn, vice-chair of the All Party Parliamentary Group on Human Rights.
The UK government and prime minister David Cameron himself were criticised by Tsege’s family and right groups for not doing enough to secure his release.
“He is a British citizen so there is no reason on earth why the British government should not take a very robust view on this,” said Corbyn on Thursday while announcing the planned visit.
He added Tsege’s constituent is “a British national in prison with no understandable, comprehensible or acceptable legal process that’s put him there”.
Clive Stafford-Smith, director, Reprieve, who will accompany the MPs to Ethiopia, said: “I think Mr Cameron doesn’t understand how serious this is. I think that Tsege is going to be seen, as the years go by, as Ethiopia’s Nelson Mandela”
A spokesperson for the Ethiopian Embassy in London claimed that Mr Tsege belongs to a “terrorist organisation” seeking to “overthrow the legitimate government of Ethiopia.”
He is being “well treated” and “torture is inhumane and has no place in modern Ethiopia,” he added.
According to the Foreign Office, the British government is pressing authorities in Ethiopian not to carry out the death penalty.
Tsege, who recently appeared on the state-run Ethiopia Television, said he was working with neighbouring Eritrea, long standing Ethiopia’s foe, to destabilise the Horn of Africa nation.
He also confessed he has been recruiting and training people in Eritrea who will cross borders to carry out attacks in Ethiopian soil.
However, opposition sources cast doubts over the seriousness of such confessions, saying they were obtained using methods of torture.
Between 1998 and 2000, Eritrea and Ethiopia fought a two-year-long bloody border war in which over 70,000 people lost their lives.
The two neighbours regularly trade accusations of hosting and providing support to each other’s rebel groups.

lørdag 17. januar 2015

“ሉዓላዊነትና ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ” ዓብይ ጉዳይ! – ኣረጋዊ በርሄ


gebru-asrat-bookኣቶ ገብሩ ኣስራት ´ሉዓላዊነትና ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ´ በሚል ርእስ ትልቅ መፅሓፍ ፅፈዋል፤ ትልቅነቱ ሃገርን ያክል ዓብይ ስብስብ የሚንዱ ወይም የሚገነቡ ርእሰ ጉዳዮች – ማለት ሉዓላዊነትና ዲሞክራሲ- በኢትዮጵያችን የደረሱበትን ኣሳሳቢ ደረጃ ኣስመልክቶ እንድንመክርበት በጥልቀት መርምሮ ስላስቀመጠልን ነው። ከዚህም ኣልፎ ላሳሳቢው ችግር መፍትሄ ይሆናሉ ያላቸውን ኣንኳር ፍሬነገሮች ግልፅ ኣድርገዋል። ከዚህ በመነሳት ይህ ትላልቅ ርእሶችን ያነገበ መፅሓፍ እንዴት መታየት እንዳለበት፤ ግድፈቶቹን ሳልተው የበኩሌን ኣስተያየት ኣጠር ባለ መልኩ ለማከል እወዳለሁ።
መፅሓፉ በ6 ምዕራፎች የተከፈለ ሲሆን የመጀመርያ 2ቱ ምዕራፎች ሉዓላዊነትና ዲሞክራሲ ኣሁን ለደረሱበት ኣሳፋሪ ደረጃ ማገናዘብያና ታሪካዊ መንደርደርያ ሲሆኑ፣ የተቀሩት 4ቱ ደግሞ የሉዓላዊነትና ዲሞክራሲ መሸርሸር እንዴት እንደተከናወነና በኢትዮጵያ ማሕበረ-ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ይዘት ላይ ያስከተለው ኣሉታዊ ተፅእኖ ይተነትናሉ። በመጨረሻም የመፍትሄ ሓሳቦችን በመሰንዘር ያጠቃልላል።
ብዙዎቹ ጠበብት እንደሚስማሙት ሉዓላዊነት የኣንድን ሃገር መብትና ጥቅም ለማስከብር የሚያገለግል ከፍተኛው ሕጋዊ ስልጣን መጨበጥ ማለት ነው። ይህ ከፍተኛው ሕጋዊ ስልጣን ከሃገራችን እውነታ ኣኳያ ሲታይ በኣሁኑ ወቅት ምን ያህል እንደተሸረሸረና ያስከተለው ጉዳት በጥቅሉ ቢታወቅም በዝርዝር ማወቁና የደረሰው ጥፋት ይሽር ዘንድ፣ ብሎም እንዳይደገም የያንዳንዱ ዜጋ ተቀዳሚ ሓላፊነት በመሆኑ ይህ መፅሓፍ ለዚህ ሓላፊነት ንቁና ብቁ የማድረግ ተልእኮ ኣለው እላለሁ።
ይህንን ሃገራዊ መብትና ጥቅም ማስከብር የመንግስት ተቀዳሚ ሓላፊነት ቢሆንም፤ ከ24 ዓመታት በፊት ስልጣን የጨበጠው ህወሓት/ኢህኣዴግ መንግስታዊ ስልጣኑ የተገለገለበት ሂደት ሲመረመር፣ ጭራሽ በሚገርም ሁኔታ የህዝቡን መሰረታዊ መብቶች በመጨፍለቅና የሃገሪቱን ኣንጡራ ጥቅሞች ለዘራፊዎች ኣሳልፎ በመስጠት እንደነበረና እንደሆነ እነሆ ኣቶ ገብሩ ከርቀት ሳይሆን በሓላፊነት ተቀምጦ ከውስጥ እንደተገነዘበው ያረጋግጥልናል። ገብሩ ይህን የኣፈናና የክህደት ቅንብር ሲታገለው እንደቆየና ዋጋ እንደከፈለበትም ከመፅሓፉ ጋር ስንከንፍ እንገነዘባለን።  የሃገር ሉዓላዊነት ሲደፈር የሃገሬው ህዝብ መጎዳቱና መቃወሙ ነባራዊ ስለሆነ፣ ይህን ፍትሃዊ ተቃውሞ ለማዳፈን ሲባል ደግሞ ዲሞክራሲያዊ መብቶች መጨፍለቅ ኣብሮ የሚሄድ የስርዓቱ ዋነኛ ፖሊሲም ተግባርም እንደሆነ በራሱ ጭምር ከደረሱ በደሎች በመነሳት ያብራራልናል። ይኸው በግልፅ የተቀመጠውን ሃቅ ደግሞ በበቂ መረጃዎች ስለታጀበልን ለመገንዘብ ኣይከብድም፤ ለግላዊ ምክንያት ዓይንን ካልጨፈኑ ወይም ህሊናን ካልሸጡ በስተቀር።
በመጀመርያው ምዕራፍ እንደተቀመጠው በኣንድ በኩል የኢትዮጵያ ህዝብ ክብሩንና ዳር ድንበሩን ለማስከበር ከመሪዎቹ ጋር በመተባበር ባካሄደው መራራ ትግልና በከፈለው እጅግ ከባድ መስዋዕትነት የባዕዳን ወረራና ሴራ እንዳከሸፈና ሉዓላዊነቱን ኣስከብሮ እንደኖረ ሲታወቅ፤ በሌላው በኩል የመለስ ዜናዊና ግብረ ኣበሮቹ ሚና ደግሞ ያንን በኣያሌ መስዋዕትነት የተገነባው ሉዓላዊነትን ለመሸርሸር ብቻ ሳይሆን ኣሳልፎ ለመስጠትም እንደነበረና፣ ምን ያህልም አክርረው እንደተረባረቡበት በንፅፅር ያስረዳል። በዓለም ዙርያ ይሁን በሃገራችን ታሪክም እንደሚታወቀው ሁሉ፣ መሪዎች የሚታወቁበት ትልቁ ሚናቸው የሃገር ሉዓላዊነትን በመጠበቅና ዳር ድንበርን በማስከበርና ሲሆን የመለስ ሚና ደግሞ የተገላቢጦሽ፤ ሉዓላዊነትን ኣሳልፎ በመስጠት በመሆኑ ልዩ ከሃዲ መሪ ያደርገዋል።
በ2ኛው ምዕራፍ በዋናነት የምንረዳው መለስ ዜናዊና ግብረ ኣበሮቹ በትግሉ ወቅት ስውር ዓላማቸውን ለማሳካት የታጋይነት ካባ ለብሰው በማድፈጥ፣ ለህዝቦች መብትና ለሉዓላዊነት መከበር የቆሙትን ሃይሎች በተቀነባበረ ሴራ ከውስጥ እንዴት መምታት እንደቻሉ ይተነትናል። እራሱ ገብሩንና መሰሎቹን እንዴት ጠልፈው እንደጣልዋቸው ወደሁዋላ ቢያብራራልንም፣ በተመሳሳይ መልክ ቀደም ብለው ከተጠለፉት ታጋዮች ትምህርት ሳይወስድ ቀርቶ መዘናጋቱ ግን ሳይገርመኝ ኣልቀረም። ኣስመሳዮችና ከሃዲዎች ወደፊትም ሊኖሩ ስለሚችሉና እንደኣሁኑ ኣዘቅት ውስጥ ላለመዘፈቅ የዚሁን ሴራ ኣደገኛነት ተተንትኖ መቅረብ ትልቅ ትምህርት የሚገበይበት ነው። ይህ ኣውዳሚ ሴራ በሚገባ የተተነተነ ቢሆንም መለስ ዜናዊና ግብረ ኣበሮቹ ራሱ ገብሩን እንዴት እንዳጠመዱትና ምን ድረስ እንደወሰዱት ቢያክልበት ኖሮ ትንተናውን በይበልጥ ያጠናክረው እንደነበር ጥርጥር የለኝም።
እነዚህ ሁለት ምዕራፎች እንደ መንደርደርያ ኣድርገን ብንወስዳቸው፤ የሚቀጥሉት 4 ምዕራፎች ሉዓላዊነት የተሸረሸረበትና ዲሞክራሲ የተረገጠበት ተግባራዊ ሂደት በማያሻማ ጭብጣዊ ኣገላለፅ በዝርዝር ያትታል። እዚህ ላይ ሉዓላዊነትን ማስደፈርና ዲሞክራሲን መጨፍለቅ ለምን ኣስፈለገ ? የሚል መሰረታዊ ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፤ ይገባልም። ዝርዝር ሂደቱን ስንመለከት የመለስ ዜናዊና ግብረ ኣበሮቹ የግል ስልጣን ጥም ማርካት ያስከተለው ረቂቅ በሽታ እንደሆነ ሊደረስበት ይቻላል። የግል ስልጣን በሽታ የተጠናወታቸው መሪዎች፥ በሌሎች መሪዎችም እንዳየነው፥ ለግል ስልጣናቸው መንከባከብ እስካገለገለ ድረስ ሉዓላዊነት ቢደፈር ፡ ዴሞክራሲ ቢጨፈለቅ ጉዳያቸው ኣይደለም። ለባዕዳን ሃይሎችም ተገዝተው የሚያገለግሉ “መሪዎችም” እንዳሉ ይታወቃል። ከነዚህኞቹ ኣንዱ መለስ ዜናዊ ሳይሆን ኣይቀርም። ይህ በተለያየ መልክ የሚንፀባረቀው ረቂቅ በሽታ ኣሁንም ወደፊትም ሊኖር ስለሚችል መድሓኒቱ የሚገኘው ከነቃና ከተደራጀ ህዝብ ብቻ ነው። ስልጣን በግለሰዎች እጅ እንዳይወድቅ፣ ህዝብ በየመልኩ ተደራጅቶ የስልጣን ባለቤትነቱን የሚያረጋግጥበት ስርዓት ፈጥሮ መኖር ይኖርበታል።
ወደ ዝርዝር ጉዳዮች ስንገባ፤ ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በይፋ መረገጥ የጀመረበት መቼና እንዴት እንደሆነ ገብሩ በማያሻማ ሁኔታ ያስረዳል። በ1983 ዓ/ም ሰንዓፈ – ኤርትራ ውስጥ በነመለስ ተረቆ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ነጻ ሆኖ ሳይመክርበት በላዩላይ የተጫነው ቻርተር ተግባር ላይ ሲውል ነው። ይህ ቻርተር ለህዝቡ ሳይሆን ለግላቸው የሚያገለገሉበት መንግስት እንዲፈጥሩ ኣስችሏቸዋል። “ኦነግ ፣ ሻዕብያና ህወሓት/ኢህኣዴግ የተስማሙበት ይህ ሰነድ በኢትዮጵያ የሚመሰረተው የሽግግር መንግስት ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ኣሳድረዋል።” (ገብሩ፤ ገጽ 181) ካለ በኃላ ከዚህ ጎን ለጎን ደግሞ የዴሞክራሲ ጥሰቱን ኣያይዞ ሲያብራራው፤ ለሉዓላዊነት መከበር ሊቆሙ የሚችሉትን ህብረ-ብሄር ድርጅቶች “ኣስተሳሰባቸው በህዝቡ ውሳኔ መሸነፍ እስካልተረጋገጠ ድረስም ትምክህተኞችና ጸረ-ሰላም ሓይሎች ናቸው በሚል ከሚቋቋመው የሽግግር መንግስት እንዲገለሉ ማድረጉ ተገቢ ኣልነበረም” በማለት የህዝቡ ይሁን የድርጅቶቹ ዴሞክራሲዊና ፖለቲካዊ መብቶች በመርገጥ  ሃገሪቱን ለማያባራ ቀውስ እንደዳረጉዋት በተጨባጭ ያስገነዝበናል። ሰፊው ህዝብን የሚያገል ተግባራት ሁሉ ዞሮዞሮ ወደ ቀውስ ማምራቱ ኣይቀርም። ሃገር የጋራ እንደሆነ ሁሉ እነዚህ መብቶችም የሁሉም ናቸውና ይህን ሃቅ ማወላገዱ ሰላምን ማደፍረስ ብሎም ኣመፅን መጋበዝ መሆኑ በሁሉም ዘንድ እንደታወቅ የግድ ይላል።
ብዙም ሳይቆይ ቻርተሩ “ሕገ-መንግስት” ወደ ተባለው ሰነድ ተቀይሮ፤ በዚህ ሰነድ ከለላ ህዝቡን ያገለለ ግን ደግሞ በህዝቡ ስም በኣውዳሚነቱ ተወዳዳሪ የማይገኝለት ሴራ ተፈፅመዋል። ከባሕር- በር ማጣት ጀምሮ የሃገሪቱን ኣንጡራ ሃብቶች እስከ ማስዘረፍ የደረሰ ክሕደት መፈፀሙ ገብሩ በዝርዝር ያስረዳል። በዚህ ወቅት 144000 (ኣንድ መቶ ኣርባ ኣራት ሺ) ኢትዮጵያዊያን ከኤርትራ በግፍ ሲባረሩ ጥብቅና የቆሙት ለወገናቸው፣ ግፍ ለደረሰበት ኢትዮጵያዊ ሳይሆን ለግፈኛው ሻዕብያ መሆኑ ሲታይ (በሰነድም, EPRDF News Bulletin,…August 30, 1991. ላይ ሲያረጋግጡ) የብዙ ሰው ልብ ማድማታቸው ጠቅሸ ማለፍ እፈልጋለሁ።
ሓምሌ 1983 ሻዕብያ ኣስመራ ላይ በጠራው የኢኮኖሚ ኮንፈረንስ ኢትዮጵያን የመዝረፍ ዕቅዱ ግልፅ እንዳደረገው፣ ገብሩና ባልደረቦቹ (ስብሓት ነጋን ጨምሮ) በታዛቢነት ተገኝተው ተገንዝበዋል። በኢትዮጵያ ኣየር መንገድ፤ ባንኮች፤ ኣውራ ጎዳና ስራ፣  ወ.ዘ.ተ. ገብተው በራሳቸው ዕቅድ እንደሚሰሩ ተዝናንተው ግልፅ ኣድርገዋል። “የኤርትራን የእድገት ኣቅጣጫ ኣስመልክቶ የፖሊሲ መነሻ ሓሳብ የሚያቀርበው ምሁር፣ ኢትዮጵያ ገብተን ራሳችን መንገድ ቀይሰን መገንባት ኣለብን ሲል እብድ ይሁን ደንቆሮ ባይገባኝም ከሻዕብያ ኣመራር ያገኘውን መመሪያ መሰረት ኣድርጎ እንደተናገረ ግን ግልፅ ነበር” (ገብሩ፤ገፅ 193) ይለናል።
ይህ የዝርፍያ ዕቅድ እንዲሁ እቅድ ብቻ ሆኖ ኣልቀረም፣ በየዘርፉ ተግባራዊ ሆኖዋል። የኢትዮጵያ ከተማዎችን እየዳሰሰ ከኤርትራ ኬንያ የሚመላለሰው የኮንትሮባንድ ስምሪት፤ የውጭ ምንዛሪ ቅርምት፤ የቡና – ሰሊጥ- እንጨት ወዘተ ዝርፊያ፤ የጦር መሳርያና የኣልኮል መጠጥ ሸቀጡ ደርቶ እንደነበረ ያደባባይ ሚስጥር ነው። ሰውም ተዘርፈዋል / ታፍኖ ተወስደዋል። ለዚህ ማፍያዊ ስምሪት መሳካት መለስ ዜናዊ ተባባሪ ብቻ ሳይሆን ኣስፈፃሚም ነበረ። በህጉ መሰረት የሃገሪቱ መንግስት ምክር ቤት፤ ፓርላማ ወይም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሳያውቁት በድብብቆሽ 1.2 ቢልዮን ብር ከኢትዮጵያ ግምጃ ቤት ወጥቶ ለሻዕብያ እንዲሰጥ ማድረጉ (ገፅ 211) ኣንድ ኣብነት ነው።
ሻዕብያ የመለስና ስብሓት ተባባሪነት ብቻውን ኣላጠገበውም። ልቅ ምኞቱን ለማሳካት ወታደራዊ ሓይልን መጠቀም ፈልጎ የሰራዊት ምልመላና ስልጠና በገፍ ተያያዘው። የጦር ዝግጅቱ ያሳሰባቸው “ተወልደ፤ ኣውዓሎምና ገብሩ፣ ሻዕብያ ወደ ጦርነት እያመራ እንደነበር ቅንጣት ታኽል ጥርጣሪ ኣልነበረንም” ሲል ገብሩ፤ በኣንፃሩ ስብሓት ነጋ ግን መረጃው ሻዕብያ ወደ ጦርነት ማምራቱ ኣያመለክትም እያለ ሲቃወም እንደነበረ ያስረዳል። ቀጥሎም በባድመ ጦርነት ዋዜማ የህወሓት ማ/ኮሚቴና የኢህኣዴግ ስራ ኣ/ኮሚቴ በጋራ የኢትዮጵያ ጦር ኣስመራ ድረስ ዘልቆ የጠላትን ሓይል ማሽመድመድ ኣለበት ብሎ ሲወስን፣ (ገፅ 286) መለስ መቃወሙ ብቻ ሳይሆን በጠነጠነው ሴራ የብዙሃኑ ውሳኔ ግቡ ሳይመታ ከከባድ ኪሳራ ጋር ተኮላሽቶ እንዲቀር ኣድርገዋል። በፆሮና ግንባር ብቻው የነበረው ከባድ ኪሳራ ሲታይ መለስና ግብረ-ኣበሮቹ ለታጋዩ ወገን የነበራቸውን ደንታ ቢስነት በግልፅ ያረጋግጣል።
ገብሩ እንዳስጨበጠን፤ ኢሳያስ ኣፈወርቂ ጦሩን ሲደልብ፤ መለስ ዜናዊ ጦሩን ሲበትንና የተረፈውን ሲያኮላሽ፤ ስብሓት ነጋ ደግሞ የሁለቱን ሴራ ሲሸፋፍን በማህሉ ሃገርና ህዝብ ሲታመሱና ሲማቅቁ ማየቱ እጅግ ኣሳዛኝ ነበር። ዋናው ቁምነገሩ ግን ማሳዘኑ ኣይደለም። ከዚሁ ኣልፎ ለምን እንዲህ ሊሆን እንደቻለ መጠየቁ ኣግባብነት ያለው ዜግነታዊ ግዴታ መሆኑ ነው። ለዚህም ነው በግለ ሰዎች እጅ ላይ የወደቀች ሃገር እጣ ፈንታዋ ይኸው ኣሳዛኝ ተርእዮ የሚሆነው የምንለው። ባጠቃላይ እንደዚህ ዓይነቱ ግለ ሰዎች የሚቆጣጠሩት ስርዓት – የፈለገው ያህል ይመፃደቁ- በኣብዝሃው ስርዓት እስካልተተካ ድረስ ኣፈናው፣ ሰቆቃውና ውርደቱ ማቆምያ ኣይኖረውም።
መለስ በሓሳብ የተቃወሙትን የድርጅቱ ኣባላት ለመምታት ሲል 160 ዓመታት ወደ ኃላ ተጉዞ “ቦናፓርቲዝም” የሚባለው ፅንሰ ሓሳብ የመዘዘበትን መሰሪ ቅጥፈት ስንመለከት ደግሞ፣ ሃገሪቱና ህዝቡ ምን ያህል የኣንድ ግለ ሰብ መጫወቻ እንደነበሩ ያስረዳናል። ቦናፓርቲዝም ምን ማለት እንደሆነ ገብሩ (ገፅ 354-5) በግልፅ ኣስፍሮታል። እንዲያው በጥቅሉ ቦናፓርቲዝም የኣምባገነንነት ኣንዱ ገፅታ ሆኖ በተለይ የኣንድ ኣወናባጅ ሰው ፈላጭ ቆራጭነትን ያመለክታል። ሆኖም መለስ ይህ የራሱን ባህርያት ውስጥውስጡን ለተቃዋሚዎቹ በመለጠፍ ቀድሞ በህቡእ ከመታቸው በኃላ እራሱ  ምንደኛ ፈላጭ ቆራጭ ሆኖ ኣረፈው። ይህን ተከትሎ የመጣው ኣሳዛኝና ኣሳፋሪ ድርጊቶቹም ገብሩ በማስረጃ ደግፎ ኣቅርቦልናል። ከብዙ በጥቂቱ፣
  • ለሃገር ሉዓላዊነት የቆሙትን “ኣፈንጋጮች” ብሎ በመሰየም በግሉ ውሳኔ ከስራቸው ማባረሩ (ገፅ 399)
  • በህዝብ ድምፅ ለብሄራዊ ምክር ቤት የተመረጡትን በግላዊ ጥላቻና ማን ኣህሎብኝነት የህዝቡን ውሳኔ ረግጦ ማገዱ (ገፅ 400)
  • “ኢንተርሃምዌ” በሚል የታወቀው የዘር ግጭት ቅስቀሳ ኢህኣዴግ እንዲጠቀምበት ውሳኔ ማስተላለፉ (ገፅ 434-5)
  • የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን “ሕገ-መንግስት መናድ” በሚል ክስ እስር ቤት እንዲወረወሩ ማድረጉ (ገፅ 442-3)
  • የሲቪል ማሕበረ ሰብ እንቅስቃሴ እንዳይኖር ኣፋኝ ሕግ ኣስወጥቶ በስራ ላይ ማዋሉ (ገፅ 444)
  • ሓሳብን በነፃነት መግለፅ እንዳይዳብር ነፃ ፕሬሱን ጨምድዶ እጁ ውስጥ ማስገባቱና ጋዜጠኞችን ኣስሮ ማሰቃየቱ (ገፅ 445)
  • በፀረ-ሽብር ሽፋን ኣፋኝ ኣዋጅ ዘርግቶ ተቃዋሚዎችን በሰበብ ኣስባቡ መፍጀት (ገፅ 447-8) ሊጠቀሱ የሚችሉ የፀረ-ዴሞክራሲ ዘመቻው ኣብነቶች ናቸው።
እነዚህና ሌሎች ያልተጠቀሱ ፀረ-ዴሞክራሲና ፀረ-ሉዓላዊነት ድርጊቶቹ መለስን ተራ ኣምባገነን ሳይሆን ኣወናባጅ ኣምባገነን ያደርጉታል። የማወናበድ መሰሪነቱ ኣልታይ ያላቸው የዋሆች፣ የጥቅም ጉዳይም ተጨምሮበት፣ መታለላቸው ኣልቀረም። ለዚህም ነው ተከታዮቹ መለስን እንደ ብልጣብልጥ ሳይሆን እንደ ኣዋቂ የሚዘምሩለት። የገብሩ መፅሓፍ የመለስን ኣስመሳይ ገፅታ ፈጦ በግልፅ እንዲታይ ስለ ኣደረገ ተከታዮቹ ባሁኑ ጊዜ በመዝሙራቸው እያፈሩ ይገኛሉ። በኣድርባይነቱ የሚቀጥሉ ካሉም የባሰውኑ መዋረድ ኣይቀርላቸውም። ያም ሆኖ የመለስን ኣወናባጅ ባህርያት ሲያጋልጡና ሲቃወሙ የነበሩት የፖለቲካና የፕሬሱ ኣባላት እንደዚሁም የድርጅቱ ኣባላት (እነ ሓየሎምን ጨምሮ) የጥቃቱ ዒላማዎች ሆኖው እንዳለፉ መዘንጋት የሌለበት ሃቅ መሆኑ ላስታውስ እወዳለሁ። ለዚህም ነው በኢትዮጵያችን ዴሞክራሲ የተዳፈነው፤ ኣሁንም ተዳፍኖ የሚገኘው።
ኣቶ ገብሩ በመፅሓፉ በጥልቀት የመረመረው የሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ መረገጥ ኢትዮጵያን ምንኛ ኣዘቅት ውስጥ እንደከተታት ለመገንዘብ – የየዋሆቹና የኣድርባዮቹ መወድስ ወደ ጎን ትተን – ተገቢው (ለጂቲመት) የባሕር በር ማጣትና ያስከተለው ከባድ እዳ እና በተጨባጭ በየዓረብ ሃገር ኤምባሲ በራፍ የሚኮለኮለው ህዝብ ቁጥር ወይም በየባሕሩ የሚሰምጠውና በየምድረበዳው ቀልጦ የሚቀረው የወጣቱ ብዛት ማስተዋል ብቻውን በቂ በሆነ ነበር። ጥናታዊ መረጃ ካስፈለገም የተባበሩት መንግስታት ዕድገት ፕሮግራም (ዩ.ኤን.ዲ.ፒ. 2013) ብንመለከት ኢትዮጵያ በሰብኣዊ ዕድገት ኣመልካች ከ 187 ሃገሮች በ 173 ኛው ደረጃ ኣዘቅዝቃ ትገኛለች። ይህ ደግሞ የመናጢ ሃገሮች ተርታ ነው። 41% ህዝቧ ከድህነት ወለል በታች የሚኖርባት ሃገር ዕድገት ኣለ ብሎ ማውራት የዕድገት ትርጉም መሳት ብቻ ሳይሆን የህዝቡን ኣሰቃቂ ሁኔታ ረስቶ በግለሰብ ኣምልኮ መጠመድ ነው። ኣድርባይነት ! ያውም ክላሲካል ኣድርባይነት ይሉታል።
ለዚህ ሁሉ ፍዳ ምክንያቱ ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲን ጨፍልቆ ኣምባገነንነትን ያነገሰው የመለስና ግብረ-ኣበሮቹ ሰንካላ ፖሊሲ መሆኑ መፅሓፉ በመረጃ ኣጅቦ ያስረዳል። የመፅሓፉ ዋናው ይዘት ይህ ሲመስል በመጨረሻም ከምንገኝበት ኣስከፊ ሁኔታ መውጣት የምንችልበትን ገንቢ ሓሳቦች ገብሩ በሚገባ ሰንዝረዋል።
የብዙ ሰው ዓይን ከፋች የሆነው፣ ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲን የሚያህሉ ትላልቅ ሃገራዊ ርእሰ ጉዳዮች በጥልቀት ተተንትነው መቅረባቸው ስለ ሃገሩ ሉዓላዊነትና ስለ ዴሞክራሲ ለሚጨነቅ ሁሉ ገብሩ ትልቅ ስጦታ ኣበርክተዋል። መፅሓፉ በዋናነት ለትውልድ የሚተርፍ ነው። ሆኖም፣ ማንም መፅሓፍ ፍፁም ኣይሆንምና ኣልፎ ኣልፎ ግድፈቶች መስለው የታዩኝን ኣንድ-ሁለት ነጥቦች ማንሳት እወዳለሁ።
1ኛ/ ቃለ-ምልልስ ኣለመጠቀም፣
ውስብስብ ታሪክ ያዘለና ፖለቲካዊ ይዘት ያለው መፅሓፍ በበርካታ ዋቢ መፃሕፍትና ጥቂት ሰነዶች ቢሸኝም ቅሉ፣ በዛ ረጅም ውጣ ውረድ ውስጥ በቀጥታ ተሳታፊ የነበሩትን (ሃገር ቤትም ባእድ ሃገርም የሚገኙትን) ነባር ኣባላት በማነጋገር ለቀረበው ይዘትና ትንታኔ ቃላቸውን ቢያክሉበት፣ ሚዛናዊነቱን በይበልጥ ከማጉላቱ በላይ ግድፈቶችንም ይሞላ ነበር እላለሁ። ይህ ግድፈት የፈጠረው ክፍተት የራሴ ገጠመኝን በማውሳት በሁለት/ሶስት ኣብነቶች ላስረዳ፣
ለምሳሌ፣ በገፅ 71 “ ከኢዴሕ ጋር የተካረሩ ውግያዎችን በምናካሂድበት በ1969 ዓ/ም በጋ ላይ ኣረጋዊ በርሄ ሽሬ እንዳስላሴ ገብቶ ከደርግ ባለስልጣናት ጋር እንደተነጋገረ … ተኩሉ ሃዋዝ (ኣሁን በህይወት የሌለ) ነገረኝ …እስካሁን ከኣረጋዊ የቀረበ ይፋዊ መግለጫ የለም” ይላል። ገብሩ ከኣረጋዊ ጋር በዚህና በሌላ ትላልቅ ጉዳዮች ላይ ቃለ-ምልልስ ቢያድርግ ኖሮ እውነታውን በቀላሉ ሊያገኘው ይችል ነበር። ይሁንና ላነሳው ጥያቄ መልሱ ‘ኣዎን ተነጋግሬ ነበር’ ነው።
ሁኔታውን ማወቅ ለፈለገ ባጭሩ እንዲህ ነበር፣ በኢድሕ ግስጋሴ ስጋት ያደረበት፣  ሽሬ የመሸገው የደርግ ጦር ኣዛዥ እንገናኝ በሚል ያገሩ ሽማግሌ ላከብን። ምዕራብ ግንባር የነበርነው ኣመራር (ስብሓት ነጋን ጨምሮ) በጉዳዩ መከርን። ግንኙነቱ ትጥቅ ያስገኝልናል ከሚል መላምት እኔ እንዳገኘው ተወሰነ፤ ከተማው ጥግ ተገናኘን። ባጭሩ እሱ በተሎ ትጥቅ ሊያቀርብልን እንደማይቻለው፣ እኔም የሁለታችን ስምሪት ማቀናጀት እንደማይቻል ሓሳብ ተለዋውጠን በዚሁ ተለያየን፣ ግንኙነቱም እዛው ኣበቃ። ለገብሩ “በወቅቱ የማይታሰበው ውይይት” ለኛ ግን ታሳቢ ነበር።
በጭንቀት መኖር የተገደደው ደርግ ከዛ በኃላም ሊገናኘን ሞክሮ ኣልተሳካለትም። ዝርዝሩ የፈለገ ጠይቆ መረዳት መብቱ ነው።
2ኛ/ ቁምነገሩን የሚያስት የቃላት ኣጠቃቀም፡
እዚህ ላይ ተራ ቃላት የሚመስሉ 2 ኣምሮች (ኮንሰፕትስ)፣  ግርግር እና ማፈግፈግ (በሞራላዊ ወይም በዲፕሎማሲያዊ እሳቤ ተጠቅሞ ሊሆን ይችላል) ፣ ኣለቦታቸው ገብተው  እውነታውን እንዴት እንደቀየሩት ኣሳያለሁ።
ሀ/ የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ኣባል የነበረው ታጋይ ተኽሉ ሃዋዝ “… በቁጥጥር ስር ከዋለ በኃላ በእስር ቤት በተፈጠረ ግርግር ሕይወቱ ኣልፏል” ይላል (ገጽ 151)። በግርግር ሕይወቱ ኣልፏል ሲል እንደ ኣጋጣሚ፣ በትርምስ፣ ሳይታሰብ ሞተ ለማለት ይመስላል። ሃቁ ግን ሆን ተብሎ ነው የተገደለው። የተለየ ኣቛም ስለ ያዘ ተገደለ ማለቱ ይበቃ ነበር፣ ያልታሰበበት ከማስመሰል።
እንደገና የማእከላይ ኮሚቴ ተወካይ የነበረው ሸዊት ዳኘውም በዚሁ መልክ “… እስር ተበይኖበት እዛው በተነሳ ግርግር የድርጅቱ ሰለባ ሆነዋል” ይላል (ገጽ 90)። ሸዊት የግርግር ሰለባ ኣልነበረም፣ ሃቁ የመለስ ጥቃት ሰለባ እንጂ።
ለ/ በሶስት ቦታ (ገጽ 108፣ 113 እና 114) መለስ ዜናዊ ከጦርነት ማፈግፈጉና ሂስ እንደደረሰበት ይተርካል። ማፈግፈግ በወታደራዊ ስምሪት፣ ተመክሮበት የሚፈፀም ስልታዊ ንቅናቄ ነው፣ ሂስም ቅጣትም ኣያስከትልም። ከጦርነት ቀጠና መሸሽ ግን ሂስም ቅጣትም ያስከትላል። ተቀጥቷልም። በመለስ ላይ ኣመራሩ የበየነው ቅጣት ኣነሰ ተብሎ ያኔ ለተከሰተው ቀውስ (ሕንፍሽፍሽ) ኣንዱ ምክንያት እንደነበረም ማከሉ ሃቁን ያጎላዋል። ስለዚህታሪኩ እንዳይዛባ ኣለቦታው የገባው ኣፈገፈገ ፣ የሚለው ኣምር ሸሸ ወይም ሸሽቶ በሚለው ቃል መተካት ይኖርበታል።
3ኛ / በድርቅ ዙርያ ትልቅ ግድፈት
የ1977 ዓ/ም ድርቅ በህዝቦቻችን ላይ ያደረሰው ኣሰቃቂ እልቂት ፣ የሻዕብያ ኢ-ሰብኣዊነት ተጨምሮበት ምን ያህል ፈታኝ እንደነበረና የተደረጉ “ጥረቶች” በሰፊው ተብራርተዋል። ሆኖም እዚህ ላይ ሁለት የሚከነክኑ ዓበይት ጉዳዮች ተዘለዋል።
ኣንደኛው/ በዛ ቀውጢ ወቅት ማሌሊት ለተባለው ጤዛ ድርጅት ምስረታ ተብሎ ሁሉም የህወሓት ካድሬዎች ከነኣመራሩ ኣንድ ወር ሙሉ በድግስ ሲንንበሸበሽና ስንዘፍን መክረማችን፣ ኣፄ ሃ/ስላሴንና ደርግን በተመሳሳይ ኣስነዋሪ ድርጊት እንዳላወገዝን ሁሉ !!!
ሁለተኛ\ እና ዋናው ያኔ በድርቁ ምክንያት ከተሰበሰበው 100 (ኣንድ መቶ) ሚልዮን ብር 50% ማሌሊትን ማጠናከርያ፣ 45% ህወሓትን መደጎምያ፣ 5% ብቻ በድርቅ ለሚጠቃው ህዝብ በማእከላይ ኮሚቴው ስብሰባ መመደቡና ድርጊቱ የግፍ ግፍ መሆኑ ኣልተጠቀሱም። ይህ የበጀት ምደባ በኣብዝሃው ማ\ኮሚቴው ስብሰባ ጸድቆ፣  ቃለ ጉባኤውም በጽሑፍ ሰፍሮ፣ በቴፕ ተቀድቶ በህወሓት ሰነዶች ማእከል ይገኛል። ከህወሓት ፋይሎች ኣልፎም የዓለምኣቀፍ የረድኤት ማሕበራት፣ እንደነ ቢቢሲ የሚድያ ተቋማትን ኣሁንም እያተራመሰ ይገኛል። በግለሰብ ደረጃም ታዋቂው የቢቢሲ ጋዜጠኛ ማርቲን ፕላውት፣  ዘፋኙ ቦብ ጌልዶፍ፣ ኢኮኖሚስቱ ፕሮፌሰር ደስታ ኣሳየኸኝ፣ ወዘተ ኣሁንም ይተቹበታል። “ኣህያውን ፈርተው ዳውላውን” እንዲሉ ገብሩ በጋራ ህዝባችን ላይ የደረሰው ጭካኔን ኣጉልቶ የሚያሳየው ትልቁ ነጥብ (ባእዳን ኣሁንም የሚነታረኩበት) ትቶ ስለተከናወኑ “መልካም” ነገሮች ብቻ መተረኩ ጭራሽ ኣልገባኝም።
ይህ ነውረኛ የበጀት ምደባ ኣስመልክቶ ኣምባሳደር-ነበር ኣውዓሎም ወልዱ ለኣዲስ ኣድማስ ጋዜጣ 27 ጥቅምት 2003 ዓ\ም ገጽ 21 ላይ ባሰፈረው መረጃ፣ “ 35% ለህዝቡ፣ 65% ለድርጅቱ ተከፋፍለዋል” ያለውን የተሻለ ጥቆማ ቢሆንም በቃለ ጉባኤው ከሰፈረው ሃቅ ጋር ግን ኣይጣጣምም። ስለዚህ ይህ ጉዳይ በድርቅ የተጠበሱት ሚልዮኖችን የሚመለከት፣ ላንዳንዱም መራር ትዝታ ስለሆነ ተስተካክሎ ይፋዊ መግለጫ እንዲሰጥበት ከወዲሁ ኣቶ ገብሩን ኣሳስባለሁ። ዋናው ቁምነገሩ ያለፈውን ጥፋት በግልፅ በማየት ይህ ዓይነት በደል ለወደፊቱ እንዳይደገም ለማድረግ ነው።
4ኛ/ ወደ ዝርዝር ሳልገባ፣ ከወደ ኃላ የተወራለት ወታደራዊ መመርያ (“ዶክትሪን”) በምንም መልኩ እንዳልታየ፣ በከተማ የተነደፈው የመጀመርያው የድርጅቱ ፕሮግራም እንደነበረና ቅጂው ኣሁንም እንደሚገኝ፣ ስለ የኢህኣፓ ምርኮኞች ኣያያዝ የቆየው የህወሓት ምርኮኛ ኣያያዝ ደንብ እንዳልተከተለ፣ ከግድፈቶች ተርታ ሊጨመሩ የሚችሉ ኣብነቶች ናቸው።
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱ ግድፈቶች ስጠቁም ዋናውን ርእሰ ጉዳይ፣  ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲን ኣስመልክቶ ለቀረበው ሰፊና ጥልቅ ጥናታዊ ዘገባ፣ ላይ ምንም ዓይነት ኣሉታዊ ተጽእኖ ያሳድራሉ ከሚል እንዳልሆነ ላረጋግጥ እወዳለሁ። እንዳውም ለዚህ ትልቅ ሃገራዊ ጉዳይ፣ ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ፣ ተብሎ ለተደረሰው መጽሃፍ ከሚቀርቡ ኣሉታዊ ትችቶች በተመለከተ ኣንድ ሁለት ነጥቦች ላክል።
የመጽሓፉ ርእስ ብሎም ይዘት ከጅምሩ እስከ ማብቂያው በሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ ያጠነጠነ ሆኖ እያለ ኣንዳንድ ”ተቺዎች”፣ ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ እንዲሉ፣ በሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ ላይ ኣንድም ቃል ሳይተነፍሱ በደራሲው ስብእና ላይ የባጡን የቆጡን ሲደረድሩ ይታያሉ።  ሃተታቸው ተጠቃሎ ሲታይ፣ ለምን ተሳስቸ ነበር ትላለህ ? ለምን ድርጅታችን ሲሳሳት ነበር፣ ኣሁንም እየሳሳተ ነው ትላለህ ? መሪዎቻችንን ለምን ታጋልጣለህ ? የሚሉ ናቸው። 1ኛ ነገር የማይሳሳት ድንጋይ ብቻ ነው፣ 2ኛ/ ስሕተትን ማየትና ሌላው እንዲማርበት ማድረግ ብልህነት ነው፣ 3ኛ/ ስሕተቱንና ችግሩን ተገንዝቦ እርማት የሚሰነዝር ሰው ኣርቆ ኣሳቢ ነውና ለነዛ ዓይነቱ “ተቺዎች” ዝርዝር መልስ ሳልሰጥ ባጭሩ ግን ለድርጅትና ለመሪዎቹ ጥብቅና ከመቆም ይልቅ ለሃገርና ለህዝብ ማስቀደም ይሻላል እላለሁ።
ጭራሽ የሚገርመው ደግሞ ሳያነቡ የሚተቹ “መሪዎች” መከሰታቸው ነው። ከነዚህ ኣንዱ –  ጠንቋይ ኣይሉት ነብይ  – ስብሃት ነጋ ነው። ለዚህ ሰውም የምለው ነገር ካለ “የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ኣላስደፈርኩም፣ ዴሞክራሲን ኣልረገጥኩም” ብለህ የኣንዲት ገፅ ፅሑፍ ኣቅርብ ብቻ ነው።
በቁምነገር መታየት ያለበት ሌላው ነገር፣ ገብሩ በመፍትሄነት ከሰነዘራቸው ዓበይት ነጥቦች ኣንዱ “ኢትዮጵያዊነትና የብሄረሰብ መብቶች ኣይነጣጠሉም” በማለቱ የሚወርዱትን የተቃውሞ ትችቶችን ይመለከታል። እነዚሀ ተቺዎች ጭራሽ የብሄረሰብ መብት ብሎ መነሳት የለበትም፣ የግለ ሰብ መብት መከበር ብቻ በቂ ነው። የብሄረሰብ መብት  ማስተናገድ ኢትዮጵያዊነትን ያዳክማል ወይም ይበታትናል ባዮች ናቸው። ይህ ዓይነቱ ሙግት በሌላ ጊዜም ተደጋግሞ ይሰማል። ፖለቲከኞችም ለተለያየ ዓላማ ይጠቀሙበታል። ሆኖም ይህ ኣመለካከት ማህበረሰባዊ ዕድገትን፣ ታሪክንና በመሬት ላይ ያለው ሃቅን ካለማንፀባረቁ ባሻገር የባሰ ብተና ወይም ቀጣይ ቀውስ እንጂ መፍትሄ ኣያመጣም። ለምን?
የግለሰብ መብት የግድ መረጋገጥ ያለበት ተፈጥሮኣዊም ፖለቲካዊም መብት መሆኑ ኣያጠያይቅም። ያለ የግለሰብ መብት መከበር፣ ዕድገት (ስልጣኔም ይሁን ፈጠራ) ኣይኖርምና። ይህ የግለሰብ መብት በኢትዮጵያችን ከተረገጠ ቆይተዋል። ዛሬ ግለሰቡ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሳይሆን የኢህኣዴግ ጢሰኛ (ሳብጀከት) ወደ መሆን ወርዷል። ለዚህም ነው ሁዋላ ቀርነት መለያችን ሆኖ ያለው።
የግለሰብ መብት ሲባል ግን ይዘትና መልክ የሰጠው ማን ነው ብሎ መጠየቅ የግድ ይላል። የግለሰብ መብት ይሁን እንደ ግለሰብ መኖር ራሱ ትርጉም የሚያገኘው በማሕበረሰቡ ከለላ ውስጥ ሆኖ ነው። ከማሕበረሰቡ ውጭ ግለሰቡ እንደ ሰው መኖርም ማደግም ኣይችልም። በእንሰሳት ማህል ያደገ ህፃን ከሰው የተወለደ ቢሆንም የእንሰሳቱ ጠባይ እንደሚይዝ ማስረጃዎች ኣልጠፉም። ስለዚህ ግለሰብና ማሕበረሰቡ ካስተሳሰብም ይሁን ከመብት ኣኳያ ነጣጥሎ ማየቱ ትክክል ኣይሆንም። የኢትዮጵያ ህዝብ ሲባል የተነጣጠለ ግለሰብ ድምር ማለት ሳይሆን ግለሰቡን ኢትዮጵያዊ ሰው ያደረገው ውስብስቡ ማሕበራዊው ስብስብ ጭምር ነው። የማሕበራዊው ስብስብ ኣንዱ ኣካል ብሄረሰብ (ወይም “ጎሳ”) ነው። ወረድ ካለም ቤተሰብ ይገኛል።
እንግዲህ ኣንድ ግለሰብ በሃገሩ መብቱን ሲነጠቅና መብቱን ለማስጠበቅ ዓቅም ሲያጣ፣ ተወደደም ተጠላ የሱን ዓይነት ችግር ከደረሰባቸውና ከሚመሳሰሉት ጋር ተሰባስቦ፣ ሓይል ፈጥሮ መብቱን ለማስከበር መፍጨርጨሩ ተፈጥሮኣዊም ዝንተሞገታዊም ሂደት ነው። ይህ ክስተት ድሮም ኣሁንም ኣለ። ኣድልዎ እስካለ ድረስ ወደ ፊትም ይኖራል። በዚህ ታሪካዊ ማዕቀብ (ኮንቴክስት) ስር ስንገነዘበው፣ የግለሰብና የማሕበረሰብ ትስስር እንደማይነጣጠሉ ሁሉ፣ ኢትዮጵያዊነትና የብሄረሰቦችዋ ህልውናም ይሁን መብት ተነጣጥሎ መታየት ኣይኖርበትም። ምናልባት የብሄረሰብ ወይም “ጎሳ” ህልውና ከነጭራሹ ካልካዱ ወይም ካልናቁት በስተቀር።
በማጠቃለል፣ ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ ዋናዎቹ የህዝብ እሴቶች እንደመሆናቸው መጠን እነዚህን እሴቶች ማእከል በማድረግ ባለፈው ሩብ ክፍለ-ዘመን ኢትዮጵያ ፊት የተደቀኑ ችግሮችና ህዝቡ ያጋጠሙት ፈተናዎች ኣቶ ገብሩ በጥልቀት ኣቅርበዋል። የሃገር ሉዓላዊነትና የህዝብ ዴሞክራሲ መብቶች የጋራ እሴቶች ሆኖው በጋራ ሓላፊነት ሊጠበቁ ሲገባ ነገር ግን ኣንድ ግለሰብና ግብረ-ኣበሮቹ እጅ ላይ ወድቀው የደረሰው ፍዳ ኣሁንም እንዳላበራ በስፋት ዘርዝረዋል። ከዚህም ባሻገር ከገባንበት የቀውስ ኣዙሪት መውጫውና ዘላቂ መፍትሄ የምንቀዳጅበት ብልሃቱ ኣመላክተዋል። ይኸውም ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲን የሚከበርበት ህዝቡ የሚቆጣጠረው የጋራ ስርዓት በቅድሚያ መመስረት ነው።
ኣቶ ገብሩ ለራሱ ሳይሳሳ፣ ሃገርንና ህዝብ በማስቀደም ለፍቶ ላቀረበልን ትልቅ መፅሓፍ ያን ያክል ምስጋና ይገባዋል።
ኣረጋዊ በርሄ     14.01.2015