ዛሬ ከሞቃዲሾ፣ ሶማሊያ ያገኘነው ዜና እንዳረጋገጠው ከሆነ፤ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ንብረት የሆነው ራሺያ ሰራሽ አንቶኖቭ 24 ሞቃዲሾ አየር ማረፊያ እንደደረሰ ተቃጥሏል። በውስጡ ከነበሩት ስድስት ሰዎች መካከል አራቱ ወዲያውኑ የሞቱ ሲሆን፤ ሁለቱ ግን ወደ ሆስፒታል ተወስደው ህክምና በመከታተል ላይ መሆናቸው ታውቋል።
- A column of thick smoke rose over the airfield, where operations were grounded
- Ammunition could be heard exploding inside the plane as the fire spread
- It was unclear what specific ammunition the plane was carrying.
- It took two hours for Mogadishu airport firefighters to extinguish the blaze
- Emergency services rescued two crew members and took them to hospital
በውስጡ በርካታ የጦር መሳሪያ የጫነው አንቶኖቭ የጦር አውሮፕላን፤ መሬት ካረፈ በኋላ ነው መቃጠል የጀመረው፤ ከዚያው ጋር ተያይዞ የጫናቸው መሳሪያዎች መፈነዳዳት መጀመራቸውና ይህም እሳቱን ያባባሰው መሆኑ ታውቋል። ኢትዮጵያ በሱማሌ ውስጥ የአፍሪቃ ሰላም አስከባሪ አባል አይደለችም። ሆኖም “የሶማሌን መንግስት ለመርዳት” በሚል ሽፋን የጦር ኃይሏን በሰፊው ማሰማራቷ ይታወቃል።
የአደጋው መንስኤ እስካሁን አልታወቀም። ሆኖም የአልሸባቡ ቃል አቀባይ አብዱላሁ አብዲ፤ ለቢቢሲ ዘጋቢ፤ “ይሄ የአምላክ ቅጣት ነው።” ነበር ያለው።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar