onsdag 30. september 2015

አርባ‬ ምንጭ የነበረው የአሜሪካ መንግስት የመከላከያ ኃይል ቡድን አካባቢውን ለቆ እየወጣ ነው



(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ) ‪አርባ‬ ምንጭ የነበረው የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ መንግስት የመከላከያ ኃይል ቡድን ከባለፈው ሳምንት ሐሙስ ጀምሮ አካባቢውን ለቆ እየወጣ እንደሆነ ታወቀ፡፡

 ‪‎ህወሓት‬ በሁመራ የሚገኙ 40 የንግድ ቤቶችን ራሱ በስውር በእሳት አቃጥሎ በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ የታጠቁ የነፃነት ድርጅቶች ለማላከክ እየሞከረ እንደሚገኝ ከውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን የተገኘው መረጃ አጋለጠ፡፡

  አርባ ምንጭ የነበረው የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ መንግስት የመከላከያ ኃይል ቡድን ከባለፈው ሳምንት ሐሙስ ጀምሮ አካባቢውን ለቆ እየወጣ እንደሆነ ታወቀ፡፡

 በአርባ ምንጭ እና አካባቢው ሲንቀሳቀስ እና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ከዚያ እያስነሳ ወደ ሚፈልገው አቅጣጫ ለጥቃት ሲያሰማራ ለረጅም ጊዜ የቆየው የአሜሪካ የመከላከያ ኃይል ቡድን ከአገሪቱ መንግስት በተሰጠው መመሪያ የቆይታ ጊዜ ኮንትራቱን አቋርጦ ሀሙስ ዕለት አካባቢውን ለቆ መውጣት መጀመሩን በቦታው የሚገኙ ምንጮቻችን ገልፅዋል፡፡

 ድሮን የታጠቀው የአሜሪካ የመከላከያ ኃይል ቡድን የአርባ ምንጭን መሬት ለቆ መንቀሳቀስ የጀመረበት ምክንያት ለጊዜው በውል ተለይቶ ባይታወቅም መንግስት ነኝ በሚለው በህወሓት አገዛዝ እና በአሜሪካ መንግስት መካከል አለመግባባት ተከስቶ ቅራኔ ሳይፈጠር እንዳልቀረ ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡

 ቡድኑ ከአሁን በፊት ከአርባ ምንጭ በተጨማሪ በድሬ ደዋ ላይ ተቀምጦ በሰው አልባ አውሮፕላኖች በሶማሊያ በሚንቀሳቀሱ የአልሸባብ ተዋጊዎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት መክፈቱ ይታወቃል፡፡ ህወሓት በሁመራ የሚገኙ 40 የንግድ ቤቶችን ራሱ በስውር በእሳት አቃጥሎ በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ የታጠቁ የነፃነት ድርጅቶች ለማላከክ እየሞከረ እንደሚገኝ ከውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን የተገኘው መረጃ አጋለጠ፡፡

 የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ገና ከሽፍትነቱ ጀምሮ በህዝብ ላይ ሴራ በማቀነባበር የሚታወቀው ህወሓት ራሱ ግንብቶ ለግለሰቦች ያከራየውን የንግድ ማዕከል ነው በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ የነፃነት ድርጅቶች ድርጊቱን እንደፈፀሙት በማስመሰል ከህዝብ ለመነጠል ሲል ነው በተቀነባበረ ሂደት በእሳት የለቀቀው ፡፡

 በህወሓት የተቀነባበረ ሴራ የተከሰተው ከባድ የእሳት አደጋ የደረሰው መስከረም 14 ቀን 2008 ዓ.ም ሲሆን ከ40 በላይ ሱቆች ተበልተው ወደ አመድነት ተቀይረዋል፤ በሚሊዮኖች ገንዘብ የሚገመት ንብረትም ወድሟል፡፡

 ህወሓት በአዲስ አበባ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት በተከሰቱት የቦንብ ፍንዳታዎች ትግራይ ሆቴልን ጨምሮ እጁ እንዳለበት የአሜሪካ ኤምባሲ ለስቴት ዲፓርትመንት የላከውን ደብዳቤ በዋቢነት ጠቅሶ ዊክሊክስ የተባለው ድረ-ገፅ ማጋለጡ የሚታውስ ነው፡፡

onsdag 23. september 2015

ትህዴን በአንድ ሳምንት ብቻ 19 ከትግራይ ክልል የመጡ ወጣቶች እንደተቀላቀሉት አስታወቀ


Photo File

የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ እንዳስታወቀው በአንድ ሳምንት ብቻ 19 የትግራይ ተወላጆች እንደተቀላቀሉት አስታወቀ:: በዚህ ሳምንት ውስጥ የህወሃት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግን ስርዓት በመቃወም በርካታ ወጣቶች ወደ ትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ድርጂት መቀላቀላቸውን ከማሰልጠኛ ማዕከል የደረሰን መረጃ አመለከተ።

ደህሚት በድረገጹ እንዳስታወቀውና ከድርጅቱ ደረሰኝ ባለው መረጃ መሰረት የወያኔን ከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ በመቃወም በርካታ ወጣቶች ወደ ማሰልጠኛ ማዕከል መቀላቀላቸውን የገለፀ ሲሆን የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል 1 ተክላይ ታፈረ ገብረዋሂድ ከትግራይ ማዕከላዊ ዞን ናዴር አዴት ወረዳ አዲ ላኪያን ቀበሌ አዲ በዛ አካባቢ 2 በሪሁ ገብረየሱስ ሃድጉ ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን ጉሎ መከዳ ቀበሌ አዲስ ተስፋ ሰፈር ደንጎሎ ከተባለው መንደር 3 ነፀረ-አብ አባዲ ፍስሃ ከሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ታህዳይ አድያቦ ወረዳ ገመሃሎ ቀበሌ ሁመር ከተባለው ሰፈር 4 ፍስሃ ገብረስላሴ ገብረ መድህን ከማዕከላዊ ዞን አህፈሮም ወረዳ ቤተ ገበዝ ቀበሌ ዝባን እንዳቦይ ገብራት ከተባለው አካባቢ 5 ጉዑሽ ሃይለ ገብረስላሴ ከስሜን ምዕራብ ዞን ታህታይ ቆራሮ ወረዳ ማይ አድራሻ

ከተባለው ቀበሌ 6 አወት ገዛኢ ፈዳይ ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን ጉሎመከዳ ወረዳ ዛላንበሳ ከተማ 7 ክብሮም ገብረ ፃድቅ ረዳ ከማዕከላዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ አድፍታው ቀበሌ አዲ ቀረዲሂም ከተባለ መንደር 8 በሪሁ አብረሃ ተላ ከትግራይ ደቡባዊ ዞን አምባላጀ ወረዳ ስስት ቀበሌ ከታረ ከተባለው ሰፈር 9 በረከት ገብረ ኪዳን ወልደማሪያም ከትግራይ ማኦከላዊ ዞን ናአዴር አዴት ወረዳ አዲ ለኪያን ከተባለው ቀበሌ 10 ሚኪኤሌ ካህሳይ በርኸ ከትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ታህታይ አድያቦ ወረዳ አዲ ፀፀር ከተባለው ቀበሌ 11 ፀጋይ ሃፍታይ ከምስራቃዊ ዞን ክልተ አውላሎ ወረዳ ፅጌረዳ ቀበሌ 12 ከድር ወህበይ አብራር ከሰሜናዊ

ምዕራብ ዞን ታህታይ ቆራሮ ወረዳ አድ ብዘት ከተባለው ቀበሌ ብዘት አካባቢ እምቢሉ ከተባለው መንደር 13 ሃጎስ ገብረ ዮሃንስ ንጉሴ ከማዕከላዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ አወት ቀበሌ 14 ግደይ ወልደሚካኤል ወልደማሪያም ከሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ሽረ ወረዳ ሰመማ ቀበሌ 15 አሸናፊ ገብረየሱስ ወልዱ ከምስራቃዊ ዞን ጉሎ መከዳ ወረዳ አዲስ አለም ቀበሌ አዲ ገናህ ከተባለው አካባቢ 16 ዘነበ አለም ገብረ ሚካኤል ከሰሜን ምዕራብ ታህታይ አድያቦ ወረዳ ባድመ ቀበሌ 17 ገብረ ሂወት ጉዕሽ ገብረ መስቀል ከማዕከላዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ ራማ ቀበሌ ሰፈር 03 18 መብርሃቶም ሃዲሽ ተክለ ከሰሜን ምዕራብ ዞን ላእላይ አድያቦ ወረዳ አድክልተ ቀበሌ ገዛ ስቃ ከተባለው መንደር 19 ክብሮም ተሾመ ክንፈ ከማዕከላዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ ማይ ወዳምበራይ ቀበሌ አዲገባ እና

 ሌሎችም ሲሆኑ በተለይ ፍስሃ ገብረ ስላሴ ስርዓቱን እንዲቃወም ያስገደደውን ምክንያት ሲናገር ስርዓቱ አገዛዙን ለማስረዘም ሲል ብድር በመስጠት ሞዴል ተሸላሚ ናችሁ ብሎ ሲያበቃ እንደገና ተገልብጦ በተላላኪዎቹ ተጠቅሞ አቶ ገብረእግዜር ጋዕሲ የተባለውን ንፁህ ዜጋ የቀፎ ንቡን በማላታይን ሲያጠፉ በማየቱ መሆኑን ገልፀዋል። ሰልጣኝ ጉዕሽ ሃይሉ ገብረስላሴ በበኩሉ ባለፈው ምርጫ አረና የተባለውን ድርጂት የመረጡ ዜጎች ከመሬት እደላ እንደተከለከሉ ከገለፀ በኋላ ቀደም ሲልም በብድር የተሰጡ ወገኖችን ጊዜው ሳይደርስ መልሱ እያሉ እያሰሩ ያሰቃዩአቸው እንደነብር ገልፀዋል።

tirsdag 22. september 2015

መንግሥት እርዳታ ፈላጊነቱን በይፋ አመነ

ከይድነቃቸው ከበደ
መንግሥት እርዳታ ፈላጊነቱን በይፋ አመነ !” መባሉ  ምን አዲስ ነገር አለው ፣ለዛውም የኢትዮጵያ መንግስት በማለት እንዳትሸወዱ ! የህውሓት/ኢህአዲግ ገዥው መንግሰት የምግብ እርዳት እና ድርቅን ለመከላከል ፣ሞቼ ነው በቁሚ የምለምነው ሲል ነበር፡፡ በአገራችን በኢሊኒኖ ምክንያት በተከሰተው ድርቅ፣ በሰው ሕይወት እና በእንስሳት  ላይ እየደረሰ ያላው አደጋ አሳሳቢነት

አስመልክቶ ፤የመንግሰት ኮሚኒኪሽን ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሬዲዋን ሁሴን “ሰባት ሞቶ ሚሊይን ብር በጀት የያዝን በመሆኑ ችግሩን መቆጣጠር እንችላለን ፣ ምንም አይነት የዉጪ እርዳታ አያስፈልገንም፣ የዚህን ያህል አሳሳቢ ደረጃ አልደረሰም” በማላት የመንግስታቸውን አቋም ነሐሴ ወር 2007 ዓ.ም መግለፃቸው የሚታወስ ነው፡፡ አቶ ሬዲዋን መግለጫውን በሰጡ ሳምንት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ   ዳያስፓራ ነን ባዩችን በሚሊኒየም አዳራሽ ሰብስበው “አሁን በክረምቱ በምስራቁ የሀገራችን ክፍል ከላይ እስከታች ድርቅ አጋጥሞናል……፣ወዳጆችን በዚህ ሰዓት ተሯሩጠው መጥተው እርዳታ ይሰጡን ነበር ፣አሁን እስኪ እናያቸዋለን በማለት ዳር ነው የቆሙት……. ፣አቅማችን እየጎለበተ ስለመጣ እራሳችን ገዝተን እራሳችን አቅርበን ህዝባችን እንዳይራብ እናደርጋለን ።” በማለት በድፍረት ተናግረዋል፡፡ይህ የድፍረት ንግግራቸው በቀጥታ ስርጭት በኢቲቪ

ተላልፏል፡፡ “ጉድ እና ጅራት ….” እንደሚባለው ሆነና አቶ ሬዲዋን ሁሴን ዛሬ ማለትም መስከረም 10 ቀን 2008 ዓ.ም የመንግስታቸውን አቋም ሲገልፁ ፤በኢሊኒኖ ምክንያት በተፈጠረው የዝናብ እጥረት የተጎዱ ዜጎች ቁጥር ቀድሞ ከተገመተው 2ነጥበ9 ሚሊየን ህዝብ በማሻቀብ ከ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ደርሷል፣ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የተጠበቀው ድጋፍ በሚፈለገው መልኩ አልተገኘም፣ይህም በመሆኑ ለልማት ከያዘው በጀት እንጠቀማለን “አሉ”፡፡ ይሄ መንግሥት ነኝ ባይ ህውሓት/ኢህአዲግ በዚህ ደረጃ፣ በአገር እና በህዝብ ላይ መቀልዱ የወደፊት የታሪክ ተጠያቂነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ፤አሁን ላይ የሥርዓቱ ውድቀት እየተፋጠነ ለመምጣቱ ከምክንያቶች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ “የተራበ ህዝብ መሪውን ይበላል” መባሉ ቀርቶ መሆኑ ይመጣ ይሆን ? መልሱን አብረን እንጠብቃለን፡፡ አሁንም ግን በአገራችን በሰሜን ምስራቅ እና በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ መጠኑ

እየጨመረ መጥቷል፡፡ በተለይ በእንስሳት ላይ እየደረሰ ያለው አደጋ እጅግ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል፣ ወገኖቻችን በምግብ እጥረት እየተሰቃዩ ለሞት እየተዳረጉ ነው፡፡የችግሩ አሳሳቢነት ደረጃ ከፍ ማለቱ ገዥው ህውሓት/ኢህአዲግ መንግስት ለመሸሸግ አልቻልም፡፡ በግልፅ ቋንቋ “ከውጭ የሚጠበቀው ድጋፍ ካልተገኘ መንግስት ለልማት የመደበውን ሀብት በማዞር ለዜጎች ምግብና ለእንስሳት የሚሆን መኖ ለማቅረብ እግደዳለው” በማላት በአቶ ሬዲዋን ሁሴን በኩል ገልፆዋል፡፡እንዲህ አይነቱ መንግስታዊ ማስፈራራት ምክንያቱን እና ውጤቱን ለመገመት ቀላል ነው፡፡ ከአንድ ወር በፊት እኔ በግሌ እንዲሁም የተለያዩ ግለሰቦች እና ተቋማት፣ ከመገናኛ ብዙሃን ኢሳት እና የውጪ ሃገር ሚዲያዎች፣ የችግሩን አሳሳቢት በተቻለ አቅም ለመግለፅ ተችሎአል፡፡

በተለይ መንግሰት “ሰባት ሞቶ ሚሊይን ብር በጀት የያዝን በመሆኑ ችግሩን መቆጣጠር እንችላለን ፣ ምንም አይነት የዉጪ እርዳታ አያስፈልገንም፣ የዚህን ያህል አሳሳቢ ደረጃ አልደረሰም” በማላት በድፍረት ሲናጋር ፣ይሄ ነገር ተገቢ አይደለም ፣የሚመጣው ነገር አይታወቅም ከአጉል ቀረርቶ እና ባዶ ሽለላ መቅረት አለበት፡፡ ስለዚህም ከችግሩ አሳሳቢነት እና ወደፊት ከሚያስከትለው አደጋ አንጻር፣ ለዓለም አቀፍ ማህብረሰብ እንዲሁም ለለጋሽ ድርጅቶች እርዳታ መጠየቅ አለበት፡፡በማለት የችግሩ አሳሳቢነት ለገለፁ ለአገር ወዳድ እና ተቆርቋሪ ኢትዮጵያዊያን የተሰጠው ምልሽ “አቅማችን እየጎለበተ ስለመጣ እራሳችን ገዝተን እራሳችን አቅርበን ህዝባችን እንዳይራብ እናደርጋለን ።

” በማለት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በአደባባይ ተዘባበቱ፡፡ ይሄን በተናገሩ ሁለት ወር ሳይሞላ የሚረዳን አጣን፣ለዚህ ጉዳይ የያዝነው ገንዘብ እያለቀ ነው፤ከዚህ በኋላ ለልማት የያዝነውን ገንዘብ ነው የምንጠቀመው፤ሲሉ መስማት ያሳፍራል፡፡ነገ ደግሞ ለልማት የያዝነው ገንዘብ ድርቁን ለመከላከል ያወጣነው ስለሆነ፣ አገር የምናስተዳድርበት ገንዘብ የለንም ይሉ ይሆን ? ያኔ ጊዜ “የተራበ ህዝብ መሪውን ይበላል” መባሉ እርግጥ ይሆናል፡፡ ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!
Redwan

mandag 21. september 2015

የኦጋዴን ነፃነት ግንባር 2 ከፍተኛ አመራሮች በአልሸባብ አንገታቸው ተቀልቶ ተገደሉ * ግንባሩ የኢትዮጵያ መንግስት እጅ አለበት ሲል ከሰሰ

 የኦጋዴን ነፃነት ግንባር ሁለት ከፍተኛ አመራሮቼ ከሶማሊያ ባይዶዋ ወደ ኦጋዴን ሲጓዙ በአልሸባብ ታጣቂዎች ታፍነው ተወስደው ተገደሉብኝ ሲል ከሰሰ። ለዚህም ተጠያቂው በስልጣን ላይ ያለው የኢትዮጵያ መንግስት ነው ብሏል::

 የኦጋዴን ነፃነት ግንባር ከቅርብ ወራት ወዲህ በጠቅላላው ከአስር የማያንሱ አባሎቼ ሶማሊያ ውስጥ በአልሸባብ ታጣቂ ቡድን ታፍነው ከተወሰዱ በኋላ አንገታቸው ታርዶ ተገድለውብኛል ብሏል ።

 እንደ ግንባሩ ክስ ከሆእ የኢትዮዽያ መንግስት የደህንነት ሰራተኞች በስውር ከአልሸባብ ንዑስ ቡድን ጋር በመገናኘት ግድያው እንዲፈፀም አሲረዋል። በስልጣን ላይ ያለው የኢትዮጵያ አገዛዝ እስካሁን ምንም ዓይነት ምላሽ ባይሰጥም ከዚህ ቀደም መንግስት የኦጋዴን ነፃነት ግንባር ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት ያለው አሸባሪ ድርጅት ነው ሲል መክሰሱ ይታወሳል::

 አማጺው ቡድንም ሆነ መንግስት እርስ በራሳቸው ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት አላቸው እየተባባሉ መካሰሳቸው ለብዙዎች ግርምታን ፈጥሯል;;

torsdag 17. september 2015

ግንቦት 7ን ሊቀላቀሉ ነው ተበለው የተያዙት እነብርሃኑ ለህዳር 21 ተቀጠሩ ‹‹የሽብር ተከሳሽ በመሆናችን ህክምና ተከልክለናል›› ተከሳሾቹ

በነገረ ኢትዮጵያ

 ሪፖርተር የኢትዮ-ኤርትራ ድንበርን አቋርጠው ኤርትራ የሚገኘውን ግንቦት ሰባት የተባለ በተወካዮች ም/ቤት ሽብርተኛ የተባለ ድርጅትን ሊቀላቀሉ ሲሄዱ ተይዘዋል በሚል የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ በድጋሜ ለብይን ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ ዛሬ መስከረም 5/2008 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የቀረቡት ብርሃኑ ተ/ያሬድ፣ እየሩሳሌም ተስፋው፣ ፍቅረማርያም አስማማው እና ደሴ ካህሳይ በድጋሜ ለህዳር 21/2008 ዓ.ም ብይን ለመስማት ተቀጥረዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ዛሬ የአቃቤ ህግን ምስክርና የሰነድ ማስረጃ መርምሮ ብይን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቅ ነበር፡፡ ተከሳሾቹ በማረሚያ ቤት እየደረሰብን ነው ያሉትን አቤቱታ ለፍርድ ቤት ያሰሙ ሲሆን፣ በተለይ ‹‹የሽብር ተከሳሽ ስለሆንን ብቻ ህክምና ተከልክለናል፤ በማንነታችን ጥቃት እየተፈጸመብን ነው›› ሲሉ ችሎት ፊት ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም ፍርድ ቤቱ እነዚህን ችግሮች በተመለከተ ለማረሚያ ቤቱ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ጠይቀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የማረሚያ ቤት ተወካይ ያለውን በማስጠራት ‹‹ማስታወሻ ያዝና አጣራ›› በማለት አልፎታል፡፡ በሌላ መዝገብ የሽብር ተከሳሽ የሆነው በአርባ ምንጭ የሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪ በፍቃዱ አበበ በበኩሉ ቀሪ የመከላከያ ምስክሮቹን ለማሰማት ለህዳር 16/2008 ዓ.ም ተቀጥሯል፡፡
birhanu tekle

fredag 11. september 2015

የዘ-ሐበሻ የዓመቱ ምርጥ ሰው – ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ * አህመዲን ጀበል፣ ቴዲ አፍሮና ገንዘቤ ዲባባም በየዘርፉ አሸንፈዋል

 

ዘ-ሐበሻ ድረገጽ የዓመቱ ምርጥ ሰው በሚል አንባቢዎቿን በማሳተፍ ምርጫ ስታደርግ ይህ ለአምስተኛ ጊዜ መሆኑ ነው:: እስካሁን መምህር የኔሰው ገብሬ; ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ; ታጋይ አንዱአለም አራጌና አብርሃ ደስታ በተከተታይ ዓመታት የአመቱ ምርጥ ሰው ሽልማቶችን አግኝተዋል::
ዘንድሮ ለአንድ ወር ያህል ዘ-ሐበሻ የሕዝብ ድምጽን በስልክ; በቫይበር; በፌስቡክ; በኢሜይል እና በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ስትቀበል ነበር:: በሺህዎች የሚቆጠሩ የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች የ2007 የዓመቱ ምርጥ ሰው ይሁንልኝ ሲሉ ድምፃቸውን የሰጧቸው ሰዎች በርካቶች ነበሩ:: የዘ-ሐበሻ ኤዲቶሪያል ቦርድ ሁሉም የሕዝብ ድምጽ ቆጠራ ካደረገ በኋላ የሚከተሉት 10 ሰዎች ከፍተኛውን ድምጽ አግኝተዋል::
1ኛ. አህመዲን ጀበል
2ኛ. አንዳርጋቸው ጽጌ
3ኛ. ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
4ኛ. አቶ ነአምን ዘለቀ
5ኛ. አቡነ መቃሪዮስ
6ኛ. ገንዘቤ ዲባባ
7ኛ. ቴዲ አፍሮ
8ኛ. ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
9ኛ. ወይንሸት ሞላ
10ኛ. ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ናቸው::
ከ10ሩ እጩዎች ውስጥ ከፍተኛውን ድምጽ ያገኙትን በየዘርፉ ከፋፍለን አቅርበናቸዋል:: በዚህም መሠረት የዘ-ሐበሻ የዓመቱ ምርጥ ሰው የሚከተሉት ናቸው::
nega
የዓመቱ ምርጥ ሰው ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

በዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ዘንድ ከፍተኛውን ድምጽ ያገኙትና የአመቱ ምርጥ ሰው የተሰኙት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ናቸው:: “ካሁን በኋላ ሰዎችን ሰብስቤ ማውራት ላቆም ነው” ባሉ በሁለተኛው ቀን ለነፃነታችን እየወደቅን እንታገላለን ብለው ጥሩ ኑሯቸውን ትተው በርሃ ወርደዋል::
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በ1958 ዓ.ም ደብረዘይት አካባቢ የተወለዱ ሲሆን ምንም እንኳ የተወለዱት ከሃብታም ቤተሰብ ቢሆንም አስተዳደጋቸው ግን ራሳቸውን ችለው እንዲያድጉ እየተማሩ ነው:: ይህንን ፕሮፌሰር ብርሃኑ በሃገር ቤት ለሚታተም ጋዜጣ በ1997 ዓ.ም ሲናገሩ “አባቴ ነጋ ቦንገርን ልጅ እያለሁ ሲኒማ ራስ ጥሩ የህንድ ፊልም ወጥቶ ለማየት ሳንቲም ስጠኝ ስለው ራስህ ሰርተህ ስታገኝ ትገባለህ ይለኝ ነበር” (ቃል በቃል የተወሰደ አይደለም) ይላሉ:: አባታቸው አቶ ነጋ ቦንገር ሲያሳድጓቸው በማሞላቀቅ ሳይሆን ራሳቸውን መቻል እንዳለባቸው በማስተማር ነበር:: ይህም ለፕሮፌሰሩ ስኬት ጠቅሟቸዋል::
ፕሮፌሰሩ ወደ ሳሪስ አካባቢ ግሎባል የሚባል ደረጃውን የጠበቀ ሆቴል ከፍተው የነበረ ቢሆንም በሽብርተኛነት በኢትዮጵያ መንግስት ከተከሰሱ በኋላ ይህ ሆቴል ተወርሷል::
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ወደ ትግሉ ዓለም የገቡት ገና የ17 ዓመት ወጣት በነበሩበት ወቅት ነው:: ያን ጊዜ ከኢህ አፓ ጋር በሚሰሩበት ወቅት ብዙ ምስጢሮች ባይነገራቸውም መኪና ይነዱ ስለነበር የኢሕአፓ አመራሮችን ከቦታ ቦታ በመውሰድ አገልግሎት ይሰጡ እንደነበር አብረዋቸው ይታገሉ የነበሩ ሰዎች ለዘ-ሐበሻ ይናገራሉ:: እንዲሁም ፕሮፌሰር ብርሃኑ በወቅቱ በኢህአፓ አመራሮች እርምጃ ሊወሰድባቸው ሲል በሱዳን በኩል አምልጠው እንደጠፉ ከታሪካቸው ያሰባሰብነው መረጃ ያመለክታል::
በሱዳን በኩል አድርገው አሜሪካ ከገቡም በኋላ ትምህርታቸው ላይ በማተኮር በከፍተኛ ማዕረግ የተመረቁ ሲሆን ኢህአዴግ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ ኢትዮጵያ ጠቅልለው በመግባት ሃገራቸውን ማገልገል ጀምረዋል:: ፕሮፌሰር በቅድሚያ ኢሕ አዴግን ለመለወጥ አዳዲስ ሃሳቦችን ቢያቀርቡም ኢህ አዴግ ግን የሚለወጥ ድርጅት ሊሆን አልቻለም:: በዚህም ተስፋ ሳይቆርጡ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች ማህበርን በመመስረት ብዙ አስተዋጽኦ አበርክተዋል::
ከምርጫ 2007 በፊት ፕሮፌሰር ብርሃኑ እና ፕሮፌሰር መስፍን በብሄራዊ ሎተሪ አዳራሽ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በመሰብሰብ ስለ ነፃነትና መብት ምንነት በሰፊው በሕዝባዊ ስብሰባ ይሰብኩ ነበር:: በርካታ ተከታዮችን እያፈሩ መምጣታቸው ያስፈራው መንግስት ሁለቱንም ታዋቂ ፖለቲከኞች ሕገመንግስቱን በኃይል ለመናድ በሚል አስሮ ሲያንገላታቸው ቆይቷል::
ምርጫ 1997 እየቀረበ ሲመጣ በየወሩ በሂልተን ሆቴል ኢትዮጵያ በ2020 በሚል ምሁራን እየተሰባሰቡ ኢትዮጵያ በ2020 ዓ.ም ምን መሆን እንዳለባት እንዲመካከሩ ያደርጉ የነበሩት ፕሮፌሰር ብርሃኑ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር በነበሩበት ወቅት ደመወዛቸውን ለችግረኛ ተማሪዎች ያከፋፍሉ እንደነበር ይነገራል::
ፕሮፌሰሩ ቀስተዳመና የተሰኘ ፓርቲ አቋቁመው ከኢድሊ ጋር በመተባበር ታላላቆቹን መኢአድና ኢዴፓ-መድህንን አንድ በማድረግ ቅንጅት ፓርቲ እንዲፈጠርና በምርጫ 97 ኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ ለውጥ እንዲፈጠር ጥረው ነበር:: በዚህም የአዲስ አበባ ከንቲባ ሆነው በሕዝብ ተመርጠው የነበረ ቢሆንም መንግስት በሃይል ያመጣሁትን ስልጣን በስኪብርቶ አለቅም በሚል የፖለቲካውን ምህዳር ዘግቶታል::
በዚህ ምርጫ ሰብሰብም ፕሮፌሰር ብርሃኑ እስር ቤት ተወርውረው ነበር:: ከ እስር ቤት ከወጡ በኋላም ሰላማዊ ትግል ብቻውን ለውጥ አያመጣም በሚል ወደ ሁለገብ ትግል በመሸጋገር ግንቦት 7ን መሰረቱ:: ግንቦት ሰባት በአሁኑ ሰዓት ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር እየተዋሃደ ትግሉ ወደ አንድ አቅጣጫ እንዲሸጋገር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ሰርተዋል:: ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ2007 የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች የአመቱ ምርጥ ሰውን ክብር ስላገኙ እንኳን ደስ ያለዎ::
genzebe 1
የዓመቱ ምርጥ ስፖርተኛ – ገንዘቤ ዲባባ
የ23 ዓመቷ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ የዘ-ሐበሻ የዓመቱ ምርጥ ስፖርተኛ ሆናለች:: ገንዘቤ በ2007 ዓ.ም አመርቂ የሆነ ውጤትን አስመዝግባለች:: ባለፉት 8 ዓመታት የአትሌትነት ቆይታዋም በርካታ ድሎችን አጣጥማለች:: ገንዘቤን ዘንድሮ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ በርካታ ትልቅ ስፖርተኞች መካከል የሚያደርጋት በአንድ ሳምንት ውስጥ ሁለት የዓለም ክብረ ወሰኖችን መስበሯ ነው::
ባለፈው ጥር ላይ በስዊድን ስቶክሆልም ከ1993 ዓ.ም ጀምሮ ያለተሰበረውን የ3 ሺህ ሜትር ሩጫ ሪከርድ ሰብራለች:: እንዲሁም ይህን ድል ካጣጣመች ከ4 ቀን በፊትም እንዲሁ በ1500 ሜትርን ሪከርድ ሰብራለች:: አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው በፓሪስ የአምስት ሺህ የዳይመንድ ሊግ ውድድር በአንደኝነት ያጠናቀቀችውም በዚሁ በተሰናባችሁ 2007 ዓመት ሰኔ ወር ላይ ነበር:: ሰኔ 27፣2007 ምሽት በተደረገው 8ኛው ዙር የዳይመንድ ሊግ ውድድር ገንዘቤ ርቀቱን በ14 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ ከ41 ማይክሮ ሰኮንድ በመግባት ነበር ያጠናቀቀችው፡፡ ገንዘቤ የእህቷን ጥሩነሽን ክብረወሰን ትሰብራለች ተብሎ ቢጠበቅም ሳይሳካላት ቀርቷል። የጥሩነሽ ክብረ ወሰን ለመስበር 4 ሰከንድ ብቻ ነበር የቀራት።
አትሌት ገንዘቤ ዲባባ ሞናኮ ውስጥ በተካሄደ የዳይመንድ ሊግ ውድድር በ 1500 ሜትር አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ያስመዘገበችውም በዚሁ ዓመት ሰኔ ወር ላይ ነበር::
ገንዘቤ በዚሁ በተሰናባችሁ 2007 ዓ.ም ቤጂንግ ላይ በተደረገው የዓለም ሻምፒዮና ላይ አንድ ወርቅ እና አንድ ነሃስ ሜዳሊያ ለሃገሯ ያስገኘች ጠንካራ አትሌት ናት:: የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች የዓመቱ ምርጥ ስፖርተኛ በሚል መርጠዋታል:: እንኳን ደስ ያለሽ::
teddy afro
የአመቱ ምርጥ አርቲስት – ቴዲ አፍሮ
ቴዲ አፍሮ “ሚስማር በመቱት ቁጥር ይጠብቃል” እንደሚባለው ሆኗል:: በመንግስት የሚደርስበት ጫና ይበልጥ ተወዳጅ እንዲሆን እያደረገው ነው:: በዚሁ ዓመት መጀመሪያ አካባቢ ላይ 70 ደረጃ የሚለውን ነጠላ ዜማ ከለቀቀ ወዲህ የሕዝብ ጆሮን አግኝቶ ነበር:: ጥቅምት 3 ቀን 2015 ዓ.ም ወደ ውጭ ሃገር ለኮንሰርት ዝግጅት ላይ በነበረበት ወቅት ድንገት ፖሊሶች አስረውት ነበር:: ምክንያታቸውም ከዚህ ቀደም ቴዲ አፍሮ- ከዓመታት በፊት የጎዳና ተዳዳሪ ገጭቶ ገድሏል የተባለበት ቢኤምደብሊው የቤት አውቶሞቢል ቀረጥ ሳይከፈልበት የገባ ነው በሚል በገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን መርማሪ ቡድን በቁጥጥር ሥር ዋለ:: በ30 ሺህ ብር ዋስም ተለቀቀ:: የሚገርመው ይህ ክስ ከብዙ ዓመታት በፊት መመስረቱ ብቻ ሳይሆን መኪናው በአሁኑ ወቅት በአርቲስቱ እጅ አለመኖሩም ጭምር ነው::
ቴዲ አፍሮ በዚህ ዓመት ‘አልሄድ አለ’ እና ‘ኮርኩማ’ አፍሪካ የተሰኙ መል ዕክት ያላቸውን ተወዳጅ ዘፈኖቹን አበርክቶልናል:: ሁለቱም ዘፈኖቹ እጅግ ተወዳጅ ሆነውለታል::
በዚህ ዓመት በቴዲ አፍሮ ላይ ከፍተኛ ጫና የተደረገበት ሲሆን ከዚህም ውስጥ የአውሮፓው ኮንሰርቱ እንዲስተጓጎል የተደረገበት ነው:: ከሃገር ሊወጣ ሲል ፓስፖርቱን ከሕግ ውጭ በደህንነቶች የተቀማው ቴዲ በአውሮፓ ማቅረብ የነበረበትን ኮንሰርት በዚህ ሳቢያ በመሰረዙ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል:: በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ሳይባል ደህነነቶች ‘ልክ እናስገባሃለን’ በሚል ፓስፖርቱን የተቀማው ቴዲ እየደረሰበት ያለውን ጫና ዘፈኑ ገልጾታል እየተባለ ነው:: “አልሄድ አለ” የሚለው ነጠላ ዜማውም ለራሱ የሰራው ነው እየተባለ ይነገራል::
ቴዲ በአዲስ ዓመት ዋዜማ በአዲስ አበባ ላፍቶ ሞል ሊያቀርበው የነበረው ኮንሰርቱ በፖሊስ ምክንያት እንዲሰረዝ ተደርጓል:: ለስርዓቱ ቅርብ የሆኑት ማዲንጎ አፈወርቅ እና አስቴር አወቀ ኮንሰርት እንዲያቀርቡ ሲፈቀድ ቴዲ በመከለከሉ የተቆጡት ኢትዮጵያውያን ኮንሰርቱን በፌስ ቡክ ለማድረግ ቆርጠው ተነስተዋል::
ቴዲ አፍሮ በዘ-ሐበሻ አንባቢዎች የአመቱ ምርጥ ሰው ሽልማትን አግኝቷል:: እንኳን ደስ ያለህ::
ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
የዓመቱ ምርጥ ጋዜጠኛ – ሃብታሙ አሰፋ
የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች የዓመቱ ምርጥ ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ ሆኗል:: የኢትዮጵያ ነፃ ጋዜጠኞች ማህበር ከፍተኛ አመራር የነበረውና በሃገር ቤትም እንደነ መብረቅ/መብሩክ; ሩሕ; ሪፖርተር እና ሌሎችም ሚድያዎች ውስጥ ሲሰራ የነበረው ጋዜጠኛ ሃብታሙ በስደት ካይሮ ከቆየ በኋላ ወደ አሜሪካ ላስቬጋስ ከተማ ኑሮውን ካደረገ በኋላ ሕብር የተሰኘች ራድዮ መስርቶ ሙያውን ቀጥሎበታል::
ሃብታሙ አሰፋ ካለምንም የሕዝብ እርዳታ; በራሱ ጥረት በየሳምንቱ የሚያዘጋጃት ሕብር ራድዮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳጅ ሆና በአሁኑ ወቅት እንደ አማራጭ የመረጃ ምንጭነት ተቀምጣለች:: ከኪሱ እያወጣ በየሳምንቱ የተለያዩ ጉዳዮችን በማንሳት ከሃገር ቤትም ሆነ ከውጭ ሃገር ቃለምልልሶችን በማቅረብ ለኢትዮጵያ ህዝብ መረጃዎችን በማድረስ አኩሪ ሥራ ሰርቷል::
ሕብር ራድዮ በ2007 ዓ.ም እድገት ካሳዩ ሚዲያዎች መካከል አንዷ ስትሆን በድረገጽ; በሳውንድ ክላውንድ; በዩቲዩብ; በጎግል እና በአፕል አፖች እንዲደመጡ ጋዜጠኛ ሃብታሙ ትልቁን ሥራ ሰርቷል::
ከራድዮው ሥራ በተጨማሪም በተለይ ለተሰደዱና ለተጎዱ ጋዜጠኞች ሞራል በመስጠት; በማስተባበር ከጎናቸው በመቆም ያደረገው አስተዋጽኦ ይጠቀስለታል::
ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋና ሕብር ራድዮ ሕዝቡ በቁሳቁስ ሊያግዛቸው ከቻለ እስካሁን ከሰሩት የበለጠ ሥራዎችን መሥራት እንደሚችሉ በየሳምንቱ እሁድ የሚያቀርቡት ፕሮግራሞች ይነግሩናል::
የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች የ2007 የዓመቱ ምርጥ ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ – እንኳን ደስ ያለህ::
hqdefault
የዓመቱ ምርጥ የሃይማኖት መሪ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል
ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በ1972 አ.ል በጂማ ከተማ ተወለደ፡፡ ኡስታዛችን ለቤተሰቦቹ የአራተኛ ልጅ ሲሆን ከህፃንነቱ ጀምሮ በሰዎች ዘንድ ፍፁም ዝምተኛና በፀባዩ ተወዳጅ ነበር፡፡ ኡስታዝ አህመዲን ከሰባ ወንድምና እህቶቹ ለወላጆቹ የተለየ ፈቅር ያለው ሲሆን በተለይ ለእናቱ ያለው ፍቅርና ታዛዥነት ከሌሎቹ ለየት ያደርገዋል፡፡
ኡስታዝ እድሜው ለትምህርት ሲደርስ 1ኛ ደረጃ ትምህርቱን ቄራ መለስተኛ ት/ቤት ይማራል፡፡ ኡስታዝ ከትምህርት ይልቅ የ mechanic ሙያን ይወድ ስለነበር ወደ እዚያው ያደላል፡፡ በዚህም የአስረኛ ክፍል ማትሪክስ ውጤት በመድገሙ አባቱ ከሙያ ትምህርቱ እንዲቆም በማድረግ ሙሉ ትኩረቱን ወደ መደበኛው ት/ት እንዲያደርግ ይመክሩታል፡፡ እናም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ጂማ high school እስከ 12ኛ ድረስ በመማር በከፍተኛ ውጤት አጠናቀቀ፡፡ ከፍተኛ ትምህርቱን በአዲስ አበባ 4 ኪሎ campus በ chemistry የትምህር ክፍል የመጀመሪያ ዲግሪውን የያዘ ሲሆን በመቀጠልም በ Arabic and litrecher ማስተርስ ዲግሪውን ይዟል፡፡
ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በ campus ውስጥ ለ6 አመታት የቆየ ሲሆን በነዚህ አመታት ውስጥ ከመደበኛ ትምህርቱ ጎን ለጎን የሙስሊም ተማሪ ጀመዓ አሚር በመሆን አገልግሏል፡፡ እንዲሁም ሙስሊሙ ህብረተሰብ ዘንድ ታዋቂና ተወዳጅ ያደረገውን “ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች” የሚለውን መፅሃፍ በግቢ ቆይታው አዘጋጅቷል፡፡ ኡስታዛችን በ6 ኪሎ campus በ history ማስተርሱን ሰርቷል፡፡ ከዚያ በኋላ ‹በሙስሊሞች ጉዳይ መፅሄት› እና በተለያዩ ድርጅቶች ሲሰራ ቆይቷል፡፡ በዚህም ብዙ መፅሃፎችን ለህትመት አብቅቷል፡፡ በራሱ ካሳተማቸው ውስጥ ‹የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የጭቆናና የትግል ታሪክ፤ የሴቶች መብት በመፅኃፍ ቅዱስና በቁርአን እንዲሁም 303 በክርስትና ዙርያ የሚነሱ ጥያቄዎች› የሚሉት ይገኙበታል፡፡ እንዲሁም ኡስታዝ አህመዲን ጀበል አሁን ላለው ኡማ እና ለቀጣዩ ትውልድ ብዙ መፃህፍቶችን በመተርጎም ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡
ኡስታዝ አህመዲን ጀበል የመጀመሪያ የዲን ቂርአቱን በጂማ ፍትህ መስጂድ በተለያዩ ኢማሞች ቀርቷል፡፡ እንዲሁም አዲስ አበባ እያለ በኡስታዝ ሸኽ ሀሰን ሀሚዲን እና ኡስታዝ ሀሚድ ሙሳ የተለያዩ የዲን ትምህርቶችን የቀሰመ ሲሆን በራሱም የተለያዩ ኪታቦችን በማገላበጥ እውቀቱን አዳብሯል፡፡
በአጠቃላይ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ከህፃንነቱ አንስቶ አሁን እስካለው የእድሜ ደረጃ ድረስ በባህሪው እጅግ ተወዳጅና የተከበረ ግለሰብ ነው፡፡ ለሰዎች ያለው አክብሮት፣ ለተቸገሩ ያለው አዘኔታ፣ ለታላቆቹ ያለው ታዛዥነትና ለታናናሾቹ ያለው አክብሮት በስነ-ምግባሩ የላቀ ያደርጉታል፡፡ ሲናገር በእርጋታ፣ ሲያስረዳ የማይቆጣ፣ ክርክርና ጥላቻን ከቀልቡ ያራቀ ድንቅ ግለሰብ ነው፡፡
ይህ ድንቅ የኢስላም ልጅ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ከአስራ ሰባቱ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች አንዱ ሲሆን ለሙስሊሙ ኡማ በትምህርት መልክ ሲሰጥ የነበረውን ዛሬ ላይ በተግባር እያሳየ ይገኛል፡፡ ኡስታዝ አህመዲን አሁን በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚገኝ ሲሆን በረመዳን ወር ላይ ከፍተኛ የሆነ ስቃይንና ፊትናን ቀምሷል፡፡ ኡስታዝ ዛሬ ለሁላችንም የሚሆን አርአያ መምህራችን ነው፡፡ ፈተና በመጣ ሰአት ከራሱ የበለጠ ለሙስሊሙ ኡማ የሚጨነቅ፣ ከነፍሱ ይበልጥ ለዲኑ የሚጨነቅና ከህይወቱ በላይ ኢስላምን የሚወድ ድንቅ መምህር፡፡ ይህንንም ዛሬ በተግባር እያሳየ ይገኛል፡፡ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በአንድ ወቅት እንዲህ ሲል ተናግሮ ነበር….
“ታሪክ ሰሪ እንጂ ታሪክ አንባቢ መሆን የለብንም…!”
አዎ! ዛሬ እርሱ ታሪክ ሰሪ ሁኗል፡፡ በኢስላም ላይ ያንዣበበውን አደጋ በመጋፈጥ፤ ለልጆቻችን ኢስላምን እንጂ አናወርስም በማለት የመጀመሪያው ድንቅ ሰው ነው፡፡ ማንም ያልሆነውን ስም ቢለጥፉበትም (አሸባሪ፣ አክራሪ፣ መንግስት ለመገልበጥ የሚሮጥ፣…..ሌላም ሌላም) እያሉ ቢጠሩትም ይህን አለመሆኑን ግን ራሳቸው ጠሪዎቹ ያውቁታል፡፡ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ሰላምን ተምሮ ሰላምን ያስተማረ፣ ሰላምን አውቆ ስለ ሰላም ያሳወቀ፣ ሰላምን በማሻተማር ላይ ህይዉን የመራ ድንቅ የኢስላም ልጅ ነው፡፡ በሰላም አደፍራሾች በተደበዱ ጊዜም፣ ኢስላም ላይ ዘመቻ በተከፈተበት ጊዜም፣ ጠላቶች በሃይል ኢስላምን ካልለቀክ እያሉ በሚያሰቃዩበት በዚህ በጭንቅ ጊዜም ሰላምን እንጂ ሌላን ያልሰበኩ ባለ ድንቅ ስብእና::
አህመዲን ጀበል እንኳን ደስ ያለህ::
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46599#sthash.VFpGzpuV.dpuf

onsdag 9. september 2015

የኢትዮጵያ አገር አንድ በዴሞክራሲ የጋራ ንቅናቄን ምስረታ በማስመልከት የወጣ ድርጅታዊ መግለጫ

 (ማክሰኞ ጳጉሜ 3 2007 ዓ.ም) የኢትዮጵያ ህዝብ የአገሩን ሉአላዊነት እና አንድነት አስከብሮ የኖረ ብቻ ሳይሆን አፍሪካዊያን ወንድሞቹና እህቶቹ ከቅኝ አገዛዝ ነፃ እንዲወጡ የራሱን አስተዋፅኦ ያደረገ ጀግና ህዝብ ነው፡፡

Birhanu
ሆኖም ይህ ጀግኛ ህዝብ ከአብራኩ በወጡ ገዥዎች ነፃነቱ ተገፎ፣ መብቶቹ ተረግጠው የመከራ ኑሮ እየገፋ አያሌ ዘመናት ኖሯል፡፡ ይህ የመከራና የሰቆቃ ኑሮ ዛሬም አላበቃም፣ እንዲያውም “ከጭቆና ነፃ አወጣንህ” እያሉ የሚሳለቁበት ግፈኛ ገዥዎች የጫኑበትን የስቃይ ቀንምበር ተሸክሞ የውርደት ኑሮ እየኖረ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ የአገር ውስጥ ገዥ መደቦች የጫኑበትን የስቃይና የመከራ ቀንበር ሰባብሮ ለመጣል፣ ፍትህ፣ ሰላምና እኩልነት የሰፈነበት ኑሮ ለመኖር ዓመታት የፈጀ ከፍተኛ መስዋዕትነት የተከፈለበት ትግል አድርጓል፡፡ እስካሁን ትግሉን በአሸናፊነት ተወጥቶ የናፈቀውን ፍትህ፣ ሰላምና ብልፅግና ማግኘት አልቻለም፡፡

 ለዚህ በርካታ ምክንያቶች ያሉት ቢሆንም ዋናው ምክንያት ህዝባዊ ትግሉን በተባበረና በተቀናጀ መልክ መስራት አለመቻሉ ነው፡፡ ይህ ስር የሰደደ ያለመተባበር ችግር በህወሓት/ኢህአዴግ ዘመን ተባብሷል፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ ሆን ብሎ የፈጠረው የመለያየት እና የከፋፍለህ ግዛው ፖሊሲ ለጋራ ድል አብሮ መታገልን በጭራሽ አስቸጋሪ ጉዳይ አድርጎት ቆይቷል፡፡ ዛሬ ግን ይህ ሁኔታ ተቀይሯል፡፡ በጋራ አብሮ በመታገል የሚገኘው ዘርፈ ብዙ ጥቅም የገባቸውና ካለፈው ተደጋጋሚ የታሪክ ስህተት የተማሩ፣ በአገራችን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲመሰረት በምድር ላይ በመንቀሳቀስ ላይ ያሉ አራት ድርጅቶች በጥምረጥ ተሳስረው በጋራ ለመታገል ወስነዋል፡፡ እነዚህ አራቱ ድርጅቶች ለብዙ አመታት የአብሮ መታገል ፍላጎት እንቅፋት የሆነውን የገዢ መደቦች የከፋፍለህ ግዛው ሴራ በጣጥሰዋል፡፡ ይህ ዛሬ በጥምረት የተጀመረው ትብብር እያደገ ሄዶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ውህደት እንዲያድግ ይደረጋል፡፡

 ከዚህም በተጨማሪ ንቅናቄው ከሌሎች ለዴሞክራሲ ስርዓት መመስረት ከሚታገሉ ኢትዮጵያዊያን ድርጅቶች ጋር ተጣምሮ ለመስራት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ ይገፋበታል፡፡ በዚህም መሰረት፣ 1ኛ) የአፋር ድርጅቶች የጋራ ንቅናቄ 2ኛ) የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ 3ኛ) የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ እና 4ኛ) አርበኞች ግንቦት 7 ለአድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ፣ የኢትዮጵያ አገር አድን በዴሞክራሲ የጋራ ንቅናቄ (በአጭሩ “የአገር አድን ንቅናቄ”) የሚባል ድርጅት ዛሬ በአዲስ ዓመት መባቻ ጳጉሜ 3 ቀን 2007 ዓ.ም ፈጥረዋል፡፡ የንቅናቄውን ምክርቤት፣ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴና የተለያዩ መምሪያዎችን ከማቋቋሙም በላይ ዶክተር ብርሃኑ ነጋን ሊ/መንበር፣ ታጋይ ሞላ አስገዶምን ም/ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል፡፡ የኢትዮጵያ አገር አድን በዴሞክራሲ የጋራ ንቅናቄ ከአራቱ አባል ድርጅቶች የተውጣጣ አገር አድን ሰራዊት አቋቁሟል፡፡

ይህ አገር አድን ሰራዊት በሚያደርጋቸው የትግል እንቅስቃሴዎች ሁሉ የአራቱ አባል ድርጅቶች ሰራዊቶች አባላት ሁሌም ከጎኑ አብረው በመሰለፍ ይታገላሉ፡፡ ባለፉት ሃያ አራት ዓመታት ከህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ በሰላማዊ መንገድ ለመገላገል የኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ ጥረት አድርጓል፣ ሁኖም ለእነዚህ ጥረቶች ከአገዛዙ የተገኘው ምላሽ እስር፣ ስደት፣ ውርደትና ሞት ብቻ ነው፡፡ ይህ በመሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ሳይወድ የህዝባዊ አመፅ አማራጭን እዲቀበል ተገዷል፡፡

በዚህም ምክንያት አሁንም ለሰላም የዘረጋውን እጅ ሳያጥፍ የህወሓት/ኢህአዴግን አገዛዝ በህዝባዊ አመፅ ለማስወገድ እንቅስቃሴውን ጀምሯል፡፡ በጋራ የሚደረገው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ በትግሉ ሜዳ ከሚደረገው ሕዝባዊ አመጽ በተጨማሪ የፖለቲካ፣የዲፕሎማሲና የሕዝብ ግንኙነት ዘርፎችን ያካተተ ይሆናል፡፡ ይህ አዲስ ጅምር የህወሓት/ኢህአዴግን አገዛዝ ዕድሜ ለማሳጠር በሚደረገው ሕዝባዊ ትግል ውስጥ የመጀመሪያውና ወሳኝ ምዕራፍ ሲሆን በዚህ አዲስ ጅምር ውስጥ አገር አድን ሰራዊቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጉያ ውስጥ እየገባ፣ ዕዝብን እያነቃና እያደራጀ ወገኑ ከሆነው ሕዝብ ጋር የሚያደርገው የትግል እንቅስቃሴ በመጪው አዲስ ዓመት በተጠናከረ መልኩ ይቀጥላል፡፡ የኢትዮጵያ አገር አድን በዴሞክራሲ የጋራ ንቅናቄ አገር አድን ሰራዊት መመስረቱን በዚህ መግለጫ ሲያሳውቅ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጎኑ እንዲቆም ያደርጋል፡፡

እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሰብዓዊ መብቶቹና ነፃነቱ ተከብረው በኢትዮጵያ ውስጥ በሰላም ሰርቶ መኖር የዜግነት መብቱ እንጂ የገዢዎች ችሮታ አለመሆኑን ማስመስከር አለበት፡፡ እኛ ኢትዮጵያዊያንን ለእስራት፤ለስደትና ለሞት የዳረገን የውርደት ኑሮ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ማብቃት አለበት፡፡ ይህንን ብሩህ ዓላማ እውን የሚያደረግ ሁለንተናዊ የአገር አድን ትግል ተጀምሯል፡፡ የኢትዮጵያ ገበሬ ሆይ ! መሬት የህዝብ ነው እየተባልክ ህወሓት/ኢህአዴግ ሲያሰኘው አንተንና ቤተሰብህን ከመሬትህ እያፈናቀለና መሬቱን ለባእዳን እየሸጠ፤ አለዚያም በገዛ መሬትህ ላይ እንደ ገባር ተቆጥረህ አገሪቱ የዝናብ እጥረት ባጋጠማት ቁጥር የዕርዳታ ሰጭዎችን እጅ ተመልካች ሆነሃል፡፡ ዛሬ ልጆችህ በአገር አድን እንቅስቃሴ ዙሪያ ተሰባስበው ከዚህ የውርደት ኑሮ ነፃ ሊያወጡህ ቆርጠው ተነስተዋል፡፡ ይህ ትግል አንተ በምትኖርበት አካባቢ፣በአንተ ድጋፍና አንተም ተሳትፈህበት የሚደረግ ትግል ነው፡፡

 ስለዚህ ልጆችህ ከህወሓት/ኢህአዴግ ጋር በሚያደርጉት ትንንቅ መሸሸጊያ ጫካቸው አንተ ነህ፡፡ ውሃ ሲጠማቸው ውሃ እያጠጣህ፤ ሲርባቸው ቤት ያፈራውን እያበላህ፤ ይህንን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚደረግ የመብት፣ የነፃነትና የእኩልነት ትግል ከልጆችህ ጋር አብረህ እድትታገል በአገር አድን እንቅስቃሴ ዙሪያ የተሰባሰቡ ልጆችህ አገራዊ ጥሪ ያቀርቡልሃል፡፡ የኢትዮጵያ ወጣት ሆይ! “የወደፊቷ ኢትዮጵያ ተረካቢ ነህ” እየተባለ በተደጋጋሚ እየተነገረህ ነው፡፡ አንተ በራስህ ዓይን እደምትመለከተው የዛሬዋም ኢትዮጵያ ለአገርና ለህዝብ ደንታ በሌላቸው ሰዎች እጅ ገብታ እፈረሰች ነው፡፡ የዛሬዋ ኢትዮጵያ ከህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ ነፃ ካልወጣች የነገዋ ኢትዮጵያ አትኖርም፡፡ የነገዋን ኢትዮጵያ የመገንባት ባአንተ በወጣቱ ጀርባ ላይ የወደቀ ኃላፊነት ነው፡፡

ይህ ስራ የሚጀምረው ህወሓት/ኢህአዴግን ከስልጣን በማባረር ነው፡፡ የስደት ኑሮ አብቅቶ በገዛ አገርህ ውስጥ ባሰኘህ ቦታ ያሰኘህን ስራ እየሰራህ የክብር ኑሮ የምትኖርበትን ጊዜ አንተው ራስህ ታግለህ ማምጣት አለብህ፡፡ ስለዚህ ዛሬ ራሳቸው አደራጅተው ከህወሓት/ኢህአዴግ ጋር ከሚፋለመው የአገር አድን ሰራዊት ጋር ዛሬውኑ ተቀላቀል፤ ይህንን ማድረግ የማትችል ደግሞ በምትኖርበት ቦታ ከምታምናቸው ጓደኞችህ ጋር ሆነህ ራስህን እያደራጀህና የመረጃ ማሰባሰብ ስራዎችን እየሰራህ በየአካባቢህ የሚገኘውን የህዝባዊ እቢተኝነት ቡድን ተቀላቀል፡፡ በአገር ውስጥና በውጭ አገሮች ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የምትታገሉ ድርጅቶች ሆይ ! ኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ተገንብቶ ማየት የሚሹ የተለያዩ ድርጅቶች ህወሓት/ኢህአዴግ ስልጣን ከመያዙ በፊትና ሥልጣን ከያዘም በኋላ በርካታ ዓመታት የፈጀ እልህ አስጨራሽ ትግል አካሂደዋል፤ዛሬም እያካሄዱ ነው፡፡ ይህ በተናጠል እየተካሄደ ያለው ትግል በመካከላችን የልዩነትና ያለመተማመን አጥር ሰርቶ ስላራራቀን ህወሓት/ኢህአዴግን ማሸነፍ ቀርቶ ጠንካራ ጡንቻ እንድናሳርፍበት እንኳን አላስቻለንም፡፡

ይልቁንም የምንታገልለት ህዝብ በየቀኑ ይታሰራል፤ ሰቆቃ ይደርስበታል፤ ይገደላል፡፡ ከዚህ ሁሉ ያመለጠው ደግሞ አገሩን ለቅቆ ይሰደዳል፡፡ በመካከላችን ያሉትን መለስተኛ ልዩነቶች ለህዝብ አቅርበን በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለመፍታት እስከተማመን ድረስ የአሁኑ ትግላችን ይህንኑ ለማድረግ ነውና ለዚህ እንቅፋት የሆነብንን የህወሓት/ኢህአዴግ ሥርዓት አብረን የማንታገልበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ ስለሆነም ሁላችንም ፍሬያማ ለሆነ ትብብር ራሳችንን እናዘጋጅ፤እንተጋገዝ፡፡ የኢትዮጵያ ምሁር ሆይ ! አገራችን ኢትዮጵያ ሁለት እጆቿን ዘርግታ ከምንግዜውም በላይ ያንተን የምሁር ልጆቿን የነቃ የትግል ተሳትፎ የምትፈልግበት ጊዜ አሁን ነው፡፡የኢትዮጵያ ምሁር ለኢትዮጵያ ሕዝብ መብትና ነፃነት መከበር ከፍተኛ አስታውጽኦ አድርጓል፤ ግን ይህ በአብዛኛው በተናጠል አንዳዴም ድርጅታዊ መልክ ይዞ የተካሄደው ትግል የኢትዮጵያን ሕዝብ መብትና ነፃነት ማስከበር አልቻለም፡፡ በዚህ ተስፋ ቆርጠህ ከዳር ቆመህ የአገርህን ውርደት ዝም ብለህ እያየህ ከነበርክ ይህ ከዳር ሆኖ የመመልከቻ ጊዜ አሁን አብቅቷል፡፡

 ስለዚህ አገር ውስጥና አገር ውጭ የምትኖረው ኢትዮጵያዊ ከወንድሞችህና እህቶችህ ጋር በመሆን ይህን የተቀጣጠለ ሕዝባዊ ትግል ተቀላቅለህ ዝንት ዓለም ስተመኝው የነበረውን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመመስረት ድርሻህን እንድታበረክት አገራዊ ጥሪ ቀርቦልሃል፡፡ የህወሓት/ኢህአዴግ አባላት ሆይ! አንዳንዶቻችሁ ከልባችሁ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የምትታገሉ መስሏችሁ፤ ከፊሎቻችሁ ደግሞ በሁኔታዎች ተገድዳችሁ፤ ሌሎቻችሁ ደግሞ አማራጭ አጥታችሁ ባለፉት ሃያ አራት ዓመታት ከለየለት የአገር ጠላት ድርጅት ጋር ተስልፋችሁ እናት አገራችሁን ስትበደሉ ቆይታችኋል፡፡ ብዙዎቻችሁ የሕዝብ ስቃይና መከራ ተሰምቷችሁ የበደላችሁትን ሕዝብ ለመካስ አመች ጊዜ እየጠበቃችሁ ነው ብለን እናምናለን፡፡ ደስ ይበላችሁ! የምትጠብቁት ጊዜ ደርሷል፡፡

መጭው እውነተኛ ዴሞክራሳዊ ስርዓት እናንተንም ነፃ የሚያወጣ ስርዓት ነውና ሁላችሁም በያላችሁበት ትግሉን ተቀላቀሉ፤መቀላቀል የማትችሉ ደግሞ መረጃ በማቀበልና ስርዓቱን ከውስጥ ሆናችሁ በማፍረስ ሕዝባዊውን ትግል ደግፉ ከህሊና እና ከታሪክ ተጠያቂነት ራሳችሁን ታደጉ፡፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሆይ ! ያንተ ኃላፊነት የአገረህን ዳር ድንበር ከጠላት መጠበቅ ሆኖ ሳለ ህወሓት/ኢህአዴግ በአገርህ አንድነት ላይ የሚሸርባችው ሴራዎች አስፈፃሚ አድርጎህ ጭራሽ ደህንነቱን ለመጠበቅና ለመንከባከብ ቃል ከገገባለት ሕዝብ ላይ መሳሪያህን እንድታነሳ እያደረገህ ነው፡፡

 አንተ የወጣኸው ከኢትዮጵያ ሕዝብ አብራክ ውስጥ ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ወልዶ ባሳደገህ ወገነህ ላይ “ተኩስ” የሚል ፀረ-ሕዝብ ትዕዛዝ ሲሰጥ በፍጹም አትቀበል፣ ይልቁንም በጠላትህ ህወሓት/ኢህአዴግ ሰርዓት ላይ አዙር ወይም መሳሪያህን እየያዝክ ወገኖችህን ተቀላቀል፡፡ እኛ ወገኖችህ ለነፃነት የምናደርገው ትግል በዘረፋና በሙስና ከከበሩ ዘራፊ ወታደራዊ መሪዎች ነን ባይ ሽፍቶች ጋር ነው እንጂ በፍጹም ካንተ ከወገናችን ጋር አይደለም፡፡ የእኛ ትግል አንተ የአገርህን ዳር ድንበር ለመጠበቅ የሚያስችልህን ብቃት ለመፍጠርና እውነተኛ የሕዝብ ሰራዊት እንድትሆን ለማድረግ ነው እንጂ አንተን ወገናችንን ለመበታተን የመጣን ጠላቶች ወይም አንተን በመግደል የምንደሰት አይደለንም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! አንድን ጨቋኝ አምባገነን ስርዓት ታግለህ በደመሰስክ ማግስት ከቀድሞው የባሰ የሚረግጥህና የሚጨቁንህ ስርዓት በላይህ ላይ እየተጫነ ተቆጥረው የማያልቁ የስድት፣ የሰቆቃና የውርደት ዓመታት ዓሳልፈሃል፡፡ አባቶችህ በደማቸው አስከብረው ያስረከቡህ የአገር አንድነት ላልቷል፤ አንተ ታግለህ ከቅኝ አገዛዝ ነፃ ያወጣሃቸው አገሮች በዕድገት ወደ ኋላ ጥለውህ ሄደዋል፤ የወለድካቸው ልጆችህ እስር ቤት ውስጥ ናቸው አልያም አንተንና አገራችውን ጥለው ተሰደዋል፡፡

 የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! “አምላኬ! አምላኬ! ይህ የመከራና የውርደት ዘመን መቼ ይሆን የሚያበቃው?” እያልክ ሰማይ ሰማዩን እየተመለከትክ ፈጣሪህን ጠይቀሃል፤ ለምነሃልም፡፡ ፈጣሪ አልረሳህም፡፡ የወለድካቸው ልጆችህ ተሰባስበውና ተደራጅተው የናፈቀህን የሰላምና የነፃነት ኑሮ የምታገኝበትን ቀን ለማቅረብ በአገር አድን ሰራዊትነት ተደራጅተው እየተፋለሙ ነው፡፡

የአገር አድን የጋራ ንቅናቄ ዓላማ አገራችን ኢትዮጵያ ፍትህ፣ ሰላምና እኩልነት የሰፈኑባት አገር እንድትሆን ነውና የምትችል በአካል ትግሉ ሜዳ ተገኝተህ በጉልበትህ፤ ይህን ማድረግ የማትችለው ደግሞ በገንዘብህ፣ በእውቀትህና ለዚህ ከጠላትጋር ለሚደረገው ትንንቅ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ለወገን ኃይሎች በማቀበል ትግሉን ተቀላቀል፡፡ አንድነት ኃይል ነው! ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

የሕወሓት አስተዳደር የመከላከያ ሰራዊት ለአባይ ግድብ መስሪያ ገንዘብ አናዋጣም አሉ

የወያኔ ኢህአዴግ ስርአት መከላከያ ሰራዊት ለአባይ ግድብ መስሪያ ገንዘብ እንዲያዋጡ ለቀረበላቸው ጥሪ እንዳልተቀበሉት የትህዴን ድምጽ ምንጮች ከመከላከያ ውስጥ ገለፁ::


Photo Fileበምንጮቹ መረጃ መሰረት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እንደ አዲስ ለአባይ ግድብ መስሪያ የሚሆን በሚል ገንዘብ እንዲያዋጡ በአመራሮቻቸው ለቀረበላቸው ጥሪ አንቀበልም ማለታቸውን የገለፀው መረጃው ለቀረበው ጥሪ ሳይቀበሉት የቀሩበት ምክንያትም “ ባለፉት ጊዚያት በተደጋጋሚ የከፈልነውን ገንዘብ ቦንድ ይሰጣቸኋል ተብለን እስከ አሁን ድረስ ግን ሳይተገበር አንከፍልም” እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል::
መረጃው በማከል።- የሰራዊቱ ከፍተኛ አዛዦች በሰራዊቱ ውስጥ አጋጥሞ ያለውን ለአባይ ግድብ ገንዘብ አንከፍልም የማለቱ የመበታተን አደጋ። እንዴት አድርገን ለሰራዊቱ እናሳምነው በሚል በከባድ ውጥረት እንደሚገኙ የተገኘው መረጃ ጨምሮ አስረድቷል ሲል የትህዴን ድምጽ ዜናውን ቋጭቷል::

fredag 4. september 2015

የተደበቀው የህወሓት ማንነት ከደደቢት እስከ ቤተ መንግስት – (ክፍል 5) ነብሰጡር ሴቶችና አዛውንቶች ሳይቀሩ በስለት ታርደዋል


meles zenawi funeral


ሰፊው የትግራይ ህዝብ ስራ አጥቶ በሴተኛ አዳሪነትና ስደት ብቻ ሳይሆን በርሃብ፣ በድንቁርና እና በሽታ እየተሰቃየ በመኖሩ ምክኒያት ጠብመንጃ አንስተን በርሃ ለመውረድ ቻልን…” ብሎን ነበር ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ያኔ በሽፍትነት ዘመኑ በ1968 ዓ.ም ባሳታመው የፖለቲካ ፕረሮግራሙ ከወደ ደደቢት፡፡ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ይህን ካለ ከ40 ዓመታት በኋላ ዛሬም ረሃብ፣ በሽታ፣ ስራ አጥነት፣ ሴተኛ አዳሪነት፣ ድንቁርና እና ስደት አለ፡፡ እንዴውም ያን እሱ የተቸውን ዘመን በመሚያስመግን ሁኔታ፡፡ ታግየለታለሁ የሚለውን ትግራይን ጨምሮ መላው የኢትዮጵያ ወጣት በየቀኑ በግፍ ይሰደዳል፡፡ ስደትን አስቆማለሁ ብሎ ጠብመንጃ ያነሳው ህወሓት በስልጣን ዘመኑ ለዕልፍ አዕላፍ ኢትዮጵያዊያን ተሰዶ በባህር በዱር በገደልና በበርሃ ማለቅ ዋነኛ ምክኒያት ሆነ፡፡ ድህነትን ከአገራችን ምድር አጠፋለሁ ብሎ ታጥቆ የተነሳው ህወሓት ኢትዮጵያን ከኒጀር ቀጥላ የዓለም ሁለተኛዋ መናጢ ደሃ አገር ሆና በውርደት መዝገብ ስሟ እዲሰፍር አድርጎ ገናና ታሪኳን ሙልጭ አድርጎ ከምድረ ገፅ አጠፋው፡፡ ኮሌጅ የበጠሱ ወጣቶች የህወሓት ትምህርት ሜኒስቴር የሰጣቸው ክርታስ እንጀራ ሊያስቆርሳቸው ባለመቻሉ ረጅም የስደት ጅረት በመፍጠር ልክ እንደወንዞቻችን የተፈጥሮ ሀብታችንን ተሸክመው ያለማቋረጥ ወደ ውጭ መፍሰሳቸውን ቀጥለዋል፡፡ የመን ውስጥ ብቻ 800 ሺህ ወጣቶች እንደሚገኙ ዓለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት /I.O.M/ ያወጣው ሪፖርት ያረጋግጣል፡፡ “ተስፋ ብቻ ያዘሉ ፍሬ ቢስ ባዶ አዎጆችና መግለጫዎች በየጊዜው ይለፈፋሉ፡፡ እነዚህ ከእውነት የራቁ መግለጫዎችና ጽሁፎች በመገናኛ መስመሮች በጭቁን ህዝብና በአገር ስም ይታወጃሉ፤ የዓዋጆች ዓላማ የህዝቡን አስተሳሰብ ለማደናገርና ወታደራዊ ደርግ በስልጣን ለመቆየት ያለው ፍላጎት እደዚሁም ቡድናዊ ጥቅም ለመጠበቅ ሆን ተብሎ የሚደረግ የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ ነው…” በሽፍትነት ዘመኑ ይህን ይፅፍ የነበረው ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ በለስ ቀንቶት ከደደቢት ምኒልክ ቤተ መንግስት ከገባ በኋላ “የላም አለኝ በሰማይ” አሰልቺ ዲስኩሩን ውሽንፍር ከጠባቡ የአዕምሮው አድማስ ወደ ሰፊዋ ምድር እያወረደና የመኖር አድባር ተራሮችን በሃሰት መባርቅት እያረሰ የፈጠራቸው በተስፋ ውሃ የተሞሉ ኩሬዎች ግማት ህዝብ አፍንጫና አፍን በእጆቹ ሸፍኖ ሽሽትን እንዲመርጥ ጋበዘው፡፡ ህዝቡን ከመደናገር ጉድጓድ እግሮቹን አውጥቶ ለቡድናቸው ጥቅም ብቻ የቆሙ ስልጣናቸውን ለማራዘም ከሚያደርጉት የማወናበድ ድርጊት ሊያባንነው የተነሳው ህወሓት የኢትዮጵያን ህዝብ የባሰውን ወደ መደናገር ሸለቆ በመወርወር ከሸለቆው አፋፍ ላይ የሚገኝ የስልጣን ጉብታ ላይ ተኮፍሶ ወደታች አዘቅዝቆ እያየ በመገልፈጥ ለ24 ዓመታት በመከራው አላገጠበት፡፡ የሚሊየነር ቡድኖችን ፈጥሮ ሚሊዮኖችን የበይ ተመልካች አደረጋቸው፤ ጫት አቅራቢ፣ መጠጥ ቸርቻሪ ሆኖ የወጣቶችን አዕምሮ በማደንዘዝ ሃሳባቸውን አኮላሽቶ በአጭር በማስቀረት በቁማቸው እንዲያንቀላፉ አደረጋቸው፡፡ “ጊዜው ያለፈበት የኢኮኖሚ ስርዓት ባስከተለው ብዝበዛ ምክንያት በህብረተሰቡ ውስጥ ያሉት መሰረታዊ ችግሮች ድንቁርና፣ በሽታ፣ ድህነትና ርሃብ የመሳሰሉ እንደዚሁም መደቦችና የመደብ ብዝበዛ ለማጥፋት ህወሓት የማያቆርጥ ትግል ታደርጋለች…” ሲል በፖለቲካ ፕሮግራሙ ላይ የፃፈው ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ራሱን በበዝባዦች መደብ ላይ አስቀምጦ ብቸኛው በዝባዥ ሆኖ በወፍ ዘራሽነት በኢትዮጵያ ጥቁር አፈር ላይ በመብቀል ልክ እንደ ባህር ዛፍ ስሩን አስረዝሞ የሌሎች ተክሎችን ምግብና ውሃ እየተሻማ አጠውልጎ በቁማቸው አደረቃቸው፡፡ ኢትዮጵያችን የድንቁርና፣ በሽታ፣ ድህነት፣ ርሃብና ስደት አሜኬላ ከባህር ዛፍ እግር ስር በቅለው የተንሰራፉባት ምድር ሆነች፡፡ በተጨማሪም ህወሓት የፖለቲካ እሳት መንዶውን ባንድ እጁ የማህበራዊ ሾተሉን በሌላኛው ዕጁ አንስቶ በህዝቡ ገላ ላይ እያሳረፈ 40 በመግረፍ አገራችንን የባሰውኑ ምድራዊ ሲኦል አደረጋት፡፡ በዚህ የተነሳ ዜጎች ሲኦልን ሽሽት ግን ወደ ሌላኛው ይሻላል ብለው ወደ ገመቱት ሲኦል መጓዛቸውን ያለምንም ፋታ ተያያዙት፡፡ በህወሓት ኃጢያት ተኮንነው ገኀነም በመግባት ትልቅ ዋጋ በመክፈል ላይ ናቸው፡፡ ትናንትና በስለት አንገት አንገታቸውን የታረዱት ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች በግፍ የፈሰሰ ደም ከሊቢያ ምድር ላይ ሳይደርቅ ዛሬ ደግሞ ሱዳን ላይ በርካታ ወጣቶች በአሰቃቂ ሁኔታ እየተገደሉ ኩላሊታቸው በመውጣት ላይ ነው፡፡ እልቂቱ፣ ግፍና መከራው፣ መሰደድና መፈናቀሉ፣ ፍዳና ሰቆቃው፣ በስለት መታረዱና በጥይት መጨፍጨፍ፣ ውርደትና ክብር ማጣቱ… በሰው አገር ብቻ ሳይሆን በገዛ አገራችንም በባሰ ሁኔታ መፈፀሙ የእኛን የኢትዮጵያዊያንን ችግር እጥፍ ድርብ ያደርገዋል፡፡ ወጣቶች ከመከራ ላይ የመከራ ካባ ደራርበው እንዲለብሱ ከሰቆቃ ላይ ሌላ የሰቆቃ ሸማ እዲጎናፀፉ ያደርጋቸዋል፡፡ ሳዑዲ አረቢያ ላይ የደረሰው መፈናቀል በኢትዮጵያችን ምድር ላይም በህወሓት ተከስቷል፡፡ ኢትዮጵያዊያን በቋንቋቸው ዘራችሁ ሌላ ነው ተብለው ከቤንች ማጅ ዞን ጉራ ፋርዳ ወረዳ ከሌሎችም በርካታ አካባቢዎች ቤት ንብረታቸውን እየተነጠቁ በተደጋጋሚ ተባረዋል፡፡ በቅርቡ በሊቢያ ውስጥ በአይሲስ የተፈፀመው የ30 ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን በስለት መታረድና በጥይት መጨፍጨፍ፤ አርባ ጉጉ በደኖ ላይ ዘራችሁ ሌላ ነው ተብለው ዕልፍ አዕላፍ ኢትዮጵያዊያን ገና ነብስ ያላወቁ ህፃናት፣ ነብሰጡር ሴቶችና አዛውንቶች ሳይቀሩ በስለት ታርደዋል፤ ህወሓት በሳለው ጎራዴ አካላቸው ልክ እንደ ዶሮ ተበልቷል፡፡ ጋምቤላ ውስጥ አኙዋኮች ብቻ እየታደኑ በህወሓት ሰራዊት መትረየስና ክላሽን ኮቭ ተጨፍጭፈዋል፡፡ በ1997 ዓ.ም ድምፃችን ተዘረፈ ብለው ለተቃውሞ ሰልፍ አደባባይ የወጡ ወጣቶች ከትምህርት ቤት የሚመለሱ ህፃናትን ጨምሮ በአልሞ ተኳሽ ግንባር ግባራቸውን ተመትተው ሰቅጣጩ አስከሬናቸው በየጎዳናው ተልከስክሷል፡፡ የህወሓት ድብቅ ሴራዎች ህወሓት በሽፍትነት ዘመኑ 17 ዓመታት ሙሉ ሴራ ሲጎነጉን፣ ሸፍጥ ሲሰራ፣ የተንኮል ዕቅድ ሲነድፍ፣ የጠልፎ መጣል ስልት ሲያቀነባብር፣ ያለምንም ድካምና ዋጋ እንዲሁም ዕውቀት የስልጣን ኮረቻ ላይ ለመፈናጠጥ የሚያስችለውን የሀሳብ ቀመር ሲቀምርና የዘር ሂሳብ ሲያሰላ ነበር የኖረው፡፡ ህወሓት በአውደ ውጊያ ካሳለፋቸው ዓመታት ይልቅ በየዋሻውና በየሸለቆው አድፍጦ የጥፋት ሴራ ሲጠነስስ የነበረባቸው ዓመታት ይበልጣሉ፡፡ የግራ ርዕዮተ ዓለም የሚያራምዱትን ሲያገኝ የሶሻሊስትነት ካባ ደርቦ በመቅረብ የቀኝ ርዕዮተ ዓለም ከሚያራምዱት ፊት ደግሞ ማርክሲስት ሌኒንስት ካባውን ሳያወልቅ የሌበራልነት ካባ በላዩ ላይ ደርቦ በመታየት እንደ እስስት ቆዳውን በመቀያየር በመስሎ አዳሪነት ባህሪውም የሚያክለው የለም፤ ሴተኛ አዳሪው ድርጅት ህወሓት፡፡ ህወሓት በሽፍትነት ዘመኑ ከአረብ አገራት እርዳታ ለማግኘት በማለም የውጭ ጉዳይ ኃላፊ የነበረውን ስዩም መስፍንን ስሙን ቀይሮ ስዩም ሙሳ ተብሎ እንዲጠራ አድርጓል፡፡ ህወሓት ገና ስሙን ሳይቀይር ተሓህት/ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ/ ይባል በነበረበት ወቅት ግገሓት/ ግምባር ገድሊ ሓርነት ትግራይ/ ከተባለው ከእሱ በፊት ተመስርቶ በትግራይና በኤርትራ አዋሳኝ መሬቶች ላይ ይንቀሳቀስ በነበረው የታጠቀ ድርጅት ጋር ሙሉ በሙሉ ውህደት ለመፈፀም ስምምነት ላይ ደርሳል፡፡ ቀጥሎም ሁለቱ ድርጅቶች ማለትም ተሓህት-ህወሓት እና ግገሓት ውህደት ወደሚፈፅሙበት ቦታ ምስራቅ ትግራይ ዘገብላ ተብላ ወደ ምትጠራው ቦታ ሰራዊታቸውን ወስደው ካሰፈሩ በኃላ አመሻሽ ላይ የተሓህት-ህወሓት አመራሮች ቀን ሲሸርቡት የዋሉትን ሴራ ለሰራዊታቸው በጠቅላላ በምስጢር እዲተላለፍ አደረጉ፡፡ ይህም እያንዳንዱ የተሓህት-ህወሓት ታጋይ ከግገሓት ታጋይ ጋር ጥንድ ጥንድ እየሆኑ እንዲተኙና ግገሓቶች እንቅልፍ ወስዷቸው የተኩስ ትዕዛዝ እስኪተላለፍ በንቃት እዲጠባበቅ የሚል ነበር፡፡ ከዚያም እኩለ ሌሊት ላይ የግገሓት ሰራዊት በእንቅልፍ ላይ መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ የተሓህት-ህወሓት ታጋዮች ከጎን ከጎናቸው ከተኙ የግገሓት ታጋዮች ላይ እንዲተኩሱ በምልክት ትዕዛዝ ተሰጥቷቸው ለውህደት የመጣው የግገሓት ሰራዊት ከነመሪዎቹ በእንቅልፍ ላይ እንዳለ ተጨፍጭፎ ሙሉ በሙሉ ተደመሰሰ፡፡ ምክትል ፕረዝዳንቱን ፍስሃ ደስታን ጨምሮ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ከፍተኛና ዝቅተኛ የደርግ ባለስልጣናትን ራሱ ደርግ እንዲረሽናቸው ህወሓት በ1970 ዓ.ም አንድ ሴራ ጠንስሶ ሙሉ በሙሉ ተሳክቶለታል፡፡ ህወሓት ደርግ እንዲረሽናቸው የሚፈልጋቸውን በከፍተኛና ዝቅተኛ የመንግስት አመራር የሚገኙ የትግራይ ብሄር ተወላጆችን ስም ዝርዝር በቀላሉ ሊሰበር በሚችል ኮድ በማስፈር እና ለህወሓት የሰሩትን ስራ ከጎን በመፃፍ ሐሰተኛ ደብዳቤ አዘጋጅቶ የከተማውን የህቡ እንቅስቃሴ ከሚመራው ተክሉ ሃዋዝ የተባለ ታጋይ ለሊቀመንበሩ አባይ ፀሃዬ የተላከ በማስመሰል ሶስት ታጋዮች ደብዳቤውን ይዘው ወደ አክሱም ከተማ እዲገቡ ካደረገ በኃላ ራሱ በተዘዋዋሪ መንገድ ጠቁሞ በደርግ ደህንነቶች ቁጥጥር ስር እንዲውሉ አስደርጓቸዋል፡፡ ከዚያም ከተክሉ ሃዋዝ ለአባይ ፀሐዬ እንደተላከ ተደርጎ የተዘጋጀው ደብዳቤ ከደርግ ደህንነቶች እጅ ይገባና ወደ መቀሌ ተልኮ ኮዱ ተሰብሮ ሰም ዝርዝራቸው ሰፍሮ የተገኙት በከፍተኛና ዝቅተኛ የመንግስት አመራር ውስጥ የሚገኙ ዕልፍ አዕላፍ የትግራይ ተወላጆች እየታደኑ ወደ ወህኒ ተወስደው አሰቃቂ ምርመራ ከተደረገባቸው በኋላ ያለ ኃጢያታቸው ተረሸኑ፡፡ ህወሓት ባዘጋጀው ሃሰተኛ ደብዳቤ ላይ አባሎቹ እንደሆኑ አስመስሎ ስማቸውን ከዘረዘራቸው የትግራይ ተወላጅ ከሆኑት የደርግ አመራሮች ምንም ሳይሆን የቀረው ፍሰሃ ደስታ ብቻ ነበር ፡፡ ህወሓት ከተመሰረተበት ከ1967 ዓ.ም እስከ 1977 ዓ.ም ድረስ በነበሩት 10 የሽፍትነት ዓመታት ውስጥ ከአመራሩ ውጭ ያሉ ታጋዮች ፆታዊ ግንኙነት ካደረጉ ያለምንም ምህረት ይረሸኑ ነበር፡፡ በመሆኑም ፆታዊ ግንኙነት አድርገው የተነቃባቸው የህወሓት ታጋዮች ከመረሸን ለመዳን ለደርግ እጃቸውን ይሰጡ ነበር፡፡ በፆታዊ ግንኙነት ምክንያት በየጊዜው የሚከዱ ታጋዮችን ደርግ በጥሩ ሁኔታ እደሚቀበላቸው መረጃው የደረሰው ህወሓት ይህን ተንተርሶ ሴራ ጠነሰሰ፡፡ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሴት ታጋዮችን ፆታዊ ግንኙነት አድርገው እንዲያረግዙ ቀጭንና የማያዳግም መመሪያ አወረደ፡፡ መመሪያ የተሰጣቸው በርካታ ሴት ታጋዮች ካገኙት ወንድ ታጋይ ጋር ሁሉ ልክ እንደ እንስሳ ፆታዊ ግንኙነት በማድረግ አርግዘው የህወሓትን መሪዎች ቀጭን ትዕዛዝ ተግባራዊ አደረጉ፡፡ ቀጥሎም የህወሓት መሪዎች እርጉዞቹ ታጋዮች ለደርግ እጃቸውን ሰጥተው በምስጢር እንዲሰልሉ አዘዙ፡፡ ይህ የሰውን ልጅ ከሰውነት ወደ እንስሳነት ተራ የሚያወርድ ሴራ እና ለስልጣን ሲባል በሴት ልጅ ላይ የተፈፀመው ግፍ በሴት ታጋዮች ላይ የሞራል ውድቀትና ሰቆቃ ከማስከተሉ በስተቀር ለህወሓት ከዚህ ግባ የሚባል ውጤት አላስገኘለትም፡፡ በጦር ሜዳ ተዋግቶ ከማሸነፍ ይልቅ በቀበሮ ጉድጓድ ውስጥ አድፍጦ ሴራ መጎንጎን የሚቀናው ህወሓት ደርግን ከትግራይ ህዝብ ነጥሎ እሱ ሰፊ ድጋፍ የሚያገኝበትን ሌላ ሼር ደግሞ ጠነሰሰ፡፡ እሱም “የሀውዜን ጫፍጨፋ” በመባል የሚታወቀው ነው፡፡ ህወሓት በፀራራ ፀሀይ በገበያ ቀን ሰራዊቱን በሀውዜን ከተማ እንዲያልፍና ከፊሉ ደግሞ በግቢያተኛው መካከል እንዲሰራጭ በማድረግ እና በተዘዋዋሪ መንገድ ለማድረግ ደህንነት ቢሮ ጥቆማ በመስጠት ህዝቡን በአውሮፕላን ቦምብ አስጨፈጨፉት፡፡ አስቀድው ባዘጋጁት የቪድዮ ካሜራም በቀጥታ በመቅረፅ ለዓለም አሰራጭተው እንወክለዋለን በሚሉት የትግራይ ህዝብ ሞት የፖለቲካ ትርፍ አጋበሱበት፡፡ ህወሓት በበረሃ አያለ ህዝቡን ለሰራዊትነት ሲመለምል ፈቃደኛ ያልሆኑ ወጣቶችን ቀሚስ አልብሶ በአደባባይ እያዞረ በህዝቡ ፊት ያሸማቅቃቸው ነበር፡፡

onsdag 2. september 2015

ለ3ኛ ጊዜ በመንግስት ቤቱ የፈረሰበት ወጣት ራሱን አጠፋ


‹‹የሳምንት አራስ ጎዳና ላይ ወድቃለች›› በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

‹‹የሳምንት አራስ ጎዳና ላይ ወድቃለች›› በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ መርካቶ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ጎላ መንደር ‹‹ህገ ወጥ የቤት ግንባታ›› በሚል በመንግስት ለሶስተኛ ጊዜ ቤቱ የፈረሰበት ወጣት ታምራት ታንቱ ባሳ ራሱን ማጥፋቱን ምንጮች ከሶዶ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ወጣት ታምራት ታንቱ ባሳ በዚህ መንደር ረዘም ላለ ጊዜ እንደኖረ የገለፁት ምንጮች ለሶስተኛ ጊዜ ‹‹ህገ ወጥ ግንባታ ነው›› ብለው እንዳፈረሱበት አቶ ታደመ ፈቃዱ የተባሉ የሶዶ ነዋሪ ለነገረ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡

 በተደጋጋሚ ቤቱ በመንግስት የፈረሰበት ታምራት ታንቱ ‹‹በዚህ ሁኔታ እንዴት ብዬ እኖራለሁ?›› ብሎ ራሱን ያጠፋው ነሃሴ 24/2007 ዓ.ም ሲሆን በትናንትናው ዕለት የቀብር ስነ ስርዓቱ እንደተፈፀመም አቶ አበራ የተባሉ የከተማው ነዋሪ ገልጸውልናል፡፡ በሶዶ ከተማ ህገ ወጥ ናቸው ተብለው ከ500 በላይ ቤቶች መፍረሳቸውን የገለፁት የአካባቢው ነዋሪዎቹ አብዛኛዎቹ ከአምስት አመት እስከ ዘጠኝ አመት በአካባቢው ኖረውበታል ብለዋል፡፡

አብዛኛዎቹ ነዋሪዎች ለከፋ ችግር እንደተጋለጡ የተነገረ ሲሆን ሚሚ ባቴ የተባለች የሳምንት አራስም ቤቷ ስለፈረሰባት ጎዳና ላይ ወድቃለች ሲሉ ገልጸዋል፡፡ በሌላ በኩል ትናንት ነሃሴ 25/2007 ዓ.ም ከምሽቱ 2 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ አምስት ሰዓት በሶዶ ከተማ ቅዳሜ ገበያ በሚባለው የገበያ ማዕከል ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ በርካታ የንግድ ቤቶች መውደማቸውን የሶዶ ከተማ ነዋሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

tirsdag 1. september 2015

የሰማያዊ ፓርቲ አመራር ከጠቅላላ ጉባኤው ሲመለሱ ተደበደቡ


ነገረ ኢትዮጵያ

የደበደበኝና የዘረፈኝ ሰው ተለቆ እኔ ታስሬያለሁ›› አቶ ጌትነት በሱፍቃድ በወላይታ ዞን ቦሎቶሶሬ ወረዳ አረካ ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር የሆኑት አቶ ጌትነት በሱፍቃድ ተደብድበው ንብረቶቻቸውን መዘረፋቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

 በምርጫው ወቅት ቅስቀሳ ላይ እያሉም በገዥው ፓርቲ ካድሬዎች ተመሳሳይ ወንጀል ተፈፅሞባቸው እንደነበር የገለፁት አቶ ጌትነት ‹‹በምርጫው ወቅት ቅስቀሳ ላይ እያለሁ በካድሬዎች ተደብድቤ ንብረቴን ተቀምቻለሁ፡፡ ሌሎች የትግል ጓደኞቼም ተመሳሳይ ወንጀል ተፈፅሞባቸዋል፡፡

 ሆኖም ከፖሊስ ጣቢያ ጀምሮ እስከ ከንቲባው ፅ/ቤት ድረስ በመሄድ አቤቱታ ብናቀርብም የሚሰማን አላገኘንም፡፡›› ሲሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በቦሎቶሶሬ ወረዳ የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ጌትነት በሱፍቃድ ከሰማያዊ ጠቅላላ ጉባኤ ተሳትፈው ከተመለሱ በኋላ ነሃሴ 20/2007 ዓ.ም በአረካ ከተማ ተመሳሳይ ወንጀል እንደተፈፀመባቸው ገልጸዋል፡፡

 ደብድቦ ስልካቸውንና የአንገት ሀብላቸውን የቀማቸው ሰው እጅ ከፍንጅ ከተያዘ በኋላ ስልካቸው በፖሊስ እንደተመለሰላቸው የገለፁት አቶ ጌትነት እሳቸው ታስረው እስከ ሌሊቱ 5 ሰዓት ሲቆዩ ወንጀሉን የፈፀመው ሰው ወዲያውኑ መለቀቁን ገልጸዋል፡፡ ‹‹የደበደበኝና የዘረፈኝ ሰው ተለቆ እኔ ታስሬያለሁ፡፡ የደበደበኝ ሰው ካድሬ ነው፡፡

 ጭራሹን ለፖሊስ ለመክሰስ በሄድኩበት ወቅት ‹እሱም ሊከስህ ስለሆነ አንተም መክሰስ የለብህም፡፡ እንዳትካሰሱ ብለን መዝገቡን ዘግተነዋል› ብለው መልሰውኛል›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡ የአቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ የትውልድ ቦታ በሆነው አረካ ከተማ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ላይ ከፍተኛ በደል እንደሚፈፀም በተደጋጋሚ የሚገለፅ ሲሆን አቶ ጌትነትም ‹‹የሚደርሰው በደል ከፍተኛ ነው፡፡

 ባለፈውም ለተፈፀመብን አሁንም ለተፈፀመብኝ ወንጀል መፍትሄ አልተሰጠኝም፡፡ ለአንድ ሰው ካድሬዎች በመንጋ መጥተው ነው የሚያጠቁህ፡፡ አቤት የምትልበት አካል የለም›› ሲሉ ገልጸውልናል፡፡