tirsdag 22. september 2015

መንግሥት እርዳታ ፈላጊነቱን በይፋ አመነ

ከይድነቃቸው ከበደ
መንግሥት እርዳታ ፈላጊነቱን በይፋ አመነ !” መባሉ  ምን አዲስ ነገር አለው ፣ለዛውም የኢትዮጵያ መንግስት በማለት እንዳትሸወዱ ! የህውሓት/ኢህአዲግ ገዥው መንግሰት የምግብ እርዳት እና ድርቅን ለመከላከል ፣ሞቼ ነው በቁሚ የምለምነው ሲል ነበር፡፡ በአገራችን በኢሊኒኖ ምክንያት በተከሰተው ድርቅ፣ በሰው ሕይወት እና በእንስሳት  ላይ እየደረሰ ያላው አደጋ አሳሳቢነት

አስመልክቶ ፤የመንግሰት ኮሚኒኪሽን ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሬዲዋን ሁሴን “ሰባት ሞቶ ሚሊይን ብር በጀት የያዝን በመሆኑ ችግሩን መቆጣጠር እንችላለን ፣ ምንም አይነት የዉጪ እርዳታ አያስፈልገንም፣ የዚህን ያህል አሳሳቢ ደረጃ አልደረሰም” በማላት የመንግስታቸውን አቋም ነሐሴ ወር 2007 ዓ.ም መግለፃቸው የሚታወስ ነው፡፡ አቶ ሬዲዋን መግለጫውን በሰጡ ሳምንት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ   ዳያስፓራ ነን ባዩችን በሚሊኒየም አዳራሽ ሰብስበው “አሁን በክረምቱ በምስራቁ የሀገራችን ክፍል ከላይ እስከታች ድርቅ አጋጥሞናል……፣ወዳጆችን በዚህ ሰዓት ተሯሩጠው መጥተው እርዳታ ይሰጡን ነበር ፣አሁን እስኪ እናያቸዋለን በማለት ዳር ነው የቆሙት……. ፣አቅማችን እየጎለበተ ስለመጣ እራሳችን ገዝተን እራሳችን አቅርበን ህዝባችን እንዳይራብ እናደርጋለን ።” በማለት በድፍረት ተናግረዋል፡፡ይህ የድፍረት ንግግራቸው በቀጥታ ስርጭት በኢቲቪ

ተላልፏል፡፡ “ጉድ እና ጅራት ….” እንደሚባለው ሆነና አቶ ሬዲዋን ሁሴን ዛሬ ማለትም መስከረም 10 ቀን 2008 ዓ.ም የመንግስታቸውን አቋም ሲገልፁ ፤በኢሊኒኖ ምክንያት በተፈጠረው የዝናብ እጥረት የተጎዱ ዜጎች ቁጥር ቀድሞ ከተገመተው 2ነጥበ9 ሚሊየን ህዝብ በማሻቀብ ከ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ደርሷል፣ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የተጠበቀው ድጋፍ በሚፈለገው መልኩ አልተገኘም፣ይህም በመሆኑ ለልማት ከያዘው በጀት እንጠቀማለን “አሉ”፡፡ ይሄ መንግሥት ነኝ ባይ ህውሓት/ኢህአዲግ በዚህ ደረጃ፣ በአገር እና በህዝብ ላይ መቀልዱ የወደፊት የታሪክ ተጠያቂነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ፤አሁን ላይ የሥርዓቱ ውድቀት እየተፋጠነ ለመምጣቱ ከምክንያቶች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ “የተራበ ህዝብ መሪውን ይበላል” መባሉ ቀርቶ መሆኑ ይመጣ ይሆን ? መልሱን አብረን እንጠብቃለን፡፡ አሁንም ግን በአገራችን በሰሜን ምስራቅ እና በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ መጠኑ

እየጨመረ መጥቷል፡፡ በተለይ በእንስሳት ላይ እየደረሰ ያለው አደጋ እጅግ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል፣ ወገኖቻችን በምግብ እጥረት እየተሰቃዩ ለሞት እየተዳረጉ ነው፡፡የችግሩ አሳሳቢነት ደረጃ ከፍ ማለቱ ገዥው ህውሓት/ኢህአዲግ መንግስት ለመሸሸግ አልቻልም፡፡ በግልፅ ቋንቋ “ከውጭ የሚጠበቀው ድጋፍ ካልተገኘ መንግስት ለልማት የመደበውን ሀብት በማዞር ለዜጎች ምግብና ለእንስሳት የሚሆን መኖ ለማቅረብ እግደዳለው” በማላት በአቶ ሬዲዋን ሁሴን በኩል ገልፆዋል፡፡እንዲህ አይነቱ መንግስታዊ ማስፈራራት ምክንያቱን እና ውጤቱን ለመገመት ቀላል ነው፡፡ ከአንድ ወር በፊት እኔ በግሌ እንዲሁም የተለያዩ ግለሰቦች እና ተቋማት፣ ከመገናኛ ብዙሃን ኢሳት እና የውጪ ሃገር ሚዲያዎች፣ የችግሩን አሳሳቢት በተቻለ አቅም ለመግለፅ ተችሎአል፡፡

በተለይ መንግሰት “ሰባት ሞቶ ሚሊይን ብር በጀት የያዝን በመሆኑ ችግሩን መቆጣጠር እንችላለን ፣ ምንም አይነት የዉጪ እርዳታ አያስፈልገንም፣ የዚህን ያህል አሳሳቢ ደረጃ አልደረሰም” በማላት በድፍረት ሲናጋር ፣ይሄ ነገር ተገቢ አይደለም ፣የሚመጣው ነገር አይታወቅም ከአጉል ቀረርቶ እና ባዶ ሽለላ መቅረት አለበት፡፡ ስለዚህም ከችግሩ አሳሳቢነት እና ወደፊት ከሚያስከትለው አደጋ አንጻር፣ ለዓለም አቀፍ ማህብረሰብ እንዲሁም ለለጋሽ ድርጅቶች እርዳታ መጠየቅ አለበት፡፡በማለት የችግሩ አሳሳቢነት ለገለፁ ለአገር ወዳድ እና ተቆርቋሪ ኢትዮጵያዊያን የተሰጠው ምልሽ “አቅማችን እየጎለበተ ስለመጣ እራሳችን ገዝተን እራሳችን አቅርበን ህዝባችን እንዳይራብ እናደርጋለን ።

” በማለት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በአደባባይ ተዘባበቱ፡፡ ይሄን በተናገሩ ሁለት ወር ሳይሞላ የሚረዳን አጣን፣ለዚህ ጉዳይ የያዝነው ገንዘብ እያለቀ ነው፤ከዚህ በኋላ ለልማት የያዝነውን ገንዘብ ነው የምንጠቀመው፤ሲሉ መስማት ያሳፍራል፡፡ነገ ደግሞ ለልማት የያዝነው ገንዘብ ድርቁን ለመከላከል ያወጣነው ስለሆነ፣ አገር የምናስተዳድርበት ገንዘብ የለንም ይሉ ይሆን ? ያኔ ጊዜ “የተራበ ህዝብ መሪውን ይበላል” መባሉ እርግጥ ይሆናል፡፡ ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!
Redwan

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar