አስቻለው የተባለ ተከሳሽ ሱሪውን አውልቆ በምርመራ ወቅት የተኮላሸውን ብልቱን በችሎት አሳይቷል። Getachew Shiferaw
#Ethiopia : በእነ ተሻገር ወልደሚካኤል ክስ መዝገብ እስረኞች አቤቱታ ሲያቀርቡ ፍርድ ቤቱ ሲያቋርጥ የሚናገረው ተከሳሽ ሀሳቡን እንዲጨርስ የተናገረ ሌላ ተከሳሽ በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ከተቀመጠበት ወጥቶ ወደ ችሎቱ እንዲቀርብ ተደርጓል።
ተከሳሹ እንዲወጣ ሲጠየቅ ሌሎች ተከሳሾች "እኛም እንወጣለን" ብለው ተቃውሞ አሰምተዋል። መሃል ዳኘው መጀመርያ " እንደሱ ከሆነ በሁላችሁም ላይ ቅጣት እንሰነዝራለን" ብለው የነበር ቢሆንም ተከሳሾቹን ለማረጋጋት ሞክረዋል።
ሆኖም የግራ ዳኛው "አሁንም ይውጣ" ብለው ተከሳሹ ከወጣ በኋላ ተከሳሹን "ምንድን ነው የሚያወራጭህ?" በማለታቸው ተከሳሾቹ ተቃውሟቸውን በጩኸት ገልፀዋል። የግራ ዳኛውን " ስነ ስርዓት ያዝ! "ሲሉም ተደምጠዋል። ዳኛ ዘርዓይ ከሰባራ ባቡር ወደዚህ የመጣው እኛን ሊመቀል ነው ብለዋል።
" እኛ የተከሰስነው አማራ በመሆናችን ነው። ልንሞት ነው የመጣነው። እንሞታለን" ብለዋል። በተቃውሞው ምክንያት ዳኞች ችሎት ጥለው ወጥተዋል።
አንድ ተከሳሽ "የሀይማኖት አባቶችም እየተሰቃዩ ነው። ትናንት ከእኛ ነጥለዋቸው ነበር። ዛሬ ጠዋትም ነጥለዋቸዋል። ልብሳችሁን እናቃጥለዋለን እያሏቸው ነው" ብሏል።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar