አረና ፓርቲ በትግራይ ውስጥ የሚንቀሳቀስ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል። ዛሬ በእስር ላይ የሚገኘው አብርሃ ደስታም የዚህ የአረና ፓርቲ ውጤት ነው። በአሁኑ ወቅት በትግራይ እየተንቀስቀሱ ካሉት የህወሃት ተቀናቃኝ ፓርቲዎች መካከል የአረና አባላት ከፍተኛ ቦታ ይሰጣቸዋል። ከገጠር እስከ ከተማ ድረስ በትግራይ ህወሃትን የሚቃወም በሙሉ “አረና” የሚል ስም እየተሰጣቸው ይዋከባሉ፤ ይገለላሉ፤ ይታሰራሉ። ህወሃት በትግራይ የሚፈራው ሌላም ሃይል አለ። በመቐለ ቢሮ ከፍቶ የሚንቀሳቀሰው የአንድነት ፓርቲ ሌላኛው ተቀናቃኝ ፓርቲ ነው። በአሁኑ ወቅት የአረና አባላት አንድነት ፓርቲን በመቀላቀል፤ የአንድነትን ፓርቲ ይበልጥ በማጠናከር ላይ ናቸው።
ከአገር ቤት የደረሰን ዘገባ እንደሚያመለክተው በዚህ ሳምንት አቶ አስገደ ገ/ስላሴ ጨምሮ በርከት ያሉ የአረና አባላት የነበሩ አንድነት ፓርቲን ተቀላቅለዋል። በዚህ መሰረት፦
1. መምህር ታደሰ ቢተውልኝ የዓረና ማ/ኮሚቴ ነበር
2. መምህር ገብሩ ሳሙኤል የዓረና ቁጥጥ ኮሚሸን አባል ነበር
3. ኦቶ ሺሻይ አዘናው የዓረና ማ/ኮሚቴ አባል ነበር
4. አቶ አስገደ ገ/ስላሴ የዓረና ሥራ አስፈፃሚ አባል ነበር
5. ኢንጂነር ዓብደልወሃብ ቡሽራ ማ/ኮሚቴ ነበር
6. ወ/ት ዘቢብ ተሰማ ማ/ኮሚቴ ነበር
7. ይልማ ይኮኖ ማ/ኮሚቴ ነበር
8. አቶ ሰለሞን አባይ እና ሌሎች የአረና አባላት ነበሩ በትናንትናው ዕለት አንድነት ፓርቲን በይፋ የተቀላቀሉ ሲሆን፤ የመቀሌ አንድነት ዞን ባዘጋጀው የእንኳን ደህና መጣችሁ ፕሮግራም ላይ የአንድነት ብሄራዊ ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ አቶ ፀጋይ አላምረው፣ እንዲሁም የብሄራዊ ምክር ቤት አባላት አቶ አሻግሬ መሸሻ እና አስራት አብርሃም ከአዲስ አበባ በእንግድነት ተገኝተዋል።
በዚህ ወቅት ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን ከዓረና ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት በተቻለ መጠን ሰላማዊና በመደጋገፍ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን፤ ማንም ሰው የፈለገውን ፓርቲ መልቀቅም ሆነ መቀላቀል መብቱ ቢሆንም ከአላስፈላጊ እሰጣ አገባ መጠንቀቅ እንደሚስፈልግ መተማመን ላይ ተደርሰዋል።
ትግሉ መተጋገዝና መተባበር ግድ የሚል በመሆኑ እንደከአሁን በፊቱ በዓረና ካሉት ጓዶች ጋር በመከባበር ላይ የተመሰረተ ግኑኝነት ይኖረን ዘንድ በጣም አስፈላጊ ነው። ምንም ጥርጥር በሌለው ሁኔታ ነገር ተመልሰን የምንገናኝ፤ አንድ ሆን የምንቀጥል በመሆኑ፤ ከሁለቱም ወገን አብሮ የመስራቱ ጉዳይ መታሰብና መግባባት አስፈላጊ ነው።

Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar