fredag 2. oktober 2015

በወልቃይት በርካታ አካባቢዎች የሚገኙ ገበሬዎች አዝመራቸውን እንዳይሰበስቡ በፌ. ፖሊስ በመታገዳቸው ጥይት ያታኮሰ ከፍተኛ ግጭት መቀስቀሱ ተሰማ


በተኸለ አምባ እና በሌሎች የወልቃይት በርካታ አካባቢዎች የሚገኙ ገበሬዎች አዝመራቸውን እንዳይሰበስቡ በፌደራል ፖሊስ በመታገዳቸው ጥይት ያታኮሰ ከፍተኛ ግጭት መቀስቀሱ ተሰማ ውጥረቱ አሁንም ተባብሶ እንደቀጠለ ነው፡፡ በወልቃይት የሚገኙ ገበሬዎች ማንኛውም ሰው ተነስቶ የሚያርሰውን በተለምዶ “ሞፈር ዘመት” እየተባለ የሚጠራውን መንገድ ተጠቅመው በግንቦትና በሰኔ ወራት ጫካ መንጥረው ምድረ በዳውን በማረስ የተለያዩ አዝዕርቶችን በተለይም ሰሊጥ ዘርተው ያበቀሉ ሲሆን አሁን በመኸር ክወና ላይ ተሰማርተው ባሉበት የህወሓት አገዛዝ ደን ጨፍጭፋችሁ አርሳችኋል በሚል ተልኮሻ ምክንያት ፌደራል ፖሊስ

 በየማሳቸው በማሰማራት ለማገድ በመሞከሩ ነው “ግንቦት እና ሰኔ ገና መሬቱን ማልማት ስንጀምር ከተቆረቆራችሁ ለምን አልከለከላችሁንም?” በሚል ህዝቡ በአንድነት ተነስቶ ግጭት የተቀሰቀሰው የህወሓት ፌደራል ፖሊሶች ተክላይ የተባለውን ገበሬ ከማሳው አስረው ወስደው አደባይ ላይ በመረሸናቸው የዘርባቢትና እድሪስ ቀበሌዎች ነዋሪዎች በአንድነት “ሆ” ብለው ተነስተው ፖሊሶችን ትንቅንቅ ገጥመዋቸዋል፡፡ በተለይም የአካባቢው ሚሊሻዎች ከህዝቡ ጎን በመቆም በፌደራል ፖሊሶች ላይ ተኩስ ከፍተው ውጊያ በመግጠም ሁለት ፖሊሶችን አቁስለዋል፡፡

 በአካባቢው የታጠቁ ሚሊሻዎችና ገበሬዎች የደረሰ አዝመራቸውን እንዳይሰበስቡ ለማገድ በየማሳው በተሰማሩ ፌደራል ፖሊሶች መካከል የተከፈተው ጦርነት ለማስቆም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የመከላከያ ኃይል በአካባቢው ተሰማርቶ ይገኛል፡፡ ሆኖም ግን ግጭቱ የባሰውን ተቀጣጥሎ የሰፈነውን ውጥረት እንዲያይል አደረገው እንጂ ሊያረግበው እንዳልቻለ የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች ገልፀዋል፡፡ 

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar