tirsdag 6. oktober 2015

የስኳር እጥረት ተከሰተ * በወያኔ ታሪክ እንደ ዓባይ ፀሀዬ ያለ ዓይን ያወጣ ዘራፊ በሙስና ሌብነት ለየስሙላ እንኳ ተከሶ አያውቅም

Image result for abay tsehaye

(ፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ) ወያኔ በኦሞ ራቴ በኩራዝ ወረዳ የጀመረው የሸንኮራ እርሻ ጠንካራ ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ በወያኔ ታሪክ እንደ ዓባይ ፀሀዬ ያለ ዓይን ያወጣ ዘራፊ በሙስና ሌብነት ለየስሙላ እንኳ ተከሶ አያውቅም፡፡

 የስኳር ልማት ኃላፊው ዓባይ ፀሀይ በየጊዜው የሚመደበውን ገንዘብ እየዘረፈ የስኳር ልማቱ ላም አለኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ መሆኑ በስፋት እየተነገረ ይገኛል፡፡ እስካሁን በስፋት በማምረት ላይ ያሉት መተሀራ፣ ወንጂ፣ ፊንጫ ስኳር ፋብሪካዎች በተለየዩ ምከንያቶች ከአቅም በታች እያመረቱ መሆናቸው በተደጋጋሚ የታወቀ ጉዳይ ነው፡፡

ሰባት አዳዲስ ፋብሪካዎች ያመርታሉ ተብሎ ቢጠበቅም ለአገር ውስጥ የሚፈለገውን 6.5 ሚሊዮን ኩንታል ማምረት ተስኗቸዋል፡፡ በሚፈለገው መጠን የሸንኮራ አገዳ አቅርቦት አለመኖሩ አንዱ ምክንያት መሆኑን ኮርፖሬሽኑ ቢያቀርብም ዋናው ምክንያት ግን ለሸንኮራ ልማት የሚመደበው ገንዘብ ወያኔዎች ሙልጭ እያደረጉ ስለዘረፉት እንደሆነ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ያስረዳሉ፡፡

 ከተመረጡት የሸንኮራ አገዳ እርሻ አካባቢዎች አንዱ የሆነው በደቡብ ኦሞ የሚገኘው ነው፡፡ ይህን የእርሻ ልማት ለማካሄድ መወሰኑን ለአካባቢው ሕዝብ ለውያይት አቅርበው ማስወሰን ሲገባቸው በማን አለብኝነት በመሬቱ ላይ የሰፈሩትን በማፈናቀል በመሆኑ ሕዝቡ ተቃውሞውን እየገለጸ ይገኛል፡፡

 ከአሁ ቀደም የግልገል ግቤ ግድብ ሲገነባ የውሀው ፍሰት ለአካባቢው ሕዝብ ችግር እንደ ሚፈጥር በመጥቀስ ሕዝቡ ተቃውሞውን ባሰማበት ወቅት የወያኔ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በአካባቢው ሰፍሮ የሚያስተባብሩትን እንደ ደበደበና እንዳሰቃየ ይታወሳል፡፡

 ይህ በእንዲህ እንዳለ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ውስጥ ስኳር በከፍተኛ ደረጃ ከገበያ እየጠፋ በመሆኑ የህንድ አግሮ ክሮፕ ኢንተርናሽናል ከሚባል ድርጅት 75 ሺ ቶን ስኳር በ29.7 ሚሊዮን ዶላር ለመግዛት ስምምነት ፈጽሟል፡፡

 በአሁኑ ወቅት ገበያ ላይ ያለው ስኳር ብዙዎቹ የኬሚካል ቅልቅል እንዳለበት በማማረር ሲናገሩ ይሰማል፡፡ ወያኔ ልክ እንደ ቅባት እህል የስኳር ምርትን በአብዛኛው ለውጪ ገበያ እያቀረበ በምትኩ በጤና ላይ ችግር ሊያስከትል የሚችል ማስገባቱ የወያኔን ደንታ ቢስነት ብቻ ሳይሆን ፀረ- ሕዝብነትም የሚሳይ መሆኑን በርካቶች ይስማሙበታል

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar