tirsdag 3. november 2015

በቡሬ ግንባር ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የህወሓት መራሹ መከላከያ ሰራዊት አባላት ከዱ

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ) ባጠቃላይ በአራቱም ማዕዘን የኢትዮጵያ ጠረፎች በቀበሮ ጉድጓድ ውስጥ የሚኖረው በህወሓት ቁጥጥር ስር የሚገኘው መከላከያ ሰራዊት አባላት በየዕለቱ ያለማቋረጥ ስርዓቱን እየከዱ ሲሆን በተለይም ደግሞ ከሰሞኑ ቡሬ ግንባር በስልጠና ላይ ይገኙ የነበሩ እጅግ በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወታደሮች ያገኙትን ቀዳዳ ተጠቅመው በቡድን በቡድን እየሆኑ በመሽሎክ ከአካባቢው ተሰውረዋል፡፡ ወሎ ውስጥ ከአንድ ቀበሌ ብቻ 10 ወታደሮች ከጦር ግንባር ከድተው ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡ አሁንም ቢሆን አብዛኛው ሰራዊት መሽሎኪያ ቀዳዳ እያነፈነፈ ሊከዳ በቋፍ ላይ እንደሚገኝ የመከላከያ ምንጮቻችን የላኩት መረጃ ያረጋግጣል፡፡
clash

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar