onsdag 18. november 2015

እነ ማቲያስ መኩሪያ ጥፋተኛ ተባሉ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
አይ ኤስ በኢትዮጵውያን ላይ የፈፀመውን አሰቃቂ ድርጊት ለመቃወም መንግስት በጠራው ሰልፍ ሰበብ የታሰሩት ማቲያስ መኩሪያ፣ ብሌን መስፍን፣ ተዋቸው ዳምጤ እና መሳይ ደጉሰው ዛሬ ህዳር 8/2008 ዓ.ም በፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በመናገሻ ምድብ ችሎት ቀርበው ጥፋተኛ ተብለዋል፡፡
ችሎቱ በቢሮ ከመታየቱም ባሻገር ችሎት አስከባሪው ‹‹መግባት አይቻልም፡፡ ተከልክሏል፡፡ የከለከልኩት ግን እኔ አይደለሁም፡፡›› በማለቱ ማንም እንዳይገባ ተከልክሎ በዝግ ታይቷል፡፡ ፖሊስ ተከሳሾቹ ላይ የቪዲዮ ማስረጃ አለኝ በማለቱ ተከሳሾቹም ‹‹የቪዲዮ ማስረጃው ለእኛም በመከላከያ ማስረጃነት ስለሚያገለግለን ይቅረብልን›› ባሉት መሰረት ቪዲዮውን አይቶ ብይን ለመስጠት ለወራት ሲቀጠርባቸው ቆይቷል፡፡
ከመሳይ ደጉሰው ውጭ ያሉት ተከሳሾች የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ናቸው፡፡ ተከሳሾቹ ከታሰሩ ከ6 ወር በላይ የሆናቸው ሲሆን በፍርድ ሂደቱ ከፍተኛ መጉላላት እየደረሰባቸው እንደሆነ በተደጋጋሚ ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡ እነ ማቲያስን ጥፋተኛ ያለው ፍርድ ቤቱ ለህዳር 22/2008 ዓ.ም ለውሳኔ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar