onsdag 11. oktober 2017

ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት አደገኛ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ተመድ አስታወቀ

(BBN) ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በከባድ ችግር ላይ እንደሚገኙ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ፡፡ ድርጅቱ የሀገራቱን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርት፣ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን አሁን ያሉበት ሁኔታ አሳሳቢ ነው ብሏል፡፡ በኢትዮጵያ እና በሌለቹ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የተከሰተው ድርቅ አስቸኳይ መፍትኤ ካልተሰጠው የሚያስከትለው ጠንቅ ከፍተኛ መሆኑንም ተመድ አስገንዝቧል፡፡

በተለይ በምስራቅ አፍሪካ ላይ ያተኮረው የመንግስታቱ ድርጅት ሪፖርት፣ ቀጠናው ከድርቅ በተጨማሪ በእርስ በእርስ ጦርነት ጭምር እየተፈተነ እንደሚገኝም አብራርቷል፡፡ በተለይ ደቡብ ሱዳን በአሁን ሰዓት በከፋ የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ እንደምትገኝ የጠቀሰው ሪፖርቱ፣ ሀገሪቱን ድርቅ በአንድ በኩል፣ በሌላ በኩል ደግሞ ጦርነት ሰቅዘው እንደያዟትም ሪፖርቱ ይገልጻል፡፡ በኢትዮጵያ፣ በኬንያ፣ በሶማሊያ ወይም ባጠቃላይ በምስራቅ አፍሪካ 24 ሚሊዬን ሰዎች በድርቅ መጎዳታቸውንም ተመድ አስታውቋል፡፡ ይህ ሁሉ ህዝብም አፋጣኝ እርዳታ እንደሚያስፈልገው ድርጅቱ በሪፖርቱ አሳስቧል፡፡ ድርቁ ወይም የረሃብ አደጋው የሌሎች ረድኤት ተቋማትን እርብርብ የሚጠይቅ እንደሆነ የጠቀሰው ተመድ፣ ለተረጂዎችም በአስቸኳይ መድረስ እንደሚያስፈልግ አሳውቋል፡፡
በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ 8 ነጥብ 5 ሚሊዬን ሰዎችን እያጠቃ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ ድርቁ አድማሱን እያሰፋ በመጣበት በዚህ ወቅት ለተረጂዎች እየተደረገ ያለው እርዳታ በቂ አለመሆኑ እየተነገረ ይገኛል፡፡ በተለይ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ያለው ድርቅ ከግጭቱ ጋር ተደማምሮ ወደ አስከፊ ምዕራፍ ተሸጋግሯል፡፡ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ የድንበር ቦታዎች ላይ የተፈጠረው ግጭት፣ ለድርቅ ተጎጂዎች እርዳታ ለማቅረብ ጋሬጣ እየሆነ መምጣቱ ከዚህ በፊት ሲገለጽ ነበር፡፡

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህንጻ ተደርምሶ የሰዎች ህይወት ተቀጠፈ

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሚገኝ አንድ ህንጻ መወጣጫው ተደርምሶ የሰዎች ህይወት መቀጠፉ ታወቀ፡፡ ህንጻው ገና ተገንብቶ ያላለቀ እና በመገንባት ላይ እንደነበረም ተነግሯል፡፡ አደጋው ሲደርስ ሰራተኞች በስራ ላይ የነበሩ ሲሆን፣ ወደ ህንጻው የሚያስወጣው እና የሚያስወርደው መሰላል መሰል መወጣጫ ድንገት በመደርመሱ አደጋው ሊደርስ እንደቻለ የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡ አደጋው ድንገት ሊከሰት የቻለበት ምክንያት እስካሁን ድረስ በይፋ አልታወቀም፡፡
የአደጋውን መድረስ ተከትሎ ሁለት ሰዎች ወዲያው ሲሞቱ፣ አስር ሰዎች ደግሞ ቀላል እና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ህክምና ተቋማት ተወስደዋል፡፡ ዛሬ መስከረም 30 ቀን 2010 ከረፋዱ አራት ሰዓት አካባቢ የደረሰው ይኸው ድንገተኛ አደጋ፣ የአንድ ወንድ እና የአንድ ሴት ህይወትን ሊቀጥፍ ችሏል፡፡ ከተጎጂዎች መካከል ደግሞ ስምንቱ ሴቶች ሲሆኑ፣ ሁለቱ ደግሞ ወንዶች መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ሰራተኞቹ አደጋው ሲደርስ በስራ ላይ እንደነበሩም ተገልጿል፡፡
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በይፋዊ ድረ ገጹ ላይ ያሰፈረው መረጃ እንደጠቆመው፣ ከሁለቱ ሟቾች ውስጥ ሴቷ ወዲያው ህይወቷ ሲያልፍ፣ ወንዱ ሟች ደግሞ ወደ ህክምና ጣብያ ተወስዶ ህክምና እየተደረገለት ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ሁኔታው አሳዛኝ ክስተት እንደሆነም ገልጿል፡፡ ከህንጻ ግንባታ ጋር ተይይዞ በርካታ አደጋዎች እየተከሱ ያሉት በአዲስ አበባ ሲሆን፣ በከተማዋ ጥቂት የማይባሉ 

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar