አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን/ቴዲ አፍሮ/በባህር ዳር ከተማ የሙዚቃ ኮንሰርት ሊያዘጋጅ ነው፡፡ቴዲ አፍሮ ከአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ጋር ልዩ ቃለ-መጠይቅ ዝግጅት ይኖረዋል፡፡
አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን/ቴዲ አፍሮ/ በባህር ዳር ከተማ የሙዚቃ ኮንሰርት ለማቅረብ ያቀረበው ጥያቄ በክልሉ መንግስትና በከተማ አስተዳደሩ ፍቃድ አግኝቷል፡፡ስለሆነም ጥር 12/2010 ዓ/ም ‹‹ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር››የሚለው የፍቅር ጉዞ ኮንሰርት በአማራ ክልል መዲና ባህር ዳር ከተማ ይካሄዳል፡፡
የአርቲስት ቴዲ አፍሮ ማኔጀር አቶ ጌታቸው ማንጉዳይ ጥር 12 በዉቢቷ ባህር ዳር አርቲስቱ የሙዚቃ ኮንሰርቱን እንዲያቀርብ የአማራ ክልል መንግስት እና የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ፍቃድ የሰጠዉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ኮንሰርቱም በተያዘለት ጊዜ በባህር ዳር ከተማ ይካሄዳል ብለዋል፡፡
የአማራ ክልል ኮምንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዳይሬክተር አቶ ንጉሱ ጥላሁን ‹‹ኮንሰርቱ ስለ ሰላም ፣ስለ ፍቅር፣ስለአንድነት ፣ስለ አብሮነት እና ስለ ኢትዮጵያዊነት የሚቀነቀንበት ነዉ፡፡ የክልላችን መንግስት እና የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የአርቲስቱን ጥያቄ ተቀብሎ ፈቃድ ሰጥቶታል ›› ብለዋል።
አርቲስት ቴዲ አፍሮ ኢትዮጵያ የሚለውን አልበም ከለቀቀ በኋላ የሚያቀርበዉ የመጀመሪያ የሙዚቃ ኮንሰርቱ ነው፡፡
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar