mandag 7. april 2014

ያልዘሩትን ማጨድ ከቶ አይቻልም!!


የወያኔ መንግስት የኢትዮጵያን ብሄር ብሄረሰቦች አጋጭቶ በመካከላቸው ጥርጣሬና መፈራራት አንግሶና የታሪክ ጠባሳዎችን እንደ አዲስ በመጓጐጥ እያደማ ከፋፍሎ ለመግዛት ካለመታከት ያደረጋቸው ሙከራዎች ገና ፍሬ ባያፈሩም ቁጥቋጦዎቹ መብቀል ጀምረዋል። እዚህም እዚያም በካድሬዎች የውስጥ ለውስጥ ተልእኮ የሚለኮሱ እሳቶች መብለጭለጭ ጀምረዋል። ሌላው ቀርቶ በአንድ ብሄረሰብ መሃል ሳይቀር በከባቢ ልዩነቶች ብቻ መናቆሮችና መጋደሎች እያስተዋልን ነው። ሰሞኑን በጉጂና በቦረና ኦሮሞዎች መካከል የወያኔ ሎሌዎች በሚያበረታቱት አተካሮ የብዙ ወገኖቻችን ህይወት ጠፍቷል። ሰዎች ከኑሮአቸው ተፈናቅለዋል። ወያኔ እንደኳስ ጨዋታ ተመልካች ዳር ሆኖ ይመለከታል፣ ያጨብጭባል።

ሰሞኑን ባህርዳር ከተማ ውስጥ በተካሄደ የስፖርት ውድድር ላይ አሳፋሪ ክስተት ነበር። ለሰሚው የሚቀፍ ብልግና የተቀላቀለበት ስድብና ቁርቋሶ አይተናል። ከበስተጀርባ ሆነው ይህንን ለፍቅር ብቻ ሊውል የሚገባ የስፖርት ዝግጅት መርዝ ረጭተውበታል። ከዚህ ላቅ ያሉ የተንኮል ድግሶችም ተደግሰው ህዝብ ውስጥ በወያኔ ከተነዙ የመርዝ ቢልቃቶች ውስጥ ስራ ላይ ሳይውሉ ቀርተዋል።

ይህ በታሪካችን ታይቶ የማይታወቅ ዘር የሚዘራው ወያኔ ያልተከፋፈለ ህዝብ አይገዛልኝም በሚል ፍልስፍና እንደሆነ በተደጋጋሚ እያየን ነው። ሶማሌ ክልል ውስጥ በተቋቋሙ ልዩ ፖሊስ በሚል ስያሜ በሚጠሩ የመንግስት ሃይሎች ጥቃት ቁጥሩ እጅግ በርካታ የሆነ የኦሮሞ ማህበረሰብ ከኖረበት መሬት ተጠራርጎ እንዲወጣ ተደርጓል። ብዙዎቹ ተገድለዋል። ብዙ ደም መቃበት ተፈጥሯል። በየክልሉ ምስኪን የአማራ ገበሬዎችን መሬት ንብረት በመንጠቅ አከባቢውን ለቀው እንዲሄዱ አድርገዋል። መሄጃ የለንም ያሉትንም ቀጥቅጠው እንደገደሏቸው ሰሞኑን ከጅባትና ሜጫ አካባቢ ያሉ መረጃዎችን አይተናል።

እነዚህ በየቦታው የሚብለጨለጩ እሳቶች በዚህ ከቀጠሉ ሁላችንም ወደ ሚያቃጥልና የሚለበልብ የሰደድ እሳት ማደጉ አይቀርም። የወያኔ ባለሟሎች ካለምንም ይሉኝታና ማሰላሰል ይህንን እሳት እያራገቡ ይገኛሉ።

ይህንን አደገኛ አዝማሚያ በንጭጩ ማስወገድ የሚችለው ራሱ ህዝቡና የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ የነጻነት ሃይሎች ድምጽና ህብረት እንጂ የወያኔ መንግስት አይደለም። ስለዚህ ህዝቡ በተለይም ወጣቶች ከዚህ ወጥመድ ሰብረው እንዲወጡ ግንቦት 7 የነጻነት፣ የፍትህና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አጥብቆ ያሳስባል። ተመሳሳይ ተንኮሎችንም ማጋለጡን ይቀጥላል። የብሄርሰብ ልሂቃንም ይህንን መርዝ እንዲቋቋሙ፣ ይልቁንም ወያኔ እንዳይመቸው ይበልጥ መቀራረብና ፈተናውን በጋራ እንድንቋቋም ጥሪያችን በድጋሜ እናቀርባለን።

ያልተዘራ አይታጨድም። ወያኔ የዘራልን መርዝ የሚያፈራው መርዝን እንጂ ሌላ አይደለም። ልዩነቶቻችን እንደዘመኑ በሰለጠነ ዲሞክራሲያዊ መንገድ እንጂ በተያዘው መንገድ ማስወገድ አይቻልም።

ዞሮ ዞሮ በዚህ ሳይጣናዊ የወያኔ መሰሪ ሴራ ለምትፈስ ለእያንዳንዶ የደም ጠብታ ተጠያቂው የወያኔ ጉጅሌ መሆኑን አጥብቀን እናሳስባለን። በመሆኑም ለመከፋፈል ከመመቻቸት ይልቅ አንድነታችን በማጥበቅ የነጻነት ሃይሎችን በመቀላቀል ራሳችን እና የሀገራችንን ህልውና ከዚህ ከወያኔ የመከፋፈል መርዝ እንታደግ።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

የአዲስ አበባ መስተዳድር ለመጪው እሁድ ሰልፍ እውቅና እንደሚሰጥ አስታወቀ፤ አንድነት የአዲስ አበባ መስተዳድርን ሰነድ ጠየቀ

የአዲስ አበባ መስተዳድር የሰላማዊ ሰልፍና የፖለቲካ ስብሰባ ክፍል ኦፊሰር የሆኑትን አቶ ማርቆስ ብዙነህን ለማነጋገር ዛሬ ጠዋት ወደ ቢሯቸው ያቀኑት ሶስት የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ አመራሮች በኦፊሰሩ ጥያቄያቸው ተቀባይነት ማግኘቱ እንደተነገራቸው ገልጸዋል፡፡
አንድነት ፓርቲ የ‹‹እሪታ ቀን›› በማለት የሰየመውን ሰላማዊ ሰልፍ ለመጋቢት 28 ቀን 2006 ለማድረግ ለመስተዳድሩ የእውቅና ጥያቄ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም መስተዳድሩ በከተማው የህዳሴ ግድቡን የተመለከቱ ዝግጅቶች በመኖራቸው ቀኑን አስተላልፉ በማለቱ ፓርቲው ሰላማዊ ሰልፉን ለአንድ ሳምንት በማራዘም ባሳለፍነው አርብ ለመስተዳድሩ በድጋሚ ደብዳቤ አስገብቶ ነበር፡፡
የደብዳቤውን ምላሽ ለመጠየቅ ዛሬ ያቀኑት የአንድነት የአዲስ አበባ አመራሮች አቶ ማርቆስን አግኝተው‹‹ሰላማዊ ሰልፉ እውቅና አግኝቷል፡፡ሰልፉ ስለሚደረግበት ቦታ ለመወሰን ሀላፊዎች እየተነጋገሩ በመሆኑ ነገ ጠዋት ወረቀቱን እንሰጣችኋለን››መባላቸውን ተናግረዋል፡፡
በተያያዘም ዜና አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለአዲስ አበባ መስተዳድር የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል አስገብቶት ለነበረ የሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ደብዳቤ የማሳወቂያ ክፍሉ ኦፊሰር በጻፉት የመልስ ደብዳቤ ‹‹የአዲስ አበባ የሰላማዊ ሰልፍና የፖለቲካ ስብሰባ ስነ ስርዓት ›› የሚል ቃል ተጠቅመው ነበር፡፡
ፓርቲው ፓርላማው ካወጣው የሰላማዊ ሰልፍና ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ ስነ ስርዓት አዋጅ ውጪ በኦፊሰሩ የተጠቀሰውን የስነ ስርዓት ደንብ ባለማግኘቱ የሰልፍና የስብሰባ ጥያቄ በሚያቀርብበት ወቅት ስነ ስርዓቱን እንዲያውቀው፣ መስተዳድሩ ያወጣው የስነ ስርዓት ደንብም ፓርላማው ካወጣው አዋጅ ጋር መቃረን አለመቃረኑን ለመመልከት ይረዳው ዘንድ ዛሬ ለሚመለከተው አካል ሰነዱን ይሰጡት ዘንድ ደብዳቤ አስገብቷል፡፡10157158_10201810226918255_7745118086856340863_n

ኢቦኒ የተባለው መጽሄት ተዘጋ

ላለፉት 6 አመታት በህትመት ላይ የነበረው ኢቦኒ መጽሄት የተዘጋው ከመንግስት ከፍተኛ የሆነ የግብር እዳ ከተጣለበት በሁዋላ ነው። ጋዜጠኛ በትረ ያቆብ የመጽሄቱን ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተሰማ ደሳለኝን ጠቅሶ እንደዘገበው የመጽሄቱ አዘጋጆች ሙሉውን ግብር ቀርቶ ግማሹንም ለመክፈል ባለመቻላቸው መጽሄቱን ለመዝጋት ተገደዋል። ድርጅቱ ከወረቀት እና ከሌሎች የህትመት ወጪዎች ጋር በተያያዘ ለከፍተኛ የገንዘብ ችግር ተዳርጎ በሚገኝበት ሰአት የግብር እዳው መምጣቱን ዘገባው አመልክቷል።
ኢቦኒ በመዝናኛ ጋዜጣነት ስራውን ቢጀምርም ካለፉት 2 አመታት ጀምሮ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮችንም መዘገብ ጀምሮ ነበር። ጋዜጠኛው ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን ጽሁፎች ማተም ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በደህንነት ሃይሎች እይታ ውስጥ ገብቶ ቆይቷል። የመጽሄቱ የቀድሞው ዋና አዘጋጅ ብስራት ወልደ ሚካኤል በ4 የደህንነት ሰራተኞች ታፍኖ ተወስዶ መደብደቡም በዘገባው ተጠቅሷል።
በወረቀትና በሌሎችም የማተሚያ ወጪዎች የተነሳ እየተንገዳገደ የሚገኘው የተወሰነው የግሉ ፕሬስ ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ከፍተኛ የሆነ ግብር እየተጣለበት እንዲሽመደመድ እየተደረገ ነው።
አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ኢትዮጵያ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት የማይከበርባት አገር ሲሉ ይፈርጁዋታል። ከጋዜጠኝነት ስራቸው ጋር በተያያዘ ለእስራት ከተዳረጉት መካከል እስክንድር ነጋ፣ ርእዮት አለሙ፣ ውብሽት ታየና የሱፍ ጌታቸው ይገኙበታል።
በለዘብተኝነተቻው ወይም በኢህአዴግ ደጋፊነታቸው ሳይቀር የሚታወቁት ጋዜጦች ከማተሚያ ቤት ችግር ጋር በተያያዘ በእለቱ አይወጡም።

søndag 6. april 2014

ከ60 ሺህ በላይ የከተማው ነዋሪዎች የተሳተፉበት ይህ ሰላማዊ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ!! “እድሜ ለአንድነት አስተነፈሰን !!! ” የደሴ ነዋሪዎች

የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባለቤትነት” በሚል መሪቃል በደሴ የተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡ በስፍራው የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ ከፍተና አመራሮችና የዞን አመራሮች በሰልፉ ለተሳተፈው የደሴ ህዝብ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ‪የደሴ ነዋሪዎችም “እድሜ ለአንድነት አስተነፈሰን” በማለት ደስታቸውን ገልጸዋል።
የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት በሚል መሪ ቃል አንድነት ፓርቲ የጀመረውን ዘመቻ በማስመልከት የመጀመሪያውን ሰላማዊ ሰልፍ በደሴ ከተማ በተሳካ ሁኔታ ማድረጉ ታውቋል።
ከቅስቀሳ ጀምሮ በደህንነቶች እና በፖሊስ ሃይሎች ወከባ እና መንግስታዊ ውንብድና የተደረገበት የደሴው ሰልፍ ህዝቡ ከፓርቲው ጎን በመቆም ለመብቱ እና ለነጻነት ያለውን ቀናኢነት በማሳየት ትልቅ ትብብር አድርግዋል። በደሴ ከተማ በዛሬው እለት የተደረገው ሰልፍ ከጠዋት ጀምሮ ህዝቡ ፍርሃቱን በመስበር ወደ አደባባይ ወጥቶ ብሶቱን ያሰማ ሲሆን ፖሊሶች መንገድ በመዝጋት ሽብር ለመፍጠር ቢሞክሩም ህዝቡ እያሳበረ በሰልፉ ላይ በመገኘት ተቃውሞውን አሰምቷል።
ከ60 ሺህ በላይ የከተማው ነዋሪዎች የተሳተፉበት ይህ ሰላማዊ ሰልፍ በተለያዩ መፈክሮች ደምቆ ነበር።ህዝቡ አንግቦት ክንበሩት መፈክሮች ውስጥ ፦
-መሬት ከካድሬው ወደ ህዝቡ ይመለስ – አንድነት ኃይል ነው
- የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ – መሬት ለህዝብ ይመለስ
- ጭቆና በቃን – ድል የህዝብ ነው – በግፍ የታሰሩ ይፈቱ ……… የሚሉ ይገኙበታል።
የደሴው ሰላማዊ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ እየተካሄደ በነበረበት ወቅት የአዲስ አበባ ፖሊሶች እና ደህንነቶች ቀበና ሼል አከባቢ የሚገኘውን የአንድነት ዋና ጽ/ቤት በመክበብ ወከባ ሲፈጽሙ ተስተውሏል።
በደሴው ሰላማው ሰላፍ ላይ የአንድነት ከፍተኛ አመራሮች የሆኑት ተቀዳሚ ም/ፕሬዝዳንቱ አቶ ተክሌ በቀለ እንዲሁም የውጪ ጉዳይ ሃላፊው ዘለቅ ረዲ የደሴ የአንድነት ሰብሳቢ ንግግር ማድረጋቸው ታውቋል። የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባለቤትነት” በሚል መሪቃል በደሴ የተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡ በስፍራው የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ ከፍተና አመራሮችና የዞን አመራሮች በሰልፉ ለተሳተፈው የደሴ ህዝብ ምስጋና አቅርበዋል፡፡10015653_835736346442828_702939082745029919_n
10152391_835736339776162_7351371086334858666_n
10153092_836259806390482_8153608612627631063_n
10155032_616009748483963_362900362438077475_n
10155823_835669356449527_3760871470725215523_n

fredag 4. april 2014

የአዲስ አበባዉ ሰልፍ ለሚያዚያ 5 ተላለፈ !

አንድነት ፓርቲ «ህግን እያከበርን የማስከበር ኃላፊነታችንን እንወጣለን» በሚል ርእስ ዛሬ መጋቢት 26 ቀን 2006 ዓ.ም ይፋ ባደረገው መግለጫ «የአዲስ አበባ ከተማ ሠላማዊ ሠልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል በመጋቢት 26 ቀን 2ዐዐ6 ዓም በቁጥር አ.አ ከስ/1ዐ/3ዐ.4/236 በላከልን ደብዳቤ ሠላማዊ ሠልፉን ለማድረግ በጠየቅንበት ቀን ተመሳሳይ የህዳሴ ግድብ ፕሮግራሞች ስላሉ ተለዋጭ ቀን እንድናቀርብ ጠይቆናል፡፡ በዚሁ መሠረት ለመጋቢት 28 ቀን 2ዐዐ6 ዓም ለማድረግ የያዝነውን ፕሮግራም ለማሸጋገር የህግ ግዴታ ስላለብን ለሚያዚያ 5 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም ያዛወርን መሆኑን ለኢትዮጵያ ሕዝብ በአክብሮት እንገልፃለን» ሲል መጋቢት 28 ቀን ሊደረግ የታሰበውን የ እሪታ ሰልፍ ለሚያዚያ 5 መተላለፉን አሳዉቋል።
UDJ

onsdag 2. april 2014

የሙስሊም መሪዎች የፍርድ ሒደት

ተከሳሾች ለፍርድ ቤቱ በሰጡት ቃል አሸባሪዎች እንዳልሆኑ፤ እስር ቤት ዉስጥ እንደተደበደቡ፤ እንደተሰቃዩና ያልተናገሩትንና ያላሉትን እንዳሉ ተደርጎ እንዲፈርሙ መርማሪዎች እንዳስፈራሯቸው ገልፀዋል
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአሸባሪነት የተከሰሱ የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ መሪዎችን የተከሳሽነት ቃል መቀበሉን ዛሬም ቀጥሎ ዉሏል።ቃሊት ያስቻለዉ የፍርድ ቤቱ አራተኛ መደበኛ ችሎት ትናንት የአንደኛ ተከሳሽ የአቡበከር አሕመድን ቃል አድምጦ ነበር።ዛሬ ደግሞ የሁለተኛ እና የሰወስተኛ ተከሳሾችን ቃል አድምጦ የተቀሩትን ተከሳሾች ቃል ለማድመጥ ለነገ-ቀጠሮ ሠጥቷል።ተከሳሾች ለፍርድ ቤቱ በሰጡት ቃል አሸባሪዎች እንዳልሆኑ፤ እስር ቤት ዉስጥ እንደተደበደቡ፤ እንደተሰቃዩና ያልተናገሩትንና ያላሉትን እንዳሉ ተደርጎ እንዲፈርሙ መርማሪዎች እንዳስፈራሯቸው ገልፀዋል።

በአዋሳ ታቦር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተነሳ ግጭት ተማሪዎች ተጎዱ



ከቋንቋ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ በተነሳው ግጭት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ተማሪዎች ከቀላል እስከ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የፌደራል ፖሊስ አባላት ከትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ የሚወጡ ተማሪዎችን ሲደበድቡ የታዩ ሲሆን፣ በውስጥ ያሉ ተማሪዎችም እንዲሁ ድንጋይ ሲወረወሩ መታየታቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል።
ግጭቱ ተባብሶ በመሄዱ የፌደራል ፖሊስ አባላት ጥይቶችን በተደጋጋሚ ተኩሰዋል። ታቦር ትምህርት ቤት መዘጋቱንም ለማወቅ ተችሎአል።
አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ሰው ከግጭቶች ጀርባ የአካባቢው ባለስልጣናት እጅ አለበት ይላሉ።በተለይም አዋሳን ወደ ፌደራሉ መንግስት ለማዘዋወር በማሰብ አንዳንድ ቦታዎች ላይ የስም ለውጦች ማድረግ በመጀመሩ ግጭቱ እንደተነሳ የሚናገሩት ወገኖች፣ ተማሪዎች ያኑሰዋቸው ጥያቄዎች በቀላሉ የሚፈቱ ሆነው ሳለ የመንግስት ባለስልጣናት ዝምታን መምረጣቸው ከግጭቱ ጀርባ እጃቸው እንዳለበት ያመላክታል ይላሉ።
በሌላ በኩል ደግሞ ከማንነት ጋር በተያያዘ እየታየ ያለው ችግር ካለፉት 5 አመታት ጀምሮ እየተጠናከረ መምጣቱን የሚናገሩት አንዳንድ ነዋሪዎች፣ በተማሪዎች የተነሳው ግጭት ከቋንቋ ጋር ብቻ መታየት እንደሌለበትና ችግሩ ስር እየሰደደ የመጣ ጉዳይ መሆኑን በማስታወስ ያስጠነቀቅቃሉ።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ እየታየ ለመጣው ከማንነትና ከጎሳ ጋር በተያያዘ ለሚፈጠሩ ችግሮች አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ከመጪው ምርጫ ጋር ሲያያይዙት ሌሎች ወገኖች ደግሞ ገዢው ፓርቲ የሚከተለው የብሄር ፖለቲካ አስከፊ ደረጃ ላይ እየደረሰ መሆኑን ያስጠነቅቃሉ።
በባህርዳር በተደረገው የክልሎች የስፖርት ጨዋታ ላይ የስነምግባር ጉድለት መታየቱ፣ በጉጂና በቦረናዎች መካከል  ግጭት መነሳቱ፣ በሻኪሶ በተነሳ ረብሻ ጉዳት መድረሱ ይታወቃል።