የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባለቤትነት” በሚል መሪቃል በደሴ የተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡ በስፍራው የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ ከፍተና አመራሮችና የዞን አመራሮች በሰልፉ ለተሳተፈው የደሴ ህዝብ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ የደሴ ነዋሪዎችም “እድሜ ለአንድነት አስተነፈሰን” በማለት ደስታቸውን ገልጸዋል።
የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት በሚል መሪ ቃል አንድነት ፓርቲ የጀመረውን ዘመቻ በማስመልከት የመጀመሪያውን ሰላማዊ ሰልፍ በደሴ ከተማ በተሳካ ሁኔታ ማድረጉ ታውቋል።
ከቅስቀሳ ጀምሮ በደህንነቶች እና በፖሊስ ሃይሎች ወከባ እና መንግስታዊ ውንብድና የተደረገበት የደሴው ሰልፍ ህዝቡ ከፓርቲው ጎን በመቆም ለመብቱ እና ለነጻነት ያለውን ቀናኢነት በማሳየት ትልቅ ትብብር አድርግዋል። በደሴ ከተማ በዛሬው እለት የተደረገው ሰልፍ ከጠዋት ጀምሮ ህዝቡ ፍርሃቱን በመስበር ወደ አደባባይ ወጥቶ ብሶቱን ያሰማ ሲሆን ፖሊሶች መንገድ በመዝጋት ሽብር ለመፍጠር ቢሞክሩም ህዝቡ እያሳበረ በሰልፉ ላይ በመገኘት ተቃውሞውን አሰምቷል።

ከ60 ሺህ በላይ የከተማው ነዋሪዎች የተሳተፉበት ይህ ሰላማዊ ሰልፍ በተለያዩ መፈክሮች ደምቆ ነበር።ህዝቡ አንግቦት ክንበሩት መፈክሮች ውስጥ ፦
-መሬት ከካድሬው ወደ ህዝቡ ይመለስ – አንድነት ኃይል ነው
- የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ – መሬት ለህዝብ ይመለስ
- ጭቆና በቃን – ድል የህዝብ ነው – በግፍ የታሰሩ ይፈቱ ……… የሚሉ ይገኙበታል።
የደሴው ሰላማዊ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ እየተካሄደ በነበረበት ወቅት የአዲስ አበባ ፖሊሶች እና ደህንነቶች ቀበና ሼል አከባቢ የሚገኘውን የአንድነት ዋና ጽ/ቤት በመክበብ ወከባ ሲፈጽሙ ተስተውሏል።

Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar