የአዲስ አበባ መስተዳድር የሰላማዊ ሰልፍና የፖለቲካ ስብሰባ ክፍል ኦፊሰር የሆኑትን አቶ ማርቆስ ብዙነህን ለማነጋገር ዛሬ ጠዋት ወደ ቢሯቸው ያቀኑት ሶስት የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ አመራሮች በኦፊሰሩ ጥያቄያቸው ተቀባይነት ማግኘቱ እንደተነገራቸው ገልጸዋል፡፡
አንድነት ፓርቲ የ‹‹እሪታ ቀን›› በማለት የሰየመውን ሰላማዊ ሰልፍ ለመጋቢት 28 ቀን 2006 ለማድረግ ለመስተዳድሩ የእውቅና ጥያቄ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም መስተዳድሩ በከተማው የህዳሴ ግድቡን የተመለከቱ ዝግጅቶች በመኖራቸው ቀኑን አስተላልፉ በማለቱ ፓርቲው ሰላማዊ ሰልፉን ለአንድ ሳምንት በማራዘም ባሳለፍነው አርብ ለመስተዳድሩ በድጋሚ ደብዳቤ አስገብቶ ነበር፡፡
የደብዳቤውን ምላሽ ለመጠየቅ ዛሬ ያቀኑት የአንድነት የአዲስ አበባ አመራሮች አቶ ማርቆስን አግኝተው‹‹ሰላማዊ ሰልፉ እውቅና አግኝቷል፡፡ሰልፉ ስለሚደረግበት ቦታ ለመወሰን ሀላፊዎች እየተነጋገሩ በመሆኑ ነገ ጠዋት ወረቀቱን እንሰጣችኋለን››መባላቸውን ተናግረዋል፡፡
የደብዳቤውን ምላሽ ለመጠየቅ ዛሬ ያቀኑት የአንድነት የአዲስ አበባ አመራሮች አቶ ማርቆስን አግኝተው‹‹ሰላማዊ ሰልፉ እውቅና አግኝቷል፡፡ሰልፉ ስለሚደረግበት ቦታ ለመወሰን ሀላፊዎች እየተነጋገሩ በመሆኑ ነገ ጠዋት ወረቀቱን እንሰጣችኋለን››መባላቸውን ተናግረዋል፡፡
በተያያዘም ዜና አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለአዲስ አበባ መስተዳድር የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል አስገብቶት ለነበረ የሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ደብዳቤ የማሳወቂያ ክፍሉ ኦፊሰር በጻፉት የመልስ ደብዳቤ ‹‹የአዲስ አበባ የሰላማዊ ሰልፍና የፖለቲካ ስብሰባ ስነ ስርዓት ›› የሚል ቃል ተጠቅመው ነበር፡፡
ፓርቲው ፓርላማው ካወጣው የሰላማዊ ሰልፍና ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ ስነ ስርዓት አዋጅ ውጪ በኦፊሰሩ የተጠቀሰውን የስነ ስርዓት ደንብ ባለማግኘቱ የሰልፍና የስብሰባ ጥያቄ በሚያቀርብበት ወቅት ስነ ስርዓቱን እንዲያውቀው፣ መስተዳድሩ ያወጣው የስነ ስርዓት ደንብም ፓርላማው ካወጣው አዋጅ ጋር መቃረን አለመቃረኑን ለመመልከት ይረዳው ዘንድ ዛሬ ለሚመለከተው አካል ሰነዱን ይሰጡት ዘንድ ደብዳቤ አስገብቷል፡፡

Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar