torsdag 17. juli 2014

የመከላከያ ሰራዊት አባላት ስርዓቱን በብዛት እየከዱ ነው

የመከላከያ ምንጮች እንደገለጹት ባለፉት 20 ቀናት ብቻ ከባድሜ ግንባር ከ 107 ያላነሱ ሰዎች ከድተው ወደ ኤርትራ እና ወደ መሃል
አገር አቅንተዋል። ከ15 ቀናት በፊት በባድሜ አካባቢ ሲያጎ በተባለው ቦታ ላይ የሰፈሩ 60 የ 33ኛ ክፍለጦር አባላት በአንድ ሌሊት ሰራዊቱን ጥለው የጠፉ ሲሆን፣ ኤርትራ መድረስና
አለመድረሳቸውን ለማወቅ የተደረገው ጥረት እስካሁን አልተሳካም።
ወታደሮቹ የጠፉት በክፈለጦሩ የተደረገውን ግምገማ ተከትሎ ነው።  ከግምገማው በሁዋላ በየቀኑ ቢያንስ 2 ሰዎች ከተለያዩ ክፍለጦሮች እየጠፉ ወደ መሃል አገርና ወደ ኤርትራ ያመራሉ።
7 አመት ያገለገሉ በርካታ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መልቀቂያ ቢያስገቡም፣ መከላከያ ሚኒስቴር ግን ወታደሮቹን ለመልቀቅ እስካሁን ፈቃደኛ አለመሆኑንም ምንጮች ገልጸዋል።  በዚህም የተነሳ
በሰራዊቱ ውስጥ ያለው ውጥረት ተባብሷል። የመከለካያ ሚኒስቴር በቅርቡ በየአገሩ እየዞረ ሰራዊት ለመመልመል ያደረገውም ሙከራም የተፈለገውን ውጤት ሊያመጣ አልቻለም።
ባለፈው ወር መጨረሻ ላይ የ33ኛ ክፍለጦር አባላት ከመቀሌ በተላኩት በኮሎኔል ሃጎስ ገብረማርያም መሪነት እንዲገመገሙ የተደረገ ሲሆን፣ ገምገማውን ተከትሎ  ኮሎኔሉ ሃጎስ በአንድ
ወታደር ተገድለዋል። ምንጮች እንደገለጹት ግምገማ ከመካሄዱ በፊት የእያንዳንዱ ወታደር ክፍል እንዲፈተሽ የተደረገ ሲሆን፣  ኢቻንግ አሊ በተባለ ከጋንቤላ አካባቢ በመጣ ወታደር ማደሪያ
ክፍል ውስጥ መጽሃፍ ቅዱስ ተገኝቷል።  ወታደር ኢቻንግ መጽሀፍ ቅዱስ ለምን እንዳስገና ሲጠየቅ፣ “አባቴ  እንደማስታወሻ የሰጠኝ ነው” በማለት የመለሰ ሲሆን፣ ገምጋሚው ኮሎኔል ሃጎስ ግን
” ይሄ የውትድርና ቦታ እንጅ የሃይማኖት ቦታ አይደለም፣ መጽሃፍ ቅዱስክን ከካምፕ ውስጥ አስወጣ” ብሎ  ትእዛዝ ሰጥቷል።  ወታደር ኢቻንግም መጽሃፍ ቅዱሱን ለማስረከብ ፈቃደኛ ባለመሆኑና
ይህን ካላደረገም  እንደሚታሰር በማወቁ፣  ኮሎኔሉ  ለእረፍት እንደወጣ መሳሪያውን  ከክፍሉ ይዞ በመምጣት በጥይት ደብድቦ ገድሎታል። ወታደር ኢቻንግ ግድያውን ከፈጸመ በሁዋላ  በገዛ መሳሪያው ራሱን አጥፍቷል።
በግምገማው ወቅት ከፍተኛ ትችት የተሰነዘረባቸው 60 የሰራዊቱ አባላት ኮሎኔል ሃጎስ በተገደሉበት እለት፣  ሌሊቱን ተመካክረው በአንድ ጊዜ መጥፋታቸውን ምንጮች አክለው ገልጸዋል።
በባድሜ አካባቢ ያለው እስር ቤት ዋጠው እየተባለ የሚጠራ ሲሆን፣ ጎንና ጎኑ በድንጋይ ተሰርቶ ከስር ስሚንቶ፣ ከስሚንቶው ስር ደግሞ ውሃ እንዳለውና እስረኞችን በቅዝቀዜ ለመቅጣት ተብሎ መዘጋጀቱን
ለማወቅ ትቸሎአል። እስረኛ ወታደሮች ቀኑን ሙሉ ብርሃን ሳያዩ በካቴና እንደታሰሩ እንደሚገረፉ የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል።
በሰራዊቱ ውስጥ እየጨመረ የመጣው ተቃውሞ ያሰጋው መንግስት የደሞዝ ጭማሪ እንደሚያደርግ ቃል በመግባት ለማረጋጋት ቢሞክርም፣  ሰራዊቱ ግን አስተዳዳራዊ በደሎችንና በሰራዊቱ ውስጥ ያለውን
ዘረኝነት በመጥላት፣ የደሞዝ ማማለያውን ባለመቀበል ጥሎ እየጠፋ ሲሆን  አንዳንድ ወታደሮች ደግሞ መልቀቂያቸው ከዛሬ ነገ ይደርሳል በማለት በተስፋ እየተጠባበቁ እንደሚገኙ መረጃው አመልክቷል።
ወታደራዊ አዛዦች በአዲስ አበባና በተለያዩ የአገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች የገነቡዋቸው ዘመናዊ ህንጻዎችና ያካበቱት የሃብት መጠን በሰራዊቱ ውስጥ ተደጋግሞ የሚነሳ ሲሆን፣ በተለይ ከህወሃት ውጭ ያሉ አንዳንድ
የአማራ እና የኦሮሞ ወታደሮች አመጽ ሊያስነሱ ይችላሉ ተብሎ በመጠርጠራቸው ልዩ ክትትል እንደሚደረግባቸው ምንጮች ገልጸዋል። የጋምቤላ ተወላጅ የሰራዊቱ አባላትም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ታማኝነታቸውን
እያጎደሉ ነው በሚል በአንዳንዶች ላይ ልዩ ክትትል እየተደረገባቸው ነው።
አንድ የመከላከያ ሰራዊት አባል ለአባይ ግድብ ማሰሪያ፣ ለመለስ ፋውንዴሽንና ለሌሎችም የክፍያ ትእዛዞች ገንዘብ ከከፈለ በሁዋላ ተቆራርጦ የሚደርሰው ክፍያ ወር እስከ ወር አያደርሰውም።  በአንጻሩ ነባር
ታጋዮች የሚባሉት የህወሃት ጄኔራሎች በመቶ ሚሊዮኖች ብር የሚቆጠር ህንጻዎችን ገንብተው በማከራየት ላይ መሆናቸው ይታወቃል።

onsdag 16. juli 2014

በኢትዮጵያ የእንግሊዝ እርዳታ ፖሊሲ ተግባራዊነት እንዲፈተሽ ታዘዘ

ኢትዮጵያ ውስጥ በአሸባሪነት ተጠርጥረዋል ተብለው የተያዙት 6 የኢንተርኔት ጸሐፍትና 3 ጋዜጠኞች ላይ ፖሊስ ሲያካሂድ የቆየው ምርመራ ተጠናቋል ቢባልም ምንም ዓይነት ውሳኔ እንዳልተሰጣቸው ጠበቃቸው አስታወቁ። ክሳቸው ዛሬ ወደ ሕጋዊ ሥርዓት ካልገባም ነገ ክስ ለመመሥረት ማሰባቸውን ጠበቃቸው አቶ አምሃ መኮንን ዛሬ  ተናግረዋል።
LOGO CPJ
ፖሊስ ምርመራውን ማጠናቀቁን ባለፈው ቅዳሜ ለፍርድ ቤት ያሳወቀው፣ ተጠርጣሪ የተባሉትም ሆነ ጠበቃቸው ባልተገኙበት ነው። ተጠርጣሪዎቹ እንዲሁም ጠበቃቸው ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ መዝገባቸው መዘጋቱን የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ድርጅት CPJ አውግዟል። በአሸባሪነት ተጠርጥረዋል ተብለው የተያዙት 3 ጋዜጠኞችና 6 የኢንተርኔት ጸሐፍት ከታሰሩ 80 ቀን ሆኗቸዋል። በዚህ ጊዜ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ሲጠይቅ የቆየው ፖሊስ ቅዳሜ ሐምሌ 5 2006 ዓም እንዲሁም ሰኞ ሐምሌ 7 2006 ዓም በተጠርጣሪዎቹ ላይ የሚያካሂደውን ምርመራ መጨረሱን ለፍርድ ቤት አስታውቆ የቀጠሮ ምርመራ መዝገቡ ተዘግቷል። ይህ የተደረገበትን መንገድ ግን የተጠርጣሪዎቹ ጠበቃ ተቃውመዋል። የተጠርጣሪዎቹ ጠበቃ አቶ አምሃ መኮንን አሰራሩ ትክክል እንዳልሆነ ነዉ የሚያስረዱት።
Zeitungen Äthiopien
ፖሊስ ምርመራውን መጨረሱን ሲያሳውቅ ተጠርጣሪዎቹም ሆኑ ጠበቃቸው እንዲገኙ አለመደረጉ በጋዜጠኞች መብት ተከራካሪዎች ተወግዟል። ድርጊቱን ካወገዙት ውስጥ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪዎቹ በምህፃሩ CPJ እንዲሁም REPORTERS WITH OUT BORDERSS ይገኙበታል። CPJ ባወጣው መግለጫ መንግሥት የፍርድ ሂደቱን ሕጋዊ ለማስመሰል ቢሞክርም የሚፈፀመው ግን በቀል እና ሂስ አቅራቢዎችን የማፈን(ጭጭ የማሰኘት) ተግባር ነው ብሏል። የድርጅቱ የምሥራቅ አፍሪቃ ወኪል ቶም ሮድስ ባለፈው ቅዳሜና ሰኞ የተፈጸመውን ሕገ ወጥ ተግባር ይሉታል።
«በነፃ የፍርድ ሂደት ከዚህ በፊት ተከሳሾችም ሆኑ ጠበቆች እንዳይቀርቡ ሲደረግ አላየንም። ይህ የኢትዮጵያንም፤ ዓለም ዓቀፍ ሕግንም የሚፃረር ነው። እናም ሁኔታው በጣም ያሳስበናል። በፍርዱ ሂደት ባህርይም እንድንገረም አድርጎናል። የፍርዱ ሂደት ይበልጥ ከፖለቲካ ጋር እንዲያያዝ ተደርጓል።»
በርሳቸው አስተያየት መንግሥት ሂስ እንዲቀርብበት አይፈልግም።
Symbolbild Mann Laptop Blog Blogger
«በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው መርህ ትችትን ለመቀበል ምን ዓይነት ቦታ የማይሰጥ ነው። ምናልባትም ይህ እርምጃ በመጪው ዓመት በግንቦት ከሚካሄደው ምርጫ ጋር የተያያዘ ይሆናል የሚል ጥርጣሬ አለኝ ።»
የ6ቱ የኢንተርኔት ጸሐፊዎችና የ3ቱ ጋዜጠኞች ጠበቃ አቶ አምሃ እሁድና ሰኞ በተፈፀመው ላይ ያላቸውን ቅሬታ በሰኞው ችሎት ለፍርድ ቤቱ አቅርበው ነበር።
አቶ አምሃ እንደሚሉት ፖሊስ ምርመራውን ካጠናቀቀ ደንበኞቻቸው ክስ ሊመሰረትባቸው አለያም በነፃ ሊለቀቁ ይገባ 

የውህደት እንቅስቃሴአችን በተሳካ ሁኔታ ቀጥሏል!! – ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና ከአንድንት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ከጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

ለውህደቱ መሳካት ጥረት እና ድጋፍ እያደረጉ ላሉ ኢትዮጵያውያን ምስጋና እናቀርባለን!1እንደሚታወቀው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የቅድመ ውህደት ስምምነት ፊርማ ካኖሩ በኋላ ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራት ውህደቱን ምሉዕ ለማድረግ የጋራ ኮሚቴ በማቋቋም እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡
ይሄው ውህደት አመቻች ኮሚቴ በስምምነት ሰነዱ በተቀመጠው መሰረት ለማጠናቀቅ ቀን ከሌሊት እየሰራ ሲሆን የሁለቱ አንጋፋ ፓርቲዎች ውህደት የተሳካ እንዲሆን ትንሽ ግዜ መጨመር አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል፡፡ በተለይም ለውህደቱ መሳካት የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን ሰፊ በመሆኑ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ደጋፊዎቻችን የአቅማቸውን ድጋፍ ለማድረግ በስምምነት ሰነዱ የተቀመጠው የውህደት ግዜ ላይ ሁለት ሳምንት መጨመር እንደሚያስፈልግ ታምኖበታል፡፡
ስለዚህ ጉባኤ ጠሪ ኮሚቴው ባደረገው ግምገማ የሁለቱ ፓርቲዎች የውህደት ግዜ ሓምሌ 19 እና 20 እንዲሆን ተስማምቷል፡፡ ከዚህ ውጭ ግን የሁለቱ ፓርቲዎች ረቂቅ ደምብና ፕሮግራም ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ የተጠናቀቀቀ ሲሆን የጉባኤ ተሳታፊዎች የውህደቱን ግዜ በጉጉት እየጠበቁ ይገኛሉ፡፡ በመጨረሻም ሁለቱ ፓርቲዎች ተዋህደውና ሌሎች ፓቲዎች ወደ መሰባሰብ መጥተው የተጠናከረ የተቃውሞ ሃይል እንዲፈጠር ብርቱ ድጋፍ ላደረጉ ኢትዮጵያውያንና የውህደት አመቻች ኮሚቴው ስራ የተቀላጠፈ እንዲሆን ድጋፍ እያደረጉ ላሉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ከፍ ያለ ምስጋና እናቀርባለን፡፡
በመቀጠልም እስከ ውህደቱ ፍፃሜ ድረስ በሀገር ውስጥና በውጭ አገር እየተደረገ ያለው ድጋፍ እንደሚቀጥል በመተማመን ለውህደቱ ድጋፍ የምታደርጉ ኢትዮጵያውያን፡-
መኢአድ፤ አቢሲንያ ባንክ፤ ቦሌ ቅርንጫፍ፤ የባንክ አካውንት ቁጥር፡- AEUP – SP 235
አንድነት፤ አቢሲንያ ባንክ፤ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ የባንክ አካውንት፡- UDJ – A/C 47
በኩል እንድታስገቡ የውህደት አመቻች ኮሚቴው አገራዊ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ስንተባባር እናሸንፈላን!!
ሐምሌ 9 ቀን 2006 ዓ.ም
አዲስ አበባudJAEUP

የድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የፍርድ ሂደት እንደገና ተራዘመ

የተለያዩ ሰበቦች እየቀረቡበት የሚራዘመው የድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የፍርድ ሂደት ዛሬም በችሎት አዳራሽ ለውጥ
ምክንያት እንዲራዘም ተደርጓል።
በአቶ አቡበክር ምዝገብ የተከሰሱት ኮሚቴዎች፣ የመከላከያ ምስክር ለፍርድ ቤቱ ማስደመጥ እንደጀመሩ ነበር የችሎት ሂደቱ በሰባሰብ እንዲራዘም የተደረገው።
ዳኞችና አቃቢ ህጎች በቃሊቲ የሚገኘው የችሎት አዳራሽ ለትራንስፖርት የማያመች በመሆኑ እንዲቀየርላቸው ባመለከተቱት መሰረት አዲሱ ችሎት ሲ ኤም ሲ ሰሚት ተብሎ በሚጠራው
የአቃቂ ቃሊቲ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ቲያትር ቤት አዳራሽ እንዲካሄድ ተወስኗል። ዛሬ የተሰየመው ፍርድ ቤትም ችሎቱ እስኪስተካከል በሚል ቀጠሮውን አራዝሟል። አዳራሹ መቼ ዝግጁ
እንደሚሆን ግን የታወቀ ነገር የለም።  ችሎቶች የሚጓተቱት እስረኞችን ለመቅጣት ታስቦ መሆኑን አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በግፍ ለታሰሩት  የኮሚቴውን አባላት ድጋፍ ለመግለጽና መንግስት ያቀረቡትን ጥያቄ እንዲመልስ ለማስገደድ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ጠንካራ ተቃውሞ ለማዘጋጀት እየተንቀሳቀሱ ነው።
ተቃውሞው የፊታችን አርብ በመላው አገሪቱ እንደሚካሄድ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

በኢትዮጵያ የእንግሊዝ እርዳታ ፖሊሲ ተግባራዊነት እንዲፈተሽ ታዘዘ

የእንግሊዝ የባሕር ማዶ ትብብር ኤጀንሲ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ሲሰጥ ከራሱ የሰብዓዊ መብቶች ፖሊሲዎች ጋር በተጣጣመ መልክ መሆንና አለመሆኑ እንዲፈተሽ አንድ የእንግሊዝ ፍርድ ቤት መወሰኑን የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቹ ሂዩማን ራይትስ ዋች አድንቋል፡፡
ዲፊድ፤ ሂዩማን ራይትስ ዋች እና መንደር ምሥረታ በኢትዮጵያ  

ሌስሊ ሌፍኮው - የሂዩማን ራይትስ ዋች የአፍሪካ መርኃግብር ምክትል ዳይሬክተርሌስሊ ሌፍኮው - የሂዩማን ራይትስ ዋች የአፍሪካ መርኃግብር ምክትል ዳይሬክተር


የእንግሊዝ የባሕር ማዶ ትብብር ኤጀንሲ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ሲሰጥ ከራሱ የሰብዓዊ መብቶች ፖሊሲዎች ጋር በተጣጣመ መልክ መሆንና አለመሆኑ እንዲፈተሽ አንድ የእንግሊዝ ፍርድ ቤት መወሰኑን የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቹ ሂዩማን ራይትስ ዋች አድንቋል፡፡
የእንግሊዝ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትናንት፤ ሐምሌ 7/2006 ዓ.ም ባሣለፈው ውሣኔ የዓለም አቀፍ ትብብር መሥሪያ ቤቱ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ሲሰጥ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን የሚያሳዩ ማስረጃዎችን በበቂ ሁኔታ አይፈትሽም ሲባል የቀረበበት ክሥ ሙሉ የፍርድ ቤት ምርመራ የሚያስፈልገው ነው ብሏል፡፡
የሂዩማን ራይትስ ዋች የአፍሪካ መርኃግብር ምክትል ዳይሬክተር ሌስሊ ሌፍኮው ለዝግጅት ክፍላችን በሰጡት ቃል ይህ የእንግሊዝ ፍርድ ቤት ውሣኔ ገና የመጀመሪያ እርምጃና ሊደነቅ የሚገባው ነው ብለዋል፡፡
ጋምቤላጋምቤላ
በጋምቤላ፣ በሶማሌ ክልልና በደቡብ ኦሞ እየተፈፀሙ ናቸው ያሏቸው አድራጎቶችም የቅርብ ፍተሻ የሚያስፈልጋቸው መሆናቸውን የጠቆሙት ሚስ ሌፍኮው ልማት ከሰብዓዊ መብቶች መከበር ጋር አብሮ መታየት እንደሚገባቸው ለጋሾች ሊገነዘቡ ይገባል ብለዋል ሚስ ሌፍኮው፡፡
መሠረታዊ የልማት ድጋፍ ይቁም የሚል አቋም ሂዩማን ራይትስ ዋች እንደሌለው ሌፍኮው አመልክተው የእንግሊዝ መንግሥት ለኢትዮጵያ በሚሰጠው እርዳታ ሰብዓዊ መብቶችን የሚረግጡ ፕሮጀክቶችን የሚያስፈፅሙ ባለሥልጣናት ደመወዝ እንደሚከፈል አመልክተዋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በሕግ በተያዘ ጉዳይ ላይ አስታያየት እንማይሰጥ የተናገረው የእንግሊዝ የዓለምአቀፍ ልማት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት እንግሊዝ ለኢትዮጵያ የሠፈራ መርኃግብር የገንዘብ ድጋፍ ሰጥታ እንደማታውቅ ገልጿል፡፡
“መሠረታዊ አገልግሎቶችን ለመጠበቅ የምንሰጠው ድጋፍ የሚውለው እንደ ጤናጥበቃ፣ ትምህርት ቤቶች እና ንፁህ ውኃን ለመሳሰሉ አገልግሎቶች ነው” ብሏል መሥሪያ ቤቱ በኢሜል በሰጠን ምላሽ፡፡
የኢትዮጵያ ባለሥልጣናትም የሠፈራ መርኃ ግብሩ የሚካሄደው በሠፋሪዎቹ ፍቃደኝነትና በግልፅነት መሆኑን ይናገራሉ፡፡
ሰዎች በቀልን በመፍራት ምክንያት አስተያየቶቻቸውን ለመግለፅ እንደማይፈልጉና መንግሥቱ በመገናኛ ብዙኃን ላይ በተከታታይ አፈና እየፈፀመ መሆኑን የሂዩማን ራይትስ ዋች መግለጫ አመልክቷል፡፡
እንግሊዝ ለኢትዮጵያ በየዓመቱ የ300 ሚሊየን ፓውንድ እርዳታ እንደምትሰጥ ሂዩማን ራይትስ ዋች የጠቀሰ ሲሆን ሌፍኮው በሰጡት ቃል “የሃገሪቱ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ግን በተከታታይ እያሽቆለቆለ ነው” ብለዋል፡፡
"የእንግሊዝ የውጭ ተራድዖ መሥሪያ ቤት የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ግድ የሚሰጠው ከሆነ በመንደር ምሥረታ መርኃግብርና በሌሎችም አሠራሮች የሚፈፀሙ ብርቱ የመብቶች ጥሰቶችን ለማስቆም የሚያስችል ጫና ሊፈጥር በሚችል ሁኔታ የክትትልና ግምገማ ሥርዓቱን መልሶ መፈተሽና ሙሉ በሙሉ ማስተካከል ይኖርበታል" ሲሉ ሌስሊ ሌፍኮው አሳስበዋል፡
፡

tirsdag 15. juli 2014

አብርሃ ደስታ ተደብድቦ ፍርድ ቤት ቀረበ

በትግራይ እየተካሄዱ ያሉ ወቅታዊ ጉዳዮችን በመዘገብ ይታወቃል። ለእውነት ሲቆም እንጂ፤ ለህይወቱ ሲሰጋ አይተነው አናውቅም። አብርሃ ደስታ ስራው መምህርነት ሲሆን፤ የአረና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊም ነው። የትግራይ ተወላጅ ሆኖ ስለትግራይ መጥፎ በመዘገቡ የተናደዱበት ይመስላል። ባለፈው ሳምንት ትግራይ ውስጥ ታፍኖ ወደ አዲስ አበባ ማእከላዊ ፖሊስ እስር ቤት መምጣቱን ዘግበን ነበር። እዚህ ማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ ብቻውን መታሰሩ እና በከፍተኛ ሁኔታ መደብደቡ አዲስ የደረሰን ዘገባ ነው።
አብርሃ ደስታ ጠያቂም ሆነ ጠበቃ የለውም። ከድብደባው የተነሳ በጣም መዳከሙ ነው የደረሰን ዘገባ የሚያመለክተው። በፍቃዱ ጌታቸው ከአዲስ አበባ እንደዘገበው ከሆነ፤ አብርሃ ደስታ እንዳይታይ በማሰብ ለሊት ነበር እስር ቤት ያስገቡት። ይህ ብቻ አይደለም። በሚገርም ወይም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ከለሊቱ 6፡30 ለሱ በተሰየመ ፍርድ ቤት ቀርቦ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። ለማወቅ ያልቻልነው ነገር፤ የፍርድ ቤቱ ሂደት፣ የክሱ ጭብጥ እና ይዘት ምን እንደሚመስል ነው። ነገሩን እንደ አንድ ተቃዋሚ ብቻ ሳይሆን እንደሰው ስናስበው ትክክል አይመስልም። አንድን ሰው አፍኖ አምጥቶ፤ ደብድቦ እና አሰቃይቶ ፍርድ ቤት ማቅረብ የደረስንበትን የፍትህ ዝቅጠት የሚያሳይ ነው።
አብርሃ ደስታ በተደጋጋሚ ሲናገር “የትግራይ ህዝብ የህወሃት ደጋፊ አይደለም” ይል ነበር። ለነገሩ የህወሃት ታጋዮች የሞቱት እና የተሰዉት እንደአብርሃ ደስታ ያሉ ሰዎች በግፍ ታፍነው እየተደበደቡ ለፍርድ እንዲቀርቡ ከነበር ያሳዝናል። ህወሃትን እንደግፋለን የሚሉ የትግራይ ተወላጆች ጭምር “የመስዋዕትነት ውጤቱ ይህ ነው?” ብለው እራሳቸውን መጠየቅ አለባቸው።
የአረና ፓርቲም አንድ አባሉ ታፍኖ እና ታስሮ ሲወሰድ በዝምታ መመልከት የለበትም። የመግለጫ ጋጋታ የታሰሩትን ባያስፈታም፤ አቋምን ማሳወቂያ መንገድ ነውና መግለጫ ማውጣት አስፈላጊ ነው። የይስሙላ ቢሆንም ለሰባዊ መብት ጠባቂ ድርጅትም ቢሆን ማሳወቅ ያስፈልጋል። ከምንም በላይ ግን አንድነት ፓርቲ እንዳደረገው በህገወጥ መንገድ ዜጎችን የሚያስሩትን ሰዎች ለፍርድ ማቅረብ ያስፈልጋል። ቢሰራም ባይሰራም የህጉን መንገድ ደጋግመን ልንሄድበት ይገባል። ለዛሬው እዚህ ላይ አበቃን።

በሽብርተኝነት ስም የሚወሰደው እርምጃ ግልጽነት ይኑረው!

በአገር ውስጥ በህጋዊ መንገድ ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም መንግስት በሽብር ጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ማዋሉ በሚዲያዎች ተገልጿል፡፡ እነዚህ አመራሮች ከ48 ሰዓታት በላይ ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውና የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በጉዳዩ ላይ ዝርዝር መረጃ አለማቅረባቸው አመራሮቹ የታሰሩት በሚያራምዱት የፖለቲካ አቋም እንዳይሆን ፓርቲያችን ስጋት አድሮበታል፡፡
የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በጉዳዩ ላይ ጥልቅ ውይይት ካደረገ በኋላ የሚከተለውን አቋም ወስዷል፡፡
መንግስት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች የተያዙበትን ምክንያት ለህብረተሰቡ ዝርዝር እና ግልጽ መረጃ እንዲሰጥ፤
የታሰሩት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 21 መሰረት ለዜጎች የተሰጠው መብት እንዲከበርላቸው፤
በአስቸኳይ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ፤ የፍርድ ሂደታቸውም ተአማኒ፤ ግልጽ እና ፈጣን በሆነ መንገድ እንዲታይ እያሳሰብን
ይህ ሳይሆን ቢቀር ግን የአገሪቱን ህግ አክብረን በሰላማዊ ትግል ከምንንቀሳቀስ ፓርቲዎች ይልቅ ከዚህ በተቃራኒ የሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ ሀይሎችን የሚያጠናክር፤ ክርክራቸውንም ምክንያታዊ የሚያደርግ እና የዴሞክራሲያዊ ግንባታውን ወደኋላ የሚመልስ በመሆኑ ጉዳዩ እጅግ እንደሚያሳስበን እንገልጻለን፡፡
ስለዚህም መንግስት የጉዳዩን አሳሳቢነት ተገንዝቦ አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጥ ኢዴፓ ያሳስባል፡፡
የኢዴፓ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ
ሐምሌ 7 ቀን 2006 ዓ.ም