onsdag 16. juli 2014

በኢትዮጵያ የእንግሊዝ እርዳታ ፖሊሲ ተግባራዊነት እንዲፈተሽ ታዘዘ

ኢትዮጵያ ውስጥ በአሸባሪነት ተጠርጥረዋል ተብለው የተያዙት 6 የኢንተርኔት ጸሐፍትና 3 ጋዜጠኞች ላይ ፖሊስ ሲያካሂድ የቆየው ምርመራ ተጠናቋል ቢባልም ምንም ዓይነት ውሳኔ እንዳልተሰጣቸው ጠበቃቸው አስታወቁ። ክሳቸው ዛሬ ወደ ሕጋዊ ሥርዓት ካልገባም ነገ ክስ ለመመሥረት ማሰባቸውን ጠበቃቸው አቶ አምሃ መኮንን ዛሬ  ተናግረዋል።
LOGO CPJ
ፖሊስ ምርመራውን ማጠናቀቁን ባለፈው ቅዳሜ ለፍርድ ቤት ያሳወቀው፣ ተጠርጣሪ የተባሉትም ሆነ ጠበቃቸው ባልተገኙበት ነው። ተጠርጣሪዎቹ እንዲሁም ጠበቃቸው ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ መዝገባቸው መዘጋቱን የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ድርጅት CPJ አውግዟል። በአሸባሪነት ተጠርጥረዋል ተብለው የተያዙት ጋዜጠኞችና የኢንተርኔት ጸሐፍት ከታሰሩ 80 ቀን ሆኗቸዋል። በዚህ ጊዜ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ሲጠይቅ የቆየው ፖሊስ ቅዳሜ ሐምሌ 5 2006 ዓም እንዲሁም ሰኞ ሐምሌ 7 2006 ዓም በተጠርጣሪዎቹ ላይ የሚያካሂደውን ምርመራ መጨረሱን ለፍርድ ቤት አስታውቆ የቀጠሮ ምርመራ መዝገቡ ተዘግቷል። ይህ የተደረገበትን መንገድ ግን የተጠርጣሪዎቹ ጠበቃ ተቃውመዋል። የተጠርጣሪዎቹ ጠበቃ አቶ አምሃ መኮንን አሰራሩ ትክክል እንዳልሆነ ነዉ የሚያስረዱት።
Zeitungen Äthiopien
ፖሊስ ምርመራውን መጨረሱን ሲያሳውቅ ተጠርጣሪዎቹም ሆኑ ጠበቃቸው እንዲገኙ አለመደረጉ በጋዜጠኞች መብት ተከራካሪዎች ተወግዟል። ድርጊቱን ካወገዙት ውስጥ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪዎቹ በምህፃሩ CPJ እንዲሁም REPORTERS WITH OUT BORDERSS ይገኙበታል። CPJ ባወጣው መግለጫ መንግሥት የፍርድ ሂደቱን ሕጋዊ ለማስመሰል ቢሞክርም የሚፈፀመው ግን በቀል እና ሂስ አቅራቢዎችን የማፈን(ጭጭ የማሰኘትተግባር ነው ብሏል። የድርጅቱ የምሥራቅ አፍሪቃ ወኪል ቶም ሮድስ ባለፈው ቅዳሜና ሰኞ የተፈጸመውን ሕገ ወጥ ተግባር ይሉታል።
«በነፃ የፍርድ ሂደት ከዚህ በፊት ተከሳሾችም ሆኑ ጠበቆች እንዳይቀርቡ ሲደረግ አላየንም። ይህ የኢትዮጵያንም፤ ዓለም ዓቀፍ ሕግንም የሚፃረር ነው። እናም ሁኔታው በጣም ያሳስበናል። በፍርዱ ሂደት ባህርይም እንድንገረም አድርጎናል። የፍርዱ ሂደት ይበልጥ ከፖለቲካ ጋር እንዲያያዝ ተደርጓል።»
በርሳቸው አስተያየት መንግሥት ሂስ እንዲቀርብበት አይፈልግም።
Symbolbild Mann Laptop Blog Blogger
«በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው መርህ ትችትን ለመቀበል ምን ዓይነት ቦታ የማይሰጥ ነው። ምናልባትም ይህ እርምጃ በመጪው ዓመት በግንቦት ከሚካሄደው ምርጫ ጋር የተያያዘ ይሆናል የሚል ጥርጣሬ አለኝ ።»
6ቱ የኢንተርኔት ጸሐፊዎችና የ3ቱ ጋዜጠኞች ጠበቃ አቶ አምሃ እሁድና ሰኞ በተፈፀመው ላይ ያላቸውን ቅሬታ በሰኞው ችሎት ለፍርድ ቤቱ አቅርበው ነበር።
አቶ አምሃ እንደሚሉት ፖሊስ ምርመራውን ካጠናቀቀ ደንበኞቻቸው ክስ ሊመሰረትባቸው አለያም በነፃ ሊለቀቁ ይገባ 

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar