የተለያዩ ሰበቦች እየቀረቡበት የሚራዘመው የድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የፍርድ ሂደት ዛሬም በችሎት አዳራሽ ለውጥ
ምክንያት እንዲራዘም ተደርጓል።
በአቶ አቡበክር ምዝገብ የተከሰሱት ኮሚቴዎች፣ የመከላከያ ምስክር ለፍርድ ቤቱ ማስደመጥ እንደጀመሩ ነበር የችሎት ሂደቱ በሰባሰብ እንዲራዘም የተደረገው።
ዳኞችና አቃቢ ህጎች በቃሊቲ የሚገኘው የችሎት አዳራሽ ለትራንስፖርት የማያመች በመሆኑ እንዲቀየርላቸው ባመለከተቱት መሰረት አዲሱ ችሎት ሲ ኤም ሲ ሰሚት ተብሎ በሚጠራው
የአቃቂ ቃሊቲ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ቲያትር ቤት አዳራሽ እንዲካሄድ ተወስኗል። ዛሬ የተሰየመው ፍርድ ቤትም ችሎቱ እስኪስተካከል በሚል ቀጠሮውን አራዝሟል። አዳራሹ መቼ ዝግጁ
እንደሚሆን ግን የታወቀ ነገር የለም። ችሎቶች የሚጓተቱት እስረኞችን ለመቅጣት ታስቦ መሆኑን አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በግፍ ለታሰሩት የኮሚቴውን አባላት ድጋፍ ለመግለጽና መንግስት ያቀረቡትን ጥያቄ እንዲመልስ ለማስገደድ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ጠንካራ ተቃውሞ ለማዘጋጀት እየተንቀሳቀሱ ነው።
ተቃውሞው የፊታችን አርብ በመላው አገሪቱ እንደሚካሄድ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar