torsdag 12. juni 2014

ኢህአዴግ ምርጫውን አስታኮ ቤቶችን ለያከፋፍል ነው

የኢህአዴግ መራሹ መንግሥት በቀጣይ ዓመት የሚጠናቀቀው የእድገትን የትራንስፎርሜሽን እቅድ በአብዛኛው ዘርፎች ባያሳካም የመጪውን ዓመት ምርጫ ተከትሎ በጊዜያዊነት የሕዝቡን ድጋፍ የሚያስገኙለትን ሥራዎች ለማከናውን አቅዶ መንቀሳቀስ መጀመሩን የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል
በዚሁዕቅድመሠረትየመኖሪያቤትለማግኘትወደ 800ሺሕዝብየተመዘገበበትበአዲስ አበባከተማበያዝነውወርእናበነሐሴወር 40 ሺኮንዶምኒየምቤቶችንእጣለማውጣትናበዚህምድጋፍለማግኘትታቅዶአል፡፡
በተመሳሳይሁኔታእስከ ታህሳስወር 2007 ባሉትጊዜያትእንዲሁወደ 40ሺየሚሆኑተጨማሪቤቶችንለተጠቃሚዎችለማስተላለፍታቅዶእየተሰራመሆኑንምንጮቻችንጠቁመዋል፡፡
ከዚህቀደምየቤቶቹግንባታ 50 በመቶ እንኩዋን ሳይጠናቀቅ በአየር ላይ ዕጣ እንዲወጣ በማድረግ ዕድለኞች ቤታቸውን እስኪረከቡ እስከ ሁለት ዓመታት ጊዜ ይፈጅ የነበረው ጊዜ አሁን ከምርጫው ጋር በተገናኘ ዕጣው በወጣ ሰሞን ዕድለኞች ቤቱን እንዲረከቡ በከተማዋ አስተዳደር በኩል ጥንቃቄ እንዲደረግ በተሰጠው ማሳሰቢያ መሰረት ለመጀመሪያ ጊዜ እድለኞች እጣው በወጣበት ሰሞን ቤታቸውን ይረከባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በአዲስ አበባ ያለው መኖሪያ ቤት ችግር የኢህአዴግ አባላትም ጭምር በየጊዜው ቅሬታ የሚያቀርቡበትና የሚጋሩት በመሆኑ ገዥው ፓርቲ በጊዜያዊነት በሚወስዳቸው እርምጃዎች ጥገናዊ ለውጥ አገኝበታለሁ ብሎ ማመኑ ተጠቁሞአል፡፡
በተለይ በአስተኛና ጥቃቅን የተደራጁ ዜጎች ችግሮቻቸውን ማለትም የብድር፣የመስሪያ ቦታና የመሳሰሉት በአፋጣኝ ተፈትቶላቸው ይህን ኃይል የምርጫ ሠራዊት ለማድረግ መታሰቡም ታውቋል፡፡
ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ እጅግ የተለጠጠ የአምስት ዓመት ዕቅዱ በቀጣይ ዓመት መጨረሻ የሚጠናቀቅ ሲሆን በዚህ ዕቅድ መሠረት ይደረስበታል ተብሎ የታሰቡ ስራዎች በአብዛኛው ሳይሳኩ ቀርተዋል፡፡
በተለይባለፉትሁለትዓመታትበቡናላይየተመሰረተውኤክስፖርትመቀዛቀዙ መንግስትን ከፍተኛገቢአሳጥቶታል፡፡
የሰለጠነየሰውሃይልእጥረት፣የፋይናንስአቅምውስንነትእንዲሁምዕቅዱሁሉንምወገንአሳታፊባለመሆኑምክንያትከግብርናወደኢንዱስትሪይደረጋልየተባለውሽግግርበአየር ላይ መቅረቱን ምንጮች ይገልጻሉ፡፡
የግልባለሃብቱንበማሳተፍረገድየታየውዳተኝነትናበኢኮኖሚውስጥየመንግስትናበገዥውፓርቲስርያሉየንግድተቋማትጣልቃገብነትመጠናከርዕቅዱእንዳይሳካትልቅአስተዋጽኦማድረጋቸው ታውቋል፡፡
ኢህአዴግ በምርጫ የማሸነፊያ ስትራቴጂው መሰረት ለከተማ ነዋሪዎች መሬት በአነስተኛ ገንዘብ ያከፋፍላል። ለአርሶአደሮች ደግሞ የማዳበሪያ እና የምርጥ ዘር እዳ እፎይታ ይሰጣል።
ኢህአዴግ ይፋዊ ያልሆነ የምርጫ ቅስቀሳውን አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ፣ በተለያዩ ወረዳዎች በመንቀሳቀስ  በአምስት አመቱ ተገኙ ያላቸውን ድሎች በራሱ ካድሬዎች አማካኝነት ህዝቡ እንዲያውቃቸው እየጣረ ነው። በአንዳንድ አካባቢዎች ህዝቡ ኢህአዴግ ካሰበው በተቀራኒ እየተናገረ ሲሆን በቅርቡ በሳምንቱ መግቢያ በደብረብርሃን ከተማ ተካሂዶ በነበረው ውይይት ላይ ህዝቡ በልማቱ ተጠቃሚ አለመሆኑን መናገሩ ታውቋል።
በደብረብርሃን የነበረውን ስብሰባ ዜና እና የህዝቡን አስተያየት በነገው ዜና የምናቀርብ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።

onsdag 11. juni 2014

የባህር ዳር ባጃጅ አሽከርካሪዎች አድማ መተው አረፈዱ

ሰኔ 4 ቀን 2006 ዓም ከንጋት ጀምረው አድማ መተው ያረፈዱት የባህር ዳር ከተማ ባጃጅ አሺከርካሪዎች ፤ መንግስት ለጥያቂያችን ምላሺ እስካልሰጠ ድርስ የስራ ማቆም አድማው ይቀጥላል ብለዋል፡፡
ከሶስት ሺህ በላይ ባጃጆች የሚርመሰመሱባት ባህርዳር ከጎዳናዋ የተሰወሩባት ከንጋቱ  ጀምሮ ከከተማዋ ተሰውረው ህብረተሰቡ እና መንግስት ሰራተኛው በትራንስፖርት ችግር ውስጥ ወድቆ አርፍዷል፡፡
የባጃጅ አሺከርካሪ ማህበራትሃላፊነቱን በወሰዱበት በዚህ አድማ ፣ “የመንግስት  ባለስልጣናትን ወደ ከተማዋ መግባት ተከትሎ  ነዳጅ እንከለከላለን፣  ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ አታደምቁም ተብለን እንዳንሰራ ታግደናል፣  የምሺት ባጃጆች በቀን እንዳይሰሩ እገዳ ተጥሏል ይነሳልን” የሚሉ ጥያቄዎችን አንስተዋል።
“መንግስት ነዳጅን ለማደል  የድጋፍ ሰልፍ መውጣትን እንደመመሪያ ማድረጉ፣ ባለስልጣን በመጣ ቁጥር  ፍተሻው ማስመረሩ፣  ባለስልጣን በመጣ ቁጥር ከምንሰራበት ቁመን የምንውልበት ቀን መብለጡ፣ ቀን የሚሰሩ ባጃጆች በምሺት እንዳይሰሩ መከልከሉ መንግሰትን ለመቃወም ምክንያት ሆኖናል” ሲሉ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ አስተያየት ሰጪዎች ለዘጋቢያችን ገልጸውላታል።
የክልሉ ንግድ እና መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ  “ባሰቸኳይ  ስራ ያልጀመረ መንጃ ፍቃድ ይነጠቃል” የሚል  ማስታወቂያ ቢያወጣም አድማው እስከ አምስት ስዓት ቀጥሎ ውሎአል። መንግስት ከባጃጅ ማህበሮች ጋር ባደረገው ውይይት ችግሩን እንደሚያቃልል ቃልበመግባቱ እና የውይይት መድረክ ለማዘጋጀት ስምምነት ላይ በመደረሱ ባለባጃጅ መኪኖቹ ወደ ስራ ተመልሰዋል።

ፖሊስ በሲኤም ሲ የቤት ለቤት ፍተሻ አካሄደ


የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ፖሊስ በእያንዳንዱ ነዋሪ ቤት እየገባ መታወቂያ የጠየቀ ሲሆን የውጭ አገር ዜጎች ደግሞ ፓስፖርት፣ ወደ አዲስ አበባ የገቡበት ቀን ፣ የቀጣሪ ድርጅታቸውን ስምና አድራሻ፣ መታወቂያና ሌሎችንም ጥያቄዎች ተጠይቀዋል።
ተመሳሳይ ፍተሻዎች በሌሎች አካባቢዎች ሊኖር እንደሚችል መረጃዎች ያመለክታሉ።
በቅርቡ የምእራብ መንግስታት አልሸባብ በኢትዮጵያ የሽብር ጥቃት ሊፈጽም እንደሚችል አስጠንቅቀው ነበር። መንግስትም 2 የአልሸባብ አሸባሪዎችን መያዙን አስታውቋል።
አልሸባብ በሶማሊ ክልል  33 የመንግስትን ወታደሮች መግደሉ ይታወሳል። ይህንን አሰቃቂ ጥቃት ተከትሎ በመንግስትና በአልሸባብ ተዋጊዎች መካከል በተደረገው ጦርነት ከሁለቱም ወገን ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

mandag 9. juni 2014

ውህደቱን ለማወክ ከተዘጋጁት መሃል አንደኛው ታገተ (ፎቶ እና የመታወቂያ መረጃ ይዘናል)

ውህደቱን ለማደናቀፍ የተላኩት የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ተልእኳቸው ተደናቅፏል-
ምንሊክ ሳልሳዊ
መኢአድ እና አንድነት የውህደት ፊርማ ተፈራርመዋል። የአንድነት የሂሳብ ክፍል ሰራተኛን ሲፈነክቱ አንድ የመኢአድ አመራር ጥርሱን በድንጋይ አውልቀውታል።
በዛሬው እለት ከጠዋቱ አራት ሰአት ጀምሮ አዲስ አበባ በሚገኘው የመኢአድ ጽ/ቤት ውስጥ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን ፖለቲከኞች ዲፕሎማቶች ጋዜጠኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ እና የአንድነት ለፍትህ እና ለዲሞክራሲ (አንድነት) የውህደት ፊርማቸውን በደመቀ ስነስር ስት መፈራረማቸውን በስፍራው የተገኙ ምንጮቻችን ገልጸዋል።
ውህደቱን ለማደናቀፍ የተወጠነው ሴራ በሁለት መልኩ ቢሆንም አንደኛው የቀድሞ መኢአድ አባላትን በማደራጀት አስርጎ ለማስገባት የተድረገው ሙከራ የመግቢያ ካርድ ባለመያዛቸው እንዲሁም ከድርጅት የተባረሩ መሆናችው ተነግሯቸው በሰላም የተሸኙ ሲሆን ሁለተኛ ብድን የመጀመርያዎቹን አለመሳካት ትክትሎ የተላከ የካድሬዎች ቡድን በር በመገንጠል ለመግባት ሲሞክር አንደኛው ሲያዝ ሌላው የቡድኑ አባላት ከቦታው ሮጠው ማምለጣቸውታውቋል።
በአከባቢው የተመደቡ ፖሊሶች እንዲይዙት ቢጠየቁም ሄዳችሁ የክስ ፋይል ክፈቱና እንይዝላቹሃልን የሚል መልስ ቢሰጡም ማንነቱ እና አድራሽው የማይታወቅ ሰው እንዴት ይከሰሳል ወንጀል ሲሰራ እጅ ከፍንጅ መያዝ ሲገባቸው በንዝህላልነት እና በአደርባይነት መንፈሳቸው ከፍትህ ጋር አብረው ተቀብረዋል።
በወቅቱ ብጥብጥ ለመፍጠር ሞክረው አልሳካ ያላችው ካድሬዎች ቢያመልጡም ከተያዘው አንደናው ኪስ ውስጥ የኢሕ አዲግ አባልነት ክፍያ ደረሰኝ እንዲሁም መታወቂያ የተገኘበት ሲሆን ለረብሻው የተላኩት ሶስቱን የትግርይ ብሄር ተወላጆች ሲሆኑ ፎቶግራፋቸው የተያዘ ሲሆን ድንጋይ በመወርውር አከባቢውን በጥብጠውታል። በፎቶግራፋቸው የምታዩት የአቶ ግርማ ሰይፉ ማሩ መኪና ተደግፎ የቆምውና አመራሮቹን በድንጋይ የፈነከተው እንዲሁም መኢአድ ግቢ ውስጥ የተያዘው ካድሬ ምስሎቻቸውን ይመልከቱ።
የአቶ ግርማ ሰይፉ ማሩ መኪና ተደግፎ የቆምው የወያኔ ባለጌ ወጣት
የአቶ ግርማ ሰይፉ ማሩ መኪና ተደግፎ የቆምው የወያኔ ባለጌ ወጣት

መኢአድ ግቢ ውስጥ የተያዘው ካድሬ
መኢአድ ግቢ ውስጥ የታገተው ካድሬ
በተመሳሳይ መልኩ በስፍራው የነበረው ጋዜጠኛ ዳዊት ሰለሞን ደግሞ ከዚህ የሚከተለውን ዘገባ ልኳል።
ውህደቱ ለማደናቀፍ ቢሞከርም ወያኔ ሳይሳካለን በሰላም መፈረሙ ታውቋል።
ዛሬ በመኢአድ ጽ/ቤት አንድነትና መኢአድ የቅድመ ውህደት ስምምነታቸውን በወረቀት ላይ ከማስፈራቸው ቀደም ብሎ ወደ ግቢው እንግባ የሚሉ የተወሰኑ ሰዎች ግርግር ለመፍጠር ሞክረው ሳይሳካላቸው ሲቀር የግቢውን በር በድንጋይ መደብደብ በመጀመራቸው የተወሰኑት በፖሊስ ተይዘዋል፡፡
ድንጋይ በመወርወር ውህደቱን ለማደናቀፍ ከሞከሩ ሰዎች መካከል የአንዱን ማንነት ለማጣራት በተደረገ ሙከራ ከኪሱ ውስጥ ለኢህአዴግ የወር መዋጮ የከፈለበት ደረሰኝ ተገኝቶበታል፡፡የመኢአድ አባል ነኝ ሲል የነበረው ወጣት ደረሰኙ ከተገኘበት በኋላ በሀፍረት ተሸማቅቆ አንገቱን አቀርቅሯል፡፡
ከረብሻ ፈጣሪዎቹ መካከል አንደኛው ተይዞ ኪሱ ሲፈተሽ ለኢህ አዴግ የአባልነት መዋጮ የከፈለበት ደረሰኝ ኪሱ ውስጥ ተገኘ፤ እሱም አንገቱን ደፋ።
ከረብሻ ፈጣሪዎቹ መካከል አንደኛው ተይዞ ኪሱ ሲፈተሽ ለኢህ አዴግ የአባልነት መዋጮ የከፈለበት ደረሰኝ ኪሱ ውስጥ ተገኘ፤ እሱም አንገቱን ደፋ።
የረብሸኛው መታወቂያ ወረቀት
የረብሸኛው መታወቂያ ወረቀት




fredag 6. juni 2014

በጋዜጣ አዙዋሪዎች ላይ እርምጃ መወሰድ መጀመሩ ታወቀ

የሰማያዊ ፓርቲ ልሳን የሆነው ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው  ሃሙስ ምሽትላይ  በተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍሎች ጋዜጣ አዙዋሪዎች በገዥው ፓርቲ የደህንነት ኃይሎች ታግተው አምሽተዋል፡፡የደህንነት ኃይሎች ‹‹ለማዞር የተደራጃችሁበትንና ፈቃድ የተሰጣችሁበትን ወረቀት አምጡ›› በማለት ወደ ጣቢያ ሊወስዱዋቸው እንደ ነበርና አዙዋዎቹም ‹‹መደራጀት አይጠበቅብንም ፣ጣቢያም አንሄድም›› ብለው የደህንነቶቹን ትዕዛዝ መቃወማቸውን ጋዜጣው ዘግቧል፡፡ መንግስትን የሚተቹ ጋዜጦችና መጽሄቶች እንዲያዞሩ እንደማይፈልግና እሱ የሚፈልገውን እያደራጀ መሆኑን አዙሪያዎቹ ለጋዜጣው  ገልጸዋል፡፡  ‹‹መንግስት በእኛ ብቻ ሳይሆን ጋዜጣ በምናስነብብባቸው ካፌዎች ላይም ጫና ተጀምሯል፡፡ካፌዎቹ ለአንድ ሰው ከአንድ ጋዜጣ በላይ እንዳንሰጥ ናአንዳንዶቹም ጭራሹን እንዳናስነብብና እንዳንሸጥ እየከለከሉንነው፡፡›› በማለት አዙዋሪዎቹመናገራቸውን ጋዜጣው ዘግቧል።
ኢሳት ጥር 28 ቀን 2006 ዓም “መንግስትአንዳንድብቅበማለትላይያሉነጻጋዜጦችንለመቅጨትእየሰራነውተባለ” በሚል ርእስ ባወጣው ዘገባ “የመንግስትኮምኒኬሽንጉዳዮችጽ/ቤትየጋዜጦችናየመጽሔቶችንስርጭትአስተካክላለሁበሚልያዘጋጀውንመጠይቅካለፈውሳምንትጀምሮለሚዲያዎችናለአከፋፋዮችበማስሞላትላይሲሆንዋናአላማውምአንዳንድብቅበማለትላይያሉትንነጻጋዜጦችንለመቅጨትያለመመሆኑን ጠቅሷል።
መንግስትእስከዛሬበስርጭትስራላይየተሰማሩዋናአከፋፋዮችከግብር፣ታክስናከመሳሰሉትሕጋዊሁኔታዎችጋርተያይዞክስበመመስረት  ስራውንምለአነስተኛናጥቃቅንተቋማትለመስጠትሃሳብመኖሩን ዘግቦ ነበር፡፡

በአዲስ አበባ የህዝብ መፈናቀል እንደሚቀጥል መረጃዎች አመለከቱ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ማደስና ፕላን ዝግጅት በሚባለው ፕሮግራሙ በመሃል አዲስ አበባ የሚገኙ ኪስ ቦታዎች ላይ የሚገኙ ነዋሪዎችን በስፋት እንደሚያፈናቅል የሚነገርለትን እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ የአስተዳደሩ ምንጮች ጠቆሙ፡፡
አካባቢን መልሶ የማልማት ገጽታ አለው በሚባለው ሥራ ውስጥ ዘንድሮ ከተካተቱ አካባቢዎች መካከል በካዛንቺስ 26 ሄክታር፣በደጃችውቤ 11.6 ሄክታር፤በሸበሌሆቴልዙሪያ 10.4 ሄክታር፣አሜሪካንግቢ 16 ሄክታር፣በአፍሪካህብረትቁጥር 2 ወደ 15 ሄክታር፣ተክለሃይማኖት 33 ሄክታር፣አሮጌውቄራቁጥር 1 እና 2እንደቅደምተከተሉ 14 ሄክታርእና 54 ሄክታር፣ባሻወልዴቁጥርየፓርላማማስፋፊያ 4 ሄክታርቤት የማፍረስ እቅድ መኖሩን ተከትሎበአንዳንድአካባቢዎችለነዋሪዎችካሳየመክፈል፣በአንዳንዶቹምየማፍረስሥራዎችእየተከናወኑመሆኑን ምንጮቹጠቅሰዋል፡፡
አስተዳደሩበመልሶማልማትፕሮግራሙበተለይየቀበሌቤቶችውስጥየሚኖሩነዋሪዎችምትክየኮንዶምኒየምቤትየሚሰጥቢሆንምበወቅቱናበሰዓቱየሚከናወንባለመሆኑነዋሪዎችለእንግልትናለተጨማሪወጪእየተዳረጉነው፡፡
በተለይየግልቤቶችምትክቦታበተመሳሳይሁኔታበፍጥነትየሚከናወንአለመሆኑ፣በቂየዝግጅትጊዜሳይሰጥነዋሪዎችእንዲነሱመገደዳቸውበየአካባቢውያላቸውንማህበራዊትስስርየሚያናጋናልጆቻቸውንምትምህርታቸውንለማስቀጠልየሚቸገሩበትሁኔታተፈጥሮአል፡፡በተለይበግለሰብቤቶችተከራይተውየሚኖሩበርካታነዋሪዎችበምትክቤቶችአሰጣጥውስጥየማይካተቱመሆኑማህበራዊቀውስእየፈጠረእንደሚገኝታውቋል፡፡
የከተማአስተዳደሩበተለይበሊዝጨረታቦታዎችንአወዳድሮሲሰጥየመሬትአቅርቦቱእጅግአነስተኛከመሆኑጋርተያይዞበአንድካሬሜትር 10ሺብርእናከዚያበላይየሚሰጡጥቂትሐብታሞችተጠቃሚየሚሆኑበት፣በአንጻሩአነስተኛናመካከለኛገቢዎችያላቸውነዋሪዎችየማይጠየቁበትሥርዓትመፈጠሩይታወቃል፡፡
የኢህአዴግ መንግስት እጅግ በውድ ዋጋ የሚሸጠው መሬት በሙስና እየተበላ መሆኑንም የሚደረሱት መረጃዎች ያመለከታሉ። የኢሳት ምንጮች እንደሚገልጹት ከመሬትና ከታክስ ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ ከፍተኛ የሆነ የዝሪፊያ መረብ የተዘረጋ ሲሆን፣ ምርጭ የሚባሉ ቦታዎች በእነዚህ ጥቂት ግልሰቦች እጅ እየገባ ነው።
እነዚህ ሰዎች ገቢዎችንና ጉሙሩክን ከጀርባ ሆነው በመቆ|ጣጠርና ስራቸውን በንጽህናና በሃቀኝነት የሚሰሩ ሰራተኞችን በተለያዩ ወንጀሎች በመክሰስ ከስራ እንዲባረሩ በማድረግ ከፍተኛ ሃብት እየመዘበሩ መሆኑን ምንጮች አክለው ገልጸዋል።
ታክስ ማጭበርበርና መሬት በህገወጥ መንገድ መዝረፍ በኢትዮጵያ አቋራጭ የመክበሪያ ስልት እየሆነ ነው።

torsdag 5. juni 2014

በሀረር ከተማ በርካታ ተማሪዎች ታሰሩ

የአቦከር መሰናዶ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የታሰሩት የሁለተኛ ደረጃ ፈተና ካጠናቀቁ በሁዋላ ከግቢያቸው በመውጣት መፈክሮችን እያሰሙ ወደ ማሃል ከተማ በመጓዝ ላይ እያሉ ነው። ተማሪዎቹ “በሀረር ክልል የሚታየው አድሎ ይቁም፣ ፍትሃዊ አስተዳደር ይኑር፣ መንግስት በህዝብ ላይ የሚያደርሰው በደል ይቁም” የሚሉና ሌሎችንም መፈክሮች እያሰሙ ተቃውሞአቸውን ሲገልጹ አርፍደዋል።
የክልሉና የፌደራል ፖሊስ በጋራ ተቃውሞውን የተቆጣጠሩት ሲሆን፣ ተቃውሞውን አስነስተዋል ያሉዋቸውን ከ25 በላይ ተማሪዎች እየደበደቡ ወደ እስር ቤት ወስደዋቸዋል። የፖሊስን ዱላ ለመሸሽ በሚል በሃረር መካነ-ስላሴ ካቴደራል ቤተክርስቲያን የገቡትን  ተማሪዎች አስወጥተው መውሰዳቸውን በተለይ ያሬድ የሚባል ተማሪ በድብደባው ክፉኛ እንደተጎዳ ወኪላችን ገልጿል።
የሀረሪ ክልል ባለስልጣናት የሚፈጽሙት አስተዳደራዊ በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ነዋሪዎች ይናገራሉ። የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች በሚኖሩባት ሃረር ፍትሃዊ የሆነ ውክልና እንደሌለና የመስተዳደሩ ባለስልጣናት ሁሉንም ብሄሮች እኩል እንደማያስተናግዱ የከተማዋ ነዋሪዎች በምሬት ይገልጻሉ።
ከ20 በላይ ነጋዴዎች ብጥብጥ በማስነሳትና የመንግስት ንብረት እንዲወድም በማስደረግ ወንጀል ተከሰው ዋስትና ተከልክለው በእስር ቤት እንደሚገኙ ይታወቃል።
በክልሉ የሚታየውን ችግር በተመለከተ ባለስልጣናቱን ለማነጋገር ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም።