የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ፖሊስ በእያንዳንዱ ነዋሪ ቤት እየገባ መታወቂያ የጠየቀ ሲሆን የውጭ አገር ዜጎች ደግሞ ፓስፖርት፣ ወደ አዲስ አበባ የገቡበት ቀን ፣ የቀጣሪ ድርጅታቸውን ስምና አድራሻ፣ መታወቂያና ሌሎችንም ጥያቄዎች ተጠይቀዋል።
ተመሳሳይ ፍተሻዎች በሌሎች አካባቢዎች ሊኖር እንደሚችል መረጃዎች ያመለክታሉ።
በቅርቡ የምእራብ መንግስታት አልሸባብ በኢትዮጵያ የሽብር ጥቃት ሊፈጽም እንደሚችል አስጠንቅቀው ነበር። መንግስትም 2 የአልሸባብ አሸባሪዎችን መያዙን አስታውቋል።
አልሸባብ በሶማሊ ክልል 33 የመንግስትን ወታደሮች መግደሉ ይታወሳል። ይህንን አሰቃቂ ጥቃት ተከትሎ በመንግስትና በአልሸባብ ተዋጊዎች መካከል በተደረገው ጦርነት ከሁለቱም ወገን ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar