lørdag 26. januar 2013

በብዙ መቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞአቸውን ሲገልጹ ዋሉ



    
            በአዲስ አበባ በአንዋር መስጊድ በተካሄደውና በብዙ መቶሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በአንዋር  መስጊድ   እና ከመስጊዱ ውጭ ያሉ መንገዶችን ሞልተው የተለያዩ መፈክሮችን አሰምተዋል።

“በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ የሚደረግ ጭቆና ይብቃ፣ በቃል ኪዳናችን እንጽና፣ ውሸት ሰለቸን፣ ኮሚቴዎች ይፈቱ፣ የሀሰት ምስክሮች አይቅረቡ ” የሚሉ መፈክሮች በብዛት መታየታቸውን የዘገበው ሪፖርተራችን፣ አንዳንድ አማንያንም “መንግስት የለም” በማለት ሲናገሩ ተሰምተዋል።

አብዛኛው ሴቶች ጥቁር ወንዶቹ ደግሞ ነጭ በመልበስ ተቃውሞአቸውን መግለጻቸው ታውቋል።
ተመሳሳይ ተቃውሞች በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች መካሄዳቸው ታውቋል።

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቃውሞአቸውን ከጀመሩ አንድ አመት ያለፋቸው ቢሆንም፣ መንግስት እስካሁን ለጥያቄአቸው መልስ አልሰጠም። በኢህአዴግ ምናልባትም በኢትዮጵያ ታሪክ ለረጅም ጊዜ በመንግስት ላይ የተካሄደው ተቃውሞ ቢኖር የሙስሊሞች ተቃውሞ ነው።

መንግስት ተቃውሞው በጊዜ ብዛት ይዳከማል የሚል እምነት መያዙ ይታወቃል። ይሁን እንጅ ተቃውሞው እየጠነከረ ከመሄድ ውጭ ሲበርድ አልታየም።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar