søndag 24. mars 2013

Active Ethnic Cleansing in Ethiopia





Killing Amharas, a Thousand at a time
TPLF is actively destroying the Oromo, Amhara, Ogaden, Anuak and many other peoples in Ethiopia.
They use different methods, this one being the latest

ለርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አባላትና ወዳጆች፤ እንዲሁም በUK እና በመላው ዓለም ለሚገኙ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ሁሉ



Reese Adbarat Saint Mary of Debre Tsion Ethiopian Orthodox Churchየተቀበሉትን የክህነት ኃላፊነት ጠብቀው በንጽሕና በመቆም እግዚአብሔርንና ሰውን ከማገልገል ይልቅ ሥጋዊ ጥቅምን አስቀድመው የተነሱ ጥቂት የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ካህናት በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ በሰንበት ት/ቤት ወጣቶችና በምእመኑ መካከል ጸብና ጥላቻ ቀስቅሰው ሁከት እንዲሰፍን በማድረግ ባለፈው ሳምንት ለንደን ወደ ሚገኘው የኢህአዲግ መንግሥት ኤምባሲ በመሄድ ቤተ ክርስቲያንን ያህል ነገር እንደ ግል ንብረት ለማስረከብ እንፈልጋለን በማለት ከጠየቁ በኋላ ከዛ በማስከተል ቤተ ክርስቲያኗን የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት በመባል በኢህአዲግ መንግሥት ጣልቃ ገብነት ለንደን ላይ ለተቋቋመው አካል አሳልፎ በመስጠት የቤተ ክርስቲያኑን አስተዳደርና ንብረት ለማስረከብ በድርድር ላይ እንደሚገኙ ለማረጋገጥ ተችሏል።

ይህ የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት (ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHEDO CHURCH DIOCESE OF NORTH WEST EUROPE) በሚል መጠሪያ የተቋቋመው ከ11 November 2011ጀምሮ ሲሆን በቻሪቲ ቁጥር 1144634 መሠረት በቻሪቲ ኮሚሽን ተመዝግቦ የሚገኝ ነው።

የዚህ ለሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ተብሎ የተቋቋመ ሀገር ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መጋቢ አዕላፍ ተወልደ ገብሩ ሲሆኑ፤ የሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ደግሞ አቡነ እንጦስ የተባሉ አባ ጳውሎስ በህይወት ሳሉ በጎሳና በመንደር ልጅነት መርጠው ጵጵስና በመሾም ወደ ለንደን የላኳቸው ናቸው። በዚሁ ሃገረ ስብከት ውስጥ በትረስቲነት (Trustees) ሆነው የተዋቀሩት ደግሞ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2005 ዓ/ም ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያንን ጥለው በመሄድ ሌላ ቤተ ክርስቲያናትን የመሠረቱ ሰዎች ናቸው።

ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ለንደን ላይ ከተመሠረተች 40 ዓመታትን ያስቆጠረች ሲሆን በዚህ ረጅም የስደት ታሪኳ ወቅት ካለፈው ከደርግ መንግሥትም ሆነ አሁን ካለው የኢህአዲግ መንግሥት ጋር ሳትወግን በልጆቿ ጥረትና ተጋድሎ ከማንኛቸውም የመንግሥትና የፓለቲካ ተጽዕኖ ራሷን ነጻ በማድረግ ሁሉም በእኩልነት የሚያመልክባት ቤተ ክርስቲያን ሆና ኖራለች።

በዚህ የፓለቲካ ወገንተኝነት በሌለው አቋሟም ቤተ ክርስቲያኗ በኢትዮጵያም ሆነ በዓለም ዙሪያ ለሚከሰቱ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮች ሁሉ ነጻና ፍትሐዊ የሆነ መሥመርን በመከተል ከክርስትና ሃይማኖትና ከቤተ ክርስቲያን የሚጠበቅን የእውነት ተግባራት ስታከናውን ቆይታለች።
ዛሬ በሕይወት ያሉና በህይወት የ
ማይገኙ አባላቶቿ ካህናትና ምእመናን ላለፉት 40 ዓመታት ባደረጉት ከፍተኛ ጥረትና ድካምም በአሁኑ ወቅት ቤተ ክርስቲያኗ በእግዚአብሔር ተራዳኢነት ለከፍተኛ የእድገት ደረጃ የበቃች ከመሆኗም በላይ ወደፊትም ከማንኛቸውም የመንግሥትና የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ነጻ በመሆን የበለጠ በማደግና በመስፋት ለስደተኛው ሕዝብና በስደት ላይ ለሚፈጠረው ትውልድ የምትተላለፍ የኦርቶዶክስ ሃይማኖትና የኢትዮጵያዊነት መገለጫ፤ ሃብትና ቅርስ ሆና የምትኖር ነች።

ይህንን የመሰለውን የቤተ ክርስቲያኗን ያለፈ ታሪክና የወደፊት ራዕይ በማፍረስ በአሁኑ ወቅት አስተዳደሯንም ሆነ ሃብትና ንብረቷን ዛሬን ኖሮ ነገ በሚያልፍ የኢህአዲግ መንግሥት የእጅ አዙር ቁጥጥርና ተጽዕኖ ሥር ለማዋል የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪና ተከታዮቻቸው በመፈጸም ላይ ያሉት የክህደት ሥራ ቤተ ክርስቲያኗን ለዚህ ያበቋት አባላቷም ሆኑ ደጋፊዎቿና መላው በስደት ዓላም የሚገኝ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የሚታገሱትና የሚቀበሉት አይሆንም።

በዚህ መሠረት ይህችን በሕዝብ ጥረትና ድካም ደርጅታ በእግዚአብሔር ተራዳኢነት ለከፍተኛ የእድገት ደረጃ የበቃች ቤተ ክርስቲያንን ያለ ሕዝብ ፍቃድ፤ እውቅናና ይሁንታ በስውር በመደራደር ለሌላ አካል አሳልፎ በመሸጥ መሾሚያና መሸለሚያ ለማድረግ መሞከር አጠቃላይ ስደተኛውን ኢትዮጵያዊ ከማዋረድ አልፎ በቁመናው እንደ መግደል ስለሚቆጠር የቤተ ክርስቲያኗ አባላት፤ የማርያም ወዳጆችና በአጠቃላይ በስደት ዓለም የሚገኘው ኢትዮጵያዊ ሁሉ የተሰነዘረበትን ጥቃት በመረዳት የተንኮሉን ገመድ በመበጣጠስ ሴራውን አክሽፎ ከእግዚአብሔር በታች የቤተ ክርስቲያኗ ባለቤት፤ አዛዥና ወሳኝ ሕዝብ ብቻ መሆኑን በተግባር የማረጋገጥ ሃይማኖታዊና ኢትዮጵያዊ ግዴታ አለበት።

በዚህ መሠረት የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አባላት፤ ወዳጆችና በUKና በመላው ዓለም የምትገኙ ስደተኛ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ሕግን ተከትሎ በመሄድ ቤተ ክርስቲያኗን ለማዳን የሚደረገው ጥረት ገንዘብ፤ ጊዜና አቅምን የሚጠይቅ መሆኑን በመረዳት አስተባባሪ ኮሚቴው በሚያወጣው መርሃ ግብርና ጥሪ መሠረት አቅማችሁ የፈቀደውን ሁሉ እንድታደርጉ በቅድስት ማርያም ስም ጥሪአችንን እናስተላልፋለን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

ከጠቅላይ ፍ/ቤት እስከ ሚንስትሮች ም/ቤት


መጋቢት 18/2005 ዓ.ም የእነ እስክንድር ነጋ ይግባኝ ለመጨረሻ ጊዜ ተብሎ ተቀጥሯል፡፡ በዚህ መዝገብ የተከሰሱት የህሊና እስረኞች ይግባኝ ከጠየቁ አምስት ወር አልፏቸዋል፡፡

ለምን? …በአዲስ መስመር እንነጋገርበት፡፡



 
የይግባኙን ውሳኔ ያዘገየው የፖለቲካ ተንታኝ እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ጉዳይ ነው፡፡

ከጠቅላይ ፍ/ቤት እስከ ሚንስትሮች ም/ቤት ምክንያቱ ደግሞ የተከሰሰው በሀሰት ስለሆነ ነው፡፡ በእርግጥ ይህንን ያልኩት እኔ አይደለሁም፤ የጠቅላይ ፍርድ ቤት የመሀል ዳኛ የሆነው አቶ አማረ አሞኘ ነው፡፡ ባለፈው ወር ዳኛው አቃቢ ህጎቹን ሰበሰበና እንዲህ አላቸው

፡-‹‹ይህን ሰው አሻባሪ ነው ብላችሁ ስትከሱት ያቀረባችሁት ማሰረጃ በተለያየ ጊዜ የፃፈውን ፅሆፎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና በአንድ የፖለቲካ ፓርቲ መድርክ ላይ ተናገረው ያላችሁትን ብቻ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ፅሁፉና ንግግሩ ያስከተለው አደጋ አልተገለፀም፤ ወይም ምንም አይነት አደጋ አላስከተለም ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ተከሳሹ ላይ ቅጣት ለመጣል አያስችልም፡፡

ስለዚህም ሌላ ጥፋተኝነቱን የሚያረጋግጥ ማሰራጃ ካላችሁ አቅርቡ? አሊያም በሚቀጥለው ቀጠሮ ሲቀርብ በነፃ እለቀዋለሁ፡፡

.አቃቢ ህጎቹ ምንም ማስረጃ አልነበራቸውምና በደፈናው ‹‹ሰውየው አሸባሪ ስለሆነ ዝም ብለህ፤ ይግባኙን ውድቅ አድርግና የከፍተኛው ፍርድ ቤቱን ውሳኔ አፅናበት›› የሚል ይዘት ያለው ተመሳሳይ አቋም አንፀባረቁ፡፡

 ዳኛው ምን አይነት መንፈሳዊ ኃይል ተጭኖበት እንደ ሆነ እንጃ! ‹‹በፍፁም ከህግ ውጪ አልሰራም፤ ህሊና አለኝ›› ብሎ ፍንክች ያባ ቢለዋ ልጅ ይላል፡፡

 ይህን ጊዜም ነገሩ ቦግ ያደረገው አንድ አቃቢ ህግ
‹‹አንተ እስክንድርን እለቃለሁ የምትለው ያገርህ ልጅ ጎንደሬ ስለሆነ ነው!››
ይለዋል ቁጣ በተቀላቀለበት ድምፅ፡፡ ዳኛ አማረም ይበልጥ ተናዶ
‹‹እኔ እሰከ ዛሬ ድረስ ያገለገልኩት ሀገሬን ኢትዮጵያ እንጂ የትውልድ መንደሬን አይደለለም፡፡

 ደግሞም ዘረኝነት የለብኝም›› ሲል መለሰለት፡፡
በእንዲህ አይነት ሁኔቴ መዋዘገቡ በመካረሩ መግባባት አልቻሉምና ጉዳዩ ሚንስትሮች ምክር ቤት ደረሰ፡፡

 በሚንስትሮች ም/ቤትም ስብሰባውን የመራው ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ ደመቀ መኮንን ሲሆን፣ ዳኛውም አብሮ ቀርቧል፡፡ አቶ ደመቀ መጀመሪያ ዳኛው ስለጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠየቀ፡፡

 ዳኛውም ስለክሱ አጠር አድርጎ ካብራራ በኋላ እንዲህ ሲል ደመደመ፡-
‹‹እስክንድር ነጋን ‹አሸባሪ› ብሎ ለመፍረድ የሚያስችል በቂ ማስረጃ ስላልቀረበ በሚቀጥለው ቀጠሮ በነፃ አሰናብተዋለሁ፤ እንዲህ ማድረግ አትችልም የምትሉኝ ከሆነ ግን ክቡራን ሚንስትሮች በዕለቱ በችሎት ለመሰየም ፍቃደኛ አለመሆኔን በትህትና ትረዱኛላችሁ ብዬ አስባለሁ!››
ከዚህ በኋላ ሚኒስትሮቹ መወያየት ጀመሩ፡፡

 ተከራከሩ፤ በመጨረሻም አቶ ደመቀ እንዲህ አለ፡-
‹‹እኔም ከአቶ አማረ ጋር እስማማለሁ፡፡ ምክንያቱም በዚህ ሰውዬ /እስክንድር/ የተነሳ ከፍተኛ አለም አቀፍ ጫና እየደረሰብን ነው፡፡ ስለዚህም ብንፈታው ተጠቃሚዎቹ እኛው ነን ብዬ አስባለሁ፡፡

››
አንድ ሚኒስትር ቀጠለ፡-
‹‹በመሰረተ ሃሳቡ ላይ እስማማለሁ፡፡ ነገር ግን እስከዛሬ አስረነው ‹ነፃ ነህ› ብለን ብንለቀው የፖለቲካ ኪሳራ ስልሚያስከትልብን፣ ከፍርዱ ላይ ቅንስናሽ አድርገን ይቅርታ ጠይቆ እንዲወጣ ብናደርግ የተሻለ ነው፡፡››
ሌላ ሚኒስትር ቀጠለ፡-
‹‹እስክንድርን እኔ አውቀዋለሁ፤ የአሜሪካን ሀገር መኖሪያ ፍቃድ እና ብዙ ሀብት እያለው እዚህ ነገር ውስጥ የገባ ሰው ነው፡፡ እናም በፍፁም ይቅርታ ለመጠየቅ ፍቃደኛ አይሆንም››
ሌላኛው ሚንስትር ቀጠለ፡-
‹‹ኧረ ለመሆኑ መለስ አለም አቀፍ ጫና እንደሚያስከትል እያወቀ ለፓርቲያችን ጥቅም ብሎ የገባበትን ጉዳይ፣ ዛሬ እርሱ አልፏል ብለን ጫና ይምንፈራበት ምክንያት ከየት የመጣ ነው? በቃ! መለስ አደገኛ ሰው ነው ብሎ አስሮቷል፡፡

 አለቃ! እዛው ይበስብስ!››
የሚንስትሮች ምክር ቤትም ቢዚህ ጉዳይ ላይ መስማማት ሳይችል በመቅረቱ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዘዳንት አቶ ተገኔ ቀርቦ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጥ ቀጠሮ ይዘው ተለያዩ፡፡

…በእርግጥ ከአቶ ተገኔ ማብራሪያ በኋላ የሚኒስትሮች ም/ቤት ምን አይነት አቋም ላይ እንደደረሰ ለማወቅ ያደረኩት ጥረት ሊሳካ አልቻለም፡፡ መረጃውንም እስከ ዛሬ ያቆየሁት ለዚህ ነበር፡፡ አሁን ግን የቀጠሮ ቀን ሰለደረሰ ልነግራችሁ ተገደድኩ፡፡

 እናም የፊታችን ረዕቡ ከጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሚከተሉት አራት ነገሮች አንዱን እናያለን ብዬ አስባለሁ፡፡

1. የሚንስትሮች ም/ቤት ጫናው ስለከበደው በነፃ ይለቀዋል፣
2. መለስ እያወቀ የገባበትን ጫና አንፈራም! (ራዕዩ እናስቀጥላለን እንደማለት ነው) በማለት የከፍተኛውን ፍርድ ቤት ውሳኔ ያፀናሉ፣
3. ከተፈረደበት 18 ዓመት ላይ ቅንስናሽ አድርገው፣ ይቅርታ እንዲጠይቅ ወደ ማግባባቱ ይሄዳሉ፣
4. ዳኛው አሞኘ እንደፎከረው ከችሎቱ ይቀርና አሁንም
‹‹የመጨረሻ›› ቀጠሮ ይሰጣል፡፡

 የሆነ ሆኖ እንዲህ የሚል አንድ እውነት ‹‹በመሪዎቻችን›› ግንባር ላይ ተቸክችኳል፡፡ ‹‹ሲቪሉ ጀግና እስክንድር ነጋ እያርበደበደው ነው!››
አዎ! እኔም እላለሁ፣ የእስክንድር እና መሰሎቹ የግፍ እስር አርብድብዶ ብቻ አይተዋችሁም!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ! ውድቀት ለአምባገነኖች!!

lørdag 23. mars 2013

በኢትዮጵያ 8 በመቶ የሚሆኑ ህጻናት ብቻ ንጽህናቸው እንደሚጠበቅላቸው ዩኒሴፍ አስታወቀ



ድርጅቱ የአለም የውሀ ቀንን ምክንያት በማድረግ ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ ከአምስት አመት በታች ያሉ ህጸናት በአብዛኛው ከውሀ ንጽህና ጋር በተያያዘ እንደሚሞቱ ገልጿል።

 በኢትዮጵያ የዩኔሴፍ የአስቸኳይና የመስክ ጥናት ቡድን ሀላፊ የሆኑት ሳንጃይ ዊስኬራ ሲናገሩ ” ቁጥሮችን ስንጠቅስ ትክክለኛውን የህጻናትን ፊት ማየት አለብን፣ አንዳንድ ጊዜ በትልልቅ ቁጥሮች ላይ እናተኩራለን፣ ከእነዚህ ትልልቅ ቁጥሮች ጀርባ ስለሚያልቁት ሰዎች ግን አንናገርም። በየቀኑ 90 ህጻናትን የጫኑ አውቶቡሶች ቢጋጩና ህጻናቱን ቢገድሉ ትልቅ ዜና ይሆናል፣ አሁን በአለም ላይ ከውሀ ንጽህና ጋር በተያያዘ እየሆነ ያለው ግን ይህ ነው” ብለዋል።

በኢትዮጵያ ከአምስት አመት በታች ከሚሞቱ ህጻናት 22 በመቶው የሚሞቱት ከውሀ ንጽህና ጋር በተያያዘ በሚፈጠር ተቅማጥ ነው። በቤንሻንጉል ጉሙዝና በጋምቤላ ችግሩ አስከፊ መሆኑንም ሪፖርቱ አመልክቷል። ኢትዮጵያ 62 በመቶ የሚሆነው ህዝብ በፈረንጆች አቆጣጠር በ2015 ንጹህ ውሀ እንዲያገኝ ለማድረግ እየጣረች መሆኑን የገለጸው ዩኒሴፍ፣ በ2011 በተደረገው ጥናት 54 በመቶው ህዝብ የንጹህ ውሀ ተጠቃሚ መሆኑን ገልጿል።

ይሁን እንጅ ይላል ዩኒሴፍ 8 በመቶ የሚሆነው ኢትዮጵያ ብቻ ነው ንጽህናው በተጠበቀ ሽንት ቤት መጠቀም የሚችለው። የንጹህ ሽንት ቤት እጥረት በመላው አገሪቱ የሚታይ መሆኑን የገለጸው ዩኔሴፍ፣ በተለይ ሴት ተማሪዎች በከፍተኛ ሁኔታ መቸገራቸውን ገልጿል።

በደቡብ ክልል ለአቤቱታ የመጡ ዜጎች ታገቱ



የተለያዩ የመብት ጥያቄዎችን ለመጠየቅ በደቡብ ክልል በቁጫ ወረዳ ለአቤቱታ የወጡ ከ1000 ያላሱ ሰዎች በፖሊስ ታግተው መዋላቸውን የአካባቢው ሰዎች ለኢሳት ተናግረዋል።

ከፍትህ ፣ ከመልካም አስተዳዳር እና ከመብት ጋር በተያያዘ በርካታ ጥያቄዎችን ላለፉት 8 አመታት ሲያቀርቡ የቆዩት የቁጫ ወረዳ ነዋሪዎች ፣ 7 ወኪሎቻቸው መታሰራቸውን በመቃወም ትናንት አቤቱታ ለማቅረብ ሲሰባሰቡ በፌደራል ፖሊሶች ታግተዋል። የታሰሩና ድበደባ የደረሰባቸው ሰዎች መኖራቸውም ታውቋል።

ጉዳዩን በማስመልከት ጥያቄ የቀረብንላቸው የአንድነት ፓርቲ የደቡብ ክልል ተወካይና የምክር ቤት የሆኑት አቶ ዳንኤል ሽበሺ በክልሉ በተለያዩ ወረዳዎች የሚታየው ችግር የቆየ መሆኑን ገልጸው፣ የትናንትናው ተቃውሞ የሽማግሌዎች መታሰር መሆኑን ገልጸዋል

አቶ ዳንኤል በሰላም በር የታሰሩት ሰዎች ህዝብን ታነሳሳለችሁ ተብለው መታሰራቸውን ገልጸው በአጠቃላይ በክልሉ ያለው የመልካም አስተዳደርና ፍትህ እጦት መባባሱን አክለዋል።

የአገር ሽማግሌዎች ለምን ታሰሩ? ለአቤቱታ የመጡ ሰዎችስ ለምን ታገቱ በማለት ጥያቄ ያቀረብንላቸው ወረዳው ፖሊስ አዛዥ ሻለቃ አኒሳ ፣ ሰዎቹ ጥያቄ ያቀረቡበት መንገድ አግባብ አይደለም በሚል መታሰራቸውን አምነው፣ ሰልፈኞቹ የመጡበት መንገድ ተገቢ ባለመሆኑ እንደመለሱዋቸውም ተናግረዋል

torsdag 21. mars 2013

የአፍሪካ መዲና-አዲስ አበባ የውሀ እና የመብራት ያለህ እያለች ነው



የውኃና የኤሌክትሪክ መቆራረጥ ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ ይሻሻላል በሚል በትዕግስት ቢጠባበቁም፣ እየባሰበት እንደመጣና መፍትሔ በማጣታቸው ግራ መጋባታቸውን በርካታ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች መግለፃቸውን ሪፖርተር ዘገበ።

እንደ ጋዜጣው ዘገባ ውኃና ኤሌክትሪክ ከዓመት እስከ ዓመት ተቋርጦባቸው እንደማያውቅ ሲነገርላቸው የነበሩ በተለይ በቤተ መንግሥት አቅራቢያ ያሉ ነዋሪዎች ሳይቀሩ አሁን ውኃ እያገኑ ያሉት በሳምንት ለሦስትና አራት ቀናት ብቻ ነው።

ኤሌክትሪክም በሳምንት ውስጥ በቀን ሁለትና ሦስት ጊዜ እየጠፋባቸው ንብረቶቻቸው ጭምር እየተቃጠሉባቸው መሆናቸውን የገለፁት ነዋሪዎቹ፤ አንዳንዴም በፍርኃት መብራት ሳያበሩ እንደሚያመሹ ገልጸዋል፡፡

በሞባይል ስልክ እየተነጋገሩ ሳለ መቃረጡን በተመለከተ ግን የተለመደ ችግር ስለሆነ ከመማረር ውጪ ምንም ሊያደርጉ አለመቻላቸውን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

የውኃና የኤሌክትሪክ ችግርን ግን በመማረር ሊያሳልፉትን ሊቋቋሙት እንዳልቻሉ ነው የሚናገሩት።

በተለይ የውኃ ችግርን መቋቋም እንደተሳናቸው የሚናገሩት ወ/ሮ በለጡ የተባሉ የ አካባቢው ነዋሪ፤ ቀደም ባሉት ጊዜያት አንዱ መንደር ውሀ ቢጠፋ በሌላ መንደር ካለ ቦኖ ውኃ ይገዙና የዕለት ችግራቸውን ይወጡ እንደነበር አስታውሰው፣ አሁን አሁን ግን በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኙ አካባቢዎች ሁሉ ውሀ ስለሚጠፋ የሚያደርጉት ግራ እንደገባቸው ተናግረዋል፡፡

የሕፃናትን ጥም ለማስታገስ የታሸገ ውኃ ለመግዛት ሲሞክሩ ለወትሮው አምስት ብር ይሸጥ የነበረው ግማሽ ሊትር እሽግ ውኃ ስምንት ብር ገብቷል እንደተባሉ የተናገሩት ወ/ሮ በለጡ፣ ነጋዴው ከሰው ያልተፈጠረ ይመስል አጋጣሚን ተጠቅሞ ለመክበር የሚያደርገው መሯሯጥ እንዳሳዘናቸው ይናገራሉ፡፡

ኤሌክትሪክ ቢቋረጥ በእንጨትና ከሰል ማብሰል እንደሚቻልና በኩራዝ ማምሸት ጊዜያዊ መፍትሔ እንደሚሰጥ የገለጹት ወይዘሮ በለጡ ‹‹የውኃን ችግር ግን ምን ያስታግሰው?›› በማለትም ይጠይቃሉ፡፡

ስለጉዳዩ በጋዜጠኞች የተጠየቁት የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋለም ባዩ ፤እርሳቸው ወደ ስብሰባ እንደሚገቡ በመጥቀስ አቶ ፈቃዱ የተባሉ የመሥርያ ቤቱ ባልደረባ ምላሽ እንደሚሰጡ ቢናገሩም፤አቶ ፈቃዱን ማግኘት ሳይቻል ቀርቷል።

አንድ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የባለሥልጣኑ ባልደረባ ግን ውኃ የሚቋረጠው እጥረት ኖሮ ሳይሆን፣ ኤሌክትሪክ ሲቋረጥ ነው ብለዋል።
“የውኃ ፓምፖች የሚንቀሳቀሱት በኤሌክትሪክ ኃይል በመሆኑ፣ ኤሌክትሪክ ሲቋረጥ ውኃም ይቋረጣል፡፡” ያሉት የመስሪያ ቤቱ ባልደረባ፤” ችግሩ የባለሥልጣኑ ሳይሆን ከኮርፖሬሽኑ ጋር የተያያዘ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የውኃ እጥረት ችግር የሚፈጠረው ከኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ ጋር በተያያዘ እንደሆነ እና ከዚህም በላይ ኤሌክትሪክ በተደጋጋሚ እየተቋረጠ የነዋሪዎችን ንብረት እያቃጠለ ስለሚገኝበት ሁኔታ ማብራሪያ እንዲሰጡ የተጠየቁት የኮርፖሬሽኑን የዲስትሪቢዩሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ብርሃነ

‹‹ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ካልገጠመ በስተቀር በተለይ ከሐምሌ ወር 2004 ዓ.ም. እስከ የካቲት ወር 2005 ዓ.ም. ድረስ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል፤›› ብለዋል።

ኃይል የሚቋረጠው በፕሮግራም ለተለያዩ ጥገና ሥራዎች፣ ለመንገድ ግንባታና ለመሳሰሉት ጉዳዮች በመገናኛ ብዙኅን እየተነገረ ነው ያሉት አቶ መስፍና፤

ሌላው ኃይል የሚቋረጠው በተፈጥሮ አደጋና ትላልቅ ግንባታዎች በሚካሄዱባቸው አካባቢዎች የተለያዩ መሣሪያዎች ወድቀው መስመር ላይ ችግር ሲከሰት ብቻ ነው ብለዋል። አልፎ አልፎ ከዋናው ማሰራጫም ቴክኒካዊ ችግሮች ሲያጋጥሙ የኃይል ማቋረጥ እንደሚገጥም አቶ መስፍን አልሸሸጉም፡፡

አቶ መስፍን ችግሩ ከበፊቱ ቀንሷል ቢሉም በተጨባጭ መሬት ላይ የሚታየው ሀቅ ችግሩ እየከፋ መምጣቱን የሚያመላክት ነው።

እንደ ጋዜጣው ዘገባ ለወትሮው የችግሩ ተጠቂ ያልነበሩት መንደሮች ናቸው አሁን በውሀ እና በመብራት ችግር እየተማረሩ ያሉት።

እንደ ወ/ሮ በለጡ ሁሉ በአብዛኛዎቹ ክፍላተ ከተሞች የሚገኙ ነዋሪዎች የውኃና የኤሌክትሪክ በየጊዜው መጥፋት ችግር እየፈጠረባቸው መሆኑን ገልጸው፣ የሚመለከተውን የውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ቅርንጫፍና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ዲስትሪክት ጽሕፈት ቤቶችን ሲያነጋግሩ፣ እንኳን መፍትሔ ሊሰጧቸው ቀርቶ ሊያነጋግሯቸው ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ከ ኢትዮጵያ አልፋ የ አፍሪካ መዲና የሆነችው አዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ የቧንቧ ውሀ፣የ ኤሌክትሪክ እና የስልክ አገልግሎት ተጠቃሚ የሆነችው በአፄ ምኒልክ ጊዜ ቢሆንም እስካሁን ድረስ የተጠቀሱትን አገልግሎቶች ማሟላት አለመቻሏ ብዙዎችን ያስገረመ ሆኗል።

ለኢሳት የሚደርሱት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በሰቆጣ፣ መቀሌ፣ እና በተለያዩ የደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ከፍተኛ የሆነ የውሀ እጥረት ተከስቷል።

በአባይ ግድብ ከሳሊኒ በመቀጠል ከፍተኛው ተጠቃሚ የወ/ሮ አዜብ መስፍን ቤተሰብ ድርጅት ነው ተባለ



ከሁለት ዓመት በፊት ኢሳት በወ/ሮ አዜብ መስፍን የእህት ልጅ በወ/ሮ አቲኮ ስዩም አምባየ የተመሰረተው ኦርቺድ ቢዝነስ ግሩፕ በጣሊያኑ ሳሊኒ ኮንስትራክሽን አማካኝነት በሚገነቡት ግልገል ጊቤ አንድ እና ግልገል ጊቢ ሁለት የሀይድሮ ኤሌክትሪክ ፕሮጀክቶች ስሚንቶ እና የግንባታ እቃዎችን እንዲሁም ከፍተኛ ማሺነሪዎችን በማቅረብ ከፍተኛ የሆነ ትርፍ ማጋበሱን ዘግቦ ነበር።

በአባይ ወንዝ ላይ የሚሰራውን የህዳሴውን ግድብ ፕሮጀክት በቅርብ የሚያውቁ ሰዎች ለኢሳት እንደተናገሩት ይህ ኩባንያ ከሳሊኒ ጋር ግልጽነት የጎደለው የቢዝነስ ስምምነት በማድረግ በአሁኑ ጊዜ ለግንባታው የሚያስፈልገውን ስሚንቶ እንዲሁም ከባድ ማሺኖችን በማቅርብ ላይ ይገኛል።

የውስጥ ምንጮች እንደሚሉት ግድቡን ከሚገነባው ሳሊኒ በመቀጠል ከፍተኛ የሆነ ትርፍ የሚያገኘው ኦርቺድ ፣ ከየትኛውም ድርጅት ጋር ሳይወዳደር በእነ ወ/ሮ አዜብ መስፍን አማካኝነት የስሜንቶና ማሸንሪዎች አቅራቢ ሆኖ ቀርቧል።

ከድርጅቱ ድረገጽ ላይ ለመረዳት እንደተቻለው ድርጅቱ በግልገል ጊቤ የሀይል ማመንጫ የመንገድ ስራ፣ በአዲስ አበባ ጅማ የመንገድ ጥገና፣ በግልገል ጊቤ ሶስት ኤር ስትሪፕ ግንባታ፣ በኮሌ ሃላላ የመንገድ ጥገና፣ በአዲስ አበባ አዳማ የመንገድ ፕሮጀክት፣ በአርባ ምንጭ አየር ማረፊያ የመንግድ ጥገና እና በሌሎችም የመንገድና የህንጻ ስራዎች ላይ ተሳትፎአል።

ኩባንያው ቦዲ ዋይዝ ጂም፣ ካፌ ፓኒኒ፣ ኦርቺድ ጄኔራል ኮንትራክተር፣ ኦርቺድ ትራንስፖርት፣ ኦርጂድ ትራንዚት፣ ኦርቺድ ማሽነሪ ሬንታል፣ ኤስ ኤንድ ኤስ እርሻ፣ ሂላላ ቱር ኤን ትራቭል፣ ሜትሮሉክስ ፍላወር፣ ናይል ስፕሪንግ ውሀ፣ ሬንቦው ጊፍት ሾፕ፣ ሪል ሳሎን፣ ወንደር ዊል ቢዝነስና ሌሎችም በአዲስ አበባና በመላው አገሪቱ ታዋቂ የሆኑ የንግድ ድርጅቶችን በስሩ አቅፎ የያዘ ነው።

ወ/ሮ አቲኮ ኢህአዴግ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር ይህ ነዉ የሚባል ኃብት እንዳልነበራቸው ታሪካቸውን ያጠኑ የኢሳት ዘጋቢዎች ያረጋገጡ ሲሆን ባለፉት 20 አመታት ግን በልዩ ትዕዛዝ “ኦርቺድ” ቢዝነስ ግሩፕ የሚባል ድርጅት ተከፍቶላቸው ሆን ተብሎ አያሌ የግንባታ ጨረታዎችን እንዲያሸንፉና በአጭር ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ቱጃሮች ተርታ ለመመደብ እንደቻሉ መግለጻችን ይታወሳል።
የሀወሀት ኢህአዴግ ባለስልጣናት በዘመዶቻቸው ስም የሚገነቡዋቸው የቢዝነስ ተቋማት እየተበራከቱ መምጣቱን በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል። የባለስልጣናትን የሀብት ምዝገባ ጨርሶ በአጭር ጊዜ ይፋ አድረጋለሁ በማለት ሲፎክር የነበረው ጸረ ሙስና ኮሚሽንም ቃሉን ለመጠበቅ እንደተሳነው መዘገባችን ይታወሳል። ኮሚሽኑ ባለስልጣናቱ በዘመዶቻቸው ስም ዬያዙትን ሀብትና ንብረት ለመመዝገብ ስልጣን እንዳልተሰጠው መግለጹ ይታወሳል።

የህዳሴውን ግድብ ለመጨረሽ ከ90 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ ይታወቃል። በቀን እስከ 30 ሰራተኞች በክፍያ ምክንያት ስራቸውን እየለቀቁ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል።

tirsdag 19. mars 2013

የግራዚያኒን ሀውልት ግንባታ በመቃወም ታሰረው የተፈቱ ዜጎች ዘራቸው እየተጠቀሰ መሰደባቸው ታወቀ



የፋሽስት ኢጣሊያ መንግስት ወኪል በመሆን በአንድ ቀን ከ30 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያንን በስድስት ኪሎ አደባባይ የጨፈጨፈውን የሮዶልፎ ግራዚያኒን ሀውልት ለማቆም እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ለመቃወም ትናንት እሁድ በስድስት ኪሎ የተሰባሰቡ የባለራእይ ወጣቶች ማህበር አባላት፣ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እንዲታሰሩ ተደርጓል።

የጸጥታ ሀይሎች ታዋቂውን የህግ ባለሙያና ፖለቲከኛ ዶ/ር ያእቆብ ሀይለማርያምን ጨምሮ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነትን ለአንድ ቀን ካሰሩዋቸው በሁዋላ በመታወቂያ ዋስ ለቀዋቸዋል።

 ከእስረኞች መካከል አንዳንዶቹ ብሄር ተብለው ሲጠየቁ ኢትዮጵያውዊ በማለት የመለሱ ዘራቸው ሳይቀር እንደተሰደበ ታውቋል።

 በርካታ ወጣቶች የኢሜል እና የፌስ ቡክ የሚስጢር ቁልፋቸውን ( ፓስወርድ) እንዲሰጡ መጠየቃቸውንም ለማወቅ ተችሎአል።

በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየታቸውን የሰጡት ለአንድ ቀን ታስረው የተፈቱት ዶ/ር ያእቆብ ፣ እርሳቸውና ሌሎች ሰዎች የታሰሩት ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ፈቃድ አልተጠየቀም በሚል ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል። ።

ዶ/ር ያእቆብ የጸጥታ ሀይሎች የወሰዱት እርምጃ መንግስት ለግራዚያኒ እንደቆመ ያስቆጥርበታል ብለዋል።

የባለራእይ ወጣቶች ማህበር መሪ ወጣት ሀብታሙ አያሌው በበኩሉ ፈቃድ የጠየቁት ከ 14 ቀናት በፊት እንደነበር ገልጿል::

በታሰሩት ላይ የተደረገው ምርመራ ከጉዳዩ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳልነበረው ወጣት ሀብታሙ ተናግሯል::

ወጣት ሀብታሙ ዛሬም አንድ አባላቸው ታስሮ እንደነበር ገልጾ ወዴት እየሄድን እንደሆን አናውቅም ብሎአል:: በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስትን አቋም ለማወቅ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

Human Rights Watch World Report 2013 – Ethiopia



Source: Human Rights Watch World Report 2013, pp 114-120
The sudden death in August 2012 of Ethiopia’s long-serving and powerful prime minister, Meles Zenawi, provoked uncertainty over the country’s political transition, both domestically and among Ethiopia’s international partners. Ethiopia’s human rights record has sharply deteriorated, especially over the past few years, and although a new prime minister, Hailemariam Desalegn, took office in September, it remains to be seen whether the government under his leadership will undertake human rights reforms.

søndag 17. mars 2013

መኢአድ መንግስት በዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲከሰሰ ጠየቀ



በቋንቋ ማንነት ህዝብን መግደል፣ ማፋናቀል እና ማሰር የዘር ማጥፋት ወንጅል ነው” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ” ሰሞኑን በቤንሻንሂል ጉሙዝ ክልል በአማራ ተናገሪ ማህበረሰብ ላይ የተከፈተው ማፈናቀል ፣ በጅጅጋ እና በአፋርም የቀጠለ ሲሆን በመላው አገሪቱ የአማርኛ ተናጋሪ ህዝብ ቤት እንዳይኖረው ፣ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ እንዳይሳተፍ በተለያየ ስልት ደሀ ሆኖ እና በጎዳና እንዲበተን የወያኔ ካድሬዎች አዲስ አበባን ጨም ሮ በሁሉም ትእዛዝ የሰጡ ሲሆን በአዲስ አበባ ከፈረሱ እና እያፈረሱ ካሉ ቤቶች አብዛኞቹ የአማራ ተናጋሪዎች መኖሪያ መሆናቸውን መታዘቡን ” ገልጿል።

በአዲስ አበባ እና በተለያዩ ከተማዎች የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች የባንክ ብድርን ጨምሮ መሬት እንዳያገኙ ከመደረጉም በላይ ከፍተኛ ግብር እየተጫነባቸው በመሆኑ ከንግድ ስርአቱ እንዲወጡ ተድርጓል ብሎአል መኢአድ
በአሁኑ ጊዜ ከ200 በላይ ከቤንሻንጉል ጉምዝ የተፈናቀሉ የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች በባህርዳር ያለመጣለያ በጎዳና እየኖሩ መሆኑን መኢአድ በመግለጫው አመልክቷል።

በባህርዳር ለጎዳናና ተዳዳሪነት ከተዳረጉት መካከል ብዙ ነፍሰጡሮችና ህጻናት የገኙበታል።

አገዛዙ ከመጀመሪያው ጀምሮ የአማርኛ ተናጋሪውን ህዝብ በብሄራዊ ጨቋኝነት በመፈረጁ በአርባ ጉጉ ፣ በበበደኖ፣ በአርሲ፣ በባሌ፣ በጋምቤላ እንዲጨፈጨፍ ሲያድረጉ አገዛዙ ምን ያክል የአማርኛ ተናጋሪውን ህዝብ ለማጥፋት እንደፈለገ አመለካች ነበር፣ የሚለው መኢአድ፣ ከአንድ አመት በፊት በቤንች ማጂ ዞን በጉራፈርዳ ወረዳ በከፍተኛ ጭካኔ በአማርኛ ተናጋሪ አርሶአደር ፣ ሴቶች፣ ነፍሰ ጡር፣ ህጻናት እና ሽማግሌዎች ላይ የተጀመረው ጭካኔ የተሞላበት ስደት ተባብሶ ቀጥሎ በየጎዳናው የሚጣለው የኔቢጤ ከመሆን አልፎ ለአውሬና ለአሰቃቂ ኑሮ የተጋለጠው የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ህብረተሰብ ቁጥር እየጨመረ በቤንሻንጉል ፣ በጅጅጋ፣ በአፋር እና በአንዳንድ የአሮሚያ ክልል እየቀጠለ ነው ብሎአል፡፡


መኢአድ ” ማንኛውም ሰው በቋንቋው ፣ በጎሳው፣ በእምነቱ፣ በቀለሙ እና በማንኛውም ልዩነት ምግብ ሲያጣ መጠለያ ሲነፈገው ጨቅላ ህጻናት በየጎዳናው ሲሞቱ፣ ነፍሰጡሮች በየበረንዳው ሲወድቁ፣ ህሊናን የሚያደማ መሆኑን ገልጾ፣ የህንን ጨቋኝ ስርአት በአለም ህዝብ ፊት በዘር ማጥፋት ወንጀል ልንከሰው ይገባል ብሎአል። በቤንሻንጉል ጉሙዝ ከ5 ሺ ያላነሱ ኢትዮጵያውያን እንዲፈናቀሉ መደረጉን መዘገባችን ይታወሳል።


ይህ በእንዲህ እንዳለ ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ የተባሉ የ67 አመት አዛውንት ” ልጄ በእሳት ተቃጥላ እንድትሞት ተደርጋ፣ ቤቴን ተነጥቄና ንብረቴ ወድሞ ከሀረር ተባረርኩ” ሲሉ ለፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ ገልጸዋል፡፡


ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ የሚባሉት እኚሁ እናት የ75 ዓመት አዛውንት የሆኑት ባለቤታቸውም እንደ እሳቸው ሁሉ ጎዳና ላይ መውደቃቸውን ከዕንባቸው ጋር እየታገሉ መግለጻቸውን ጋዜጣው ዘግቧል። “በሐረር ከተማ ቀበሌ 17 ውስጥ ከ30 ዓመት በላይ ኖሬ፤ ሀብትና ንብረት አፍርቼ እኖር ነበር አሁን ግን በአካባቢው እንዳልኖር ተደርጌያለሁ” የሚሉት ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ “ከ30 ዓመት በላይ የኖርኩበትን ቤቴን የወረዳው አስተዳዳሪ እና የወረዳው ፓሊስ አዛዥ አስጠርተው ቤትሽን ለወ/ሮ አኒሳ መሐመድ ሸጠሽ ግቢውን እንድታስረክቢያት አሉኝ፡፡” ብለዋል።


” እኔ ቤቴን የመሸጥ ሐሳብ የለኝም፡፡ ቤቴን ሸጪ የት እወድቃለሁ? አልሸጥም አልኳቸው እንቢ ካልሽ ከአገራችን እናባርራሻለን በገንዘብ አልሸጥም ካልሽ በባዶሽ ተባረሽ ወደ አገርሽ ትሄጃለሽ አሉኝ፡፡ እኔ ሌላ አገር የለኝም የምሄድበትም ቦታ የለኝም መንግስት ባለበት አገር ቤትሽን ተቀምተሽ ውጪ የሚለኝ የለም ብዬአቸው ተመለስኩኝ” በማለት የችግሩ መነሻ አስረድተዋል።


ጎስቋላዋ የ67 ዓመት እናት በማያያዝም “በማግስቱ እኔ ቡና አፍልቼ፣ ባለቤቴም ጫማውን አውልቆ ፍራሽ ላይ አረፍ እንዳልን፤ አንድ ፓሊስ በሩን በሰደፍ እና በእርግጫ መቶት በረገደው፡፡ ምንድነው? ብለን ስንወጣ ከ30 በላይ ፓሊሶች ቤታችንን ከበውታል፡፡ ይህች ናት፡፡ ነይ ውጭ! ብሎ ለሁለት ሶስት ሆነው ጎተቱኝ፡፡ እባካችሁ ምን አደረኩ ብዬ ስለምናቸው አንቺ ለህግ አልገዛ ያልሽ አመጸኛ ነሽ! ወንጀለኛ ነሽ እያሉ መሬት ለመሬት ጎተቱኝ፡፡ እባካችሁ ምንም የሰራሁት ወንጀል የለም ብዬ ጮኩኝ፡ ፡ ጎረቤት ተሰበሰበ ምንድነው ብሎ ጠየቀ ማንም ምላሽ አልሰጠም” የሚሉት ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ ሟች ልጃቸውን በሀዘን ተውጠው እያስታወሱ ይቀጥላሉ “ልጄ ባል አግብታ የምትኖረው ሌላ ቦታ ነው፡፡ ቀን ቀን ምግብ እየሰራች ትሸጣለች ፓሊሶች እናትሽን ከበው እየደበደቡ ናቸው ብሎ ጎረቤት ሲደውልላት ሮጣ መጣች፡፡ ደርሳ ምን አድርጋ ነው ብላ ብትጠይቅ ቤቱን አስረክቢ ስትባል እንቢ ብላ ነው አሏት፡ ፡ የተወለድንበትና ያደግንበትን ቤት ከህግ ውጭ እንዴት እንነጠቃለን ብላ ስትጮህ ጥላው ሄዱ” በማለት በለቅሶ ያስረዳሉ፡፡


ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ “ያንለቱኑ ማታ ልጄ ምግብ የምትሸጥበት ቦታ ሁለት ሰዎች ተመጋቢ መስለው ከገቡ በኋላ ፣ ረመዳን የተባለ ፓሊስና እንዳለ ግርማ የተባለ ወጣት፣ ቤቱን አስረክቡ ስትባሉ አናስረክብም የምትሉት ለምንድነው ብለው ረመዳን ልብሷና ሰውነቷ ላይ ጋዝ ሲደፋባት እንዳለ ግርማ የተባለው ላይተር ለኩሶ አቃጥለዋታል፡፡ ሳትሞት ሆስፒታል ደርሳ ነበር፡፡ በማግስቱ አዲስ አበባ አምጥቼ ላሳክም መኪና ተከራይቼ ይዤ ስወጣ ፓሊስ እዚህ አትታከም እንጂ ከሐረር አትወጣም ብሎ ከለከለኝ፡፡ እኔም ገንዘብ ካለኝ እንኳን አዲስ አበባ አሜርካን ወስጄ ባሳክም ለምን እከለከላለሁ ብዬ ብጮህ ባለቅስ ማንም ሊደርስልኝ አልቻለም፡፡ ልጄ ህክምና አጥታ ሞተች፡፡” ብለዋል፡፡


አዛውንቷ ከልጃቸው ሞት በኋላ የደረሰባቸውን በምሬት ሲገልጹ “እኔንም ከቤቴ አስወጥተው ቦታውን ሺጭላት ላሏት ሴት ሰጧት፡ ፡ አሁን ቦታዬ ላይ ፎቅ እየተገነባ ነው፡፡ እኔና ባለቤቴ ግን ጎዳና ተጣልን፡፡ የአካባቢው ህብረተሰብ አዋጥቶ የሰጠኝን 3ሺ ብር አንድ ፓሊስና አንድ ደላላ መጥተው ነጠቁኝ፡፡ ሐረር ውስጥ አደሬ ወይም ኦሮሞ ካልሆንክ አቤት የሚባልበት ቦታ የለም፡፡ አማራ ነው ከተባለ ሁሉም ባለስልጣን በደረሰበት ግፍና ስቃይ ይስቅበታል፡፡ በደርግ ጊዜ የሐረር ፓሊስ አዛዥ ትግሬ ነበር፤ የማረሚያ ቤት አዛዥም ትግሬ ነው፡፡ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ትግሬ ነው፡፡ ለምን ትግሬ ሆነ ያለ አንድም ሰው የለም፡፡ ዛሬ በሀረር በየትኛውም መስሪያ ቤት አማራ ባለስልጣን የለም፡፡ ባለቤቴ ኦሮሞ ነው፡፡ ልጆቼም ኦሮሞ ናቸው፡፡ እኔ አማራ በመሆኔ ብቻ ይህ ሁሉ ጉዳት ተፈጸመብን፡፡” የሚሉ ወይዘሮዋ፣ የተፈፀመባቸው የሰብአዊ መብት ጥሰት ዘራቸውን መሰረት ያደረገ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡


አክለውም “አዲስ አበባ መጥቼ ለእንባ ጠባቃ ተቋም አመለከትኩኝ፡፡ ፌደራል እንባ ጠባቂ ተቋም እንዴት እንዲህ ይፈጸማል ብለው ይዘውኝ ሐረር ተመለሱ፡፡ የቤቴ ካሳ እንዲከፈለኝ ተወሰነልኝ፡፡ የክልሉ ባለስልጣናትም እሺ ይፈጸምሎታል ብለው ቃል ገቡልኝ፡፡ እንባ ጠባቂዎቹ ወደ አዲስ አበባ ተመልሱ፡፡ እነሱ ከተመለሱ በኋላ ግን ምንም መፍትሄ አልሰጡኝም፡፡ በድጋሚ አዲስ አበባ መጥቼ ለእንባ ጠባቂ ተቋም ባመለክት እነሱም ውሳኔያቸውን እንደ አጀማመራቸው ሊያስፈጽሙልኝ አልቻሉም፡ ፡ ጉዳዬንም ለመስማት ፍቃደኛ አልሆኑም፡፡ ” በማለት የበደላቸውን ስፋት ለፍኖተ ነፃነት ዘጋቢ በዝርዝር አስረድተዋል፡፡


“ዛሬ እኔ አዲስ አበባ ላይ ባለቤቴ ደግሞ ሐረር ላይ ጎዳና ላይ ነን፡፡ መፍትሔ ማግኘት አልቻልኩም” ሲሉ ተስፋ መቁረጥና ምሬት ተሞልተው በለቅሶ የመንግስት ያለህ … የህዝብ ያለህ በማለት ጥያቸውን ማቅረባቸውን ጋዜጣው ዘግቧል።

fredag 15. mars 2013

አሁን ያለው ሕወሐት ቆዳ ነው” እነ ስብሃት



   ሁለት ቦታ የተከፈለው የሕወሐት አመራር ልዩነቱን በማስፋት እየተወዛገበ መሆኑን ከመቀሌ ታማኝ ምንጮች  ገለፁ። ስብሃት    እና አዜብ የሚመሩት ሁለቱ ቡድን አነጋጋሪ አቋም ይዞ መውጣቱን ምንጮቹ ጠቁመዋል።

    በስብሃት ነጋ የሚመራው ቡድን ባስቀመጠው አቋም « መለስ ሕወሐትን ገድሎ ነው የሔደው! አሁን ያለው ሕወሐት ቆዳ ነው።

 ጥያቄው ግልፅ ነው፤ ሕወሐት መቀጠል አለበት.. ወይስ የለበትም?» ሲሉ በድርጅቱ ቀጣይ ሕልውና ላይ ጥያቄ አሳርፈዋል።

 ከዚህ በተቃራኒ የቆመውና አባይ ወልዱ፣ አዜብና ከጀርባ በረከት ስምኦን ያሉበት ቡድን በበኩሉ « የሕወሐት ወራሾች እኛ ነን፤» ሲል ለነስብሃት ምላሽ መስጠቱ ታውቋል።

 በተጨማሪ በሁለቱም ቡድኖች በልዩነት ነጥብ ተደርጎ የተወሰደው በ1993ዓ.ም ከፓርቲው የተባረሩት አመራሮች « ይመለሱ» ፣ « አይመለሱም»
 የሚለው እንደሚገኝበት ተጠቁሟል። የሁለቱም ጐራ ፖለቲካዊ ግብ አንዱ ሌላኛውን ገፍትሮ ከሜዳው ማስወጣትና ፓርቲውን ብሎም አገሪቱን በፈላጭ ቆራጭነት ለመቆጣጠር ያለመ እንደሆነ አንድ የፓርቲው ቅርብ ሰው ጠቁመዋል።

በፓርቲው በተለኮሰው ስር የሰደደ ፖለቲካዊ ፍጥጫ ካድሬው ለሁለት ተከፍሎ ሲነታረክ መሰንበቱን ምንጮች ጠቁመዋል።

በፓርቲው አባላት « አደገኛ» የተባለውን ይህን ፍጥጫ መሰረት በማድረግ በቴውድሮስ አድሃኖምና ብርሃነ ገ/ክርስቶስ የሚመራ ቡድን ራሱን « የአስታራቂ ሽማግሌዎች ቡድን» በሚል ሰይሞ ባለፉት ቀናት ሲነቀሳቀስ መቆየቱን ገልፀዋል።

 ሆኖም ሁለቱን ጎራዎች አቀራርቦ ለማነጋገርና ለማስማማት የተጀመረው ጥረት በሁለቱም በኩል በሚታየው አክራሪ አቋም ምክንያት ተስፋ ሰጪ ሁኔታ እንደማይታይ ምንጮቹ አስታውቀዋል።

 አሁንም ድርድሩ መቀጠሉን ምንጮቹ አልሸሸጉም።

የሕወሐት ሕልውና አጣብቂኝ ውስጥ በገባበት በአሁኑ ወቅት በሌላ ጐራ የተነሱ ወጣት የፓርቲው ካድሬዎች ባነሱት ጥያቄ ፥ ሁሉም አንጋፋ አመራሮች ከድርጅቱ እንዲለቁ ጥያቄ ማቅረባቸውንና ይህን ለማድረግ ፈቃደኛ ካልሆኑ ግን ሕወሐት ሊፈርስ እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ጭምር መስጠታቸውን ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል።

በተያያዘም « ጉባኤ ይጠራ» በሚል በካድሬዎች የቀረበውን ጥሪ እነ አባይ ወልዱና አዜብ ያሉበት ቡድን ውድቅ እንዳደረገው ታውቋል። አባይና አዜብ የሚመሩት እንዲሁም ትርፉ ኪዳነማሪያም፣ ሃድሽ ዘነበ፣ አለም ገ/ዋህድ፣ በየነ ምክሩ፣ ተክለወይኒ አሰፋና ሳሞራ የኑስ የተካተቱበት ቡድን በጉባኤው አሸናፊ ሆነው እንደማይወጡ ከወዲሁ በማመናቸውና በነስብሃት በኩል ከፍተኛ ሃይል እንደተደራጀባቸው ጠንቅቀው ስለተረዱ ነው ሲሉ የጠቆሙት ምንጮቹ አክለውም ሳሞራ በመከላከያ እጣ ፈንታቸው ተመሳሳይ መሆኑን በማመናቸው ከነአዜብ ጋር ተሰልፈው እንደሚገኙ ገልፀዋል።

የበላይነትን እየያዘ ነው የሚባለውና በስብሃት የተደራጀው እንዲሁም በደብረፂዮን የሚመራው ቡድን አብዛኛውን የማ/ኮሚቴ አመራር በዙሪያው ያሰባሰበ ሲሆን ከነዚህም፥ አዲስአለም ባሌማ፣ አርከበ እቁባይ፣ ቅዱሳን ነጋ፣ ፈትለወርቅ፣ ፀጋዬ በርሄ፣ አባዲ ዘሙ፣ ሃ/ኪሮስ ገሰሰ፣ ተ/ብርሃን…በዋንኛነት እንደሚገኙበት ምንጮቹ አመልክተዋል። የሽማግሌው ቡድን ስብስባ እንደቀጠለ ተጠቁሞዋል።

onsdag 13. mars 2013

Listening Post Feature - Ethiopia: Journalism akin to terrorism

እንደምን ሰነበታችሁ? ይህ ለአፋና እጅ የማይሰጥ የህዝብ ድምፅ ነው፡፡



እንደምን ሰነበታችሁ? ይህ ለአፋና እጅ የማይሰጥ የህዝብ ድምፅ ነው፡፡ለዜጎች ክብር የማይሰጠው ኢህአዴግ፣ ህዝብ በሚከፍለው ግብር መልሶ የሚያፍነው ኢህአዴግ፣ የሀይማኖት ተቋማትን ወደ ‹‹አጋር ፓርቲ››ነት እየቀየረ ያለው ኢህአዴግ ፍትህ ጋዜጣን እና አዲስ ታይምስ መፅሄትን በጉልበት ከነጠቀን በኋላ፣ ለሶስተኛ ጊዜ በሌላ ጋዜጣ ተመልሰናል፡፡ ጋዜጣዋ ‹‹ልዕልና›› ትባላለች፡፡

 ከተመሰረተች ጊዜ ጀምሮ ለአንዴ ብቻ ታትማ ተቋርጣ ነበር፡፡ አሁን ግን የነበረባት የመንግስት ዕዳ ተከፍሎ፣ አሳታሚ ድርጅቱ በሀገሪቱ የአክሲዮን ሽያጭ ህግ መሰረት ወደ እኛ መዞሩን አበስራለሁ፡፡

 እናም ዛሬ በዕለተ ቅዳሜ ለአንባቢያን ትደርሳለች፡፡ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ግን ‹‹አርብ አርብ ይሸበራል፤ …›› እንዲል ንጉስ ቴውድሮስ፣ ልዕልና ጋዜጣም የዕለት አርብ ድምፅ ሆና ትቀጥላለች፡፡

እንደመውጫም ይሆነኝ ዘንድ በአዲሷ ጋዜጣችን ላይ ‹‹ከተዘጋው በር ጀርባ›› በሚል ርዕስ ላቀረብኩት ፅሁፍ መግቢያ ያደረኩትን እዚህም ልድገመው፡-
እነሆ በሶስተኛው በር ተገናኝተናልና አብዝቼ አላማርርም፡፡

 ባማርርስ የት እደርሳለሁ? ማነው አገዛዙንስ ከስሶ የረታ? ደግሞስ ከመቼ ወዲህ ነው በሀገሬ መሬት ላይ ህግ የበላይ ሆኖ የሚያውቀው? ለማንኛውም የጠፋው ብርሃን በዚህ መልኩ ዳግም ይፈነጥቅ ዘንድ ስለተከፈለው ዋጋ ወይም ውጣ ውረድ ገድል የመፃፍ ፍላጎት የለኝም፡፡

 ፍላጎቴ ከባልደረቦቼ ጋ በፀና መንፈስ በጀመርነው ጎዳና እንተም ዘንድ የመንግስትን አፈና አውግዛችሁ የሞራል ድጋፍ ለሰጣችሁን ኢትዮጵያውያን፤ እንዲሁም የአለም አቀፍ የፕሬስ ነፃነት ተሟጋች ተቋማት ላሳያችሁት አጋርነትና ተቆርቋሪነት፣ በሀገሬ ላይ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ይሰፍን ዘንድ ዋጋ በከፈሉና እየከፈሉ ባሉ ወንድምና እህቶቼ ስም ልባዊ ምስጋናዬን ማቅረብ ነውና-ቺርስ ለነፃነታችን!

መንግስት ታላቁን የአፋር ኡለማ ሊያስር ነው!


አፋሮች ትግሉን መቀላቀላቸው ተከትሎ ታላቁ የሀይማኖት መሪ ሸህ መሀመድ አወል ሃይታንን ለማሰር ፌዴራል ፖሊስ እየተጠራ እንደሆነ ታወቀ::

በአፋር ህዝብ ዘንድ እንደ አባት የሚታዩትን ታላቁን ዐሊም ሸህ መሀመድ አወል ሀይታንን ለማሰር መንግስት እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሆነ ታወቀ፡፡
 መንግስት ይህን እርምጃ ሊወስድ ያሰበው ለወትሮውም ቢሆን ለዲኑ ቀናኢ መሆኑ የሚታወቀው የአፋር ህዝብ በአሁን ሰዐት በዲኑ ላይ እየደረሰ ያለውን ጭቆና ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን መቃወም በመጀመሩ ነው፡፡

 ሆኖም ግን የአፋር ነዋሪዎች እንደሚሉት የአፋር ህዝብ ስለ ዲኑና ስለ ማንነቱ ጠንቅቆ ያወቀበት ደረጃ ላይ በመድረሱ የትኛውንም አይነት ጭቆና ለመቀበል ፍቃደኛ አይደለም፤ ለዚህም ተቃውሞውን ተቀላቅሏል፡፡

 የአፋር ህዝብ ከጊዜ ወደ ጊዜ መንቃቱ ያሰጋው መንግስት በበኩሉ በህዝብ ዘንድ ትልቅ ክብር ያላቸውን ሸህ ለማሰር እንደወሰነ፣ ይህ ደግሞ ትልቅ ዋጋ እንደሚያስከፍለው እየተነገረ ነው፡፡

መንግስት ታላቁን የአፋር ኡለማ ሊያስር ነው! ሸህ መሀመድ አወል ሀይታን በሎጊያና በሰመራ በአፋርኛ የቁርዐን ተፍሲርና ሃዲስ ህዝቡን ከማስተማራቸውም በላይ ህዝቡ እርስ በእርሱ እንዲቀራረብ ፣ እንዲከባበር፣ እንዲዋደድና ከሌላው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ጋርም እንዴት ተቻችሎ መኖር እንደላለበት የሰበኩ ታላቅ የሃይማኖት አባት መሆናቸው ይታወቃል፡፡

 የህዝቦች መቀራረብና ሰላም መሆን ምቾት ለማይሰጣቸው የመንግስት አካላት ግን ጉዳዩ ፍርሃት ስለለቀቀባቸው ሸሁን ማሰር አማራጭ አድርገው እንደያዙት ታውቋል፡፡

 ሸህ መሀመድ እንዲታሰሩ ለመንግስት ያማከሩ ግለሰቦችና ምክሩንም ተቀብለው ተግባራዊ ያደረጉ ባለስልጣናት የመንግስትን ውድቀት የሚሹ እንደሆኑ የጠቆሙት ምንጮቻችን ቁርዐንና ሃዲስ ለምን አወራህ፣ ህዝብ እንዲከባበርና አንድ እንዲሆን ለምን መከርክ በሚል ሰበብ ሸሁ እዲታሰሩ ሲወስኑ የአፋር ህዝብን በሙሉ ሰብስቦ እስር ቤት እንደማስገባት አድርገው ሊቆጥሩ እንደሚገባና ይህም ትልቅ ዋጋ የሚያስከፍላቸው እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአፋር ህዝብ ሀይማኖቱን የሚጨቁኑበትንና የሀይማኖት አባቶቹን ወደ እስር ቤት የሚልኩበትን አካላት በሰላማዊ መንገድ ለመቃወም ከምንግዜውም በላይ እንደተዘጋጀ ታውቋል፡፡

 መንግስት ሸህ መሀመድ አወል ሀይታንን ለማሰር በእንቅስቃሴ ላይ መሆኑ እንደታወቀ የአካባቢው ሰዎች እንደገለፁት ‹‹መንግስት ህዝብን ማዳመጥ አለበት፣ ህዝብ ያልፈለገውን ነገር በግድ ለመጫን መሞከር ከመንግስት አይጠበቅም፡፡

 መንግስት ለሀገርና ህዝብ ደህንነት ያስባል በሚል አመት ሙሉ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ሰላማዊ ጥሪ ላይ ቢገኝም አንዳንድ የመንግስት ፅንፈኛ ባለስልጣናት ከታሪክ መማር ባለቻላቸው ለሀገሪቷ የማይጠቅም ውሳኔ ውስጥ እየገቡ ነው ›› ሲሉ ወቅሰዋል፡፡

 አያይዘውም ‹‹የህዝብ ሙስሊሙ ጥያዌ ምላሽ ያገኛል በሚል ተስፋ ላይ እያለን ጭራሽ በክልላችን እንደ አባት የምናያቸውን ታላቁን ዐሊማችንን ለማሰር መወሰኑ የአፋርን ህዝብ ከምንግዜውም በላይ ድምፁን እንዲያሰማ ያደርገዋል እንጂ ወደ ኋላ አይጎትተውም›› ብለዋል፡፡

tirsdag 12. mars 2013

በአፋር ክልል ነዋሪዎችን የማፈናቀሉ ዘመቻ ቀጥሎታል


ከክልሉ ያገኘነው መረጃ እንደሚያስረዳው ከሸንኮራ አገዳ ልማት ጋር በተያያዘ ተጠናክሮ የቀጠለው የህዝብ መፈናቀል ህብረተሰቡን ለከፋ ድህነት እየዳረገው ነው።

 የመንግስትን ትእዛዝ ለመቀበል ፈቃደኛ ያልሆኑ ሴቶች እስከ ልጆቻቸው መታሰራቸውን የክልሉ የመኢአድ ጠጠሪ የሆኑት አቶ አሊ ሚራህ ለኢሳት ገልጸዋል

ህዝቡ ጉዳዩን ገለልተኛ አካል መጥቶ እስከሚያየው ድረስ ከቦታችን አንነሳም ማለቱን አቶ አንፍሬ ተናግረዋል
በአፋር፣ በቦረና ዞን እና በዋልድባ አካካቢዎች ከስኳር ልማት ጋር በተያያዘ የሚታየውን የህዝብ መፈናቀል ስንዘግብ መቆየታችን ይታወሳል።

በሁሉም ክልሎች የአማራ ተወላጆች እንዲወጡ መደረጉ እጅግ አሳሳቢ ሆኗል ሲል መኢአድ ገለጸ



የመኢአድ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ወንድማገኝ ደነቀ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ” በሁሉም ክልሎች የሚገኙ የአማራ ተዋላጆች ወደ ክልላቸው እንዲመለሱ መታዘዙ፣ ችግሩን በእጅጉ ውስብስብ አድርጎታል።

በደቡብ ክልል በጉርዳ ፈርዳ ወረዳ የተጀመረው መፈናቀል ሳይቆም፣ በባሌ፣ በአፋርና በሶማሊ ክልሎች ተመሳሳይ መመሪያዎች እየተላለፉ መሆኑን የገለጡት ምክትል ሊቀመንበሩ ፣ ተፈናቃዮች ለሞት መዳረጋቸውን ገልጸዋል

አቶ ወንድማገኝ በአማራ ተወላጆች ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ የህወሀት የቆየ የዘር ፖሊሲ መሆኑን ገልዋል
” መኢአድ መግለጫ ከማውጣት ባለፈ ችግሩን ለማስቆም ምን የሚወስደው እርምጃ አለ ተብለው የተጠየቁት አቶ ወንድማገኝ፣

ችግሩ የሚቆመው መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሲተባበርና ድርጅቶችም በጋራ ሲቆሙ መሆኑን ገልጸው፣ የተቃውሞ ሰልፎችን ለማካሄድ እቅድ መኖሩንም ተናግረዋል

ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለው በአማራ ክለል ዋና ከተማ ባህርዳር የደረሱ የአማራ ተወላጆች የክልሉ ባለስልጣናት መፍትሄ እንዲሰጡዋቸው ቢጠይቁም ፣ ባለስልጣናቱ ጉዳዩ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ጉዳይ በመሆኑ እንደማያገባቸው መግለጻቸውን ተፈናቃዮች ለኢሳት መግለጻቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

እነ አቶ አያሌው ተሰማ ጥፋተኞች ተባሉ


የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 8ኛው ወንጀል ችሎት የአያት አክሲዎን ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አያሌው ተሰማ፣ የአክሲዮን ማህበሩ የፋይናንስና ኢንቨስትምንት ዳይሬክተሩ ዶ/ር መሀሪ መኮንን እና የፋይናንስ ዋና ክፍል ሀላፊ አቶ ጌታቸው አጎናፍር በተደራጀ መልኩ የባንክ ስራን ሲሰሩ በመገኘታቸውና በታክስ ማጭበርበር በፍርድ ቤት ጥፋተኞች ተብለዋል።

ተከሳሾች ከቀረበባቸው ክሶች ውስጥ በ21ዱ ጥፋተኞች ሲባሉ፣ የዱቤ አገልግሎት በማከናወን፣ በዱቤ የተሸጡ ቤቶችን ካርታ በመያዝ በእነዚህም ካርታዎች ከባንክ ብድር በመበደር ወንጀል መከሰሳቸውን ፍርድ ቤቱ ገልጿል።

አክሲዮን ማህበሩ ከ1996 እስከ 2001 ባሉት አምስት አመታት ውስጥ 287 ሚሊዮን ብር ቢያንቀሳቅስም መክፈል የነበረበትን 8 ሚሊዮን ብር ታክስ አልከፈለም የሚል ክስ ቀርቦበታል።

 አንዳንድ ወገኖች መንግስት የተወሰኑ ብሄር ተወላጆችን ባለሀብቶች ሆን ብሎ እየመታ ነው በማለት እንደመከራከሪያ ከሚያቀርቡዋቸው ምክንያቶች አንዱ የአቶ አያሌው ተሰማ ጉዳይ ነው።

 ግለሰቡ እንደ ማንኛውም ሰው ተለቀው ጥፋት አለባቸው ከተባሉ እንኳ ስራአቸውን እየሰሩ እንዲከራከሩ ማድረግ ይቻል ነበር፣ በማለት ጉዳዩ ከታክስ ባለፈ ፖለቲካዊ ይዘት እንዳለው እነዚህ ወገኖች ይከራከራሉ።

 በቅርቡ በተመሳሳይ የታክስ ማጭበርብር ተከሰው 4 አመታት ተፈርዶባቸው የነበሩት የሜጋው ም/ል ስራ አስኪያጅ አቶ እቁባይ በርሄ ከአንድ ሳምንት የእስር ቤት ቆይታ በሁዋላ ከእስር እንዲለቀቁ መደረጉ ይታወሳል።

ፎቶ ጋዜጠኛ ቢንያም መንገሻ ተሰደደ


በተለያዩ ፎቶግራፎቹ ከፍተኛ እውቅና ያተረፈው ጋዜጠኛ ቢንያም መንገሻ አገሩን ጥሎ ለመሰደድ የተገደደው በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አገዛዝ አገሪቱን ሙሉ በሙሉ እያወደማት መሆኑን በመገንዘብ፣ የራሱን አስተዋጽኦ ለማድረግ ነው።

ጋዜጠኛ ቢንያም ከኢሳት ጋር ባደረገው ሰፊ ቃለምልልስ በስልጣን ላይ ያለው ሀይል ኢትዮጵያ በመኖርና ባለመኖር መካከል ከትቷታል።

በመንግስት የተበላሸ ፖሊሲ የተነሳ ኢትዮጵያ በፍጥነት ወደ ምደረ በዳነት እየተቀየረች መሆኑን በፎቶግራፍ በማስደገፍ ለኢሳት ገልጿል።

ፎቶ ጋዜጠኛ ቢንያም መንገሻ በሪፖርተር ጋዜጣ እና በአቢ ዊክሊ መጽሄት ሲሰራ ከቆየ በሁዋላ፣ ያራሱን ግላመር ፎቶ ስቱዲዮ በማቋቋም ፎቶ ኢግዢቢሺኖችን ማሳየቱን፣ በዚህም ስራው፣ የአገሪቱን መልካም ገጽታ አበላሽቷል በሚል በደህንነት ሀይሎች ሲዋከብ እንደነበር ገልጿል።

ከጋዜጠኛ ቢንያም መንገሻ ጋር የተደረገው ቃለምልልስ በቅርቡ ይቀርባል።
ሰሜንና ደቡብ ኮሪያ ተፋጠዋል

የውጭ አገር ባለሀብቶች በመንግስት ካድሬዎች ተማረናል አሉ


በኢትዮጵያ ውስጥ በኢንቨስትመንት ስራ ላይ የተሰማሩ የአውሮፓ እና አሜሪካ ባለሀብቶች ፣ በመንግስት ካድሬዎችና ሹመኞች በመማረራቸው ስራ ለመስራት በማይችሉበት ደረጃ ላይ መገኘታቸውን ገልጸዋል።

ባለሀብቶቹ ይህን የገለጹት የሁለት አመት ከስድስት ወራት የ እድገት እና ትራንስፎርሜሽንኑን እቅድ ለመገምገም በተጠራ ስብሰባ ላይ ነው።

ሪፖርተር እንደዘገበው ” የመንግሥት ካድሬዎችና የበታች ቢሮክራቶች በውጭ ኢንቨስተሮች መስተንግዶ ላይ የሚያደርሱት መጉላላት ከፍተኛ በመሆኑ ባለሀብቶቹ ኢንቨስት ከማድረግ እንዲታቀቡ እያደረጋቸው ነው።”

የመንግስት ባለስልጣናት ባለሀብቶች ያቀረቡት ቅሬታ ትክክል መሆኑን ለማመን መገደዳቸውን ጋዜጣው ዘግቧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ጋዜጣው በኢትዮጵያ ውስጥ በሁለቱም ሀይማኖቶች መካከል ለተፈጠረው መከፋፈል በውጭ አገር የሚገኙ ፖለቲከኞችን ተጠያቂ አድርጓል። ሪፖርተር ” በሚያሳዝንና በሚያሳፍር ሁኔታ በእስልምናና በክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ውስጥ መከፋፈል እየታየ ነው፡፡ መራራቅ እየተስተዋለ ነው፡፡ ክፍተት እየተፈጠረ ነው፡፡

 በተከፈተው ቀዳዳም ሌሎች ገብተው ለማባባስና እሳት ለማያያዝ ሲሞክሩ እየታየ ነው፡፡

 ሕዝብ እንደድሮው በመቻቻል፣ በፍቅርና በመግባባት መኖር ይፈልጋል፡፡

 ይህን የማይፈልጉ ቡድኖችና ግለሰቦች ይህን መልካም ጉዳይ ለማበላሸት እየጣሩ ናቸው፡፡

 ለግል ጥቅምና ለቡድን ጥቅም ሲባል የሕዝብና የአገር ጥቅም ለአደጋ እየተጋለጠ ነው፡፡

 ዋ! ” በማለት ከገለጠ በሁዋላ ፣ ” በሚያሳዝንና በሚያሳፍር ሁኔታ ውጭ አገር የሚገኙ የፖለቲካ ተቃዋሚ ነን ባዮች ዘላቂውን የአገር ጥቅም ከማሰብ ይልቅ ብጥብጡ ለሥልጣን መወጣጫና ኢሕአዴግን ለመጣል ያመቸናል በሚል፣ ጠባብና ከአፍንጫ የማይርቅ የዓይን እይታ በመያዝ አገርንና ሕዝብን የሚጎዳ ቅስቀሳና ያዙኝ ልቀቁኝ እያሰሙ ናቸው፡፡

 ለጊዜያዊ ጥቅም ተብሎ የአገርና የሕዝብን ጥቅም ለአደጋ የሚያጋልጥና ለጠላት መሣሪያነት የሚያገለግል እንቅስቃሴ ነው፡፡

søndag 10. mars 2013

በዲላ ከተማ እና በወልቂጤ የሚኖሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ አሰሙ



ከአንድ አመት በላይ የተካሄደው የድምጻችን ይሰማ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ፣ ዛሬ በአዲስ አበባና በሌሎች ዋና ዋና ከተሞች ረገብ ብሎ የዋለ ቢሆንም፣ በዲላ እና በወልቂጤ ተቃውሞ መደረጉን ማህበራዊ የመገናኛ ብዙሀን ገልጸዋል።

በፌስ ቡክ ላይ በፎቶግራፍ የተደገፉ መረጃዎች መረጃዎ እንዳማለከቱት፣ ሙስሊም ኢትዮጵያውያኑ መንግስት ድምጻቸውን እንደሰማ ጠይቀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በትናንት ሌሊት በደሴ ከተማ ከ30 ሺ በላይ በራሪ ወረቀቶች መበተናቸውን ማህበራዊ የመገናና ብዙሀን ዜናውን አሰራጭተዋል።

<< መንግሰት የደሴ ሙስሊሞችን ለማዳከም የተለያዩ ሴራዎችን ሲሰራ ቆይቷል>> የሚሉት የተቃውሞው አስተባባሪዎች፤ <<መስጂዶቻችንን በመቀማት እና ኢማሞቻችንን በማባረር ከመስጂድ እንድንርቅ አድርጎን ቆይቷል፤ በዚህም ሳቢያ በደሴ የነበረው እንቅስቃሴ በተወሰነ መልኩ ተቀዛቀዞ የነበረ ሲሆን ዝምታው ለሊት ተሰብሯል፡፡

>> ብለዋል አንዳንድ ሙስሊሞች በፌስቡክ ባሰራጩት መልእክት።

ወረቀቶቹ ፤በቧንቧ ውሀ፤በሮቢት፤ በአሬራ፤በሸዋበር፤በአራዳ፤በሳላይሽ፤በሰኞ ገበያ፤በአሬራ፤በሜጠሮ ፤በቢለን እና በሌሎች በርካታ የከተማዋ አውራ መንደሮች ነው የተበተኑት።

በወረቀቶቹ ከሰፈሩት መፈክሮች ውስጥ “ኢትዮጵያን እየበጠበጠ ያለው የእስልምና አክራሪነት ሳይሆን የፖለቲካ አክራሪነት ነው፤”ኢቲቪ የውሸት ኢንዱስትሪ ነው!በእምነታችን አንደራደርም! አሚሮቻችንን ማሰር እኛን ማሰር ነው!፤የእምነት መቻቻል እያደፈረሰ ያለው ሙስሊሙ ህብረተሰብ ሳይሆን መንግስት ነው” የሚሉት ይገኙበታል፡፡

በሌላ በኩል ሌሊት የተበተኑትን በራሪ ወረቀቶች ተከትሎ ፖሊሶች በተለያዩ ሰፈሮች ተበታትነው ሙስሊሞችን በማሰር ላይ እንደሚገኙ አስተባባሪ ኮሚቴው ገልጿል።

በዚሁ አሰሳ ከቄራ መስጂድ አካባቢ ቤት ተከራይተው ቁርዓን ይቀሩ የነበሩ 8 ደረሶች ታፍሰው መወሰዳቸው ተገልጿል።
ዛሬ በደሴ ስልተበተነው ወረቀት መንግስት የሰጠው መግለጫ የለም።

የሙስሊሞች ጥያቄ የኢህአዴግ አባላትን እና አመራሮችን እየከፋፈላቸው መምጣቱን መዘገባችን ይታወሳል።

የአማራ ክልል ባለስልጣናት ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ለተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች ” ምንም ማድረግ እንደማይችሉ ገለጹ



ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለው በአማራ ክለል ዋና ከተማ ባህርዳር የደረሱ የአማራ ተወላጆች የክልሉ ባለስልጣናት መፍትሄ እንዲሰጡዋቸው ቢጠይቁም ፣ ባለስልጣናቱ ጉዳዩ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ጉዳይ በመሆኑ እንደማያገባቸው መግለጻቸውን ተፈናቃዮች ለኢሳት ገልጸዋል።

ምንም መፍትሄ ያላገኙት ተፈናቃዮች፣ ሀብት ንብረታቸውን አስረክበው ለጎዳና ተዳዳሪነት መዳረጋቸውን ተናግረዋል።

በትናንትናው እለት ከ5 ሺ ያላነሱ የአማራ ተወላጆች ከቤንሻንጉል ጉሙዝ እንዲወጡ መደረጉን መዘገባችን ይታወሳል። ከሶስት ሳምንት በፊት ደግሞ በሶማሊ ክልል በጅጅጋና አጎራባች አካባቢዎች የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ንብረታቸውን እየተቀሙ ክልሉን እንዲለቁ መታዘዛቸውን ነዋሪዎችን በማናገር መዘገባችን ይታወሳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከደቡብ ክልላዊ መንግስት ቤንች ማጂ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ በመፈናቀል ላይ ያሉ ዜጎች ልጆቻቸውን በጉዲፈቻ የሚወስድላቸው አካል እንደሚፈልጉ ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ማስታወቃቸውን ጋዜጣው ዘግቧል፡፡

‹‹በአማርኛ ተናጋሪነታችን ሠርተን የመኖር ልጆቻችንን የማሳደግ ህልውና ያጣን ነን፡፡

›› የሚሉት እነዚህ ዜጎች “በተደጋጋሚ ጥቃት እየተሰነዘረብን ነው፤ ከ20 ዓመት በላይ ከኖርንበት መሬት ተፈናቅለናል፡፡ ከአውሬ ጋር እየታገልን ያለማነውን መሬት ተነጥቀናል፡፡ እነሱ የሚሉን እናንተ አማራ ስለሆናችሁ በዚህ ክልል መኖር አትችሉም፡፡

 ወደ ክልላችሁ ሂዱ ይሉናል፡፡ አማራ ክልልን እንኳን ሰርተን የምንበላበት መሬት ቀርቶ ጎጆ ቀልሰን የምንኖርበት ቦታ ሊሰጡን ፈቃደኛ አይደሉም፡፡” ሲሉ ቅሬታቸውን መግለጻቸውን ጋዜጣው ዘግቧል።


ተፈናቃዮቹም ‹‹በቀበሌና በወረዳ ደረጃ የሚፈጸሙብንን ወንጀሎች ለዞንና ለክልል ብናመለክት እኛን ወንጀለኛ አድርገው ጥፋተኞቹን ያበረታታሉ፡፡

 በፌዴራል ደረጃ ያሉ ባለስልጣናትም አንድም የሚሰጡት መፍትሄ የለም፡፡

 ከላይ እስከ ታች ያሉት በጠቅላላው የሚሰሩት ወንጀል ተመሳሳይ ነው፡፡

 ስለዚህ ከእንግዲህ መፍትሄ እናገኛለን ብለን አንጠብቅም፡፡›› ሲሉ ተስፋ መቁረጣቸውን ተናግረዋል።

ተፈናቃዮች “ቤት የሌለው መቆሚያና ማረፊያ የሌለው ሰው ቤተሰብ መስርቶ ልጅ ማሳደግ ንብረት ማፍራት አይችልም፡፡

 እኛ ከእንግዲህ እንደሆንን እንሆናለን፡፡ ልጆቻችን ግን ማደግ አለባቸው፡፡

 በማያውቁት ነገር ሊሰቃዩ አይገባም፡፡

 ስለዚህ የአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ አገር ጉዲፈቻ የሚያሳድጉ ድርጅቶች እንዲወስዱልን እንፈልጋለን፡፡

›› በማለት ተማጽነዋል።

ሟቹ ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ የነደፉት በዘር ላይ የተመሰረተ አስተዳደር አላማ ፣ የኢትዮጵያን የዘመናት አንድነት በመሸርሸር ለአገዛዙ እድሜ ለማራዘም መሆኑን ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች በተደጋጋሚ ሲናገሩ መቆየታቸው ይታወሳል።

አቶ መለስ በበኩላቸው ከደቡብ ክልል የተፈናቀሉት አርሶአደሮች በህገወጥ መንገድ ወደ ክልሉ ሄደው መሬት የወረሩ ናቸው በማለት ፖሊሲያቸውን ከትችት ለመከላከል መሞከራቸው ይታወቃል።

ምን እንኳ የዘር ፖለቲካው ዋና መሪ የነበሩት አቶ መለስ ከዚህ አለም ቢለዩም፣ የእርሳቸውን አገዛዝ የተከተለው የአቶ ሀይለማርያም መንግስት ተመሳሳይ ፖሊሲ እያስፈጸመ ይገኛል።

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ለሦስተኛ ጊዜ በሌላ ህትመት ወደ አንባብያን መመለሱን አስታወቀ



ተመስገን ይህን ያስታወቀው፤ <<ይህ ለአፈና እጅ የማይሰጥ የህዝብ ድምጽ ነው>> በሚል ርዕስ በፌስ ቡክ ገፁ ባሰፈረው ጽሁፍ ነው።

ቀደም ሲል ፍትህ ጋዜጣን፣ ከዚያም አዲስ ታይምስ መጽሔትን በ እግድ ምክንያት ያጣው ተመስገን ለሦስጠኛ ጊዜ በሌላ ህትመት መመለሱን ባስታወቀበት በዚሁ ጽሁፍ፤<<ለዜጎች ክብር የማይሰጠው ኢህአዴግ፣ ህዝብ በሚከፍለው ግብር መልሶ የሚያፍነው ኢህአዴግ፣ የሀይማኖት ተቋማትን ወደ ‹‹አጋር ፓርቲ››ነት እየቀየረ ያለው ኢህአዴግ፤ ፍትህ ጋዜጣን እና አዲስ ታይምስ መፅሄትን በጉልበት ከነጠቀን በኋላ፣ ለሶስተኛ ጊዜ በሌላ ጋዜጣ ተመልሰናል>>ብሏል።


አዲሷ ጋዜጣ ‹‹ልዕልና›› እንደምትባልና ከተመሰረተች ጊዜ ጀምሮ ለአንዴ ብቻ ታትማ ተቋርጣ እንደነበር የጠቀሰው ጋዜጠና ተመስገን፤ አሁን ግን የነበረባት የመንግስት ዕዳ ተከፍሎ፣ አሳታሚ ድርጅቱ በሀገሪቱ የአክሲዮን ሽያጭ ህግ መሰረት ወደ እኛ መዞሩን አበስራለሁ ብሏል።

እሱ የተሳተፈባት <<ልዕልና>>ጋዜጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ ቅዳሜ ለአንባቢያን እንደምትደርስም አስታውቋል።

<< ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ግን ‹‹አርብ አርብ ይሸበራል፤ …›› እንዲል ንጉስ ቴውድሮስ፣ ልዕልና ጋዜጣም የዕለት አርብ ድምፅ ሆና ትቀጥላለች፡፡>>ብሏል።

በአዲሷ ጋዜጣ ላይ ‹‹ከተዘጋው በር ጀርባ›› በሚል ርዕስ ላቀረበው ፅሁፍ መግቢያ የተጠቀመበትን መግቢያም እንደሚከተለው አስፍሮታል፦
በጽሁፉ መግቢያ፦<<…እነሆ በሶስተኛው በር ተገናኝተናልና አብዝቼ አላማርርም፡፡

 ባማርርስ የት እደርሳለሁ? ማነው አገዛዙንስ ከስሶ የረታ? ደግሞስ ከመቼ ወዲህ ነው በሀገሬ መሬት ላይ ህግ የበላይ ሆኖ የሚያውቀው? ለማንኛውም የጠፋው ብርሃን በዚህ መልኩ ዳግም ይፈነጥቅ ዘንድ ስለተከፈለው ዋጋ ወይም ውጣ ውረድ ገድል የመፃፍ ፍላጎት የለኝም፡፡

 ፍላጎቴ ከባልደረቦቼ ጋ በፀና መንፈስ በጀመርነው ጎዳና እንተምም ዘንድ ፤የመንግስትን አፈና አውግዛችሁ የሞራል ድጋፍ ለሰጣችሁን ኢትዮጵያውያን፤ እንዲሁም የአለም አቀፍ የፕሬስ ነፃነት ተሟጋች ተቋማት ላሳያችሁት አጋርነትና ተቆርቋሪነት፣ በሀገሬ ላይ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ይሰፍን ዘንድ ዋጋ በከፈሉና እየከፈሉ ባሉ ወንድምና እህቶቼ ስም ልባዊ ምስጋናዬን ማቅረብ ነው>>በመለት ነው ተመስገን የገለጸው።

በአፋር ክልል ነዋሪዎችን የማፈናቀሉ ዘመቻ ቀጥሎታል



ከክልሉ ያገኘነው መረጃ እንደሚያስረዳው ከሸንኮራ አገዳ ልማት ጋር በተያያዘ ተጠናክሮ የቀጠለው የህዝብ መፈናቀል ህብረተሰቡን ለከፋ ድህነት እየዳረገው ነው።

 የመንግስትን ትእዛዝ ለመቀበል ፈቃደኛ ያልሆኑ ሴቶች እስከ ልጆቻቸው መታሰራቸውን የክልሉ የመኢአድ ጠጠሪ የሆኑት አቶ አሊ ሚራህ ለኢሳት ገልጸዋል

ህዝቡ ጉዳዩን ገለልተኛ አካል መጥቶ እስከሚያየው ድረስ ከቦታችን አንነሳም ማለቱን አቶ አንፍሬ ተናግረዋል
በአፋር፣ በቦረና ዞን እና በዋልድባ አካካቢዎች ከስኳር ልማት ጋር በተያያዘ የሚታየውን የህዝብ መፈናቀል ስንዘግብ መቆየታችን ይታወሳል።

በሁሉም ክልሎች የአማራ ተወላጆች እንዲወጡ መደረጉ እጅግ አሳሳቢ ሆኗል ሲል መኢአድ ገለጸ



የመኢአድ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ወንድማገኝ ደነቀ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ” በሁሉም ክልሎች የሚገኙ የአማራ ተዋላጆች ወደ ክልላቸው እንዲመለሱ መታዘዙ፣ ችግሩን በእጅጉ ውስብስብ አድርጎታል።

በደቡብ ክልል በጉርዳ ፈርዳ ወረዳ የተጀመረው መፈናቀል ሳይቆም፣ በባሌ፣ በአፋርና በሶማሊ ክልሎች ተመሳሳይ መመሪያዎች እየተላለፉ መሆኑን የገለጡት ምክትል ሊቀመንበሩ ፣ ተፈናቃዮች ለሞት መዳረጋቸውን ገልጸዋል

አቶ ወንድማገኝ በአማራ ተወላጆች ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ የህወሀት የቆየ የዘር ፖሊሲ መሆኑን ገልዋል
” መኢአድ መግለጫ ከማውጣት ባለፈ ችግሩን ለማስቆም ምን የሚወስደው እርምጃ አለ ተብለው የተጠየቁት አቶ ወንድማገኝ፣
ችግሩ የሚቆመው መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሲተባበርና ድርጅቶችም በጋራ ሲቆሙ መሆኑን ገልጸው፣ የተቃውሞ ሰልፎችን ለማካሄድ እቅድ መኖሩንም ተናግረዋል

ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለው በአማራ ክለል ዋና ከተማ ባህርዳር የደረሱ የአማራ ተወላጆች የክልሉ ባለስልጣናት መፍትሄ እንዲሰጡዋቸው ቢጠይቁም ፣ ባለስልጣናቱ ጉዳዩ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ጉዳይ በመሆኑ እንደማያገባቸው መግለጻቸውን ተፈናቃዮች ለኢሳት መግለጻቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

onsdag 6. mars 2013

ወታደሮች በኦጋዴን የውሀ ጉድጋዶችን በመያዝ ህዝቡን እያሰቃዩት ነው ተባለ


የኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት ለኢሳት በላከው መግለጫ እንዳመለከተው ሰራዊቱ እና የሶማሊ ልዩ ምልሻ በጋራ ከየካቲት አጋማሽ ጀምሮ የውሀ ጉድጓዶችን ተቆጣጥረው ህዝቡን ገንዘብ በማስከፈል እያሰቃዩት ነው።

ድርጅቱ ለአለማቀፍ ድርጅቶች ባሰማው የድረሱልን ጥሪ ሰራዊቱ በአንድ ሰው እና በእንስሳ ቁጥር ልክ ገንዘብ እያስከፈለ ነው።

አንድ ቤተሰብ ወደ ውሀ በወሰዳቸው ግመሎች፣ ፍየሎችና በጎች ልክ ለውሀው እንደሚከፍል የገለጠው መግለጫው በአማካኝ አንድ ቤተሰብ እስከ 12 ሺ ብር በወር የመክፈል ግዴታ ጠጥሎበታል ሲል አስታውቋል።

ከፍተኛ ድርቅ በተስፋፋበት ኦጋዴን እንዲህ አይነት ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ መውሰድ በህዝቡ ላይ የሚፈጸም የዘር ማጥፋት እርምጃ በመሆኑ መንግስት ተጠያቂ መሆን እንዳለበት ድርጅቱ ገልጿል።

በተለይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአስቸኳይ ጣልቃ ገብቶ በህዝቡ ላይ እየደረሰ ያለውን ሰቆቃ እንዲታደግ ድርጅቱ ጥሪ አቅርቧል።

በጉዳዩ ዙሪያ የኢትዮጵያ መንግስት የሰጠው አስተያየት ለማግኘት ጥረት ብናደርግም አልተሳካልንም። የኦጋዴን አካካቢ አሁንም ከፍተኛ የጤር ቀጠና መሆኑ ይታወቃል።

ታዛቢዎች የቤተክህነቱ ” ጅሀዳዊ ሀረካት” ያሉት መጽሀፍ እየተሰራጨ ነው



በስደት የሚገኙነትን አራተኛው ፓትርያርክ ጨምሮ በውጪ አገር ያሉ አባቶችን ስሕተት፣ ጥፋትና ዕርቀ ሰላሙን ማፍረስ የሚያትት እንዲሁም ፓትርያርኩ ከሥልጣን የወረዱት ተገደው ሳይሆን በራሳቸው ፈቃድ መሆኑን የሚያትት ባለ 52 ገጽ አነስተኛ መጽሐፍ ታትሞ በመሰራጨት ላይ መሆኑን ደጀሰላም ዘግቧል።

ይኸው በአቡነ ማቲያስ ዕለተ ሲመት ጀምሮ መሰራጨት የጀመረው መጽሐፍ በብዙዎች አባባል የቤተ ክህነቱ “ጂሐዳዊ ሐረካት” የተሰኘ ሲሆን አዲስ ተሿሚው ፓትርያርክ ይቀጥላል ሲሉ ተስፋ ከሰጡት የዕርቅ ሒደት ተቃራኒ ሆኖ መገኘቱን ድረገጹ ዘግቧል።

በኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም “ዶኩመንታሪ” ፊልም እንዲሰራበት ኮሚሽን ተከፍሎበታል በሚባለው በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ዕርቁን በጉጉት ይጠብቅ የነበረውን ምእመን ለማሳመን ረብጣ ብር እየፈሰሰ እንደሚገኝም አጋልጧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ 13 አባላት ባሉት የፓትርያርክ አስመራጭ ኮሚቴ ውስጥ የምዕመናኑ ወኪል ተብለው ከተሰየሙ ሶስት አባቶች መካከል አንዱ፣ የካቲት 25 ቀን አቡነ ማትያስ ለመጀመሪያ ጊዜ በመሩት የቅዱስ ሲኖዶሱ ስብሰባ ላይ “ቅ/ሲኖዶሱ ያወጣውን ሕገ ደንብ መፈጸምና ማስፈጸም የማይችል ከኾነ ቤተ ክርስቲያን ለከፋ ፈተና እንደምትጋለጥ እሰጋለሁ።

አስመራጭ ኮሚቴውም የድካሙን ያህል ውጤት አስገኝቷል ብዬ አላምንም። ከዚህ ሁሉ የመራጮች እንግልትና የገንዘብ ወጭ ይልቅ ቅዱስ ሲኖዶሱ በዝግ ስብሰባ የሚሻለውንና ወቅቱን የዋጀውን አባት መርጦ ቢሠይም ደግና የዋህ በኾነው ምዕመናን ዘንድ ተቀባይነት ያገኛል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ” ማለታቸው ታውቋል።

በዚሁ ስብሰባ ላይ የአስመራጭ ኮሚቴውን ሪፖርት ለመስማት እንኳ ያልታገሡት የቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ‹‹ሲኖዶሱንና ሲኖዶሱን፤ ሲኖዶሱንና ቤተ ክርስቲያንን ማእከል አድርጎ ከግለሰብ እና ከሌሎች አካላት ጫና ነጻ ኾኖ መሥራት ካልተቻለ ችግሩ ይቀጥላል፤ የከፋም እንዳይኾን ሁላችንም የበኩላችንን ጥረት ማድረግና እንደ አባትም መጸለይ አለብን፤›› ብለው በመናገር ስብሰባውን አቋርጠው እንደወጡ ተሰምቷል።

የ6ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ የምርጫ መርሃ ግብር፣ ሙሉ ለሙሉ የስርዓቱ ጣልቃ ገብነት የተንፀባረቀበትና፣ መራጮችም ድምፃቸውን ለፈቀዱት አባት በነፃነት እንዳይሰጡ የተዋከቡበት እንደነበር መዘገቡ ይታወሳል።

በዚሁ የፓትርያርክ ምርጫ የተካፈሉ አንድ ከምዕራብ ጎጃም ሃገረ ስብከት የመጡ ድምፅ ሰጪ፣ በአዳራሹ ከነበረው የጀርመን ድምጽ ራድዪ ወኪል ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ “ምርጫው እገሌን ምረጡ ይሄን ምረጡ የሚባል አሰቃቂና በጣም አስቀያሚ ነገር አለው” በማለት የምርጫው ክንውን ከመነሻው ጀምሮ በፍፁም ነፃነት እንዳልተከናወነ ለመጠቆም ሞክረዋል።
 ዘገባውን ያጠናከረው የአውስትራሊያው ቅዱስ ሀብት በላቸው ነው።


ኢህአዴግ በርካታ የመረጃ ሰዎችን በሆቴል ቤት ሰራተኝነት ስም ቀጥሮ አሰማራ



በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ ሻሂ ቤቶች፣ ምግብ ቤቶችና ሆቴሎች ውስጥ የ ኢህአዴግ መንግስት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ወጣት ሴቶችን በማሰልጠን እና አንድ ለአምስት በመጠርነፍ መረጃ እንዲያቀርቡ እያሰማራ እንደሚገኝ ታውቋል።

 መንግስት ከሻሂ ቤቶችና ሆቴሎች ስራ አስኪያጆች ጋር በሚስጢር በመነጋገር ደሞዝ የሚከፍላቸውን አስተናጋጆች አሰማርቶ ከህዝቡ መረጃ እየሰበሰበ ነው።

ቀደም ሲል መንግስት ሰዎችን በማስረግ ብቻ የመረጃ ማሰባሰቡን ስራ ይሰራ እንደነበር ለዘጋቢያችን የገለጡ አንድ ስማቸው እንዳይነገር የፈለጉ የድርጅቱ ሰው፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በተጠናከረ ሁኔታ እራሱ ደሞዝ የሚከፍላቸውን ሰዎች በተመረጡ የመስተንግዶ ቤቶች መድቧል።

 ወጣት ሴቶች በትምህርት ደረጃቸው ዲፕሎማ ሳይቀር ያላቸው ሲሆን፣ ድርጅቱ ለረጅም ጊዜ በመረጃ አሰባሰብ ስራ በደህንነት ሰራተኞች እንዳሰለጠናቸውም ታውቋል።

የመረጃ ሰዎች የሰበሰቡትን መረጃ ለተወካያቸው የደህንነት ሰራተኞች በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ የሚገልጹ ሲሆን፣ መስሪያ ቤቱም መረጃዎችን በመተንተን ሊከሰቱ የሚችሉ ስጋቶችን አስቀድሞ ለመከላከል ይጠቀምበታል ።

ከመረጃ ሰዎች የሚሰበሰቡትን መረጃዎች በመንተራስ ስርአቱን ይጠላሉ ተብለው የሚጠረጠሩ ሰዎች ውሎአቸው እየታየ የተግባር ግሳጼ መስጠት መጀመሩ ታውቋል።

በተለይ ከተቃዋሚ ፖለቲከኞችና ከግል ጋዜጠኞች ጋር የሚገናኙ ሰዎች ከግሳጼው በሁዋላ ግንኙነታቸውን ከላቋረጡ፣ በገንዘብ ለመደለል፣ ንብረታቸው ሊወሰድባቸው እንደሚችል በማስፋራራት፣ በመንግስት ቤት ውስጥ የሚኖሩ ከሆነም ቤታቸውን እንደሚቀሙ በማስጠንቀቅ በፖለቲከኞችና በህዝብ መካከል ያለውን ግንኙነት ለመበጠስ እቅድ መያዙን ጉዳዩን ሲከታተለው የቆየው አዲስ አበባው ዘጋቢያችን ገልጿል።

ዘጋቢያችን ፒያሳ በሚገኝ አንድ ሻሂ ቤት ውስጥ በመሄድ ስላጋጠመው ገጠመኝ ሲገልጽ ” ከአንድ ባልንጀራየ ጋር ድምጼን ከፍ በማድረግ ስለወቅቱ ፖለቲካ እወያይ ነበር።

 አንዲት ወጣት መልከመልካም ቀይ ሴት የማስተናገዱን ስራ ትታ ጆሮዋን ወደ እኛ ቀስራ የምንናገረውን ለመስማት ትጥራለች ፤ ጉዳዩን ያልተረዳው የቅርብ ዘመዴ የሆነው የሻሂ ቤቱ ባለቤትና ስራ አስኪያጅ የሚያስተናግደን መስሎ በመምጣት፣ በለሆሳስ ‘የምታወሩትን አቁሙ ልጂቱ እኛ የቀጠርናት ሳይሆን መንግስት የቀጠራት አስተናጋጅ ነች አለን።

” ብሎአል።

የሆቴሉ ስራ አስኪያጅ አስተናጋጁዋ ከመንግስት በመጣ ትእዛዝ እንድትቀጠር መደረጉን፣ አብዛኛው ስራዋም ሰዎች የሚነጋገሩትን መቅዳት መሆኑን እና ድርጅቱ ምንም አይነት ደሞዝ እንደማይከፍላት ለዘጋቢአችን አረጋግጠውለታል።

 የስለላ ሰራተኞች በብዛት ይገኙባቸዋል ተብለው በተጠቆሙት ሆቴል ቤቶች በመዘዋወር ከአንዳንድ ስራ አስኪያጆች ጋር በመነጋገር መረጃውን ያረጋገጠው ዘጋቢያችን፣ አስተናጋጆቹ ሆቴሎች ደሞዝ ባይከፍሉዋቸውም ያለምንም ማንገራገር የተሰጣቸውን መስተንግዶ ስራ ይሰራሉ። የድርጅቶቹ ባለቤቶች ሰላይ አስተናጋጆች እነሱንም የሚሰልሉዋቸው ስለሚመስሉዋቸው ብዙ እንደማይናገሩዋቸው ለማወቅ ተችሎአል።

የደህንነት መስሪያ ቤት ቀጥሮ ካሰማራቸው ሴት አስተናጋጆች በተጨማሪ በኮሚኒኬሽንና ጆርናሊዝም ትምህርት የተመረቁ በርካታ ተማሪዎችን በአሁኑ ጊዜ በአዋሳ የደህንነት ጽህፈት ቤት መረጃ ስለመሰብሰብ፣ መረጃ ስለማስተላለፍ እና መረጃ ስለመተንተን ስልጣና እየተሰጠ ነው።

በኢትዮጵያ የሚታየው አፈና እየጨመረ መምጣት በተለይም የሙስሊሞ እንቅስቃሴ መጠናከር እና ተቃዋሚዎች ይህን እንቅስቃሴ ለራሳቸው ግብ ሊጠቀሙበት ይችላል የሚለው ስጋት እያየለ መሄድ መንግስት በርካታ የደህንነት ሰራተኞችን አሰልጥኖ ለማሰማራት መገደዱ ይገመታል።

የደህንነት ክትትሉ ቢጨምርም፣ ህዝቡ ግን አሁንም ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ስሜቱን ከመግለጽ ወደ ሁዋላ አይልም።

በቅርቡ በአዳማ ከተማ ይፋ የሆነ አንድ የኢህአዴግ ሪፖርት እንዳመለከተው የአንድ ለአምስት አደረጃጀት የታሰበውን ያክል ውጤት ሊያስገኝ አልቻለም።

 በብዙ መስሪያ ቤቶች እና ቀበሌዎች ተግባራዊ የተደረገው የአንድ ለአምስት አደረጃጀት ባለመሳካቱ ኢህአዴግ ሌሎች የመረጃ ማሰባሰብ ዘዴዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ግድ ብሎታል።

tirsdag 5. mars 2013

በጀርመን የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ


እ.ኤ.አ. በማርች 01 ቀን 2013 ዓ.ም. በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ በጠራው የተቃውሞ ሠልፍ ላይ ከተለያዩ የጀርመን ከተሞች የተሰባሰቡ ቁጥራቸው ከ400 በላይ የሆኑ ኢትዮጵያውያን፣ትውልደ-ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የተገኙ ሲሆን ፣ በተለያዩ መፈክሮችና የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ በማሸብረቅ ጉዞውን ወደ ኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት አድርጓል።

”የህሊና እስረኞች ይፈቱ!” ፣”የፕሬስ ነጻነት ይከበር!” ”ሃሳብን በነጻነት የመግለፅ መብት ይከበር!” ”ጅሃዳዊ ሐረካት የወያኔ ፈጠራ ነው!” ”የሃይማኖት ነፃነት ይከበር!” ”በአለም ዙሪያ ያሉ የወያኔ ቆንስላ ፅ/ቤቶች የኢትዮጵያን ህዝብ አይወክሉም!” ”የአውሮፓ ህብረት ለአፋኙ የወያኔ አገዛዝ የሚያደርገውን የገንዘብ ድጋፍ ያቁም!” ”ከአባይ በፊት ሙስናና ዘረኝነት ይገደብ!” የሚሉ መፈክሮች በሰፊው የተደመጡ ሲሆን ከአንድ ሰዓት ተኩል የእግር ጉዞ በኋላ ተሰላፊው ቆንስላው ጽ/ቤት ፊት ለፊት ሲደርስ በከፍተኛ ጩኸት እና ፉጨት ተቃውሞውን ማሰማት ችሏል።

በመጨረሻም የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ተወካይ፣የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች እና የሙስሊሙ ማህበረሰብ ተወካዮች በአካል ተገኝተው አጠር ያለ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎም ከኔዘርላንድ የላከው ደብዳቤ መነበቡን ኢንጂነር ዳዊት ፋንታ የላከው ዘገባ ያመለክታል።

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አርቲስት ታማኝ በየነ የመራው የኢሳት የአውሮፓ የገቢ ማሰባሰብ ዝግጅት ተጠናቀቀ



ላለፉት አራት ሳምንታት በአውሮፓ ከተሞች በመዘዋወር ስለ ሰብአዊ መብቶች ቀላል፣ ግልጽ እና አስተማሪ በሆነ መንገድ እያቀረበ ለኢሳትም የድጋፍ ማሰባሰብ ስራ የሰራው እውቁ አርቲስት ታማኝ በየነ የአውሮፓ ጉዞውን ቅዳሜ ማርች 2፣ 2013 በጀርመንዋ የፍራንክፈርት ከተማ በደመቀ ዝግጅትና ስነስርአት አጠናቋል።


አርቲስት ታማኝ ጉዞውን በጄኔቫ ስዊዝርላንድ ጀምሮ በ ስዊድን ስቶክሆልም፣ በ ኖርዌይ ኦስሎ ፣በ ጀርመን ሚዩኒክ ፣ በኔዘርላንድስ አምስተርዳም ፣ በ እንግሊዝ ለንደን ፣ በ ቤልጂየም ብራሰልስ ቆይታ ካደረገ በሁዋላ በ ጀርመን ፍራንክፈርት አጠናቋል።


አርቲስት ታማኝ በአውሮፓ ቆይታው ከኢትዮጵያውያን ባሻገር ከአውሮፓ የፓርላማ አባል ከተከበሩ ሚስ አና ማሪያ ጎሜዝ ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ውይይት አድርጓል። እንዲሁም በኖርዌይ አገር ለሚታተም ጋዜጣ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ቃለምልልስ ሰጥቷል።


በፍራንክፈርቱ ዝግጅት በርካታ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት የመዝጊያ ስነስርአቱ በደመቀ ሁኔታ ተጠናቋል።


በፍራንክፈርት የነበረውን ዝግጅት በተመለከተ ከዜናው በሁዋላ ተጨማሪ ዘገባ ይቀርባል።

የሰብዓዊ መብት ሊጉ የዩኒቨርሲቲው ውሳኔ ፖለቲካዊና ዘረኝነት ላይ ያነጣጠረ ነው አለ።



የምሥራቅ አፍሪቃ የሰብዓዊ መብት ሊግ በቅርቡ በ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል የተፈጠረን ግጭት ተከትሎ 10 የኦሮሞ ተወላጆች ከትምህርታቸው እንዲታገዱ መደረጋቸውን አጥብቆ አወገዘ።

የሰብዓዊ መብት ሊጉ ከትምርታቸው የታገዱትን ተማሪዎች ፎቶ አስደግፎ ባወጣው መግለጫ ተማሪዎቹ ከትምህርት ገበታቸው የታገዱት የመጀመሪያ ሴሚስተር ፈተናቸውን አጠናቅቀው የሁለት ሳምንት እረፍት ወስደው ከተመለሱ በሁዋላ ነው።

ሊጉ ከውስጥ የደረሱትን መረጃዎች ዋቢ አድርጎ እንደገለጸው ይህ በግልጽ ፖለቲካዊ የሆነውና ዘረኝነት ላይ ያነጣጠረው ውሳኔ የተላለፈው <<ዲሲፕሊን ኮሚቴ>>ተብሎ በሚጠራው የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር አካል ሲሆን፤ኮሚቴው ለዚህ ውሳኔ ምክንያት የሆነውም ባለፈው ጥር ወር በኦሮሞና በትግራይ ተወላጅ ተማሪዎች መካከል የተፈጠረው ግጭት ነው።

በሁለቱ ብሔረሰብ ተወላጆች መካከል ግጭቱ ሊፈጠር ቻለውም ጥቂት የትግራይ ተወላጅ የ ኦሮሞ ብሄረሰብን አስመልክቶ ተገቢ ያልሆነና ቆስቋሽ ጽሁፍ ጽፈው በመለጠፋቸው ምክንያት እንደሆነ ማረጋገጡን ሊጉ አውስቷል።

ይህን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ በግጭቱ ሳቢያ ከ10 በሚበልጡ ተማሪዎች ላይ የ እስራት፣የግርፋትና የድብደባ እርምጃ መወሰዱን፤ ከታሰሩት መካከል ብዙዎቹ የ ኦሮሞ ተወላጆች እንደሆኑ ይፋ ማድረጉንም ሊጉ አስታውሷል።

በግጭቱ ምክንያት ከትምህርታቸው እንዲታገዱ የተደረጉት አስሩም ተማሪዎች ኦሮሞዎች መሆናቸውን እና ከመካከላቸው አንዷ ሴት መሆኗን ያመለከተው ሊጉ፤ሁሉም ለ አንድ ወር ያህል ታስረው በዋስ ከተለቀቁ በሁዋላ ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመልሰው እንደነበር ጠቅሷል።

ከትምህርታቸው የታገዱት የኦሮሞ ተማሪዎች ከወለጋ ነቀምት የመጣው የ 3ኛ ዓመት ተማሪ ታደለ ታረቀኝ፣ ከደቡብ ሸዋ ኦሮሚያ የመጣው የ3ኛ ዓመት ተማሪ አበጀ ቱጂ ጫላ፣የ 4ኛ ዓመቱ ተማሪ ገመቹ ደለቶ ዳፎ፣የ 4ኛ ዓመት ተማሪ መልካሙ ሙሉጌታ፣የ 3ኛ ዓመት ተማሪ ፈቃዱ መሰራ፣ የ4ኛ ዓመቷ ሴት ተማሪ አዲስ ጋቴራ ያደሳ፣የ 4ኛ ዓመቱ ተማሪ በቃሉ ስዩም ተሻለ፣የ3ኛ ዓመቱ ተማሪ ቀጀላ አድማሱ ደሬሳ፣የ 2ኛ ኣመት ተማሪው ኢሳያስ ኢታና እና የ 4ኛ ዓመት ተማሪው አራርሳ ዋቅቶላ ኦልጅራ ናቸው።

ግጭቱን ከቀሰቀሱትም ሆነ በግጭቱ ከተሳተፉት የትግራይ ተወላጆች አንድም ተማሪ ላይ እርምጃ አለመወሰ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ተብየው ውሳኔ በግልጽ ፖለቲካዊና ዘር ላይ ያነጣጠረ መሆኑን እንደሚያሳይ የሰብዓዊ መብት ሊጉ አመልክቷል።

ይህ ውሳኔ ከሰብዓዊ መብት ሊጉ ባሻገር ብዙዎችን ያስገረመ እና ጥቂት በማይባሉም ታዛቢዎች ዘንድ፦<<በ እርግጥም ይህች አገር የማናት?>>የሚልን ጥያቄ ያጫረ ሆኗል።

33 የአዳማ ፔትሽን ፈራሚ ፓርቲዎች የመግባቢያ ሰነድ ፈረሙ



ፓርቲዎቹ የመግባቢያ ሰነዱን የፈረሙት ባለፈው ቅዳሜ ነው። በፊርማ ስነስርአቱ ላይ የፓርቲዎቹ ጥምረት ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አስራት ጣሴ ” የተፈረመው ሰነድ የመጀመሪያ የመግባቢያ ሰነድ መሆኑን ገልጠው፣ የኢህአዴግ የ21 አመታት አብዮታዊ ዲሞክራሲ ኢትዮጵያን ለረሀብ፣ ለድህነት፣ ለስደት፣ ለሰብዓዊ መብቶች ጥሰት፣ ለኢፍትሀዊነት፣ ለሙስና ዳርጓታል ብለዋል።

የአዲሱ ስብስብ ሰብሳቢ አቶ ግርማ በቀለ በበኩላቸው በዚህ ታሪካዊ የአድዋ ቀን ይህን የመጀመሪያ ደረጃ መግባቢያ ሰነድ በመፈራረማችን ደስታ ይሰማናል ፣ የፓርቲዎቹ የጋራ ጉዞ ይቀጥላል ብለዋል።

ፓርቲዎቹ ” ገዢዎቻችን ከሰጡን የአስተሳሰብ አድማስና የትግል ድንበር ወሰን ተሻግረን ልዩነቶቻችችንን በአወንታዊ ጎኑ በመጠቀም፣ አገራችንን ህዝባችን በማስቀደም ሁላችንም በእኩል ተጠቃሚ የሚያደርግ ስርአት ለመመስረት በትብብር ቆመን የሰው፣ ሙያ፣ እውቀትና ልምድ፣ ማቴሪያልና ፋይናንስ በማሰባሰብ ህገመንግስታዊ መብታችንን ሰላማዊ የትግል ስልቶችን ተግባራዊ በማድረግ ህዝባዊ ንቅናቄ በመፍጠር በጋራ እንሰራለን” ሲሉ በሰነዱ ላይ አስፍረዋል።

33ቱ ፓርቲዎች < መንግስት በሚወስዳቸው የሀገር እና የህዝብ ዘላቂ ጥቅሞችን በሚጎዱ እርምጃዎች ላይ ተወያይቶ የጋራ አቋም ለመያዝ፣ ገዢው ፓርቲ ህገወጥ እርምጃ በሚወስደበት ጊዜ ሁሉም ፓርቲዎች እርምጃውን እንዲቃወሙ፣ ምርጫውን በተመለከተ የጋራ ስልት መቀየስ፣ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት ተግቶ መስራት፣ በጋራ የፋይናንስ ድጋፍ ማሰባሰብ፣ በተቃዋሚዎች ላይ የሚሰነዘሩ የማጥላላት፣ የማንኳሰስና የመከፋፈል አፍራሽ እንቅስቃሴ በጋራ ማውገዝ” የሚሉትን በጋራ ለማከናወን ተስማምተዋል።

33ቱ ፓርቲዎች አብረው ለመስራት ስምምነት ላይ የደረሱት፣ በ2005 የሚደረገውን የአዲስ አበባና አካባቢ እንዲሁም የወረዳዎች ምርጫ አፈጻጸም ከተቃወሙ በሁዋላ ነው።

søndag 3. mars 2013

ጉምሩክና ግብር ከፋዮች እየተወዛገቡ ነው



የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ከ1994 ዓ.ም ጀምሮ በተከማቸ የአክስዮን ድርሻ ላይ 10 በመቶ ክፍያ እንዲፈጸም ያወጣው መመሪያ አሁንም ከከፍተኛ ግብር ከፋዮቹ ጋር እያወዛገበው ይገኛል፡፡

በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 መሰረት አክስዮን ማኀበራት ወይም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር ካከፋፈሉት የአክስዮን የትርፍ ድርሻ 10 በመቶ እንዲከፍሉ የሚያስገድድ ቢሆንም ላለፉት ዓመታት በህግ አስፈጻሚው ችግር አዋጁ ተግባራዊ ሳይሆን ቆይቷል፡፡

የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን አዋጁ ከወጣ ከ10 ዓመታት በኋላ በያዝነው ዓመት መጀመሪያ የአፈጻጸም መመሪያ በማውጣት ወደኋላ ሄዶ ውዝፍ ዕዳ ከነቅጣቱ እና ወለዱ ለመሰብሰብ መነሳቱ ከፍተኛ ግብር ከፋዮችን አስቆጥቷል፡፡

ከፍተኛ ግብር ከፋዮቹ ባለስልጣኑ በራሱ ችግር መሰብሰብ ያልቻለውን ግብር ከ10 ዓመታት በኋላ ወደኋላ ሄዶ ለመጠየቅ የህግም የሞራልም ድጋፍ የለውም በሚል ተቃውሞአቸውን በተደጋጋሚ ቢያሰሙም ጨርሶ መግባባት አልቻሉም፡፡

ነጋዴዎቹ ግብር አለመከፈሉ ጥፋት እንኳን ተደርጎ ቢወሰድ በይርጋ ይታገዳል የሚል መከራከሪያ አቅርበዋል፡፡

 በተጨማሪም ባለሰልጣኑ በራሱ ድክመት ያልሰበሰበውን ግብር ድንገት ተነስቶ እኛን ባለዕዳ ከማድረግ
ባለፈ ቅጣትና ወለድ ከፋይ ለማድረግ መነሳቱ አሳዛኝ ነው ብለውታል፡፡

በነጋዴዎች ተቃውሞ ጫና የበዛበት የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ካለፉት ሳምንታት ጀምሮ ግብሩን ወደኋላ ሄዶ መጠየቁ እንደተጠበቀ ሆኖ ከግብር አለመከፈሉ ጋር ተያይዞ የጠየቀውን ቅጣትና ወለድ ለማንሳት ተገዶአል፡፡

በተጨማሪም የተጠየቀውን ፍሬግብር ክፍያ በረዥም ጊዜ እንዲከፈል መወሰኑን ለነጋዴዎቹ ይፋ አድርጓል፡፡

ይህም ሆኖ አሁንም በርካታ ግብር ከፋዮች አስቀድመን ባከፋፈልነው የአክስዮን ድርሻ እና መልሰን ለኢንቨስትመንት ያዋልነውን ገንዘብ አሁን ወደኋላ ተመልሰን ከየት አምጥተን ግብር እንከፍላለን በሚል በተቃውሞአቸው ቀጥለዋል፡፡

ባለስልጣኑ በየኣመቱ ከሚሰበስበው ግብር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ድርሻ እስከ 80 በመቶ ይደርሳል፡፡

በኢትዮጵያ “የጥበብን ስራ እንኳ በነጻነት ማካሄድ አይቻልም” ሲሉ አንድ የጀርመን ፋውንዴሽን ዳይሬክተር ተናገሩ



ከኢትዮጵያ ለቅቆ የወጣው የጀርመን ሄንሪክ ቦል ፋውንዴሽን የኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ፓትሪክ በርግ ድርጅታቸው ከኢትዮጵያ ስለለቀቀበት ምክንያት ለብሉበርጉ ዊሊያምስ ዳቪሰን ሲናገሩ “በኢትዮጵያ የጥበብ ስራ እንኳን በአሁኑ ጊዜ በጥርጣሬ የሚታይ ነው፣ ከመብት ጋር የተያያዘውን ስራችሁን አቁሙ በመባላችን ስራችንን ለቀን ወጥተናል” ብለዋል።

የሲቪክ ሶሳይቲና ቻርቲ ህግ የሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ውርስ መሆኑን የገለጠው ብሉምበርግ፣ ህጉ ከመንግስት የተለየ ሃሳብ ያላቸውን ተቃዋሚዎች እና ድርጅቶች ለመቆጣጠር የወጣ መሆኑን አምነስቲ ኢንተርናሽናልን በመጥቀስ ዘግቧል።

የሂውማን ራይትስ ወች የአፍሪካ ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል በቀለ ፣ መንግስት ያወጣው የሲቪክ ሶሳይቲና ቻሪቲ ህግ የአለማቀፍ ማህበረሰቡን ለማግለል ታስቦ የተረቀቀ አለመሆኑን ገልጸው ፣ ዋና ግቡ በአገር ውስጥ ካለው ፖለቲካ እና ሲቪክ ሶሳይቲ ስራ ጋር የተያያዘ ነው ብለዋል።

“ህጉ ለ1997 ምርጫ መልስ ነው። ለመራጮች የተሰጠው ትምህርት ከፍተኛ መራጮች እንዲገኙ ማድረጉ፣ ሲቪክ ሶሳይቲው ምርጫውን መታዘቡና ልዩነቶችን መሸምገሉ፣ በመንግስት በኩል ሲቪክ ሶሳይቲው የፖለቲካ ስራ እየሰራ ነው የሚል መልእክት ማስተላለፉን” ገልጸዋል።

የመንግስት ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ፣ ህጉ በሙስና የተዘፈቁ የሲቪክ ድርጅቶችን ለመቆጣጠር ተብሎ የተረቀቀ መሆኑን በመግለጽ፣ የመንግስትን አቋም አንጸባርቀዋል።

በፓትርያርኩ ምርጫ መንግስት ሙሉ በሙሉ እጁን አስግብቶ ነበር ተባለ



የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ 6ኛ ፓትርያርክ ምርጫ ጋር በተያያዘ መንግስት እጁን ሙሉ በሙሉ አስገብቶ እንደነበርና ምርጫው ነጻ፣አሳታፊና ገለልተኛነት በሆነ መልኩ እንዳልተካሄደ ምንጮቻችን ጠቆሙ፡፡

የቀድሞ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ በሕይወት ከነበሩበት ጊዜ ጀምሮ ለሶስት ዓመታት ያህል በውጪ አገር ካለው ስደተኛው ሲኖዶስ ጋር ሰላም ለመፍጠር ቀጥሎ የነበረው ጥረት እንዲከሽፍና የፓትርያርክ ምርጫው በተፋጠነ ሁኔታ እንዲካሄድ እንዲሁም መንግስት የሚፈልጋቸው ፓትርያርክ እንዲመረጡ በቀጥታና በተዘዋዋሪ በቤተክርስትያናቱ መሪዎች
ላይ የመንግስት አካላት ግልጽ ተጽዕኖ ሲያሳርፉ ቆይተዋል፡፡

በመንግስት በየትኛውም መዋቅር ውስጥ የለሁበትም የሚሉትና ድንገት እየተነሱ ያሻቸውን የሚናገሩት አቦይ ስብሃትን ጨምሮ ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ቤክርስትያኒቱን አባቶች በማንጓጠጥና በማዋረድ ሥራ ሆን ብለው በተከታታይ ያከናወኑ ሲሆን የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር እና የመንግስት የደህንነት ኃይሎች አባቶችን እግር በእግር በመከታተል፣የስልክ ግንኙነታቸውን በመጥለፍ፣በማስፈራራት ሒደቱ በሚፈልጉት መልክ እንዲሆን ሰፊ ሚና ተጫውተዋል፡፡

ከ53ቱ አገረ ስብከቶች ለመራጭነት የታጩ ሰዎችን ለአቡነ ማቲያስ ድምጽ እንዲሰጡ እስከማግባባት የዘለቀ ሥራ በይፋ ማከናወናቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችንን አመልክተዋል፡፡

የመንግስት ኃሎች ከሕገመንግስቱ ድንጋጌ በተቃራኒ በሃይማኖት የውስጥ ጉዳይ ሊገቡ የፈለጉት ገዥው ፓርቲ ሁሉንም ነገር ለመቆጣጠር ካለው ከፍተኛ ፍላጎት ጋር የተገናኘ ሳይሆን አይቀርም።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 6ኛውን ፓትርያርክ ለመምረጥ ከትላንት ጠዋት ጀምሮ 806 መራጮች ድምጽ የሰጡ ሲሆን ከሰዓት በኋላ በተደረገው ድምጽ ቆጠራ ብፁዕ አቡነ ማትያስ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ በ500 ድምጽ የመጀመሪያውን ድምጽ በማግኘት 6ኛው ፓትርያርክ ሆነው ተመርጠዋል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ኢህአዴግ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት አጥብቀው በመቃወም የሚታወቁት አባ አምሀ እየሱስ የፓትርያርኩ ምርጫ ” የመንግስት ምርጫ እንጅ የምእመናን ምርጫ አይደለም” ብለዋል

lørdag 2. mars 2013

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቃዉሞ

ዛሬ ከጁመዓ ሶላት በኋላ በየመሳጂዱና በየአካባቢዉ የተሰበሰበዉ ምዕመን የመንግሥት ታጣቂዎች ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ የሙስሊሞችን ቤት በሌሊት መበርበራቸዉን እና ሐብት፥ ንብረታቸዉን ዘርፈዋል በመባሉንም አዉግዟል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ሙስሊሞችን ማዋከብ፥ መበደሉንና በሐይማኖታዊ ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን እንዲያቆም በተለያዩ የሐገሪቱ ከተሞች የሚኖሩ ሙስሊሞች ዛሬም በድጋሚ ጠየቁ።ዛሬ ከጁመዓ ሶላት በኋላ በየመሳጂዱና በየአካባቢዉ የተሰበሰበዉ ምዕመን የመንግሥት ታጣቂዎች ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ የሙስሊሞችን ቤት በሌሊት መበርበራቸዉን እና ሐብት፥ ንብረታቸዉን ዘርፈዋል በመባሉንም አዉግዟል

ሰው ሊኖር ሰው ሞቷል

ሰው ሊኖር ሰው ሞቷል»ያኔ
ይኸው በእኛ ዘመን ዛሬ 117ኛው የአድዋ ድል በዓል የሚከበርበት እለት ሆኖ ተጽፏል፡፡ ታሪክ ለማውራት እንጂ ለመስራት ያልታደልን ዘመነኞች፡፡ያኔ ያኔ ነጻነታችን ሊጋፋ፣ ክብራችንን ሊገፍ፣ የመጣው ባዕድ ነበርና እናት አባቶቻችን ለእኛ ለልጆቻቸው ባርነትን ላማውረስ ሲሉ፣ ስለነጻነታችን ሲሉ፣ ጠላትን ተጋፈጡልን፣ ህይወታቸውን ከፈሉልን፡፡የእኔ የምንግዜም ምርጥ ተቀኚ እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) እነርሱን በአመሰገነችበት «አድዋ» ሙዚቃዋ እንደተቀኘችውም ያኔ «ሰው ሊኖር ሰው ሞቷል» አሁንስ?
እንዲህም አስባለሁ፡፡ አሁን እኚያ የሞቱልን የቀደሙቱ ወገኖቻችን እንደው ለአንድ አፍታ ከመቃብራቸው ወጥተው «እኛ የሞትንላት ኢትዮጵያን የት አለች? ያወረስናችሁ ነጻነትስ ወዴት አለ? ልጆቻችን ሆይ!!የኢትዮጵያዊነት ከፍታ ከምን ደረሰ ? የእናንተ ዘመን መዘመን ምን በጃችሁ? ጠግባችሁ ማደርስ ቻላችሁ?» ብለው ቢጠይቁንስ ምን ብለን እንመልስ ይሆን? እኔስ በኩራትና በድፍረት የምመልሰው ነገር የለኝም ፡፡የእነርሱን የመስዋዕትነትና የድል ታሪክ ግን ለእኔም ዘመን እመኘዋለሁ፡፡ሁሌም አንዲት ኢትዮጵያ!!!
«ሰው ሊኖር ሰው ሞቷል»ያኔ
ይኸው በእኛ ዘመን ዛሬ 117ኛው የአድዋ ድል በዓል የሚከበርበት እለት ሆኖ ተጽፏል፡፡ ታሪክ ለማውራት እንጂ ለመስራት ያልታደልን ዘመነኞች፡፡ያኔ ያኔ  ነጻነታችን ሊጋፋ፣ ክብራችንን ሊገፍ፣ የመጣው ባዕድ ነበርና እናት አባቶቻችን ለእኛ ለልጆቻቸው ባርነትን ላማውረስ ሲሉ፣ ስለነጻነታችን ሲሉ፣ ጠላትን ተጋፈጡልን፣ ህይወታቸውን ከፈሉልን፡፡የእኔ የምንግዜም ምርጥ ተቀኚ እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) እነርሱን በአመሰገነችበት «አድዋ» ሙዚቃዋ እንደተቀኘችውም ያኔ «ሰው ሊኖር ሰው ሞቷል» አሁንስ? 
 እንዲህም አስባለሁ፡፡ አሁን እኚያ  የሞቱልን የቀደሙቱ ወገኖቻችን እንደው ለአንድ አፍታ ከመቃብራቸው ወጥተው «እኛ የሞትንላት ኢትዮጵያን የት አለች? ያወረስናችሁ ነጻነትስ ወዴት አለ? ልጆቻችን ሆይ!!የኢትዮጵያዊነት ከፍታ ከምን ደረሰ ? የእናንተ ዘመን መዘመን ምን በጃችሁ? ጠግባችሁ ማደርስ ቻላችሁ?» ብለው ቢጠይቁንስ ምን ብለን እንመልስ ይሆን? እኔስ በኩራትና በድፍረት የምመልሰው ነገር የለኝም ፡፡የእነርሱን የመስዋዕትነትና የድል ታሪክ ግን ለእኔም ዘመን እመኘዋለሁ፡፡ሁሌም አንዲት ኢትዮጵያ!!!

fredag 1. mars 2013

የኩማ አስተዳደር ህዝቡን ማፈናቀሉን በዘመቻ መልክ ጀመረ


ከስልጣኑ ለመልቀቅ የሁለት ወራት ጊዜያት የቀሩት የኩማ አስተዳደር“ፈጣን ለውጥ አምጪ” በሚለው ፕሮግራሙ በተለያዩ አካባቢዎች በልማት ስም የአዲስአበባን ነዋሪ የማፈናቀል ስራውን በዘመቻ መልክ እያከናወነ መሆኑ ተጠቆመ፡፡

ከባቡር፣ከመንገድ እና በኢንቨስትመንት ስም በተለይ በቦሌ፣በቂርቆስ፣በልደታ፣በኮልፌ ቀራኒዮ፣በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተሞች ካለፉት ሁለት ሳምንት ወዲህ ዜጎችን ከሕግና ስርዓት ውጪ የማፈናቀሉን ሥራ ተፋፍሞ መቀጠሉን ከየአካባቢው ያገኘናቸው መረጃዎች እየጠቆሙ ነው፡፡

ከባቡር መስመር ዝርጋታ ጋር በተያያዘ በ22 አካባቢ በአምስት ቀናት ጊዜያት ውስጥ ንብረታቸውን እንዲያነሱ ዜጎች በመገደድ ላይ ናቸው፡፡ በአካባቢው የሚገኙ የግል ይዞታ ባለንብረቶች ሕጉ በሚፈቅደው መሰረት ተገቢውን ካሳ በወቅቱ ያልተከፈላቸው ሲሆን የካሳው ጉዳይ በተመለከተ ውጪ ሆናችሁ ተከታተሉ የሚል ምላሽ በመስጠት ሜዳ ላይ እንዲወድቁ መደረጉ እንዳሳዘናቸው አንድ የችግሩ ሰለባ ለኢሳት ዘጋቢ ነግረውታል፡፡

በኡራኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ የኮንስትራክሽን የፋብሪካ ውጤቶችን በማከፋፈልና በመቸርቸር የንግድ ስራ የተሰማሩና ወደአንድ ሺ የሚጠጋ ጊዜያዊና ቋሚ ሰራተኞች ያሏቸው ነጋዴዎችም በተመሳሳይ መልክ በአምስት ቀናት ጊዜ ውስጥ እንዲለቁ መገደዳቸውን ጠቅሰው በሕግና በስርዓቱ ቢሆን ቢያንስ የ90 ቀናት ማስጠንቀቂያ ሊሰጣቸው ይገባ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

የኡራኤል አካባቢ ከሊዝ ነጻ በምደባ ለአንድ የእምነት ተቋም ተሰጥቷል የተባለው በ1998 ዓ.ም እንደነበር ነጋዴዎቹ አስታውሰው በቦታው ላይ ያለን ነጋዴዎች በሕጉ መሰረት የማልማት ቅድሚያ እንዲሰጠን ጥያቄ ብናቀርብም ሰሚ ማግኘት አልቻልንም ብለዋል፡፡

በአካባቢው የሚገኙ የተወሰኑ የመንግስት ቤቶች መኖራቸውን እና የኪራይ ውል እስከ2006ዓ.ም የታደሰ እንዳላቸው ነጋዴዎቹ አስታውሰው ቀድሞ የኪራይ ውሉ ሳይቋረጥ ምንም ዓነት ማስጠንቀቂያ ሳይደርሳቸው በድንገት በአምስት ቀናት ልቀቁ መባላቸው አሳዛኝ እንደሆነባቸው ተናግረዋል፡፡

የኩማ አስተዳደር የሊዝ ቦርድ በሕግ ከተሰጠው ስልጣን ውጪ ከሶስት ጊዜ በላይ አንድን ጉዳይ ማየት እንደማይችል እየታወቀ ቦርዱ ግን ለስድስት ጊዜያት ያህል ጉዳዩን በማየት በሕገወጥ ውሳኔ እንድንፈናቀል ተደርጓል ብለዋል፡፡

ነጋዴዎቹ አያዘውም በስራቸው በርካታ ሰራተኞችን እንደሚያስተዳድሩ ከፍተኛ ግብርም ከፋዮች መሆናቸውን በማስታወስ ቦታው ለሃይማኖት ተቋም በነጻ ከሚሰጥ በሊዝ ክፍያ የማልማት የቅድሚያ መብታችን ይከበርልን በሚል ያነሳነው ጥያቄ ተቀባይነት እንዲያጣ መደረጉ እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል፡፡

ነጋዴዎቹ በዛሬው ዕለት ከህግና ከስርዓት ውጪ እየተወሰደ ያለው እርምጃ እንዲቆምላቸው ለፍርድ ቤት አመልክተው ፍ/ቤቱ ለፊታችን ሰኞ ወረዳው ምላሹን ይዞ እንዲቀርብ የታዘዘበትን ወረቀት ቢያስገቡም ሰዎቹ ከአድራጎታቸው ሊታቀቡ እንዳልቻሉ በመጥቀስ ከፍ/ቤት ውጪ ለማን አቤት እንላለን ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

የኩማ አስተዳደር በሚያዝያ ወር 2005 ኢህአዴግ ብቻውን ከሚወዳደርበት ምርጫ በኋላ ፈርሶ በሌሎች የኢህአዴግ ሰዎች ይተካል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከዚህ ቀደም በተለያዩ በላፍቶና በቦሌ ክፍለከተሞች የተፈናቀሉ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች መፍትሄ ሳያገኙ አሁንም በከፍተኛ ችግር ላይ ወድቀው ይገኛሉ።

በጅጅጋ የአማራ ተወላጆች ቤታቸው እየተነጠቁ ለጎዳና ተዳዳሪነት መዳረጋቸውን ገለጡ


በክልሉ የሚገኙ የአማራ ተወላጆች ለኢሳት እንደገለጡት ፣ ካለፉት 40 አመታት ጀምሮ በሶማሊ ክልል በጅጅጋ ከተማ ይኖሩ የነበሩ የአማራ ተወላጆች ቤቶቻቸውን እያስረከቡ ለጎዳና ህይወት ተዳርገዋል።

እስካሁን ድረስ በከተማዋ ውስጥ ዋና ዋና የንግድ ቦታዎች የነበሩዋቸው የአማራ ተወላጆች፣ ለሶማሊ ተወላጆች እንዲያስረክቡ በመዳረጋቸው ብዙዎች ድርጅቶቻቸውን አስረክበው ወደ መሀል አገር ሄደዋል።

ተወልደው ያደጉበትን ቦታ አንለቅም በማለት እስካሁን የቆዩትም በተለያዩ አስተዳዳራዊ ጫናዎች ከተማዋን ለቀው እንዲወጡ በደብዳቤ እና በቃል ተነግሯቸዋል።

በጅጅጋ ከተማ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ለኢሳት በጻፉት ደብዳቤ ” የአንድ ብሄር የበላይነት በሰፈነበት መልኩ አማራ ወይም ሀበሻ የሚል መጠሪያ ተደርጎልን እነሆ ከህጻናት እስከ ትልቅ በመንገድም በቢሮም እየተሰደብንና እየተተፋብን መኖራችን ሳያንስ፣ አሁን ደግሞ ያለምንም ልዋጭ ቤታችን ተቀምቶ ጎዳና ላይ ተጥለን እንገኛለን።
” ብለዋል።

ነዋሪዎቹ አክለውም ” የእኛ ልጆች እንደልብ በመንገድ ላይ መሄድ አይችሉም፣ ሱሪ የለበሰች ሴት በፖሊስ ዱላ ትደበደባለች፣ ማን ፖሊስ ማን ሀላፊ እንደሆነ በማናውቀው ሁኔታ፣ የሸሪያ ፍርድ ቤት የሚል ተቋቁሞ ቤታችንን እንድንለቅ እያስገደደን ነው። ተወልደን ባደግንበት አገር እንደ ሁለተኛ ዜጋ እንደቆሻሻ እየታየን ነው” ብለዋል።

አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ የከተማው ነዋሪ በክልሉ የመኖር ተስፋቸው መሟጠጡን ተናግረዋል
ኢሳት በጅጅጋ ከተማ በአማራ ተወላጆች ላይ የሚደርሰውን በደል በተደጋጋሚ ቢዘግብም መንግስት ዝምታን መርጧል።

ብፁዕ አቡነ ማትያስ 6ኛው ፓትርያርክ ሆነው ተሾሙ


ብፁዕ አቡነ ማትያስ 6ኛው ስት ከፍተኛ ድጋፍ የነበራቸው በትግራይ አጋሜ አውራጅ በስቡህ ወረዳ የተወለዱት ብፁዕ አቡነ ማትያስ 6ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ሆነው የፊታችን እሁድ ይሾማሉ።

በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት ሊቀ ጳጳስ ብፁእ አቡነ ማትያስ በቤተክርስቲያኗ ጉዳይ እጁን የከተተው የሕወሃት/ኢሕአዴግ መንግስት ምርጫም እንደሆኑ አስቀድሞም ሲነገር የነበር ሲሆን፣ እርሳቸውን ለዚሁ ሹመት ለማግባባት ባለፈው ታህሳስ ወር አንድ የልኡካን ቡድን ወደ ኢየሩሳሌም አቅንቶ እንደነበር በቤተክርስቲያኗ ጉዳይ የሚያተኩረው ደጀ ሰላም ድረ ገጽ በወቅቱ መዘገቡ ይታወሳል።

ለይስሙላ እንደተካሄደ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጨ ባለው ምርጫ አቡነ ማትያስ ከ800 መራጮች ውስጥ 500 ድምጽ እንዳገኙ ተነግሮላቸዋል።

 የአቡነ ማትያስን መመረጥ ተከትሎ ከቤተክርስቲያኗ አባቶችም ሆነ ከምዕመናኑ ብዙ ጥያቄዎች ሊነሱ እንደሚችሉ የሚገመት ሲሆን በተለይም በቅርቡ ተረቅቆ በሲኖዶሱ የፀደቀውን የፓትርያርክ ምርጫ ሕግ ከነዚህ ውስጥ ዋነኛው ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

'በተለይም ይህንን ሕግ በማርቀቁ ስራ ላይ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው ብፁዕ አቡነ ሳሙዔል፣ ብፁእ አቡነ አብርሃምና ብፁእ አቡነ ገብርዔል ባለፈው ሳምንት በተካሄደው የሲኖዶሱ ጉባዔ ላይ የአሜሪካ ዜግነታቸውን ከመለሱ ወደ ኢትዮጵያ የመጡበትን ፓስፖርት እንዲያሳዩ ጠይቀዋቸው ለማሳየት አለመቻላቸውን ኢሳት በወቅቱ መዘገባችን ይታወሳል።

 በተጨማሪም ሶስተኛው የቤተክርስቲያኗ ፓትርያርክ በነበሩት በብፁእ ወቅዱስ አቡነ ተክለ-ሃይማኖት ተላፎባቸው የነበረው ውግዘት ሌላው አጠያያቂ ጉዳይ ይሆናል ተብሎአል።

በ1971 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት ኤጲስ ቆጶስ ኾነው የተሾሙት ብፁዕ አቡነ ማትያስ፣ በ1974 ዓ.ም በስደት ወደ አሜሪካ በማቅናት እስከ 1984 ዓ.ም ከቆዩ በኋላ ወደ አገር ተጠርተው መጀመሪያ የአሜሪካ፣ ቀጥሎም የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ በመኾን ተመድበው እስካሁን ድረስ ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

አዲሱን ፓትርያርክ መመረጥ ተከትሎ የተለያዩ ወገኖች አስተያየታቸውን አስፍረዋል። በኦሮቶዶክስ አማንያን ዘንድ ከፍተኛ ተጽኖ ከሚያሳድሩ ድረገጾች መካከል ታዋቂ የሆነው ደጀሰላም ፣ ከጳጳሱ ሹመት በሁዋላ ” ድራማው ተጠናቀቀ” ብሎአል።

ድረገጹ ” ለረዥም ጊዜ እንደታየው፣ ብዙዎች ቀጣዩ ፓትርያርክ አቡነ ሳሙኤል ይሆናሉ ወይም አቡነ ጎርጎርዮስ የሚል የተሳሳተ ግምት ነበራቸው። ሁለቱም የጨዋታው አዳማቂዎች እንጂ በጨዋታው ውስጥ ቦታ አልነበራቸውም። ወይም ርዕስ መሆናቸው በራሱ የጨዋታው አንድ አካል ነበር።

 ብዙ ሰው አሁንም ከጠቅላላው ድራማ አንዱ ክፍል ላይ ብቻ በመከራከር ጊዜውን እያጠፋ ነው። ጉዳዩ ቤተ ክርስቲያን ነጻ ናት ነጻ ወይስ አይደለችም የሚለው ነው። ” በማለት የአቡኑን መመረጥ አጣጥሎአል።

ማህሌት ሰለሞን የተባሉ ሰው በፌስቡክ ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ ” መራጩም መንግስት ተመራጩም አቡነ ማቴያስ እንደሆኑ እያወቀን ምንም እንደማናውቅ ሊያታልሉት ይፈልጋሉ።

 ሐዋርያዊት ለሆነችው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በእኔ እድሜ አይናችን እያየ ለሁለተኛ ጊዜ ኢመንፈሳዊ በሆነ መንገድ ፓትሪያርክ ተሾመላት:: ይሄ አሳፋሪ የታሪክ ማህተም በምን ይሻር ይሆን ? በዘመኑ የነበርነውስ መልሳችን ምን ይሆን ? የተደረገልን እንደ ገዢው መንግስት ፈቃድ ነው:: እውነታው እሱ ነው።’ ብለዋል።

በስደት ላይ የሚገኘው ሲኖዶስ አዲስ የሚሾሙትን ፓትሪያርክ ህዝቡ እንዳይቀበል ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል።

ሲኖዶሱ ” ላለፉት 21 አመታት በመንግስት አስተባባሪነትና ደጋፊነት በህገ ወጥ መንገድ በተቀመጡት አባት ምክንያት ቤተ ክርስቲያናችንን ክፉኛ የጎዳው መከፋፈል እና መለያየት ሳያንስ አሁን ደግሞ እነዚህ ጥቂት ጳጳሳት በስልጣን ያለውን የመንግስት ሀይል መከታ አድርገው ፓትሪያርክ ብለው የሚሰይሙትም ፣ አባትነቱ የሀሰት አባት፣ ሹመቱም የሲሞን መሰርኢ ስለሆነ ቅዱስ ሲኖዶስ አጥብቆ ያወግዘዋል በማለት ሹመቱን ውድቅ አድርጎታል።

ታዛቢዎች እንደሚገልጹት የአዲሱ ፓትርያርክ ሹመት ዘረኝነትና ፖለቲካዊ ወገንተኝነት በእጀጉ የተነጸባረቀበት ነው። ላለፉት 21 አመታት ተከፋፍላ የቆየችው ቤተክርስቲያን በአቡነ ጳውሎስ ሞት አንድ ልትሆን ተችላለች በማለት ተስፋ አድርገው የነበሩ ምእመናን ተስፋቸው ከተስፋነት ሳይዘል ቀርቷል።

አቶ ተፈራ ዋልዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያን የነፍጠኛው ዋሻ ሆናለች በማለት በ 97 ምርጫ ወቅት መናገራቸው ይታወሳል።

ብፁዕ አቡነ ማትያስ 6ኛው ስት ከፍተኛ ድጋፍ የነበራቸው በትግራይ አጋሜ አውራጅ በስቡህ ወረዳ የተወለዱት ብፁዕ አቡነ ማትያስ 6ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ሆነው የፊታችን እሁድ ይሾማሉ።

በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት ሊቀ ጳጳስ ብፁእ አቡነ ማትያስ በቤተክርስቲያኗ ጉዳይ እጁን የከተተው የሕወሃት/ኢሕአዴግ መንግስት ምርጫም እንደሆኑ አስቀድሞም ሲነገር የነበር ሲሆን፣ እርሳቸውን ለዚሁ ሹመት ለማግባባት ባለፈው ታህሳስ ወር አንድ የልኡካን ቡድን ወደ ኢየሩሳሌም አቅንቶ እንደነበር በቤተክርስቲያኗ ጉዳይ የሚያተኩረው ደጀ ሰላም ድረ ገጽ በወቅቱ መዘገቡ ይታወሳል።

ለይስሙላ እንደተካሄደ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጨ ባለው ምርጫ አቡነ ማትያስ ከ800 መራጮች ውስጥ 500 ድምጽ እንዳገኙ ተነግሮላቸዋል።

 የአቡነ ማትያስን መመረጥ ተከትሎ ከቤተክርስቲያኗ አባቶችም ሆነ ከምዕመናኑ ብዙ ጥያቄዎች ሊነሱ እንደሚችሉ የሚገመት ሲሆን በተለይም በቅርቡ ተረቅቆ በሲኖዶሱ የፀደቀውን የፓትርያርክ ምርጫ ሕግ ከነዚህ ውስጥ ዋነኛው ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

 በተለይም ይህንን ሕግ በማርቀቁ ስራ ላይ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው ብፁዕ አቡነ ሳሙዔል፣ ብፁእ አቡነ አብርሃምና ብፁእ አቡነ ገብርዔል ባለፈው ሳምንት በተካሄደው የሲኖዶሱ ጉባዔ ላይ የአሜሪካ ዜግነታቸውን ከመለሱ ወደ ኢትዮጵያ የመጡበትን ፓስፖርት እንዲያሳዩ ጠይቀዋቸው ለማሳየት አለመቻላቸውን ኢሳት በወቅቱ መዘገባችን ይታወሳል። በተጨማሪም ሶስተኛው የቤተክርስቲያኗ ፓትርያርክ በነበሩት በብፁእ ወቅዱስ አቡነ ተክለ-ሃይማኖት ተላፎባቸው የነበረው ውግዘት ሌላው አጠያያቂ ጉዳይ ይሆናል ተብሎአል።

በ1971 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት ኤጲስ ቆጶስ ኾነው የተሾሙት ብፁዕ አቡነ ማትያስ፣ በ1974 ዓ.ም በስደት ወደ አሜሪካ በማቅናት እስከ 1984 ዓ.ም ከቆዩ በኋላ ወደ አገር ተጠርተው መጀመሪያ የአሜሪካ፣ ቀጥሎም የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ በመኾን ተመድበው እስካሁን ድረስ ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

አዲሱን ፓትርያርክ መመረጥ ተከትሎ የተለያዩ ወገኖች አስተያየታቸውን አስፍረዋል። በኦሮቶዶክስ አማንያን ዘንድ ከፍተኛ ተጽኖ ከሚያሳድሩ ድረገጾች መካከል ታዋቂ የሆነው ደጀሰላም ፣ ከጳጳሱ ሹመት በሁዋላ ” ድራማው ተጠናቀቀ” ብሎአል።

ድረገጹ ” ለረዥም ጊዜ እንደታየው፣ ብዙዎች ቀጣዩ ፓትርያርክ አቡነ ሳሙኤል ይሆናሉ ወይም አቡነ ጎርጎርዮስ የሚል የተሳሳተ ግምት ነበራቸው። ሁለቱም የጨዋታው አዳማቂዎች እንጂ በጨዋታው ውስጥ ቦታ አልነበራቸውም። ወይም ርዕስ መሆናቸው በራሱ የጨዋታው አንድ አካል ነበር።

 ብዙ ሰው አሁንም ከጠቅላላው ድራማ አንዱ ክፍል ላይ ብቻ በመከራከር ጊዜውን እያጠፋ ነው። ጉዳዩ ቤተ ክርስቲያን ነጻ ናት ነጻ ወይስ አይደለችም የሚለው ነው። ” በማለት የአቡኑን መመረጥ አጣጥሎአል።

ማህሌት ሰለሞን የተባሉ ሰው በፌስቡክ ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ ” መራጩም መንግስት ተመራጩም አቡነ ማቴያስ እንደሆኑ እያወቀን ምንም እንደማናውቅ ሊያታልሉት ይፈልጋሉ።

 ሐዋርያዊት ለሆነችው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በእኔ እድሜ አይናችን እያየ ለሁለተኛ ጊዜ ኢመንፈሳዊ በሆነ መንገድ ፓትሪያርክ ተሾመላት:: ይሄ አሳፋሪ የታሪክ ማህተም በምን ይሻር ይሆን ? በዘመኑ የነበርነውስ መልሳችን ምን ይሆን ? የተደረገልን እንደ ገዢው መንግስት ፈቃድ ነው:: እውነታው እሱ ነው።’ ብለዋል።

በስደት ላይ የሚገኘው ሲኖዶስ አዲስ የሚሾሙትን ፓትሪያርክ ህዝቡ እንዳይቀበል ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል።

ሲኖዶሱ ” ላለፉት 21 አመታት በመንግስት አስተባባሪነትና ደጋፊነት በህገ ወጥ መንገድ በተቀመጡት አባት ምክንያት ቤተ ክርስቲያናችንን ክፉኛ የጎዳው መከፋፈል እና መለያየት ሳያንስ አሁን ደግሞ እነዚህ ጥቂት ጳጳሳት በስልጣን ያለውን የመንግስት ሀይል መከታ አድርገው ፓትሪያርክ ብለው የሚሰይሙትም ፣ አባትነቱ የሀሰት አባት፣ ሹመቱም የሲሞን መሰርኢ ስለሆነ ቅዱስ ሲኖዶስ አጥብቆ ያወግዘዋል በማለት ሹመቱን ውድቅ አድርጎታል።

ታዛቢዎች እንደሚገልጹት የአዲሱ ፓትርያርክ ሹመት ዘረኝነትና ፖለቲካዊ ወገንተኝነት በእጀጉ የተነጸባረቀበት ነው።

 ላለፉት 21 አመታት ተከፋፍላ የቆየችው ቤተክርስቲያን በአቡነ ጳውሎስ ሞት አንድ ልትሆን ተችላለች በማለት ተስፋ አድርገው የነበሩ ምእመናን ተስፋቸው ከተስፋነት ሳይዘል ቀርቷል።

አቶ ተፈራ ዋልዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያን የነፍጠኛው ዋሻ ሆናለች በማለት በ 97 ምርጫ ወቅት መናገራቸው ይታወሳል።