onsdag 7. august 2013

በቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ የተገጣጠሙ የህዝብ አውቶብሶች አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ60 በመቶ በላይ የሚሆኑት ተበላሹ



-የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ያመረታቸው እና የገጣጠማቸው የከተማ እና  አገር አቋራጭ  አውቶብሶች አመት ሳይሞላቸው ለጉዳት ተደርገዋል።
አውቶብሶቹ ከግማሽ በላይ አካላቸው በሀገር ውስጥ ሙሉ ለሙሉ የተመረተ ቢሆንም በውጭ ሃገር ግዥ የተፈፀመው የሞተር አካላቸው ግን ምንም ዓይነት ስራ ሳያከናውኑ ከጥቅም ውጭ ሁነዋል፡፡
የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ ምክትል ስራ አስኪያጅና የኦፕሬሽን ሃላፊ ሻምበል ገብረመድህን ሀይሉ እንዳሉት ቢሾፍቱ እስከ አሁን ከ500 በላይ የከተማ አውቶብሶችን ሰርቶ አስረክቧል፡፡ከ 500 አውቶቡሶች መካከል ከ 300 በላይ የሚሆኑት አገልግሎት መስጠት በጀመሩ  በወራት ውስጥ ከአገልግሎት ውጭ ሆነዋል፡፡ ለደሴ ፤ ጎንደር እና አዳማ ለህዝብ ትራንስፖርት ከቀረቡት ስድስት የከተማ አውቶብሶች ውስጥ አራቱ ከገቡበት ቀን አንስቶ ቆመዋል፡
ችግሩ የተከሰተው ቢሾፍቱ ወደ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪው ሲገባ በተሟላ የሰው ሃይልና ቁሳቁስ እንዳልበር ሃላፊው ገልፀው አብዛኛው ስራ መሳርያን ሳይሆን የሰው ጉልበት መሰረት ያደረገ ነበረ፡፡
ይህን  ማድረግ ያስፈለገውም መስራት እንችላለን የሚለውን አስተሳሰብ ለማስረፅና ሁሌም የጎደለውን በማሰብ ብቻ ከስራ የመሸሽ ልማድን ለመስበር ነበር ብለዋል፡፡
አሁን ቢሾፍቱ ከውጭ የሚገቡ መቀያሪያ እቃዎች ለሙስናና ብልሹ አሰራር የተጋለጡ ናቸው ያሉት ውስጥ አዋቀዊዎች በዚህ ረገድ ቢሾፍቱ ከውጭ ሙሉ በሙሉ አካላቸውን በማምጣት ከመገጣጠም ባለፈ አሁን ለተከሰተው ችግር በጥገና መፍትሄ ለማምጣት መቸገሩም ታውቋል
በዘንድሮው አመት ብቻ 60 መንገደኞችን የመጫን አቅም ያላቸው ከ100 በላይ እጅግ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ያካተቱ ተሽከርካሪዎችን አምርቶ ከፊሉን ቢሸጥም ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ከአገልግሎት ውጭ ሆነዋል። በደሴ አውቶብሶቹ መበላሸታቸው የተነገረው ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ አቀባበል እንዲያደርግ  በተደረገ ማግስት ነው፡፡ ለተፈጠረው ኪሳራ የአሸከርካሪ ባለንብረቶች እና የመንግስት ቢሮዎች የእድሳት ወይም ዋስትና እንዲሰጣቸው ቢጠይቁም ምንም ምላሽ ማጣታቸው ታውቋል።
የቢሾፍቱ የመኪና የሞተር ክፍሎች ከቻይና ሐገር ኩባንያ ጋር በተወሰደ የውል ስምምነት የተገዙ ናቸው፡፡
የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ በጄኔራል ክንፈ ዳኘው በሚመራው በመከላከያ ሜታልስ እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የተቋቋመ ድርጅት ነው። ድርጅቱ ለአዲስ አበባ 500፣ ለደሴ፣ ሀዋሳ፣ደብረዘይትና ጅጅጋ ደግሞ 75 አውቶቡሶችን በመገጣጠም መሸጡን ከድርጅቱ ድረገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar