fredag 16. august 2013

አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ የሚያዘጋጀው የታላቁ ሩጫ የንግድ ፈቃድ ተሰረዘ


መንግስት ፈቃዱን የቀማው ከተሰጣቸው ፈቃድ ውጪ ሲንቀሳቀስ ተገኝቷል በሚል ነው። ከታላቁ ሩጫ በተጨማሪ  እስላማዊ የምርምርና የባህል ማዕከል ፣ ጎህ ቻይልድ ዩዝ ውመንስ ዴቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን ፣ዋን ዩሮ ኢትዮጵያ ፣ ብራይት አፍሪካ ኢንተግሬትድ ዴቨሎፕመንት አሶሲየሽን እና ፓድ ኢትዮጵያ ሊትሬሲ ኢዱኬሽን ኤንድ ቮኬሽናል ሴንተር ናቸው።
የድርጅቶቹን ሃብትና ንብረት በስማቸው በማዞር ሲጠቀሙ ፥ የፋይናንስ ምንጫቸውም ከተፈቀደው በላይ የሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም በሰራተኞቻቸው ላይ አስተዳደራዊ በደሎች የፈፀሙት ድርጅቶች መዘጋታቸውን የመንግስት የመገናኛ ብዙሀን ገልጸዋል። ድርጅቶቹ  በንግድ ስራ መሰማራት ፣ ባልተገባ ሃይማኖታዊ ተግባር መሳተፍ እና የድርጅትን ገንዘብ ለግል ጥቅም ማዋል በሚሉትም ተከሰዋል።
14 የሚሆኑ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችም በአቅም ውስንነት ፣ በፕሮጀክቶቹ መጠናቀቅ እና በሌሎችም ምክንያቶች ተዘግተዋል።

አትሌት ሀይሌን  ስለድርጅቱ መዘጋት ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግም አልተሰካልንም። አትሌቱ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት የመሆን ምኞት እንዳለው መግለጹ ይታወሳል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar