መምህራን እንደገለጹት አደረጃጀቱ ተግባራዊ በሆነባቸው በጎንደር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የኢህአዴግ አባላት ከሆኑ ከመምህራን አንድ፣ ከተማሪዎች አንድ ከፖሊስ አንድ እንዲሁም ከወላጆች አንድ በትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚገኙ መምህራንን የቀን ተቀን እንቅስቃሴ፣ ፖለቲካ አመለካከት እና ሌሎችንም ተያያዥ ጉዳዮች ይከታተላሉ።
መመሪያው በሁሉም ትምህርት ቤቶች የወረደ ሲሆን፣ በአብዛኛው ትምህርት ቤቶች የአንድ ለአምስት አደረጃጀቱ ተግባራዊ ሆኗል።
በዚህ ድርጅት ውስጥ የሚመደቡት የኢህአዴግ አባላት ከተራው መምህር በላይ ስልጣን ያላቸው ሲሆን፣ መምህራንም እነሱን በመፍራት ሀሳባቸውን በግልጽ ለመናገር እየተቸገሩ ነው።
ኢህአዴግ በመላው አገሪቱ እየገነባ ባለው የአንድ ለአምስት አደረጃጀት ህዝቡን ለመቆጣጠር ሙከራ ቢያደርግም እስካሁን ውጤታማ አለመሆኑን ገንባሩ ከወራት በፊት ባደረገው ጉባኤ መግለጹ ይታወቃል።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar