torsdag 27. august 2015

አቶ ማሙሸት አማረ ለውሳኔ ተቀጠሩ

‹‹ምስክርነቱ የሀሰትና የተጠና ነው!›› ጠበቃው
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

mamushet
mamushetአይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም መንግስት ከጠራው ሰልፍ አንድ ቀን ቀድሞ ከለቅሶ ቤት ወደ ቤተ መንግስት ለተደረገውና ለዋናው (ለሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም) ሰልፍ አነሳስቷል በሚል ክስ የተመሰረተበት አቶ ማሙሸት አማረ ዛሬ ነሃሴ 20/2007 ዓ.ም አራዳ ምድብ ችሎት ቀርቦ ለነሃሴ 22/2007 ዓ.ም ለውሳኔ ተቀጠሯል፡፡ አቶ ማሙሸት አማረ ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም በተካሄደው ሰልፍ ላይ ሁከትና ብጥብጥ ፈጥሯል በሚል ተከሶ የነበር ቢሆንም በወቅቱ ከምርጫ ቦርድ ጋር በነበረው ክርክር ሰልፉ ላይ አለመገኘቱን የሚያጋግጥ መረጃ በማቅረቡ በነፃ እንዲለቀቅ ተወስኖ ነበር፡፡ ነገር ግን ክሱ ወደማነሳሳት ተቀይሮ እስር ቤት እንዲቆይ ተደርጓል፡፡


አቶ ማሙሸት በአዲሱ ክስ የአቃቤ ህግን ምስክሮች ለመስማት ከ5 ጊዜ በላይ ፍርድ ቤት እንደተመላለሰ የተገለፀ ሲሆን በተለይ አንዱ ምስክር በፖሊስ ተይዞ እንዲመጣ ቢጠየቅም ፖሊስ ሳያስፈፅም ቀርቷል፡፡ ከአራቱ ምስክሮች መካከል ሶስቱ ዛሬ የመሰከሩ ሲሆን ‹‹አቶ ማሙሸት አማረ 300 ብር ከፍሎ ሰልፍ እንድንወጣ አድርጎናል›› ሲሉ መስክረዋል፡፡

ይሁንና ምስክሮቹ ከማሙሸት ጋር በተገናኙበት ወቅት እንዲሁም ገንዘቡ ሲሰጣቸው፣ ሰልፉ ያለፈባቸውን ቦታዎችና ስለ ሌሎችም ጉዳዮች ሲጠየቁ ‹‹አላስታውሰውም›› ከማለት ባለፈ ዝርዝር የምስክርነት ቃል ሳይሰጡ ቀርተዋል፡፡ ከምስክሮቹ መካከል ሁለቱ አቶ ማሙሸትን ያስያዙ ደህንነቶች መሆናቸውን አቶ ማሙሸትና ጠበቃው በችሎቱ የገለፁ ሲሆን ምስክሮቹ በበኩላቸው ስራቸውን ሲጠየቁ ‹‹የግል›› እያሉ ከመመለስ ውጭ የመንግስት ስራ እንደማይሰሩ ተናግረዋል፡፡ ሆኖም የመንግስት ሰራተኛ መሆናቸውን የሚያሳይ መታወቂያ ሲጠየቁ ሊያሳዩ አልቻሉም፡፡ ከሶስቱ ምስክሮች መካከል አንደኛው ስራውን ሲጠየቅ ‹‹የግል›› ብሎ የነበር ቢሆንም በመስቀለኛ ጥያቄ የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ጥቃቅንና አነስተኛ አመራር መሆኑን አምኗል፡፡

ከምስክሮቹ መካከል ሁለቱ የመኢአድ ደጋፊዎች መሆናቸውን ሲጠቅሱ አንደኛው አቶ ማሙሸት ባቀረቡበት የመስቀለኛ ጥያቄ ከምርጫ በኋላ የወጣቶች ሊግና የኢህአዴግ አባል መሆኑን አምኗል፡፡ የኢህአዴግ አባል ሆኖም ቢሆን መኢአድን እንደሚደግፍም ገልጾአል፡፡ ዳኛው ‹‹በሁለት ወር ውስጥ እንዴት ብለህ የወጣቶች ሊግ አባል መሆን ቻልክ?›› ሲሉት መልስ ሳይሰጥ አልፎታል፡፡
የአቶ ማሙሸት አማረ ጠበቃ ሶስቱም ምስክሮች አብዛኛዎቹን ጉዳዮች እንደማያስታውሱ በመግለፃቸው የተጠና የምስክርነት ቃል መሆኑን ለችሎቱ አስረድተዋል፡፡ በተጨማሪም ከ7 አመት በላይ አዲስ አበባ ውስጥ ኖረው መስቀል አደባባይን ጨምሮ ሰልፉ አመራባቸው የተባሉትን ቦታዎች አናውቃቸውም ማለታቸው፣ መተዳደሪያ ስራቸውን መደበቃቸውና መታወቂያ ለማሳየትም ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ምስክርነቱ የሀሰት እንደሆነ ስለሚያረጋግጥ ደንበኛቸው በነፃ እንዲለቀቁ ጠይቀዋል፡፡

onsdag 26. august 2015

በእነሀብታሙ አያሌው ጉዳይ ማረሚያ ቤት ላይ ክስ ቀረበ

ኤልያስ ገብሩ

habtamu ayalew
ሰኔ 01 ቀን 2006 ዓ.ም በሽብርተኝነት ወንጀል ከተጠረጠሩ በኋላ፤ በእነዘላለም ወርቅአገኘሁ የክስ መዝገብ፣ ከአንድ ዓመት በላይ ጉዳያቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ሲታይ ቆይቶ ባለፈው ሳምንት ነሐሴ 14 ቀን 2007 ዓ.ም በነጻ እንዲሰናበቱ በችሎቱ ትዕዛዝ ከተሰጣቸው አምስት ግለሰቦች መካከል 2ኛ ተከሳሽ ሀብታሙ አያሌው እና 7ኛ ተከሳሽ አብርሃም ሠለሞን እስከአሁን ድረስ ከቂሊንጦ እስር ቤት መፈታት ባለመቻላቸው የተነሳ፣ በዛሬው ዕለት ማረሚያ ቤቱ ላይ ክስ መቅረቡ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት የቀረበው ክስ እንደሚያስረዳው ከሆነ፣ ከላይ በተጠቀሰው ቀን፤ ፍርድ ቤቱ፣ በክሱ ከተራ ቁጥር 2-5 እና 7ኛ ተከሳሽ ክሱን መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ እንዲሰናበቱ በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት የመፍቻ ትዕዛዙን በ15/12/2007 ዓ.ም ለማረሚያ ቤቱ ቢደርስም ተከሳሾቹ እስከአሁን ድረስ ከእስር ሊለቀቁ አለመቻላቸውን ይጠቅሳል፡፡ በመሆኑም ‹‹ፍርድ ቤቱ ይህንን ባደረጉ የማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎች ላይ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ባለማክበራቸው ሕጋዊ እርምጃ ከመውሰድ ጋር ተከሳሾቹን እንዲለቅ ጥብቅ ትዕዛዝ እንዲሰጥልኝ በማክበር አመለክታለሁ›› ሲሉ ለ2ኛ ተከሳሽ ሀብታሙ አያሌው ባለቤቱ ወ/ሮ ቤተልሄም አዛናው እና ለ7ኛ ተከሳሽ አብርሃም ሠለሞን ወላጅ እናቱ ወ/ሮ መሠረት ገ/ጊዮርጊስ በዛሬው ዕለት ትዕዛዙን ለሰጠው ችሎት ክሳቸውን ማቅረባቸው ታውቋል፡፡ ፍርድ ቤቱ በነጻ ካሰናበታቸው ተከሳሾች መካከል አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋና ዳንኤል ሺበሺ ችሎት በመድፈር ወንጀል ሁለት ጊዜ ያህል መቀጣታቸው የሚታወስ ሲሆን ባለፈው ሳምንት ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ውሳኔ ተከትሎ አቃቤ ሕግ በአምስቱም ተከሳሾች ላይ ይግባኝ ጠይቆ ከእስር እንዳይፈቱ ዕግድ አቅርቦ ነበር፡፡ እንዲሁም የተቀሩት አምስት ተከሳሾች እንዲከላከሉ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ መስጠቱ ይታወቃል፡፡

fredag 21. august 2015

በሰላም አስከባሪ ስም የሕወሓት ባለስልጣናት የሚቀራመቱትን የሰራዊቱን ዶላር ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን እንዲህ ይመሰክራል

ዛሬ ለኢሳት የደረሰው ጥብቅ መረጃ 11ዓመታትን ወደ ኋላ በትዝታ ወሰደኝ:: ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከዋናው ጸሀፊ ቢሮ አፈትልኮ የወጣው መረጃ እንደሚያጋልጠው ለሰላም አስከባሪ 11 ሺህ የኢትዮጵያ ሰራዊት የሚከፈለው ደምወዝ ከ90 በመቶ በላይ የህወሀት ካዝና ውስጥ የሚገባ ነው:: በወር 13 ሚሊዮን ዶላር(500 ሚሊዮን ብር ገደማ) የወታደሩ ገንዘብ ህወሀቶች ይቀራመቱታል:: ይህን ጉዳይ የመንግስታቱ ድርጅት የሚያውቀው ይመስለኛል:: ለዚህም እኔ የተሳተፍኩበትን የሰላም አስከባሪ ዘመቻ አጋጣሚ በአስረጂነት ማሳየት እችላለሁ::
Mesay mekonenn
እኤአ በ2003-2004 በመንግስታቱ ድርጅት የበላይነት: በአፍሪካ ህብረት አስፈጻሚነት ከተላከው የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ሰራዊት ጋር ወደ ቡሩንዲ ሄጄ ነበር:: ወደ 18 የምንሆን አስተርጓሚዎች ከ8 ወር እስከ 1 ዓመት ቆይተናል:: ዝርዝሩን ሌላ ጊዜ በሰፊው እመለስበታለሁ:: ከገንዘብ ጋር በተያያዘ የተፈጸመውን የህወሀቶችን ለከት ያጣ ስግብግብነትን ላጫውታችሁ::



በዘመቻው በUN ደረጃ ወርሃዊ ደምወዝ ከ1000 ዶላር ያላነሰ: የመስክ ክፍያ በቀን 60 ዶላር: የበዓል ክፍያ በአንድ በዓል 1000 ዶላር: የላብ መተኪያ: …..በጣም ብዙ ዓይነት ክፍያዎች ነበሩት:: አብዛኛው የሰላም አስከባሪ ሰራዊት አባላት በተስፋ ነበር ወደ ቡሩንዲ የተጓዘው:: እዚያ እንደደረስን ነገሮች ሁሉ የተገላቢጦሽ ሆኑ:: ቃል የተገባው: በውል የታሰረው( የሚገርመው የውሉን 3 ኮፒዎች አንሰጥም ብለው እዚያው መከላከያ ግቢ ቀርቷል:: መንግስትን አምነን ነው የተጓዝነው) ክፍያ የለም:: በወር 40 ዶላር ለኪስ እየተሰጠን: ምግብና መጠጥ በአላሙዲን እየቀረበልን: እየበላንና እየጠጣን መኖር ብቻ ሆነ:: ከኢትዮጵያ ሌላ የደቡብ አፍሪካና ሞዛምቢክ የሰላም አስከባሪ ሃይሎችም ለተመሳሳይ ዘመቻ ቡሩንዲ ገብተዋል:: ለእነሱ የሚገባቸው ክፍያና ጥቅማጥቅም ሀገራቸው በባንክ አካውንታቸው የሚገባላቸው ይህንንም የሚያረጋግጥ ደረሰኝ በየወሩ እንደሚደርሳቸው በነበረን ቅርበት ተረዳን:: እኛ ግን ምንም የለም:: ስንጠይቅ ኢትዮጵያ ይጠራቀምላችኋል የሚል መልስ ከማስፈራሪያ ጋር ይሰጠናል::
በእኛና በሌሎቹ ለተመሳሳይ ዘመቻ በመጡ ሀገራት የሰላም አስከባሪው ዘመቻ አባላት መሃል ያለው የኑሮ ሁኔታ የሰማይና የምድርን ያህል የሚራራቅ ነበር:: በህወሀት ስግብግብነት የተነሳ በጣም በሚያሳፍር የኑሮ ገጽታ መቀለጂያ ሆንን:: በሰራዊቱ ውስጥ ቅሬታው ስር ሰደደ:: ተስፋው ጨለመ:: በወር 40 ዶላር እየወረወሩ እዚያ ይጠራቀምላችኋል በምትል ከቃል ያለፈ በደረሰኝ ያልተረጋገጠች ተስፋ ብቻ ይዘን በብስጭት ገፋን:: በመሃል ሲብስብን አስተርጓሚዎች ተነጋግረን ቡጁምቡራ በሚገኝ የUN ጽ/ቤት አቤቱታ ልናቀርብ ሄድን:: የተሰጠን ምላሽ ተስፋችንን ይበልጥ ገደለው:: “ስለ እናንተ የተፈራረምነው ከመንግስታችሁ ጋር በመሆኑ አይመለከተንም:: መንግስታችሁን ጠይቁ::” የሚል ወሽመጥ የሚቆርጥ ምላች ተሰጠን::

በመሃሉ መለስ ዜናዊና ሳሞራ የኑስ ሊጎበኙን ቡጁምቡራ መጡ:: ሳሞራ ሰብስቦን ችግር ካለ ንገሩኝ አለ:: ሰራዊቱ የክፍያው ነገር ሲያንገበግበው ስለከረመ ሳሞራን ሲያገኝው በየተራ እየተነሳ ጠየቀው:: ሳሞራ ጀት ሆነ:: ባለጌ አፍ እንዳለው ያረጋገጥኩት የዚያን ዕለት ነው:: የኢትዮጵያን የችግር መዓት ሲዘረዝር: መዓት ሲያወራ ቆየና ” ሰው እንደ ቤቱ እንጂ እንደ ጎረቤቱ አይኖርም:: የሌሎችን እያያችሁ እንደነሱ እንሁን ማለት አደጋ አለው:: እዚህ ገንዘብ ምንም አያደርግላችሁም:: በብር ኢትዮጵያ እየተጠራቀመላችሁ ነው:: ለሸርሙጣ ፈልጋችሁ ከሆነ ኢትዮጵያ ስትመለሱ ትደርሱበታላችሁ…..” እያለ ወረደብን::
ሰራዊቱ ቅስሙ ተሰበረ:: ብዙ የምንሰራው ስራ አለ:: ትምህርት ቤት እንገነባለን:: ….እያለ ተንዘባዘበ:: የዚያን ዕለት ሌሊት ከአምቦ የመጣ የሰራዊቱ አባል በታጠቀው መሳሪያ ራሱን አጠፋ:: ባርቆበት ነው የሚል ሪፖርት እንድናዘጋጅ በህወሀት የጦር አዛዦች መመሪያ ተሰጥቶን የውሸት ሪፖርት አዘጋጅተን ለUN ተላከ:: ይህ የሆነበትም ራሱን ካጠፋ UN ካሳ አይከፍልም:: እርግጠኛ ነኝ በዚህ የተገኘውን በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠር ዶላር ህወሀቶች ኪስ ገብቷል::
ወደ ኢትዮጵያ ስንመለስ እየተጠራቀመላችሁ ነው እየተባለ ስንሸነገል የከረምንበትን ገንዘብ ሊሰጡን ተዘጋጁ:: ለአንድ የሰላም አስከባሪ ሰራዊቱ አባል በትንሹ ከ250ሺህ ብር በላይ ወይም በወቅቱ ምንዛሪ 10ሺህ ዶላር መከፈል ነበረበት:: በጣም የሚያሳፍር የሚያስደነግጥ ነገር ነበር የጠበቀን:: እንደ ቆይታ ጊዜ ከ15ሺህ እስከ 25ሺህ የኢትዮጵያ ብር ሰጥተው አሰናበቱን:: ከእያንዳንዳችን ከ200ሺህ ብር በላይ ህወሀቶች ተቀራመቱት:: …በሌላ ጊዜ በስፋት እመለስበታለሁ::

onsdag 19. august 2015

በአማራ ክልል አንዳንድ ዞኖች አርበኞች ግንቦት 7ንና ትህዴንን ትደግፋላችሁ በሚል እስራትና ድብደባ እየደረሰባቸው ነው


በአማራ ክልል የሚገኙ አንዳንድ ዞኖች ላይ የሚኖሩ ንፁሃን ዜጎችን የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ የተቃዋሚ ድርጅቶችን ትደግፋላችሁ በሚል እስራትና ከፍተኛ ድብደባ እየደርሰባቸው መሆኑ ታወቀ። የደህሚት ድምጽ ደረሰኝ ባለው መረጃ እንዳመለከተው በክልሉ አንዳንድ ዞኖች ላይ የሚኖሩ ዜጎችን ከፌድራል የደህንነት መስሪያ ቤት የተላኩ ደህንነቶች ንፁሃን ዜጎችን የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ ድርጅቶችን እየደገፋችሁ ወጣቶችንም ወደ አርበኞች ግንቦት 7ና ትህዴን እየላካችሁ ነው በሚል የሃሰት ውንጀላ እየደበደቡና እያስፈራሩ መሆኑን የገለፀው መረጃው እንደዋና መነሻነትም የኢሳትን ቴሌቪዥንና የተቃዋሚዎችን ሬዲዮ ስታዳምጡ ተገንታችኋል የሚል መሆኑን አስረድቷል። በክልሉ የአምባገነኑ መንግስት ተላላኪነት የሃሰት ውንጀላ ከደርሰባቸው መካከል በአዊ ዞን አንከሻ ጓጉሳና ጃዊ ወረዳዎች በምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ሰከላና ወምበርማ ወረዳዎች በሰሜን ወሎ ዞን መቄትና ዋድላ ወረዳዎች የሚገኙ ንፁሃን ዜጎችን እያሰቃዩ ናቸው::

mandag 17. august 2015

ኤርትራ ሊገቡ ሲሉ ተያዙ ተበለው የተከሰሱት እነ ብርሃኑ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ ‹‹ድርጊቱን ፈጽመናል፣ ጥፋተኞች ግን አይደለንም››


በነገረ ኢትዮጵያ


 ሪፖርተር የኢትዮ-ኤርትራ ድንበርን በማቋረጥ ኤርትራ ከሚገኘው ግንቦት ሰባት የተባለ በተወካዮች ምክር ቤት ሽብርተኛ ተብሎ ከተፈረጀ የሽብር ቡድን ጋር ለመቀላቀል ሲጓዙ ድንበር አካባቢ ማይካድራ ላይ እንደተያዙ በመግለጽ በመንግስት የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው እነ ብርሃኑ ተክለያሬድ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ፡፡

 ዛሬ ነሐሴ 11/2007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ 14ኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ እየሩሳሌም ተስፋው፣ ፍቅረማርያም አስማማውና ደሴ ካህሳይ ‹‹በክሱ ላይ የተመለከተውን የወንጀል ድርጊት ፈጽመዋል ወይስ አልፈጸሙም›› የሚል ጥያቄ ከፍርድ ቤቱ እየተነሳላቸው፣ በየተራ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ በዚህም አራቱም ተከሳሾች ድርጊቱን እንደፈጸሙ በመግለጽ፣ ነገር ግን ጥፋተኛ አለመሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ አንደኛ ተከሳሽ ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ ‹‹ሀገሬ በፋሽስት አምባገነኖች ተይዛ ዜጎች በጨቋኝ ስርዓት ውስጥ ስላሉ ሀገሬንና ህዝቤን ነጻ ለማውጣት ወጣትነቴን ሰውቼ ለመታገል ግንቦት ሰባት ከሚባል ነጻ አውጭ ድርጅት ጋር ለመቀላቀል ወስኜ ወደዚያው አቅንቻለሁ፡፡

 ስለዚህ ድርጊቱን ፈጽሜያለሁ፣ የግንቦት ሰባት አባል ነኝ፡፡ ወንጀለኛ ግን አይደለሁም›› ሲል ቃሉን ለፍርድ ቤቱ ሰጥቷል፡፡ ሁለተኛ ተከሳሽ እየሩሳሌም ተስፋው በበኩሏ፣ ‹‹ድርጊቱን ፈጽሜያለሁ፤ ነገር ግን ጥፋተኛ አይደለሁም›› ብላለች፡፡ ሦስተኛ ተከሳሽ ፍቅረማርያም አስማማው ደግሞ፣ ‹‹ህገ-መንግስቱን አምኜ በሰላማዊ ትግል ውስጥ ስሳተፍ የደረሰብኝን አውቃለሁ፡፡ ሰላማዊ ትግል እንደማያዋጣም ተረድቻለሁ፡፡ በዚህ ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲን ለመገንባት የሚያስፈልገው የነጻነት ትግል ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ግንቦት ሰባት ነጻ አውጭን ለመቀላቀል ስጓዝ ማይካድራ ላይ ተይዣለሁ፡፡ ስለዚህ ድርጊቱን ፈጽሜያለሁ፤ ጥፋተኛ ግን አይደለሁም›› ብሏል ለችሎቱ፡፡ አራተኛ ተከሳሽ ደሴ ካህሳይ በበኩሉ፣ ‹‹አርሶ አደር ነኝ፣ ሰሊጥ አመርታለሁ፡፡

 ነገር ግን ያመረትሁትን ሰሊጥ የኢህአዴግ ወታደሮች ይዘርፉኛል፤ መስራት አልቻልኩም፡፡ በዚህ ምክንያት ሌላ ስራ መስራት ስላልቻልኩ የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባርን ተቀላቅያለሁ፡፡ ለዚህ ግን ጥፋተኛ አይደለሁም›› ሲል የእምነት ክህደት ቃሉን ሰጥቷል፡፡ ፍርድ ቤቱ የተከሳሾችን ቃል ካዳመጠ በኋላ የአቃቤ ህግን አስተያየት የጠየቀ ሲሆን፣ አቃቤ ህግ ተከሳሾች ጥፋተኝነታቸውን ስላላመኑ ማስረጃ እንዲያቀርብና እንዲያሰማ እንዲፈቀድለት ጠይቋል፡፡ ስለሆነም ፍርድ ቤቱ የአቃቤ ህግ ማስረጃን ለመስማት ለነሐሴ 22/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡

fredag 14. august 2015

ፍርድ ቤቱ ለሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች የሰጠው ዋስት በፖሊስ ታገደ

ነገረ ኢትዮጵያ


nከምርጫው ማግስት ከአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በፖሊስ ተይዘው ነሃሴ 6/2007 ዓ.ም እያንዳንዳቸው በ15 ሺህ ብር ዋስ እንዲወጡ ተጠይቀው የነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ዋስትናቸው በአቃቤ ህግና በፖሊስ መታገዱን የፓርቲው የምዕራብ ጎጃም ዞን አስተባባሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
ፖሊስ በአመራሮቹ ላይ ላቀረበው ክስ ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻሉ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት ነሃሴ 6/2007 ዓ.ም ከምርጫው ማግስት እየታደኑ የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን ጨምሮ 8 የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና አባላትን እያንዳንዳቸው የ15 ሺህ ብር ዋስ አቅርበው እንዲፈቱ የወሰነ ሲሆን ሁለቱ ወዲያውኑ ወጥተዋል፡፡ ይሁንና የዋስትናው ገንዘብ እስኪሞላላቸው እስር ቤት የቆዩት 6ቱ አመራሮች ትናንት ነሃሴ 7/2007 ዓ.ም የክልሉ አቃቤ ህግና ፖሊስ ለማረሚያ ቤቱ ባቀረቡት ጥያቄ ዋስትናቸው መታገዱ ታውቋል፡፡ አመራሮቹና አባላቱ ዋስትናቸው የታገደው ገንዘቡን ካስያዙ በኋላ መሆኑም ታውቋል፡፡ እንዲከፍሉ የተጠየቁትን ገንዘብ ካስያዙ በኋላ ዋስትና የተከለከሉት አመራሮች፡-
1. ልዑልሰገድ እምባቆም
2. ፋንታሁን ብዙአየሁ
3. መንግስቴ ታዴ
4. አዳነ አለሙ
5. ስማቸው ምንይችል
6. አበባው አያሌው ናቸው

torsdag 13. august 2015

የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የመጨረሻ መጽሃፍ – መጽሃፍ ቅዱሱን ተነጠቀ!!

ዳዊት ከበደ ወየሳ እንደዘገበው)

 ሃሳቡን በጽሁፍ ስላቀረበ “አሸባሪ” ተብሎ 18 አመት የተፈረደበት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፤ በእስር ቤት ውስጥ በከፍተኛ ጫና እየደረሰበት መሆኑ ተገለጸ። ምንም ነገር ማንበብም ሆነ መጻፍ ተከልክሏል። በአንድ ለሊት እስከሶስት ግዜ ክፍሉ እየመጡ፤ ከእንቅልፉ በመቀስቀስ ፍተሻ ያደርጉበታል። ይህ ሁሉ የሚደረገው ደግሞ ከህግ እና ህገ መንግስቱ ተጻራሪ በሆነ መንገድ ነው። ለምሳሌ – በህገ መንግስቱ አንቀጽ 21 ላይ፤ “የህግ እስረኛ መብት ሊጠበቅ ይገባል።

” ይላል። አንድ ታሳሪ ሰብአዊ ክብሩም መጠበቅ እንዳለበት ይዘረዝራል። ይህ ብቻ አይደለም። በዚሁ አንቀጽ ቁጥር 2 ላይ “ማንኛውም እስረኛ ከሚቀርበው ሰው ጋር መገናኘት ይችላል” ይልና መብቱን በዝርዝር ሲገለጽ- ከትዳር ጓደኛው፣ ከቅርብ ዘመዶች፣ ጓደኞች ከሃይማኖት አማካሪው፣ ከሃኪሙ እና ከህግ አማካሪው ጋር የመገናኘት መብት እንዳለው ብቻ ሳይሆን፤ ስለጾም እና ጸሎት ለመማከር ቢፈልግ የሃይማኖት አባት ማነጋገር እንደሚችል ተደንግጓል። በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ ግን ራሳቸውን ከህገ መንግስቱ በላይ ያደረጉ የወህኒ ቤቱ አዛዦች ሰብአዊ መብቱን የሚጋፉ ድርጊቶች በተደጋጋሚ ሲፈጽሙበት ቆይተዋል።


eskinder2

 ይህም በጨለማ ቤት ውስጥ ከማሰር ጀምሮ ቤተሰብ እና ጓደኞቹ እንዳይጠይቁት እስከማድረግ ድረስ ይዘልቃል። በተለይም ከቅርብ ግዜ ወዲህ ገብረወልድ የተባለ ደህንነት በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ ተመድቦበት፤ በቁም እንዲሰቃይ እያደረገው ነው። በቀን እና በለሊት በማንኛውም ግዜ ጋዜጠኛ እስክንድር ወደታሰረበት ክፍል በመግባት ያዋክበዋል፤ የሚጠቀምበትንም ቁሳቁስ ይወስድበታል። ለምሳሌ – እስረኞች እዚያው ከሚሰሩትና ገዝተው ከሚጠቀሙባቸው ቁሳቁሶች መካከል እዚያው ግቢ ውስጥ የሚሰራው መቀመጫ አንዱ ነው። ይህን መቀመጫ ከጋዜጠኛ እስክንድር ክፍል ውስጥ ወስደውበታል።

 እንዲህ ያለ ተራ ተግባር ነው እየተፈጸመ ያለው። ከእስር ቤት አካባቢ የደረሰን መረጃ እንደሚያስረዳው፤ መቀመጫ ወንበሩን ከጋዜጠኛው ላይ ከወሰዱበት በኋላ፤ በእስር ክፍሉ ውስጥ የሚገኘውን ባልዲ ገልብጦ፤ እንደወንበር ይጠቀምበታል። “ይህን ዘገባ ሲመለከቱ ደግሞ፤ ይህቺኑ ባልዲ ሊወስዱበት ይችላሉ” ብለውናል ዘገባውን ያደረሱልን ግለሰቦች። ይህን እንደምሳሌ ገለጽን እንጂ፤ በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ ከዚህ በላይ የሰብአዊ መብት ጥሰት ሲደርስበት ነበር፤ አሁንም እየደረሰበት ነው። በአሁኑ ወቅት ምንም አይነት መጽሃፍ ወይም ወረቀት እንዲኖረው አይፈቀድለትም። ባለፈው ሳምንት ክፍሉን የበረበረው ገብረወልድ ሲያስጠነቅቀው፤ “እስክሪብቶ እንኳን ይዘህ እንዳይህ አልፈልግም።

” ሲል ነበር የዛተበት። ሌላው ቀርቶ እስክንድር ያነበው የነበረውን የመጨረሻ መጽሃፍ – መጽሃፍ ቅዱሱን ጭር ወስደውበታል። ይህን መጽሃፍ ቅዱስ በእስር ላይ በነበረበት ወቅት ባለቤቱ ሰርካለም ፋሲል የሰጠችው ነበር። ከምንም ነገር በላይ ግን ከአምላኩ ጋር የሚገናኝበት፤ በጸሎት ግዜ የማይለየውን መጽሃፍ ቅዱስ የወሰዱበት የጋዜጠኛውን ቅስም ጭምር ለመስበር ቢሆንም፤ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ግን አሁንም በመንፈሰ ጠንካራነት ከሚታወቁት እስረኞች መካከል አንዱ ነው። ኢትዮጵያ በህገ መንግስቷ ላይ እንደተገለጸው ከሆነ የአለም አቀፍ ሰብአዊ መብቶችን ትቀበላለች። ሆኖም በጋዜጠኛ እስክንድር ላይ የሚደርሰው ግፍ ግን የሰው ልጅ ሊሸከመው የሚከብድ ነው። ትላንት ለሌሎች ኢትዮጵያውያን መብት መከበር ይቆረቆር እና ይጽፍ የነበረው ጋዜጠኛ ህክምና ጭምር ተከልክሎ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው። ይቅርታ ጠይቆ እንዲወጣ ተጠይቆ ፈቃደኛ ባለመሆኑጥርስ ተነክሶበታል።

 እንደኢትዮጵያ አለም አቀፉን የሰብአዊ መብት አያያዝ የፈረሙ አገሮች የእስረኞችን ሰብአዊ ክብር ይጠብቃሉ። እስረኞች እንደየሃይማኖታቸው መጽሃፍ ቅዱስም ሆነ ቅዱስ ቁርአን እንዳያነቡም ሆነ እንዳይኖራቸው አይከለከሉም፤ በኢትዮጵያ ግን እየሆነ ያለው ከዚህ በተቃራኒ ነው። (በዚህ አጋጣሚ የቤተ ክርስቲያን ሰዎች – የጋዜጠኛው መጽሃፍ ቅዱስ እንዲመለስለት ጠቅላይ ሚንስትሩን እንዲጠይቁ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን) በአሁኑ ወቅት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በታሰረበት ክፍል ውስጥ፤ እሱን ጨምሮ አምስት እስረኞች አሉ። ከነሱም ውስጥ “መንግስትን በሃይል ወይም በመፈንቅለ መንግስት ለመገልበጥ ሙከራ አድርጋችኋል” ተብለው ሞት የተፈረደባቸው ጌታቸው ብርሌ እና መላኩ ተፈራ፤ ከመኢዴፓ ክንፈሚካኤል ደበበ (አበበ ቀስቶ) እና በከፍተኛ ሙስና የታሰረው የጉምሩኩ ገብረዋህድ አብረው ነው የታሰሩት። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከታሰረ በኋላ፤ ሃብት እና ንብረቱን – ገንዘብ እና ቤቱን ሳይቀር መንግስት አግዶበታል። የወላጆቹን ንብረት እንዳይሰበብ ሆኗል።

 በሚሊዮን ይቆጠር የነበረውን እና እናቱ በባንክ አካውንታቸው ያስቀመጡት ገንዘብ ከፍርድ ቤት እግድ ውጪ እንዳይንቀሳቀስ ተደርጓል። እናቱ በህይወት በነበሩበት ወቅት፤ ክሊንካቸውን እንዲዘጉ ከተደረጉ በኋላ ንብረታቸውን አዘርፍታል። አራት ኪሎ የሚገኘው ቤታቸው ተወስዶባቸው ሆቴል ውስጥ ነበር የሚኖሩት። በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ፤ የእስር ብቻ ሳይሆን የግል መኖሪያ ቤቱ እና ንብረቱ ጭምር እግድ ወጥቶበታል። ይሄ ሁሉ ሆኖ ግን ከሁለት አመት በፊት፤ የመጨረሻ ውሳኔ ሲሰጠው፤ “እኛ ሁላችን እናልፋለን። ልጄ ናፍቆት እክንድር አድጎ፤ አንድ ቀን ንብረታችንን ያስመልሰዋል።” የሚል ምላሽ ለፍርድ ቤቱ መስጠቱ ይታወሳል። ከዚህ በታች ያወጣነው ለፍርድ ቤቱ የተጠየቀው የእግድ ደብዳቤ ነው። በደብዳቤው ላይ እንደተገለጸው፤ 1ኛ ንፋስ ስልክ ላፍቶ የሚገኘው G+2 መኖሪያ ቤት፤ ከእናቱ በውርስ ያገኘው የካ ወረዳ የሚገኘው ትልቅ ቪላ ቤት እንዲሁም ልጁን ናፍቆት እስክንድርን ትምህርት ቤት ያመላልሱበት የነበረው አቶዝ መኪና በባለቤቱ በወ/ሮ ሰርካለም ተመዝግቦ እንደሚገኝ ደብዳቤው ገልጾ፤ በመንግስት እንዲወረስ ጥያቄ ቀርቧል።

onsdag 12. august 2015

መንግስት በሕዝብ የተመረጠው ቴዲ አፍሮን በስነጥበብ ዘርፍ ለመሸለም ፍላጎት እንደሌለው በይፋ አሳየ


በየዓመቱ የሚካሄደና ዘንድሮም ለ3ኛ ጊዜ ነሐሴ 30 ቀን 2007 ዓም በአዲስ አበባ ካፒታል ሆቴል በሚከናወነው ‹የዓመቱ በጎ ሰው ሽልማት› በየዘርፉ የተመረጡ የመጨረሻዎቹ አምስት ዕጩዎችን መንግስት ልክ እንደምርጫው አጭበርብሮ ራሱ የሚፈልጋቸውን ሰዎች አስቀመጠ:: ካለፈው ታህሳስ ወር ጀምሮ በተሰጠው የሕዝብ ጥቆማ የዓመቱ በጎ ሰው በሚል በስነጥበብ ዘርፍ ዝነኛው ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ከፍተኛ የሆነ የሕዝብ ምርጫን ቢያገኝም መንግስት በምርጫው እንደማጭበርበር እንደለመደው በፖለቲካዊ ውሳኔ ከ እጩዎች ዘንድ እንዳይካተት መደረጉ ተጋልጧል:: ከታኅሣሥ ወር ጀምሮ በተሰጠው የሕዝብ ጥቆማ መሠረት ታሪካቸውና ሥራቸው ተሰብስቦ፣ በበጎ ሰው ሽልማት የምርጫ ሂደት ኮሚቴ የተመረጡት 45 ዕጩዎች ናቸው ብሎ መንግስት ካስቀመጣቸው ሰዎች መካከል ሁሉም መንግስት ራሱ እንዲሸለሙልኝ እፈልጋለሁ ያላቸውን እንዳጨ የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታውቀዋል:: ቴዲ አፍሮ በስነጥበብ የዓመቱ በጎ ሰው ዘርፍ የበርካታ ሕዝብ ድምጽን ቢያገኝም ከ እጩዎች ዝርዝር እንዲወጣ ተደርጓል:: ዘንድሮ መንግስት 9 ሰዎችን በሕዝብ ምርጫ እሸልማለሁ ቢልም ቅሉ ምርጫው ለመንግስት ፖለቲካ ቅርበት ያላቸው ሰዎችን የሚያካትት እንጂ ትክከለኛው የሕዝብ ጥቆማ እንዳልሆነ ታማኝ ምንጮች ይናጋራሉ:: ሕወሓት የሚመራው መንግስት በሕዝብ የተጠቆሙ ሰዎችን ትቶ በራሱ መንገድ ሕዝብ መረጣቸው ብሎ ያስቀመጣቸው ሰዎች ዝርዝራቸው የሚከተለው ነው፡፡ በ2007ዓም በልዩ ልዩ ዘርፎች ዕጩ የሆኑ በጎ ሰዎች በሳይንስ ምርምር ዘርፍ ዕጩዎች 


1. ፕ/ር ኢ/ር አበበ ድንቁ (አአዩ)
2. ኬሚካል መሐንዲስ ጌታሁን ሄራሞ
3. ዶክተር አበበ በጅጋ
4. ፕሮፌሰር አሥራት ኃይሉ
5. ዶ/ር ይርጉ ገ/ሕይወት (ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል) በሥነ ጥበብ ዘርፍ ዕጩዎች
1. አቶ አለ ፈለገ ሰላም
2. እማሆይ ጽጌ ማርያም ገብሩ
3. አቶ ተስፋየ አበበ(የክብር ዶክተር)
4. ሰዓሊ ታደሰ መስፍን
5. አባተ መኩሪያ በበጎ አድራጎት ዘርፍ ዕጩዎች
1. ወ/ሮ አበበች ጎበና
2. አቶ አስመሮም ተፈራ /ሲኒማ ራስ አካባቢ የተቸገሩትን የሚረዳ/
3. ስንታየሁ አበጀ (የወደቁትን አንሱ) እንጦጦ ማርያም አካባቢ)
4. አቶ አስፋው የምሩ /የአሠረ ሐዋርያት ት/ቤት መሥራች/ ዊንጌት አካባቢ
5. ትርሐስ መዝገበ በቢዝነስና ሥራ ፈጠራ ዘርፍ ዕጩዎች
1. አባ ሐዊ /አቶ ገብረ ሚካኤል (በትግራይ ክልል ለአብርሃ ወአጽብሐ አካባቢ ገበሬዎች ሥራ የፈጠሩ ገበሬ)
2. ሰላም ባልትና
3. አዋሽ ባንክ
4. ካፒቴን ሰሎሞን ግዛው
5. ካልዲስ ቡና በቅርስና ባሕል ዘርፍ ዕጩዎች
1. አቶ ዓለማየሁ ፋንታ
2. አቶ ሀብተ ሥላሴ ታፈሰ
3. አቶ ዓለሙ አጋ
4. EMML /HMML(የኢትዮጵያ የብራና መጻሕፍት ማይክሮ ፊልም ድርጅት)
5. ማኅበረ ቅዱሳን በማኅበራዊ ጥናት ዘርፍ ዕጩዎች
1. ፕ/ር ሪቻርድ ፓንክረስት
2. ደሳለኝ ራሕመቶ
3. ዶክተር ፈቃደ አዘዘ
4. ፕሮፌሰር ሺፈራው በቀለ 5. ፕሮፌሰር በላይ ካሣ በጋዜጠኛነት ዘርፍ ዕጩዎች
1. አቶ መዓርጉ በዛብህ
2. አቶ ያዕቆብ ወልደ ማርያም
3. አቶ ነጋሽ ገብረ ማርያም
4. ታምራት ገብረ ጊዮርጊስ(ፎርቹን ጋዜጣ)
5. ቴዎድሮስ ጸጋየ በስፖርት ዘርፍ ዕጩዎች
1. አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው
2. መምህር ስንታየሁ እሸቱ (ከበቆጅ ብዙ አትሌቶች እንዲወጡ ያደረገ መምህር)
3. መሠረት ደፋር
4. ኢንስትራክተር ሽፈራው እሸቱ
5. ዶክተር ወ/መስቀል ኮስትሬ መንግሥታዊ ኃላፊነትን በብቃት በመወጣት ዘርፍ ዕጩዎች 1. አቶ ግርማ ዋቄ(የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩ)
2. አቶ መኮንን ማን ያዘዋል
3. አቶ ሽመልስ አዱኛ
4. ዐማኑኤል የአእምሮ ሕክምና ሆስፒታል
5. ኢንጅነር ስመኘው በቀለ

tirsdag 11. august 2015

የቀድሞ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት መግለጫ አወጡ

ቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት፤ በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር ተበትነው እንደሚገኙ ይታወቃል። በውጭ አገር የሚገኙት እነዚህ የሰራዊቱ አባላት በቅርቡ ባደረጉት ስብሰባ፤ በቅርቡ በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላይ የተሰጠውን ውሳኔ ተቃወዋል። ዘረኛው የኢህአዴግ መንግስት ላለፉት 24 አመታት በህዝባችን ጫንቃ ላይ ተንሰራፍቶ በመቀመጥ እያደረሰ ያለውን መከራ መዘርዘር ግዜ ማባከን መሆኑን የገለጸው ይኸው መግለጫ፤ ህዝቡ ይህንን አምባገነን ስርአት ለማስወገድ በሰላማዊ መንገድ ለማካሄድ ቢሞክርም የህዝቡን ትግል እንደፍርሃት በመቁጠር ከፍተኛ ንቀት በማሳየታቸው ህዝቡ ወዳላስፈላጊ የትግል አቅጣጫ አምራቱን፤ መግለጫው አብራርቷል።
መግለጫው በማጠቃለያው ላይ፤ በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ የተሰነዘረውን ዘመቻ በመቃወም የቀድሞው የሰራዊቱ አባላት ከህዝቡ ጎን በመቆም የዜግነት ግዴታቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል።

lørdag 8. august 2015

ብአዴኖች ብቃት የተላበሰ አመራር የለንም ሲሉ አቶ አለምነው መኮንን ተናገሩ

የብአዴን የጽህፈት ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን ብአዴን የየተመሠረተበትን 35ዓመት ህዳር 11 ቀን 2008 ዓ.ም ለማክበር በማሰብ፣ ከሚዲያ አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ብአዴን የህዝቡን ፍላጎት የሚያሟላ ብቃት የተላበሰ አመራር የለውም ብለዋል። በግዮን ሆቴል ብአዴን በጠራው የሚዲያና ኮምኒኬሽን ባለሙያዎች የተሳተፉበት ስብሰባ ላይ ማብራሪያ የሰጡት አቶ አለምነው መኮንን፤ ብአዴን ያለበትን ተግዳሮቶች በዘረዘሩበት መግለጫቸው፣ ባለፉት 24 ዓመታት የህዝቡን ፍላጎት የሚያረካ የተሟላ የአመራር ብቃት አለመታየቱን አምነዋል፡፡

 «ሕዝቡ በመቶ ኪሎሜትር እየሄደ፣ አመራሩ በ80 ቢሄድ የ20 ኪሎሜትር ክፍተት አለ» በሚል በምሳሌ ያስረዱት አቶ አለምነው፣ በአመራር ብቃት በኩል ሕዝቡ የሚፈልገውን እርካታ ለማምጣት አልቻልንም ብለዋል። በክልሉ ፍትሐዊ አስተዳደርና ሕዝብ በየደረጃው የሚጠቀምበት አሰራር እንዲሁም ወጣቶችን በልማት ለማሳተፍና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ የተሰራው ስራ አመርቂ አለመሆኑን ባለስልጣኑ ተናግረዋል። ልማትን በተመለከተም በክልሉ ከአካባቢ አካባቢ ልዩነቶች አሉ ያሉት አቶ አለምነው፣ እንደየአካባቢው ባህርይ ልዩነት ማጋጠሙ የሚጠበቅ ቢሆንም የአካባቢዎችን ዕድገት ለማመጣጠን መስራት ይኖርብናል ብለዋል፡፡


ብአዴን የዛሬ 35 ዓመት በ38 ታጋዮች የጫካ ትግል መጀመሩን ያብራሩት አቶ አለምነው፣ ንቅናቄው ከ1973 አስከ 1983 በትጥቅ ትግል አምስት ክፍለጦሮችን ይዞ መቆየቱን፣ በአሁኑ ወቅት የንቅናቄው አባላት ቁጥር 1 ነጥብ 6 ሚሊየን መድረሱን በመግለጽ ንቅናቄው ከፍተኛ ስኬት አስመዝግቦአል ሲሉ በኩራት መንፈስ ተናግረዋል፡፡ የብአዴን ከፍተኛ አመራር አባል የሆኑበት የኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮምቴ ከአምስት ዓመት በፊት ያስቀመጠውን የአመራር መተካካት ወደጎን በመተው በዕድሜ መግፋትና በጤና ችግሮች ውስጥ ያሉ ነባር የድርጅቱ አመራሮች አሁንም በስልጣን ላይ ናቸው።

 በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ከፍተኛ ድርቅ በተነሳበት በዚህ ወቅት፣ ድርጅቱ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ በማውጣት ልደቴን አከብራለሁ ማለቱ በስፋት እያነጋገረ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ከአስር ሸህ በላይ የሚበልጡ የሂሳብ መዝገቦች ምርመራ ባለመደረጉ በንግድ ስራ የተሰማሩ ነጋዴዎች በስራችን ላይ ጫና እየተፈጠረብን ነው ሲሉ ተናግረዋል። የነጋዴዎቹ አቤቱታ ብአዴን ሰሞኑን ባደረገው ጉባኤ ላይ ቀርቧል። የክልሉ ገቢዎች ባለሰሰልጣን የታክስ ኦዲት ና የህግ ማስከበር ዋና ስራ ሂደት ዳይሬክተር አቶ ጠብቀው ወርቁ የክልሉ መንግስት ባዘጋጀው የምከክር መድረክ ላይ ” የነጋዴዎች ቅሬታ ትክለለኛ እና ፍርሃት ፈጣሪ ነው ” በማለት የችግሩን አሳሳቢነት ገልጸዋል።

 በሌላ በኩል ከፊደራል መንግስት ወደ ክልል መንግስታቶች በድጉማ መልክ የሚፈሰውን ገንዘብ በክልሎች በገቢ አቅም ለመተካት የሚሰራው ስራ ላፉት 25 ዓመታት አለመሳካቱ ተገልጿል። የፌደራል ገቢዎች ሚኒስቴር እንዳለው ክልሎች በተሰጣቸው ኮታ ልክ ገንዘብ ሰብስበው ራሳቸውን ባለመቻላቸው፣ መንግስትን በከፍተኛ እዳ ውስጥ ጥለውታል ብለዋል። በዚሁ ስብሰባ ላይ የሀገሪቱን ብድር ቀጣዩ ሶስት ትውልድ ከፍሎ አይጨርስውም ሲል የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ሚንስትር ተወካይ ገልጸዋል። ኢህአዴግ ካለፉት መንግስታት አራት እጥፍ የሚልቅ ገንዘብ ከውጭ መንግስታት እና እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ቢበደርም የአገሪቱ እዳ የመክፈል አቅም አነስተኛ በመሆኑ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገልጿል። ነኅሴ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና -

fredag 7. august 2015

የአርበኞች ግንቦት 7 አመራር ኤፍሬም ማዴቦ አስመራ ወርደው የትጥቅ ትግሉን ተቀላቀሉ




(ዘ-ሐበሻ) ከአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራሮች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ኤፍሬም ማዴቦ አስመራ ሄደው የትጥቅ ትግሉን
መቀላቀላቸው ተሰማ:: የአርበኞች ግንቦት 7 መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እንዲሁም አቶ ነአምን ዘለቀ አስመራ ወርደው ትግሉን ከተቀላቀሉ ሳምንታት የተቆጠረ ሲሆን አቶ ኤፍሬም ማዴቦም ከትናንት በስቲያ ትግሉን ተቀላቅለዋል::

 አርበኞች ግንቦት 7 በሕወሓት መንግስት ሠራዊት ላይ በሰሜን በኩል ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ አፍቃሬ ወያኔ ሚዲያዎች በሰሜን በኩል ትግል የለም ለማለት “የኢትዮጵያ መንግስት ሰራዊቱን ወደ ሱማሊያ አሰማራ” የሚሉ ዜናዎችን በማስተጋባት ላይ ይገኛሉ::

 ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ከአቶ ኤፍሬም በተጨማሪ ሌሎች ስማቸው ያልጠቀሰ የድርጅቱ አመራሮች ትልቅ ገቢ የሚያስገኝላቸው ሥራቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን በመተው የትጥቅ ትግሉን ተቀላቅለዋል::

  የዛሬ 25 ዓመት ወደ ስደት ገብተው በሰሜን አሜሪካ የተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተማሩት አቶ ኤፍሬም ከጆርጅ ሜሰን ዩኒቨርሲቲ በማዕረግ የተመረቁ ታዋቂ የፖለቲካ ሰው ናቸው::

torsdag 6. august 2015

ለአንዳርጋቸው ጽጌ መያዝ ምክንያት ናቸው ተብለው የሚጠረጠሩ የሕወሓት ቀኝ እጅ በአስመራ ተያዙ





ከወደ አስመራ አዳዲስ ወሬዎች እየተሰሙ ነው የመላዋ ኤርትሪያ የፀጥታ ኃላፊ በቁጥጥር ስራ ውለዋል::

ከዚህ በፊት ፕሬዝዳንት ኢሳይያስን ከስልጣን ለማውረድ አሲረዋል በሚል አስራ አምስት ባለስልጣናት ወህኒ አስገብተው የነበሩት የኤርትሪው የፀጥታ ሹም ተራቸው ደርሶ ወህኒ ወርደዋል፡፡

ከአስመራ እየወጡ ያሉ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የጸታው ሹም ለበርካታ ዓመታት የኤርትሪያን መረጃ ሙሉ በሙሉ ለኢትዮጵያ ሲያቀብሉ ኖረዋል በኤርትሪያ የወያኔ ተቃዋሚ የነበሩ ሰዎችን ወያኔ እያደነ ሲገድልና ሲያስር የነበረው በእኚሁ የፀጥታ ሹም መረጃ የተነሳ ነበር የወያኔን ባለስልጣናት ለመግደል አሲረዋል ተብለው ወህኒ የተጣሉት የአማራ ብሔር ተወላጅ የወያኔ ጄነራሎችን ሚስጥር ለወያኔ የሰጡት እኚሁ ሰው ናቸው::

የአንዳርጋቸው ፅጌ በወያኔ እጅ መውደቅ ሚስጥሩም በእኚህ ሰው እጅ ነው አጠቃላይ እኚህ ሰው ለወያኔ ወሳኝ ሰው የነበሩ ሲሆን ለኤርትሪያ ደግሞ ራስ ምታት የነበሩ ናቸው ግለስቡ በወንድማቸው ስም አዲስ አበባ ላይ ባለ አሥር ፎቅ ህንፃም ማስገንባታቸው አስመራ ላይ መነጋገሪያ ሆኗል::

 በኤርትራው ፕሬዝደንት ክፉኛ ጥርስ የተነከሰባቸው እኚህ ሰው ከትናንት በስቲያ ባልታወቀ ቦታ የታሰሩ ሲሆን በእኚህ ሰው መያዝ የወያኔ የፀጥታ መ/ቤት በመናጥ ላይ ነው ከትናንት ሐምሌ 27/97 ምሽት 5 ሰዓት ጀምሮ የህወሓት ከፍተኛ የጸጥታ ባለስልጣናት ምክር ላይ ናቸው ከዚህ በኋላ በኤርትሪያ በኩል ያለው የመረጃ መረባቸው ስለሚበጣጠስ የወያኔው አገዛዞች የአፈ ሙዝ ጨዋታቸውን ይጀመራሉ ተብሎም ተገምቷል፡፡

‹‹ ጊዜ የለም አዳራሹን ለቀህ ውጣ ››

በአንዲት ጎደሎ ቀን ም/ፕሬዝደንቱን ጨምሮ አስራ አምስት የኤርትሪያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ለኤርትሪያ ይበጃታል ያሉትን አንድ ቀና ነገር አሰቡ፤ ሃሳባቸውም ፕሬዝደንት ኢሳይያስን ከስልጣናቸው በፈቃዳቸው እንዲለቅቁ አድርገው በምትካቸው ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር ሊቀላቅላቸው የሚችል ትንሽ ትምህርት ቀመስ የሆነ ሰው በስልጣን ላይ ማስቀመጥ የሚል ነበር ይህንንም እቅድ ውስጥ ውስጡን ሲያበስሉት ቆዩና በመግቢያዬ እንደገለፅኩት በአንዲት ጎደሎ ቀን በኮድ ስሟ ‹‹ 011 ›› በተባለች አዳራሽ

ተሰብስበው ፕሬዝደንት ኢሳይያስን ይጠብቃሉ ሰዓቱ 21 ፡00 ሲል ፕሬዝደንቱ ወደ አዳራሹ ገቡ ገና መቀመጫቸው ወንበሩን ከመንካቱ ጥቂት ምስጢራዊ ሰዎች ብቻ የሚያውቋት ስልካቸው ተንጫረረች አነሷት የተደወለው ከሀገሪቱ የፀጥታ መስሪያ ቤት ከፍተኛ ባለስልጣን ከአብረሃ ካሳ ነበር ስልካቸውን ወደ ጆሮአቸው አስጠጉ ‹‹ ጊዜ የለም አዳራሹን ለቀህ ውጣ ›› የሚል መልእክት ሰሙ ፤ ፊታቸው አመድ መሰለ በቀስታ ዘወር ብለው በአዳራሹ የተሰበሰቡትን አስራ አምስት የኤርትሪያ ከፍተኛ ባለስልጣናትን በዓይናቸው ቃኟቸው ሠላሳ ዓይኖች አፍጥጠውባቸዋል፤ ሹልክ ብለው በመጡበት እግራቸው አዳራሹን ለቀው ወጡ ፡፡

 እነዚያ ለኤርትሪያ ሲሉ ስንት መስዋዕትነት የከፈሉ አንቱ የተባሉ ባለስልጣናት እጅና እግራቸው በካቴና ተጠፍንገው ጨለማ ቤት ተወረወሩ ታዲያ ያኔ መፈንቅለ መንግሥት ሊያደርጉብህ ነው ብለው አስራ አምስት ፊደላትን ብቻ በፕሬዝደንቱ ጆሮ አሰምተው አስራ አምስቱን ባለስልጣናት ያስበሉ የፀጥታው መ/ቤት ሹም አብረሃ ካሳ ዛሬ የወያኔ ሰላይ ሆነው በውል የተረጋገጠ 1. አዲስ አባባ ላይ ባለ አስር ፎቅ ህንጻ ፣ 2. ጋምቤላ ሰፊ እርሻ ፣ 3. አፍዴራ የጨው ማምረቻ እንዲሁም 4. አዲስ አበባ ቦሌ መድኃኒዓለም ጀርባ ቋሚ ነዋሪነቱን ሱዳን ካደረገ ነቢል አልቁሙስ (አል-ኩሙስ) ከተባለ ግብፃዊ ጋር በሽርክና ዓለም አቀፍ አስጎብኚ ድርጅት


በወንድማቸው ስም ከፍተው ቢዝነሱ ውስጥ ሲጨማለቁበት በምላሹም ወያኔዎች የኤርትሪያን ፣የግንቦት ሰባትን የአርበኞች ግንባርን መረጃዎች አንድ በአንድ ሲዘረግፉ ኖረው ተደርሶባቸው በተራቸው ጨለማ ቤት ተዘግቶባቸዋል በዚህ ሁኔታም የኤርትሪያ ፕሬዝደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ የሚይዙት የሚጨብጡት አጥተዋል ዛሬ 8/5/2015 ነሐሴ 29 ቀን 2007 ዓ.ም ከግለሰቡ ጋር ቅርብ ግንኙነት ያላቸው ዘጠኝ ሰዎች በቁጥጥር ሥር ሲውሉ የግለሰቡ ዘመዶችም ተጠቃለው በየማጎሪያው ገብተዋል በመጨረሻም አቶ ኢሳይያስ እንዲህ ሲሉ ተደምጠዋል ‹‹ ግድ የለም እናንተ ሆዳችሁን አስፉ እኛ ደግሞ አዲኳላን እናሰፋለን ›› አዲኳላ ምን ይሆን ?

tirsdag 4. august 2015

Obama and the circus of clowns in Ethiopia By Abebe Gellaw

The historic state visit of U.S. President Barack Obama to Ethiopia has just accomplished what was expected all along. On the one hand, TPLF and its cronies tried to use it as a spectacle full of absurdities, comedic political circus and amateurish propaganda. On the other hand, it was a golden opportunity for Ethiopia as the crimes of the regime were exposed at a global scale.
From the moment the U.S. President landed at Bole International Airport to his departure, there were disorganized roadshows that revealed a tyrannical clique running around like a headless chicken. While making the U.S. President stroll around on shabby doormats and rugs rolled out as “red carpets” may seem a side issue, it drew ridicule globally even from bloggers in Kenya, where he was accorded a stately and colorful welcome. But for the TPLF goons what mattered the most was the photo opportunity and the cheap propaganda.Obama and the circus of clowns in Ethiopia
The circus started at Bole International Airport, where ministers and senior government officials were head over heels pushing each other to see and touch Mr. Obama. They behaved as if they were kids fighting over candies. Communication minister Redwan Hussein, Deputy Foreign Minister Berhane GebreKristos and an unnamed lady who was running around like a clueless midfielder can take the trophies for their disgraceful manner and lack of self-respect as dignitaries.
But the positive outcome for the majority of Ethiopians was the fact that the repression and crimes of the TPLF junta were exposed at a global scale. Major U.S. and international media outlets have turned their cameras and sharpened their pens to expose the realities behind the hype. The crimes that the regime is committing against innocent journalists, dissidents and ordinary citizens with impunity were revealed for the world to see.
At a joint press conference with Obama came an opportunity for incompetent Hailemariam Desalegn. He was asked to explain Ethiopia’s record for being the second top jailer of journalists in Africa. It was a hard challenge that he could not coherently take up.
“Mr. Prime Minister,” said an African-American journalist. “The Committee to Protect Journalists ranks your country as the second worst jailer of journalists in Africa. Just before President Obama arrived here, some journalists were released. Many more are still being detained. Would you explain what issues or objections you have to a free press?”
Here is what he said verbatim: “As far as Ethiopia is concerned, we need journalists. We need more of them and quality of them [sic], because we have not only bad stories to be told, but we have many success stories that has [sic] to be told. And so we need you. This is very important. But we need ethical journalism to function in this country.
“And there is limitation capacity [sic] in all aspects of our works [sic]. There is also capacity limitations in journalism and that way [sic]. Maybe those of you who are in developed nations, you [sic] can help our journalists — domestic journalists — to increase their capacity to work on ethical manner [sic]. But the only thing as a leader of this nation we do not want to see is journalism has to be respected [sic] when it doesn’t pass the line [sic]; that working with violent terrorist groups is not allowed –even in the United States. And we need civilized journalism as a culture and as a profession.
“So I think my government is committed to this issue that we need many young journalists to come up and help this country to understand what’s going on. And for us, it’s very important to be criticized because we also get feedback [sic] to correct our mistakes and limitations. So we need journalists. And I think this is our view. And rest assured that we’ll continue to do so, because the media is one of the institutions that has to be nurtured for democratic discourse. And so that’s why we agree that institutional capacity-building in all aspects of democracy in this country is essential.”
What this can be translated into, despite the incoherence, is that they only need journalists that praise them, just like the ones working for state-run media outlets. The reality is that those working for the regime, as mouthpieces, are not even journalists. They do not have the right and freedom to report the truth as journalists. They can only do what they are told to do and echo the workshop speeches of TPLF officials.
Hailemariam was trying to say that those journalists that courageously speak out and expose the atrocities of the regime, corruption, abuse of power or human rights violations are “unethical terrorists”. Those who boldly criticize the regime will be locked up as it has been the fate of so many courageous journalists like Eskinder Nega, Reeyot Alemu, Wubishet Taye and Zone 9 bloggers, Muslim rights activists, just to mention a few among so many others.
Even if no one had asked him about capacity building, the ridiculous man appealed to the very journalist who raised the question to train and help “domestic” journalists. What a shame!
While President Obama highlighted efforts to deepen areas of cooperation, he also mentioned the need for the regime to guarantee basic freedom and human rights, as well as opening the political space that has been closed to opposition parties. In his address to African rulers, he singled out Ethiopia’s predicament. He said: “I believe Ethiopia will not fully unleash the potential of its people if journalists are restricted or legitimate opposition groups can’t participate in the campaign process.”
It is an open secret that the U.S. foreign policy is based on national interest. Such a narrowly-framed policy has undermined the claims of the United States as a paragon of freedom and human rights. Hanging out with the terrorists misruling Ethiopia will only backfire and have the unintended consequences. No power in the world can promote liberty, justice and dignity with empty rhetoric. It needs a resolve to act and consistently stand by those who are oppressed and abused by the criminals in power.
As a postscript, we may need to look at the billboards that adorned major streets in the capital. One of the billboards expressed gratitude to Obama: “Thank you for vesting Ethiopia!” Another one reads: “We Ethiopians loves you mach!” Apparently, a TPLF-connected cowboy businessman was paid over 1 million birr from the treasury. After all, Ethiopia is a nation run by corrupt 3rd graders.
For the privileged ones, there is not the need to learn how to spell before making big billboards for the whole world to see. After all, even the Prime Minister cannot form a few sensible and coherent sentences in front of the international media.
Here is my message to the “heroic” and shameless TPLF junta: “Excselent! Wat maters iz ze meni. Pliz ran awey bifor zey kech yu!”