ከወደ አስመራ አዳዲስ ወሬዎች እየተሰሙ ነው የመላዋ ኤርትሪያ የፀጥታ ኃላፊ በቁጥጥር ስራ ውለዋል::
ከዚህ በፊት ፕሬዝዳንት ኢሳይያስን ከስልጣን ለማውረድ አሲረዋል በሚል አስራ አምስት ባለስልጣናት ወህኒ አስገብተው የነበሩት የኤርትሪው የፀጥታ ሹም ተራቸው ደርሶ ወህኒ ወርደዋል፡፡
ከአስመራ እየወጡ ያሉ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የጸታው ሹም ለበርካታ ዓመታት የኤርትሪያን መረጃ ሙሉ በሙሉ ለኢትዮጵያ ሲያቀብሉ ኖረዋል በኤርትሪያ የወያኔ ተቃዋሚ የነበሩ ሰዎችን ወያኔ እያደነ ሲገድልና ሲያስር የነበረው በእኚሁ የፀጥታ ሹም መረጃ የተነሳ ነበር የወያኔን ባለስልጣናት ለመግደል አሲረዋል ተብለው ወህኒ የተጣሉት የአማራ ብሔር ተወላጅ የወያኔ ጄነራሎችን ሚስጥር ለወያኔ የሰጡት እኚሁ ሰው ናቸው::
የአንዳርጋቸው ፅጌ በወያኔ እጅ መውደቅ ሚስጥሩም በእኚህ ሰው እጅ ነው አጠቃላይ እኚህ ሰው ለወያኔ ወሳኝ ሰው የነበሩ ሲሆን ለኤርትሪያ ደግሞ ራስ ምታት የነበሩ ናቸው ግለስቡ በወንድማቸው ስም አዲስ አበባ ላይ ባለ አሥር ፎቅ ህንፃም ማስገንባታቸው አስመራ ላይ መነጋገሪያ ሆኗል::
በኤርትራው ፕሬዝደንት ክፉኛ ጥርስ የተነከሰባቸው እኚህ ሰው ከትናንት በስቲያ ባልታወቀ ቦታ የታሰሩ ሲሆን በእኚህ ሰው መያዝ የወያኔ የፀጥታ መ/ቤት በመናጥ ላይ ነው ከትናንት ሐምሌ 27/97 ምሽት 5 ሰዓት ጀምሮ የህወሓት ከፍተኛ የጸጥታ ባለስልጣናት ምክር ላይ ናቸው ከዚህ በኋላ በኤርትሪያ በኩል ያለው የመረጃ መረባቸው ስለሚበጣጠስ የወያኔው አገዛዞች የአፈ ሙዝ ጨዋታቸውን ይጀመራሉ ተብሎም ተገምቷል፡፡
‹‹ ጊዜ የለም አዳራሹን ለቀህ ውጣ ››
በአንዲት ጎደሎ ቀን ም/ፕሬዝደንቱን ጨምሮ አስራ አምስት የኤርትሪያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ለኤርትሪያ ይበጃታል ያሉትን አንድ ቀና ነገር አሰቡ፤ ሃሳባቸውም ፕሬዝደንት ኢሳይያስን ከስልጣናቸው በፈቃዳቸው እንዲለቅቁ አድርገው በምትካቸው ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር ሊቀላቅላቸው የሚችል ትንሽ ትምህርት ቀመስ የሆነ ሰው በስልጣን ላይ ማስቀመጥ የሚል ነበር ይህንንም እቅድ ውስጥ ውስጡን ሲያበስሉት ቆዩና በመግቢያዬ እንደገለፅኩት በአንዲት ጎደሎ ቀን በኮድ ስሟ ‹‹ 011 ›› በተባለች አዳራሽተሰብስበው ፕሬዝደንት ኢሳይያስን ይጠብቃሉ ሰዓቱ 21 ፡00 ሲል ፕሬዝደንቱ ወደ አዳራሹ ገቡ ገና መቀመጫቸው ወንበሩን ከመንካቱ ጥቂት ምስጢራዊ ሰዎች ብቻ የሚያውቋት ስልካቸው ተንጫረረች አነሷት የተደወለው ከሀገሪቱ የፀጥታ መስሪያ ቤት ከፍተኛ ባለስልጣን ከአብረሃ ካሳ ነበር ስልካቸውን ወደ ጆሮአቸው አስጠጉ ‹‹ ጊዜ የለም አዳራሹን ለቀህ ውጣ ›› የሚል መልእክት ሰሙ ፤ ፊታቸው አመድ መሰለ በቀስታ ዘወር ብለው በአዳራሹ የተሰበሰቡትን አስራ አምስት የኤርትሪያ ከፍተኛ ባለስልጣናትን በዓይናቸው ቃኟቸው ሠላሳ ዓይኖች አፍጥጠውባቸዋል፤ ሹልክ ብለው በመጡበት እግራቸው አዳራሹን ለቀው ወጡ ፡፡
እነዚያ ለኤርትሪያ ሲሉ ስንት መስዋዕትነት የከፈሉ አንቱ የተባሉ ባለስልጣናት እጅና እግራቸው በካቴና ተጠፍንገው ጨለማ ቤት ተወረወሩ ታዲያ ያኔ መፈንቅለ መንግሥት ሊያደርጉብህ ነው ብለው አስራ አምስት ፊደላትን ብቻ በፕሬዝደንቱ ጆሮ አሰምተው አስራ አምስቱን ባለስልጣናት ያስበሉ የፀጥታው መ/ቤት ሹም አብረሃ ካሳ ዛሬ የወያኔ ሰላይ ሆነው በውል የተረጋገጠ 1. አዲስ አባባ ላይ ባለ አስር ፎቅ ህንጻ ፣ 2. ጋምቤላ ሰፊ እርሻ ፣ 3. አፍዴራ የጨው ማምረቻ እንዲሁም 4. አዲስ አበባ ቦሌ መድኃኒዓለም ጀርባ ቋሚ ነዋሪነቱን ሱዳን ካደረገ ነቢል አልቁሙስ (አል-ኩሙስ) ከተባለ ግብፃዊ ጋር በሽርክና ዓለም አቀፍ አስጎብኚ ድርጅት
በወንድማቸው ስም ከፍተው ቢዝነሱ ውስጥ ሲጨማለቁበት በምላሹም ወያኔዎች የኤርትሪያን ፣የግንቦት ሰባትን የአርበኞች ግንባርን መረጃዎች አንድ በአንድ ሲዘረግፉ ኖረው ተደርሶባቸው በተራቸው ጨለማ ቤት ተዘግቶባቸዋል በዚህ ሁኔታም የኤርትሪያ ፕሬዝደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ የሚይዙት የሚጨብጡት አጥተዋል ዛሬ 8/5/2015 ነሐሴ 29 ቀን 2007 ዓ.ም ከግለሰቡ ጋር ቅርብ ግንኙነት ያላቸው ዘጠኝ ሰዎች በቁጥጥር ሥር ሲውሉ የግለሰቡ ዘመዶችም ተጠቃለው በየማጎሪያው ገብተዋል በመጨረሻም አቶ ኢሳይያስ እንዲህ ሲሉ ተደምጠዋል ‹‹ ግድ የለም እናንተ ሆዳችሁን አስፉ እኛ ደግሞ አዲኳላን እናሰፋለን ›› አዲኳላ ምን ይሆን ?
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar