fredag 7. august 2015
የአርበኞች ግንቦት 7 አመራር ኤፍሬም ማዴቦ አስመራ ወርደው የትጥቅ ትግሉን ተቀላቀሉ
(ዘ-ሐበሻ) ከአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራሮች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ኤፍሬም ማዴቦ አስመራ ሄደው የትጥቅ ትግሉን
መቀላቀላቸው ተሰማ:: የአርበኞች ግንቦት 7 መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እንዲሁም አቶ ነአምን ዘለቀ አስመራ ወርደው ትግሉን ከተቀላቀሉ ሳምንታት የተቆጠረ ሲሆን አቶ ኤፍሬም ማዴቦም ከትናንት በስቲያ ትግሉን ተቀላቅለዋል::
አርበኞች ግንቦት 7 በሕወሓት መንግስት ሠራዊት ላይ በሰሜን በኩል ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ አፍቃሬ ወያኔ ሚዲያዎች በሰሜን በኩል ትግል የለም ለማለት “የኢትዮጵያ መንግስት ሰራዊቱን ወደ ሱማሊያ አሰማራ” የሚሉ ዜናዎችን በማስተጋባት ላይ ይገኛሉ::
ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ከአቶ ኤፍሬም በተጨማሪ ሌሎች ስማቸው ያልጠቀሰ የድርጅቱ አመራሮች ትልቅ ገቢ የሚያስገኝላቸው ሥራቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን በመተው የትጥቅ ትግሉን ተቀላቅለዋል::
የዛሬ 25 ዓመት ወደ ስደት ገብተው በሰሜን አሜሪካ የተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተማሩት አቶ ኤፍሬም ከጆርጅ ሜሰን ዩኒቨርሲቲ በማዕረግ የተመረቁ ታዋቂ የፖለቲካ ሰው ናቸው::
Abonner på:
Legg inn kommentarer (Atom)
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar