søndag 24. februar 2019
mandag 11. februar 2019
የሶርያ ኃይሎች በአማፅያን ቡድን የተያዙ ቦታዎችን ማስመለሳቸውን ገለፁ
የካቲት 11, 2019
- ቪኦኤ ዜና

ፎቶ ፋያል
አስተያየቶችን ይዩ
በዩናይትድ ስቴትስ የሚደገፉት የሶርያ ዲሞክራስያዊ ኃይሎች እስላማዊ መንግሥት ነኝ በሚለው ፅንፈኛ የአማፅያን ቡድን ተይዘው የነበሩ 41 ቦታዎችን አስመልሰናል አሉ።
በዩናይትድ ስቴትስ የሚደገፉት የሶርያ ዲሞክራስያዊ ኃይሎች እስላማዊ መንግሥት ነኝ በሚለው ፅንፈኛ የአማፅያን ቡድን ተይዘው የነበሩ 41 ቦታዎችን አስመልሰናል አሉ። እስላማዊ መንግሥት ነኝ የሚለው ቡድን ከሚቆጣጠረው የመጨረሻ ምሽግ ለማባረር እየተዋጉ መሆናቸው ታውቋል።
"ሙስጣፋ ባሊ" የተባለው የሶርያ ዲሞክራስያዊ ኃይሎች ቃል-አቀባይ ባግሁዝ በተባለው መንደር የነበረውን የጽንፈኛው ቡድን ምሽግን አፍርሰናል ሲል በትዊተር አስታውቋል። ይሁንና ከባድ ውጎያ መቀጠሉን ሳይገልፁ አላለፈም።
ቀራፂ በቀለ መኮንን ስለ አፄ ኃይለ ሥላሴ ሐውልት ይናገራል

ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት መመስረት ጉልህ ሚና ከነበራቸው መሪዎች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሱት የግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ የመታስቢያ ሐውልት በአፍሪካ ሕብረት ቅጥር ጊቢ ውስጥ የካቲት 03/2011 ዓ.ም ተመርቋል።
በሥነ ሥርዓቱ ላይ የአፍሪካ ሕብረት አዲስ አበባ ውስጥ በሚያካሂደው 32ኛ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የመጡ የሃገራት መሪዎች እና የተጋበዙ እንግዶች ተገኝተዋል። የእርሳቸው ሐውልት መቆሙንም ተከትሎ በርካቶች ሲነጋገሩበት ነበር።
ሐውልቱን ከቀረፁት ቀራፂያን መካከል በግምባር ቀደምትነት የሚጠቀሱትን ሰዓሊና ቀራፂ እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሥነ ጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት መምህር የሆኑት ተባባሪ ፕሮፌሰር በቀለ መኮንንን አነጋግረናል።
ቢቢሲ፡ የቆመው ሐውልት ጃንሆይን አይመስልም የሚሉ አስተያየቶች ሲሰሙ ነበር። ለዚህ ያለህ ምላሽ ምንድን ነው?
በቀለ፡ አንድ ሥራ ተሰርቶ ሲጠናቀቅ ብዙ ዓይነት ሃሳብ እንደሚመጣ ይጠበቃል። ሃሳቦቹ ትክክል ናቸው ማለት ግን አይቻልም፤ እኔም ሰምቻቸዋለሁ። ስለዚህ ይህንን አስተያየት የሰጡት በሙሉ ንጉሡንም ሐውልቱንም አይተዋቸው አያውቁም።
ይህንን ሃሳብ ይዘው ሲጨቃጨቁ የነበሩት አንድ ተማሪ በስርቆሽ ያነሳውን የሐውልቱን ፎቶ ይዘው ነው፤ ዛሬ ላይ ሳይ ቀረብ ብለው ሐውልቱን የጎበኙ ሰዎች 'አፉ በሉን! 'እያሉ ሲለጥፉ አይቻለሁ። (ሳቅ) ፎቶ ሲነሳ ጥንቃቄና ሙያ ይጠይቃል እንግዲህ ንጉሡ አልፈዋል (ሳቅ) የቢቢሲው ጋዜጠኛ ያነሳውን ፎቶግራፍ ገፃችሁ ላይ አይተው በእርሱ መዳኘት ይችላሉ። የንጉሡ ቤተሰቦችም በእያንዳንዱ ሒደት ይጎበኙት ነበር፤ አሁን ባለውም ደስተኞች ናቸው።
ቢቢሲ፡ ሐውልቱን ለመስራት እንደ ሞዴል የተጠቀማችሁት ፎቶ ግን የትኛውን ነው?
በቀለ ፡ ከ300 ፎቶግራፎች በላይ ከተለያዩ ቦታዎች ተሰብስበው ስናጠና ነው ቆየነው፤ ቅርፅ ለመስራት አንድ ፎቶ ብቻ መጠቀም አይቻልም፤ በእርግጥ እርሳቸውን መግለፅ ይኖርበታል። አንድ እንግሊዛዊ ቀራፂ ንጉሡ በሕይወት እያሉ እንግሊዝ በቆዩበት ጊዜ አጠገባቸው ሆኖ እያየ ሁለት ሦስት መልክ ያለው ሐውልት ሰርቷል። የጥበብ ሥራ በመሆኑ ቅርፁን ስታይው ጃንሆይን አይመስሉም።
በመሆኑም በአፍሪካ ኅብረት ምስረታ ጊዜ የነበሩ ፎቶግራፎች ብዙ ናቸው። ወደ 100 የሚሆኑ በአፍሪካ ህብረት ምስረታ ወቅት የነበሩ ፎቶዎችን ሰብስበናል። እንግዳ ሲቀበሉና ስብሰባ ሲያደርጉ የሚለብሷቸው ልብሶችና የሚገልጿቸው አካላዊ ገለፃዎች ላይ ተመስርቶ ተሰራ እንጂ የአንድ ፎቶግራፍ ውጤት ብቻ አይደለም።
ቢቢሲ ፡ የተጠቀምከው ጥበባዊ ግነት አለ?
በቀለ፡ በትክክል! እጃቸውና ደረታቸው ላይ፤ ደረታቸው አካባቢ ገነን ለማድረግ ሞክረናል። የጠቢቡ ነፃነት የሚባል ነገር አለ አይደል? በማይበላሽና ከስርዓት በማይወጣ መንገድ ገነን ለማድረግ ሞክረናል። ሌላው ሰውነታቸው መለስ ይላል። በእርግጥ በአካልም እንደዚህ ነበሩ፤ እጃቸውንም ሲፅፉ እንደሚታየው፤ እኛም ዳቦ ስንቀበል እንዳየነው ሎጋ ቀጠን ቀጠን ያሉ ጣቶችን በማድረግ የምንችለውን ሁሉ አድርገናል።
ቢቢሲ፡ ሐውልቱ ከምንድን ነው የተሰራው?
በቀለ፡ የተሰራው ከነሃስ ነው።
ቢቢሲ፡ በቀላሉ በዝናብና በፀሀይ እንዳይበላሽ የተለየ ጥበብ ተጠቅማችኋል ?
በቀለ፡ ነሃስ የሚመረጠው ለዚህ ነው፤ ዓለም ላይ ለልዩ ጉዳዮች ካልሆነ በስተቀር የህዝብ ሐውልቶች ብዙ ጊዜ የሚሰሩት በነሃስ ነው። በነሐስ እንዲሰሩ የሚፈለገው በውስጣቸው ያለው አብዛኛውን የሚይዘው መዳብ ነው፤ መዳብ ደግሞ ኦክስጅን ስለሚይዝ አሮጌ ሲሆኑ የሻገተ አረንጓዴ ይሆናሉ።
እናም ኦክስጅን እንዲስብ አድርገን ነው የሰራነው ይህም አካበባቢውን እንዲመስልና በጊዜ ሂደት መልኩ እንዲለወጥ ይፈለጋል...ያ እንዲሆን አድርገን ነው የምንሰራው። ጠንካራ ብረትም ስለሆነ አይሰበርም አይሸማቀቅም፤ ነገር ግን ኦክስጅን ይወስዳል... ልክ መዳብ ያላቸው ሳንቲሞች ሲቆዩ እንደሚፈጥሩት ቀለም ዓይነት፤
ቢቢሲ፡ ቀመቱና ክብደቱ ምን ያህል ነው?
በቀለ ፡ ከነመቆሚያው ወደ ሦስት ሜትር ነው። ይህም የእርሳቸውን ቁመት ሁለት እጥፍ ይሆናል ማለት ነው። ክብደቱ ደግሞ ከ650 እስከ 680 ኪሎግራም ይመዝናል። በትክክል ይታወቃል ነገር ግን ሲበየድ የተጨመሩ የብየዳ ብረቶች ኪሎ ስለሚጨምር ነው የ30 ኪሎ ግራም እንደ ግምት የተቀመጠው።
ቢቢሲ፡ የት ነው የተሰራው?
በቀለ፡ የሸክላ ሞዴሉ አዲስ አበባ የኒቨርሲቲ ሲሆን ቀሪው ሥራ የተከናወነው እንግሊዝ ኤምባሲ አካባቢ በተከራየነው ቤት ነው። ቁርጥራጮቹን ይዘን የመጨረሻውን ሞዴል የሰራነው በእኔ ስቱዲዮ ውስጥ ነው።

ቢቢሲ፡ ሐውልቱ ተቀርፆ ለመጠናቀቅ ምን ያህል ጊዜ ፈጀ?
በቀለ፡ እንደሌሎች አገራት ለጥበብ ሥራዎች የሚሆኑ ግብዓቶች የማግኘት እድሉ ባለመኖሩ ረዘም ያለ ጊዜ ፈጅቶብናል ... ስድስት ወር አካባቢ ነው የፈጀው።
ቢቢሲ ፡ ሥ ራው ወደ እናንተ የመጣው እንዴት ነበር ?
በቀለ፡ እኔ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነው የማስተምረው፤ እኔን ቢያነጋግሩኝም በዩኒቨርሲቲው ያሉ ባለሙያዎችን በቡድን ነው ስንሰራ ቆየነው። ፕሮፌሰር ዘይኑ፣ ተመራቂ ተማሪ የሆነው አቶ ሔኖክ አዘነና ሌሎች በነሃስ ጥበብ ላይ ሙያ ያላቸው ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል።
ቢቢሲ፡ ምን ያህል ገንዘብ ወጣበት?
በቀለ፡ ብዙ ነው የፈጀው... እ... እስካሁን አልደመርኩትም ብዙ ገንዘብ ነው የወጣበት። ገንዘብ ብቻ ሳይሆን ተፈላጊውን ውጤት ለማምጣት የሰው ጉልበትም በጣም የበላ ነው።
ቢቢሲ፡ እንደው ገንዘቡን ከእዚህ እስከዚህ ብሎ ማስቀመጥ ይቻላል?
በቀለ፡ ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ ነው፤ ለሂደቱ የሚያስፈልጉ ኬሚካሎች አሉ አገር ውስጥ የሌሉ... ቁሳቁሶች አሉ .. በጣም ብዙ ነገሮች አሉ ...
ቢቢሲ፡ እንደው በትክክል ባይሆንም ስንት አወጣ ማለት እንችላለን?
በቀለ፡ ከ1.5 ሚሊየን ብር በላይ ነው ለማቴሪያል ብቻ የወጣው።
ቢቢሲ፡ ምን ያህል ነው የተከፈላችሁ?
በቀለ ፡ ታክስ ይኖራል... ገና ነው ...ሰርተን ያስረከብነውም ሰሞኑን ስለሆነ ቀስ ብለን የምናየው ነው የሚሆነው ...ብዙ ገንዘብ አይኖረውም ትንሽ ስለሆነ፤ የሥራውን ጥበባዊም ሆነ የሰው ኃይል ዋጋውን እንደማይመልስ ግን አረጋግጣለሁ።
ቢቢሲ፡ የገጠማችሁ ተግዳሮት ምንድን ነው?
በቀለ፡ ብዙ ነገር የተሳካ ነበር ማለት ይቻላል፤ የግብዓት ጉዳይ ግን እጥረት ሳይሆን ሙሉ በሙሉ ጠፋ ማለት ይቀላል። ከእርሳስ አቅም እራሱ አላሰራ እስኪል ድረስ ... ልክ የጋፋት የቴዎድሮስ ሰዎች አፈር አቅልጠው ብረት ሥሩ እንደተባሉት ዓይነት ነገር ነው። ብቻ በጥንታዊው መንገድም ቢሆን ብዙ የሰው ኃይል በመጠቀም ወደሚፈለገው ነገር መጥተናል።
ቢቢሲ ፡ የሐውልቱን ወ ጪ የሸፈነው ማነው?
በቀለ ፡ ኢትዮጵያን ወክሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው።
ቢቢሲ፡ ሌላ ተባባሪ አካል የለም?
በቀለ፡ እኛ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ነው የምንገናኘው
ቢቢሲ፡ ከዚህ በፊት በሌሎች አገራት ከተሰሩት የቀዳማዊ ኃይለ ሥ ላሴ ሐውልቶች ይህን ለየት የሚያደርገው ምንድን ነው?
በቀለ፡ በዚህ መጠን ሙሉ ነሃስ ተሰርቶ አያውቅም። የትም አገር፤ የትም ቦታ! የእርሳቸውን መጠን ሁለት እጥፍ ተሰርቶ አያውቅም እሱ ነው ለየት የሚለው።
ቢቢሲ፡ ሐውልቱ መቆሙን ተከትሎ የተቃውሞና የድጋፍ ሀሳቦች እየተንሸራሸሩ ነው፤ ይህንን እንዴት ትመለከተዋለህ?
በቀለ ፡ ኖርማል ነው... ጤና ነው ብዬ ነው የማስበው። ሰው አንድ ዓይነት አይደለም። አንድ ዓይነት አለመሆኑም ጥሩ ነው፤ አንዳንዴ የኛ የሚከፋው እ... ነገራችንን ሁሉ የክፋት የክፋት መንገዱን ሁሉ እየነቀስን እየነቀስን.. እዚች አገር አንድም ጥሩ፣ እንድም ደግ፣ አንድም አዋቂ፣ አንድም ፃድቅ እንዳይኖር እስከማድረስ ድረስ እንሄድና ፅንፋዊ ሆነን ራሳችን ማጥፋታችን ነው እንጂ የሚከፋው... እየሱስም ተቃዋሚ ነበረው አይደል ? ተቃዋሚ መኖሩ አይደለም ክፋቱ እኔ ከሌለሁበት ሁሉንም ነገር ይጥፋ የሚል ነገር አለብን፤ እሱ ነው ክፉ ነገር እንጂ የተወሰኑ ሰዎች ቢቃወሙ ጤነኛ ነገር ነው ብየ አስባለሁ።
በተለይም እርሳቸው ከሄዱ በኋላም ብዙ የሰራናቸው ያጠፋናቸው ነገሮች አሉ። እነርሱን የምንቆጥር ከሆነ እንዳልኖርን ነው የሚቆጠረው፤ ቢያንስም ቢበዛ ደግ ደጉን ስናነሳ ነው እንደ እድሜ የምንቆጥረው ጊዜውን...
ቢቢሲ፡ ሐውልቱ በመቀረፁ እንደ ግለሰብ ምን ተሰማህ?
በቀለ ፡ ልጅም ሆኜ ቢሆን አስታውሳቸዋለሁ ከእጃቸው ዳቦና ብር ተቀብያለሁ፤ ብዙ ጊዜ አይቻቸዋለሁ። ታሪካቸውንም እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ አውቃለሁ፤ ትልቅና ኢትዮጵያን ያኮሩ ሰው አንደሆኑ፣ በተለይ ከእርሳቸው በኋላ ኢትዮጵያ ምን እንደሆነች እንደኛ ኖሮ ለሚያውቅ ሰው ቢመለከት ከእርሳቸው ምን እንደታጣ ማመዛዘን ስለሚችል ይህን ሁሉ ስታስቢ እንዴት ደስ ላይል ይችላል?
ቢቢሲ፡ ስለ እርሳቸው ምን ትውስታ አለህ?
በቀለ፡ እንግዲህ ተወልጄ ያደኩት ደብረዘይት ነው፤ አሁንም ከደብረዘይት አልተነጠልኩም፤ ጃንሆይ ደብረ ዘይት በየሳምንቱ ይመጡ ነበር። ለመዝናኛ ይመርጧታል።
ያኔ ከዘጠኝ ዓመት አንበልጥም ያን ጊዜ ሕፃናት ተሰልፈን ስንጠብቃቸው እንግዳ ያዙም አልያዙም ይቆማሉ፤ ቆመው ብርና ዳቦ ይሰጡናል። አርብ አርብ ደብረዘይት ቅዳሜና እሁድን ለማሳለፍ እንዲሁም ለማስቀደስ ይመጣሉ፤ እንጠብቃቸዋለን።
የእጃቸው ስስነት ያ የሚነገርላቸው ግርማ ሞገስ በተለየ ዓይን ነበር የምንመለከታቸው። እቤት ደግሞ ገንዘቡን ስንሰጥ የብዙ ልጆች እናት ገንዘቡ በረከት እንዲኖረው ተብሎ ከእንጀራ ስር ይቀመጣል።
ይህ ሕብረተሰቡ ምን ያህል ለንጉሡ ታማኝ እንደነበረ የሚያሳይ ነው። ዓለምም እንደዚህ ነው የሚያያቸው፤ ምንም ይሁን ምን ብዙ ታሪክ ያላቸው ሰው ናቸው።
fredag 6. juli 2018
ሰበር ዜና….ብጹዕ አቡነ ማቲያስ ስልጣናቸውን በሚቀጥሉት ሳምንታት በፈቃዳቸው ሊለቁ ነው

ባለፈው ሳምንት ሲካሄድ የነበረውና ለአራት ቀናት ያክል የተካሄደው 36ኛውየሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ ላይ ከሌሎች ጳጳሳትና ከቤተክህነት አስተዳደር ጋር በአደባባይ እስጥ አገባ ውስጥ ያሳለፉት አቡነ ማትያስ በጉባዔው ጣልቃ ስልጣናቸውን ለመልቀቅ እንደሚፈልጉ ለቅርብ ሰዎቻቸው ተናግረዋል። በቤተክህነቱ አካባቢ ስልጣናቸውን የሚገዳደሩና የማይታዘዟቸው እየበዙ በመምጣታቸው ክፉኛ የተበሳጩት አቡነ ማቲያስ በመጪው ጊዜ በሚጀምረው የሲኖዶሱ ጉባዔ ላይ መልቀቂያ ማቅረብ እፈልጋለሁ ብለዋል። የፓትርያርኩ እርምጃ ያሳሰበው መንግሥት ፓትርያርኩ ሀገሪቱ ያለችበትን አስቸጋሪ ሁኔታ አጢነው ስልጣን ከመልቀቅ ይልቅ በውይይት ችግሮችን እንዲፈቱ ከማክሰኞ ምሽት ጀምሮ አንድ ቡድን በመላክ እያግባባቸው ነው።
አቡነ ማትያስ የቤተክርስቲያኒቱ የወንጌል ማስፋፋትና ትምህርት አንድ አሀድ ከሆነው ማኀበረ ቅዱሳን ጋር የተካረረ ውዝግብ ውስጥ የቆዩ ሲሆን መንግሥት ማኅበሩን እንዲዘጋው እስከመጠየቅ ደርሰዋል። ማኀበሩ በቅርቡ የጀመረውን የቴሌቭዥን ስርጭትም ህገወጥ በመሆኑ ሊታገድ ይገባል ባይ ናቸው አቡነ ማትያስ። ፓትርያርኩ ለአራት ቀናት በተካሄደው የመንፈሳዊ ሰበካ ጉባዔ ላይ የማኅበረ ቅዱሳን ተወካዮች እንዳይካፈሉ ትዕዛዝ ሰጥተው ማኅበሩን እንዳይሳተፍ ማድረግ ቢችሉም የቤተክህነት አስተዳደርና ሌሎች ገዳማት የማኅበረ ቅዱሳንን ሚና የሚያጎላና የሚያወድስ ሪፖርት ማቅረባቸው አቡነ ማትያስን አስከፍቷቸዋል።
ጉባዔው ማኅበረ ቅዱሳንን ከማውገዝ ይልቅ ለቤተክርስቲያኒቷ አለኝታ የሆነና ድጋፍ ሊደረግለት የሚገባ መሆኑንም የተናገሩ አባቶች ነበሩ። በአራቱ ቀን ጉባዔ ከአቡነ ፋኑኤል ጋር የከፋ የቃላት ልውውጥ ያደረጉት ፓትርያርኩ ብዙውን ጊዜ በዝምታና በማኩረፍ እንዳሳለፉ ከጉባዔው ተሳታፊዎች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የውዝግቡን መካረር ተከትሎ መንግሥት የጉባዔውን ሂደት በቅርብ ሲከታተል የቆየ ሲሆን በማጠቃለያ የአቋም መግለጫ ላይ የማኅበረ ቅዱሳን የቴሌቭዥን ስርጭት “ህገ- ወጥ” መሆኑን የሚገልፅ አንቀፅ ከጉባዔተኛው ስምምነት ውጪ እንዲጨመር መደረጉ ብዙዎችን አሳዝኗል። አንቀፁ የተጨመረው አቡነ ማትያስን “ተሰሚ” አድርጎ ለመሳል “በትዕዛዝ” የተካተተ እንደሆነ ከቃለጉባዔ መዝጋቢዎች ተሰምቷል።
አቡነ ማትያስ
ምንጭ አንድነት ጋዜጣ
ነፃነት ተጎናፅፈናል የብልፅግና ጉዞም ተጀምሯል ለወጡን እንጠብቅ! (ታዬ ደንዳዓ
ለኢትዮጵያ ህዝብ
ለወጡን እንጠብቅ! (ታዬ ደንዳዓ)
እንደ ህዝብ እና እንደ ሀገር ፍላጎታችን ነፃነት እና ብልፅግና ነዉ። ይህ ያልተሳካልን በእርግማን ሳይሆን ከጅቦች አገዛዝ ራሳችንን ማላቀቅ ባለመቻላችን ነዉ። አሁን ነፃነት ተጎናፅፈናል። የብልፅግና ጉዞም ተጀምሯል። ክብር እና ዕድሜ ለዶር አብይ እና ለጓዶቻቸዉ! በሦስት ወር ጊዜ ዉስጥ በጣም ብዙ ለዉጥ አይተናል። በዝህ ፍጥነት በሁለት እና ሦስት ዓመታት በሀገራችን መሠረት ያለዉ ሠላም፣ ዴሞክረሲ እና ልማት ይገነባል። ለዝህ ላበቁን ቄሮዎች፣ ፋኖዎች እና ዘርማዎች ክብር ይገባል።
ለወጡን እንጠብቅ! (ታዬ ደንዳዓ)
እንደ ህዝብ እና እንደ ሀገር ፍላጎታችን ነፃነት እና ብልፅግና ነዉ። ይህ ያልተሳካልን በእርግማን ሳይሆን ከጅቦች አገዛዝ ራሳችንን ማላቀቅ ባለመቻላችን ነዉ። አሁን ነፃነት ተጎናፅፈናል። የብልፅግና ጉዞም ተጀምሯል። ክብር እና ዕድሜ ለዶር አብይ እና ለጓዶቻቸዉ! በሦስት ወር ጊዜ ዉስጥ በጣም ብዙ ለዉጥ አይተናል። በዝህ ፍጥነት በሁለት እና ሦስት ዓመታት በሀገራችን መሠረት ያለዉ ሠላም፣ ዴሞክረሲ እና ልማት ይገነባል። ለዝህ ላበቁን ቄሮዎች፣ ፋኖዎች እና ዘርማዎች ክብር ይገባል።
ጅቦች ግን እያዛጉ ነዉ። ነፃነታችንን አይፈልጉም። የነሱ ብልፅግና በችጋራችን ላይ የተመሠረተ ነዉ። ስለዝህ ለዉጡን ቀልብሰዉ ወደነበርንበት ሊመልሱን እየተሯሯጡ ነዉ። ሩጫቸዉ በሁለት አቅጣጫ ነዉ። አንደኛዉ ሠላም ማደፍረስ ነዉ። በዝህ ረገድ ሰዉን ለመግደል እና ንብረት ለማዉደም ቅጥረኛን አሰልጥነዉ ከብዙ ገንዘብ ጋር አሰማርቷል። በተለያዩ ቦታዎች በየቀኑ ቦምብ እየተያዘ ነዉ። በየቦታዉ ሰዉ ሲሞት እና ንብረት ሲወድም ስጋት ይሰፍናል። የኢትዮጵያ ህዝብ ሠላም ካጣ የዶር አብይን አስተዳደር ጠልቶ የጅቦችን አገዛዝ ይመኛል። ያኔ ጅብ የሚፈልገዉን ያገኛል።
ሁለተኛዉ ደግሞ የኢኮኖሚ አሻጥር ነዉ። ጅቦች በተደራጀ ሌብነት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በበላይነት ተቆጣጥሯል። ብዙ ሸቀጦች በእነሱ እጅ ነዉ። ይህን አቅም በመጠቀም የገበያን ነፃ ዉድድር ለማወክ አቅዷል። ገባያ ሲዛባ አርተፍሻል እጥረት ይፈጠራል። ይህ ህዝብን ለረሀብ ይዳርጋል። ህዝብ ደግሞ ሲራብ በዶር አብይ አስተዳደር ላይ ይነሳል። በዝህ መሀል ጅብ ወደ ስልጣኑ ይመለሳል። ስሌቱ ይህን ይመስላል።
ስለዝህ ምን እናድርግ? ዋናዉ ጉዳይ ይህ ነዉ። ተጨማሪ ነፃነትን እንጅ ባርነትን አንሻም! ያገኘነዉን ዉጤት ለማስጠበቅ እና ተጨማሪ ስኬት ለማስመዝገብ ደግሞ ሁላችንም የበኩላችንን አስተዋፅኦ ማድረግ አለብን።
1. እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በያለበት የሀገሩ ደህንነት ሆኖ የጅቦችን እንቅስቃሴ በአንክሮ መከታተል አለበት። አዲስ ነገር ባዬ ጊዜ በመረጃ አስደግፎ ለፀጥታ አካላት ያሳዉቅ። ሰላማችን በእጃችን ላይ ነዉ።
2. የኢኮኖሚ ችግርን በተመለከተ
ሀ. አያንዳንዳችን አሻጥረኞችን እንከታተል። ችግር ከተከሰተ ተጠያቂዉ መንግስት ሳይሆን የቀን ጅብ መሆኑ ከወዲሁ ይታወቅ።
ለ. ሀገር ወዳድ በለሀብቶች የሚፈጠሩ ክፍተቶችን ለመሙላት ከወዲሁ ዝግጅት ያድርጉ።
ሐ. መንግስት ችግሮችን ወደ ዕድል ይቀይር። የኢኮኖሚ አሻጥረኞችን በጥብቅ ተከታትሎ ንብረታቸዉን በመዉረስ ለህዝብ ጥቅም ያዉል። በቦታቸዉ ደግሞ ስራ አጥ ወጣቶችን አሰልጥኖ እና አደራጅቶ ያስገባ። ጫዉ ለራሱ ሲል ይጣፍጣል።
3. የኢትዮጵያ የፀጥታ ሀይል አባላት ከህዝብ ጋር እጅና ጓንት በመሆን ለሀገራቸዉ አንድነት እና ሠላም ዘብ መቆም አለባቸዉ።
ህብረታችን የማይንደዉ ተራራ የለም! የተባበረ ህዝብ ሁሌም አሸናፊ ነዉ!
ሠላም ዋሉ!
ስለዝህ ምን እናድርግ? ዋናዉ ጉዳይ ይህ ነዉ። ተጨማሪ ነፃነትን እንጅ ባርነትን አንሻም! ያገኘነዉን ዉጤት ለማስጠበቅ እና ተጨማሪ ስኬት ለማስመዝገብ ደግሞ ሁላችንም የበኩላችንን አስተዋፅኦ ማድረግ አለብን።
1. እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በያለበት የሀገሩ ደህንነት ሆኖ የጅቦችን እንቅስቃሴ በአንክሮ መከታተል አለበት። አዲስ ነገር ባዬ ጊዜ በመረጃ አስደግፎ ለፀጥታ አካላት ያሳዉቅ። ሰላማችን በእጃችን ላይ ነዉ።
2. የኢኮኖሚ ችግርን በተመለከተ
ሀ. አያንዳንዳችን አሻጥረኞችን እንከታተል። ችግር ከተከሰተ ተጠያቂዉ መንግስት ሳይሆን የቀን ጅብ መሆኑ ከወዲሁ ይታወቅ።
ለ. ሀገር ወዳድ በለሀብቶች የሚፈጠሩ ክፍተቶችን ለመሙላት ከወዲሁ ዝግጅት ያድርጉ።
ሐ. መንግስት ችግሮችን ወደ ዕድል ይቀይር። የኢኮኖሚ አሻጥረኞችን በጥብቅ ተከታትሎ ንብረታቸዉን በመዉረስ ለህዝብ ጥቅም ያዉል። በቦታቸዉ ደግሞ ስራ አጥ ወጣቶችን አሰልጥኖ እና አደራጅቶ ያስገባ። ጫዉ ለራሱ ሲል ይጣፍጣል።
3. የኢትዮጵያ የፀጥታ ሀይል አባላት ከህዝብ ጋር እጅና ጓንት በመሆን ለሀገራቸዉ አንድነት እና ሠላም ዘብ መቆም አለባቸዉ።
ህብረታችን የማይንደዉ ተራራ የለም! የተባበረ ህዝብ ሁሌም አሸናፊ ነዉ!
ሠላም ዋሉ!

lørdag 26. mai 2018
የኢትዮጵያ ትግልና የአንዳርጋቸው ጽጌ ግንኙነት ለምን የቁርባን ግንኙነት ሆነ?! (መስቀሉ አየለ)
መስቀሉ አየለ
የአንዳርጋቸው አባት አቶ ጽጌ ስድስት እህትና ወንድሞቻቸውን አይናቸው እያየ ለጣሊያን ባደሩ ባንዳዎች እንደ አይሲስ በገጀራ ሲታረዱ እሳቸውና አንዲት እህታቸው ብቻ ነበሩ የተረፉት። እህቲቱ ባዩት ሁኔታ ልባቸው ከተሰበረበት አልጠገን ብሎ ከሰው ሳይነጋገሩ፣ በህጻንነታቸው መንኩሰው በዘጠና አመታቸው ሞቱ። አቶ ጽጌ ግን አርበኞቹን የሚመሩ አንድ የታወቁ ደጃዝማች አግኝተዋቸው ለአንድ ጉራጌ ገበሬ ደብዳቤ ጽፈውና ማህተም አትመው ጦርነቱ እስኪያልቅ ድረስ አደራ ሰጥተዋቸው ወደ ግንባር ሄደዋል።ያን ግዜ ብላቴናው ጽጌ እድሜያቸው ስድስት ወይንም ሰባት ቢሆን ነው፤እርግጡን አላውቀውም; እንደ እከሌ ልጅ ባክል ነው ይላሉ።
ጦርነቱ ሲያልቅ አርበኛው ደጃዝማች አልተመለሱም።ስለሆነም ባንዲራ ስትነሳና ንጉሱ ወደ አገር ውስጥ ሲመለሱ የጉራጌው ባላባት አራት አመት ሙሉ የያዙዋቸውን አቶ ጽጌን አዲስ አበባ ወስደው ንጉሱ ከቤተክርስቲያን ሲመለሱ እግራቸው ስር ተደፍተው አቤት አሉ፤ “ምን ሆነሃል?” ሲባሉ ደብዳቤውን እና “ብላቴናውን ጼጌ ሃብተማርያምን ተረከቡኝ፤ ስመ እግዚአብሔር ጠርቸ የተቀበልኩት አደራ ነው” አሉ። ታሪካቸው ቢነበብ ልብ የሚነካ ሆኖ ተገኘ። ደጃዝማቹም በህይወት አልተመለሱምና ንጉሱ ብላቴናውን በጉዲፈቻ ተቀብለው አዳሪ ትምህርት ቤት አስገቡዋቸው። የመጀመሪያውም የፊደል ሰራዊት አባል ሆነው ትምህርታቸውን አጠናቀቁ።
አቶ ጽጌ ሃብተማርያም በቀይ ሽብር ዘመን እንደገና የአንድ ልጃቸውን አስከሬን በመቶ ብር ገዝተዋል፤ ራሳቸውም ተሸክመው ከእስር ቤት እንዲያወጡ ተገደዋል። በዚህም የተነሳ በዚህች አገር ላይ ያለው ውስብስብ ፖለቲካ አንዳርጋቸውን በአባቱ በኩል ዘር አልባ አድርጎ አስቀርቶታትል። እርሱ ዘር ማንዘሮቹ ዋጋ በከፈሉበት አገር የባንዳዎቹ የልጅ ልጆች ደግሞ እርሱን አስረው በክፋታቸው ልክ እልሃቸውን ተወጥተውበታል። የአንዳርጋችውም ጽናቱ ፣ስለ አገርና ነጻነት ያለው ጥልቅ ፍልስፍና እንዲሁም አርባ አመት ሙሉ ያደረገው ያልተቋረጠ ተጋድሎ ይህን እየሰማና እያየ ማደጉ ነው። አረጋዊው ጽጌ ሃብተ ማርያምም ሶስት እሩቡን ወጥተው በአራተኛው እሩብ የእድሜ መገዳደጃ ላይ ማረሚያ ቤት ደጃፍ ቆመዋል ስንል ግብግቡ የተጀመረው ከሶስት ትውልድ በፊት ነው ለማለት ነው።መለስ ዜናዊ ይኼንን ስለሚያውቅ ቤተሰቡን በሙሉ “The Militant Family” ብሎ ይጠራው ነበር ።
torsdag 26. april 2018
Ethiopia: A Call for Worldwide Remittance Embargo
To all Ethiopians who are concerned about the dire fate of our country and eager in shortening the suffering of our people under the brutal Woyane regime.
Credible evidences coming from various sources indicate that the TPLF-led regime is immersed in a major political, economic, and security crises. It has come to light that, by all indicators and measures, the regime is in big economic collapse.
A recently leaked document authored by the so-called National Security Council confirms the regime’s anxiety about the economic crisis it has faced in recent months. This document admits that:
- Foreign aid has been reduced due to the regime’s worst human rights record;
- Tourism has shrunk due to the instability throughout the country;
- Wealthy people and foreign investors have started migrating their money out of the country; and
The regime is therefore convinced that these and other factors are contributing to the general economic crisis.
Meanwhile, in his report to TPLF parliament early November 2017, the Governor of the National Bank highlighted the serious shortage of foreign currency and warned that unless this shortage is resolved in a short period of time, it will aggravate the economic crisis.
Currently, the foreign currency shortage has reached to a level where even regime-run organizations including those which are used for surveillance and repressive purposes, such as Ethiotelecom, are defaulting on their foreign financial obligations. Further, these organizations reported that their inability to import equipment and hardware due to lack of foreign currencies has hampered their operations. As the foreign currency reserve of the country plummeted from $3 billion to $700 million, importers revealed to domestic media that they should wait for more than a year before they receive a Letter of Credit for their imports and even then, they only get a fraction of what they ask for.
As other sources of foreign currency dry up, the regime is placing its hope on the remittance of Diaspora Ethiopians to pick up the slack. The regime has publicly stated that the magnitude of the remittance from Ethiopians living and/or working abroad reaches over $4 billion per year.
There are a few fundamental facts that each Ethiopian needs to keep in mind when discussing the issue of foreign currency in relation to Ethiopia:
- The wealth and economy of the country including the foreign trade sectors are vastly controlled by TPLF-owned and affiliated entities such as Endowment Fund for the Rehabilitation of Tigray (EFFORT); Tigray Development Association (TDA), and Relief Society of Tigray (REST);
- Those who benefit or hurt by the availability or shortage of foreign currency are mostly the above mentioned TPLF organizations and numerous companies owned by them;
- The economic/financial crunch the regime is facing currently will undermine the material, technological and economic capability of its security and police forces that are used to suppress, maim and kill Ethiopians;
- Crippling the regime’s economic backbone is a necessary form of struggle to shorten its political lifespan, and depriving the regime access to foreign currencies plays a critical role in this respect.
As every Ethiopian would note, at this moment our people are paying huge sacrifices to regain their freedom and ownership of their beloved country. The popular uprising of the past two years has dragged the regime into a huge crisis despite the fact that it is costing our people very dearly. The political and economic crises the regime is facing right now are in one way or another the fruits of the tenacious popular struggle. However, to ensure that this ever-growing popular struggle becomes victorious, it requires everyone’s action and involvement. In this regard, we must recognize that Diaspora Ethiopians have a unique opportunity and capacity to undermine the regime’s economic and political power.
At this point, the money we Ethiopians in the Diaspora remit to our relatives back home is the only source of foreign currency for the regime. Depriving the regime access to this hard currency is a power we have in our hands that we can and must use to exacerbate the regime’s economic crisis and constrain its ability to stifle and repress our people. It must be remembered that we have the responsibility and the ability to weaken the economic muscle of the regime, to shorten the suffering of our people, and ensure that their dear sacrifices are leading to victory.
The Worldwide Ethiopian Joint Task Force is therefore calling upon fellow Ethiopians in the Diaspora to stop remitting money through money transfer channels that allow the regime to acquire the hard currency.
Respectfully and on behalf of the people of Ethiopia, the Task Force calls up on everyone who wants to see an end to the suffering of our people to implement the following strategies and actions:
- Stop sending foreign currencies through the formal channels such as Western Union and Money Gram. The following alternative ways are suggested to send money that are deemed to minimize the chance of the regime accessing the hard currency:
- Ethiopian-owned convenience stores and individuals in your community who are providing money transfer services; ensure they are not regime-affiliated.
- Individuals in your community who have relatives in Ethiopia that are keen on exchanging Ethiopian birr for hard currency, often at a much better exchange rate than what the banks in Ethiopia offer. These folks often use the hard currency to import goods and services directly for their domestic businesses.
- Send money through friends and acquaintances travelling to Ethiopia. This allows your relatives to exchange the hard currency in the black market at a higher rate than what the banks offer.
- Send goods such as laptops and cell phones instead of money; your relatives will sell them for a much better value than they will gain by exchanging the dollar to birr in the bank.
- If the formal money transfer channels such as Western Union and Money Gram are your only option and you must send money to Ethiopia, depending on the financial needs of your relatives, the Task Force encourages you to consider reducing the amount and/or the frequency of your remittance by up to 30 percent.
- If your relatives in Ethiopia are financially well-off and your remittance has a relatively minimal impact on their economic well-being, the Task Force encourages you to consider stopping sending money altogether for at least a limited time as a show of support to the life-and-death struggle of our people.
- As the leaked National Security Council document admitted and the reality on the ground attests, the two-year long political and economic uncertainty is forcing wealthy Ethiopians (most of whom are regime-affiliated) to migrate and money-launder their wealth abroad. Considering this and the desperate need of the regime for hard currency, transferring money to Ethiopia now for commercial or investment ventures will do more harm than good to Ethiopia and Ethiopians. The Task Force therefore calls up on Diaspora Ethiopians who plan to invest in Ethiopia to cancel, delay, or limit their plans or activities for the time being. Doing so will not only support the popular struggle; it will also safeguard your hard-earned money given the uncertain economic and political climate in the country.
The people of Ethiopia will be victorious!
Long Live Ethiopia in glory!
Worldwide Ethiopian Joint Task Force
Abonner på:
Innlegg (Atom)

