tirsdag 31. desember 2013

የደቡብ ሱዳን ተፋላሚዎች ለድርድር ወደ አዲስ አበባ ቢያመሩም ጦርነቱ አልቆመም

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለኤ ኤፍ ፒ እንደገለጹት ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር እና የተቃዋሚው መሪ ሪክ ማቻር ለውይይት በአዲስ አበባ ይገኛሉ።
ማቻር የሰላም ድርድሩን የተቀበሉት የዩጋንዳው መሪ ዩዎሪ ሙሰቬኒ አገራቸውና የኢጋድ አባላት በደቡብ ሱዳን ግጭት ውስጥ እጃቸውን በማስገባት አማጽያኑን እንደሚወጉ ማስጠንቀቃቸውን ተከትሎ ነው የሚለውን ዘገባ መሪው አስተባብለዋል። ለፕሬዚዳንት ሙሰቬኒ ምላሽ በሚመስልና የድርድር ቦታቸውን በሚያጠናክር መልኩ፣ አማጽያኑ ቦር የምትባለውን ከተማ ዛሬ መልሰው መያዛቸውን አስታውቀዋል።
ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ስልጣናቸውን ለተቃዋሚው መሪ አካፍሉ የሚለውን ሀሳብ እንደማይቀበሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትራቸው ግልጽ አድርገዋል።
ሁለቱ ሀይሎች በአዲስ አበባ የሰላም ስምምነት የማይፈራረሙ ከሆነ አካባቢውን ወደሚያተራምስ የዘር ፍጅት ሊገቡ ይችላል ተብሎ ተሰግቷል።

ኢህአዴግ በሶስት ድርጅቶች ላይ አዲስ ዘጋቢ ፊልም እያዘጋጀ መሆኑ ተሰማ

በመሰራት ላይ ያለው አዲስ ፊልም ኦነግ ፤ ኦብነግ እና ግንቦት ሰባትን በሽብርተኝነት የሚያወግዝ ነው።
ኢህአዴግ በዚህ ሰአት ፊልሙን ለምን ለመስራት እንደፈለገ ግልጽ የሆነ ነገር የለም። አንዳንዶች እንደሚገምቱት ከሆነ ግን ገዢው ፓርቲ በድርጅቶች እንቅስቃሴ ስጋት እየገባው ነው።
እየተሰራ ባለው ፊልም ውስጥ ኢሳትንም ለመወንጀል እየታሰበ መሆኑን ምንጮች አስታውቀዋል። ዘጋቢ ፊልሙ እስካሁን ባለመጠናቀቁ እና የመጨረሻውን የአርትኦት ይለፍ ባለማግኘቱ በይዘቱ ላይ ሙሉ አስተያየት ለመስጠት አላስቻለም።
ኢህአዴግ ሶስቱን ድርጅቶች አሸባሪ ብሎ ከሰየማቸው ጀምሮ ተከታታይ ዘጋቢ ፊልሞችን ሲሰራ ቆይቷል።

ኢትዩጵያ ህጻናትን ወደ ውጭ በጉዲፈቻ ስም በመላክ ከአፍሪካ ቀዳሚ መሆኑዋና መረጃዎች አመለከቱ

በቅርቡ የወጡ መረጃዎች እንዳሳዩት በአፍሪካ ባለፉት 6 ዓመታት በጉዲፈቻ ስም ወደ ውጭ ከተላኩት 34 ሺ 342 ህጻናት ውስጥ 63 በመቶ ወይም 21 ሺ 365 ሰዎችን በመላክ ቀዳሚ ናት።
በሃገሪቱ በሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ፈቃድ የተሰጣቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ጉዳይ አስፈፃሚ የጉዲፊቻ ደላሎች ተበራክተዋል፡፡ በአብዛኛው ለጉዲፈቻ በሚቀርቡ ህፃናት የህይዎት ታሪክ ላይ የሚጻፈው ” ተጥለው የተገኙ ወይም ወላጆቻቸውን  በህይዎት ያጡ ” የሚል በመሆኑ በልጆቹ ህይወት ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ አለው።
የሴቶች እና ህፃናት ሚኒስቴር የሆኑት ወ/ሮ ዘነቡ መንግስት ህጻናቱን ወደ ውጭ ለማላክ ለፍርድ ቤት የሚያስከፍለው 25 ብር ብቻ መሆኑን ይናገሩ እንጅ፣ የጉዲፈቻ አሳዳጊዎች፣ አንድ ህጻን ለማግኘት እስከ 20 ሺ ዶላር እንደሚከፍሉ ይናገራሉ፡፡
የደቡብ ክልል የሴቶች እና ህፃናት ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ  በህፃናት የሚነግዱ አካላት በርካታ መሆናቸውን ይገልጻሉ፡፡ ኢትዩጵያ ያወጣችው አማራጭ የህፃናት መመሪያ በራሱ ሙሉ አለመሆኑንና ለችግሩ መባባስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉንም ይገልፃሉ፡፡ በርካታ የፖሊስ እና የመንግስት አካላት ” ህጻናት ወደ ውጪ ቢሄዱ ይለወጣሉ” የሚል አመለካከት መያዛቸው ስህተት ነው የሚሉት ሃላፊዋ፣ በደቡብ ክልል እንደወጡ የቀሩ ልጆችን የሚጠብቁ እናቶች ዛሬም መንግስትን እያማረሩ ነው ፡፡
ኢቲቪ በቅርቡ ባቀረበው ዘገባ 832 ህጻናት በየአመቱ ከኢትዮጵያ ይወጣሉ ብሎአል። ይሁን እንጅ ከፌደራል መደበኛ ፍርድ ቤት የተገኘ መረጃ እንደሚያሳየው በ2005 ብቻ 2 ሺ 201 ህጻናት ከአገር እንዲወጡ ፈቃድ ተሰጥቷል።
ከአፍሪካ ሀገራ ላይቤራ እና ዛምቢያ ጉዲፊቻን በማገድ ለህጻናቱ በቂ እንክብካቤ እንደሚሰጡ አስታውቀዋል። በኢትዮጵያ ጉዲፈቻ ለመጀመርያ ጊዜ የሕግ ከለላ የተሰጠው በ1952 ዓ.ም. በወጣው የፍትሐ ብሔር ሕግ ነው፡፡

የውጭ ሃገር የስራ ስምሪት ኤጀንሲዎች መካከል ከ100 በላይ የሚሆኑት ሊከሰሱ ነው

የሳዑዲ መንግስት የመኖሪያና የስራ ፈቃድ የሌላቸውን ኢትዮጽያዊያን ማባረሩን ተከትሎ በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ ኤጀንሲዎች መካከል ከ100 በላይ በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ተሳትፈዋል የተባሉ ኤጀንሲዎች ላይ ክስ ለመመስረት መዘጋጀቱን ከአዲስ አበባ ከተማ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የተገኘ መረጃ ጠቆመ፡፡
በኢትዮጽያ በአጠቃላይ 470 የውጭ ሃገር የስራ ስምሪት ኤጀንሲዎች የሚገኙ ሲሆን 100 ያህሉ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ ተሳትፈዋል በሚል ተጠርጥረዋል፡፡
ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ እጃቸው አለበት የተባሉት ኤጀንሲዎች ወደ ውጭ ሃገር ለስራ የሚልኳቸውን ዜጎች በህጉ መሰረት በነጻ ሊልኳቸው ሲገባ ክፍያ በመቀበል ፣ የስምሪት ፈቃድ ከተከለከለ በኋላ በድብቅ በመላክ እና ለስራ የላኳቸውን ዜጎች መረጃዎችን ሲጠየቁ ምላሽ ለመስጠት ያለመቻል ጥፋቶች ተገኝተውባቸዋል ተብሎአል፡፡
በግልም ሆነ በኤጀንሲዎች በኩል በቅጥር ወደየተለያዩ ሃገራት የሚደረገው ጉዞ በአሁኑ ወቅት መታገዱ የሚታወስ ሲሆን፥ ይህን ተከትሎም በህጋዊ መንገድም ጭምር ወደ የተለያዩ የአረብ ሃገራት ለስራ የሄዱ ዜጎች በቀጣሪዎቻቸው የሚደርስባቸውን እንግልት እና የአገልግሎት ክፍያ ክልከላ ለላኩዋቸው ኤጀንሲዎች ቢያሳውቁም ምላሽ ማጣታቸውን በተደጋጋሚ በማንሳት ቅሬታ ማቅረባቸው የሚታወስ ነው።
የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ብቻም ሳሆን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በቅርቡ ከሳዑዲ ተመላሾችን በማስመልከት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ጣታቸውን ህገወጥ ወደአሉዋቸው ኤጀንሲዎች መቀሰራቸው መንግስት በተለያዩ የኣረብ አገራት ኢትዮጽዊን እየረደሰባቸው ያለውን ሰቆቃ ወደአንድ ወገን በመውሰድ ራሱን ከተጠያቂነት ለማንጻት መፈለጉን የሚያሳይ ነው በሚል ከወዲሁ ትችቶች እየቀረቡበት ነው፡፡
በፌዴራል ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ብቻ ከ2001 እስከ 2005 ዓ.ም ድረስ በህጋዊ መንገድ ወደዓረብ አገራት 459 ሺህ 810 ኢትዮጵያዊያን መጉዋዛቸውን መረጃዎች ያሳያሉ።
በሌላ ዜና ደግሞ በሪያድ ሳውድ አረቢያ የሚገኙና የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ስራ ለመቀጠር ባለመቻላችን ለከፍተኛ ችግር ተዳርገናል ይላሉ። የሳውዲ መንግስት ለኩባንያ ባለቤቶች በሚያስተላልፈው ትእዛዝ ኢትዮጵያውያኑ ካለፉት 3 ወራት ጀምሮ ስራ ለመቀጠር አለመቻላቸውንና ቤተሰቦቻቸውም የምግብ፣ የቤት ኪራይና ሌሎች ወጭዎችን ለመሸፈን እንደተሳናቸው ገልጸዋል። በሳውድ አረቢያ ለመኖር ህጋዊ የስራ ፈቃድ የላችሁም በሚል ከ150 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው መመለሳቸው የሚታወስ ሲሆን፣ በአገሪቱ የቀሩት ዜጎች ” የኢትዮጵያ መንግስት” አንድ መፍትሄ ይፈልግልን ሲሉ ተማጽነዋል።

mandag 30. desember 2013

የጋዜጠኞችና የጋዜጠኝነት ይዞታ በኢትዮጵያ

በአሁኑ መንግሥት ሳንሱር ሲነሳ የግል ጋዜጦች ቁጥር ከፍ ቢልም በሂደት ግን ቁጥራቸው አሽቆልቁሎ አሁን በጣት የሚቆጠሩ ብቻ ቀርተዋል ፤ ከ1997 ምርጫ ወዲህ የጋዜጠኞች መከሰስ መታሰርና ከሀገር መሰደድ ተባብሷል ። ለዚህም በምክንያትነት የሚነሱት የሃገሪቱ የፕሬስና የፀረ ሽብር ሕግ ናቸው ።
በኢትዮጵያ ጋዜጠኝነት በየስርዓቱ ባጋጠሙት ልዩ ልዩ እንቅፋቶች ሰበብ የሚጠበቅበትን ሚና መጫውት እንዳልቸለ የመስኩ ባለሞያዎች ያስረዳሉ ። ባለሞያዎች እንደሚሉት ለዚህ አብዩ ምክንያት ሙያው በተለይ በየስርዓቱ የሚደርስበት ፖለቲካዊ ጫና ነው ። በኢትዮጵያ በቀደሙት ሁለት መንግሥታት መገናኛ ብዙኃን በሳንሱር ማነቆ ስር ነበር የሚሰሩት። በአሁኑ መንግሥት ሳንሱር ሲነሳ የግል ጋዜጦች ቁጥር ከፍ ቢልም በሂደት ግን ቁጥራቸው አሽቆልቁሎ አሁን በጣት የሚቆጠሩ ብቻ ቀርተዋል ፤ ከ1997 ምርጫ ወዲህ የጋዜጠኞች መከሰስ መታሰርና ከሃገር መሰደድ ተባብሷል ። ለዚህም በምክንያትነት የሚነሱት የሃገሪቱ የፕሬስና የቨረ ሽብር ሕግ ናቸው ። የጋዜጠኞችና ሰነ ምግባር እና የሙያ ብቃት ጉድለትም በሀገሪቱ ጋዜኝነት ተገቢውን ድርሻ ላለመወጣቱ በምክንያትነት ይጠቀሳሉ ። እንወያይ በኢትዮጵያ የጋዜጠኞችና የጋዜጠኝነትን ይዞታ ይቃኛል ። ተወያዮቹ የሬፖርተር ጋዜጣ አዘጋጅ የማነ ናግሽና የቀድሞው የአዲስ ነገር ጋዜጣ አዘጋጅ መስፍን ነጋሽ ናቸው ።

የጋዜጠኞችና የጋዜጠኝነት ይዞታ በኢትዮጵያ

በአሁኑ መንግሥት ሳንሱር ሲነሳ የግል ጋዜጦች ቁጥር ከፍ ቢልም በሂደት ግን ቁጥራቸው አሽቆልቁሎ አሁን በጣት የሚቆጠሩ ብቻ ቀርተዋል ፤ ከ1997 ምርጫ ወዲህ የጋዜጠኞች መከሰስ መታሰርና ከሀገር መሰደድ ተባብሷል ። ለዚህም በምክንያትነት የሚነሱት የሃገሪቱ የፕሬስና የፀረ ሽብር ሕግ ናቸው ።
በኢትዮጵያ ጋዜጠኝነት በየስርዓቱ ባጋጠሙት ልዩ ልዩ እንቅፋቶች ሰበብ የሚጠበቅበትን ሚና መጫውት እንዳልቸለ የመስኩ ባለሞያዎች ያስረዳሉ ። ባለሞያዎች እንደሚሉት ለዚህ አብዩ ምክንያት ሙያው በተለይ በየስርዓቱ የሚደርስበት ፖለቲካዊ ጫና ነው ። በኢትዮጵያ በቀደሙት ሁለት መንግሥታት መገናኛ ብዙኃን በሳንሱር ማነቆ ስር ነበር የሚሰሩት። በአሁኑ መንግሥት ሳንሱር ሲነሳ የግል ጋዜጦች ቁጥር ከፍ ቢልም በሂደት ግን ቁጥራቸው አሽቆልቁሎ አሁን በጣት የሚቆጠሩ ብቻ ቀርተዋል ፤ ከ1997 ምርጫ ወዲህ የጋዜጠኞች መከሰስ መታሰርና ከሃገር መሰደድ ተባብሷል ። ለዚህም በምክንያትነት የሚነሱት የሃገሪቱ የፕሬስና የቨረ ሽብር ሕግ ናቸው ። የጋዜጠኞችና ሰነ ምግባር እና የሙያ ብቃት ጉድለትም በሀገሪቱ ጋዜኝነት ተገቢውን ድርሻ ላለመወጣቱ በምክንያትነት ይጠቀሳሉ ። እንወያይ በኢትዮጵያ የጋዜጠኞችና የጋዜጠኝነትን ይዞታ ይቃኛል ። ተወያዮቹ የሬፖርተር ጋዜጣ አዘጋጅ የማነ ናግሽና የቀድሞው የአዲስ ነገር ጋዜጣ አዘጋጅ መስፍን ነጋሽ ናቸው ።

የኢትዮጵያ መንግስት ዜጎችን ከደቡብ ሱዳን ማስወጣት መጀመሩን አስታወቀ


የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ 1 ሺ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ከቦርና ቢንቲዩ ግዛት መውጣታቸውን እና 650 የሚሆኑት ወደ ኢትዮጵያ ቀሪዎቹ ደግሞ ዋና ከተማዋ ጁባ መግባታቸውን ገልጸዋል። ቃል አቀባዩ እንዳሉት ሁኔታዎች እየከፉ የሚሄዱ ከሆነ ቀሪዎቹን ዜጎች የማውጣት እቅድ አለ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በግጭቱ ውስጥ ከሞቱት 1 ሺ ሰዎች መካከል ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙበትም አስታውቋል። እስካሁን ምን ያክል ኢትዮጵያን በትክክል እንደሞቱ አልታወቀም፡ የኢትዮጵያ መንግስትም መረጃውን ይፋ አላደረገም፣ ይሁን እንጅ የአሜሪካ ድምጽ በአገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በመጥቀስ ከ30 ያላነሱ ኢትዮጵያውያን እንደሞቱ ዘግቧል።

የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በደቡብ ሱዳን ከ15 ሺ ያላነሱ ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙ ገልጿል። ይሁን እንጅ አንዳንድ ወገኖች ቁጥሩ 50 ሺ ይደርሳል ይላሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኡጋንዳው መሪ ዪዎሪ ሙሰቨኒ ለአማጽያኑ መሪ ሪክ ማቻር ፣ "የሰላም ስምምነቱን የማትቀበል ከሆነ ሽንፈት ይጠብቅሃል" ሲሉ ማስጠንቀቂያ ልከዋል። ዩጋንዳም ጦሯን ወደ ሱዳን ማስገባቱዋን በይፋ አስታውቃለች።

የዩጋንዳ መንግስት ያዘው አቋም በደቡብ ሱዳን የተጀመረውን የሰላም ጥረት እንደሚያበላሸው አማጽያን አስጠንቅቀዋል።

søndag 29. desember 2013

Ethiopia swamped by wave of returned migrants

More than 120,000 undocumented migrants were forced out of Saudi Arabia and face an uncertain future at home.

Many returning migrants suffered physical and sexual abuse in Saudi Arabia [AFP]
Addis Ababa, Ethiopia - The return of 120,000 young undocumented migrant workers from Saudi Arabia to Ethiopia has sparked fears that the influx will worsen the country’s high youth unemployment and put pressure on access to increasingly scarce land.
As a result, a growing number of young Ethiopians are choosing to migrate to Sudan to circumvent an indefinite travel ban slapped by the Ethiopian government last month on Ethiopian workers traveling to Middle Eastern countries.
Esther Negash, 28, is from a family of nine that lives on a four-hectare farm dedicated to growing maize in the Tigray region of northern Ethiopia. She has been out of work since leaving school 10 years ago.
Negash’s family recently decided to use their savings to fund her migration to Khartoum in search of employment.
“In the last two months, there have been many people returning from Saudi Arabia. This makes things worse for people like me who cannot find work,” she said.
“The rains were short this year and we did not have a good harvest. My family is large, if we don’t get a good harvest then it is very difficult. We heard about work opportunities in Sudan and thought this was our only solution.”
A large number of Ethiopians migrate every year in search of brighter economic prospects, with the Middle East being the dominant destination.
Saudi Arabia’s crackdown on undocumented foreign workers began after a seven-month amnesty period expired on November 3. Since then, 120,000 Ethiopian migrants have been repatriated to Ethiopia after being corralled in a deportation camp for two months, where conditions are reportedly abject.
Human rights violations
Many Ethiopians have reported human rights violations at the hands of their employers as well as while under the control of security forces inside the camps.
One 23-year-old woman had just arrived in Ethiopia after working as a domestic in Riyadh for two years. Her account is similar to many other experiences narrated by returnees.
“My employer would sexually abuse me and beat me. I was forced to work seven days a week, 20 hours a day. I was not allowed to leave the house. It was hell,” she said.
“They did not pay me for one year even though I worked also for their relatives. I am so tired and so sad. [But] I am so happy to be back in Ethiopia,” she said.
Despite the many terrible experiences recounted by Ethiopian returnees, poverty and limited economic prospects will continue to force Ethiopian workers to migrate to countries like Sudan and overseas, says the International Labour Organisation, which is working to make regular migration methods more attractive for Ethiopians instead of using unaccountable and illegal brokers to facilitate their migration.
After the ban, people will try any means possible to work abroad due to a lack of employment opportunities in their home country
George Okutho, International Labour Organisation
“After the ban, people will try any means possible to work abroad due to a lack of employment opportunities in their home country,” George Okutho, director of the ILO Country Office for Ethiopia and Somalia, said.
“These returnees travelled to Saudi Arabia looking for economic opportunities with a greener pasture mindset in the hope that they could send their family remittances to raise living standards at home. However, most of the time migrant workers are acting on misinformation about the prospects and country of destination,” he said.
A lack of education and skills make Ethiopian migrants especially vulnerable to working in dangerous and exploitative working conditions, both at home and abroad, said Okutho.
“The problem is many of Ethiopia’s migrant workers are uneducated and ill-equipped even for the domestic work they seek outside the country,” he said. “The result is that even if they go to the Middle East or Sudan, they can earn a little more than when at home, but because they are untrained they end up working in very extreme and difficult circumstances without knowing their rights. ”
The Ethiopian government’s planning and logistical capacity has been overwhelmed by the rapidly rising number of returnees. An initial expectation of 23,000 returnees jumped to 120,000 in one month.
“We are engaged with the Saudi government and we are working hard to return Ethiopians stranded in Saudi Arabia,” Dina Mufti, a foreign affairs spokesperson, said.
“The number of Ethiopians working illegally is much higher than we anticipated. The Ethiopian government recognises that these people will need employment and so we are trying to create opportunities to assist these people, many of them young, and rehabilitate them back into their communities,” she said.
Dwindling land access in Ethiopia is a critical issue for 80 percent of the population who make a living as small farmers. In the mountainous region of Tigray, the average land availability per household is 3.5 ha.
As life expectancy increases, the potential for subdividing farm plots reduces, leaving many of Ethiopia’s youth food insecure and unemployed.
In the last year, a large number of young people have joined regular protests staged in the country’s main cities to demonstrate their dissatisfaction with high unemployment and inflation.
The inundation of over 120,000 people has the potential to further disenfranchise youth in Ethiopia, where the majority of the population of 91 million earn less than two dollars a day.
Hewete Haile, 18, lives outside Sero Tabia, a small town where youth unemployment is spiraling. Out of 2,200 households, 560 young people between 17 and 35 are unemployed, without access to land or income.
Outside the Sudanese embassy in Addis Ababa, Haile is queuing with several hundred other young girls, mostly from remote rural villages, in hopes of obtaining a visa to allow her to look for work in Khartoum.
Hewete’s friends say a domestic in Khartoum is paid eight dollars a day compared to four dollars in Addis Ababa.
“I would not be leaving my country if there was a way for me to work and make a good income here in my country,” she said.
“If Sudan does not work out then I will travel from there to the Middle East. I know what happened in Saudi Arabia. I would not be leaving Ethiopia if I could get work here, but it is getting more difficult all the time,” she said.


lørdag 28. desember 2013

በደቡብ ሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን መንግስት እንዲታደጋቸው እየተማጸኑ ነው

ዩኒቲ በሚባለው ግዛት ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያን በጦርነት አጣብቂኝ ውስጥ መገኘታቸውንና ህይወታቸው አደጋ ውስጥ መውደቁን ተናግረዋል።
በግዛቱ ውስጥ በአንድ የመንገድ ስራ ድርጅት ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ 6 ኢትዮጵያውያን እንደተናገሩት በሁለቱ ተፋላሚ ሀይሎች መካከል የሚደረገውን የተኩስ ልውውጥ ለማምለጥ ያለፉትን ሁለት ቀናት በከባድ ማሽነሪዎች ውስጥ በመደበቅ ለማሳለፍ ተገደዋል። በአካባቢያቸው 2 ኢትዮጵያውያን መገደላቸውንና 3ቱ ደግሞ መቁሰላቸውን ተናግረዋል።
እስካሁን ድረስ ምን ያክል ኢትዮጵያውያን እንደሞቱ ባይታወቅም፣ የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በአገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በማነጋገር እንደዘገበው የሞቱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር እስከ ታህሳስ 17፣ 2006 ዓም ድረስ ቢያንስ 30 ይደርሳል።
ኢሳት ያነጋገራቸው ኢትዮጵያውያን እንደሚሉት መንግስት እስካሁን ድረስ ዜጎቹን ለመሰብሰብ ጥረት እያደረገ አይደለም። ጎረቤት አገሮች ኬንያና ኡጋንዳ ዜጎቻቸውን ሲያስወጡ የኢትዮጵያ መንግስት ምንም አይነት እርምጃ ለመውሰድ አለመፈለጉ ለብዙዎች እንቆቅልሽ ሆኗል። ኢትዮጵያውያን አሁንም መንግስት እንዲደርስላቸው ጥሪ አቅርበዋል
በጆንግሌ ግዛት የተደፈሩ 4 ኢትዮጵያውያን ጁባ ውስጥ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሆስፒታል ውስጥ ህክምና እንዲያገኙ ተድርጓል።x
ይህ በእንዲህ እንዳለ የምስራቅ አፍሪካ መንግስታት በናይሮቢ ኬንያ ያደረጉትን ስብሰባ ተከትሎ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በግላቸው ተኩስ እንደሚያቆሙ አስታውቀዋል። አገራቱ የመንግስትን እርምጃ የደገፉ ሲሆን፣ የኬንያው መሪ ኡሁሩ ኬንያታ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠን መሪ በሀይል ለማውረድ የሚደረገውን እንቅስቃሴ እንደማይደግፉ ገልጸዋል።
የተቃዋሚዎች መሪ የሆኑት ሪክ ማቻርም በተመሳሳይ መንገድ ተኩስ እንዲያቆሙ የምስራቅ አፍሪካ መሪዎች ተማጽኖ አሰምተዋል። መሪዎቹ በሚቀጥሉት 4 ቀናት ፊት ለፊት ተገናኝተው እንዲወያዩ ኢጋድ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።እስካሁን በተካሄደው የእርስ በርስ ጦርነት ከ1 ሺ በላይ ሰዎች መገደላቸውን አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል;፡

mandag 23. desember 2013

የኢህአዴግ አዲሱ አሰላለፍ ፪ – ከተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)






በድህረ-መለስ ኢትዮጵያ የፖለቲካው ሥልጣን በስርዓቱ ልሂቃን መካከል ከሚደረገው የኃይል መተናነቅ አንጻር፣ ዛሬም ከመፈራረቅ ጣጣው የተላቀቀ የማይመስልባቸው ምልክቶች መታየታቸው እንደቀጠለ ነው፡፡ ከአራት ወር በፊት በዚህ መፅሄት ላይ ‹‹አዲሱ የኢህአዴግ አሰላለፍ›› በሚል ባቀረብኩት ፅሁፍ በገዥው ፓርቲ ውስጥ ተፈጥሮ ከነበረው ክፍፍል የትኛው ቡድን የበለጠ ጉልበት አግኝቶ በአሸናፊነት መውጣት እንደቻለ ከገለፅኩ በኋላ ፅሁፉን የቋጨሁት እንዲህ በማለት ነበር፡- ‹‹የፓርቲው የታሪክ ድርሳን እንደሚነግረን ‹ይሆናሉ› የተባሉት ተቀልብሰው፣ ባልተጠበቁ ሁነቶች (የኃይል መገለባበጥ ተከስቶ) ፖለቲካው የሚመራበት አጋጣሚ ሊፈጠር የሚችልበት ዕድል ሊኖር እንደሚችልም መዘንጋት አያስፈልግም፡፡››
 እነሆ በዚህ ፅሁፍ ደግሞ በቅርቡ በተጨባጭ የታዩትን አዳዲስ ኩነቶች እና ይህንኑ ተከትለው ሊመጡ ይችላሉ ብዬ የምገምታቸውን ‹የቢሆን ዕድሎች› (Scenarios) ለማየት እሞክራለሁ፡፡
 ሰላም የራቀው-ኢህአዴግ
 በግንባሩ አባል ድርጅቶች መካከል ዛሬም ድረስ ሙሉ በሙሉ የተረጋጋ ፖለቲካ አልሰፈነም፤ የዚህ ዋነኛ ምክንያቱ ደግሞ፣ ቁልፍ የሥልጣን ቦታዎችን ጠቅልሎ ይዞ በነበረው በቀድሞ ሊቀ-መንበሩ ህልፈት ሳቢያ የተፈጠረው የአመራር ክፍተት እና እርሱን ሊተካ የሚችል መሪ ማግኘት ባለመቻሉ ይመስለኛል፡፡ እንዲህ አይነት አጋጣሚዎችም በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባለ ከሕግ ይልቅ የጠመንጃ ኃይልና የግለሰብ አምባገነናዊነት በገነነበት ሀገር ‹የማይገመቱ ክስተቶች› (Unpredictable Event) ማምጣታቸው የሚጠበቅ ነው፡፡
የሆነው ሆኖ በዚህ አጀንዳ ለመመልከት የምሞክረው ጉዳይ፣ በአሁኑ ጊዜ ሀገር እየመራ ያለው ኃይል ለሁለት የተከፈለ ቢሆንም፣ በአንፃራዊነት በጥምር የሚሰራ መሆኑን በማስረገጥ ነው፡፡ የእነዚህ ሁለት ቡድኖች የጉልበት ምንጭም የታጠቀውን ኃይል በመቆጣጠር እና የፖለቲካውን ሥልጣን በመያዝ ላይ የተመሰረተ ነው፤ ይኸውም ሠራዊቱ እና የደህንነት መስሪያ ቤቱ ሙሉ በሙሉ በህወሓት ሰዎች ሲንቀሳቀሱ፣ ፖለቲካውን ደግሞ የብአዴን መሪዎች፣ ከተወሰኑ የኦህዴድና ደህአዴን የአመራር አባላት ጋር ተባብረው መያዛቸውን የሚያሳዩ ምልክቶች መኖራቸው ነው፡፡
 የህወሓት ኃይል
ህወሓት የቀድሞው ፍፁማዊ የበላይነቱን ለመመለስ ዋና ችግር የሆነበት በውስጡ ለተፈጠረው መከፋፈል እስካሁን መፍትሄው ተለይቶ አለመታወቁ ነው፤ ከዚህ ቀደም በዚሁ መፅሄት፣ አንዱ ኃይል የተሻለ ጉልበት በማግኘቱ ሌላኛውን (እነአዜብ መስፍንን ጨምሮ አባይ ወልዱና ቴዎድሮስ ሀጎስን የመሳሰሉ ከፍተኛ ካድሬዎች የተሰባሰቡበትን) በመብለጥ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን እንቅስቃሴያቸውን መገደቡ ተሳክቶለት እንደነበረ ማስነበቤ ይታወሳል፡፡ ይህ ክፍፍል ምንም እንኳ እንደ 1993ቱ ከፓርቲ እስከ ማስወጣት የሚደርስ አለመሆኑ ቢታወቅም፣ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል እና ጌታቸው አሰፋ የተሰለፉበት ቡድን ተፅእኖ ፈጣሪ ሆኖ መውጣት ችሏል፤ ይህም ሆኖ ውስጥ ውስጡን የሚገመደው ተንኮልም ሆነ ሽኩቻ ገና መቋጫ አለማግኘቱ ግልፅ ነው፡፡
 በዚህ ፅሁፍ ጠመንጃ የታጠቀውን ክፍል ‹የህወሓት ኃይል› እያልኩ የምገልፀበት ዓብይ ምክንያት፣ በጄነራል ሳሞራ የኑስ ኤታ ማዦር ሹምነት የሚመራው የመከላከያ ሠራዊት እና በማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ጌታቸው አሰፋ ስር ያለው የደህንነት ኃይል ለሚደግፉት ቡድን መጠናከር እያበረከቱት ያለውን አስተዋፅኦ ከግምት በመክተት ነው፡፡ ሁለቱም ሰዎች ለመለስ ፍፁም ታማኝ የነበሩ ቢሆንም፣ ከህልፈቱ በኋላ እንደእርሱ ተጭኖ ሊቆጣጠራቸው የሚችል ጉልበታም ህወሓትን ጨምሮ በሁሉም የግንባሩ አባል ፓርቲ ውስጥ አለመኖሩ፣ በፖለቲካው ‹ቼዝ› የ‹ዘመነ መሳፍንቱ›ን ሚካኤል ስሁል አይነት ሚና እንዲጫወቱ አስችሏቸዋል፤ ሁለቱም ከስራቸው የነበሩትንና ‹ስልጣን ሊጋፉ ይችላሉ› ብለው የጠረጠሯቸውን ባልደረቦቻቸውን አስቀድሞ ገለል ማድረጉ ከሞላ ጎደል የተሳካላቸው ይመስለኛል፡፡
 በተለይም ጌታቸው አሰፋ ከራሱ ወንበር አልፎ ከእነአዜብ መስፍንና አባይ ወልዱ ጋር በመተባበር አንድ ቀን በጠቅላላው የመንግስት የሥልጣን እርከን ላይ ‹ናቡቴ ሊሆን ይችላል› የሚል ስጋት ያሳደረበትን እና ‹መለስ ዜናዊ ሞት ባይቀድመው በእርሱ ቦታ ሊተካው ነበር› እየተባለ የሚነገርለትን የመረጃ ኃላፊ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል በሙስና የሚወነጀልበትን መንገድ አመቻችቶ ለእስር ባይዳርገው ኖሮ ‹‹ለቁርስ ያሰቡንን…›› አይነት ታሪክ ራሱን መድገሙ አይቀሬ ነበር ብዬ አስባለሁ፡፡
 ጄነራል ሳሞራ የኑስ በበኩሉ ተቀናቃኙ አድርጎ ይመለከታቸው የነበረው ሶስቱ ከፍተኛ መኮንኖች እንደ ወልደስላሴ ‹ፍንቀላ መሳይ ነገር ሊሞክሩ ይችላሉ› ተብለው አይደለም፡፡ የእነርሱ የመጀመሪያው ችግር ከወታደራዊ ዲሲፕሊን በማፈንገጥ አለቃቸውን አለማክበራቸው ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ሳሞራ ‹በየትኛውም ምክንያት ከኃላፊነቴ ብነሳ የቆየ ፋይል አገላብጠው አደጋ ላይ ሊጥሉኝ ይችላሉ› በሚል ስለሚጠረጥራቸው ነው፡፡ እነዚህ መኮንኖች የሰሜን ዕዝ አዛዥ ሌፍተናንት ጄነራል ሰዓረ መኮንን፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ መልካም ግንኙነታቸው እንደቀድሞው እንዳልሆነ የሚነገረው የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሌፍተናንት ጄነራል አበባው ታደሰ እና የአየር ኃይሉ አዛዥ ሜጀር ጄነራል ሞላ ኃይለማርያም ናቸው፡፡ እናም ሰዓረ እና አበባው በቀጥታ ሠራዊት ከሚያዙበት ቦታ ተነስተው በመከላከያ ሚኒስትር ውስጥ በቢሮ ስራ ላይ ሲመደቡ፣ ሞላም ከነበረበት ኃላፊነት አኳያ ብዙም ይመጥነዋል የማይባል የቢሮ ስራ ተሰጥቶታል፤ በእርሱም ቦታ ሜጀር ጄነራል አደም መሀመድ ተተክቷል፡፡ የሳሞራ እና የሞላ ልዩነት በመለስ ዘመንም በአደባባይ የሚታወቅ እንደነበረ ሰምቻለሁ፡፡
Samora (2)
 ለጉዳዩ ቅርብ ከሆነ የመረጃ ምንጬ እንዳረጋገጥኩት የአስተዳደር ዘይቤውን በማኪያቬሊያዊ አስተሳሰብ (ከፋፍለህ ግዛ) የሚያሳልጠው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ፣ ለሞላ ትዕዛዝ የሚሰጠውም ሆነ ማንኛውንም ጉዳይ በተመለከተ የሚያነጋግረው የዕዝ ተዋረዱን ጠብቆ በኤታ ማዦሩ በኩል ሳይሆን፣ በቀጥታ በመገናኘት መሆኑ፣ አየር ኃይሉን ከመከላከያ ሚኒስቴር የተገነጠለ አስመስሎት ነበር፤ ይህ ሁኔታም በሁለቱ መኮንኖች መካከል ያለው ግንኙነት የሥልጣን ተዋረድን የጠበቀ እንዳይሆን በማሰናከሉ በጄነራሉ ላይ ደፍሮ የማይናገረው ቅሬታ ሊያሳድርበት ችሏል፤ ከመለስ ህልፈት በኋላም ሳሞራ ሂደቱን ለማስተካከል መሞከሩ፣ በየግምገማው ላይ እስከ መዘላለፍ አድርሷቸው ነበር (በነገራችን ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ እንደ ጦር ኃይሎች አዛዥነቱ፣ ከጄነራሎቹ ጋር መደበኛ /Official/ በሆነ መንገድ ትውውቅ አላደረገም፤ እነዚህ ሶስት ጄነራሎችም ለዚህ አይነቱ የአሰራር መፋለስ ጥፋተኛ የሚያደርጉት አለቃቸውን ሳሞራ የኑስን ነው፤ ከምንጮቼ እንደሰማሁት ከሆነም ከወራት በፊት ኃይለማርያም ደሳለኝ በተገኘበት ‹ጎልፍ ክለብ› በሚባለው የጄነራሎቹ መዝናኛ በተዘጋጀ ፕሮግራም ማጠናቀቂያ ላይ ሳሞራ አንድ ጠረጴዛ ከበው ወደ
 ተቀመጡት እነዚህ ጄነራሎች ጋ ሄዶ ‹ኑ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ላስተዋውቃችሁ› ማለቱን እና እነርሱም በጥያቄው ተበሳጭተው ቢሮ ያላቸው መሆኑን እና ክብራቸውን በሚመጥን መልኩ መተዋወቅ እንደነበረባቸው በኃይለ ቃል መመለሳቸውን ነው)
የሳሞራ የኑስ እና ሰዓረ መኮንን መነቋቆር ከትግሉ ዘመን ጀምሮ የመጣ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ሳሞራ ከማንም በላይ የሚፎካከረውም ሆነ መበለጥ የማይፈልገው በሟቹ ጄነራል ኃየሎም አርአያ እንደ ነበር የቀድሞ ጓዶቻቸው ያስታውሳሉ፤ ይህ ሁኔታ ዛሬም ድረስ በስራ ላይ ያሉ መኮንኖችን ‹የሳሞራ› ወይም ‹የኃየሎም ተከታይ› በማለት መከፋፈሉ በጓዶቻቸው እና በፓርቲው መሪዎች አካባቢ የሚታወቅ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ለማዕረግ እድገት የተለየ የድጋፍ አስተያየት የሚያገኙት በዛን ዘመን ‹የሳሞራ ተከታይ› የሚባሉት እየተመረጡ እንደነበረ በወሬ ደረጃ ይናፈሳል (በነገራችን ላይ ጄነራል ሳሞራ ከጤንነት ጋር በተያያዘ በአጭር ጊዜ ውስጥ በጡረታ ይሰናበታል በተባለበት ጉዳይ ላይ እያንገራገረ እንደሆነ ከመከላከያ አካባቢ የሚወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ፤ እንደ ምክንያት የሚጠቀሰው ደግሞ ‹ለእኔ በጎ አመለካከት የላቸውም› በሚል የሚጠራጠራቸው ጄነራሎች በሥራ ላይ እያሉ የእሱ ጡረታ መውጣት ከመስሪያ ቤቱ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ያደሩ የሙስና ካርዶች የሚመዘዙበትን ዕድል ያሰፋዋል የሚል ነው፤ በተለይም በግዙፍ የቢዝነስ ሥራዎች ላይ በታላቅ ተፎካካሪነት እየተሳተፈ የሚገኘው ‹መቴክ› ምንም እንኳ ማረጋገጫዎች ባይቀርቡበትም በመከላከያ ሥር ከነበረበት ዘመን እስከ 2002 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ ከግዥዎች ጋር ተያይዘው የሚነሱ በርካታ የሙስና ሁኔታዎች በመኖራቸው ነው፡፡
 መቴክ ካለፉት አራት ዓመታት ጀምሮ በአዋጅ የልማት ድርጅት እንዲሆን ቢደረግም፣ ዛሬም ዳይሬክተሩ የሠራዊቱ አባል ብርጋዴር ጄነራል ክንፈ ሲሆን፣ መከላከያ ደሞዝ የሚከፍላቸው ጥቂት የማይባሉ ሠራተኞችንም እንዳቀፈ ይታወቃል፡፡ እናም ሳሞራ ሃሳቡ ከተሳካለት ለጥቂት ተጨማሪ ዓመታት በሥልጣኑ ላይ ሲቀጥል፣ አሊያም ‹የወንድ በር› ለማግኘት በትግሉ ዘመን የእርሱ ሰልጣኝ እንደነበረ የሚነገርለትን እና በቅርቡ ብቸኛው ከሜጀር ወደ ሌፍተናት ጄነራል ማዕረግ ያደገው ዮሀንስ ገ/መስቀል እንዲተካው መንገድ ጠረጋውን ማመቻቸቱ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራበት ጉዳይ ይመስለኛል)
samora
ይህም ሆኖ የተኮረኮርን ያህል የምንስቀው ጄነራል ሳሞራ የኑስ በቅርቡ ለታተመው ‹‹ህብረ ብሔር›› መፅሄት ሙስና ለሠራዊቱ አደገኛ መሆኑን እንዲህ በማለት መግለፁን ስናነብ ነው፡-
‹‹ሙስና ሠራዊቱን ሊያበላሸው ይችላል፡፡ ሙስና ፀረ-ልማት ነው፤ ሠራዊቱን ሊበትነው እና ሕዝባዊ ባህሪውን እንዲያጠፋ ሊያደርገው ይችላል፤ አንድ ሠራዊት ሠራዊት ነው የሚባለው እንደ ወታደር እንደ አንድ አካል ሲያስብ እንጂ ለግሉ ሲያስብ አይደለም፡፡ …በአጠቃላይ (ሠራዊቱ) በዚህ ነው የሚፈርሰው፡፡››
መቼም ጄነራሉ ይህንን የተናገረው እራሱን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ መኮንኖች እንደ እንግሊዝ ንጉሳውያን ቤተሰቦች በተንጣለለ ቪላ ቤት ውስጥ፣ የተቀማጠለ ኑሮ መኖራቸውን ረስቶት አይመስለኝም፤ ‹ይህ የተንዛዛ ወጪያቸውም የሚሸፈነው ከደሞዛቸው በሚያገኙት ገቢ ነው› ብሎ ቧልት መሳይ ክርክር ሊያመጣ አይችልም፡፡ ይሁንና እታች ያለው ጭቁን የኢትዮጵያ ሠራዊት ምንም እንኳ በአለቆቹ ‹ቴክሳስ›ነት ላይ ለመቆጣት ባይደፍርም፣ እንደማንኛውም ዜጋ ለኑሮ ውድነትና አስከፊ ድህነት የተጋለጠ መሆኑን መካድ አይቻልም፡፡
 የሆነው ሆኖ ተሰሚነታቸው እየተቀዛቀዘ የመጣው አቦይ ስብሃት ነጋ ከወራት በፊት ለ‹‹ውራይና›› መፅሔት ‹‹ህወሓት ትንሳኤ ያስፈልገዋል›› በማለት የሰጡትን ምክር ተከትሎ፣ ጄነራል ሳሞራ እና አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ ከድርጅቱ ምክትል ሊቀ-መንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ጋር በመተባበር ህወሓትን ለማጠናከር እና በፖለቲካ ውስጥ የነበረውን የአንበሳውን ድርሻ ለማስከበር (ጉዳዩን ከለጠጥነው ደግሞ ‹ለማስመለስ›) እየሰሩ እንደሆነ ይነገራል (በነገራችን ላይ የሳሞራና ጌታቸው ተፅእኖ መጨመሩን ለመረዳት፣ መከላከያ ‹አገራዊ ጥቅምንና ደህንነትን ለመከላከል› በሚል ‹እጅግ ጥብቅ ሚስጢር ብሎ የሰየማቸውን የሰው ኃይል ፕሮፋይል፣ የሒሳብ መዝገቦችና ሰነዶች እና የክፍያ ማስረጃዎች ለማንም አካል እንዳይገለፅ› የሚያስችለውን ስልጣን፣ ደህንነቱ ደግሞ በስራ ላይ የሚፈፅማቸው ማንኛውም ጉዳዮች ወደፊት በህግ እንዳይጠይቅ እስከ መከላከል የሚደርሰውን አዲስ የተዘጋጁትን አዋጆች ማንበቡ በቂ ነው፡፡ በርግጥ እነዚህ ባለሥልጣናት እንዲህ ባለ ተመሳሳይ መንገድ እንዲጓዙ ያስተሳሰራቸው አንዱ ጉዳይ ‹ህወሓት ተዳከመ፣ ተሸነፈ፣ አበቃለት…› የሚለው የካድሬውና ደጋፊው ቁጭት እንጂ ወትሮም መልካም ግንኙነት ኖሯቸው አይመስለኝም)
ለማንኛውም በጥቅሉ ሲታይ የህወሓት ትልቁ ችግር ተብሎ በአመራር አባላቱ የሚጠቀሰው ‹በዚህ ወቅት ወደፊት መምጣት የሚችሉ ጠንካራ ቴክኖክራቶችን አለማፍራቱ፣ ሁለንተናዊ ድጋፍ የሚያደርግለትን የታጠቀውን ኃይል ተጠቅሞ የፖለቲካ ልዩነቱን ጨፍልቆ በአሸናፊነት ይዞት መውጣት የሚችል መሪ እንዳይኖረው አደረገ› የሚል ነው፡፡ በርካታ የላይኛ እና የታችኛው ካድሬዎችም ‹ለእንዲህ አይነቱ ክፉ ጊዜ ድርጅቱ የሚያስፈልገው፣ በትግሉ ዘመን ልምድ ያካበተ ታጋይ ብቻ ነው› የሚል አቋም እንዳላቸው ይነገራል፡፡ ስርዓቱ ከሚያራምደው ርዕዮተ-ዓለም ጋር ጠንካራ ትውውቅ ያሌለውን እና የትግሉን ዘመን በአሜሪካን ሀገር በማሳለፉ ‹የምዕራባውያን ድጋፍ አለው› ለሚባለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የሚሰጡት ዝቅተኛ አመለካከት መግፍኤም ይኸው ይመስለኛል፡፡
 ለነገሩ እርሱም ቢሆን በጠንካራ ድርጅታዊ ዲሲፕሊን ካለመታነፁ እና መሰል ጉዳዮች ጋር በሚያያዙ ምክንያቶች ለትንፋሽ ጊዜ የማይሰጠውን የድርጅት ሊቀ-መንበርነትንም ሆነ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ የሚወራውን ያህል ይፈልገዋል ብሎ መደምደሙ አስቸጋሪ ነው ብዬ አስባለሁ፤ ከዚህ ይልቅ በተፈጥሮ ከታደለው የተግባቢነት ባህሪው አኳያ እንደ ሕዝብ ግንኙነት የመሳሰለ ብዙም የማያጨናንቅ ሥራን ይመርጣል፡፡ ለዚህም ይመስለኛል ከሰለጠነበት ሙያ ጋር የቀጥታ ተያያዥነት ያለውን የጤና ጥበቃ ሚኒስትር በሚመራበት ዘመን፣ ከውጭ ሀገር በርካታ የተቋረጡ ፈንዶችን እንደገና ለማስለቀቅ መቻሉ እንደ ታላቅ ስኬት የሚወራለት፤ አልፎ ተርፎም ‹ወባን ከኢትዮጵያ ምድር ለማጥፋት ብርቱ ትግል አደረገ› ተብሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሳይቀር እስከ መሸለም የደረሰው እዚህ መስሪያ ቤት እያለ እንደሆነም ይታወቃል፡፡

ትንቅንቅ
ትንቅንቅ
 በሌላ በኩል ደግሞ በፓርቲውም ሆነ በመንግስት አስተዳደር ከህወሓት ሰዎች ትልቁን ስልጣን የያዘው ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ከምዕራባውያን ጋር የቆየ ቀረቤታ እንዳለው ሰምቻለሁ፤ እንደሚታወሰው ደብረፅዮን ከክፍፍሉ በፊት (የደህንነት መስሪያ ቤቱ እንዲህ እንደ ዛሬው እጅግ ዘመናዊ በሆነው የቻይና ቴክኖሎጂ ሳይጥለቀለቅ) ከነበረው ከፍተኛ የሥልጣን ቦታ ላይ ተነስቶ፣ ቁልቁል ወርዶ በሁመራ በአንድ ዞን እንዲሰራ የተመደበው (ሁላችንም ስንገምት እንደነበረው) የአንጃው አባል ወይም ደጋፊ ሆኖ አይደለም፤ ይልቁንም የእነስዬ-ተወልደ ቡድን በመባል የሚታወቀው (‹አፈንጋጩ› ኃይል) ደብረፅዮንን በሲ.አይ.ኤ እና ሞሳድ ወኪልነት የመክሰሱ ጉዳይ የድርጅቱን በርካታ አባላት ቀልብ በመሳቡ፣ መለስ ይህንን ተከትሎ ከሚመጣበት አደጋ ራሱን ለመከላከል የወሰደው እርምጃ በመሆኑ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት እስከ 1998 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ በሁመራና ራያ አካባቢዎች በዞን ደረጃ ለማገልገል ተገዷል፡፡ እናም እርሱን የምዕራቡ ዓለም ፊት-አውራሪ አሜሪካና ሸሪኮቿ ወዳጅ ነው የሚያስብለው በቀድሞ መስሪያ ቤቱ በኩል በነበረው ግንኙነት ይመስለኛል።
 የፖለቲካውን መዘውር የጨበጠው ኃይል
የዚህ ቡድን አምበል እንደ ድርጅት ብአዴን ቢሆንም፣ በቋሚ ተሰላፊነት ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ አባዱላ ገመዳ፣ ሙክታር ከድር እና ሬድዋን ሁሴን እንደሚገኙበት ይነገራል፤ ለብአዴን ‹በተሻለ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ላይ ለመገኘቱ መደላድል ፈጥሮለታል› የሚለውን ሙግት ምክንያታዊ የሚያደርገው ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲና ጥናት ምርምር አማካሪ በረከት ስምዖን፣ የኢህአዴግን የካድሬ ማሰልጠኛ ማዕከል በዳይሬክተርነት የሚመራው አዲሱ ለገሰ፣ ደርቦ ይዞት የነበረውን የትምህርት ሚኒስትርነት ለሽፈራው ደሳለኝ በመልቀቅ፣ በአሁኑ ወቅት ሙሉ የስራ ጊዜውን በግንባሩ ፅ/ቤት የሚያውለው ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እና የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ-ጉባኤው ካሳ ተክለብርሃን የያዙት ሥልጣን ያለውን የፖለቲካ አቅም መመዘኑ ይመስለኛል፡፡ በመከላከያ ሠራዊቱ ውስጥም ከሳሞራ አንድ እርከን ዝቅ ባለ ሥልጣን ከሌሎች ሁለት ጄነራሎች ጋር የሚገኘው አበባው ታደሰ እንደ ቀድሞው በዕዝ አዛዥነቱ (በቀጥታ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ወታደሮችን ማንቀሳቀስ የሚችልበት) ላይ ቢሆን ኖሮ ጥንካሬውን የተሟላ ማድረጉ አይቀሬ እንደነበረ መገመት ይቻላል፡፡
ከዚህ ሌላ ለእነበረከት ቡድን ተጨማሪ የፖለቲካ ጉልበት እየሆናቸው ያለው የኃይለማርያም ደሳለኝ ቢሮ እና በአባዱላ ገመዳ አፈ-ጉባኤነት የሚመራው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ነው፡፡ አባዱላ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪፖርት ለማቅረብም ሆነ ለመታዘዝ ፍቃደኛ ያልሆኑ አንዳንድ ባለስልጣናት፣ በውስጥ መስመር በሚተላለፍለት ‹ጥቅሻ› በምክር ቤቱ በኩል የሚመለከተው የቋሚ ኮሚቴ አባላት አስጠርቶ የተሰጠውን ኃላፊነት የሚገመግምበት ስልት እየተገበረ ነው፡፡ በአናቱም ምን ጊዜም የሳምንቱን የሥራ መጨረሻ ቀን አርብን ጠብቆ የሚሰበሰበው የሚኒስትሮች ም/ቤትን ከሞላ ጎደል ይህ ቡድን እየጠቀመበት ይመስለኛል፡፡ በርግጥ ሚኒስትሮቹ በሚገናኙበት አብዛኛውን ሰዓት ሳይግባቡ (በጭቅጭቅ) ማሳለፋቸው ይነገራል፤ የዚህ ምክንያቱ ደግሞ በአቶ መለስ ዘመን ም/ቤቱ የሚሰበሰበው የተለያዩ አጀንዳዎችን ለማቅረብ እና በቀረበው አጀንዳ ላይ ለመከራከር (ለመመካከር) ሳይሆን፣ መለስ ወስኖ የመጣበትን የሥራ ድርሻ ተቀብሎ ለመበተንና ሪፖርት ለመስማት የነበረው አሰራር፣ ዛሬ ተቀይሮ በርካታ የተነቃቁ ሚኒስትሮች የየራሳቸው ሃሳብ ተቀባይነት እንዲያገኝ (ለማንፀባረቅ) የሚታገሉበት መድረክ ወደ መሆን በመሸጋገሩ ነው፡፡ ይህም ሁናቴ ዋናውን የመንግስት ሥራ የመገምገም እና የማስፈፀም አቅምን ሳይቀር ከሚኒስትሮች ም/ቤት ወደ ኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ አሻግሮታል የሚያስብሉ ማሳያዎች አሉ፡፡ ይሁንና በዚህስብሰባ ላይም ቢሆን ደፈር ብሎ ከበረከት ስምዖን እና አባይ ፀሀዬ የተሻለ አዳዲስ ሃሳብ የሚያቀርብ ባለሥልጣን እንደሌለ ሰምቻለሁ (በነገራችን ላይ ምክንያቱን ባላውቅም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹የፖሊሲና ጥናት ምርምር አማካሪ› ተደርገው የተሾሙት በረከት ስምዖን፣ አባይ ፀሀዬ፣ ኩማ ደመቅሳ እና ዶ/ር ካሱ ኢላላ የሥራ ቦታቸው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅ/ቤት ሳይሆን መገናኛ አካባቢ በሚገኝ አንድ ህንፃ ላይ ነው፡፡ የተሰጣቸው ኃላፊነት ኃይለማርያምን በቅርብ እንዲያገኙ ከማስገደዱ እና በግልፅ ከሚታወቀው የአማካሪ አስፈላጊነት አኳያ ካየነው ግን ግራ የሚያጋባ ይመስለኛል)

አቶ አባይ ጸሐዬ
አቶ አባይ ጸሐዬ

 ጠቅላይ ሚኒስትሩ…
ኃይለማርያም ደሳለኝ ይህንን ቦታ ከያዘ በኋላ፣ ብዙዎች በስልጣኑ የማዘዝ አቅሙ ላይ አመኔታ እንደሌላቸው (አንጋፋ ታጋዮች እንደ ‹አሻንጉሊት› ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ) ደጋግመው መግለፃቸው ይታወሳል፡፡ በግልባጩ ‹አፈንግጦ ለመውጣት መሞከሩ አይቀሬ ነው› የሚሉ ግምቶች ነበሩ፡፡ በርግጥ እነዚህ መላ-ምቶች ዛሬም ድረስ እልባት ባያገኙም፣ እዚህ ጋ ያልጠቀስኳቸው አንዳንድ ጉዳዮች ላይ ያሳያቸው ወጣ ያሉ አቋሞቹን ሳስተውል ግን፣ አሁን ያለው አሰላለፍ (የአነበረከት እና አባዱላ ፖለቲካዊ መጠናከር) ለእርሱም የተረፈው ይመስለኛል፡፡ እንዲሁም ከቤንች ማጂ የተባረሩ አማርኛ ተናጋሪዎችን አስመልክቶ በድርጅቱ ውስጥ ባልተለመደ መልኩ ‹አጥፊዎቹ ላይ እርምጃ እወስዳለሁ› ከማለት አንስቶ (በነገራችን ላይ በአማካሪ ብዛት እንዲከበብ ካደረገው ምክንያት አንዱ ጓዶቹ በዚህ ንግግሩ መበሳጨታቸው ነው) በቅርቡ ህወሓትን ለመሸምገል በተዘጋጀ መድረክ ላይ ‹ሁኔታዎች እንዲህ እየተካረሩ ከሄዱ ወደ ማሰሩ መግባታችን አይቀርም› በማለት ማስፈራራቱ እና በቴዎድሮስ አድህኖም የሶሻል ሚዲያ አጠቃቀም ላይ የመቆጣቱ ጉዳይ ድረስ የሚካተቱ እውነታዎች ሰውየው የራሱን መንገድ ለመከተል እየሞከረ መሆኑን ያሳያሉ ብዬ አስባለሁ፡፡
የሆነው ሆኖ እነዚህ ሁናቴዎች የፖለቲካውን ጉልበት ሙሉ በሙሉ በብአዴንና በተባባሪነት በጠቀስኳቸው የኦህዴድና ደህአዴን የአመራር አባላት አካባቢ ቢያከማቻቸውም፣ በማንኛውም ሰዓት ያሻውን ማድረግ የሚችለው የታጠቀው ኃይል ደግሞ ከህወሓት ጎን እንደተሰለፈ ይገኛል፡፡ መጪውን ጊዜም አዲስ ክስተት እንድንጠብቅ ገፊ ምክንያት ይህ አይነቱ የኃይል አሰላለፍ ይመስለኛል፡፡
 ምን እንጠብቅ?
ከረጅሙ የፓርቲ ፖለቲካና መንግስታዊ መንገራገጮች በኋላ፣ የሁለቱንም የኃይል መሰረቶች ጠቅልሎ በመዳፉ ሥር የከተተው መለስ ዜናዊ በሞተ ማግስት ‹የኃይል መገዳደሮች ሊከሰቱ ይችላሉ› የሚለው የብዙዎቹ ግምት ነበር፤ ከወራት በፊት አስነብቤ በነበረው ከላይ በተጠቀሰው ፅሁፍም ግምቶቹ እውን መሆን እንደ ጀመሩ ማሳያዎች ማቅረቤ ይታወሳል፡፡ ኢህአዴግ ውስጥ ራሳቸውን ያቧደኑት ኃይሎች ዋነኛ ግብ ከሥልጣን የሚነሱ ጥቅሞችና አነስተኛ የየራሳቸው ፓርቲ ፍላጎቶች የፈጠሩት በመሆኑ፣ እንደ ሟቹ ደመ-ቀዝቃዛ አምባገነን አይነት በጠንካራ መዳፍ ሥር የሚያሰባስባቸው ባለመገኘቱ በየጊዜው የኃይል መሸጋሸጎች ሊከሰቱ እንዲችሉ አድርጓቸዋል፤ አሁንም እየተስተዋለ ያለው ይኸው እውነታ ነው፡፡ በዚህ አውድ ላይ ቆመን ሊፈጠሩ የሚችሉ የቢሆን ሃሳቦችን ስናስቀምጥም በጠረጴዛው ላይ የምናገኘው ሁለት ዕድሎችን ይመስለኛል፡፡
የመጀመሪያ ሲናሪዮ የሚሆነው ከላይ የጠቀስኩት ቡድንተኝነት እንዳለ ሊቀጥል ይችላል የሚል ነው፤ ይህም የሚሆንበት ምክንያት ባለኝ መረጃዎች መሰረት የፖለቲካውን መስመር የያዘው ቡድን መሪ አባላት፣ አሁን ያላቸውን መንግስታዊ ሥልጣን ጠብቀው መቆየትን መሰረታዊ መሰባሰቢያ አጀንዳ ማድረጋቸው ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የሳሞራና ጌታቸው ጥምረት ህወሓትን ወደ ቀደመው ዘመኑ ለመመለስ ቢሻም፣ ሊሄድበት የሚችልበት መንገድ አደገኛ መሆኑ (ወታደራዊ ላዕላይ መዋቅሩንና የደህንነት ኃይሉን ከመያዙ አኳያ) ሁኔታዎችን ባሉበት ይዞ መቀጠልን በትርፍ-ኪሳራ ስሌት የተሻለ አማራጭ አድርጎ ይወስደዋል ብዬ አስባለሁ፡፡
 ሁለተኛው የቢሆን ዕድል፣ ዳግመኛ የኃይል መሸጋሸግ ሊፈጠር መቻሉ ነው፤ ሰዎቹ ጥቅመኛ በመሆናቸው የቋንቋ ተናጋሪነት ልዩነቶቻቸውንና የኋላ የመቆራቆስ ታሪኮቻቸውን ተሻግረው፣ አንዳቸው ከአንዳቸው ጋር ሌላ መልክ ያለው ስብስብ ሊፈጥሩ ይችሉ ይሆናል፤ ይህ አይነቱ አዲስ የኃይል አሰላለፍም፣ ከቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ በፊት በማይታወቀው ተሰዊና ሰዊ ሊጠናቀቅም ይችላል፡፡
 በመጨረሻም ምንም ይፈጠር ምን፤ እኛን ሊያግባባን የሚገባው ጭብጥ፣ የትኛውም ቡድን በግንባሩ ውስጥ ቢነሳ፣ የማዕከላዊ መንግስቱን ህልውና ወደሚበታትን ሂደት መግባቱ ሊሰካለት አለመቻሉ ነው፤ ምክንያቱም በዚህ መልኩ ሄዶ የሚጣሉበትን ጠረጴዛ መስበሩ ምን እንደሚያስከትል ያውቁታልና ወደዚህ ምዕራፍ እንደማይሻገሩ አምናለሁ፡፡ ይሁንና ከፓርቲው ዝግነት እና ከፖለቲከኞቹ አቋም የለሽነት አንፃር አሁንም ሆነ በቀጣይ ጊዜያት ከማንም ግምት ውጪ ያሉ ክስተቶች እንደ ደራሽ ውሃ ድንገት ሳይታሰብ ግንባሩን ሊያተራምሱት ይችላሉ ብሎ መገመቱ አግባብ ይመስለኛል፡፡
 Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of various information and content providers. The Website neither represents nor endorses the accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.
Related Posts:
•አዲሱ የኢህአዴግ አሰላለፍ –…
•ከፋውንዴሽኑ ጀርባ… (ክፍል ፩)…
•የኢህአዴግ ቀጣይ የፖለቲካ ሴራዎች…
•የደህንነት ከፍተኛ ባለስልጣን…
•13 ባለስልጣናት ተሾሙ

onsdag 18. desember 2013

Tight celebration of Nationalities’ Day in Jijiga shows Region’s instability: Observer


An Ethiopian government official, who preferred to remain anonymous, said to ESAT that during his stay in the region he leant that the main problem of the Region was the absence of peace.

He said although the government stated that the 8th Ethiopian Nations, Nationalities and Peoples’ Day Celebration in JigJiga, Ethiopia had ended without any problem, the truth was far from that.

In the suburbs of Jijiga city there were tanks, vehicles carrying heavy weapons, special commandos, fully armed soldiers and Federal police officers were giving a 24 hour protection while fighting helicopters were conducting surveillance. All vehicles were banned from moving on the Day. The official said the celebration was held inside the Stadium while the rest of the City looked like a city of death. Even in war zones, events are not celebrated under such a tight security, particularly foreigners and his own workmates that visited the city have come to understand what ‘peace’ meant in the ruling Front’s lexicon, the official added.

According to the source, the Speakers of the Houses of the Kenya and Rwanda, who have been invited as guests were under an inconvenience as they were provided appropriate reception and protocol. The Kenyan Speaker of the House was invited by Abadula Gemeda, his Ethiopian counterpart while the Ugandan Speaker of the House was invited by Kasa Teklebirhan, Speaker of the House of Federation of Ethiopia. When the two Speakers arrived at Jijiga airport, neither Abaduala nor Kasa were there to receive them at the airport. There were not also other officials who were there to accept them. After staying for a while at Jijiga airport, the Jijiga Police took them to Jijiga hotel with an old police vehicle. The official said the Hotel the two diplomats stayed in was below the standard. When the two guests arrived, Abadula and Kasa were taking pleasure in their guesthouse.

The incoming delegation was deeply angry at the uncharacteristic protocol they were provided as well as the quality of the Hotel they were forced to stay in. It is to be recalled that the officials of the Somali Regional Administration expressed their displeasure as the officials of the Federal government were not providing the proper ‘respect’ to guests from overseas.

søndag 15. desember 2013

Core leaders of the “Let Our Voices be Heard” told to defend


Main leaders of the Dimtaschen Yisema (Let Our Voices Be Heard) that were charged with terrorism have yesterday been told by the court in Ethiopia to defend. Twelve detainees have been acquitted and released.  “Terrorism” charges against Abubaker Ahmed and others have been dropped and changed to “inciting terror”.  Murad Shekur Jemal, Nuru Turki Nuru, Shekih Baheru Umar Shekur and journalist Yusuf Getachew have been ordered to defend the charges of “supporting terror”. The defendants have been ordered to present their defences between the dates of January 30 to February 4, 2014.
The solicitor of the defendants, Temam Ababulgo, said although the article that they were asked to defend reduces the punishment, he still thinks they should be acquitted fully. He said the government’s charge on article 3 which charged that “terror attacks have been committed”, has been annulled.
Temam said when the decisions were read out the defendants did not show any emotions. He said “my clients are religious teachers who know why they have been detained and teach us endurance”.
Abubakar Ahmed, Ahmedin Jebel Mohammed, Yasin Nuru Isali, Kemil Shemsu Siraj, Bedru Hussien Nur Hussien, Shekih Mekte Muhe Mekonen, Sabir Yirgu Mandefro, Mohammed Abate Tessema, Ahmed Mustefa Habib, Abubeker Alemu Muhe, Munir Hussien Hassen, Shekih Seid Ali Juhar, Mubarak Adem Getu Aliye and Kalid Ibrahim Balcha have been ordered to defend the charges.
Hassen Ali Shuraba, Shekih Sultan Haji Aman, Shekih Jemal Yasin Rajuju, Shekih Tahir Abdulkadir, Hassen Abi Seid, Ali Meki Bedru, Shekih Haj Ibrahim Tuhafi, Shekih Abdurahman Usman Kelil, Habiba Mohammed, Docter Kemal Haj Geletu and two other organisations have been acquitted.

ከ600 በላይ አባዎራዎች ቤታቸውን በ3 ቀናት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ ታዘዙ



ትእዛዙን የሰጠው የቦሌ ክፍለከተማ ሲሆን፣ ነዋሪዎቹ እስከ ማክሰኞ ቤታቸውን ለቀው ካልወጡ ፣ አፍራሽ ግብረሀይል በጉልበት እንደሚያፈርስባቸው አስታውቋል።
“በሶስት ቀናት ውስጥ የት እንሄዳለን?’ ሲሉ የሚጠይቁት ነዋሪዎች ፣በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባ የሚታየው የቤት ኪራይ መጨመር አስግቶናል ብለዋል። ሜዳ ላይ እንዃ እንዳንወድቅ ሜዳውም እየታረሰ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ምሬታቸውን ገልጸዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በኦሮሚያ ልዩ ዞን የሚገኙ ባለስልጣናት በስልጣናቸው ደሀ ገበሬዎችን እያፈናቀሉ ቦታዎቻቸውን እየወሰዱባቸው ነው። ነዋሪዎች እንደሚሉት አርሶአደሮች በጉልበት መሬታቸውን እየተቀሙ ለደነነት  ተዳርገዋል። መሬታቸውን ከተቀሙት አርሶ አደሮች መካከል በሰበታ ነዋሪ ከሆኑት አንዱ ሲናገሩ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሆኑት የአቶ ደምሴ ቡላ ባለቤት መሬታቸውን በጉልበት እንደነጠቁዋቸውና ክስ ሲመሰርቱም እንዳሳሰሩዋቸው ተናግረዋል።
በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ቤት ሰርተው ይኖሩ ነበሩ ሰዎች ቤቶቻቸው ከፈረሱባቸው በሁዋላ ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸው ይታወቃል።

onsdag 11. desember 2013

በኢትዮጵያ ለሚታየው መብራት መጥፋት መስሪያቤቶች እርስ በርስ እየተካሰሱ ነው



በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች እና በሰሜን የአገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ከተሞች መብራት በተደጋጋሚ እየተቋረጠ ሲሆን፣ መብራት ሀይል የተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተናበው ለመስራት አልቻሉም በሚል ወቀሳ አሰምቷል።  በጉዳዩ ዙሪያ ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው የኢትዩጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ     40 በመቶ የሚሆነው ኤሌክትሪክ ሃይል መቆራረጥ የሚፈጠረው በሰው ሰራሺ አደጋ ነው ያሉ ሲሆን፣  ከአዲስ አበባ መንገድ እና ትራንስፖርት ባለሰልጣን ጋር ተናበን መስራት ባለመቻላችን በዚህ አራት ወራት ብቻ የኤሌክትሪክ ባቡር መስመር ዝርጋታ በሚል ሰበብ ከ120 ሚልዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሞብናል ብለዋል፡፡
በቅርቡ በቦሌ ሩዋንዳ በኮንክሪት የተገነባው ባለ 33 ኪሎ ቮልት   ትራንስፎርመር እና መሰል እቃዎች የ በአዲስ አበባ የመንገድ ስራ ድርጅት የመንገድ ቁፋሮ ሃለፊነት በጎደለው ሁኔታ ከስሩ በመጣላቸው ከ450 ሺ ብር በላይ ንብረት መውደሙን  ገልጽዋል፡፡
የአዲስ አበባ መንገድ እና ትራንስፖርት ባለስልጣን በሚፈጥረው ችግር ደንበኞችን ማርካት አልቻልም  በዚህም የኤሌክትሪክ ሃይል ተጠቃሚ ደንበኞች ሮሮ እያሰሙ ነው በማለት ሀላፊው ተናግረዋል።
በተያያዘ ዜናም ከባህር ዳር አምስት ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኝ ይነሴ የገጠር ቀበሌ በ66 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ተሸካሚ ሰባት የብረት ታዎሮች በመዘረፋቸው በዚህ የኤሌክትሪክ መሰመር ሃይል የሚያገኙ በዳንግላ እና ፓዊ ሳብስቴሺን የሚገኙ ደንበኞች ሃይል አጥተዋል ፡፡ ምእራብ ጎጃም በከፊል  መራዊ ፤ ቢኮሎ ፤ ዱርቤቴ ፤ይስማላ ፤ሊበን ፤ቁንዝላ ፤ዲንካራ ፤ በሰሜን ጎንደር  ሻውራ እና አካባቢው ፤ በአዊ ዞን ዳንግላ ፤ቲሊሊ ፤ እንጅባራ  አዲስ ቅዳም ፤ግምጃ ቤት ፤መተክል ፤ ሰከላ፤ በቢንሻንጉል ጉምዝ መተከል ዞን በሙሉ በጨለማ ውስጥ መሆናቸውን አቶ ምስክር ነጋሺ ተናግረዋል፡፡
ኮርፖሬሺኑ ችግሩን ለመፍታት እየሰራሁ ነው ቢልም እስካሁን ድረስ የታየ ለውጥ የለም

40 በ 60 እና 10 በ 90 የቤት እቅዶች መንግስትን ፈተና ውስጥ ጥለውታል


መንግስት በውጭ አገር ለሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ሀቅሙ ላላቸው ዜጎች የ40 በ60 እንዲሁም በአዲስ አበባ በአነስተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ዜጎች ደግሞ የ10 በዘጠና እና የ20 በ80 የቤት ልማት እዶችን ዘርግቷል።
በ10/90 850 ሺ በ 20/80 ደግሞ 350 ሺ የአዲስ አበባ ነዋሪ ተመዝግቦ እድሉን በመጠባበቅ ላይ ሲሆን ከ12 ሺ በላይ በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ደግሞ 40 በ60 በሚባለው ውስጥ ታቅፈዋል።
በመርሀግብሩ ዝግጅት የተሳተፉ የውስጥ ምንጮች እንደገለጹት መንግስት ይህን እቅድ ለማሳካት ከፍተኛ የሆነ ፈተና ገጥሞታል ።
የውስጥ ምንጮች እንደሚሉት እቅዱን ለመተግበር 4 ዋና ዋና ችግሮች አጋጥሟል። የመጀመሪያው ችግር በሁሉም ደረጃዎች የተመዘገቡ ሰዎችን ፍላጎት ለማርካት ወደ 2 ሚሊዮን የሚደርሱ ቤቶች መገንባት ይኖርባቸዋል። ይህን ያክል ቤት ለመገንባት ደግሞ ቢያንስ 30 ሺ ሄክታር መሬት ስፋት ያለው ቦታ ያስፈልጋል። አዲስ አበባ ደግሞ ይህን ያክል ሰፊ መሬት ለማግኘት አትችልም።
የፌደራል መንግስቱ ለአዲስ አበባ ታላቅ የማስተር ፕላን በማዘጋጀት እና በማስተር ፕላኑ ውስጥ የኦሮሚያ ልዩ ዞኖች የሚባሉትን ሱሉልታ፣ ሰንዳፋና ገላንን በማካተት በቂ የቤት መስሪያ ቦታዎችን ለማፈላለግ እቅድ ነድፎ ቢንቀሳቀስም፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ” ከእንግዲህ መሬት ለአዲስ አበባ  መስተዳድር  መሬት የምንሰጠው በመቃብራችን ላይ ነው” የሚል አቋም በመውሰዱ እቅዱ ሳይሳካ ቀርቷል።
በኦሮሚያ ክልል አቋም አጣብቂኝ ውስጥ የገባው የፌደራሉ መንግስት ከተለያዩ መስሪያ ቤቶች የተውጣጡ ባለስልጣናትን በመሰብሰብ እና አንድ ኮሚቴ በማዋቀር ወደ ክልሎች ልኳቸዋል። እነዚህ ባለስልጣኖች ወደ ተለያዩ ክልሎች በመውረድ ክልሎች ለዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ቤት መስሪያ ቦታ እንዲያዘጋጁ ለማግባባት ይሞክራሉ። ክልሎች ፈቃደኛ ሆነው ሲገኙ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የዲያስፖራ አባላት ከአዲስ አበባ ወጣ ብለው በክልሎች ግንባታ እንዲያካሂዱ ለማግባባት እንቅስቃሴ ይጀምራሉ።
መንግስት ከዳያስፖራው የሰበሰበውን ገንዘብ ለመመለስ ፈቃደኛ ባለመሆኑ የቀረው ምርጫ የዲያስፖራ ቤተ ሰሪዎችን በክልሎች ሄደው እንዲሰሩ ማግባባት መሆኑን ምንጮች ይናገራሉ። በዘር ላይ የተመሰረተው የፌደራል ስርአት የአንዱ ክልል ወደ ሌላው ክልል ሄዶ ቤት ለመስራት እንቅፋት የሚፈጥር በመሆኑ መንግስትን ለተጨማሪ ራስ ምታት ዳርጎታል።
መንግስትን የገጠመው ሌላው ፈተና የገንዘብ እጥረት ነው። ንግድ ባንክ ለቤቶች ግንባታ የሚሆን 12 ቢሊዮን ብር ብድር መስጠት የሚኖርበት ሲሆን፣ በቅርቡ የንግድ ባንኩ ፕሬዚዳንት ከጠ/ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ጋር በተገናኙበት ወቅት ባንካቸው ማበደር የሚችለው 6 ቢሊዮን ብር ብቻ መሆኑን ገልጸውላቸዋል። አቶ ሀይለማርያምም ባንኩ ቢያንስ 10 ቢሊዮን ብር ማበደር እንዳለበት ትእዛዝ ሰጥተዋል። ባንኩም ለታዋቂዎቹ የመጠጥ አምራች ድርጅቶች ማለትም ለሀይነከንና ዲያጎ የቢራ አምራች ፋብሪካዎች ፈቅዶት የነበረውን የ3 ቢሊዮን ብር የብድር ውል በመሰረዝ፣ ድርጅቶቹ 560 ሚሊዮን ብር ብቻ እንዲበደሩ በማድረግ ቀሪውን ገንዘብ ለዚሁ ፕሮጀክት ለማዋል  ተስማምቷል። ባንኩ እስካሁን 8 ቢሊዮን ብር ለማሰባሰብ የቻለ ሲሆን፣ የመንግስትን ጥያቄ ለማሙዋላት ተጨማሪ 2 ቢሊዮን ብር ከየት እንደሚያመጣ ግልጽ አልሆነም።
በሌላ በኩል ደግሞ የቤቶች መስሪያ ዋጋ መጀመሪያ ከታቀደበት መጠን እንዲከለስ ተደርጓል። በመጀመሪያ ለ3 መኝታ ቤት መስሪያ የተመደበው ገንዘብ 385 ሺ የነበረ ሲሆን በተከለሰው አዲስ ዋጋ ግን ይህ ዋጋ  በእጥፍ አድጎ 779 ሺ ብር እንዲሆን ተደርጓል። ይህ ዋጋ በቅርቡ እየታየ ያለውን የዋጋ ንረት ግምት ውስጥ በማስገባት ወደ አንድ ሚሊዮን እንደሚጠጋ ምንጮች ገልጸዋል። ዲያስፖራው ይህን ገንዘብ ግማሹን በአንድ ጊዜ ቀሪውን ደግሞ በአንድ ወር ውስጥ እንዲከፍል ይጠበቅበታል። አስገራሚው ነገር ይላሉ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች፣ መንግስት ከሚሰራው ቤት የተሻለ ጥራት ያለው ቤት በ450 ሺ ብር ማግኘት መቻሉ ነው።
ንግድ ባንክ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ሲመዘግብ ቆይቶ በመጨረሻም ምዘገባው እንዲቋረጥ ማድረጉ ይታወቃል። የኢትዮጵያ ዜግነት ያላቸው የዲያስፖራ አባላት እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ በብር መክፈል ሲገባቸው በዶላር እንዲከፍሉ መገደዳቸው የአገሪቱን ህግ ከመጻረሩም በላይ ፣ መንግስት ራሱ ለሚያትመው ብር ዋጋ እንዳልሰጠ የሚያመለክትና ለብር ውድቀት ሌላ ምክንያት የሚሆን ነው በሚል ምዝገባው ተቋርጧል።
መንግስት ከዳያስፖራው ገንዘብ በዶላር ለመቀበል የፈለገበት አንዱ ምክንያት ከአባይ ግድብ ጋር የተያያዘ መሆኑን ምንጮች ይገልጻሉ። አቶ መለስ በህይወት በነበሩበት ጊዜ ዲያስፖራው ለግድቡ ማሰሪያ 1 ቢሊዮን ዶላር ያዋጣል የሚል እቅድ ዘርግተው ነበር። ይሁን እንጅ እስከዛሬ የተሰበሰበው 19 ሚሊዮን ዶላር ብቻ መሆኑ ያስደነገጣቸው የመንግስት ባለስልጣናት በቤት ግንባታ ስም ለግድቡ ማሰሪያ ተጨማሪ ገንዘብ ለማሰባሰብ ተጨማሪ እቅድ ቢያቅዱም ይህም እቅድ አደጋ ገጥሞታል።
ፕሮጀክቶችን ለማስፈጸም ሌላው ችግር የሆነው ተናቦ ለመስራት አለመቻል መሆኑን የውስጥ አዋቂዎች ይገልጻሉ። ለቤቶች ግንባታ ሃላፊነት በተሰጣቸው ሚኒስትር መኩሪያ ሀይሌ፣ በአዲስ አበባው ከንቲና ድሪባ ኩማ፣ በንግድ ባንክ ፕሬዚዳንትና በውጭ ግንኙነት ሚ/ሩ ቴዎድሮስ አዳህኖም መካከል መናበብ በመጥፋቱ ፕሮጀክቱ ባለበት የቆመ ሲሆን፣በተለይም እያንዳንዱ ባለስልጣን ኢህአዴግን ከመውደቅ ያዳንኩት እኔ ነኝ ለማለት ሁሉም የራሱን እቅድ አውጥቶ ሳይናበብ እየሰራ መሆኑን ምንጮች ተናግረዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ አዲስ አበባን ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማን ለማነጋገር ስልክ ብንደውልላቸውም ሌላ ጊዜ ደውሉ ካሉን በሁዋላ በተለያዩ ጊዜያት ብንደውልም ልናገኛቸው አልቻልም። የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት አቶ አለማየሁ አቶምሳም ስልክ በደወልንበት ወቅት  ለተጨማሪ ህክምና ወደ ውጭ በመውጣታቸው ልናገኛቸው አልቻልንም። በዚህ ጉዳይ የተሰራውን ዝግጅት በቅርቡ የምናቀርብ መሆናችንን ለመግለጽ እንወዳለን።

tirsdag 10. desember 2013

የቦንጋ አስተዳዳሪ ከመምህራን ጋር ለመወያየት ቀጠሮ ያዙ


ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በሚል ያለፈቃዳቸው የአንድ ወር ደሞዛቸው የተቆረጠባቸው የቦንጋ መምህራን፣ የስራ ማቆም አድማ እንደሚያደርጉ ካስታወቁ በሁዋላ፣ ዋና አስተዳዳሪው ማከስኞ ከመምህራን ጋር ለመነጋገር ቀጠሮ መያዛቸው ታውቛል።
ከመምህራን ተወካዮች ጋር የተነጋገሩት ባለስልጣኑ፣ ስምምነት ለመድረስ ባለመቻላቸው ከመላው መምህራን ጋር ለመነጋገር ወስነዋል። መምህራን የተቆረጠባቸው ደሞዝ መልሶ የማይሰጣቸው ከሆነ በአድማው ለመቀጠል እየተናገሩ ነው።

የሶማሊ ክልል ለመከላከያ አዛዦች አዛዦች የመክበሪያ ቦታ መሆኗን ምንጮች አስታወቁ



በጅጅጋ ከፍተኛ መስሪያ ቤቶች ውስጥ የሚሰሩ የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የህወሀት  ከፍተኛ የመከላከያ አዛዦች ወደ ሶማሊ ክልል ሲመዱ  ከክልሉ መንግስት ጋር በመተባበር ከፍተኛ ሀብት አጋብሰው እንደሚመለሱ ተናግረዋል።
በአሁኑ ጊዜ ተቀማጭነታቸው ጅጅጋ የሆኑት እና በክልሉ ቁጥር አንድ ሀብታም የሚባሉት /ወ/ት ሀዋ የሌተናንት ጄኔራል ዮሀንስ ገ/መስቀል ሁለተኛ ሚስትና የልጅ እናት ሲሆኑ፣ ግለሰቧ ከተራ ጫት ነጋዴነት በአንድ ጊዜ በብዙ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ሀብት ለማጋበስ የቻሉት በፍቅር ጓደናቸው አማካኝነት መሆኑን ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ ሰራተኞች ለኢሳት ገልጸዋል።
ጄኔራል ዮሐንስ ከወ/ት ሀዋ ጋር የተዋወቁት በኮሎኔልነት ማእረግ የምእራብ ጎዴ አዛዥ በነበሩበት ወቅት ሲሆን፣ በወቅቱ ክልሉ ያወጣውን የምእራብ ጎዴን የካናል ጠረጋ የመከላከያ ሰራዊት እንዲያሸንፍ በማስደረግና የሰራዊቱ አዛዥም ስራውን ወ/ት ሀዋ ኩባንያ አቋቁመው በሰብ ኮንትራትነት እንዲሰጣቸው በማድረግ በአንድ ጊዜ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ እንዲያገኙ አድርገዋቸዋል።
በጄኔራል ዮሀንስና በወ/ት ሀዋ መካከል ያለው የፍቅር ግንኙነት እየደራ ሲሄድ፣ ወ/ት ሀዋ ከፍተኛ ሀይል እየተሰማቸው ከታክስ ጋር በተያያዘ ጥያቄ የሚያቀርቡባቸውን የክልል ሰራተኞችን ሳይቀር የመከላከያን መኪኖች ይዞ በመሄድ በማስፈራራት ከግብር ራሳቸውን ነጻ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ምንጮች ይናገራሉ።
ወ/ት ሀዋ ከፍቅር ጓደኛቸው ከጄ/ል ዮሐንስ ጋር በመሆን ባቋቋሙት ኩባንያ በጅጅጋ ሁለት ታላላቅ ፎቆችን የገነቡ ሲሆን፣ ከዚህም በተጨማሪ ያለምንም ጫረታ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ሀብት የፈሰሰባቸውን ፕሮጀክቶች እንዲሰሩ ተፈቅዶላቸዋል።
ከፕሮጅቶች መካከል የቀብሪ ደሀር የውሀ አቅርቦት፣ የደገሀቡር የውሀ አቅርቦት፣ ጅጅጋ መምህራን ማሰልጠኛ ማስፋፊያ፣ የክልል የትምህርት ቢሮ ፕሮጀክት፣ ጅጅጋ አየር ማረፊያ አካባቢ የሚገኘው ዘመናዊ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ግንባታና ሌሎችንም ውድ ፕሮጀክቶች ይገኙበታል። ምንም እንኳ /ወ/ት ሀዋ ግንባር ቀደም ሆነው ሀብቱን ቢቆጣጠሩትም ከጀርባ ሆነው የክልሉን ፕሮጀክቶች የሚያሰሩት ጄኔራል ዮሐንስ መሆናቸውን ምንጮች ይናገራሉ።
ጄ/ል ዮሐንስ በአዲስ አበባ ቦሌ መድሀኒያለም አካባቢ እጅግ ዘመናዊ ፎቅ አሰርተዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ በክልሉ ውስጥ አሁን በመከላከያ አዛዥነት የሚንቀሳቀሱ አንድ የህወሀት የመከላከያ ኮሎኔል የክልሉ ፕሬዚዳንት የትውልድ ቦታ ላይ አንድ የውሀ ፕሮጀክት እንዲሰሩ የ120 ሚሊዮን ብር ተፈራርመው ስራውን ከጀመሩ በሁዋላና አስፈላጊው ክፍያ ከተፈጸመ በሁዋላ ፐሮጀክቱ አለመሳካቱን ምንጮች ገልጸዋል። ባለፈው ወር ለእኝሁ ኮሎኔል 22 ሚሊዮን ብር ከክልል መስተዳደር ወጪ ተደርጎ እንደተከፈላቸውም ምንጮች ገልጸዋል።
ሰሞኑን በተከበረው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ዝግጀቶችን ከማዘጋጀት ጀምሮ የሽያጭ እቃዎችን እስከማቅርብ የሚደረሱ ስራዎችን ከህወሀት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው ሰዎች በኮንትራት ወስደው ከፍተኛ ትርፍ እንዳገኙበት እነዚሁ የመስተዳድሩ የአስተዳደር ሰራተኞች ገልጸዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ የክልሉን ጽሬዚዳንት ለማነጋገር ወደ ጽህፈት ቤታቸውው ስልክ ብንደውልም አልተሳካልንም።

fredag 6. desember 2013

በላይ አርማጭሆ ትክል ድንጋይ ወረዳ አንድ አውቶቡስ ተገልብጦ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት በአደጋው 40 ሰዎች የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል። የአደጋው መንስኤም ከአቅም በላይ ጭነት መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል።
በጭልጋ ወረዳ ደግሞ አንድ ነዳጅ የጫነ ቦቴ መኪና ተገልብጦ ተሽከርካሪዎች ለመተላላፍ ባለማቻላቸው መቸገራቸውን ለማወቅ ተችሎአል።
መኪናው ነዳጅ እንደጫነ በመገልበጡ እሳት ይፈጠራል የሚል ስጋት ማሳደሩን የአካባቢው ሰዎች ግልጸዋል።

ጅጅጋ በከፍተኛ ወታደራዊ ጥበቃ ስር ናት

8ኛውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ለማክበር በሚል የጅጅጋ ከተማ በፌደራል ፖሊስ  አባላት መወረሯን ነዋሪዎች ገልጸዋል። የፌደራል ፖሊስ አባላት ከተማውን ከተቆጣጠሩት በሁዋላ ልዩ ፖሊስ እየተባሉ የሚጠሩት ሀይሎችን ወደ ዳር የገፉዋቸው ሲሆን፣ ፖሊሶቹ በየተወሰኑ ሜትሮች ቁጥጥር እያደረጉ ነው። የጸጥታ ጥበቃው በሄሊኮፕተር ላይ በሚደረግ ቅኝት የታጀበ ሲሆን፣ በየ አቅጣጫውም በዙ 23 እና በሌሎች ከባድ መሳሪያዎች ጥበቃ እየተደረገ ነው። ጄኔራል ሳሞራ የኑስ ከሶስት ቀናት በፊት የአካባቢው የጸጥታ አጠባበቅ ምን እንደሚመስል ጎብኝተው መመሪያ ሰጥተው መሄዳቸው ታውቋል።
የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት በቅርቡ በእጅ ስልካቸው ላይ ከአልሸባብ መልክት እንደደረሳቸው መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን፣ በትናንትናው እለት ደግሞ እንግዶች ከሚያርፉበት የክልሉ መስተዳድር ግቢ ውስጥ 4 የተቀበሩ ፈንጆች በአነፍናፊ ውሾች መገኘታቸውን ጅጅጋ የሚገኙ የውስጥ ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል። ፈንጂዎቹ እንደተገኙም እንግዶቹ ” ተረፍን” ሲባባሉ ተሰምቷል። ሁኔታው በበአሉ ላይ ለመገኘት በሄዱ የክልል ባለስልጣኖች ላይ ከፍተኛ ድንጋጤ መፍጠሩንም የቅርብ ምንጮች ገልጸዋል።
ለበአሉ ከክልሎች የመጡ ዋና ዋና እንግዶች የመስተዳድሩ መስሪያ ቤቶች ተዘግተው፣ በመስተዳድሩ ግቢ ውስጥ አልጋ ተዘርግቶላቸው እንዳረፉ መዘገባችን ይታወሳል።
ይህ ከ250 ሚሊዮን ብር በላይ የወጣበት ዝግጅት በወጪ ደረጃ  አምና በባህርዳር የተካሄደውን ዝግጅት በ50 ሚሊዮን ብር እንደሚበልጥ ለማወቅ ተችሎአል። ከፍተኛ ሙስና ተፈጽሞበታል በተባለው በዚህ ዝግጅት ላይ አርቲስቶች በተለይም የህወሀት ሰዎች ከፍተኛ ተጠቃሚዎች መሆናቸውን የደረሰን መረጃ ያሳያል። አርቲስት ኪሮስ ወልደስላሴ የማስታወቂያውን ስራ ለመስራት 8 ሚሊዮን ብር ውል የተፈራረመ ሲሆን፣ የባዛር ዝግጅቱን እና በባዛሩ ላይ ለሽያጭ የቀረቡት᎐ አብዛኞቹ የህወሀት ኩባንያዎች ምርቶች መሆናቸው ታውቋል።
ውድ ተመልካቾቻችን በክልሉ ውስጥ የህወሀት ጄኔራሎች ስለገነቡት የሀብት ኢምፓየርና ለበአሉ እንዲደርስ ተሰርቶ  በዛሬው እለት እንደፈረሰ በተነገረለት የመለስ ሀውልት ዙሪያ ላይ  በነገው እለት ተጨማሪ ዘገባ ይዘን እንቀርባለን።

ከሳውድ አረቢያ ከሚመለሱ ኢትዮጵያውያን ጋር በተያያዘ የመንግስት እንቅስቃሴ እየተተቸ ነው

የመኖሪያና የስራ ፈቃድ የላችሁም በሚል ከሳዑዲዓረቢያ ወደ አገራቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ሲሆን ቁጥሩ መንግስት አስቀድሞ ካሰበው እጅግ አሻቅቧል፡፡ በዚህ ም ምክንያት ተመላሾቹን ለመቀበልና ለማቋቋም  መንግስት በቂ በጀት አለመያዙ እንደ አገር አሳፋሪ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልጸዋል፡፡
መንግስት የተመላሾቹ ቁጥር 23 ሺ ገደማ መሆኑንና እነዚህም ወገኖች ለመመለስ መመዝገባቸውን በመግለጽ ለተመላሾቹ 50 ሚሊየን ብር እንደመበ መግለጹ ይታወቃል፡፡ ይህም ሆኖ የተመላሾቹ ቁጥር ከፍተኛ መሆኑ ከታወቀ በሁዋላ እንደገና መረጃውን በማሻሻል ተመላሾቹ ከ50 እስከ 80 ሺ እንደሚገመቱ ይፋ አደርጎአል፡፡ ይሁን እንጅ እስትናንት ድረስ ከ100 ሺ በላይ ሰዎች መመለሳቸውን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡ከነዚህ መካከል 8 ሺህ የሚሆኑት ነፍሰ ጡር መሆናቸው ተገልጿል ፡፡
መንግስት ለተመላሾቹ 50 ሚሊየን ብር መመደቡን ከመግለጽ ውጪ መልሶ ለማቋቋም ምንም ያሰበው
ነገር አለመኖሩን የጠቀሱት ምንጮቹ  ተመላሾቹን ተቀብሎ በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ጊዜያዊ ማረፊያ ካቆየ በኃላ ክልሎች ስራ ይሰጡዋቹሃል በማለት እያባበለ ወደትውልድ አካባቢቸው እንዲሄዱ እያደረገ መሆኑን  ጠቁመዋል፡፡ተመላሾቹ  በሰው አገር መከራና ስቃይን ከማሳለፍ ባሻገር  ያፈሩትን ሐብትና ገንዘብ ይዘው መመለስ አለመቻላቸውን ያስታወሱት እነዚሁ ምንጮች በዚህ ሁኔታ ላይ ያሉትንና  በተስፋ መቁረጥ የተጎዱትን ወገኖች በባዶ እጅ ወደ ቤተሰብ መስደድ እጅግ አሳዛኝ ነው ብለዋል ፡፡
በፌዴራል ዋና ኦዲተር ሪፖርት መሰረት መከላከያና ሌሎች መንግስታዊ መ/ቤቶች  በ2004 የበጀት አመት 3 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ያለበቂ ሰነድና ተጠያቂነት በባከኑበት አገር፤ በአንጻሩ ከስደት ተመላሽ ዜጎች በበቂ ሁኔታ እንኩዋን መረዳት የሚችሉበት ሁኔታ አለመመቻቸቱ፣ ጉዳያቸውም ለፖለቲካ ፍጆታ መጠቀሚያ ብቻ መዋሉ ያስቆጫል ብለዋል᎗ የኢሳት የአዲስ አበባ ዘጋቢ ያነጋገራቸው ወገኖች፡፡
መንግስት ለተመላሽ ወገኞች ህዝቡ እርዳታ እንዲደርግ ባቀረበው ጥሪ መሰረት ባላሃብቶች ሰባት ሚሊየን ብር ለመለገስ ቃል የገቡ ሲሆን ከዚህም ውስጥ ሁለት ሚሊየን ብሩ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የለገሰችው ነው፡፡ በአጠቃላይ እስካሁን ያለው የዕርዳታ ጥያቄ ምላሽ አጥጋቢ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን በመንግስት በኩልም ተጨማሪ በጀት መድቦ ሰዎቹን በዘላቂነት ለማቋቋም ፍላጎት አለመታየቱ አሳዛኝ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች እየገለጹ ነው ።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በሳዑዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈፀመውን ግፍ በመቃወም በስዊዘርላንድ ለሁለተኛ ጊዜ የተቃውሞ ሰልፍ ተደርጓል።
ከሳምንት በፊት በስዊዘርላንድ-በርን በሚገኘው የሳኡዲ አረቢያ ኤምባሲ ፊት ለፊት በመውጣት ተቃውሟቸውን የገለጹት ኢትዮጵያውያን፤ በጀኔቭ ከተማ ለሁለተኛ ጊዜ ባደረጉት ሰልፍ በወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ላይ እየተፈፀመ ያለውንና ሊያባራ ያልቻለውን ግፍና ሰቆቃ አውግዘዋል።
በጀኔቭ የተባበሩት መንግስታት ዋና ጽህፈት ቤት  በተደረገው ሰልፍ ኢትዮጵያውያኑ በዜጎቻቸው ላይ እየተፈፀመ ያለውን ግፍ ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ ከማሰማታቸውም ባሻገር የቪዲዮ ማስረጃዎቸን  በ አንድ ላይ አሰባስበው በማደራጀት ለጽህፈት ቤቱ እንዲደርስ አድርገዋል።
ከቀኑ 14 ሰዓት እስከ 17 ሰዓት በቆየው በዚሁ ሰልፍ ላይ ፓርቲያቸውን በውጭ ሃገራት የማስተዋወቅ ተግባር እያከናወኑ ያሉት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ-መንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ተሳትፈዋል።
ከአስተባባሪዎቹ -አንዱ የሆነው ወጣት አክቲቪስት ጴጥሮስ አሸናፊ ሰልፉን አስመልክቶ ከኢሳት ጋር ባደረገው አጭር ቆይታ፤የወገኖቻችን ሰቆቃ እስኪያባራ ድረስ ያለድካምና መታከት ጩኸታችንን  ለዓለማቀፉ ማህበረሰብ ማሰማታችንን እንቀጥላለን ብሏል።
በሰልፉ ላይ የኢትዮጵያውያኑን ስሜት የነካ ግጥም ያቀረበችው ወጣት ነጃት በበኩሏ-ከሁሉም በተለየ መልኩ ግፉና መከራው ኢትዮጵያውያን ላይ ብቻ ማየሉ እረፍት እንደነሳት ትናገራለች።
ለሰልፈኞቹ ንግግር እንዲያደርጉ የተጋበዙት የሰማያዊነፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በበኩላቸው፤በኢትዮጵያ ለወገኖቻቸው ድምፃቸውን ለማሰማት ባልቻሉበት ወቅት ወደ  ወጪ አገር መጥተው  ለመሰለፍ  መብቃታቸው እንዳስገረማቸው ተናግረዋል።

onsdag 4. desember 2013

በጅጅጋ የሚታየው ስረአት አልባነት ተባብሷል



በጅጅጋ በማንኛውም ሰአት ዜጎች ቤታቸው በጸጥታ ሀይሎች ይፈታሻል። የጸጥታ ሀይሎችም ከሞባይል ስልክ ጀምሮ እስከ ላፕቶፕ እንዲሁም ገንዘብ ይወስዳሉ። የቀበሌ መታወቂያዎችን ሳይዙ ከሄዱ ደግሞ ተጠርጥረው ይያዛሉ። የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚሉት ጅጅጋ ለኢትዮጵያውያን ከሳውድ አረቢያ በላይ የስቃይ መሬት ሆናለች ።
አንድንድ ምንጮች እንደሚሉት ችግሩን የተወሳሰበ ያደረገው አልሸባብ  በጅጅጋው ፕሬዝዳንት የግል ሞባይል ላይ የብሄር ብሄረሰቦች በአል በከተማዋ የሚከበር ከሆነ  እርምጃ እንደሚወስድ መሀላ ያለበት የዛቻ ኤስ ኤም ኤስ መላኩን ተከትሎ
ከፍተኛ ፍተሻ በየጎዳናው እየተደረገ ሲሆን ከነሱ ጋር ግንኙነት አለህ በሚል አንድ የጅጅጋ ነዋሪ ጫካ ተወስዶ  ሲደበድቡት በድንገት በመሞቱ ለቤተሰቡ 50 ሺ ብር ካሳ ተሰጥቶ ሬሳው ከከተማ ውጭ እንዲቀበር ተደርጓል፡፡  ከአልሸባብ ጋር በተያያዘም አንዲት ወጣት ሴት ከአካባቢው ተወስዳ ማእከላዊ ታስራ መደፈሩዋም ታውቋል፡፡
ህዳር 29 የሚከበረውን  የብሄር ብሄረሰቦች ቀን  እንዲሳተፉ የተጋበዙ አንዳንድ የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር የካቢኔ አባላት በጸጥታና ደህንነት ምክንያት ለመሄድ አለመፈለጋቸውንም የደረሰን መረጃ ያመለክታል።  ይህንን ተከትሎም ከፍተኛ ባለስልጣኖች ለካቢኔ አባላት ጠንካራ ደብዳቤ በመጻፍ በስፍራው እንዲገኙ እያዘዙ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ  በኢ.ፌ.ዳ.ሪ. የፌዳሬሽን ምክር ቤት እና በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልላዊ መንግሥት ትብብር 8ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል አከባበር ለውይይት የቀረበ በሚል ርእስ የተዘጋጀው ጽሁፍ ለኢሳት አስቀድሞ የደረሰው ሲሆን  በጽሁፉ ውስጥ ስለክልሉ ታሪክ አነጋጋሪ የሆኑ ጉዳዮች መካተታቸውን ተመልክቷል።
በጽሁፉ ውስጥ “የአቢሲንያ መኳንንት ወደ በረሃው የሚወርዱት ሊያጋጥም የሚችለውን የወባ በሽታ በሚክስ ደረጃ ፈጣንና ትርፋማ የከብት ዘረፋ ለማድረግ ብቻ ነው፡፡” ለምሳሌ ሽፍቶችን በማጥፋት ስም የአፄ ምኒሌክ ጦር አባላት በ1902 እ.ኤ.አ. ከ50ሺ በላይ የእንስሳት ሀብት ከማኅበረሰቡ ተዘርፎ በጅጅጋ በኩል ወደ ሀረር እንዲላክ ተደርጓል፡፡ ” ይላል።
በኀይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥትም የክልሉ ሕዝቦች እንደ ሌሎች የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በሀገሪቷ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ተገለው የቆዩበት ጊዛ ነበር ካለ በሁዋላ፣ የጭቆና ቀንበራቸውን በመጫንና ሕዝቡን ለመቆጣጠር ጥቂት ለሆዲቸው ለኖሩ የጎሳ መሪዎች የተወሰነ ጊዚያዊ ጥቅም በመስጠትና በማታለል ይንቀሳቀሱ ነበር ብለዋል፡፡ የኢጣሊያ ወራሪ ኀይል ኢትዮጵያን ቅኝ ለመግዛት በሚያደርገው ዝግጅት የተደናገጡት አፄ ኀይለስላሴ በመጀመርያ ጊዜ የክልሉን ታዋቂ ግለሰቦችና የጎሳ መሪዎች ሀረር ላይና በመቀጠል በቀብሪደሀር ከተማ በመሰብሰብ የክልሉ ሕዝብ ሀገሪቷን ከወራሪው ኀይሌ እንዲከላከል ጠይቀው ነበር ጽሁፉ ያመለክታል፡፡ጽሁፉ በኢህአዴግ ዘመን ለክልሉ የተሻለ እድል መምጣቱንም ያትታል።

ኢህአዴግ ለግንቦት7 ያቀረበው የእንደራደር ጥያቄ የተለያዩ አስተያየቶችን እያስተናገደ ነው

በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚኖሩ ዜጎች በስልክ እየሰጡ ባለው አስተያየት  ግንቦት7 ከኢህአዴግ ጋር መነጋገሩን አይደግፉም። አብዛኞቹ የሚሰጡት ምክንያት ደግሞ “ኢህአዴግ ተዳክሟል፣ ኢህአዴግ የሚታመን ድርጅት አይደለም” የሚሉ ናቸው። በዚህ ዙሪያ ኢትዮጵያውያን የሰጡት አስተያየት የሚከተለውን ይመስላል
በሌላ በኩል ደግሞ የተወሰኑ ኢትዮጵያውያን የድርድሩ ዜና መልካም ወሬ መሆኑን ለኢሳት በላኩት የኢሜል መልክት አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉም ፓርቲዎች በሰላም ተነጋግረው ለአገራቸው ቢሰሩ መልካም መሆኑን የጠቀሱት እነዚህ አስተያየት ሰጪዎች ድርድሩ ከልብ የመጣና ኢህአዴግ እውነተኛ ለውጥ ለማምጣት ዝግጁ ከሆነ፣ ለአገሪቱ መልካም ዜና ነው ብለዋል።
ኢህአዴግ ለግንቦት7 የድርድር ጥያቄ ማቅረቡን መዘገባችን  ይታወቃል። ግንቦት 7 በተለያዩ ምክንያቶች የቀረበለትን  ድርድር ሳይቀበለው ቀርቷል።

mandag 2. desember 2013

አለማቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተቆርቋሪ ድርጅት የሳውድ አረቢያ መንግስት በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ ለተፈጸመው ጥቃት ምርመራ እንዲያደርግና እርምጃ እንዲወስድ አሳሰበ

ህዳር ፳፫(ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-ሂውማን ራይትስ ወች ባወጣው መግለጫ የሳውዲ የጸጥታ ሀይሎችና የሳውዲ ዜጎች በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ የሀይል እርምጃ በመውስድ ጉዳት አድርሰዋል። በኢትዮጵያውያን ሰራተኞች ላይ ለተፈጸመው ጥቃት የሳውድ አረቢያ መንግስት አስፈላጊውን  ምርመራ በማድረግ በአጥፊዎቹ ላይ ተገቢውን እርምጃ ሊወስድ ይገባል ያለው ድርጅቱ በአሁኑ ሰአት በማጎሪያ ካምፖች ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በቶሎ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እስከዚያው በቂ ምግብ፣ መጠለያና የህክምና አገልግሎት እንዲሰጣቸው ጠይቋል።
የሳውዲ መንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና ዜጎች በኢትዮጵያውያን ላይ ጥቃት ከመፈጸሙ በፊት ፣ ኢትዮጵያውያንን የሚያጥላሉ ቅስቀሳዎች ይደረጉ እንደነበር ድርጅቱ አያይዞ ጠቅሷል።

ኢህአዴግ ለግንቦት7 የድርድር ጥያቄ አቀረበ



ህዳር ፳፫(ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሰዎች እንደገለጹት ኢህአዴግ የእንደራደር ጥያቄውን በሁሉት ወር ጊዜ ውስጥ ለ3ኛ ጊዜ ማቅረቡ ነው።
ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ኢሳት ላቀረበው ጥያቄ በሰጠው የጽሁፍ መልስ “የእንደራደር” ጥያቄ እንደቀረበለት አምኖ፣ “ይሁን እንጅ ንቅናቄው በዋናነት  ወያኔ እንደለመደው ድርድርን ለውጥረት ማስተንፈሻነት ለመጠቀም” ያደረገው ነው ብሎአል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚመኘውም ሆነ ግንቦት 7 የሚፈልገው ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በሰላማዊ መንገድ በሚደረግ ትግልና በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረጉ ዉይይቶች ቢመጣ መሆኑን ጠቅሶ ንቅናቄውን ሁለገብ ትግል ውስጥ እንዲገባ ያስገደደው የወያኔ እምቢተኝነትና እብሪት ብቻ ነው ብሎአል። የድርድር ሂደትን በሚመለከት ሁሌም ለድርድር ክፍት መሆኑን የገለጸው ግንቦት7፣  ይህ የድርድር ሂደት እንዲያው ለለበጣ የሚደረግ ሳይሆን ወደሚፈለገው ነጻነት በአነስተኛ መስዕዋትነት ሊያደርስ ይችል ከሆነ በሩን ላለመዝጋት እንጂ፣ በምንም አይነት ኢትዮጵያን እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሀገር ማድረግን፤ የሚቀይር ወይንም ከዚያ ያነሰ ውጤትን ለመቀበል መፍቀድን ፈጽሞ የማያመለክት ነው ሲል አቋሙን ገልጿል።
የግንቦት 7 ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የእንደራደር መልዕክት እንደደረሰው በጉዳዩ ዙሪያ በሰፊው እንደተወያየመበት በመጥቀስ የኢትዮጵያን ሕዝብ ባጠቃላይ እንጂ ግንቦት 7ን ብቻ የሚመለከት ጉዳይ እንዳልሆነ ከድምዳሜ ላይ መድረሱንም በመግለጫው አመልክቷል።
ንቅናቄው አክሎም ኢህአዴግ የ “እንደራደር” ጥያቄውን ከዚህ በፊት እንዳደረገው ለገባበት የፖለቲካ ውጥረት ማስተንፈሻ፣ ለውሸት ፕሮፓጋንዳው መጠቀሚያ፤ ለጊዜያዊ የፖለቲካ ትርፍ መሰብሰቢያ፤ የዴሞክራሲ ታጋዮችን ትጥቅ ማስፈቺያና ወኔ መስለቢያ አድርጎ እንዲጠቀምበት እንደማይፈቅድለት ገልጿል።
ምንም ዓይነት ድርድር ከመደረጉ በፊት መንግስት ጉዳዩን ከምር የወሰደው መሆኑን የሚያሳዩ “የመተማመኛ” እርምጃዎች መውሰድ ተገቢ መሆኑን የገለጸው ድርጅቱ ከእነዚህም መተማመኛዎች መካከል   ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች፤ ጋዜጠኞች፤ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ፣ በግልጽ የሚታወቁ እስረኞችን ብቻ ሳይሆን በድብቅ የተቋቋሙ ማጎሪያና ማሰቃያ ቤቶች ያሉትን ሁሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መፍታት ፣  በሕዝብ በተለይ በተቃዎሚ ኃይሎች ላይ በየቀኑ እያካሄደ ያለውን ወከባና እንግልት ባስቸኳይ ማቆም፣ ሰብዓዊና የዜግነት መብታቸውን ማክበር ፣  በፖለቲካ ምክንያት ከዚህ በፊት የተወሰዱ ሁሉም ዓይነት ፍርድ ተብየ ውሳኔዎች እንዲሻሩ ማድረግ፤ በሂደት ላይ ያሉ ከፖለቲካ ጋር የተያያዙ ምንም አይነት ክሶችን ማቋረጥ ፣ ሕዝብን በፍርሃትና በስጋት ለማቆየት ሆነ ተብለው የወጡ አፋኝ ህጎችን በአስቸኳይ ማንሳት፣  ማንኛውም ድርድር ገለልተኛ የሆኑ ሶስተኛ ወገኖች ባሉበት፤ የድርድሩ ሂደት በምስልና በድምጽ ተቀርጾ በገለልተኛ ወገኖች እጅ ብቻ የሚቀመጥ፣ የድርድሩ ቦታም የተደራዳሪ ወገኖች በጋራ በሚስማሙበት ቦታ መሆኑን መቀበልና ይህንንም በግልጽ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ማሳወቅ የሚሉት ተጠቅሰዋል።
” ወያኔ እነዚህን እርምጃዎች ለመውሰድ ቁርጠኝነት ሳይኖረው ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መመስረት የሚደረግ ድርድር ላይ ከምር ይሳተፋል ብለን ማመን በፍጹም አንችልም የሚለው ግንቦት7 ፣ እስከዚያው ድረስ ግን ግንቦት 7ም ሆነ ሌሎች ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መመስረት በቁርጠኝነት የሚታገሉ ኃይሎች፣ ወያኔ እነኝህን የመተማመኛ እርምጃዎች እስኪወስድና ቀደም ብለው በተቀመጡት መርሆች መሠረት በሚደረግ ድርድር በተግባር ሊመነዘር የሚችል ስምምነት፣ አልፎም ለምንም አይነት ማጭበርበርና መንሸራተት እድል የማይሰጥ ጠንካራ መጠበቂያዎች መኖራቸው እስኪረጋገጥ ድረስ፣ የጀመሩትን ትግል አጠንክረው እንዲገፉበት ጠይቋል።
ግንቦት7  የድርድሩ ውጤት የኢትዮጵያን ሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት ያረጋገጠ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን በአስቸኳይ እውን ማድረግ መሆኑን ገልጾ፣   በሥልጣን ላይ ባለው ኃይል በኩል ወደዚህ ግብ ለመድረስ ቁርጠኝነቱ በሌለበት ሁኔታ በሚደረግ ማንኛውም አይነት ድርድር ውስጥ ግንቦት 7 አይሳተፍም ሲል አቋሙን አንጸባርቋል።
ድርጅቶችን በተናጠል እየለያዩ “እንደራደር” ማለት በራሱ ጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅም ስሌትን የያዘ እሳቤ እንጂ፣ በዘላቂነት አገሪቱን እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ አገር ለማድረግ መፈለግን አያመለክትም በማለት የሚገልጸው ንቅናቄው፣ ለአንድ ድርጅት ለብቻው የሚመጣ ወይም የሚጠቅም ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ባለመኖሩ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የመፍጠር ፍላጎት ያለው ድርድር በአገሪቱ ያሉትን የተለያዩ የፖለቲካም ሆነ የሲቪክ ኃይሎችን ያካተተና ያመኑበት መሆን ይኖርበታል ብሎአል።
“የሚደረገው ድርድር ማን በስልጣን ላይ ይውጣ ወይንም የፖለቲካ ስልጣንን ባሉት ኃይሎች መሀከል እንዴት እናከፋፍለው የሚል የስልጣን ቅርምት ድርድር ሳይሆን፤ ሕጋዊና የሕዝቡን የሥልጣን ሉዓላዊነት ባረጋገጠ ሁኔታ የፖለቲካ ስልጣን እንዴት እንደሚያዝ ፍትሀዊ የሆነ ሂደትን ለማስጀመር የሚደረግ ድርድር መሆን አለበት” ሲል በድርድር ዙሪያ ያለውን መርህ አስቀምጧል።