ኢትዮጵያ ለዘመናት በነጻነቷ የተከበረች ፣ኣኩሪ ባህሏ እና ጥንታዊ ቅርሷ በአለም የታወቀች፣ ለጥቁር ህዝቦች የነጻነት ፋና ያፈነጥቀች፣በእምነት የመቻቻል ባህሏ ኣለምን ያስደነቀች ኩሩ አገር ናት።
ሃገረ እንደሃገር ሊቆም የሚችለው ሃገሩን የሚወድ ህዝብ እና መንግስት ሲኖር ብቻ ነው ።የሃገራችን ህዝብ ከዘመነ መሳፍንት እስከ ዘመነ ወያኔ የተለያዩ የሃገር ገዢዎች ሲያስተዳድሩ ኖረዋል።በነዚህም ገዢዎች የተለያየ ዘመናት የተለያየ የፖለቲካ አመለካከቶች ተነጸባርቀዋል ። ገዢዎቹ የተለያየ የፖለቲካ ኣመለካከቶችን ሲያራምዱ ቢቆዩም ፣ህዝቡ ግን አበሻዊ ጨዋነቱን በመበጠቅ ፣ስለመሪዎቹ ሳይሆን ስለአገሩ በማሰብ ኣንድነቱን ሲያጠናክር እና ሲጠብቅ ቆይቷል።
ከሃገር ፍቅር ይልቅ የጎሳና የጎጠኝነት ፍቅር ያስቀደመውና ቅንጣትም ያክል ያገር ፍቅር የለለው የወያኔ መንግስት ነው ።ዛረ ህዝባችን ተገልጾ በማያልቅ መከራና ስቃይ ውስጥ ይገኛ ።የመጻፍ የመናገር የመቃወም መብቶቹ ተነፍገዋል ።
ጎጠኝነት በግድ በስራ ቦታ ፣በማህበራት ፣በቤተክርስቲያንና በእስልምና እምነት ጭምር እንዲስፋፋ ተደርጓል ።ህዝቦች በነጻነት የሚፈልጉትን የሃይማኖት መሪ እንኳን መምረጥ እንዳይችሉ ተደርገዋል ።ገበሬውች ለዘመናት ይዘውት የነበረው መሬታቸው ፣ለዘመናት ኢትዮጵያን ለመቀራመት ያልሙና ይቋምጡ በነበሩ የሳውዲ አረቢያና በህንድ፣እንዲሁም በሌሎች ቀማኞች ተነጥቀዋል ።በገዛ አገሩ በገዛ ዕርስቱ ተቀጥሮ እንኳን መስራት አቅቶት ለስደት ተዳርጓል ።
ትላንት የዳቦ ቅርጫት ተብላ ትጠራ የነበረች አገራችን ፣ዛሬ የረሃብ ምሳሌ ሆናለች ።
ትላንት በሃይማኖት ተቻችሎ በመኖርን ለአለም ምሳሌ በመሆን ፣ለነብዩ መሐመድ ተከታዮች ጥገኝነት በመስጠት በአለም ተቀዳሚ የሆነች አገር፣ ዛሬ ብትቸገር ውለታዋን ክደው ፊት ነሷት።ዛሬ ህዝቦቿ ባደባባይ ተዋረዱ ።ዛሬ የውለታዋ ምላሽ የዜጎጎቿ መደፈር ሆነ ።ዛሬ ዜጎቿ ባደባባይ ተገለው ፣ሰው መሆኗቸው እንኳን ተክዶ |*ውሻውን ገደልነው *| ተባሉ።
ብሄራዊ ክብራችን ተነካ ፣ተዋረደ።ይህ ሁሉ ሲሆን የወያነ መንግስት አይቶ እንዳላየ ፣ሰምቶ እንዳልሰማ ሆነ ።ይባስም ብሎ ይህንን እኩይ ተግባር ለመቃወም የወጡ ዜጎቹን ደበደቡ ፣ከደፋሪዎች ጎን በመቆም ህዝቡን አሰሩት። ብሄራዊ ውርደት ላከናነበን የሳውዲ አረቢያ መንግስት ወግነው ህዝባችንን ኣሰሩት ።ዛፍ ያጣ ጉረዛ ኣደን ያበረረው የተባለው ብህል ተተግብሮበታል።
አገር ተራራና ዛፍ ፣ወንዝ እና ኣፈር ብቻ አደለም ።ሃገር ህዝብ ነው።ህዝብ ነው መንግስት። ህዝብ ነው ባለስልጣን ። ህዝብን ጨፍልቆ መግዛት አይቻልም ።ወያኔ ብሄራዊ ክብራችንን ሸጧል።ብሄራዊ ክብራችንን በማይረባ የኢንቨስትመንት ጥቅም ለውጦታል ።ከብሄላዊ ክብራችን ይልቅ ለአሳፋሪው የሳውዲ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ይጨነቃል ።
ዛሬ በሳውዲ አረቢያ ደማቸው ለፈሰሰው ወንድሞቻችን ፣ለተደፈሩት እህቶቻችን ስንልና ከምንም በላይ ለተደፈረው ብሄራዊ ብራችን ስንል በዘር፣በጎሳ፣በሃይማኖት መከፋፈላችንን ትተን በአንድነት የሃገራችን ነቀርሳ የሆነውን ወያኔ፤ሃገር እያለን አንደሌለን ያረገን ጎጠኛ ወያኔን ፤ ክብር እያለን ክብራችንን የሸጠውን ማፈሪያ ወያኔ ከስሩ መንቅለን ለመጣል ፤አንድ እንሁን።አንድነት ሃይል ነው።
አንድነት ክብር ነው።አንድነት ጌጥ ነው። አንድነት የማንነት መገለጫ ነው ።አንድ እንሁን ።አንድ የሆነ ህዝብ ምንጊዜም ያሸንፋል ።ድር ቢያብር አምበሳ ያስር ነውና።
ምንጭ ከ አቶ እምሻዉ!! ኢትዮጲያ ለዘላለም በክብር ትኑር!!!
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar