tirsdag 31. desember 2013

ኢትዩጵያ ህጻናትን ወደ ውጭ በጉዲፈቻ ስም በመላክ ከአፍሪካ ቀዳሚ መሆኑዋና መረጃዎች አመለከቱ

በቅርቡ የወጡ መረጃዎች እንዳሳዩት በአፍሪካ ባለፉት 6 ዓመታት በጉዲፈቻ ስም ወደ ውጭ ከተላኩት 34 ሺ 342 ህጻናት ውስጥ 63 በመቶ ወይም 21 ሺ 365 ሰዎችን በመላክ ቀዳሚ ናት።
በሃገሪቱ በሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ፈቃድ የተሰጣቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ጉዳይ አስፈፃሚ የጉዲፊቻ ደላሎች ተበራክተዋል፡፡ በአብዛኛው ለጉዲፈቻ በሚቀርቡ ህፃናት የህይዎት ታሪክ ላይ የሚጻፈው ” ተጥለው የተገኙ ወይም ወላጆቻቸውን  በህይዎት ያጡ ” የሚል በመሆኑ በልጆቹ ህይወት ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ አለው።
የሴቶች እና ህፃናት ሚኒስቴር የሆኑት ወ/ሮ ዘነቡ መንግስት ህጻናቱን ወደ ውጭ ለማላክ ለፍርድ ቤት የሚያስከፍለው 25 ብር ብቻ መሆኑን ይናገሩ እንጅ፣ የጉዲፈቻ አሳዳጊዎች፣ አንድ ህጻን ለማግኘት እስከ 20 ሺ ዶላር እንደሚከፍሉ ይናገራሉ፡፡
የደቡብ ክልል የሴቶች እና ህፃናት ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ  በህፃናት የሚነግዱ አካላት በርካታ መሆናቸውን ይገልጻሉ፡፡ ኢትዩጵያ ያወጣችው አማራጭ የህፃናት መመሪያ በራሱ ሙሉ አለመሆኑንና ለችግሩ መባባስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉንም ይገልፃሉ፡፡ በርካታ የፖሊስ እና የመንግስት አካላት ” ህጻናት ወደ ውጪ ቢሄዱ ይለወጣሉ” የሚል አመለካከት መያዛቸው ስህተት ነው የሚሉት ሃላፊዋ፣ በደቡብ ክልል እንደወጡ የቀሩ ልጆችን የሚጠብቁ እናቶች ዛሬም መንግስትን እያማረሩ ነው ፡፡
ኢቲቪ በቅርቡ ባቀረበው ዘገባ 832 ህጻናት በየአመቱ ከኢትዮጵያ ይወጣሉ ብሎአል። ይሁን እንጅ ከፌደራል መደበኛ ፍርድ ቤት የተገኘ መረጃ እንደሚያሳየው በ2005 ብቻ 2 ሺ 201 ህጻናት ከአገር እንዲወጡ ፈቃድ ተሰጥቷል።
ከአፍሪካ ሀገራ ላይቤራ እና ዛምቢያ ጉዲፊቻን በማገድ ለህጻናቱ በቂ እንክብካቤ እንደሚሰጡ አስታውቀዋል። በኢትዮጵያ ጉዲፈቻ ለመጀመርያ ጊዜ የሕግ ከለላ የተሰጠው በ1952 ዓ.ም. በወጣው የፍትሐ ብሔር ሕግ ነው፡፡

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar