የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለኤ ኤፍ ፒ እንደገለጹት ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር እና የተቃዋሚው መሪ ሪክ ማቻር ለውይይት በአዲስ አበባ ይገኛሉ።
ማቻር የሰላም ድርድሩን የተቀበሉት የዩጋንዳው መሪ ዩዎሪ ሙሰቬኒ አገራቸውና የኢጋድ አባላት በደቡብ ሱዳን ግጭት ውስጥ እጃቸውን በማስገባት አማጽያኑን እንደሚወጉ ማስጠንቀቃቸውን ተከትሎ ነው የሚለውን ዘገባ መሪው አስተባብለዋል። ለፕሬዚዳንት ሙሰቬኒ ምላሽ በሚመስልና የድርድር ቦታቸውን በሚያጠናክር መልኩ፣ አማጽያኑ ቦር የምትባለውን ከተማ ዛሬ መልሰው መያዛቸውን አስታውቀዋል።
ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ስልጣናቸውን ለተቃዋሚው መሪ አካፍሉ የሚለውን ሀሳብ እንደማይቀበሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትራቸው ግልጽ አድርገዋል።
ሁለቱ ሀይሎች በአዲስ አበባ የሰላም ስምምነት የማይፈራረሙ ከሆነ አካባቢውን ወደሚያተራምስ የዘር ፍጅት ሊገቡ ይችላል ተብሎ ተሰግቷል።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar