tirsdag 30. april 2013
በተለያዩ የአለም ክፍሎች መንግስት ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው
ለባይ ግድብ መዋጪ ለማሰባሰብ በኖርዌይ ኦስሎ የተጠራው ስብሰባ ለሁለተኛ ጊዜ በአገሪቷ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንዲቋረጥ ተደርጓል።
በተመሳሳይ ሁኔታም በካልፎሪኒያ ሳንዲያጎ ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ተብሎ የተጠራው ስብሰባ በአካባቢው በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ተቃውሞ ሰብሰባው እንዲቋረጥ ተደርጓል።
በሌላ በኩል ደግሞ በኔዘርላንድስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአማራ ተወላጆች ላይ የሚፈጸመውን የማፈናቀል ዘመቻ አውግዘዋል።
የኢትዮጵያውያን ማህበር በሆላንድ ትናንት በአምስተርዳም ከተማ በጠራው ስብሰባ የህወሀት ኢህአዴግ አገዛዝ በቤንሻንጉል
ጉሙዝና እና በሌሎችም የአገሪቱ ክፍሎች በአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰውን ግፍ ፣ በእስር ቤት ውስጥ በሚገኙ የህሊና እስረኞች ላይ የሚደርሰውን እንግልት እንዲሁም በሙስሊሙና በክርስቲያኑ ላይ የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ለአውሮፓ መንግስታት ለማሳወቅ ሜይ 15፣ 2013 በአውሮፓ ህብረት መቀመጫ በሆነችው ብራሰልስ የተቃውሞ ሰልፍ ማዘጋጀቱን አስታውቋል።
በሌላ ዜና ደግሞ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት የጠራው ስብሰባ በጀርመን ተካሂዷል።
mandag 29. april 2013
የህወሀት ጄኔራሎች በአለም ላይ ውድ የሆነውን የታንታለም ማእድንን በህገወጥ መንገድ እየዘረፉ ለውጭ ገበያ እያቀረቡ ነው
ኬንቲቻ ቦረና የኢትዮጵያ ማእድን ልማት አክሲዮን ማህበር የተባለ መንግስታዊ ድርጅት ከአመታት በፊት በጉጂ ዞን በሻኪሶና አናሶራ ወረዳዎች 2ሺ 500 ቶን የሚጠጋ ንጹህ የታንታለም ማእድን ማግኘቱ የመገናኛ ብዙህንን ትኩረት ስቦ ነበር።
ኩባንያው ምንም አይነት የማጣሪያ ስራ ሳይሰራ ይህን ውድና ስትራቴጂክ ማእድን በርካሽ ዋጋ መሸጡ አገሪቱን እንደሚጎዳ የዘርፉ ባለሙያዎች ለሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ደጋግመው አቤቱታቸውን በማቅረብ ፣ ጥሬ እቃውን ወደ ውጭ መላኩ እንዲቋረጥ ተደርጓል።
መንግስት በወቅቱ እገዳውን ሲጥል የሰጠው ምክንያት ማእድኑን በዘመናዊ ዘዴ በማምረት የተሻለ ዋጋ ለማግኘት እንዲሁም ከማእድኑ ጋር አብሮ የሚገኘው ዩራኒየም የሚያወጣው ሬዲዮ አክቲቭ ጨረር ለጤና ጠንቅ በመሆኑ የተሻለ አያያዝ ለመፍጠር የሚል ነበር።
እገዳው መንግስት የታንታለም ማጣሪያ ማሽን እስከሚገነባበት ጊዜ ድረስ እንደሚቀጥል በወቅቱ መጠቀሱ ይታወቃል።
ኢትዮጵያ በየአመቱ የምታመርተው ምርት የአለምን ገበያ 20 በመቶ የሚሸፍን ሲሆን፣ እገዳውም በአለም የታንታለም ዋጋ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ አሳርፎ ቆይቷል።
ዶድ ፍራንክ የተባለው ህግ ኩባንያዎች ግጭት ባለባቸው አገሮች ማእድኖችን ሲገዙ ማእድኖቹ ከግጭቶች ጋር የተያያዙ አለመሆናቸውን ማረጋገጥ አለባቸው ስለሚልና በአለም ላይ አብዛኛውን የታንታለም ማእድን የምታመርተው በጦርነት የምትታመሰዋ ዲሞክራቲክ ኮንጎ በመሆኗ ኢትዮጵያ በማእድን መላኩ ላይ የጣለችው እገዳ በአለም የታንታለም ገበያ ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሯል።
ታንታለም ሊተካ የማይችል እጅግ ውድ የሆነ ማእድን ሲሆን፣ የሞባይል ስልኮችን፣ ኮምፒዩተሮችን እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ፣ ለተለያዩ የኬሚካልና የፋርማሲዩቲካል ውጤቶች መስሪያ፣ ለኤሮስፔስ፣ ለኢነርጂና ባልስቲክ ምርቶች በግባትነት ያገለግላል።
የኢትዮጵያ መንግስት ይህን በአንድ በኩል ውድ ፣ አላቂና ስትራቲጀክ በሌላ በኩል ደግሞ ለጤና አደገኛ የሆነውን ማእድን ወደ ውጭ የመላኩ ስራ ለጊዜው እንዲገታ ቢያደርግም፣ ይህን እገዳ ተጠቅመው የህወሀት ጄኔራሎች ከአንዳንድ ማእድኑን በማውጣት እውቀቱ ካላቸው ቻይናዎች ጋር በመመሳጠር ማእድኑን በመከላከያ መኪናዎች እየጫኑ ፣ አሽዋ ነው በማስባል በሶማሊላንድ በኩል ወደ ውጭ ሲያሻግሩ መቆየታቸውና በብዙ መቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ሀብት መዝረፋቸውን በኩባንያው ውስጥ የሚሰሩ ምንጮቻችን ገልጸዋል።
የመከላከያ ሰራዊት ኩባንያ በአካባቢው የመንገድ ስራ ተቋራጭ በመሆን መንገድ እየሰራ ሲሆን፣ ለመንገድ ስራ ተብለው የተመደቡት መኪኖች ከመንገድ ስራ ይልቅ የታንታለም ማእድንን እየዘረፉ በሶማሊላንድ በኩል ሲያሻግሩ መቆየታቸውን ሰራተኞች ተናግረዋል።
በቅርቡ ደግሞ መንግስት ከፍተኛ የገንዘብ ጥረት ያጋጠመው መሆኑን ተከትሎ ፣ የማእድን ማውጣቱን እና መላኩን እንደገና ለመጀመር በመወሰኑ እነዚህ የህወሀት ጄኔራሎች ከአንድ የቻይና ኩባንያ ጋር አክሲዎን በመመስረት ታንታለም በጅቡቲ በኩል መላክ መጀመራቸውን ሰራተኞች አስረድተዋል።
ሰራተኞች ” ይህ ማእድን እያለቀ ነው፣ ታንታለም ስትራቴጅ ማእድን ነው፣ ማእድኑ አሁን ካለቀ አገሪቱ ለወደፊቱ ከፍተኛ የሆነ ገቢ ታጣለች በማለት ሰራተኞች” ገልዋጸዋል።
የሀወሀት ጄኔራሎች ዝርፊያውን የሚፈጽሙት ከዞን ባለስልጣናት ጋር በመዛመድ መሆኑን መንጮች ገልጸዋል።
ምንም እንኳ ኢሳት በአካባቢው ያሉ ተወካዮችን ለማረጋገጥ ባይችልም፣ በህገወጥ መንገድ ከሚወጣው ማእድን ጨረር ጋር በተያያዘ በርካታ የአካባቢው ሰዎች መሞታቸውን ሰራተኞች ገልጸዋል።
መንግስት እገዳው ከመጣሉ በፊት 80 በመቶ የሚሆነውን የኢትዮጵያን ታንታለም የሚሸጠው ቻይና ውስጥ ነበር።
በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስት ባለስልጣናትን ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም።
የህወሀት ጄኔራሎች በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚገኙ ዘመናዊ ህንጻዎች እና የንግድ ድርጅቶችን ሰርተው እንደሚገኙ ኢሳት በማስራጃ አስደግፎ ማቅረቡ ይታወሳል።
fredag 26. april 2013
በአፋር የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ልዩ ወረዳ መጠየቃቸውን የአፋር ሰብአዊ መብቶች ድርጅት ተቃወመ
የዞን ሁለት ዋና ከተማ በሆነው አብአላ የሚኖሩ 15 ሺ የሚጠጉ የትግራይ ተወላጆች ራሳችንን በራሳችን ለማስተዳደር ልዩ ወረዳ ይሰጠን በማለት ያቀረቡት ጥያቄ ተገቢ አይደለም ሲሉ የአፋር ሰብአዊ መብቶች ሃለፊ አቶ ገአስ አህመድ ገልጸዋል።
አቶ ጋአስ በዱብቲ ከተማ በርካታ የአማራ፣ የኦሮሞ እና የትግራይ ተወላጆች ቢኖርም አንድም ቀን የወረዳ ጥያቄ አለማንሳታቸውን ገልጸው፣ ከመቀሌ በ45 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው አብአላም ከተማ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ያቀረቡት ጥያቄ አሳዛኝ መሆኑን ገልጸዋል።
የአፋር ክልል በህወሀት ሰዎች የሚመራ መሆኑን የገለጹት አቶ ገአስ፣ ተወላጆቹ ወረዳ ይሰጠን ከሚሉ ክልሉ የራሳቸው መሆኑን ቢያውቁት ይሻል ነበር ብለዋል።
አቶ ገአስ እንደሚሉት በአብላ የሚኖሩት የትግራይ ተወላጆች ከተማዋ ሸከት ተብላ እንድትጠራ እንዲሁም የአፋር ክልላዊ መንግስት በከተማዋ መሬት ለኢንቨስትመንት መስጠት አይችልም የሚሉት ጥያቄዎች የመብት ጥያቄዎች ሳይሆኑ የመሬት ይገባኛል ጥያቄዎች መሆናቸውን ገልጸዋል።
በአሁኑ ጊዜ በአፋር ክልል የህወሀት ባለስልጣናት ግምገማ እያስደረጉና የራሳቸውን ሰዎች እየሾሙ ክልሉን ለውድመት መዳረጋቸውን አቶ ገአስ አመልክተዋል
በጉዳዩ ዙሪያ የአብአላ የትግራይ ተወላጆችን ተወካይ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።
onsdag 24. april 2013
በወልድያ ከተማ በርካታ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ታሰሩ
በመላው አገሪቱ ከሚካሄደው የሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በወልድያ ከተማ 10 ሙስሊም የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከአለፈው አርብ ጀምሮ መታሰራቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
በዛሬው እለትም እንዲሁ አንድ የሁለተኛ ደረጃ እንግሊዝኛ መምህር የሆኑት አቶ አብደላ እና የመደርሳ ትምህርት ቤት የእቃ ግምጃ ቤት ሀላፊ የሆኑ ግለሰቦች ተይዘው ታስረዋል።
መንግስት የሙስሊሙን እንቅስቃሴ ለማፈን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተቃውሞው አስተባባሪዎች ናቸው የሚላቸውን ሰዎች እየያዘ በማሰር ላይ ይገኛል። የተያዙት ተማሪዎች በአሁኑ ጊዜ በወልድያ እስር ቤት ውስጥ ይገኛሉ።
mandag 22. april 2013
የትም ይኑር የትም ነው እኮ ህጋዊ
የትም ይኑር የትም ነው እኮ ህጋዊ
አንዱ ሁሉም ቦታ ሁሉም በ አንድ ቦታ
ተወስኖ እንዲኖር አልፈቀደም በ አንድ ጌታ።
ይገደብ ሚለው ቃል ለ አባይ መስሎኝ ነበር
እንደምን ተርጉመው አረጉት ለብሔር።
በ አ የሚጀምር ሁሉ ይገደብ ሲል
አባይን ጀምሮ አማራ ሲከተል
እኔስ ልቤ ፈራ በ አፋር እንዳይቀጥል
ትናንት ከደቡቡ ዛሬ ከ ቤንሻንጉል
እያነጣጠሩ አንድን ብሔር ማግለል
መፍትሔውን ሳይሆን ውድቀቱን ያመጣል።
ይሄ መፈናቅል በእስር ቤት ከሰራ
አሣምነው ጽጌ እንዲሁም ተፈራ
ዝዋይ ሆነላቸው ክልሉ የ አማራ።
ተብሎ ተጠርቶ እንኳን ኢትዮጵያዊ
ሌላም ስም ቢሰጠው ገላጭ ለምድራዊ
በፈቃድ ከገባ ሆኖ ሰላማዊ
የትም ይኑር የትም ነው እኮ ህጋዊ
የትም ይኑር የትም ነው እኮ ህጋዊ።
አንዱ ሁሉም ቦታ ሁሉም በ አንድ ቦታ
ተወስኖ እንዲኖር አልፈቀደም በ አንድ ጌታ።
ይገደብ ሚለው ቃል ለ አባይ መስሎኝ ነበር
እንደምን ተርጉመው አረጉት ለብሔር።
በ አ የሚጀምር ሁሉ ይገደብ ሲል
አባይን ጀምሮ አማራ ሲከተል
እኔስ ልቤ ፈራ በ አፋር እንዳይቀጥል
ትናንት ከደቡቡ ዛሬ ከ ቤንሻንጉል
እያነጣጠሩ አንድን ብሔር ማግለል
መፍትሔውን ሳይሆን ውድቀቱን ያመጣል።
ይሄ መፈናቅል በእስር ቤት ከሰራ
አሣምነው ጽጌ እንዲሁም ተፈራ
ዝዋይ ሆነላቸው ክልሉ የ አማራ።
ተብሎ ተጠርቶ እንኳን ኢትዮጵያዊ
ሌላም ስም ቢሰጠው ገላጭ ለምድራዊ
በፈቃድ ከገባ ሆኖ ሰላማዊ
የትም ይኑር የትም ነው እኮ ህጋዊ
የትም ይኑር የትም ነው እኮ ህጋዊ።
søndag 21. april 2013
በኖርዌይ አገር በሚገኙ ኢትዮጵያዊን ስደተኞች ተዋርዳ የተባረረችው የወያኔ ዲፕሎማት ጀሌ በስዊዲን ወይዘሮ መብራት በየነ::
የወያኔ/ ህውሃትና ጀሌዎች በአለም ላይ የሚያደርጉት የአባይ ገቢ ማሰባሰብያ በየአለማቱ ተቋውሞ እየደረሰበት ይገኛል።
በደቡብ አፍሪካ የተጀመረው ገቢ ማሰባሰብያ ሳይሳካ እንደውም ወያኔ የተከራየውን አዳራሽ ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር በማስወጣት ያሳዩትን ጀግንነት ቀጥሎ በሌሎች አገርም በአሜሪካ፣ በሳውዲ አረቢያ( ጅዳ) ፣በጀርመን ተቀጣጥሎ በቀጠለበት ሁናቴ በኖርዌይ
ከፍተኛ የሆነ ተቋውሞ ደርሶበታል ።በኖርዌይ የተጀመረው ገቢ ማሰባሰብያ ስብሰባ በመቃወም ወያኔ የተከራየውን ገቢ ማሰባሰብያ አዳራሽ ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር በማስወጣት የወያኔን ባንዲራ በማውረድ የኢትዮጵያን ትክክለኛውን ባንዲራ በመስቀል በማውለብለብ ወያኔዎችንና ጀሌዎችን በማባረር አዳራሹን ተቃዋሚዎቹ ተቆጣጥረውታል ።
በአለማቱ ያሉቱ የወያኔ ቅጥረኛ አምባሳደር ተብዬዎች አንገታቸውን ያስደፋና እንደ ቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስተራቸው አንገትን አስደፍቶ፣አስደንግጦ ወደ መጡበት ያስመለሰ ነበር።አዳራሹ ውስጥ የነበሩት ተቃዋሚዎች ሙሉ በሙሉ ይበልጣሉ።ታሪክ በውጪ ባሉ ኢትዮጵያዊያን እየተሰራ ይገኛል!
lørdag 20. april 2013
The police came out with three cars and six policemen and stopped a meeting of Tasta bydelshus where the atmosphere was becoming so very irritably among the more than 300 Ethiopian origin attendees.
The 300 attendees were Ethiopian asylum seekers or people with Ethiopian background. The police feared that it would get completely out of control when people in the audience went to the hard verbal confrontation against two representatives
from the Ethiopian Embassy in Stockholm who had called for and chaired the meeting.
The police gave the first message that all protesters to leave the meeting while the two embassy people and their potential supporters can be seated. This denied the attendees protesters, and several feared it would come to an open confrontation between police and people in the audience. Then, specific efforts manager Øyvind Sveinsvoll of Rogaland police to stop the meeting and clear the room.
It was a wise decision, said several of those present protesters. They did not want the two embassy people should be left as “victors” while they were evicted.
- Our goal was to stop the meeting. We managed, says one of them to Eve magazine
fredag 19. april 2013
ወደ ቤንሻንጉል ጉሙዝ የተመለሱ የአማራ ተፈናቃዮች በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ ታወቀ
ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሀይል ተፈናቅለው በፍኖተሰላም እና ቻግኒ ከተሞች ሰፍረው የነበሩ ከ8 ሺ ያላነሱ የአማራ ተወላጆች ኢትዮጵያውያን ባሳደሩት ጫና ወደ መጡበት አካባቢ እንዲመለሱ ቢደረግም፣ በአካባቢው ያጋጠማቸው ያልጠበቁትና በህይወት የመቆየታቸውን ነገር አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን ያነጋገርናቸው ሰዎች ገልጸዋል።
መሬት ያላቸው ተወላጆች ተመላሽ ተፈናቃዮችን ስራ ለመቅጠር ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሰርተው ለማደር ተቸግረዋል። የዞን እና የወረዳ ባለስልጣናት የአካባቢው ሰዎች ተፈናቃዮችን ስራ እንዳይቀጥሩዋቸው ቅስቀሳ በማድረጋቸው ሰዎቹ ለመቀጠር አለመቻላቸውን ያነጋገርናቸው ተፈናቃዮች ይገልጻሉ።
የተፈናቃዮችን ችግር ያባባሰው ደግሞ መንግስት የሰጣቸው የምግብ ዱቄት የጤና ችግር ማስከተሉ ነው። ብዙዎቹ ተፈናቃዮች በተቅማጥ በሽታ እየተሰቃዩ መሆኑን ይናገራሉ።
በአካባቢው ያለው መለስተኛ የጤና ተቋም በአማካኝ ከአራት ሰአት የእግር ጉዞ በሁዋላ የሚገኝ ሲሆን፣ በእግር ተጉዞ ህክምና ለማግኘት እንኳ የገንዘብ ችግር አጋጥሟቸዋል። አርሶአደሮች እንደሚሉት ለበሽታ የዳረጋቸው ጊዜው ያለፈበት የተበላሸ ዱቄት ስለተሰጣቸው ነው።
የተለያዩ ተፈናቃይ አርሶአደሮችን አነጋግረን ለመረዳት እንደቻልነው ተፈናቃዮቹ ባለቡት ቦታ ስራ ለመጀመር ካልቻሉ ወደ መጡበት ቦታ ለመመለስ ፍላጎት አላቸው። አርሶደአሮቹ ንብረታቸው በሙሉ በዝርፊያ ያጡ በመሆኑ እንደ መጀመሪያው ጊዜ የትራንስፖርት ከፍለው ወደ መጡበት ቦታ መመለስ አይችሉም።
በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ህጻናት የትምህርት እድል አጥተው ጊዜያቸውን በከንቱ እያሳለፉ መሆኑንም ለማወቅ ተችሎአል።
በጉዳዩ ዙሪያ የፌደራል መንግስቱ ባለስልጣናትን አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ምክትል ሚኒስትር የሆኑት አቶ ብርሀነ ገብረክርስቶስ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉት የአማራ ተወላጆች ህገ ወጥ የመሬት ወራሪዎች በመሆናቸው መፈናቀላቸውንለጀርመን ድምጽ መግለጻቸው ይታወሳል።
የራዲዮ ጋዜጠኛዋ ” የክልሉ መንግስት እኮ ተሳስተን ነው ያፈናቀልናቸው በማለት መግለጫ ሰጥተዋል የሚል ጥያቄ ሲቀርብላቸው ” ተፈናቃዮቹ መመለሳቸውን አላውቅም” በማለት የሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ ውስጥ መንግስት አለ እንዴ? የሚል ጥያቄ በማስነሳት እያወያየ ይገኛል።
onsdag 17. april 2013
የርዕዮት ሽልማትና የእኛ ዝምታ (ከዳዊት ሰለሞን)
ይቺን ፅሁፍ ከፌስ ቡክ ሰፈር ነው ያገኘኋት፡፡ ባለቤቷን ሳላስፈቅድ ነው እዚህ ያመጣኋት፡፡ ካጠፋው ልጥፋ… (አልልም) ይቅርታ ግን እጠይቃለሁ!
ጋዜጠኛና መምህርት ርዕዮትአለሙ የቤተሰቦቿ የመጀመሪያ ልጅ እንደመሆኗ መጠን ሃላፊነት ነበረባት፡፡ይህንን ሃላፊነት ለመወጣትም ርዕዮት ከማስተማር ሞያዋ ጎንለጎን በትርፍ ጊዜዋ ህጻናትን ታስተምር ነበር፡፡ከዚህ የሚገኘው ገቢ ደግሞ የቤተሰቡን ኑሮ ይደጉማል፡፡
በሩጫ የተሞላው የጋዜጠኛዋህይወት በአንድ ማለዳ ቀለም ወደ ምትመግባቸው የምስካዬ ህዙናን ትምህርት ቤት ተማሪዎች ክፍል ለመግባት ስትዘጋጅ የእስር ማዘዣባወጡባት የፌደራል ፖሊሶች እጅ ወደቀች፡፡ርዕዮት ታስራለችና ቤተሰቡ ከእርሷ ያገኘው የነበረውን ድጉማ ማጣቱ ግድ ሆነ፡፡
አምላክ ሳይደግስ አይጣላምእንደሚሰኘው እስከዳር የርዕዮትን ፍኖት በመከተል የቤተሰብ ግዴታዋን ለመወጣት በሞያዋ ስራ ማፈላለጉን ተያያዘችው፡፡እናም ተሳካ፡፡በጥሩደሞዝ በአንድ የግል ድርጅት ውስጥ ተቀጠረች፡፡ይህ ከርዕዮት መታሰር በኋላ ለቤተሰቡ የተደመጠ የመጀመሪያው መልካም ዜና መሆኑ ነው፡፡ቹቹ(የእስከዳር የቤት ስም ነው)ባገኘችው አዲስ ስራ ብዙም መቀጠል አልቻለችም፡፡ቀጣሪዋ ወደ ቢሮው ጠርቷት‹‹የሆኑ ሰዎች ትናንት አንቺከቢሮ ከወጣሽ በኋላ መጥተው ነበር፡፡
ይህቺን ልጅ ካላስወጣችኋት ድርጅታችሁ ከመንግስት አንዳች ነገር ቢፈልግ ትብብር አይደረግለትምብለውኝ ወጡ፡፡ስለዚህ እባክሽ ምን እናድርግ?››እስከዳር አላመነታችም‹‹ምንም ችግር የለም በእኔ ምክንያት እናንተ መጉላላት የለባችሁምስለዚህ ስራውን መልቀቅ እችላለሁ››ቢሮውን ለቅቃለት ወጣች፡፡ከትንሽ መውጣትና መውረድ በኋላ ቹቹ ሌላ ስራ አገኘች፡፡የዚህን ስራየአንድ ወር ደሞዝ እንኳን መብላት ሳትችል አሰሪዋ ‹‹ውጪልኝ ሰዎች መጥተው ከእሷና ከድርጅትህ አንዱን ምረጥ ብለውኛል ››አላት፡፡እየሳቀችስራውን ለቀቀችለት፡፡
በቅርቡ ግን ያጋጠማትለየት ያለ ነው፡፡ጥሩ ስራ በመገኘቱ ያለሽን የትምህርትና የስራ ልምድ አስገቢ ተብላ በጓደኞቿ በመወትወቷ ነገ ሊያሥወጡኝ በሚልስሜት ወደ ተባለው ቦታ አመራች፡፡ለስራው ብቁ የሚያደርጋትን ማስረጃ አስገብታ ከገባችበት ቢሮ ስትወጣ አንድ ጉስቁስቁል ያለ ወጣትከአፉ የሚያወጣቸውን ቃላት ጠንከርና ረገጥ እያደረገ‹‹አትልፊ እኔ እያለሁ አንቺ ስራ አትቀጠሪም››ብሏት ሊቀጥራት ወዳናገራት ድርጅትመሰስ ብሎ ገባ ይሄው ድርጅቱም እስካሁን ድረስ አልደወለላትም፡፡
ቹቹ አሁን በዚህች አገር ሰርታ መኖር እንዳትችል የሆነ የፈረደባትአካል እንዳለ ማመን በመጀመሯ ከአሁን በኋላ ስራ ፍለጋ እግሬን ንቅንቅ አላደርገውም የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሳለች፡፡ብዙዎቻችን እንደምናውቅየርዕዮት አባት አቶ አለሙ የህግ ባለሞያ ናቸው፡፡ልጃቸው ቃሊቲ ከመውረዷ በፊት የተለያዩ የፍርድ ቤት ጉዳዩችን በመያዝ ገቢ አግኝተዋል፡፡አሁንግን ጥብቅና እንዲቆሙላቸው የሚጠይቁ ደምበኞች ወደ እርሳቸው ቢሮ እንዳይመጡ አንድ ስውር እጅ ሆነ ብሎ እየቀሰቀሰባቸው ይገኛል፡፡
‹‹እርሳቸውየሚይዙት ጉዳይ ፍርድ አያገኝም››ወደ አቶ አለሙ ቢሮ ለማምራት ለሚፈልጉ ሰዎች የሚነገር ማሸማቀቂያ ነው፡፡እናም የስራ ነገር ለአቶአለሙ አሁን እጅግ ከባድ ሆኗል፡፡የርዕዮት የሞያና የፍቅርአጋር የሆነው ጋዜጠኛ ስለሺ ሀጎስ ከእጮኛው መታሰር በፊት ህይወትን ለማሸነፍ በሁሉም አቅጣጫ የሚታትር ብርቱ ነበር፡
፡ ቃሊቲ ፍቅሩንከነጠቀችው በኋላ ግን የህይወት ትግሉ ላይ በረዶ እንደተደፋበት ስሜቱ ቀዝቅዟል፡፡የጸሀይ ብርሃንን የፈራ ያህል ለቃሊቲ ጉዞ ካልሆነበቀር ከቤቱ መውጣትን አይፈቅድም፡፡የርዕዮት መታሰር ስንቱን እንዳሰረ አያችሁን?እርግጥ ነው እኛ ኢትዮጵያዊያንጀግኖች እንዲወለዱ እንጸልያለን እንጂ የተወለዱት ጀግኖች መከራ በደረሰባቸው ጊዜ አብረናቸው አንቆምም፡፡ርዕዮት፣እስክንድር፣ ውብሸት፣አንዷለም፣ናትናኤልናሌሎቹም ከራሳቸው ርቀው ስለ ህዝብ በመጮሃቸው የቃሊቲ ደጃፍ ተቆልፉባቸዋል፡፡የእነዚህ ሰላማዊ ታጋዮች መታሰር በቤተሰቦቻቸው፣በሚረዷቸውሰዎችና በልጆቻቸው ላይ ከሚያደርሰው የህሊና እና የስነ ልቦና ቀውስ በተጨማሪ የኢኮኖሚ ምስቅልቅሉ በቃላት ሊገለጽ የማይችል ነው፡፡የታጋዮቹአሳሪዎችም ከምንም በላይ የህዝቡን አለመደጋገፍ የሚገነዘቡ በመሆናቸው የሚያቀርቡት የመጀመሪያ ጥያቄ‹‹ለምን ለልጆችህ ለመኖር አትፈልግም››የሚል ነው፡፡የውብሸት ልጅ ውብሸትበመታሰሩ ምክንያት ለትምህርት ቤት የሚከፍልለት አጥቶ ወደ ዝቅተኛ ትምህርት ቤት እንዲሸጋገር መደረጉ ስድቡ ውብሸትን አደንቀዋለሁለምንለው እኛ እንጂ ለእርሱ አይደለም፡፡
ይህንን እያዮና እየሰሙ እንዴት ሌሎች ውብሸቶች ይፈጠሩ?ውብሸት የታሰረ ሰሞን እኔና ጋዜጠኛነብዮ ሀይሉ ከውብሸት ጋር አብሮ ይሰራ የነበረን አንድ የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ባልደረባ ቀጥረን አገኘነውና‹‹ውብሸት በመታሰሩቤተሰቡ ችግር ላይ ሊወድቅ ይችላል፡፡ስለዚህ ለምን የሆነች መዋጮ በማድረግ የምንችለውን አናደርግም ››አልነው፡፡ምላሹ ያልጠበቅነውነበር‹‹መንገስት እርሱን መንግስት ያሰረው በሽብርተኝነት ጠርጥሮት በመሆኑ አሁን እገዛ ብናደርግ እኛንም ተባባሪ ሊያደርገን ይችላል››አለን፡፡ውብሸትይቅርታ ጠይቆ ሊወጣ ነው በተባለ ሰሞን ይህ ጋዜጠኛ የፌስ ቡክ ገጹን በውብሸት ፎቶግራፍ ሞልቶ ማየቴም እፍረት አሳድሮብኝ ነበር፡፡ለማንኛውም ዛሬ ማለዳያደመጥኩት ዜና ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ፈጥሮብኛል፡፡
ፈረንጆች ለእኛ የመብት ተሟጋቾች እውቅና በመስጠት ሽልማት እያበረከቱ ነው፡፡በዚህመነሻነትም ርዕዩት ሃሳብን በነጻነት ለመግለጽ በከፈለችው መስዋዕትነት የተነሳ የ25.000 ዶላር አሸናፊ ሆናለች፡፡ ከገንዘቡ ባሻገር በርዕዮት ዙሪያ ላሉ ሰዎች በሙሉ ይህትልቅ ማበረታቻ ነው፡፡እናም የርዕዮት እህት፣ አባትና እጮኛ በመሆናቸው ብቻ ዋጋ እየከፈሉ ያሉትን በሙሉ በዚህ አጋጣሚ እንኳንደስ አላችሁ ማለት ወደድኩ፡፡ከወሬ የዘለለ ማድረግ ላልቻልን ከቃሊቲ በመለስ ላለን ለእኛ ግን አፈርኩ፡፡
tirsdag 16. april 2013
In the local and City Administration Elections held in Ethiopia in the presence of a few opposition parties yesterday, the ruling Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front ( EPRDF) has garnered unexpected outcomes.
...
“Although EPRDF was eyeing a 99 to 100 percent election win, the messages that voters put on the voting Cards was what it did not expect.” An observer said.
In some areas, Kebele and Woreda officials were seen appeasing election observers and vote counters to be silent of what they saw.
According to witnesses, in Woldeya, Northern Wello Zone, over half of the papers and cards found ballot boxes were blank while the rest contained messages that urged the ruling party to leave, called freedom of religion and arrested religious leaders to be freed.
In another election station in Northern Shewa, the majority of the voters did cast blank papers into the ballot boxes.
Election stations in Addis Abeba like Waliya School Election Station in Kirkos Sub city were “hit with voters’ dearth”.
In some regions where vote counting has already started, the ruling Front has won the election with 99 to 100 percent. Observers state that this election result would not only beat EPRDF’s own 99.6 percent election results of 2010 but would remain the only in the election history of Ethiopia.See More
søndag 14. april 2013
የፍትህ ጋዜጣ አሳታሚ እና የሰማያዊ ፓርቲ አመራር ከመንግስት ሸሽተው ተሰደዱ!
የፍትህ ጋዜጣ አሳታሚ የሆነችው ማስተዋል የህትመት ስራ ድርጅት ስራ አስኪያጅ የነበረው ማስተዋል ብርሃኑ እና የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር እና የፍትህ ጋዜጣ ድረ ገጽ አዘጋጅ የሆነው አርአያ ጌታቸው መንግስትን ሸሽተው ከሀገር ተሰደዱ!
ማስተዋል ብርሃኑ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የሚያዘጋጃት ፍትህ ጋዜጣ አሳታሚ የነበረ ሲሆን በተለይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት በኋላ ፍትህ፤ ”
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሞቱስ ለምን ሞቱ ትላለች…” ተብላ ከሰላሳ ሺህ ኮፒ በላይ እንድትቃጠል ቢደረግም መንግስታችን በቅጡ ስላልተደሰተ በአዘጋጁ ተመስገን እና በአሳታሚው ማስተዋል ብርሃኑ ላይ ክስ መመስረቱ ይታወቃል፡፡ (የማይታወቅ ከሆነ አሁን ይታወቅ)
እነ ማስተዋል ብርሃኑ በተከሰሱበት በዚህ ክስ በ50 ሺህ ብር ዋስትና ተለቀው ለሚያዝያ 17 2005 የተቀጠሩ ሲሆን በክሱ ጥፋተኛ ከተባሉ እስከ አስራ ሰባት አመት እስር ይጠብቃቸዋል፡፡ ማስተዋል ሸሽቶ ከመውጣቱ በፊት የመንግሰት ደህነነት ሰዎች በተደጋጋሚ እየተከታተሉ የእጅ ስልኩን በመንጠቅ ከማን ጋ እንደተደዋወለ እና ምን አይነት መልዕክት (ሜሴጅ) እንደተለዋወጠ በግድ ያዩበት እንደነበር ነግሮኛል፡፡
በነገራችን ላይ የፍትህ አሳታሚ እና ፍትህ ጋዜጣ በቀጠሮ ከተያዘው ክስ በተጨማሪ ወደ አርባ የሚጠጉ በይደር የተያዙ ክሶችም አሉበት፡፡
በተጨማሪም ከስድስት አመታት በፊት የተቃውሞውን ጎራ የተቀላቀለው ወጣት አርአያ ጌታቸው በበኩሉ በተለይ የፍትህ ጋዜጣ ድረ ገጽን ማሰናዳት ከጀመረ ወዲህ የበረታ ክትትል እና ማስፈራሪያ ከመንግሰት የስጋ ዘመዶች እንደደረሰበት ይናገራል፡፡
ከዚህ በፊት አንድ የፌደራል ፖሊስ ኮማንደር በመኪና አፍኖ የማያውቀው ቦታ ከወሰደው በኋላ ለተመስገን ደሳለኝ ከውጪ ሀገር ያሉ አሸባሪ ዲያስፖራዎች የሚያደርጉለት የገንዘብ እርዳታ መኖሩን እና በመሃል ሆኖ ገንዘቡን የሚያቀባብለው ደግሞ እርሱ እንደሆነ ነግሮት፤ ይህንን ድርጊቱን የማያቆም ከሆነ በእህትህ እና በእናትህ ላይ ፈርደሃል ማለት ነው… የሚል ዛቻ አድርሶበታል፡፡
ከአመት በፊት ይህ ማስፈራሪ የደረሰው አርአያ፤ ለቤተሰቦቹ ደህንነት ሲል ቤት ተከራቶ መኖር ቢጀምርም፤ ከአመት በላይ የዘለቀው ይኸው ማስፈራሪያ አሁንም እጅግ ተባብሶ “ከፍትህ ጋዜጣ ጋር ያለህን ግንኙነት አቁም ብለንህ እስካሁን አላቆምክም ስለዚህ እንገድልሃለን!” በሚል ቃል በቃል ማስጠንቀቂያ ሲደርሰው “ገዳዮቹን” መሸሹን ይናገራል፡፡
አርአያ የፍትህ ጋዜጣ ድረ ገጽ አዘጋጅ የነበረ ከመሆኑም በላይ ሰማያዊ ፓርቲን ከመሰረቱት ግንባር ቀደም ወጣቶች አንዱ ነው፡፡
በፍትህ ምክንያት የተሰደዱት ማስተዋል ብርሃኑ እና አርአያ ጌታቸው አሁንም የደህንነታችን ነገር ስጋት ላይ ነው፤ ብለው ያሉበትን ቦታ እንዳልናገር አደራ ብለውኛል፡፡
የምናገረው ነገር ግን አለኝ፤ በአዲስ መስመር እንዲህ እላለሁ፤
እንደዚህ እያባረሩ እና እንደዚያ እያማረሩ ስንት አመት መዝለቅ ይቻላል፡፡
እውነት እውነት እላችኋለው ከጥቂት እርምጃ በኋላ እግራችሁ እግራችሁን ጠልፎ ይጥላችኋል!
ነብር… መንግስት
ሰሞኑን “ከሀገራችን ውጡ” ተብለው ከሀገራቸው እና ከቤታቸው የተባረሩ ሰዎችን ጉዳይ ሳስብ፤ መንግስታችን አስሮ የሚያንገላታቸውን ጋዜጠኞች እና ፖለቲከኞች ጉዳይ ሳስብ፤ በየቀኑ ባህር አቋርጠው የሚሰደዱ ወግኖቻችንን ሳስብ… ሳስብ ሳስብ ሳስብ… በዛን ሰሞን ወዳጃችን ሰለሞን ሞገስ ያወጋን ጨዋታ ትዝ አለችኝ፤ እንደሚከተለው ትቀርባለች፤
በአንድ ወቅት በቻይና ውስጥ እንዲህ ሆነ አሉ፤
ሴትዮዋ በአንድ ጫካ ጥጋት ላይ ከሁለት ጨቅላ ልጆቿ ጋር ቁጭ ብላ እየዬ እያለች ታለቅሳለች፡፡
በአካባቢዋ አንድም ሰው አልነበረም፡፡ ልቅሶዋ እጅግ በበረታ ጊዜ ግን አገር አቋርጦ የሚያልፍ አንድ መኪና ድንገት አጠገቧ ቆመ እና ከውስጡ ሰዎች ወረዱ፡፡ እዚህ ቦታ ሰው ይኖራል ብለው አላሰቡም ነበርና ሰው ማየታቸው ሲያስገርማቸው፤ የእናቲቱ ለቅሶዋ ደግሞ እጅግ አስጨነቃቸው፡፡
“ምን ሆነሽ ነው እዚህ ብቻሽን ተኮራምተሸ የምታለቅሺው…” አሏት፡፡
ጭራሽ ሀዘኗ በረታ! የሆነችውንም ዘርዝራ ስትነግራቸው እየተንሰቀሰቀች ነበር፡፡
“የጫካ ነብር ባሌን በላብኝ፤ የእርሱ ሀዘን ከልቤ ሳይወጣ ትልቁ ልጄን አሁን ነጠቀኝ አሁንም ትንሽ ቆይቶ መምጣቱ አይቀርም…” ስትል ተንሰቀሰቀች፡፡
ነገሩ በጣም ያስጨነቃቸው መንገደኞች፤ “ታድያ እዚህ ቁጭ ብላችሁ ሞታችሁን ከምትጠባበቁ ለምን ወደ ከተማ አትወጡም…?” አሏት፡፡
እርሷም፤ “ከተማማ መንግስት አለ!” አለቻቸው፡፡
ከነብር ይበልጥ ተናካሽ እና ተንኳሽ ከሆነ መንግስት ይሰውረን፡፡
torsdag 11. april 2013
የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የመብራት እና ውሀ እጥረት አማረረን ይላሉ
በአዲስ አበባ መብራት ለተከታታይ ሶስት ቀናት ማግኘት ትልቅ ዜና እየሆነ ነው የሚለው ዘጋቢያችን፣ የመብራት መቋረጥን ተከትሎ በሚፈጠረው ችግር ባንኮች፣ አየር መንገዶችና ሌሎች ድርጅቶች ስራቸውን በተገቢው መንገድ ለመስራት እንዳልቻሉ ገልጿል።
ኢትዮጵያ ለጅቡቲ የኤሌክትሪክ ሀይል ሽያጭ መጀመሩዋን የተናገረው መንግስት፣ መብራትን በፈረቃ ለማቅረብ መዘጋጀቱንም የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በመብራት እጦት ብቻ ሳይሆን በውሀ ችግርም እየተሰቃዩ ነው፡፡ አንዳንድ አካባቢዎች ካለፉት ሶስት ቀናት ጀምሮ ውሀ አላገኙም።
ወደ ቤንሻንጉል ጉሙዝ የሚጓዙ የአማራ ተወላጆች ሁኔታ አሳሳቢ ነው ተባለ
ቁጥራቸው ከ5 ሺ በላይ የሚጠጉ ከፍኖተሰላም ወደ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እንዲመለሱ የተደረጉት የአማራ ተወላጆች በሚመለሱበት ቦታ የደህንነት ዋስትና እንደሌላቸው ያነጋገርናቸው ተፈናቃዮች ገለጹ። የክልሉ መንግስት በበኩሉ ስህተት መፈጠሩን በማመን
ችግሩን የፈጠሩት ታች ያሉ አመራሮች ናቸው ብሎአል።
ትናንት ማክሰኞ 21 መኪኖች፣ በዛሬው እለት ደግሞ 14 መኪኖች ተፈናቃዮችን ከአቅማቸው በላይ በመጫን ወደ ቤንሻንጉል ጉሙዝ አቅንተዋል። የክልሉ መንግስት ፕሬዚዳንት ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለጹት ተፈናቃዮች እንዲወጡ የተደረገው በስህተት መሆኑን ተናግረው ይቅርታ ጠይቀዋል። ፕሬዚዳንቱ የዞንና የወረዳ አመራሮችን ተጠያቂ ያደረጉ ሲሆን፣ እርምጃ እንደሚወሰድባቸውም ተናግረዋል።
” እርምጃ ይወሰድባቸዋል የተባሉት የከማሸ ዞን አስተዳዳሪ እና የያሶ ወረዳ አስተዳዳሪ “የአካባቢውን ተወላጆች አማራ ወረራችሁ ተነሱ እያሉና እየሰበኩ ወደጫካ መግባታቸውን የደረሰን መረጃ የሚያመለክት ሲሆን የፌደራል ፖሊሶችም የሸፈቱትን ባለስልጣናት በመፈለግ ላይ መሆናቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ሁለቱ ባለስልጣናት ስለመሸፈታቸው ኢሳት እስካሁን ከገለልተኛ ወገን ለማረጋገጥ አልቻለም።
በከማሺ ዞን በአንድ የግብርና ኢንቨስትመንት ስራ ውስጥ ተቀጥረው እስካሁን ያልተፈናቀሉ የአማራ ተወላጅ እንደገለጹት በክልሉ እየተነዛ ያለው ወሬ አደገኛ በመሆኑ ተፈናቃዮች ሲመለሱ ችግር ሊደርስባቸው እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል
ትናንት እና ከትናንት በስቲያ በመተከል ከተማ ቁጥራቸው ከ4 እስከ 5 ሺ የሚጠጉ ተፈናቃዮች የተቃውሞ ሰልፍ ያደረጉ ሲሆን፣ መንግስት የተዘረፉ ንብረቶቻቸው እንዲመለሱላቸው እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
አብዛኛው የከተማው ነዋሪዎች ድጋፋቸውን ለተፈናቃዮች ሲያሳዩ እንደነበር ከስፍራው የደረስን መረጃ ያመለክታል።
mandag 8. april 2013
ትግል… ሽንፈት፤… ድል፤ ሽንፈት… (ተመስገን ደሳለኝ)
ከምሽቱ አንድ ሰአት አልፏል፤ የእጅ ስልኬ ደጋግሞ ቢጮኽም ትኩረት አልሰጠሁትም፡፡ ከጥቂት ሰከንዶች ፋታ በኋላ የቢሮዬ ስልክ ጮኸ፤ አነሳሁት፡፡ ለካስ እንዲህ በአንዱ አልመልስ ስላት፣ በሌላው እያፈራረቀች የምትደውለው ዕድሜዋ ወደ ሰባ እየተጠጋ ያለው አሮጊቷ እናቴ ኖራለች፡-
‹‹አቤት! እናቴ››
‹‹ለምንድነው የዚህን ያህል ስልኩ ሲጮኽ የማትመልሰው?›› ቆጣ ብላ ጠየቀችኝ፡፡
‹‹አስቸኳይ ስራ ላይ ስለነበርኩ ነው››
‹‹ኤዲያ! አንተ ደግሞ ሁል ጊዜ ጠብ ለማይል ነገር፣ ችክ ማለት ትወዳለህ››
…በእርግጥ እናቴ እውነቷን ነው! ችክ ያልኩ ቸካካ ነገር ሳልሆን አልቀርም ፡፡
‹‹ልዕልና›› ጋዜጣ ታግዳለች፤ እንደ‹‹ፍትህ›› እና ‹‹አዲስ ታይምስ›› ሁሉ የስርዓቱ የአፈና ሰለባ ሆናለች፤ የሚገርመው ግን መታገዷ አይደለም፣ የታገደችበት መንገድ እንጂ፡፡ ከዚህ ቀደም ደጋግሜ እንደገለፅኩት አቶ መለስን የተኩት ሰዎች ከእረሱም የባሱ ጭፍን አምባገነኖች ናቸው፡፡ ማንንም አይፈሩም፡፡ እግዚአብሄርንም ቢሆን ‹‹በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ካልተጠመቅህ አምላክ ሆነ እንድትቀጥል አንፈቅድልህም›› ከማለት አይመለሱም፡፡
የሆነ ሆኖ የስርዓቱ አይን አውጣነት የደረሰበትን ደረጃ ለመገንዘብ የሚከተለውን በጥሞና አንብቡ፡፡
የ‹‹ልዕልና›› አሳታሚ ድርጅት በሁለት ወዳጆቼ ስም ከተገዛ በኋላ፣ ስም ከመዞሩ በፊት ስርዓቱን ወጥመድ ውስጥ የሚከት ስልት (አይን ያወጣ አምባገነን ባህሪውን ወዳጆቹ ሳይቀር ይኮንኑት ዘንድ ወደ አደባባይ የሚያወጣ) ተነደፈ፡፡ በስልቱ መሰረትም ከቀድሞ የድርጅቱ ባለቤቶች ጋር አንድ ስምምነት ተደረገ፡፡ ይኸውም እኔ የሚጠበቅብኝን የአክሲዎን ሽያጭ ክፍያ አስቀድሜ ብከፍልም፤ ምንም አይነት የስም ዝውውር ሳይደረግ ባለቤትነቱ በእነርሱ ስም ሆኖ እንዲቀጥል ተስማማን፡፡ በዚሁ መንገድ ስራው ተጀመረ፡፡ ለአፈና ሲንደረደር ግራና ቀኝ ለማያጣራው መንግስት ደግሞ እንዲህ የሚል የ‹‹ተጋገረ›› መረጃ በጋዜጣችን ላይ አስተላለፍን ፡-
‹‹በህጋዊ መንገድ የስም ዝውውር አድርገን ነው ስራ የጀመርነው፡፡››
እነሆ ይህ በሆነ በአስራ ሶስተኛው ቀን (13/07/05) ብሮድካስት ውስጥ ያሉ ዞምቢዎች ‹‹ድርጅቱ ለሌላ ሶስተኛ ወገን በህገ-ወጥ መንገድ የስም ዝውውር አስተላልፏል›› ሲሉ ድምፃቸውን አሰሙ፡፡
መቼ ተላለፈ? የተላለፈላቸው ሰዎችስ ስም ማን ይባላል? የሚሉት መሰረታዊ ጥያቄዎች ብሮድካስትን አያሳስቡትም፤ ያውም አንድ የሚዲያ ተቋምን ያህል ነገር ሲዘጋ (በነገራችን ላይ የስም ዝውውር የተደረገው ብሮድካስት ደብዳቤውን ከፃፈ ከአምስት ቀን በኋላ /በ18/07/05/) ነው፡፡
ለብሮድካስት ህገ-ወጥ እግድ ጋዜጣዋ መገዛት እንደሌለባት አዘጋጆቹ ስምምነት ላይ ስለደርሰን በ20/07/05 ታተመች፡፡ ሆኖም ሌላው ዞምቢ ድምፁን አሰማ-ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፡፡ ይህ መስሪያ ቤት ያለምንም ማጣራት ጋዜጣዋ በወጣችበት ዕለት (20/07/05) ንግድ ፍቃዳችንን መሰረዙን የሚገልፅ ደብዳቤ ላከልን፡፡ በእጅጉ የሚገርመው ሁለቱም ‹‹ተቋምዎች›› ህገ-ወጥነታችንን የገለፁት ተመሳሳይ የአዋጅ ቁጥር በመጥቀስ መሆኑ ነው፡፡ ‹‹ከመገናኛ እና ብዙሃን የመረጃ ነፃነት አዋጅ ቁጥር 590/200 ከሚፈቅደው ውጪ…›› በማለት፡፡ …ይህ ምን ማለት ነው? በዚህ አዋጅ ውስጥ በርካታ አንቀፆች ተደንግገዋል፡፡ ስለአታሚ፣ አሳታሚ፣ ዋና አዘጋጅ፣ መረጃ የማግኘት መብት፣ የማሳተምና የመደራጀት ነፃነት፣ ስለአከፋፋዮች… አጅግ ብዙ ጉዳዮችን ያካትታል፡፡ ታዲያ እኛ የታገድነው ከእነዚህ ሁሉ አንቀፆች የትኛውን ተላልፈን ነው? …ቢያንስ መንግስት የሚመስል ነገር ወይም ‹‹መንግስት ነኝ›› የሚል ካለ ጥፋታችንና የተላለፍነውን የአዋጁን አንቀፅ ቢነግረን ሌላው ቢቀር ከስሜት መጎዳት እንድን ነበር፡፡ ነገር ግትን ዞምቢዎቹ እንደከዚህ ቀደሙ አንቀፅ በመጥቀስ ማስመሰል እንኳን አልቻሉም፡፡ በደፈናው የአዋጅ ቁጥር ጠቀሱና አረፉት፡፡
…አሁን ሀገራችን አስፈሪ ደረጃ ላይ ደርሳለች፡፡ በአደባባይ ህግ ለመጣስና የፈቀዳቸውን ለማድረግ ትንሽ እንኳ በማያመነቱ አደገኛ ሰዎች መዳፍ ስር ወድቃለች፡፡ የአማርኛ ቋንቋ ተናገሪዎች ለዓመታት ከሰፈሩበት ቀዬ በኃይል መፈናቀላቸው ቀጥሏል፡፡ በእርግጥ በመለስ ዘመንም ቢሆን መፈናቀሉ ነበር፡፡ ኧረ እንዲያውም ‹‹ደን እየጨፈጨፉ ስላስቸገሩ ነው›› ብሎ ሁሉ አላግጦባቸዋል፡፡
የአማራው ‹‹ወኪል›› ነኝ የሚለው ብአዴንም ቢሆን ከታምራት ላይኔ ክፉ መንፈስ ገና ነፃ አልወጣም፡፡ ታምራት ላይኔ በስልጣን ዘመኑ በርካታ የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ተወላጆች በየአካባቢው ሞትና መፈናቀል እየደረሰባቸው እንደሆነ ሲነገረው ‹‹እኛ ከክልል ሶስት ውጪ ስለሚኖሩ አማሮች አያገባንም፡፡ ምክንያቱም በነፍጠኝነት ለወረራ የሄዱ ናቸው›› ብሎ ተሳለቆ ነበር፡፡ ዛሬ እነኦቦ አዲሱ ለገሰም ከዚህ አቋማቸው አልተቀየሩም፡፡ ተወልደ ወ/ማርያም በክፍፍሉ ወቅት ብአዴኖች ከመለስ ጎን በመቆማቸው ተበሳጭቶ ‹‹የፖለቲካ ደሀ ናችሁ›› ሲል መተቸቱ በረከት ስምዖን ዛሬም የገባው አይመስለኝም፡፡
የማፈናቀሉ መሀንዲስ ህወሓትም ቢሆን ይህ መንገድ ብዙ ርቀት የማያስኬድ ስለመሆኑ ከሃያ ዓመት በኋላም አልተገለፀለትም፡፡ ለዚህም ይመስለኛል ከፋፍሎ በመግዛት እና በማዳከም ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ በመከተል ጉልበቱን እያዛለ ያለው፡፡ በነገራችን ላይ መረሳት የሌለበት ቁም-ነገር የጥፋት ስራው ተጠያቂ ህወሓት እንጂ ‹‹እወክለዋለው›› የሚለው የትግራይ ህዝብ አለመሆኑ ነው፡፡ አማራ-በብአዴን፣ ኦሮሞ-በኦህዴድ እንደማይገለፀው ሁሉ፣ የትግራይ ህዝብም በህወሓት ይገለፃል የሚል የጨዋታ ህግ የለም፡፡ እነዚህ ሰዎች ለስልጣናቸው እስከጠቀመ ድረስ የማይፈፅሙት ህገ-ወጥ ድርጊት አለመኖሩ ላይ መስማማት የሚኖርብን ይመስለኛል፤ የማይፈፅሙት ጭካኔም የለም፡፡ ይህንን የሚያሳይ አንድ ነገር ልንገራችሁ፡፡ ታሪኩ የቀድሞ የደህንነት ሹም የነበረው ክንፈ ገ/መድህንን በጥይት ደብድቦ ስለገደለው ሻለቃ ፀሀዬን የሚመለከት ነው፡፡ እንደሚታወቀው ሟችም ገዳይም ትግርኛ ተናጋሪዎች ቢሆኑም፣ ሻለቃው ወንጀሉን ከፈፀመ በኋላ ለብዙ ችግር ተዳርጎ ነበር፣ ያውም ከነቤተሰቡ፡፡ መጀመሪያ ባለቤቱን ከምትሰራበት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት አባረሯት፡፡ እግር በእግርም እየተከታተሉ በኪራይ ከምትኖርበት ቤት አፈናቀሏት (በጊዜው እስክንድር ነጋ የገንዘብ ድጋፍ ያደርግላት ነበር) ሻለቃውም ለስድስት ዓመት ያህል በጨለማ ቤት ውስጥ በመታሰሩ የአይን ብርሃኑ በከፍተኛ ደረጃ ተጎዳ፡፡ ፍርድ ቤት ሲቀርብ እንዴት ለመራመድ ይቸገር እንደነበረ አስተውለናል፡፡ እኔ እያልኩ ያለሁት ያጠፋ ሰው በህግ አይጠየቅ አይደለም፤ ከህግ ውጪ ስለምን የበቀል ሰለባ ይሆናል ነው? ሰዎቹ ከየትኛውም ብሄር ተወለዱ በጠላትነት ከመዘገቧችሁ ለጭካኔያቸው ወደር የለውም፡፡
የሆነው ሆኖ ስርዓቱ ገደብ ላጣው ጭካኔው ‹‹ብሄር›› የተሰኘ አጥር የለውም ያስባለኝ በሻለቃው ህይወት መጨረሻ የተፈፀመው ድርጊት ነውና እሱን ልንገራችሁ፡፡
ዕለቱ የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች ‹‹ፍልሰታ›› እያሉ የሚጠሩት የአስራ ስድስት ቀን ፆም ዋዜማ ነው-ሐምሌ 30ቀን፡፡
ሻለቃው ይህች ቀን የመጨረሻዋ መሆኗን ሊያውቅ የሚችልበት አገጣሚ አልነበረምና ጥብቅ ሀይማኖተኛ በመሆኑ ለፆሙ የመንፍስና የቁስ ዝግጅቱን አጠናቆ በደስታ እየጠበቀ ነው፡፡ የሆነው ግን በተቃራኒው ነበር፡፡
በፃሃፊ ብዕር ልተርክላችሁ፡፡
…ወቅቱ ክረምት ቢሆንም ፀሀይ ህቡዕ የገባች እስኪመስል ድረስ ዝናብን አግደው የያዙ የሰማይ መስኮቶች ከንጋት ጀምረው ላንቃቸውን ከፍተው ምድሪቱን እያረሰረሷት ነው፡፡ ቀኑ ተገባዶ አስር ሰዓት ላይ ደርሷል፡፡ አብዛኛው እስረኛ በየክፍሉ ከቷል፡፡ ጥቂቶቹ ደግሞ ውሽንፍሩን ተከትሎ ያረበበውን ቅዝቃዜ ይከላከልልናል በሚል ካፍቴሪያ ውስጥ ቁጭ ብለው ሻይና ቡና ደጋግመው ያዛሉ፡፡
አንዲት የደህንነት መኪና ሾፌሩን ጨምሮ አራት ሰዎች አሳፍራ ወደማረሚያ ቤቱ አስተዳደር መግባቷን ማንም አላስተዋለም፡፡ መኪናዋ የኃላፊውን ቢሮ ታካ ስትቆም የቡድኑ መሪ ቀልጠፍ ብሎ ወርዶ በቀጥታ ከፊቱ ወደአለው ቢሮ በመግባት፣ ከማረሚያ ቤቱ ኃላፊ ጋር ለጥቂት ደቂቃዎች ቆይታ ከአደረገ በኋላ በወህኒ ቤቱ ውስጥ ያልተለመደ ትዕዛዝ ተላለፈ፤ ሁሉም እስረኛ ወደ ክፍሉ እንዲገባ የሚል፡፡
እስረኞቹ በሙሉ ወደ ክፍላቸው መግባታቸው ከተረጋገጠ በኋላ የሞት ፍርድ ተፈርዶበት ቀኑን እየጠበቀ የነበረው ሻለቃ ፀሀዬ ከክፍሉ ወጥቶ ከደህንነት ቢሮ ወደመጣችው መኪና ውስጥ እንዲገባ ተደረገ፡፡ መኪናዋም በመጣችበት ፍጥነት የመልስ ጉዞ አደረገች፡፡ ይህ ሁሉ ነገር ተካሄዶ ያለቀው በአስራ አምስት ደቂቃ ውስጥ ነበር፡፡
…ጎዳናው ላይ አልፎ አልፎ እየተንገዳገደ ከሚያዘግም ሰካራም እና ከሚያላዝኑ የመንገድ ዳር ውሾች በቀር አንዳች እንቅስቃሴ አይታይም፤ ጭር ብሏል፡፡ የክረምቱ ቅዝቃዜ በድቅድቅ ጨለማ ቁጥጥር ስር ከዋለው ሌሊት ጋር ተቀላቅሎ በእጅጉ ያስፈራል፡፡ የሻለቃው ባለቤት ወ/ሮ አምሳለ የመኖሪያ ቤቷ በር ሲንኳኳ ከሶስት ልጆቿ ጋር በእንቅልፍ ዓለም ውስጥ ነበረች፡፡ ማንኳኳቱ ሳይቋረጥ ለደቂቃዎች በመቀጠሉ ድንገት ካሰጠማት እንቅልፍ አባነናት፡፡ እናም በሩን ከፈተች፡፡ ከዚህ ቀደም አይታቸው የማታውቃቸው ሁለት ሰዎች ቆመዋል፡፡ ደነገጠች፡፡
‹‹ምንድን ነው? ምን ፈልጋችሁ ነው?›› አከታትላ ጠየቀች፡፡
‹‹ፖሊሶች ነን፣ ሻለቃ ፀሀዬ በጣም ስለታመመ አምሳለን ጥሩልኝ ስላለን ነው የመጣነው›› ሲል መለሰ አንደኛው ሰውዬ፡፡
‹‹ቀን ስንቅ ስወስድለት ደህና አልነበረ እንዴ? አሁን ምን ተፈጠረ?››
‹‹ድንገት ነው የታመመው፤ ልታዪው የምትፈልጊ ከሆነ ቶሎ እንሂድ?›› አለና አጣደፋት በሌሊት ከሰው ደጅ ቆሞ መመላለሱ ያልተመቸው ሁለተኛው ሰው፡፡ ወ/ሮ አምሳለም ስጋት እንደሞላት ሰዎቹን አሳፍራ በመጣችው መኪና ውስጥ ገብች፡፡ ሆኖም መኪናዋ ወደመጣችበት መመለሰ ስትጀምር መንገዱ ወደቃሊቲ የሚወስደው እንዳልሆነ ተረዳች፡፡ ከሃያ ደቂቃ ጉዞ በኋላም መኪናዋ አንድ ግቢ ውስጥ ገብታ ቆመች፡፡ ሁሉም ወረዱ፡፡
‹‹የታለ ባለቤቴ?›› አምሳለ ጠየቀች፣
‹‹ያው! እዛ ክፍል ውስጥ ግቢ፣ እየጠበቀሽ ነው›› አላት አንደኛው ሰው፣ በሩ ወደተከፈተ ክፍል በእጁ እያመለከተ፡፡
እንደተባለችው ገርበብ የተደረገውን በር ሙሉ በሙሉ ከፍታ ገባች፡፡ …ክፍሉ ወለል መሀል ላይ ሻለቃው በጥይት ተበሳስቶ በጀርባው ተዘርሯል፡፡ …ያልጠበቀችውን ክስተት የተመለከተችው የሻለቃው ባለቤት እንደሎጥ ሚስት የጨው አምድ ሆነች፡፡ …የዚህን ያህል ነው የህወሓት ጭካኔ፡፡ ከመስመሩ ካፈነገጣችሁ ትግሬ ሆናችሁ አማራ ጉዳዩ አይደለም፡፡ እናም ማቆሚያ ላጣው የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች መፈናቀልም ብቸኛው ተጠያቂ ህወሓት እንጂ ‹‹ወከልኩት›› የሚለው ህዝብ በፍፁም ሊሆን አይችልም፡፡ ይህ አመለካከት የተሳሳተ ከመሆኑም በላይ የማይታረም አደጋ ያስከትላል፡፡
የሆነ ሆኖ እንዲህ አይነቱን አጓጉል ችግር ፈጣሪ ድርጊት ሁላችንም በጋራ ለማስቆም መሰለፍ አለብን፡፡ በይበልጥ ደግሞ ከሀገሪቱ የተለያዩ አካባባዎች መጥታችሁ፣ የተለያየ አካባቢ ሰፍራችሁ ሀብት እያፈራችሁ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን ነጋዴዎች ይህ አይነቱ ማፈናቀል ባስቸኳይ ይቆም ዘንድ ነግ በእኔ ብላችሁ ስርዓቱ ላይ ጫና ማሳደር አለባችሁ፡፡ ቀጣዩ ተረኛ እናንተ ላለመሆናችሁ ምንም ማረጋገጫ የለም፡፡
የስርዓቱ ደጋፊዎችም ሆናችሁ ልሂቃኖች፣ በአሰልቺ ዜማ ጠዋትና ማታ ‹‹አባይ፣ አባይ…›› የምትሉ አርቲስቶች ከምንም በፊት ስለንፁሀን እምባ መገደብ ልትናገሩ ይገባል፡፡ አገዛዙ የዱርዬ ባህሪውን ይገድብ ዘንድ ስትዘምሩ መስማት እንፈልጋለን፡፡ … እስቲ ዙሪያችንን እንመልከት፤ ትላንት ከኋላችው ቆምን ነፃ ያወጣናቸው ሀገራት ዛሬ የብሄር ፖለቲካን ለእኛ ጥለውልን ርቀው ሄደዋል፡፡ በዘላቂነት አብሮን ለማይቆይና ጠብ ለማይል ነገር እንማስናለን፡፡ እናቴም እንዲሁ ነበር ያለችኝ ‹‹ችክ አትበል! ጠብ ለማይል ነገር!›› ሆኖም ግሳጼዋን ችላ ብዬ ለምን እንደደወለችልኝ ጠየኳት፡፡
‹‹ትላንት ለምን ወደ ቤት አልመጣህም?››
‹‹ምነው ፈልገሽኝ ነበር እንዴ?››
‹‹አዎ! የአባትህ 13ኛ ሙት ዓመት ነበር እኮ›› …ደነገጥኩ፡፡ ጊዜው እንዴት ይሮጣል? ግና በለሆሳስ ‹‹አባቴ ሆይ ነፍስህ በአፀደ ገነት እንዳለች አምናለሁ!›› ስል እናቴ ማነብነቤን ሰምታኝ ኖሮ ምን እንዳልኩ ጠየቀችኝ፡፡
‹‹አይ! ምንም አላልኩም››
‹‹ለማንኛውም ዛሬ ወደ ቤት እንድትመጣ?››
‹‹እናቴ! ቢሮ ስለማመሽ ልመጣ አልችልም፤ ራሴ ቤት ነው የማድረው››
‹‹እረስተከዋል እንዴ! ዛሬ እኮ መጋቢት ሀያ ሰባት ነው››
‹‹እና ታዲያ?››
‹‹የተወለድክበት ቀን ነዋ!›› …ሌላ የተረሳ ጉዳይ፡፡ ይህ ሳምንት ድብልቅልቅ ያለ ነው፡፡ የአባቴ 13ኛ ሙት ዓመት፣ የልደት ቀን፣ ሽልማት (በነገራችን ላይ
‹‹ኢትዮቲዩብ›› ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን ለማስከበር አስተዋፆ አድርገሀል በማለት የሸለመው እኔን ብቻ ሳይሆን ባልደረቦቼንና አንባብያንንም ጭምር በመሆኑ በሁሉም ስም እንዲህ ማመስገኑ አስፈላጊ ሆኖ አግኝቸዋለው፡- ‹‹እንዳከበራችሁን እግዚአብሄር ያክብርልን፤ መጪውም ከዚህ የበለጠ ስራ የምትሰሩበት የስኬት ዘመን ይሆንላችሁ ዘንድ እመኛለሁ››)
ይህንን ርዕሰ ጉዳይ ከማሳረጌ በፊት መልዕክቴን ላስተላልፍ፡-
አሁንም ትግሉ ይቀጥላል፡፡ ‹‹ልዕልና›› ብትዘጋም ሌላ ይከፈታል፡፡ ትግል… ሽንፈት፤ …ድል፤ እንደገና መሸነፍ… ተስፋ አንቆረጥም፤ ገና ወደፊት እንቀጥላለን፤ በዘመናችን ብዙ ነገር አይተናል፤ ርዕዮተ-ዓለም ሲሸነፍ ተመልከተናል፤ ስርዓት ድል ሲመታ አይተናል፤ ህዝብ እንደ ህዝብ ሲሸነፍ ግን ማንም ተመልክቶ አያውቅም፡፡ እናም እኔ ጋዜጠኛ ነኝ ‹‹ለዲሞክራሲና መልካም አስተዳደር ፀልዩ›› ብዬ ልመክር አልችልም፡፡ ነገር ግን እልፍ ሆነን እንዘምር ዘንድ ድምፄን ከፍ አድርጌ እጠይቃለሁ፡-
አትነሳም ወይ? አትነሳም ወይ?
ይሄ ባንዲራ የአንተ አይደለም ወይ?
…ኢ-ፍታሀዊነትን እንዋጋለን፣ የከፋፍለህ ግዛን አስተዳደር እንቀይራለን፡፡ በሩንም በሰላም ይከፍቱልን ዘንድ ደጋግመን እናንኳኳለን፤ ካልከፈቱልንም ገንጥለን እንገባለን፡፡ ከዛ በኋላም ሀገራችንን የራሳችን እናደርጋለን! ያዘኑትም ይስቃሉ፤ የታሰሩትም ይፈታሉ፤ የተሰደዱትም ይመለሳሉ፤ የወጡትም ይወርዳሉ፡፡
(መጋቢት 27/2005 ዓ.ም እኩለ ሌሊት)
lørdag 6. april 2013
ሙስና እና ፖለቲካ ብአዴንን እየፈተኑት ነው
ማንኛውም ሰው” ይላሉ አንድ የብአዴን ከፍተኛ አመራር ” ስለ እነ አቶ በረከት ክፉ ቢያወራ በደቂቃዎች ውስጥ ራሱን እስር ቤት ውስጥ ያገኘዋል፣ ባበህርዳር።”
በ9ኛው የኢህአዴግ ጉባኤ ኪራይ ሰብሳቢነት፣ በተለመደው ቋንቋ ሙስና ወይም ጉቦኝነት የድርጅቱ ዋነኛው የመወያያ አጀንዳ ሆኖ ነበር።
የብአዴን ነባር ታጋይ አቶ ህላዊ ዮሴፍ፣ እውን ከፍተኛውን አመራር የምንጠይቅበት ስርአት አለን?” ሲሉ ያቀረቡት ጥያቄ ብዙዎች በዚያ መድረክ ይጠየቃል ብለው ያልጠበቁት ነበር።
አቶ ህላዊ ዮሴፍ፣ የአማራ ልማት ማህበር ሊ/መንበር በነበሩበት ጊዜ ፣ የድርጅቱን የሂሳብ ሰነዶች አቃጥለው ያለተጠያቂነት ወደ አዲስ አበባ እንዲዛወሩ መደረጋቸው አንዳንድ የብአዴን አባላትን ሲያብሰከስክ የቆየ ቢሆንም ፣ በኢህአዴግ 9ኛው ጉባኤ ላይ ባሳዩት ጠንካራ አቋምና ባቀረቡት ንግግር ብዙዎቹ ተደስተዋል። አስገራሚው ነገር ይላሉ የ ብአዴኑ ሰው ” ከሽማግሌዎቹ የብአዴን አመራሮች በስተቀር ሌሎች ወጣት አመራሮች ምንም ነገር ሳይናገሩ ጉባኤው ተጠናቋል። ወጣት አመራሮች እንደ ተራው አባል ሁሉ “እናውቃለን፣ ብንናገር እናልቃለን “ የሚሉ የመስለኛል ይላሉ አባሉ።
የባህርዳር ከተማ ህዝብ እና የብአዴን አባላት የሚያሰሙት የውስጥ ለውስጥ ተቃውሞ ማየል ያሰጋቸው አቶ በረከት ስምኦንና አቶ አዲሱ ለገሰ፣ ቁልፍ ሰዎች የሚሉዋቸውን፣ የክልሉን የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ የነበሩትን አቶ ከበደ ጫኔን እና የክልሉን የፍትህ ቢሮ ሀላፊ የነበሩትን አቶ ጌታቸው አምባየን ወደ ፌደራል መንግስቱ እንዲዛወሩ አደረጉ። አቶ ከበደ ከጸጥታ ዘርፍ ሃላፊነት ወደ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒሰትርነት፣ አቶ ጌታቸው ደግሞ ከፍትህ ቢሮ ሀላፊነት በምክትል ከንቲባነት ማእረግ የመሬት ባንክ ሃለፊ ሆነው ተሾሙ።
ሁለቱ ባለስልጣናት ወደ አዲስ አበባ እንደተዛወሩ በባህርዳር ከተማ ነዋሪ የሆኑት ታዋቂው ባለሀብት ለእያንዳንዳቸው ሁለት ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ቤት ገዝተው ቁልፉን አስረከቧቸው።
ባለሀብቱ በባህርዳር እምብርት ላይ የተገነባው የጋሳ ሆቴል ባለቤት ናቸው። አቶ በረከት በቦርድ ሰብሳቢነት የሚመሩት የዳሽን ቢራም ብቸኛ አከፋፋይ ናቸው።
ደሻን ቢራንን ከ1995 ዓም ጀምሮ እንዲያከፋፍሉ ሲመረጡ ያለማንም ተቀናቃኝ ነው። በተለምዶ አየር ማረፊያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢም ፣ በተንጣለለ መሬት ላይ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል እያስገነቡ ነው።
በሁመራ ለሰሊጥ ምርት ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ደግሞ ለተለያዩ የእርሻ ስራዎች የሚውሉ እጅግ ሰፊ መሬት አግኝተዋል። ከ5 በላይ ዩሮ ትራክተሮች፣ በርካታ ዶዘሮች፣ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ሚኒባሶች እና ሌሎች በርካታ ድርጅቶች ያሉዋቸው ባለሀብት፣ ለርጅም ጊዜ በልብስ ሰፊነት ነበር የሚተዳደሩት።
ወጣት የብአዴን አመራሮችን ያሳሰበው ጉዳይ ግለሰቡ በአጭር ጊዜ ቱጃር መሆናቸው ሳይሆን፣ ሀብታቸውን ተከትሎ ያላቸው ፖለቲካዊ ጫና እየጎላ መምጣቱ ነው። በአቶ በረከት ፣ በአቶ አዲሱ እና በአቶ ታደሰ ካሳ ላይ ትችት የሚያቀርቡ፣ እርሳቸውን የተመለከቱ ጥያቄዎችንም የሚያነሱ የብአዴን አባላትም ሆኑ የባህርዳር ነዋሪዎች፣ በምሽት ራሳቸውን ” የደህንነት ሹም በነበሩት አቶ ከበደ ጫኔ ቢሮ ውስጥ” ማግኘቱ የተለመደ ነው፣ እንደ ውስጥ አዋቂው የብአዴን ከፍተኛ አመራር። የክልሉን ፍትህ ቢሮ በበላይነት ሲዘውሩት የነበሩት አቶ ጌታቸው አምባየም የህግ ከለላ በመስጠት፣ ብቅ ብቅ የሚለውን የብአዴን ወጣት አመራር አንገቱን ያስደፉታል።
የክልሉ ምክር ቤት፣ የክልሉ ካቤኒ እና የክልሉ የጸረ ሙስና ኮሚሽን ከህዝቡና ከብአዴን አባላት የሚደርሳቸው ጥቆማ እያየለ መምጣቱን ተከትሎ፣ በጉዳዩ ዙሪያ መወያየት ጀመሩ።
የክልሉ ገቢዎችም በባለሀብቱ በአቶ ሸጋው ላይ ክስ መሰረተ፤ ዳሸን ቢራን ሲያከፋፍሉ 15 ሚሊዮን ብር ቫት ለመንግስት መክፈል ሲገባቸው አልከፈሉም በማለት። አቶ ሸጋውም ተይዘው ታሰሩ። ወጣት የብአዴን አመራሮችም ግለሰቡ ከህግ በላይ አለመሆናቸውን በማሳየታቸው ተደሰቱ። ደስታቸው ግን ለረጅም ጊዜ የዘለቀ አልነበረም። በቫት የተከሰሰ ሰው ዋስትና እንደሌለው ቢታወቅም፣ አቶ ሸጋው ማታውን በ150 ሺ ብር ዋስ እንዲወጡ ተደረጉ፣ በሁለተኛውም ቀንም ክሱ መቋረጡ ተሰማ።
ትእዛዙን የሰጠው ሰው ሳይታወቅ ቀረ፣ ወጣት የብአዴን አመራሮችም ሆድ ይፈጀው ብለው የውስጥ ትግላቸውን ቀጠሉ።
አቶ በረከት ዳሸን ቢራን በቦርድ ሰብሳቢነት ቢመሩትም፣ ለረጅም ጊዜ ስራ አስኪያጅ በመሆን ያገለገሉት አቶ ብርሀኑ አድማሱ ነበሩ። አቶ ብርሀኑ፣ ሪፖርተር ጋዜጣ በዳሸን ቢራ ላይ አሉታዊ ዘገባ አቅርቧል በማለት ፣ ዋና አዘጋጁ አቶ አማረ አረጋዊ ጎንደር ተወስዶ እንዲታሰር ያደረጉ ናቸው። ግለሰቡ በአቶ በረከት እና በአቶ አዲሱ በእጅጉ ይመካሉ።
ዊኪሊክስ ይፋ ባደረገው መረጃ ላይ በአንድ የእራት ምሽት ላይ አንድ የአሜሪካ የፖለቲካ አታሼ ለአቶ ብርሀኑ እንዲህ ሲል ይጠይቃቸዋል” ለመሆኑ እርስዎ ተጠሪነትዎ ለማን ነው?” አቶ ብርሀኑም ” ለእግዚአብሄር” ብለው መለሱ።
“ለአቶ በረከትና ለአቶ አዲሱ ሪፖርት አያደርጉም?” አሉዋቸው ደግመው፣ “በርግጥም ለሁለቱ ብቻ” ሪፖርት አደርጋለሁ።” አሉ። ዲፕሎማቱ ስለአቶ አማረ ሲያነሱባቸው ደግሞ “ I can make or break anyone. I have the right to kill” ( ማንንም እንደፈለኩ ማድረግ እችላለሁ፣ የመግደል መብት አለኝ።
’ የአሜሪካው ዲፕሎማትም አስተያየቱን በመጨረሻ ሲያሰፍር ” With this growth comes an increased sense of power and invincibility for the leadership of the brewery ” ፋብሪካው እያደገ ሲመጣ ስልጣንም፣ ማንም አይደፍረኝም ባይነትም ፣ በአመራሩ ዘንድ እያደገ መጣ”
ስራ አስኪያጁ አቶ ብርሀኑ በአቶ በረከት፣ በአቶ አዲሱ፣ በአቶ ከበደ፣ በአቶ ጌታቸው፣ በአቶ ታደሰ ካሳና በአቶ ሸጋው በተሰራው ጎጆ ውስጥ አብረው የሚኖሩ ነበሩ።
ግለሰቡ በርካታ ጠርሙስ ቢራዎች ያለአግባብ እንዲወጡ በማድረግ፣ የሙስናውን ጎጆ ሲያደራጁ ከቆዩ በሁዋላ፣ ለእርሳቸው የሚሰጠው ድርሻ እያነሰ መምጣቱን በመቃወም ከሌሎች አመራሮች ጋር መጨቃጨቅ ጀመሩ። አካሄዳቸው ያላማራቸው እነ አቶ በረከት ” ማንም አይነካኝም፣ የመግደል መብት ተሰጥቶኛል” በማለት ሲፎክሩ የነበሩትን ግለሰብ በሙስና ከሰው እስር ቤት ወረወሩዋቸው። ለጊዜውም እፎይታ አገኙ።
በ9ኛው የኢህአዴግ ጉባኤ ላይ የብአዴን ወጣት አመራሮች የሆዳቸውን በሆዳቸው ይዘው፣ የነባር አመራሮችን ” ሙስናን እንዋጋለን” ዲስኩር ፈገግ እያሉ ይሰሙ ነበር።
ህዝቡም አቤታቱን ማሰማቱን ቀጥሎአል፤ ወጣት አመራሮችም ታገሱ ይላሉ።
ባለሀብቱን አቶ ሸጋውን አፈላልገን በማግኘት ” ስለ እነ አቶ ጌታቸው አምባየ..”ልናነጋግሮት ነው ብንላቸው ” ንቀት በተሞላበት ሁኔታ ” ስልካቸውን ዘጉብን።
አቶ ሸጋውም ሆኑ የመንግስት ባለስልጣናት ከዘገባው በሁዋላ ምላሻቸውን የሚሰጡ ከሆነ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆናችንን ለመግለጽ እንወዳለን።
torsdag 4. april 2013
በአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰውን መፈናቀል ኢትዮጵያውያን ማውገዛቸውን ቀጥለዋል
ከ5 እስከ 10 ሺ የሚደርሱ የአማራ ተወላጆች ከቤንሻንጉል ጉሙዝ አካባቢ ተፈናቅለው ወደ መጡበት የትውልድ ቀያቸው እንዲመለሱ መደረጉ ኢትዮጵያውያንን ከጫፍ እስከ ጫፍ ማነጋገሩን ቀጥሏል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን በመወከል በሩዋንዳ በተፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል የፍርድ ሂደት በአቃቢ ህግነት የተሳተፉት ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝና በጉራፈርዳ ወረዳ የተፈጸመው አማርኛ ተናጋሪዎችን የማፈናቀል ድርጊት በዘር ማጥራት ወንጀል በማንኛውም ጊዜ ሊያስጠይቅ እንደሚችል የተለያዩ አለማቀፍ ድንጋጌዎችን በመጥቀስ ለኢሳት መግለጻቸው ይታወሳል። አንድን ዜጋ በአገሩ በክልሉ ታጥሮ እንዲኖር ማስገደድ የዘር ማጥራት ወንጀል መሆኑን የገለጡት ዶ/ር ያእቆብ፣ ኢትዮጵያውያን መረጃዎችን በማሰባሰብ ተባብረው ጉዳዩን ወደ አለማቀፍ ፍርድ ቤት መውሰድ እንደሚኖርባቸው ገልጸው ነበር።
ኢሳት የነጋገራቸው የተለያዩ የሲቪክ ተቋማት እና የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች እንዲሁም ታዋቂ ጋዜጠኞች ድርጊቱን በመኮንን ኢትዮጵያውያን በቃ ሊሉት እንደሚገባ እየመከሩ ነው።
በአገር ውስጥ በመንቀሳቀስ ላይ ካሉት የሲቪክ ተቋማት መካከል የባለራእይ ወጣቶች ማህበር ሊቀመንበር የሆነው ወጣት ሀብታሙ አያሌው ፣ የብሄር ፖለቲካ የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ኢትዮጵያን ሊበታትናት እንደሚችል ገልጾ፣ በኢትዮጵያዊነት መልክ ና ቅርጽ የተፈጠረውን ዜጋ መልሶ በመጎተት ወደ ጎሳ ቋጥኝ ማስገባት በልዩነት ላይ የተመሰረተ አስተዳደር ማራመድ መሆኑን ተናግሯል። ወጣት ሀብታሙ የብሄር ፖለቲካ አገሪቱን ይበታትናታል እየተባለ በምሁራን ሲሰጥ የነበረው የነበረው አስተያየት አሁን ፊት ለፊት እየመጣ በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊነሳ ይገባዋል ብሎአል::
ሌላው አስተያየት ሰጪ ደግሞ እውቁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሲሆን ፣ ተመስገን አማርኛ ተናጋሪዎች ከተለያዩ ክልሎች እንዲወጡ መደረጋቸውን በማስታወስ፣ ” ካራቱሬን የመሳሰሉ ድርጅቶ በኢትዮጵያ ገብተው ሀብትና ንብረት እንዲያፈሩ ሲፈቀድላቸው የኢትዮጵያ ዜጎች ግን ይህን መብት ሊያገኙ አልቻሉም ብሎአል። እየመጣ ያለው አደጋ በአማርኛ ተናጋሪዎች ላይ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ዜጋ ላይ የሚደርስ መሆኑን የገለጸው ጋዜጠኛ ተመስገን፣ ተፈናቃዮች ሰዎች በመሆናቸው ብቻ ፣ “ነግ ለእኔ” ተብሎ ድርጊቱ ሊወገዝ ይገባል ሲል በአጽንኦት ተናግሯል።
ከጉራ ፈርዳ የተፈናቀሉ አማርኛ ተናጋሪዎች ከ1 ሺ ገጸች በላይ ያለው ማስረጃ ለአቶ መለስ ዜናዊ አቅርበው እንደነበር ያስታወሰው ጋዜጠኛ ተመስገን፣ አቶ መለስ ዜናዊ መልስ ሳይሰጧቸው በመሞታቸውን እሳቸውን የተኳቸው ባለስልጣናትም በእጅ አዙር ተመሳሳይ ፖሊሲ እየተገበሩ መሆኑን ገልጿል። ለሁሉም ድርጊት ህወሀት ተጠያቂ ነው የሚለው ጋዜጠኛ ተመስገን፣ የአማራውን ህዝብ እወክላለሁ የሚለው ብአዴንም ከተጠያቂነት እንደማያመልጥ ተናግሯል።
ቀደም ብሎ የተፈጠሩትም ሆነ አሁን እየተፈጠሩ ያሉት ህገወጥ ድርጊቶች በአፋጣኝ እልባት ካልተሰጣቸው አገሪቱ ወደ እርስ በርስ ግጭት መግባቱዋ አይቀርም በማለት ጋዜጠኛ ተመስገን ተናግሯል።
ጋዜጠኛ ዘሪሁን ተስፋየ በፌስ ቡክ ባሰፈረው ጽሁፍ ደግሞ ” ዛሬም ወያኔዎች ቀድሞ ሲያቀነቅኑለት የነበረውን ስሜት እያንጸባረቁ ነው። ትንሽነት አደገኛ ነው፤ በሽታው አጥንትን ሰርስሮ ይገባል። ይህንን ማከም ደግሞ የሁሉም ሕዝብ ድርሻ ቢኾንም፣ “ወያኔ ከሌለ እከሌ የሚባል ቡድን ያጠቃኛል” የሚል ስሜት ይዞ የሚያቀነቅነው እና ለወያኔ ርኩስ ፕሮጀክት ዋነኛ ተዋናይ የኾነው ሕዝብ ከፍተኛውን ሚና መጫወት ይኖርበታል። “እኔ ልሁን ደህና” በሚል ስሜት ዛሬ ነገሩን አቅልሎ ማየት ነገ የሚያስከፍለውን ዋጋ ያከብደዋል። ” ብሎአል።
|
በኢትዮጵያ ውስጥ አንድ የወረዳ አስተዳዳሪ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ግለሰቦችን “በሕገ ወጥ መንገድ ስለገቡ ወደመጡበት መመለስ” የሚችልበት ምንም ሕጋዊ መሠረት የለም። የአባራሪነት እና የተባራሪነት ፖለቲካው የመነጨው ከጭፍን ፖለቲካዊ አመለካከት በመኾኑ ይህ ውሳኔ በኢትዮጵያ ምድር ኢትዮጵያዊን ሕገወጥ እንዲባል አድርጎታል። እንግዲህ አንዳንዶች እንደሚሉት “አማራ” መኾን ዕዳ ነውን? ቤንሻንጉል መኾን በረከት ነውን? ትግሬ መኾን መታደል ነውን? የአንድ ብሔር ተወላጅ መኾን ከሰው ልጅ ሰብአዊ ፍጥረትነት ይልቃልን? የብሔር ፖለቲካ መርዝ ማለቂያ ወደሌለው አስቸጋሪ ፈተና ውስጥ የሚከተን ይህ ዓይነቱ አመለካከት በዜጎች መካከል እጅግ እየዳበረ በመጣ ቁጥር ነው። ይህ አይነቱ አስተሳሰብ ስር እየሰደደ እንዲመጣ ደግሞ መንግሥት ዋናውን ሚና ከተጫወተ አገር ተበላሸ ይባላል። ” በማለት ገልጿል።
ጃዋር ሙሀመድም እንዲሁ ” አሳዛኙ ነገር ገዢዎች በስልጣን ላይ የመቆያ ጊዜያቸውን ለማራዘም ቤተመንግስት ቁጭ ብለው የትኛውንም አይነት የማታለያ ዘዴ ሲጠቀሙ፣ ከአንድ ዶላር በታች በሆነ ገቢ ኑሮአቸውን የሚገፉ ጎስቋሎች ፣ ንጹህ አርሶ አደሮች ግን ወደ ጎን መገፋታቸው ነው። ዜጎች ኑሮ ውድነቱ የተነሳ ለመኖር በሚታትሩበት ወቅት ፣ ዜጎችን ከቤታቸው ማፈናቀል ፣ አገደኛ የሆነ ትምህርት ጥሎ የሚያልፍ፣ ጭቃኔ የተሞላበት ወንጀል በመሆኑ ፣ ሁላችንም የትኛውንም አይነት የፖለቲካ አስተሳሰብ ይኑረን ልናወግዘው ይገባል።” ብሎአል።
ከፖለቲካ ድርጅቶች ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ ” ዜጎች በፈለጉት የሀገሪቱ ምድሮች ያለምንምና ያለማንም ጣልቃ ገብነት የመኖርና ንብረት የማፍራት የዜግነት መብታቸው ሆኖ እያለ፣ በተቀነባበረና በተሰላ ሁኔታ ዜጎችን ለዓመታት ሲኖሩበት ከነበሩበት ቀያቸው የሚናገሩት ቋንቋ ብቻ እንደመመዘኛ አድርጎ እንዲፈናቀሉ ማድረግ ከህግ ውጭ የሚደረግ ብቻ ሳይሆን በዘር ማጥፋት የሚያስጠይቅም ነው ” ብሎአል።
ውድ ተመልካቾቻችን በዚህ ጉዳይ ላይ የተለያዩ ኢትዮጵያውያንን በማናገር የተቀናበረውን ዝግጅት በትኩረት ፕሮግራም በሚቀጥሉት ቀናት የምናቀርብ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።
በአማራው ላይ የዘር ማጥፋት (ጀኖሳይድ) ሲካሄድ፣ ዝም ማለት ለሕሊና የሚከብድ ነው!
Abonner på:
Innlegg (Atom)