በሱዳን፣ ኢትዮጵያ እና ግብጽ መካከል በካርቱም የተካሄደው የአንድ ቀን ስብሰባ ያለውጤት ተጠናቋል። በኢትዮጵያና ግብጽ መካከል ልዩነቶች የተፈጠሩ ሲሆን፣ ልዩነቶችን ለማጥበብ ስለሚወሰደው እርምጃም አልተስማሙም። ብዙ ክብደት ተሰጥቶት የነበረው ስብሰባ በአንድ ቀን መጠናቀቁ በሁለቱ አገራት መካካል ያለው ልዩነት እየሰፋ መሄዱን የሚያሳይ ነው ተብሎአል። ምንም እንኳ ከአንድ ወር በሁዋላ አገራቱ ተመልሰው እንደሚገናኙ ቢገለጽም፣ ግብጽ ዬያዘችው አቋም የኢትዮጵያን መንግስት የሚያስደስት አልሆነም። የኢትዮጵያ መንግስት ግንባታው ቆሞ ጥናት እንዲካሄድ የሚለውን ሀሳብ አልተቀበለውም።
የኢትዮጵያ መንግስት በአገር ውስጥ ለዲፐሎማሲ ከግብጽ በኩል የቀረበ ችግር እንደሌለ ሲገልጽ፣ በሌላ በኩል ግን ግብጽ እያቀረበችው አለው ጥያቄ ከባድ እንደሆነበት ተመልክቷል።
ሁለቱ አገራት ችግሮቻቸውን በውይይት ለመፍታት ከተሳናቸው ወደ ግጭት ሊያመሩ የሚችሉበት እድል ሰፊ መሆኑን ተንታኞች ይናገራሉ።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar