mandag 28. april 2014
ኢትዮጵያ የታሰሩ ጋዜጠኞችና ጸሃፊዎችን እንድትፈታ ሂውማን ራይትስ ወች ጠየቀ
መንግስት ተጨባጭ ማስረጃ እስካላመጣ ድረስ ከ3 ቀናት በፊት ያሰራቸውን 3 ጋዜጠኞች እና 6 ጸሃፊዎችን በአስቸኳይ እንዲፈታ የሰብአዊ መብት ድርጅቱ አሳስቧል፡፡
ኢትዮጵያን የሚጎበኙት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ጆን ኬሪ ፍትሃዊ ባልሆነ ዳኝነት በእስር የሚሰቃዩ ጋዜጠኞች እንዲሁም ያለበቂ ማስረጃ የሚታሰሩት ጋዜጠኞች እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እንዲፈቱ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫና እንዲያሳድሩ ሂውማን ራይትስ ወች ጠይቋል።
የሂውማን ራይትስ ወች የአፍሪካ ዳይሬክተር ሌስሌ ሌፍኮ “የ9ኙ ሰዎች መታሰር መንግስትን የሚተቹ ሁሉ አፋቸውን እንዲዘጉ እንደሚደረጉ ማሳያ ነው” ብለዋል።
ዞን 9 እየተባለ የሚጠራ የፌስ ቡክ አካውንት በመክፈት ጽሁፎችን ሲጽፉ ከነበሩት ወጣቶች መካከል በፈቃዱ ሃይሉ፣ አጥናፍ ብርሃኔ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ ዘላለም ክብረት እና አቤል ዋቤላ ከስራ ቦታቸውና ከመንገድ ላይ ታፍሰው መታሰራቸውን፣ ጋዜጠኛ ተስፋ አለም እና ኤዶም ካሳየም እንዲሁ ፖሊስ ወደ ማእከላዊ እስር ቤት ተወስደው መታሰራቸውን ድርጅቱ ገልጿል። የአዲስ ጉዳይ መጽሄት ዋና አዘጋጅ አስማማው ሃይለ ጊዮርጊስም እንዲሁ ወጣቶቹ በታሰሩ ማግስት መታሰራቸውን በመግለጫው ጠቅሷል።
በእስር ላይ የሚገኙት ወጣቶች ከማንም ጋር እንዳይገናኙ ተደርጎ የታሰሩ በመሆኑ ለጥየቃ የሄዱ ቤተሰቦች ሳያገኙዋቸው ቀርቷል።
ዞን 9 እየተባሉ የሚጠሩ ወጣቶች ከዚህ ቀደም ተደጋጋሚ የሆነ ማስፈራሪያ ሲደርስባቸው ነበር።
ሂውማን ራይትስ ወች የኦባማ አስተዳደር በኢትዮጵያ ስለሚታየው የሰብአዊ መብት ጥሰት ምንም አለማለቱን ወቅሷል።
የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ (ኢጋመ) ባወጣው መግለጫ ደግሞ መድረኩ እስካሁን በሰበሰበዉ መረጃ መሰረት ወጣቶቹን ለእስር የሚያበቃ ምን ም አይነት ማስረጃ ለማግኘት አለመቻሉን ገልጿል።
ለእስር ከመዳረጋቸው በፊት ከመንግስት ሲርስባቸዉ በነበረዉ ህገወጥ ድርጊቶች ምክንያት ለረጅም ጊዜ ስራቸዉን ካቋረጡ በኋላ በቅርቡ ወደ ስራ መመለሳቸዉን ይፋ አድርገው እንደነበር ከድረገጻቸው ላይ ለመረዳት መቻሉን ኢጋመ ጠቅሷል።
የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ መንግስት ታሳሪዎቹን ለማሰር ያበቃዉ ተጨባጭ ማስረጃ ካለ ለህዝብ ይፋ እንዲያደርግ፤ ያ ካልሆነ ግን እስረኞቹን በአስቸኳይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቅ ጥያቄ አቅርቧል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ለገዢው ፓርቲ ቅርበት አለው የሚባለው ዛሚ ኤፍኤም 90.7 ከዞን 9 ጋር በተያያዘ የታሰሩ ጸሃፊዎችና ጋዜጠኞች ላይ የተጀመረው እስር በሌሎችም ላይ እንደሚቀጥል የሚያረጋግጥ ዘገባ አቅርቧል፡፡
ሬዲዮው ከፖሊስ ታማኝ ምንጮቼ አገኘሁት ባለው መረጃ መሠረት ከዞን 9 ጋር በተያያዘ የታሰሩ ብሎገሮችና ጋዜጠኞች በህቡዕ ተደራጅተው መንግስትን በአመጽ ለመጣል ማሴራቸውን፣ እንዲሁም ማናቸውንም ዓይነት ሰላማዊ ሰልፎች እንዲካሄዱና በሰልፎቹ ላይ መንግስትን ለመቃወም ስልጠናዎችን በውጪና በአገር ውስጥ መውሰዳቸውን አትቷል፡፡
እንደዘገባው ከሆነ ጤናን የሚመለከት ሰልፍም ቢሆን እንዴት ወደተቃውሞ መቀየር እንደሚቻል ተጠርጣሪዎቹ ስልጠና መውሰዳቸውን ተናግራል፡፡
ሬዲዮው ከታሰሩት በተጨማሪ በሕጋዊ መንገድ በመመስረት ሒደት ላይ የሚገኘው ኢትዮጽያ የጋዜጠኞች መድረክ (ኢጋመ) በተመሳሳይ መንገድ በውጪ አገር ከሚንቀሳቀሱ ተቁዋማት ጋር ግንኙነት እንዳለው ከፖሊስ መረጃ አግኝቻለሁ ከማለቱም በተጨማሪም በማህበሩ ላይ ፖሊስ ክትትል እያደረገ መሆኑን ገልጿል፡፡ ይህ ሁኔታ በቀጣይ ማህበሩ ላይ ትኩረት መደረጉን እንደሚያሳይ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ጠቁመዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሚያዝያ 17 እና 18 ቀን በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ውለው የነበሩ ሦስት ጋዜጠኞችና ስድስት ጦማርያን በትላንትናው ዕለት እሑድ ሚያዝያ 19 ቀን 2006 ዓ.ም. በሶስት መዝገብ ፖሊስ ፍርድ ቤት አቅርቦአቸው የጊዜ ቀጠሮ እንደጠየቀባቸው ሪፖርተራችን ስቱዲዮ ከመግባታችን በፊት የላከችው ዘገባ ያስረዳል፡፡
ሚያዝያ 19 ቀን 2006 ዓ.ም. በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት፣ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል መርማሪ ፖሊስ ያቀረባቸው በፍቃዱ ኃይሉ፣ ማህሌት ፋንታሁን አቤል ዋበላ በአንድ መዝገብ፤ ዘለዓለም ክብረት፣ ተስፋዓለም ወልደየስና አስማማው ኃይለጊዮርጊስ በሌላ መዝገብ እንዲሁም አጥናፉ ብርሃኔ፣ ናትናኤል ፈለቀና ኤዶም ካሳዬ አንድ ላይ፣ ዘጠኙም ተጠርጣሪዎች ሦስት ሦስት ሆነው ቀርበዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ነን ከሚሉ የውጭ ኃይሎች ጋር በሙሉ ሐሳብና በገንዘብ በመስማማት፣ ሕዝብን የሚያተራምስና አገርና መንግሥትን የሚያፈርስ ዘገባ በኢንተርኔትና በማኅበራዊ ድረ ገጾች ያልሆነ መረጃ ማስተላለፋቸውን ፖሊስ ለፍ/ቤቱ ገልጾአል፡፡ ፖሊስ ምርመራውን ባለመጠናቀቁም የ15 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቢጠይቅም የተፈቀደለት የ10 እና 11 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ነው፡፡ እስካሁን መንግስት በተጠርጣሪዎቹ ጉዳይ በይፋ የሰጠው መግለጫ የለም፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ለገዢው ፓርቲ ቅርበት አለው የሚባለው ዛሚ ኤፍኤም 90.7 ከዞን 9 ጋር በተያያዘ የታሰሩ ጸሃፊዎችና ጋዜጠኞች ላይ የተጀመረው እስር በሌሎችም ላይ እንደሚቀጥል የሚያረጋግጥ ዘገባ አቅርቧል፡፡
ሬዲዮው ከፖሊስ ታማኝ ምንጮቼ አገኘሁት ባለችው መረጃ መሠረት ከዞን 9 ጋር በተያያዘ የታሰሩ ብሎገሮችና ጋዜጠኞች በህቡዕ ተደራጅተው መንግስትን በአመጽ ለመጣል ማሴራቸውን፣ እንዲሁም ማናቸውንም ዓይነት ሰላማዊ ሰልፎች እንዲካሄዱና በሰልፎቹ ላይ መንግስትን ለመቃወም ስልጠናዎችን በውጪና በአገር ውስጥ መውሰዳቸውን አትታለች፡፡
እንደዘገባው ከሆነ ጤናን የሚመለከት ሰልፍም ቢሆን እንዴት ወደተቃውሞ መቀየር እንደሚቻል ተጠርጣሪዎቹ ስልጠና መውሰዳቸውን ተናግራለች፡፡
ሬዲዮው ከታሰሩት በተጨማሪ በሕጋዊ መንገድ በመመስረት ሒደት ላይ የሚገኘው ኢትዮጽያ የጋዜጠኞች መድረክ (ኢጋመ) በተመሳሳይ መንገድ በውጪ አገር ከሚንቀሳቀሱ ተቁዋማት ጋር ግንኙነት እንዳለው ከፖሊስ መረጃ አግኝቻለሁ ከማለቷም በተጨማሪም በማህበሩ ላይ ፖሊስ ክትትል እያደረገ መሆኑን ገልጻለች፡፡ ይህ ሁኔታ በቀጣይ ማህበሩ ላይ ትኩረት መደረጉን እንደሚያሳይ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ጠቁመዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሚያዝያ 17 እና 18 ቀን በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ውለው የነበሩ ሦስት ጋዜጠኞችና ስድስት ጦማርያን በትላንትናው ዕለት እሑድ ሚያዝያ 19 ቀን 2006 ዓ.ም. በሶስት መዝገብ ፖሊስ ፍርድ ቤት አቅርቦአቸው የጊዜ ቀጠሮ እንደጠየቀባቸው ሪፖርተራችን ስቱዲዮ ከመግባታችን በፊት የላከችው ዘገባ ያስረዳል፡፡
ሚያዝያ 19 ቀን 2006 ዓ.ም. በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት፣ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል መርማሪ ፖሊስ ያቀረባቸው በፍቃዱ ኃይሉ፣ ማህሌት ፋንታሁን አቤል ዋበላ በአንድ መዝገብ፤ ዘለዓለም ክብረት፣ ተስፋዓለም ወልደየስና አስማማው ኃይለጊዮርጊስ በሌላ መዝገብ እንዲሁም አጥናፉ ብርሃኔ፣ ናትናኤል ፈለቀና ኤዶም ካሳዬ አንድ ላይ፣ ዘጠኙም ተጠርጣሪዎች ሦስት ሦስት ሆነው ቀርበዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ነን ከሚሉ የውጭ ኃይሎች ጋር በሙሉ ሐሳብና በገንዘብ በመስማማት፣ ሕዝብን የሚያተራምስና አገርና መንግሥትን የሚያፈርስ ዘገባ በኢንተርኔትና በማኅበራዊ ድረ ገጾች ያልሆነ መረጃ ማስተላለፋቸውን ፖሊስ ለፍ/ቤቱ ገልጾአል፡፡ ፖሊስ ምርመራውን ባለመጠናቀቁም የ15 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቢጠይቅም የተፈቀደለት የ10 እና 11 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ነው፡፡ እስካሁን መንግስት በተጠርጣሪዎቹ ጉዳይ በይፋ የሰጠው መግለጫ የለም
Abonner på:
Legg inn kommentarer (Atom)
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar