በአሉ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እየተከበረ መሆኑን የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።
ኢትዮጵያውያን ስልክ በመደወል የመልካም ምኞት መግለጫ መልእክቶችም አስተላልፈዋል ከበአሉ ጋር በተያያዘ የተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች መከናወናቸውን የደረሱን መረጃዎች ያሳያሉ። በበአሉ ዋዜማ ወቅት ከፍተኛ አደጋ የታየው በጋምቤላ ክልል በጎደሬ ዞን በጎሸም ቀበሌ ሲሆን፣ የመዠንገር ብሄረሰብ አባላት 9 ሰዎችን ገድለዋል። ግጭቱ አሁንም ድረስ የቀጠለ በመሆኑ የሟቾች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊሆን ይችላል። ካለፉት 3 ወራት ጀምሮ በአካባቢው በመካሄድ ላይ ባለው ግጭት በርካታ ሰዎች ተገድለዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ የደቡብ የአማራ፣ የጉራጌና የኦሮሞ ተወላጆች አካባቢውን ለቀው ተሰደዋል።
በሌላ ዜና ደግሞ በደቡብ ክልል በሰገን ወረዳ ከ100 ያላነሱ ወጣቶች ተይዘው መታሰራቸው ታውቋል። ወጣቶቹ ህዝቡን ለአመጽ ታነሳሳላችሁ ተብለው መታሰራቸው ታውቋል። ከ3 አመት በፊት 5 ብሄረሰቦች
በአንድ ላይ ሰገን የተባለ ዞን እንዲመሰርቱ የተደረገ ሲሆን፣ ወጣቶቹ ከፍትህና አስተዳደር ጋር በተያያዘ ጥያቄ ማንሳታቸው ለመታሰራቸው ምክንያት መሆኑን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል፡፡
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar