በስዊዲን የሚገኙ ኢትዮጵያኖች ከዚህ በሆላ እንደድሮው በውጪ እየወጡ መዝናናት የለም በማለት አምባሳደሯን እንቁላል በመወርወር ከፍተኛ የሆነ ውርደት እንድተከናነብ አድርገዋል። አብረዋት የነበሩ የወያኔ ጠባቂዎችም ራሳቸውን ከድብድባው ለማምለጥ ሲሉ ጥለዋት ሄደዋል። የስዊድን ፖሊሶች በርካታ የፖሊስ መኪናዎችን በማምጣት ጸጥታውን ለመቆጣጠር የቻሉ ሲሆን ከረጅም እግታ በሆላ በፖሊሶች እርዳታ ከመኪናዋ ወጥታ ለመሄደ ችላለች።
እንቁላል አትጨርሱ ዛሬ የባንዳዎች እና የነነዋይ ውርደት በእንቁላል ቢጫ እናድረጋቸዋለን እና እሶ ላይ ብቻ አትጨርሱ፣ መኪናው የእንቁላል ጌጥ በዛበት የሚል አስቂኝ ክስተቶችም ነበሩበት።
በውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያኖች በተጠናከረ መልኩ የወያኔን ባለስልጣናት በሄዱበት የማዋረድና እጃቸው ደም የተበከለ መሆኑን በተደጋጋሚ እየተነገራቸው ሲሆን በቅርቡ በተመሳሳይ ሬድዋን ሁሴን በዋሽንግተን ዲዲ የደረሰበት ውርደት ይታወሳል።
በአሁኑ ሰአት በርካታ የወያኔ ባለስልጣኖች ወደ ውጪ መጓዝን እንደማይመርጡ የደረሰን ሪፖርት ያመላክታል።
በስዊዲን የኢትዮጵያ አባሳደር ላይ የገማ አሳና እንቁላል እንዳይወረወርባቸው ሲከላከሉ የሚያሳይ ፎቶ
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar