onsdag 15. mai 2013
በባህርዳር 17 ሰዎችን በጥይት አርከፍክፎ በግፍ የገደለው የፌደራል ፖሊስ አባል ከዘር ጋር የተያያዘ ምክንያት የለውም ሲሉ የአማራ ክልል የፖሊስ አዛዥ ተናገሩ
እሁድ ግንቦት4፣ 2005 ዓም ከምሽቱ 2 ሰአት ከ45 ደቂቃ ላይ ፣ የሁለት አመት ህጻንን ጨምሮ 17 ሰዎችን በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 11 ወይም በተለምዶ አባይ ማዶ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በግፍ የገደለው የፌደራል ፖሊስ አባል ማንነት መለየቱን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አስታውቋል።
ኢሳት ትናንት ፖሊሱ የሌላ ብሄር ተወላጅ መሆኑን ጠቅሶ የዘገበ ሲሆን አንዳንድ ወገኖች ይህን በመንተራስ ጉዳዩ ከዘር ጋር ሊያያዝ ይችላል በማለት አስተያየት በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
በዛሬው እለት የገዳይ ወታደር ኮንስታብል ፍቃዱ ናሻ አስከሬን ጨረጨራ እየተባለ በሚጠራው በጣና ሀይቅ እና በአባይ ወንዝ መለያያ አካባቢ በተሰራው ግድብ ውስጥ የተገኘ ሲሆን፣ ገዳዩ ፊቱ አካባቢ በአሳዎች እንደተበላ በስፍራው ነበሩ የአይን እማኞች ገልጸዋል። ወታደሩ እስከነ ሙሉ ዩኒፎርሙ በጠላቂ ዋናተኞች ሊወጣ መቻሉን የአይን እማኞች አክለው ገልጸዋል።
የሆኑት ሙሉጌታ ወርቁ ” ወታደር ፈቃዱ ግድያውን የፈጸመው ከዚህ ቀደም ያፈቅራት የነበረችው ጓደኛው ወ/ት ዘቢደር ከእርሱ ጋር ለመቀጠል ፈቃደኛ ባለመሆኗ በመበሳጨት በቂም በቀል በመነሳሳት ነው” ብለዋል። የግድያው መንስኤ ከዘር ጋር የተያያዘ ነው የሚለውን እንደማይቀበሉት ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።
ባህርዳር ዛሬም በሀዘን ድባብ ውስጥ እንደምትገኝ ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል።
Abonner på:
Legg inn kommentarer (Atom)
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar