onsdag 15. mai 2013

በቻግኒ ከተማ የህዝብን ተቃውሞ ተከትሎ አንድ መስጊድ ታሸገ


በአዊ ዞን በቻግኒ ከተማ መስጊድ አረህማን እየተባለ የሚጠራው ነባር መስጊድ የታሸገው ህዝቡ መንግስት የወከለውን አሰጋጅ አንቀበልም በማለት ተቃውሞ በማሰማቱ ነው። በመስጊዱ መግቢያ ላይ የተለጠፈው ወረቀት ፣ ” ከዛሬ ጀምሮ በዚህ መስጊድ መስገድ በህግ ያስቀጣል” የሚል ይዘት እንዳለው የአይን እማኞች ተናግረዋል።

ነባሩ መስጊድ እንዲታሸግ መደረጉን ተከትሎ ህዝበ ሙስሊሙ መንገድ ላይ መስገድ መጀመሩን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ከዚህ ቀደም 9 ሙስሊሞች ተቃውሞ በማሰማታቸው በስድስት ወራት እስራት መቀጣታቸው ይታወሳል።

መንግስት በሙስሊሙ ማህበረሰብ የሚቀርበውን ተቃውሞ ለማፈን በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ እና መንግስት በመረጣቸው አሰጋጆች ለመስገድ ፈቃደኛ ያልሆኑ ሰዎች የሚሰግዱባቸውን መስኪዶች እያሸገ እንደሚገኝ መዘገባችን ይታወሳል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar