fredag 24. mai 2013
ሰማያዊ ፓርቲ በማንኛውም መልኩ ሰልፉን ለማካሄድ መወሰኑን አስታወቀ
የፓርቲው ሊቀመንበር ኢንጀነር ይልቃል ጌትነት ትናንት ለኢሳት ሬዲዮ እንደገለጹት የፓርቲው አመራሮች የፈቃድ ደብዳቤ ለማስገባት ወደ አዲስ አበባ መዘጋጃ ቤት የሰላማዊ ሰልፍና የህዝባዊ ስብሰባ ማስታወቂያ ቢሮ ቢሄዱም ሃላፊዎቹ ደብዳቤውን ለመቀበል ፈቀደኛ አልሆኑም።
ፓርቲው ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የቢሮ ሀላፊ ደብዳቤ አልቀበልም በማለታቸው የፓርቲው አመራሮች ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የተባሉ ከከንቲባው ጽህፈት ቤት ሀላፊ እሰከ ካቢኔ ጉዳዮች ምክትል ሀላፊ ድረስ ላሉ ሰዎች ለመስጠት ቢሞክሩም ” ደብዳቤ እንዳንቀበል ከበላይ ታዘናል” የሚል መልስ እንዳገኙ ገልጿል።
ከፓርቲው በኩል ሶስት ሰዎች ከማዘጋጃ ቤቱም እንዲሁ ሶስት ሰዎች በተገኙበት ደብዳቤውን ለሰላማዊ ሰልፍና ለህዝባዊ ስብሰባ ማስታወቂያ ቢሮ ሀላፊ ጠረጴዛ ላይ ማስቀመጣቸውን መግለጫው አመልክቷል።
ፓርቲው አክሎም ” ሰልፉን ለማድረግ እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ በህግ በኩል የጎደለ አንድም ቅንጣት ነገር ባለመኖሩ ሰልፉ በታቀደው ቦታና ሰአት የሚካሄድ መሆኑን ” አስታውቋል።
Abonner på:
Legg inn kommentarer (Atom)
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar