mandag 20. mai 2013
ሰበር ዜና..... ፋሲለደስ የተባለች ጀልባ በጣና ሀይቅ የመገልበጥ አደጋ በመድረሱ ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች ህይወት ተቀጠፈ!!
ይችን እና ሌሎች መሰሎቿን ጀልባዎች ፤ጣና ላይ ጥሏቸው የሄደው ጣልያን ነበር።ፋሲለደስ፣ታጠቅ፣ሊማሊሞ፣አንድነት ተብለው ተስመዋል።በአካባቢው ኗዋሪዎች የአሽዋ መርከብ ተብለውም ይጠራሉ።አብዛኛው ስራቸው ከደልጊ ባህርዳር አሸዋ ማጓጓዝ ነው።የጣና ሃይቅ ትራንስፖርት(ናቢጋ ጣና)፣'በመንግስት' የተረሳ ድርጅት በመሆኑ በአዲስ ሊተካቸው አልቻለም።
ይባስ ብሎ ለህዝብ ማጓጓዣነት ይጠቀምባቸዋል (የጨነቀው እርጉዝ ያገባል እንዲሉ)...አማራጭ የሌለው ወገኔ ነብሱን ሽጦ በነዚህ መርከቦች መጠቀም ግድ ይለዋል።
የአገሬ ሰው ከጎርጎራ-ደልጊ-እሰይደብር-ቁንዝላ-ደቅ(ጉረር)-ዘጌ-ባህርዳር በነዚህ ጥርሳቸውን በፈጁ የአሸዋ መርከቦች ሲቀዝፍ ባጅቷል። እስከ ዛሬ ድረስ ይህን ያህል የከፋ አደጋ ደርሶ አያውቅም ነበር፣መንግስት ቢጨክንበትም እሩህሩሁ ጣና እና ጀልባዎቹ ተስማምተው ይወስዱት ይመልሱት ነበር።
ዛሬ ግን አልሆነም። ጣናም በሞገድ ተናጠ ፤ከመርከቦቹ አንዷ የሆነችው ፋሲለደስም ሩጫዋን ጭረሰች እና ሰጠመች። አማራጭ የለሹ ድሃው ወገኔም አለቀ አሉኝ! ነብሱን ሽጦ የተሳፈረው ወገኔ የፈራው ደርሰበት። እህህህ.....ወገኔ መከራህ መከራዬ በዛ! ስቃይህ ስቃዬ አላልቅ አለ!...እህህህ.....
Abonner på:
Legg inn kommentarer (Atom)
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar