torsdag 30. januar 2014

ኢህአዴግ ልማቱን ለመጨረስ ከ40 እስከ 45 አመት ያስፈልገዋል ሲሉ አቶ በረከት ተናገሩ

የጠ/ሚንስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ አማካሪ የሆኑት አቶ በረከት ስምዖን ይህን የተናገሩት ለኢህአዴግ ከፍተኛ ካድሬዎች ነው። ለማንኛውም የመገናኛ ብዙሃን ዝግ በሆነው የካድሬዎች ስብሰባ ላይ ጥናታዊ ወረቀታቸውን ያቀረቡት አቶ በረከት፣ ኢህአዴግ የህዝቡን የነፍሰ ወከፍ ገቢ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ለማድረስ  ቢያንስ ከ40 እስከ 50 ዓመታት እንደሚያስፈልገው ገልጸዋል።
አቶ በረከት የወደፊቱ የህዳሴ መንገድ በሚል ባቀረቡት ጽሁፍ ፣ ግንባሩ የኢትዮጵያ ህዳሴ በስንት ዓመታት ሊጠቃለል ይችላል የሚለውን ከእነኮሪያና ታይዋን ልምድ በመውሰድ መስራቱን ተናግረዋል። አገሮች ከዝቅተኛ ወደ መካከለኛ ከዚያም ወደ ከፍተኛ ገቢ ለመድረስ ከ40 እስከ 50 ዓመታት መውሰዳቸውን ገልጸዋል ።
አቶ በረከት መካከለኛ ገቢ የሚባለው ከገቢ አንጻር ሲሰላ ዝቀተኛው 1000 ዶላር ከፍተኛው ደግሞ 5 ሺ ዶላር መሆኑን ጠቅሰዋል። ባለፈው 10 አመታት የጀመርነውን እድገት ከቀጠልን በሚቀጥሉት 10 አመታት የመካከለኛው ገቢ ዝቀተኛ ጣራ ከሆነው 1000 ዶላር የነፍስ ወከፍ ገቢ ደረጃ ላይ እንደርሳለን የሚሉት አቶ በረከት፣ የመካከለኛ ገቢ ከፍተኛ ጣራ ከሆነው 5 ሺ ዶላር የነፍስ ወከፍ ገቢ ለመድረስ እንደገና ተጨማሪ 15 ወይም 20 አመታት ይወስድብናል ብለዋል;፡
የከፍተኛው ገቢ የመጨረሻው ደረጃ ለሆነው የ10 ሺ ዶላር የነፍስ ወከፍ ገቢ ደረጃ ለመድረስ ሌላ ከ15-20  ተጨማሪ አመታት እንደሚያስፈልግ አቶ በረከት አክለዋል። ይህንን ጊዜ ለማሳጠር ብንፈልግ ልናሳጥረው አንችልም የሚሉት አቶ በረከት ፣ እድገቱ አንዳንዴም ልክ ቱኒዚያ፣ ታይላንዳና ማሌዢያ እንደተቋረጠባቸው ሊቋረጥ ይችላል ብለዋል።
ይህን እደገት ለማስቀጠል ፈተናዎች አሉ ያሉት አቶ በረከት፣ አንደኛው ፈተና  እድገቱን ህብረተሰቡ ሳይሰለች ማስቀጠል ይችላል ወይ  የሚለው ነው ሰሉ ተናግረዋል።
“ነባሩ አመራር  በእድሜ፣ በጤናና በመድከም ከሃላፊነት የሚወጣ በመሆኑ አዲሱ ትውልድ በተመሳሳይ ትኩረትና ፍጥነት እድገቱን ይዞት ሊሄድ ይችላል ወይ?’ የሚለው ጥያቄ ያልተመለሰና መመለስ ያለበት ነው ሲሉ ኢህአዴግ ያጋጠመውን ፈተና ገልጸዋል። ኢሳት የድምጽ መልእክቶችን በመላክ የሚተባበሩንን ከፍተኛ የኢህአዴግ አመራሮች ለማመስገን ይወዳል።

የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ጎንደር ላይ ታሰሩ

ከድንበር ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ እና በሱዳን መንግስታት መካከል ያለው ንግግር ለህዝብ ግልጽ እንዲሆን ለመጠየቅ በመጪው እሁድ በጎንደር ከተማ ለማካሄድ የታቀደውን ሰልፍ ለማስተባበር ወደ ጎንደር ያቀኑት የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ፣ ሌሊት ከተማዋ ደርሰው በማግስቱ የቅስቀሳ ስራ ሲጀምሩ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል።
አመራሮቹ ሲታሰሩ የተመለከተ አንድ ታዛቢ ከኢሳት ጋር ባደረገው አጭር ቆይታ እንደገለጸው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው ወጣት ብርሃኑ ተክለያሬድ፣   ዮናታን ተስፋየ፣ ወይንሸት ሞላ፣ አቤል ኤፍሬምና ጌታነህ ባልቻ ታስረዋል።
ሰማያዊ ፓርቲ በመጪው እሁድ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ የቅስቀሳ ስራ በመስራት ላይ ይገኛል። ሰሜን ጎንደር ፖሊስ አዛዥን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።
ባለፈው አርብ በትግራይ አዲግራት ከተማ ከህዝብ ጋር ለመወያየት ለቅስቀሳ ስራ ሄደው የነበሩት አቶ አስገደ ገብረስላሴ፣ መምህር አብርሃ ደስታና አቶ አምዶም ገብረስላሴ መደብደባቸው ይታወቃል።

tirsdag 28. januar 2014

በሽብርተኝነት ህጉ ውይይት ስም የአዲስ አበባ ህዝብ እየተሸበረ ነው ሲሉ አንዳንድ ተወያዮች ገለጹ

በቅርቡ በአዲስ አበባ ውስጥ ለሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞችና በተዋረድም ከህዝቡ ጋር እተደረገ ባለው የሽብርተኝነት ህግ ውይይት፣  ነዋሪዎች ጥላቸውን እንኳን ማመን እንደሌለባቸው በአሰልጣኞች እየተነገራቸው ሲሆን፣ በስልጠናው ላይ የተካፈሉ አንዳንድ የመንግስት ሰራተኞች፣ ስለሽብረተኝነት ልንማር ሂደን ተሸብረን መጣን ሲሉ ተናግረዋል።
በመንግስት  ከፍተኛ አመራሮች የተዘጋጀው የማሰልጠኛ ሰነድ ኢሳት እጅ የገባ ሲሆን፣ ሰነዱ ህብረተሰቡ ከመንግስት ጎን ቆሞ ልማቱን እንዲጠብቅና እንዲያፋጥን ይጠይቃል። በመስተዳድሩ የሚገኙ  የቢሮ ሃላፊዎች፣ በአዲስ አበባ ከፍተኛ የፖለቲካ አመራር በሆኑት በአቶ ተወልደ ወ/ጻዲቅ መሪነት በሰነዱ ላይ ውይይት አድርገውበታል ። በሰነዱ ላይ የመስተዳድሩ የየደረጃው  አመራሮችና ሲቪል ሰራተኞች እንዲሁም የከተማው  ህዝብ እየተወያዩበት ነው።
እስካሁን ባተካሄደው ውይይት እንደታየው የመንግስት ሰራተኞች በስልጠናው ላይ የሚገኙት የስም ምዝገባ ስላለ  እንጅ በዝግጀቱ አምነውበት አይደለም ይላሉ ተሳታፊዎች።
በውይይቶች ወቅት የመንግስት ባለስልጣኖች ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጡት ከህዝቡ ስለሚጠበቀው ግዴታ መሆኑን የሚናገሩት ተሳታፊዎች ፣ የአገሪቷን ደህንነት ፖሊስና የደህንነት ሃይሉ ጠብቆ ስለማይችል፣ ህዝቡ ከኮሚኒቲ ፖሊስ ጋር በመተባበር ነቅቶ መጠበቅ እንዳለበት ባለስልጣኖች ማሳሰቢያ መስጠታቸውን ተሰታፊዎች ይገልጻሉ።
የፌደራል ፖሊስ ሽብርተኝነትን ለመከላከልና ወንጀለኛን ለመለየት የአፍና የጸጉር ምርመራ ሊያደርግ እንደሚችል፣ ምርምራው እንዲደረግበት የተጠረጠረ ሰው ፈቃደኛ ካልሆነ ተመጣጣኝ ሃይል በፖሊስ ሊወሰድበት እንደሚችል፣  በማንኛውም ጊዜ በድነገት በከተማ ባስና በታክሲ ላይ ፍተሻ ሊደረግ ስለሚችል ህዝቡ መተባበር እንዳለበት የመንግስት ባለስልጣናት ተናግረዋል።
የመንግስት ሰራተኞች  ቦርሳ፣ፌስታልና መሰል ቁሳቁሶችን ቢሮ ውስጥ ጥለው እንዳይሄዱ የተነገራቸው ሲሆን ፣ ቢሮ ውሰጥ የተገኙ ፌስታሎችና ቦርሳዎች ለአደጋ ከማጋለጣቸው በፊት በጥንቃቄ እንዲታዩ ምክር ተሰጥቷል።
ለማወያያነት በቀረበው ሰነድ ላይ በግልጽ እንደሚታየው “ከፍርድ ቤት ፈቃድ በመውሰድ በሽብርተኝነት የተጠረጠረን ሰው የስልክ፣ የሬዲዮ፣ የኢንተርኔት የኤሌክትሮኒክስ፣ የፋክስ፣ የፖስታ ግንኙነት እና የመሳሰሉ ግንኙነቶችን ለመጥለፍ ወይም ለመከታተል፣ ጠለፋውን ለማስፈፀም ወደ ማንኛውም ቤት በሚስጢር የመግባት ወይም ይህንኑ ለመፈጸም የሚያስችሉ መሳሪያዎችን ለማስቀመጥ ወይም ለማንሳት የፌደራል ፖሊስ ስልጣን ተሰጥቶታል።
እንዲሁም “ ማስረጃ ከሚሰበሰብባቸው የተለያዩ ዘዴዎች መካከል አንዱ በሽብርተኝነት ወንጀል ከተጠረጠረው ሠው ላይ ናሙናዎችን መውሰድ እና የህክምና ምርመራ እንዲያደርግ ማድረግ በመሆኑ ፣ ተጠርጣሪውም በምርመራ ሂደት ናሙናውን ለመስጠት ወይም የህክምና ምርመራ ለማድረግ ፍቃደኛ ካልሆነ ፖሊስ ተመጣጣኝ ኃይል ተጠቅሞ ናሙናውን የመውሰድ ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡
ሰነዱ “ የሀይማኖት አክራሪነትና አሸባሪነት ዋናው ምንጭ ድህነትና ተስፋ መቁረጥ ” መሆኑን ከገለጸ በሁዋላ ፣  ”ፍትሀዊ በሆነ መንገድ ተጠቃሚ የሚሆንበትን ፈጣን ልማት ለማረጋገጥ በመንግስት የወጡ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎችና እቅዶች ተግባራዊ በማድረግ ሂደት ሰፊ ርብርብ ማድረግ” ከህብረተሰቡ እንደሚጠበቅ ይገልጻል።
ኢሳት አስተያታቸውን የጠየቃቸው ሰልጣኞች እንዳሉት ውይይቱ ህዝቡን የበለጠ የሚያሽብር ቢሆንም መንግስትም ሽብር ውስጥ መግባቱን ያመለክታል።
በሰነዱ ላይ  ኦነግ፣ ኦብነግ፣ ግንቦት7፣ አልሸባብና አልቃይዳ አሸባሪ ድርጅቶች ተብለዋል

lørdag 25. januar 2014

የአራና አመራር አባላት በሕወሃት ካድሬዎች በአዲግራት ተደበደቡ


ወጣት አብርሃ ደሳትን ጨምሮ በርካታ የአራና አመራር አባላት በሕወሃት ካድሬዎችን በአዲግራት እንደተደበደቡ በስፋት ኡእይተዘገበ ነዉ። አራና፣ አዲግራት በሚያደርጋቸው ስብሰባ ሕዝቡ እንዲሳተፍ በከተማዋ እየተዘዋወሩ ሲቀሰቀሱ ነዉ ተይዘው የተደበደቡት። ከአቶ አብርሃ በተጨማሪ፣ አቶ አሰግዴ ገብረስላሴ፣ አቶ አምዶም ገብረስላሴ ይገኙበታል። የተደበደቡት የአመራር አባላት ፣ ወደ ፖሊስ ተወስደዉ ፣ ለአራት ሰዓታት ታስረዉ፣ ስብሰባዉን እንዲሰርዙ ማስጠንቀቂያ ተሰቷቸው ተመልሰዋል። የደረሰባቸው ድብደባ በጣም የከፋ በመሆኑ አቶ አምዶም እና አስቶ አሰገዴ ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።
የአዲግራትን ስብሰባ በተመለከተ፣ ከመደብደቡ በፊት በአብርሃ ደስታ የቀረበዉን ጽሁፍ እንደሚከተለው አቅርበናል ፡
የዓረና-ዓጋመ የእሁድ ስብሰባ – አብርሃ ደስታ
=====================
ዓረና መድረክ ከዓጋመ (ዓዲግራት) ህዝብ ጋር በፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ለመወያየት ለእሁድ ጥር 18, 2006 ዓም በዓዲግራት ህዝባዊ አዳራሽ (ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ) ቀጠሮ መያዙ ይታወቃል። ዓረና ፓርቲ ለተሰብሳቢው ህዝብ አማራጭ ፖሊሲው ያስተዋውቃል፣ ፖለቲካዊ ትምህርት ይሰጣል፣ ያደራጃል፣ መረጃ ይለዋወጣል። የዓረና ዋነኛ ዓላማ ህዝብ ከጭቆናና ባርነት ለማላቀቅ ማስተማር ነው።
ህዝብ ካሁኖቹ ጨቋኞች እንዲሁም ለወደፊቱ ሊመጡ ከሚችሉ ጨቋኞች ነፃ እንዲወጣ ለማድረግ ፖለቲካ (ስለ መብትና ነፃነት) እናስተምራለን። ምክንያቱም አንድ ህዝብ (ወይም ብዙ ህዝቦች) ከጭቆና ለማላቀቅ ህዝብ መሳርያ ማስታጠቅ አለብን። የፀረ ጭቆና ሚሳኤል ፖለቲካዊ ትምህርት ነው። የፖለቲካ ትምህርት በመስጠት የህዝብ የፖለቲካ ንቃተህሊናው ከፍ እንዲል ማድረግ ይቻላል። ህዝብ የፖለቲካ ንቃተህሊናው ካዳበረ ለማንም ጨቋኝ ስርዓት አሜን ብሎ አይገዛም። መብቱ ማስከበር ይችላል። ነፃነቱን አሳልፎ አይሰጥም። ስለዚህ ፖለቲካዊ ትምህርት ፀረ ጭቆና ሚሳኤል ነው። ህዝብ ራሱ ከጨቋኞች ነፃ ለማውጣትና ለመከላከል ከፈለገ (አንድ) ፖለቲካ ማወቅ አለበት፣ (ሁለት) መደራጀት አለበት። ወደ ዓዲግራትና ሌሎች አከባቢዎች የምንቀሳቀሰውም ይህንን ፀረ ጭቆና ሚሳኤል ለማስታጠቅና ለማደራጀት ነው።
ህወሓቶች ግን ይህን ዓላማ እንዳይሳካ ጥረት ማድረጋቸው አይቀርም። ምክንያቱም ህዝብ ፀረ ጭቆና ሚሳኤል ከታጠቀ ለህወሓቶች አሜን ብሎ የሚገዛ አይሆንም። መብቱ ይጠይቃል፤ ነፃነቱ ይፈልጋል። ስለዚህ ህወሓቶች ህዝብ ይህንን ፀረ ጭቆና ሚሳኤል እንዲታጠቅ አይፈልጉም። በዚህ መሰረት ህዝብ ዓረና በጠራው የህዝብ ስብሰባ እንዳይሳተፍ የተለያዩ ዕንቅፋቶች መፍጠራቸው አይቀርም። ህዝቡ በስብሰባ እንዳይሳተፍ ማስፈራራታቸው አይቀርም። ምክንያቱም ህወሓቶች የህዝብን ማወቅ ያስፈራቸዋል። ምክንያቱም የህዝብ ማወቅ ለስልጣናቸው ስጋት ነው። ህዝብ አሜን ብሎ የሚገዛ እስካላወቀ ድረስ ብቻ ነው። ስለዚህ የህወሓቶች ስትራተጂ ህዝብ ወደ ስብሰባው እንዳይገባና እንዳያውቅ መከልከል ነው የሚሆነው።
የህወሓቶች ዕንቅፋት ሳይበግረን እንገባበታለን። ምክንያቱም የህዝብን የማሳወቅ ዓላማ አንግበናል። የኛ ዓላማ ህዝብ ስለ ፖለቲካዊ መብቱ ግንዛቤ ኖረት የራሱ ዕድል በራሱ እንዲወስን ማስቻል ነው። ለዚሁ ዓላማ ሟቾች ነን። ህወሓቶችም ለስልጣናቸው ሟቾች ናቸው። የህወሓት ሃይማኖት ስልጣን ነው። ስለዚህ ህወሓት ለስልጣኑ መስዋእት ይከፍላል። ለስልጣኑ ይሞታል። እኛም ለዓላማችን እንሞታለን። ሁለታችን ለተለያየ ዓላማ እንሞታለን፤ እንፎካከራለን። በመጨረሻም ሁላችን ፖለቲከኞች ሞተን የመጨረሻ ድሉ የህዝብ ይሆናል። ህዝብ ያሸንፋል።

fredag 24. januar 2014

በይርጋጨፌ መምህራን ለሁለተኛ ጊዜ የስራ ማቆም አድማ አደረጉ


ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በሚል ያለፍላጎታቸው ደሞዛቸው የተቆረጠባቸው የይርጋ ጨፌ ሁለተኛ ደረጃ መምራህራን ከወር በፊት የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ተከትሎ ፣ የተቆረጠባቸው ደምዞ ተመልሶ እንደሚሰጣቸው ቃል ተገብቶላቸው የነበረ ቢሆንም፣ የወረዳው አስተዳዳሪ ገንዘቡ በዝግ አካውንት የገባ በመሆኑ፣ ገንዘብ ለመክፈል አንችልም በሚል ምላሽ መስጠታቸውን ተከትሎ መምህራኑ ከትናንት ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ አድረገዋል። አድማው ዛሬም የቀጠለ ሲሆን አስተዳደሩ ከመምህራኑ ጋር ለመነጋገር ስብሰባ ጠርተዋል። ይህን ዘገባ እስካጠናከርንብ ጊዜ ድረስ የስብሰባው ውጤት ምን እንደሆን ለማወቅ አልተቻለም።
መምህራኑ የትምህርት ጊዜውን አጠናቀው ፈተና ለመስጠት ዝግጁ በሚሆኑበት ወቅት የጀመሩት የስራ ማቆም አድማ መስተዳድሩን ማስደንገጡ ታውቋል። አንዳንድ መምህራን ስራ እንዲጀምሩ ለማባበል ባለስልጣናቱ እየተራወጡ ቢሆንም፣ መምህራኑ ግን አሻፈረን ብለዋል። ደመዞቻው እስከ ሳምንቱ መጨረሻ የማይከፈላቸው ከሆነም ሰኞ አድማውን እንደሚቀጥሉበት ገልጸዋል።
ተመሳሳይ የስራ ማቅም አድማ እድርገው የነበሩ የዲላ መምህራን የተቆረጠባቸው ደሞዝ ተመልሶ እንዲሰጣቸው በመደረጉ ስራ ለመጀመር ችለዋል። በዚህ የተበረታቱት የይርጋ ጨፌ ሁለተኛ ደረጃ መምህራን እንደ ዲላ ጓደኞቻችን ያለፈቃዳችን የተቆረጠው ደሞዝ ይመለስልን በማለት ያለፈውን አንድ ወር በስራ ላይ ሆነው ሲጠይቁ ቆይተዋል። በጉዳዩ ዙሪያ የወረዳውን ባለስልጣናት ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

ለወራት ተቋርጦ የነበረው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ተጀመረ

በዛሬው የሰደቃ እና ዱአ መርሀ ግብር በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የሚገኙ ሙስሊሞች በእስር ላይ የሚገኙ የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላትን አስበው ውለዋል። እጆቻቸውን ወደ ላይ በማንሳትም ለፈጣሪያቸው ተመጽኖ አቅርበዋል።
በአዲስ አበባ በታላቁ አንዋር መስጊድ በመቶሺዎች የሚቆጠር ህዝብ ተገኝቶ ድዋ አድርጓል። መንግስት የሙስሊሙን እንቅስቃሴ ተቆጣጥሬዋለሁ በማለት መግለጫዎችን ሲሰጥ ቆይቷል። የተለያዩ ፊልሞችን በመስራትም የሙስሊሙን ተቃውሞ ከሽብርተንነት ጋር ለማያያዝ ሙከራ እያደረገ ነው። የዛሬው ተቃውሞ በመንግስት ሊመቀርበው የቅስቀሳ ፊልሞችና በ ቃሊቲ የሚገኙት አስተባባሪዎች ሙስሊሙ ትግሉን እንዲቀጥል ላቀረቡት ጥሪ የተሰጠ ምላሽ ይመስላል።
በሌላ ዜና ደግሞ ከሙስሊሙ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ለእስር የተዳረገው ጋዜጠኛ የሱፍ ጌታቸው በቂልጦ ማረሚያ ቤት ስቃይ እየደረሰበት ነው።
በቂልንጦ በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ የሱፍ ጌታቸው በዞን 2 ውስጥ በተነሳ ፀብ ምክኒያት ሶላት እንዳይሰግዱ መከልከሉ የታወቀ ሲሆን በሰንሰለት ታስሮም ተደብድቧል። ለጋዜጠኛው ቅርብ የሆኑ ምንጮች እንደገለጹት ድብደባው የተፈጸመበት ለምን ብሎ ጥያቄ ስላነሳ ነው። በክፍሉ ውስጥ በቡድን ለተነሳው ጸብ መንስኤ ነህ በሚል ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶታል። በግልም ሆነ በቡድን የኢሻ የመግሪብ የሱብሂ ሶላት በክፍሉም ውስጥ እንዳይሰግድ እገዳ ተጥሎበታል።

torsdag 23. januar 2014

የዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ከፓርቲ ፖለቲካ መራቅ

የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በእንግሊዝኛው ምህጻሩ UDJ ሊቀመንበርነታቸውን መልቀቃቸውን አስታወቁ። ሊቀመንበርነታቸውን ብቻም ሳይሆን ከUDJ አባልነትም የተሰናበቱት ዶ/ር ነጋሶ ከዚህ በኃላ በማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ አልሳተፍም ብለዋል።
Äthiopien Partei UDJ
ይህ ማለት ግን ከኣገሪቱ ፖለቲካ ጨርሶ መራቅ ኣለመሆኑንም ኣክለው ኣስታውቐል።
ዶ/ር ነጋሶ ከዚህ ውሳኔ የደረሱት የእድሜ ጫናን ጨምሮ በጤንነታቸው ምክንያትና በተለይም ደግሞ በፓርቲያቸው ውስጥ በተፈጠሩ ፖለቲካዊ ልዩነቶችም ጭምር መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
ዶ/ር ነጋሶ ከኣንድነት ፓርቲ ብቻም ሳይሆን ከዚህ በኃላ በማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ እንደማይሳተፉም ነው የገለጹት።
አንደኛው ምክንያት የእድሜ ጫና ሲሆን የጤንነታቸው ሁኔታም እንደ ምክንያት ተጠቅሷል። ይህ ብቻም ሳይሆን ግን ዶ/ር ነጋሶ እንደሚሉት በእርሳቸው እና በተቀሩት የኣንድነት ፓርቲ ኣመራሮች መካከልም ልዩነቶች ተፈጥሯል።
Bildergalerie Demonstration Oppositionspartei UDJ in Äthiopien
ቀደም ባሉት ዓመታት የኦሮሞ ነጻነት ግንባርን ጨምሮ በኦሮሞ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዲድ) ውስጥም ከፍተኛ የዓመራር አከል የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በቡድን መብቶች መከበር ላይ የማይደራደሩ ፖለቲከኛ መሆናቸው ሲታወቅ ህብረ ብሔራዊ ከሆነው የኣንድነት ፓርቲ ኣመራር አባላት ጋር ያልተጣጣሙበት ሌላኛው ምክንያት በግለሰብ መብት እና በቡድን መብት መካከል ባለው ኣንድነት፣ ልዩነትና ቅደም ተከተል ላይ ነው የሚሉ ወገኖችም ኣሉ።
ዋናው ምክንያት ግን ዶ/ር ነጋሶ እንደሚሉት ከመድረክ ጋር ሊኖር በሚገባው ግንኙነት ላይ ነው። የኣንደነት ኣመራሮች ከዚህ በኃላ ውህደት ካልሆነ በግንባርነት ከማንኛውም ፓርቲ ጋር ላለመቀናጀት አቋም ሲይዙ ዶ/ር ነጋሶ ግን በዚህ ኣይስማሙም።
ምንም እንኳን ምርጫ በተቃረበበት ወቅት ቢሆንም የእኔ መገለል በፓርቲው ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ያንን ያህል የጎላ ኣይመስለኝም የሚሉት ዶ/ር ነጋሶ ከፓርቲ ፖለቲካ ቢለዩም ታዲያ ከኣገሪቱ ፖለቲካ ጨርሶ እንደማይርቁ ግን ኣረጋግጧል።
Äthiopien Partei UDJ
ከ1960 ዎቹ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ ጀምሮ በኣውሮፓ የኦሮሞ ተማሮዎች ማህበር ኣመራር አካል የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ በጀርመን ኣገር የኦሮሞ ነጻነት ግምባር ከፍተኛ ዓመራርም የነበሩ ሲሆን ከ1983 ዓም ጀምሮ ግን ወደ ኣገር ቤት ተመልሰው የኦሮሞ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዲድን) መቀላቀላቸው ይታወቃል።
ኦህዲድን በመወከል ከካቢኔ ሚኒስትርነት እስከ ር/ብሔርነት የደረሱት ዶ/ር ነጋሶ በገዢው ፓርቲ ውስጥ ተፈጥሮ በነረው ፖለቲካዊ ቀውስ ከጠ/ሚ መለስ ጋር ቅራኔ ውስጥ በመግባታቸው ሰኔ 15 ቀን 1993 ዓም ያውም በድፍረት ተናግረው ኦህዲድንም ሆነ ኢህኣዲግን ለቀው በመውጣት ጭምር ይታወቃሉ።
ከዚያ ወዲህ በኢንጅነር ግዛቸው ተተክተው ሲመሩ የቆዩትን ኣንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲንም ኣሁን ሲለቁ እንደ ኢህኣዲግ እያወገዙ ሳይሆን ግን መልካሙን ሁሉ በመመኘት መሰናበታቸውን ኣውጀዋል። ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ።

በመንግስት ተቋማት ላይ ሙስና መስፋፋቱ ተነገረ

ጸረ ሙስና ኮሚሽን ከለጋሽ አገሮች ባገኘው ድጋፍ ተመስርቶ የውጭ ባለሀብቶችን በማሳተፍ ባስደረገው ጥናት የመንግስት ግዢዎችና ኮንትራቶች ግልጽነት የጎደላቸው መሆናቸውን አረጋግጧል። የውጭ ባለሀብቶች አራት አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ሙሰኞች ብለው እንደፈረጁዋቸው ሪፖርተር ዘግቧል።
71 በመቶ የሚሆኑ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ውስጥ ቢዝነስ ለማቀላጠፍ አስቸጋሪ ነው ይላሉ። ባለሀብቶቹ በዋናነት ያነሱትም ሙስና ተስፋፍቷል የሚል ነው። ውስብስብ የሆነው የግዢ ሂደትም ችግር መፍጠሩን ይናገራሉ።
ከ67 በመቶ በላይ የውጭ አገር ባለሀብቶች ጉዳያቸውን ለማስፈጸም ለመንግስት ባለስልጣናት እና ሰራተኞች ጉቦ እንደሚሰጡ ገልጸዋል። የተወሰኑ ባለሀብቶች ጉቦ ከመስጠት ሌላ አማራጭ በማጣታቸው ጉቦ እንደሚሰጡ ተናግረዋል።
ጉምሩክ፣ ትራንስፖርት፣ የመሬት አስተዳደርና መብራት ሃይል ከፍተኛ ጉቦ የሚበላባቸው መስሪያ ቤቶች ናቸው ተብሎአል።

tirsdag 21. januar 2014

ከሱዳን ጋር የሚደረገው የድንበር ውዝግብ የሞራልና የሶሻል ጥያቄ እንጅ የህግ ድጋፍ የለውም ሲሉ አንድ የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ተናገሩ

ባለስልጣኑ ይህን የተናገሩት የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናትና የደህንነት ሰራተኞች በተገኙበት በተደረገው ግምገማና ውይይት ላይ ነው።
በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ያለውን ድንበር የማካለል እንቅስቃሴ ከ1965 ዓም ጀምሮ በጊዜው የውጭ ጉዳይ ሚ/ር በነበሩት ዶ/ር ምናሴ ሃይሌና በሱዳኑ አቻቸው ጃፋር ኤሊ ሜሪ መካከል የተጀመረ እና እስካሁኑም የዘለቀ መሆኑን ባለስልጣኑ አውስተዋል።
ሱዳኖች “ኢትዮጵያውያን የጉዊን መስመር እየተባለ የሚጠራውን ቦታ አልፈዋል” በሚል  ባቀረቡት አቤቱታ ላይ ተመሰርቶ ኮሚቴ መቋቋሙን ያወሱት ባለስልጣኑ፣ “ይሁን እንጅ ኮሚቴው ምንም አይነት የድንበር ማካለል ሳያደርግ እስከዛሬ ቆይቷል ።”
“አሁን በሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል የሚደረገውን ውይይት የምትገዛው ደብዳቤ ሁለቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተለዋወጡት ደብዳቤ መሆኑን  ባለስልጣኑ ጠቅሰው ፣ ኮሚቴው በጊዜው ችግሩን በሰላም ለመፍታት የመፍትሄ ሃሳቦችን አቅርቦ እንደነበርም አክለዋል።
“ሱዳኖች ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያን መሬት ለመውሰድ አቅም አልነበራቸውም ” የሚሉት ባለስልጣኑ ፣ በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1995/96 የግብጹን መሪ አዲስ አበባ ላይ ለመግደል የተደረገውን ሙከራ ተከትሎ የኢትዮጵያ ጦር አካባቢውን ከተቆጣጠረው በሁዋላ የ ትግራይና የአማራ ክልሎች ለኢንቨስተሮች በመቶ ሺዎች የሚቆጠር የሱዳን  መሬት  መስጠታቸውን ገልጸዋል። ሱዳኖች ቀደም ሲል ጀምሮ ግዛታችንን መልሱ የሚል ጥያቄ ሲያቀርቡ ቢቆዩም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጥያቄያቸው እየገፋ ምጣቱን አብራርተዋል። 1965 ዓም ጀምሮ መሬት የሚባል ለሱዳን አለመሰጠቱትነ አጠንክረው የተናገሩት ባለስልጣኑ፣ በቅርቡ ግን የኢትዮጵያ መንግስት ልኡካን ሱዳንን በጎበኙበት ወቅት ሱዳኖች ያቋቋሙት ኮሚቴ አዲስ ሃሳብ ይዞ መቅረቡን ገልጸዋል።  አዲሱም ሀሳብ ” መሬቱን እንደያዛችሁት ቆዩ፣ የዜጎቻችሁን መብቶች እናስጠብቃለን፣ ነገር ግን ቢያንስ በንደፈ ሃሳብ ደረጃ መሬቱ የእኛ መሆኑን የሚያሳየውን ካርታ ተቀብላችሁ አረጋግጡልን ” የሚል መሆኑን ባለስልጣኑ አስረድተዋል
“በረኻት የሚባል የትግራይ ከተማ ላይ ሆናችሁ ሞባይላችሁን ብታወጡ የሚያሳያችሁ ሱዳንን ነው፣ እንዲሁም አርማጭሆ ላይ ሆናችሁ ሞባይሎቻችሁን ብታዩ ያላችሁበት ኢትዮጵያ የሚባለው ቦታ ሱዳን ነው ” የሚሉት ባለስልጣኑ፣ “የፈለገውን ፖለቲከኛ መሸወድ ይቻላል፣ ሳይንሱን ግን መሸወድ አይቻልም” በማለት ገልጸዋል
የአርማጭሆ መሬት ለሱዳን ተሰጠ እየተባለ የሚወራው ውሸት ነው ያሉት ባለስልጣኑ ፣  “አንዳንድ ጊዜ የሱዳን ፖሊስ ድፍረቱ ሲኖረው እየገባ ግጭት ይፈጥራል፣ የኛ ሚሊሺያዎችም የሚሰንፉ አይደሉም ፣ እንዲያውም የእኛ ሚሊሺያዎች የሱዳንን ወታደሮች እንደ ወታደር አይቆጥሩዋቸውም” በማለት በሱዳንና በኢትዮጵያ ድንበር ፖሊሶች መካከል ያለውን ልዩነት ተናግረዋል።
“አይናችን የሚያየውን ሁሉ እንይዛለን ማለት አይደለም” ያሉት ባለስጣኑ፣ በእርግጥ እንያዝ ካልን ካርቱምንም መያዝ እንችላለን ሲሉ የሱዳንን የመከላከያ ብቃት አጣጥለዋል።
አቶ መለስ በነበሩበት ጊዜ በሱዳኖች በኩል ለቀረበው ሃሳብ መልስ እንዲሰጥ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ኮሚቴ በሀሳቦች ልዩነት የተነሳ እስካሁን መልስ መስጠት አለመቻሉንም ባለስልጣኑ ገልጸዋል።  አንዳንዱ የኮሚቴ አባል “ከአሁን በሁዋላ ሰዎቻችን ተነሱ ቢባሉስ እንዴት እሽ ብለው ይነሳሉ” የሚል ሀሳብ ያቀርባል ብለዋል።
“ጥያቄችን የሞራል እና የሶሻል እንጅ  የህግ ድጋፍ የለውም” የሚሉት ባለስልጣኑ፣ እርሳቸው አንዱ የኮሚቴው አባል ቢሆኑም መልስ ለመስጠት እንኳን እንደተቸገሩ ተናግረዋል።
“በ1965 በሞፈር ዘመት መሬት የያዙ አርሶአደሮች ከአርባ አመት በሁዋላ የያዛችሁት መሬት አገራችሁ አይደለም ሲባሉ ቢቃወሙ የሚገርም አይሆንም” የሚሉት ከፍተኛው ባለስልጣኑ፣ “የህግ ክርክሮች ቢነሱ የማንኮራባቸው ጉዳዮች ቢኖሩም ቅሉ እስካሁን ግን የድንበር ማካለል ስራ አልተጀመረም  ።
ሱዳን ትሪቢዩን የተባለው ጋዜጣ በፈረንጆች አቆጣጠር በ2007 ሰፊ መሬት ከኢትዮጵያ  ለሱዳን መሰጠቱን የአካባቢውን አስተዳዳሪ ጠቅሶ መዘገቡ ይታወሳል።

የደህንነት ሰራተኞች ሃላፊነታችን ለአገር ወይስ ለፖለቲካ ስርአቱ ነው የሚል ጥያቄ አነሱ


መንግስት በመረጃዎች አያያዝ ዝርክርክነት ፣ በሳይበር በሚደረጉ ስለላዎች እና ከውስጥ ባሉ የመንግስት አካላት እየሾለኩ በሚወጡ መረጃዎች ህልውናየ አደጋ ላይ ወድቋል በማለት ግመገማ ማድረጉን ተከትሎ  ”የደህንነት ሰራተኞች ሃላፊነታችን ለማን ነው?” የሚል ጥያቄ ማንሳታቸውን  ከደህንነት መስሪያ ቤት ለኢሳት የደረሰው በድምጽ የተደገፈ መረጃ አመለከተ። በስብሰባው ላይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና የመንግስት ሹሞችም ተገኝተው ነበር።
ጥያቄውን ያነሱት በፌደራል ስር የሚገኙ የደህንነት ስራተኞች እና ቀደም ብሎ በአቶ መለስ ዜናዊ ዘመን በትግራይ ውስጥ በመቀሌ ዩኒቨርስቲ ሽፋን የተቋቋመው ኤም አይ ቲ እየተባለ በሚጠራው ከመቀሌ ከተማ 9 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በተገነባው ተቋም ውስጥ ተመርቀው የወጡት የደህንነት ሰራተኞች ናቸው።
የደህንነት ሰራተኞቹ “የእኛ ሃለፊነት የአገር ደህንነትን ማስጠበቅ ነው የፖለቲካ ስርአቱን ?” በሚል  ጥያቄ ያነሱ ሲሆን፣ አንድ  የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን  ” የፖለቲካ ስራ የማይሰራ ደህንነት የለም፣ የደህንነት ስራ ሲጀመር ስርአት የማቆየት ስራ ነው፤ ስርአቱን የምናቆይበት ደግሞ ፕሮፌሽናል ነው፣ በስርአቱ ላይ እምነት ማሳደር የሚጠይቅ ተግባር ነው፣ የግንቦት7ትን አስተሳሰብ የሚያቀነቅንና ስርአቱ በጉልበት መፍረስ አለበት ብሎ የሚያስብ ሰው፣ የተስፋየ ወልደ ስላሴ አይነት የደህንነት ብቃት አለው ቢባል፣ ሞሳድ 20 አመታት አሰልጥኖታል ቢባል ስርአቱን ከማፍረስ ውጭ ደህንነቱን ሊያስጠብቅ አይችልም” ፣ ስለዚህ የደህንነት ስራ ለሚሰሩ ወገኖች የፖለቲካ ወገንተኝነታቸው ወሳኝ ነው የሚል መልስ ሰጥተዋል ።
“የደህንነት ተቋሙ ፣ ሰራዊቱና ሚዲያው በተቃዋሚዎች ዘንድ መቼውንም ቢሆን ገለልተኛ ተደርጎ አይቆጠርም” ያሉት እኝህ ከፍተኛ ባለስልጣን ፣ ገለልተኛ ማድረግ የሚባል አስተሳሰብ ያለው ካለ እንደዛ ሊሆን አይችልም፣ ሊሆን የሚችለው የተቃዋሚዎችን ሰዎች ደህንነት ውስጥ ማስገባት ነው ብለዋል። ” በተለይም በተቋም ደረጃ ፤በምህጻረ ቃል ኢንሳ እየተባለ የሚጠራው የመረጃ ደህንነት መስሪያ ቤት፤ የዜግነት እና ኤምግሬሺን ፤የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤በጀኔራል ሳሞራ የኑስ የሚመራው የመከላከያ ደህንነት ፤የአስተዳደር እና ፀጥታ ፤ የፌደራል ፖሊስ ፤ የፀረ ሽብር ግብረ ሃይል በእዝ ሰንሰለት በሚፈጠር ልዩነት እርስ በርስ እየተወዛገቡ ሲሆን፣ ተቋሞቹን በትክክል የሚመሩትን አካላት  ለመለየት አስቸጋሪ ሆኖ መገኘቱና እርስ በርስ በሚፈጥሩት  እሰጥ አገባ  አንዱ አንዱ የሚሰራውን የማጠፋፋት እርምጃ እየወሰዱ መሆኑ በግምገማው ላይ ተነስቷል፡፡
የመንግስት ሚስጥሮች ለሶስተኛ ወገኖች ተላልፈው እየተሰጡ በመሆኑ ሚስጢሮችን  መደበቅ የማይቻልበት ደረጃ ላይ ተደርሷል ሲሉ አንዳንድ ባለስልጣኖች አስተያየቶችን ሰጥተዋል።
ለተነሱት አስተያየቶች መልስ የሰጡት ባለስልጣኑ፣ ኢንሳ የተቋቋመውም ይህን ለመስራት መሆኑን  ገልጸው፣ “አገሮች ሙሉ በሙሉ ከሳይበር ስለላ ነጻ ባለመሆናቸው አቶ ሃይለማርያምም ነጻ ናቸው ብየ አላስብም” ብለዋል። “አሜሪካኖች የምንናገረውን ሁሉ ከፈለጉ ይሰሙታል” የሚሉት እኝሁ ባለስልጣን፣ “እኛም የአቅማችንን ያክል አሜሪካኖች የሚናገሩትን ለማዳመጥ እንሞክራለን” ብለዋል። የሳይበር ስለላ ለማካሄድ ጥሩ ጅምሮች ቢኖሩም፣ ያን ያክል የምንኩራራበት ግን አይደለም በማለት ኢነሳ ያለበትን ደረጃ አመላክተዋል
ከኦሮሚያና ከደቡብ የመጡ የደህንነት ሹሞች ደግሞ “በመከላከያ የደህንነት ተቋሞች ውስጥ የአንድ ብሄር የበላይነት ጎልቶ ይታያል” በሚል ቅሬታ ያነሱ ሲሆን ፣ ባለስልጣኑም “የሰራዊት ማመጣጠን ስራ በረጅም ጊዜ የሚሰራ ስራ  ነው ” በማለት ለመመለስ ሞክረዋል።
” ትግሉን መርተው እዚህ ድረስ የመጡ ሰዎችና በመከላከያ ውስጥ ያለውን የመኮንኖች ቦታ የያዙት ከአንድ አካባቢ የመጡ መሆናቸው ግልጽ ነው የሚሉት ባለስልጣኑ፣ ያም ሆኖ ከትግራይ የመጡ በርካታ ጄኔራሎች ጡረታ እንዲወጡ ቢደረግም ሂደቱ ግን ረጅም ጊዜ የሚወሰድ ነው ሲሉ አክለዋል።
“የብሄር ተዋጽኦ ብቻ የአንድን ሰራዊት ጠንካራና ደካማ ጎን መገለጫ ተደርጎ መወሰድ ካለበት አደጋ አለው ” ያሉት ባለስልጣኑ፣ የአንድ ብሄር የበላይነት አለ ተብሎ በአጭር ጊዜ ለማመጣጠን ብቻ በአንድ አዳር ሁሉንም ነገር መቀየር እንደማይቻል መንግስት ያምናል ሲሉ ተናግረዋል
አቶ መለስ ዜናዊ በውጭ ሃይሎች ተገድለዋል ይባላልና በምን እንደሞቱ በትክክል ይነገረን በሚል ባለስልጣናት ላነሱት ጥያቄም የደህንነት ባለስልጣኑ፣ “አቶ መለስ በውጭ ሃይሎች ተገድለዋል የሚል ትክክለኛ ማስረጃ የለም በማለት መመለስ የጀመሩት ባለስልጣኑ፣ እርሳቸው የሞቱት በስራ ብዛት ተዳክመው እና ህክምናውን መቋቋም ባለመቻላቸው ነው ሲሉ ደምድመዋል።
በተያያዘ ዜናም የሃገሪቱን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል ከኢሳት ጋር በመሆን እየሰራችሁ ነው፣ ለኢሳትም መረጃ ታቀብላላችሁ  ተብለው የተጠረጠሩ  5 የደህንነት አባላት በቁጥጥር ስር ውለዋል።  ወጣት መብራቴ ታምራት ፤ወጣት ጀማል አወል ፤ወጣት ደጀኔ አድማስ ፤ ወጣት ሃይሉ ጨርቆስ ፤መቶ አለቃ አሰፋ አብርሃ ሰሞኑን በደህንነቶች ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኢሳት የደህንነት ምንጮች ገልጸዋል።
በተመሳሳይ ዜናም በሃገሪቱ በ28ቱ ዩኒቨርስቲዎች የሚገኙ የህወሃት አባላት ተማሪዎች እና የደህንነቶች ሃለፊዎች ግምገማ መጀመራቸውን ለማወቅ ተችሎአል።
በግምገማው ወቅት የኦህዴድ እና የብአዴን መሪዎች የተማሪዎችን እንቅስቃሴ በመከታተል ባሰዩት ውጤት የተገመገሙ ሲሆን፣ ባለፉት ስድስት ወራት የአክሱም ፤ ደብረ ታቦር እና ደብረ ብርሃን የኒቨርስቲዎች ከፍተኛ የአመጽ እንቅስቃሴ የታየባቸው በመሆኑ ልዩ የደህንነት ክትትል እንደሚያስፈልጋቸው ተወስቷል።

torsdag 16. januar 2014

አርሶ አደሩን እንደፈለገ ብናደርገው በኢህአዴግ ላይ አይነሳም ሲሉ አቶ በረከት ተናገሩ

የጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ አማካሪ የሆኑት አቶ በረከት ስምኦን ለመንግስት ሚኒስትሮችና ለከፍተኛ የኢህአዴግ አመራሮች በተዘጋጀው የምርጫ ውይይትና ግምገማ ላይ ባቀረቡት ንግግር ላይ እንደገለጹት አርሶ አደሩ እስካሁን በተሰረላት ስራ በመርካቱ ” መንግስት ሰላማዊ ሰልፍ ውጣ ቢለው ይወጣል፣ መንግስት ተኛ ቢለው ይተኛል፣ ግፍ ብንፈጽም አርሶአደሩ ይህን መንግስት ምንም አይለውም፣ ይሸከመዋል” ብለዋል።
30 በመቶ የሚሆነውን ወጪ የምንሸፍነው በውጭ እርዳታ በመሆኑ፣ ከውጭ ተጽእኖ ለመላቀቅ ወጪያችንን የሚሸፍን ገቢ ማግኘት አለብን ያሉት አቶ በረከት፣ “በ1997 ምርጫ ወቅት የውጭ ሃይሎች ጥፋት ያጠፉትን መሪዎችን ወደ ፍርድ ቤት የምትወስዱዋቸው ከሆነ እርዳታ እናቆማለን ባሉት መሰረት እርዳታ አቁመውብን ነበር” ሲሉ ለራሳቸው ባለስልጣኖች ተናግረዋል።
አቶ በረከት  ”በ1884ቱ ድርቅ ጊዜ የአሜሪካ የእርዳታ ድርጅት ሃላፊው የመሬት ፖሊሲያችሁን ካልቀየራችሁ እርዳታ አንሰጥም” ብለዋቸው እንደነበር ተናግረዋል።
ኢህአዴግ ከዋናዎቹ አመራሮች ጀምሮ በተዋረድ ለሌሎች አመራሮችም ምርጫውን ስለሚያሸንፉበት ሁኔታ ስልጠና እየሰጠ ነው። ኢህአዴግ የገጠሩን ድምጽ ሙሉ በሙሉ እንደሚያገኝ አቶ በረከትና ኢህአዴግ ሙሉ በሙሉ ተማምነዋል። ይሁን እንጅ የኢህአዴግ ካድሬዎች  በየገጠሩ በመዞር ያልተደራጀውን አርሶአደር በአንድ ለአምስት በማደራጀት፣ በመሬት እጥረት የተከፋውን ወጣት የወል መሬት እየሸነሸኑ በመስጠት ላይ መሰማራታቸውን የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።