onsdag 8. januar 2014

ተስፋ የተጣለበት የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት አደጋ ውስጥ መውደቁ ተሰማ


ሰሞኑን አዲስ አበባ ውስጥ ተካሂዶ የነበረው የሰላም ድርድር ውጤት ሊያመጣ ይችላል ተብሎ ተገምቶ የነበረ ቢሆንም ፣ የመንግስት ሀይሎች ቤንቲዩ እየተባለች የምትጠራውን የነዳጅ ዘይት የሚገኝበትን ቦታ ለመቆጣጠር ጥቃት መጀመራቸው በሰላም ስምምነቱ ላይ ያለው ተስፋ እንዲጨልም አድርጎታል።
የፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ተቀናቃኝ የሆኑት ሪክ ማቻር ደጋፊዎች ካልተፈቱ የሰላም ስምምነት ለመፈራረም እንደሚቸገሩ አማጺያኑ ቢገልጹም መንግስት ግን እስረኞችን ለመፍታት ፈቃደኛ አልሆነም።  የድርድሩ ቦታ ከአዲስ አበባ ወደ ጁባ የሚዞር ከሆነ እስረኞቹ ቀን ቀን እየተደራደሩ ማታ ወደ እስር ቤት መመለስ ይችላሉ ሲሉ ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል። አማጽያኑ ግን እንዲህ አይነቱን ቅድመ ሁኔታ አልተቀበሉትም።
በቤንቲዩ የሚደረገውን ጦርነት በመሸሽ በርካታ ስደተኞች አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል። እስካሁን ድረስ ከ1 ሺ ያላነሱ ዜጎች በግጭቱ ተገድለዋል። በመቶሺዎች የሚቆጠሩ የአገሪቱ ዜጎችም አካባቢያቸውን ለቀው ተሰደዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ዜጎቹን ከደቡብ ሰዳን ለማስወጣት  እንቅስቃሴ አልጀመረም።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar