30 በመቶ የሚሆነውን ወጪ የምንሸፍነው በውጭ እርዳታ በመሆኑ፣ ከውጭ ተጽእኖ ለመላቀቅ ወጪያችንን የሚሸፍን ገቢ ማግኘት አለብን ያሉት አቶ በረከት፣ “በ1997 ምርጫ ወቅት የውጭ ሃይሎች ጥፋት ያጠፉትን መሪዎችን ወደ ፍርድ ቤት የምትወስዱዋቸው ከሆነ እርዳታ እናቆማለን ባሉት መሰረት እርዳታ አቁመውብን ነበር” ሲሉ ለራሳቸው ባለስልጣኖች ተናግረዋል።
አቶ በረከት ”በ1884ቱ ድርቅ ጊዜ የአሜሪካ የእርዳታ ድርጅት ሃላፊው የመሬት ፖሊሲያችሁን ካልቀየራችሁ እርዳታ አንሰጥም” ብለዋቸው እንደነበር ተናግረዋል።
ኢህአዴግ ከዋናዎቹ አመራሮች ጀምሮ በተዋረድ ለሌሎች አመራሮችም ምርጫውን ስለሚያሸንፉበት ሁኔታ ስልጠና እየሰጠ ነው። ኢህአዴግ የገጠሩን ድምጽ ሙሉ በሙሉ እንደሚያገኝ አቶ በረከትና ኢህአዴግ ሙሉ በሙሉ ተማምነዋል። ይሁን እንጅ የኢህአዴግ ካድሬዎች በየገጠሩ በመዞር ያልተደራጀውን አርሶአደር በአንድ ለአምስት በማደራጀት፣ በመሬት እጥረት የተከፋውን ወጣት የወል መሬት እየሸነሸኑ በመስጠት ላይ መሰማራታቸውን የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar