tirsdag 30. desember 2014

24 ኢትዮጵያውያን ወደ የመን ሲያቀኑ ባህር ላይ ሰጠሙ

የየመን አገር ውስጥ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ኢትዮጵያውያኑ  ሞቻ በሚባለው የወደብ ከተማ አቅራቢያ  ሲደርሱ የተሳፈሩበት ጀልባ በመስጠሙ 24ቱም አትዮጵያውያን አልቀዋል።
የሁሉም አስከሬን መገኙቱን ባለስልጣኑ ሲናገሩ፣ የተረፉ ካሉም በማፈላለግ ላይ መሆኑን አስታውቋል።
ባለፈው ወር ከ79 ያላነሱ ኢትዮጵያውያን ባህር ላይ ማለቃቸው ሲታወስ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ባህር ላይ የሞቱ ኢትዮጵያውያንን ቁጥር 100 አድርሶታል።
ስቴት ዲፓርትመንት ባወጣው ዘገባ በየቀኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን አገራቸውን ለቀው ይሰደዳሉ። መንግስት በተደጋጋሚ አገሪቱ 11 በመቶ እንዳደገች ቢግልጽም ስደቱ ግን አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሎአል።

mandag 29. desember 2014

በእግሪ ሓሪባ የህወሓት ፍፃሜ የደረሰ ይመስላል (አምዶም ገብረስላሴ – ከትግራይ)


ትናንት ኰሓ ከተማ አለፍ ብለህ የምትገኘው እግሪ ሓሪባ ለመጀመርያ ግዜ ጎበኘሁ። ሁኔታው ልብ ይሰብራል። ህዝቡን ከልቡ ለሚወድ ሰው ሁኔታው አይቶ ልቡ ደም ታነባለች።እና እንዲህ የሚል ድምዳሜ ደርሻለሁ። ህወሓት መፈጠር አልነበረባትም! ለትግራይ ህዝብ ሲባል ህወሓት የምትባል ድርጅት በ1967 መረገዝ አልነበረባትም። እንደ አጋጣሚ ከተረገዘች ደግም በባህላዊ ይሁን በህከምና ሽሉ ከትግራይ ህዝብ ማህፀን በእንጭጩ ማስወረድ (abortion) መደረግ በተገባ ነበር።
ባልተከሰተ ነገር በቁጭት መነጋገሩ ይቆይልንና በተጨባጭ ነገር እስኪ እንነጋገር። በነገራችን ላይ ከዛ በፊት ከጥቂት ዓመታት,በፊት ከአብርሃ ደስታ ጋር በሃሳብ የተጋጨንበትና አሁን የኔ ስህተት መሆኑ የገባኝ አንድ ነገር ልንገራቹህ። ይህ ሃሳብ በፌስቡክም ለቆት ነበር። እኔና አብርሃ የተከራከርነው ግን በዩንቨርሲቲ ግቢ ካፍቴርያ ሻይ እየጠጣን ነው። አንድ ካድሬ አስተማሪ ጓደኛዬ አብርሃ ደስታ ሲያልፍ ጠራውና አብረን ሻይ እየጠጣን ማውራት ጀመርን ።ወሬያችን ስለአስተዳደራዊ ግድፈቶች ነበር። ጥሩ እየተግባባን ቆይተን ድንገት አብርሃ “እነ መለስ በረሃ የወጡት እኮ ለስልጣን ሲሉ እንጂ ለትግራይ ህዝብ ሲሉ አይደለም ” አለ። ካድሬው አስተማሪ ረጋ,ብሎ ለማስረዳት ሲሞክር ገረመኝ። እንደዎትሮው ስሜታዊ አለመሆኑ ነገሩ ያመነበት መስሎ ታየኝ። እኔ በበኩሌ ከረር ባለመልኩ የአብርሃን ሀሳብ ተቃወምኩት። ወያኔዎች የተበላሹት ስልጣን,ከያዙ በኋላ,ነው መጀመርያ,ትምህርታቸው አቋርጠው በረሀ እንዲወጡ ያደረጋቸው ግን ያኔ የነበረው ጨቋኝ ስርዓትና ያለህዝብ ፍላጎት ስልጣን የያዘ ወታደራዊ መንግስት ነው ብዬ ተናገርኩ። ነገሩ አሁን ከፃፍኩት በላይ ስሜታዊ ሁኜ የተናገርኩት አብረሀ ደስታ በፌስቡክ ፅሁፉ ካወቅኩት ጀምሮ ,የትግራይ,ህዝብ ብርሀን ነውና የሱ በእምነት ደረጃ ትንሽ መሳሳት በምናደርገው ትግል ዋጋ ያስከፍለናል ብዬ በሌላ አገላለፅ ለሱ ካለኝ ክብር የተነሳ ነው።
አሁን መልሼ ሳስበው ግን የአብርሃ ደስታ ሀሳብ ትክክል መሆኑ ለማመን ተገድጃለሁ። ሁለተኛ ወያኔ ነን ብለው ራሳቸው,የሰየሙ ተማሪዎች በረሃ,የወጡት ለትግራይ ህዝብ አንድም ለኢትዮጵያ ህዝብ ብለው አልነበረም። ስለዚህ የአስራ ሰባት ዓመት ትግሉ አስፈላጊ አልነበረም። ደርግ በስልጣኑ ከመጣህበት ይገድለሀል። ወያኔዎች ወደ ወንበራቸው ከተመለከትክ ይገድሉሀል። ፍትህ በማስፈኑና ሙስናን በመቆጣጠር በንፅፅር ደርግ ይሻላል። የትና የት! ደርግ በሀገር ጉዳይ አይደራደርም። ህወሓት በሀገርና,በህዝብ ጉዳይ የገንዘብ,ትርፍ,የሚያገኝበት,ከሆነ ይደራደራል። ደርግ የተማረ ሰው የሚያግዘው,ቢያገኝ እሱ ቢገዛ,ይሻል,ነበር።
ወደ ዋናው ጉዳይ ስገባ የጣብያ እግሪ ሓሪባ ህዝብ በአንድ ድምፅ ወደ ከተማ መግባት አንፈልግም በማለቱ በመንግስት አሰቃቂ ብቀላ ተካሂዶበታል። ት /ቤቶች ተዘግተዋል። ማንኛውም የመንግስት መሰረታዊ አገልግሎቶች ከተቋረጡ ድፍን ዓመት አለፋቸው። ህፃናቶችና ጎልማሳዎች መማር አቋርጠዋል። የነበረው ጤና,ጣብያ ተዘግቶዋል። እግሪሓሪባ,ውስጥ ያሉት ህፃኖቶች በተለይ ካለፈው ዓመት ወዲህ የተወለዱ ምንም ዓይነት ክትባት አያውቁም። ውድ አንባቢዎቼ እየነገርኳቹህ ያለሁት ትላንት ራሴ ህጄ ያረጋገጥኩትና በሃያ አንደኛው ክፍለዘመን በኢትዮጵያ: ትግራይ: እንደርታ ወረዳ: በህወሓት ምክንያት እየተፈፀመ ያለ ግፍ እንጂ ባለፉት ክፍለዘመናት በነገስታት የተፈፀመ ታሪክ አይደለም። እናቶች ህክምና መውለድ ባለመቻላቸው እየሞቱ ያሉበት ሁኔታ ነው,ያለው። ባየሁት ልብ የሚሰብር ሁኔታ እስካሁን አንገቴን እንደደፋሁ ነው። በሌሎች የትግራይ አካባቢዎች ተመሳሳይ ሁኔታ ሲያጋጥም ወያኔ እንዴት እንደሚፈታው አውቃለሁ። አሁን ህወሓት በእንደርታ ህዝብ ላይ የባሰ ንቀትና ጥላቻ እንዳላቸው ለመገንዘብ ችያለሁ። እናንተ የህወሓት አመራሮች የሂትለር አምሳያዎች ሆይ የእንደርታ ህዝብ የቀደማይ ወያኔ መነሻ መሆኑን የረሳቹሁት መሰለኝ። አንገቱ ደፍቶ ይቆይና አንዴ ከተነሳ,ግን በዋዛ,እንደማይለቃቹህ የገባቹህ አይመስለኝም። የሰብዓ እንደርታ ህዝብ የዋህ እንጂ ሞኝ አይደለም!
ባለፈው ግዜ በእግሪ ሓሪባ የመንግስት ፀጥታ አስከባሪዎች ባለመኖራቸው ከሌሎች አካባቢ ሌቦችና ዘራፊዎች ገብተው ነበር። የእግሪ ሓሪባ ህዝብ ግን በሚያስደንቅ ሁኔታ ዘራፊዎቹ በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ በዱላ እየዠለጠ እግራቸው ስባብሮ እያነከሱ ወደ ኰሗ ከዛ ወደ መጡበት እንዲመለሱ አድርገዋል። ህዝቡ ዘራፊዎቹን ለመንግስት ያላስረከበው ከላይ እንደገለፅኩት ከመንግስት ጋ,የከረረ ጥል ውስጥ ስላለ ነው።
ጋዜጠኞቻችን ስለነዚህ ህዝቦች ለአንድ ቀን እንኳ ለማቅረብ ተስኖአቸው,ለአርባኛው ዓመት ግን እየዘፈኑና እየጨፈሩ ነው። ዝቃጮች። አባይ ወልዱ የሚሉት ሰውዬ ይህን ያህል ጅል አይመስለኝም ነበር። ለማንኛውም የካቲት 11 ሲደርስ ከእግሪ ሓሪባ ህዝብ ላሳልፈው አስቤያለሁ። ሌሎች የህወሓት ተቃዋሚዎችም እኔ ጋ ብትመጡ ደስ ይለኛል። በነገራችን ላይ ኰሓ ያገኘሁት አንድ የመንግስት ሰራተኛ እንደነገረኝ ወደ እግሪ ሓሪባ,ገብተው የነበሩት ዘራፊዎች በወያኔው መንግስት የተላኩ ናቸው አለኝ። ሊሆን ይችላል።
የህወሓት ፍፃሜ የተቃረበ ይመስላል!!

lørdag 27. desember 2014

በ15 ከተሞች በተመሳሳይ ሰዓት ሰልፍ ሊደረግ ነው


የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ሁለተኛ ዙር መርሃ ግብሩን ይፋ አደረገ
∙በ15 ከተሞችበተመሳሳይ ሰዓት ሰልፎች ይደረጋሉ
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
የ9ኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል ያወጣውን ሁለተኛ ዙር መርሃ ግብሩን ዛሬ ታህሳስ 17 ቀን 2007 ዓ.ም ይፋ አድርጓል፡፡ ትብብሩ የመጀመሪያ ዙር መርሃ ግብሩን በህዳር ወር በተለያዩ እንቅስቃሴዎች ማከናወኑ የሚታወስ ሲሆን፣ ሁለተኛ ዙር መርሃ ግብሩ ደግሞ ለ2 ወራት የሚቆይ እንደሚሆን ተገልጹዋል፡፡
የትብብሩ አመራሮች በሰማያዊ ጽ/ቤት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት በሁለተኛ ዙር የትብብሩ መርሃ ግብር መሰረት የካቲት 15 ቀን 2007 ዓ.ም በተመሳሳይ ሰዓት በ15 የሀገሪቱ ትላልቅ ከተሞች ላይ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፎች ይደረጋሉ፤ በአዲስ አበባ፣ በሀዋሳ፣ በባህር ዳርና በአዳማ ደግሞ ህዝባዊ ስብሰባዎች እንደሚደረጉ የትብብሩና የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ይልቃል ጌትነት (ኢ/ር) በመግለጫው ወቅት ተናግረዋል፡፡
‹‹የመግባቢያ ሰነዳችንና የጥናት ሪፖርታችንን እንዲሁም ከመጀመሪያው ዙር ያገኘውን ተሞክሮ በሠረት በማድረግ ይህን የሁለተኛ ዙር የሁለት ወር ዕቅድ (ከታህሳስ 16 እስከ የካቲት 15 /2007) አውጥቶ በቀዳሚነት ለዋነኛ ባለቤቶቹና ፈጻሚዎቹ ኢትዮጵያዊያን ሲያቀርብ እንደመጀመሪያው ዙር ከጎኑ እንደሚቆሙ ሙሉ እምነት በማሳደር ነው›› ያለው መግለጫው፣ በትብብሩ በኩል በአመራር ከፊት ቆመው ትግሉን ለመምራት ዝግጁነትና ቁርጠኝነት መኖሩን አስረድተዋል፡፡
‹‹የያዝነው የትግል መንገድ ሠላማዊና ህገ-መንግሥታዊ ብቻና ብቻ፣ መጓጓዣችን ዴሞክራሲያዊ ምርጫ፣ መድረሻችን መድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት፣ እንዲሁም በጉዞኣችን ላይ የቱንም ያህል አረመኔያዊ የኃይል እርምጃ ይወሰድብን፣ ትግሉ የቱንም ዓይነት ዋጋና መስዋዕትነት ይጠይቅ ከጅምሩ ያለመስዋዕትነት ድል የለም ብለን ተነስተናልና ከያዝነው ዓላማ ኢንች የማናፈገፍግና ለቃላችን በጽናት የምንቆም መሆኑን ዳግም እናረጋግጣለን›› ብሏል ትብብሩ በመግለጫው፡፡
እቅዱ የመጀመሪያው ዙር ቀጣይ መሆኑን ያተተው የትብብሩ መግለጫ፣ ‹‹ዓላማችን የምርጫ ሁኔታዎች ባልተሟሉበትና የመራጩ ህዝብ ነጻነት በሌለበት ስለምርጫ መናገር አስቸጋሪ ነው፣ እነዚህ በሌሉበት አማራጭ የምርጫ ኃሳቦች በህዝብ ውስጥ ሊንሸራሸሩም ሆነ አማራጭ ኃሳባችንን ከህዝብ ማድረስ አይቻልም፣ ሚናችንም የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታው አማራጭ ሆኖ መቅረብ ሣይሆን የህወኃት/ኢህአዴግ አጃቢነትና የሀገር ሃብት በአላስፈላጊ መንገድ የማባከን ሥራ ተባባሪነት የዘለለ አይሆንም ከሚል የመነጨ ነው›› ሲል አቋሙን አሳውቋል፡፡ ነጻነት በሌለበት ተጨባጭ ሁኔታ ምርጫ ቧልት ነው ሲልም አክሏል መግለጫው፡፡
ሁለተኛ ዙር ፕሮግራም ዕቅዱ እንደባለፈው ተደጋጋፊ፣ ተመጋጋቢና ተከታታይ ሦስት ዋና ዋና ተግባራትና በሥራቸው አስራ አራት ዝርዝር ተግባራት ማካተቱም ተመልክቷል፡፡ እነዚህ በትብብሩ አስተባባሪ ኮሚቴ ጥልቅና ዝርዝር ውይይት ተደርጎባቸው የጸደቁ ዋና ዋና ተግባራትም፡-
1. የአባላትና የትብብሩ አቅም ግንባታ፡- የትብብሩን አባላት አብሮነት ማጠናከርና የጋራ ዓላማውን የማስፈጸም አቅም ማጎልበት፤
2. የህዝብ ግንኙነት ተግባራት፡- የህዝብ ተደራሽነት ማስፋትና ዓላማ ማስተዋወቅ፣
3. የህዝብ ንቅናቄ መድረኮች ማመቻቸት፡- በአዲስ አበባና የተመረጡ ከተሞች አራት የአዳራሽ/አደባባይ የህዝብ ውይይት፤ በአዲስ አበባና በተመረጡ አስራ አምስት የክልል ከተሞች በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግን፤ የሚያጠቃልሉ ናቸው፡፡
የትብብሩ አስተባባሪ ኮሚቴ ተግባራቱን በጊዜ ሠሌዳ በማስቀመጥ ለነዚህ ተግባራት ማስፈጸሚያ የብር 1,215, 000.00 (አንድ ሚሊየን ሁለት መቶ አስራ አምስት ሺህ ) በጀት ማጽደቁንም ለማወቅ ተችሏል፡፡ ትብብሩ ለያዘው ሠላማዊና ህገ-መንግሥታዊ የመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ትግል በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከጎኑ እንዲቆሙ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡ ሌሎች ትብብሩን ያልተቀላቀሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ትብብሩን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

onsdag 17. desember 2014

በበባህር ዳር ከተማ የሚታው የነዳጅ ችግር ተባብሶ ቀጥሏል፡፡

ሰሞኑን እንደ ሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች በነዳጅ አቅርቦት ሲቸገሩ የቆዩት የባህርዳር የታክሲና ባጃጅ አሽከርካሪዎች ዛሬም ድረስ ችግሩ ተባብሶ መቀጠሉን ለዘጋቢያችን ተናግረዋል።
በትናንትናውና በዛሬው እለት በከተማዋ ካሉት ከአስር በላይ ማደያዎች በአንዱ ብቻ ነዳጅ የሚገኝ መሆኑን የተናገሩት አሽከርካሪዎች ፣ በዚህ ነዳጅ ማደያ ለመቅዳት እስከ ሁለት መቶ ሜትር ተሰልፈው ለሰዕታት እንደሚቆዩ ተናግረዋል፡፡
ሁል ጊዜ በወሩ መጨረሻ የነዳጅ ዋጋ ማሻሻያ ይደረጋል በማለት ማደያዎች ከንግድና ኢንዱስትሪ ባለሙያዎች ጋር በሚያደርጉት የውስጥ ስምምነት በተገልጋዩ ላይ እጥረት እንደሚፈጥሩ አሽከርካሪዎች ተናግረዋል፡፡
ባለማደያዎቹ በበኩላቸው መንግስት ያደረገው የዋጋ ማሻሻያ እንደማያዋጣቸው ይናገራሉ። በነዳጅ እጥረት ሳቢያ መንገደኞች ከፍተኛ መንገላታት እየደረሰባቸው መሆኑን ይገልጻሉ።

በሃረር ከ10 ሺ በላይ ህገወጥ ቤቶች ይፈርሳሉ

የክልሉ መንግስት የሃማኖት፣ የእድር፣ የአፎቻ መሪዎችን፣ የአገር ሽማግሌዎችንና ታዋቂ ግለሰቦችን በራስ መኮንን የህዝብ አዳራሽ ታህሳስ 5 ቀን 2007 ዓም ሰብስቦ ባወያየበት ወቅት ፣ ከ1990-2004 ዓም ባለው ጊዜ ውስጥ የተሰሩ ቤቶች በሰነድ አልባ ቤትነት የተመዘገቡ እና ከከተማው ማስተር ፕላን ጋር የማይጋጩ ከሆነ ህጋዊ ይደረጋሉ፣ ከ2004 ዓም እስካሁን ካርታና ፕላን ለሌላቸው ከሊዝ ውጪ የተገነቡት ግን በሙሉ ይፈርሳሉ ብሎአል።
ስብሰባውን የመሩት የክልሉ ፍትህና ጸጥታ ጉዳይ ቢሮ ም/ል ሃላፊ አቶ ሳላሃዲን ቶፊቅ ፣  የከተማ ፕላንና ኮንስትራክሽን ሃላፊ አቶ ካሊድ አብዱረህማንና የኦህዴድ ተወካይ አቶ አብዲ ናቸው።
ባለስልጣናቱ ለውይይት ያነሱት መነሻ “ሐረር ከተማ ከሌላ አካባቢ በመጡ ሰዎች ተወራለች፤ መሬት በመወረሩ እና ህገወጥ ግንባታ በመስፋፋት ስርአት አልበኝነት ነግሷል፣ የክልሉ የቆዳ ስፋት እጅግ ጠባብ በመሆኑ መጪው ትውልድ መሬት የማግኘት መብቱን ያሳጣል፣ በአሁኑ ወቅት ከ10-30 ሺ ቤቶች ተገንብተዋል ” የሚሉት ይገኙበታል።
ህገ-ወጥ ግንባታ ተስፋፍቶባቸዋል ከተባሉት የከተማና ገጠር ወረዳዎች መካከል በዋነኝነት ከሶፊ ወረዳ ደከር፣ ከሐኪም ወረዳ ሐኪም ጋራ አካባቢ ገልመሺራ ቀበሌ፣ ከአቦከር ወረዳ ጊዮርጊስ አካባቢ፣ ከድሬጥያራ ወረዳ ፣ ወንዝ ማዶና መቆራን ተብለው የሚጠሩት አካባቢዎች ናቸው።
በስብሰባዎች ላይ የተሳተፉ ነዋሪዎች በበኩላቸው ” ህገ-ወጥ የተባሉት ቤቶች ሲገነቡ መንግስት እያየ ዝም ብሎ አሁን ዜጎችን ማፈናቀልና በቢሊዮኖች የሚገመት ሃብትና ንብረት ማውደም ተገቢ ነውን? አብዛኛው ህገ-ወጥ ግንባታ የተፈፀመው በባለሥልጣናትና በቤተሰዎቻቸው ስለሆነ እነርሱ ምሳሌ ሆነው እንዲያፈርሱ ለምን አይደረግም ? ህገ ወጥ የተባሉት ቤቶች ሲገነቡ የማዘጋጃ ቤትና የከተማ ልማት ኃላፊዎች ከፍተኛ ብር እየወሰዱ የተፈፀመ ድርጊት በመሆኑ መንግስት ለምን ራሱን አይፈትሽም? ሙስና በፈፀሙት ላይስ እርምጃ ለምን አይወሰድም? ዜጎች መሬት ሲጠይቁ ዘርና ሃይማኖት እየተለየ ስለሚሰጥ ለህገ-ወጥነት መስፋፋት ምክንያት ሆነኗል፡፡ ለባለሥልጣናትና ለቤተ ሰዎቻቸው ከከተማ ማሰተር ፕላን ጋር የሚጋጭ ቦታ እየተሰጣቸው ካርታና ፕላን እንዲወስዱ በማድረግ ህጋዊ ይደረጋሉ፣ ይህ ለምን ይሆናል? ” የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል።
ባለስልጣናቱ ለተነሱት ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ ሳይሰጡ ቀርተዋል። መንግስት ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው አፍራሽ ግብረሃይልና በፖሊስ ልዩ ሃይል አማካኝነት ከህዳር 25 ቀን 2007 ዓ/ም ጀምሮ የማፍረስ ዕርምጃ እየወሰደ ሲሆን ህብረተሰቡም በድርጊቱ ከፍተኛ ተቃውሞ እየገጠመው ነው፡፡

ህወሃት በመንግስት ወጪ 40ኛ አመቱን ለማክበር ሸርጉድ እያለ ነው

በከፍተኛ ዝግጅት ይከበራል የተባለው የህወሃት 40ኛ አመት በአል ወጪ የሚሸፈነው ከመንግስት ካዝና መሆኑ በአባል ድርጅቶች መካከል መነጋገሪያ አጀንዳ እየሆነ መምጣቱን የሚናገሩት የኢህአዴግ ምንጮች፣ ከመንግስት ካዝና ለሚወጣው ገንዘብ የተሰጠው ሰበብ  ገጽታ ግንባታ የሚል መሆኑን ገልጸዋል።
ህወሃት በአሉን ከድርጅቱ ካዝና በተለይም የአገሪቱን ሲሶ ሃብት ከተቆጣጠረው ኢፈርት ካዝና መጠቀም እየቻለ፣ ወጪውን መንግስት እንዲሸፍነው ማስደረጉ ለብዙዎቹ አልተዋጠላቸውም። አጠቃላይ ዝግጀቱ ምን ያክል ገንዘብ እንደሚያስወጣ እስካሁን በግልጽ ባይታወቅም፣ እስካሁን እየተደረጉ ባሉ እንቅስቃሴዎች ወጪውን እየሸፈኑ ያሉት የክልሉ መንግስትና የፌደራሉ መንግስት በጋራ ነው።
የካቲት 11 ቀን የሚከበረውን የህወሃት ቀን አስመልክቶ የተመረጡ ጋዜጠኞችና አርቲስቶችን በመንግስት ወጪ  ታህሳስ 13 ቀን 2007 ዓ.ም ወደ ትግራይ ይጓዛሉ። ህወሃት ከበዓሉ አስቀድሞ የትግራይ ክልልን ለማስጎብኘት ያሰበው ከወዲሁ ሰፊ የፕሮፖጋንዳ ስራ ለማከናወን እንዲመቸው በማሰብ መሆኑን ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልጸዋል፡፡

CPJ: at least 220 journalists imprisoned around the world - See more at: http://www.zehabesha.com/cpj-at-least-220-journalists-imprisoned-around-the-world/#sthash.LyWSwHNR.dpuf


186254PanARMENIAN.Net – There are at least 220 journalists imprisoned around the world, with 132 of them held on anti-state charges of terrorism or subversion, says a report released Wednesday, Dec 17, by the Committee to Protect Journalists (CPJ).
According to Al Jazeera, the CPJ census on jailed journalists indicates that 2014 is the second worst year for jailed journalists since the organization started conducting its annual census in 1990. The worst year was 2012, when 232 journalists were jailed.
The report does not count journalists being held by nonstate actors, such as the Islamic State of Iraq and the Levant (ISIL or IS), which the CPJ estimates is holding 20 journalists.
The number of journalists held by nonstate actors — about 80 have been taken by various groups since the Syrian conflict started in 2011 — is unprecedented, according to Robert Mahoney, deputy director at the CPJ.
“We’ve never seen so many journalists held captive — for ransom or other reasons — by nonstate actors,” he said.
Mahoney said it’s clear that the journalism landscape is shifting. “The targeting of journalists has been increasing to alarming proportions,” he said. “Journalists are now losing the protected observer status that they had, and now they’ve become the story rather than being the witness to the story to some groups.”
The world’s leading jailer of journalists is China, which is holding 44 reporters, according to the CPJ. Increasingly, the CPJ study notes, governments are enacting laws that facilitate media crackdowns based on the notion of state security, as is the case with a new law in Japan.
It’s an argument used by major jailers of journalists, such as China, Iran and Egypt, where the number of jailed reporters has double since 2013, to 12 identified cases.
Egypt has held three Al Jazeera journalists — Peter Greste, Mohamed Fahmy and Baher Mohamed — since Dec. 29, 2013, with sentences ranging from seven to 10 years. Their appeal is scheduled to be heard on Jan. 1, 2015.
Although Turkey, deemed “the world’s worst jailer” of journalists by the CPJ in 2012 and 2013, released a number of reporters this year, a recent raid resulting in the detention of at least 23 journalists employed by news organizations linked to a cleric who is at odds with President Recep Tayyip Erdogan has raised red flags.
“In the case of Turkey, definitely, it is a regressive step. That’s a disturbing trend because Turkey is an important democracy in the region,” said Mahoney.
In Iran the number of detained reporters in is down to 30, from 35 in 2013, the CPJ study says. But the July arrest of Washington Post reporter Jason Rezaian has led to concerns of worsening crackdowns in the country.

የዞን 9 ጠበቃን ደብዳቤ ይዘናል

ከኦነግ እና ግንቦት 7 ጋር አብረው ሰርተዋል:: የሚል ክስ የተመሰረተባቸው ወጣት ጦማርያን ፍርድ ቤት በድጋሚ ቀርበው ነበር:: የቀረቡበት ምክንያት… የተጠቀሰው የወንጀል ዝርዝር እና አንቀጹ ተዛማጅ ባለመሆናቸው የጦማርያኑ ጠበቃ በክሱ ላይ ማስተካከያ እንዲደረግ ጠይቆ ነበር:: ጠበቃው ለፍርድ ቤት ካቀረቡት ደብዳቤ ውስጥ ገጽ 2 እና 3ትን ከዚህ  ቀጥሎ አቅርበነዋል::
zon9 bloggers
zon9 bloggers2
በፌዴራሉ ዐቃቤ ሕግ በሕቡዕ በመደራጀት፣ የወንጀል አድማ ስምምነት በማድረግ፣ በውጪ ኃይሎች በመደገፍና በማህበራዊ ድረ-ገፆች በመጠቀም እንዲሁም መንግሥት አሸባሪ ብሎ ከሚጠራው ግንቦት 7 እና ኦነግ ጋር በመተባበር ሁከትና ብጥብጥን ሊያስነሱ ሲንቀሳቀሱ ነበር በሚል የሽብር ወንጀል ክስ በመሠረተባቸው በእነሶሊያን ሽመልስ የክስ መዝገብ ላይ አሁንም በድጋሚ መጥራት ያለባቸው ጉዳዮች አሉ በሚል; ከላይ በተገለጸው አይነት የተከሳሽ ጠበቆች አቤቱታቸው በፅሁፍ አቅርበዋል።
ማኅሌትና ኤዶም በልደታው ካንጋሮ ፍርድ ቤት፡፡
ማኅሌትና ኤዶም በልደታው ካንጋሮ ፍርድ ቤት፡፡

zone9_2

mandag 15. desember 2014

ሰኞ ከሰዓትን በቂሊንጦ እስር ቤት

(By: Elias Gebru Godana)
‹‹ሰላም ነን፤ ሰላም ሁኑልን!›› ጦማሪያን አቤል ዋበላ እና ዘላለም ክብረት
‹‹በርቱ፣ በሰላም ለመብታችሁ ታገሉ!›› ኡስታዝ አቡበከር አህመድ
———–
ዛሬ ከነበረን የፍርድ ቤት ውሎ በኋላ ከአሸናፊ አሳምረው ጋር ወደቢሮ አመራን፡፡ ችሎት ቁጭ ብዬ ከችሎት በኋላ ቂሊኒጦ እስር ቤት ሄጂ የምወዳቸውን እና የማከብራውን ወዳጆቼን ለመጠየቅ ዕቅድ ቀይሼ ነበር፡፡ በሀሳብ ብቻ አልቀረም፤ ለአሹ ነገርኩት፡፡ እሱም ለመሄድ ፈቃደኛ ሆነ፡፡ አብነት ረጋሳን ጨምረን ‹‹ምሳ እንብላ፣ ቡና እንጠጣ›› ሳንባባል ጉዞ ወደቂኒንጦ አደረግን!
ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ጎዳና
ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ጎዳና
የፈራረሱ የአዲስ አበባ የተወሰኑ መንገድ አድካሚነታቸው እና አቧራቸውም አይጣም ነበር፡፡ …እስር ቤቱ ደጃፍ 9፡00 ሰዓት ግድም ደረስን፡፡ እኔ ዳንኤል ሺበሺ፣ አቤል ዋበላ፣ ዘላለም ክብረት፣ አቡበከር አህመድ፣ አቡበከር አለሙ …ወዘተ ወዳሉበትና በቅርቡ ታስሬበት ወደነበረው ዞን አንድ ተመዝግቤ እና አስመዝግቤ ገባሁ፡፡ አሸናፊ እነበፍቄ፣ አጥናፍና አብርሃ ደስታ ወዳሉበት ዞን ሁለት አመራ፡፡ አብነት ደግሞ ሀብታሙ አያሌውን ሊጠይቅ ዞን ሶስት ከተመ፡፡
በተለያዩ አጋጣሚዎች መሄድ ሳልችል ቀርቼ ስለነበረ ከእስሬ በኋላ ወደቂኒንጦ ሳመራ የመጀመሪያዬ ነበር፡፡ አልዋሽ ነገር፣ አለመሄዴ የአዕምሮ ዕረፍት ነስቶኛል፡፡ ከእነ አቤሎ፣ ዞላ፣ ዳኒ፣ አብበከር ….ጋር የነበሩኝ ደስ የሚሉ ቆይታዎች በትውስታዬ ውስጥ ብዙ ጊዜ ይመላለሱ ነበር – የእሰራቸው ሁኔታ አሳዛኝነት እንዳለ ሆኖ ማለት ነው፡፡
ዛሬ፣ ሁሉንም አገኘኋቸው፡፡ ባለችን 50 ደቂቃ የቻልነውን ያህል ስለተለያዩ ሀገራዊ ሁነቶች አወጋን፡፡ ቁም ነገርን ተካፈልን፣ በቀልዶችም ዳግም ፈገግ አልን፡፡ የዞላንና የአቤሎን ተረብ አጣታምኩት፡፡ ከምር ደስ የሚሉ ልጆች ናቸው! አምላክ ከሁሉም ጋር ይሁን!
በመጨረሻም የስንብት ደቂቃ ደረሰች፡፡ አቤል እና ዘላለም ‹‹ሰላም ነን፤ ሰላም ሁኑልን!›› የሚል መልዕክትን አድርሰዋኋል፡፡ (በነገራችን ላይ ነገ የፍርድ ቤት ቀጠሮ አላቸው) ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ደግሞ ‹‹በርቱ፣ በሰላም ለመብታችሁ ታገሉ!›› ሲል ቅንና ጠንካራ መልዕክቱን ልባዊ በሆነው ፈገግታ አጅቦ ዘንዝሯል፡፡
እኔ፣ አሹና አብነት ለጥየቃ ከገባንባቸው ዞኖች ስንወጣ በፖሊሶች አመራር ተይዘን ‹‹ለምን ለአንድ ተሳሪ በላይ ጠየቃችሁ?›› በሚል ለ10 ደቂቃ ያህል ደስ የማይል የሃሳብ ልውውጥ ካደረግን በኋላ ስማችን ከመታወቂያችን ላይ ተመዘግቦና ማስጠንቀቂያ መሰል ምላሽ ከሰጠን በኋላ ቂሊንጦን ከነአዋራዋ አቋርጠን ወደሰፈራችን ደርሰናል፡፡

onsdag 10. desember 2014

“መድረክ በጠራው ሰልፍ ላይ እስከ 100ሺ ሰው ሊሳተፍ ይችላል”


በምርጫ 2002 የተስተዋሉ ጉድለቶች ሳይስተካከሉ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ መወጣቱን እና ወደ ምርጫ 2007 መገባቱን በመቃወም ሊያደርገው ባሰበው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ እስከ 100ሺ ሰዎች ሊሳተፉ እንደሚችሉ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ገለፀ።
የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጥላሁን እንዳሻው እንደገለፁት በ2002 ዓ.ም የተካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ደረጃው የወረደ እና ዴሞክራሲያዊነቱን ያልጠበቀ በመሆኑ ህዝቡ በነፃነት ምርጫ መርጧል በማያስብል መልኩ መጠናቀቁን ተከትሎ በወቅቱ ፓርቲው በምርጫው ውስጥ ጉድለቶች መኖራቸውን በማንሳት ከገዢው ፓርቲ ጋር ለመደራደር ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን ቢያቀርብም እስከ አሁን ድረስ አዎንታዊ ምላሽ ማግኘት አልቻለም። ይህን ጥያቄ ለምርጫ ቦርድም ገልፆ እንደነበረ የገለፁት አቶ ጥላሁን፤ ይልቁንም የነበሩት ግድፈቶች ምንም አይነት እርምት ሳይደረግባቸው የምርጫ ጊዜ ሰሌዳን በማውጣት ወደ ምርጫ 2007 መጓዝ መምረጡንም ገልፀዋል። በመሆኑም ገዢው ፓርቲ ለጥያቄው አዎንታዊ ምላሽ አለመስጠቱን በመቃወም የፊታችን ታህሳስ 5 ቀን 2007 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ አስቧል። ሰላማዊ ሰልፉ መነሻውን ግንፍሌ ወንዝ ድልድይ በማድረግ በቀበና ወንዝ ድልድይ እና በባልደራስ በኩል በማድረግ መድረሻውን ወረዳ 8 ኳስ ሜዳ አድርጎ ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ 7 ሰዓት ይካሄዳል።
ሰላማዊ ሰልፉ የፓርቲው ብቻ ሳይሆን የህዝቡ በመሆኑ ህዝቡ በንቃት ከተሳተፈ ወደፊት የማይገፉበት እና ግቡንም የማይመታበት ሁኔታ እንደሌለ አቶ ጥላሁን ገልፀው፤ የሰልፉ መረጃ ለህዝቡ በአግባቡ ከደረሰ ከአዲስ አበባ እና አካባቢዋ የተውጣጣ በትንሹ ከ20 እስከ 30ሺህ የሚደርስ ህዝብ እንደሚሳተፍ ገልፀዋል። የቅስቀሳ ስራው በአግባቡ ከተሰራ ግን እስከ 100 ሺህ የሚደርስ ህዝብም ሊሳተፍ እንደሚችል አቶ ጥላሁን ጨምረው ገልጸዋል።
ፓርቲው ሰላማዊ ሰልፉን ለማካሄድ ጠይቆ የነበረው ቦታ መነሻውን የፓርቲው ጽ/ቤት በማድረግ በራስ መኮንን ድልድይ ፒያሳ ጀጎል አደባባይን ይዞ ቸርቸል ጎዳናን አልፎ መዳረሻውን ድላችን ሀውልት ለማድረግ የነበረ ሲሆን፤ ነገር ግን ፈቃድ ማግኘት ባለመቻሉ ሰልፉ መደረግ ስላለበት ሁለተኛውን አማራጭ ለመቀበል መገደዱን አቶ ጥላሁን ገልፀዋል። የፓርቲው መጀመሪያ ምርጫ በመሀከል ከተማ የሚያልፍ እና ከአራቱም የከተማዋ አቅጣጫ ሰዎች ሊሳተፉበት የሚችሉበት ቦታ መሆኑን የገለፁት አቶ ጥላሁን፣ አሁን በተፈቀደላቸው ቦታ በሚደረገው ሰልፍ ላይ ግን የተሳታፊው ቁጥር የተጠበቀውን ያህል ላይሆን እንደሚችል ገልጸዋል።
ሰላማዊ ሰልፍን በተመለከተ ሕገ መንግሥቱ ማስፈቀድ ሳይሆን ማሳወቅ ስለሚል ፓርቲው እውቅና እንዲሰጠው ጠይቆ የእውቅና ደብዳቤ በአጭር ጊዜ ውስጥ መውሰዱ የተገለፀ ሲሆን፤ በፈቃድ ደብዳቤው ፓርቲው ቅስቀሳ የሚያደርግባቸውን መንገዶች ያካተተ ፍቃድ እንደተሰጠው ገልጿል። ፓርቲው በማይክሮፎን፣ ወረቀት በመለጠፍ እና በራሪ ወረቀቶችን ጭምር በመበተን ቅስቀሳ የማድረግ ፈቃድም እንደተሰጠው አቶ ጥላሁን ጨምረው ገልፀዋል። ፓርቲው ከዚህ ቀደም ካጋጠሙት ነገሮች ትምህርት ወስዶ እንደሆን የተጠየቁት አቶ ጥላሁን፤ በሰላማዊ ሰልፍ ወቅት ችግር የሚገጥመው ከፓርቲው ሳይሆን ከገዢው ፓርቲ የማደናቀፍ ስራ የተነሳ መሆኑን ገልፀው፤ ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ ቅስቀሳው እየተካሄደ እንደሆነ እና ከመጪው አርብ ጀምሮም ወረቀቶቹ እንደሚለጠፉ፤ በራሪ ወረቀቶችም እንደሚበተኑ አሳውቀዋል።

mandag 8. desember 2014

70 ኢትዮጵያውያን ቀይ ባህር ላይ አለቁ

ስደትን የህይወታቸው የመጨረሻ አማራጭ በማድረግ በጅቡቲ በኩል አድርገው ወደ የመን ለመግባት የሞከሩ 70 ኢትዮጵያውያን ቀይ ባህር ላይ ሰጥመው መሞታቸውን የየመን ባለስልጣናት ገልጸዋል።
ታይዝ በምትባለዋ ግዛት የሚገኙ ባለስልጣናት ለአሶሴትድ ፕሬስ እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያውያኑን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረችው ጀልባ ባጋጠማት ከባድ አውሎ ንፋስና ማእበል አል ማክታ እየተባለ ከሚጠራው ወደብ ራቅ ብሎ ለመስመጥ ተገዳለች። ባለስልጣናቱ እንዳሉት ጀልባዋ 70 ኢትዮጵያውያንን ጭና የነበረ ሲሆን በደጋው ሁሉም ኢትዮጵያውያን አልቀዋል።
የመን የሚገኘው ጋዜጠኛ ግሩም ተክለሃይማኖት በበኩሉ በጀልባዋ ላይ የነበሩት 81 ሰዎች ሲሆኑ፣ 71 ኢትዮጵያውያንና 9 ሶማሊያዎች አልቀዋል። አይ ኦ ኤም የተባለው የስደተኞች ድርጅት አስከሬን ለመሰብሰብ ሙከራ ቢደረግም እስካሁን ምን ያክል አስከሬን እንደተሰበሰበ ለማወቅ አለመቻሉን ገልጿል
ግሩም እንደሚለው በአንድ ወር ውስጥ ብቻ 8 ሺ ኢትዮጵያውያን የመን ሲገቡ፣ በ7 ወር ውስጥ እስከ 50 ሺ ኢትዮጵያውያን ተሰደዋል።

በአገዛዙ አረመኔያዊ እርምጃ ትግላችን አይቆምም! – ከትብብሩ የተሰጠ መግለጫ

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ባለፈው አንድ ወር ‹‹ነጻነት ለፍትሓዊ ምርጫ›› በሚል መርሃ ግብር ቀርጸን ስንቀሳቀስ ዋናው አላማችን የስርዓቱን አረመኔያዊነት ለህዝብ በማጋለጥ የኢትዮጵያ ህዝብ በትግሉ እንዲሳተፍ ማድረግ ነው፡፡ እንደጠበቅነው ገና ከጅምሩ የህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ ትግላችንን በጭካኔ ለማስቆም ጥሯል፡፡ ህዳር 7/2007 ዓ.ም የመጀመሪውን የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ በጠራንበት ወቅት ስብሰባውን በኃይል በትኗል፡፡
ትብብራችን ከመቸውም ጊዜ በላይ ያሰጋው ህወሓት/ኢህአዴግ በተለይ የህዳር 27/28 2007 ዓ.ም የአደባባይ አዳር ሰልፍን እንዳይካሄድ የትብብሩን አመራሮችና አባላቶቻችን በማዋከብ፣ በመደብደብና በማሰር ተጠምዶ ሰንብቷል፡፡ በተለይ በትናንትናው ዕለት ሰልፍ በወጣንበት ወቅት ስርዓቱ አመራሮችንን፣ አባላቶቻችንን፣ ተሳታፊዎችንን እንዲሁም አልፎ ተርፎ መንገደኛውን ህዝብ በጭካኔ ደብድቧል፡፡ አፍሶ አስሯል፡፡ ሙስሊም እህትና ወንድሞቻችን በየጎዳናው ታፍሰው የአገዛዙ አረመኔያዊ እርምጃ ሰለባዎች ሆነዋል፡፡ በርካቶችም በእ
በየ እስር ቤቶቹ ታጉረዋል፡፡ እስካሁን ባለን መረጃ ከ300 በላይ የትብብሩ አመራሮችና አባላት የታሰሩ ሲሆን የትብብሩና የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበርን ጨምሮ በርካታ አመራሮች ከፍተኛ የአካል ጉዳት ድርሶባቸዋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ አባል የሆነው አቤል ኤፍሬም ራሱን እስኪስት ተደብድቧል፡፡ በሰላማዊ ሰልፉ የተገኙ ሴት አመራርና አባላት አንድ አገርን እየመራሁ ነው ከሚል አካል በማይጠበቅ መንገድ በጭካኔ ተደብድዋል፡፡ እነዚህ በጭካኔ የተደበደቡ አመራሮች፣ አባላትና የሰልፉ ተሳታፊዎች ህክምና እንዳያገኙ ተከልክለዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በጥበቃ ሰራተኝነት የሚሰሩ የ72 አመቱ አቶ ቀኖ አባጆቢር ከስራ ሲወጡ በደህንነት ኃይሎች ታፍነው የተወሰዱና እስካሁን የት እንደደረሱ ያልታወቀ ሲሆን ይህም አገዛዙ የመጨረሻው የአረመኔነት ደረጃ ላይ እንደደረሰና ይህን የስርዓቱ ውንብድና ለማስቆም ጊዜ የማይሰጠው ተግባር መሆኑን በግልጽ የተገነዘብንበት ነው፡፡
አገዛዙ በትናንትናው ዕለት በፍጹም ሰላማዊ ሰዎች ላይ የወሰደው የውንብድና እና አረመኔያዊ እርምጃ በትግሉ ውስጥ የምንጠብቀውና ስርዓቱ ለኢትዮጵያ የማይበጅ መሆኑን ዳግመኛ ያያ
ረጋገጠበት ነው፡፡ የትናንትናው ትላችን አገዛዙ ለይስሙላ እከተለዋለሁ ከሚለው ‹‹ህጋዊ ሰርዓት›› ይልቅ ስልጣኑን በኃይል ለማስጠበቅ ቆርጦ መነሳቱን እና በህገ መንግስት ስም ህዝብን የሚበድልበትን የአረመኔያዊነት ጭንብል ገልጠን ለዓለም ያሳየንበት የትግላችን ውጤት ነው፡፡
አገዛዙ ላላፉት 24 አመታት ስልጣኑን በኃይል ለማስጠበቅ ሲጥር ቆይቷል፡፡ በትናንትናው ዕለት የፈጸመው ፍጹም አረመኔያዊ እርምጃም እንደተለመደው ሰላማዊ ታጋዮችን ያሸማቅቃል ብሎ አስቦ እንደሆነ እሙን ነው፡፡ ነገር ግን ይህ የአገዛዙ አረመኔያዊነት ከሰላማዊነታችን ፍጹም ወደኋላ ሊያንሸራትተን አይችልም፡፡ ወደ ትግል ስንገባ የስርዓቱን ጭካኔና ለኢትዮጵያ የ
ማይመጥን መሆኑን አውቀንና የሚያስከፍለውን መስዋዕትነት ለመክፈል ተዘጋጅተንም ነው፡፡ አሁንም አገዛዙ የህዝብን ድምጽ በማፈን ስልጣኑን ለማስጠበቅ ተመሳሳይ እርምጃ እንደሚወስድ እንጠብቃለን፡፡ ነገር ግን መጀመሪያውንም ትግሉን ስንቀላቀል አስበን የገባነው እየቆሰልን፣ እየታሰርንም፣ እየሞትንም ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ ለመሆን ነውና ከትግላችን ቅንጣት ሊያደናቅፈን አይችልም፡፡ ስለሆነም ወደፊትም ይህን የአገዛዙን አረመኔያዊነት በማጋለጥና ህዝቡን በትግሉ በማሳተፍ ለኢትዮጵያ የሚገባት ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ለመመስረት በቀጣይነትም ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን፡፡
በዚህ አጋጣሚ ሰላማዊ ሰልፉን ለማሳካት እንዲሁም የህወሓት/ኢህአዴግ ቡድን የፈጸመውን ጭካኔ በማውገዝ ከጎናችን ለቆማችሁ ሁሉ ምስጋናችን የላቀ ነው፡፡ ከህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ ጋር የሚደረገው ትግል እልህ አስጨራሽ፣ ከፍተኛ መስዋዕትነት የሚያስከፍልና የእያንንዳንዳችን ትብብር የሚጠይቅ መሆኑን ተገንዝበን ሁላችንም በጋራ እንድንቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን
ያለ መስዋዕትነት ድል የለም፡፡

lørdag 6. desember 2014

(ሰበር ዜና) መስቀል አደባባይን በርከት ያሉ ፖሊሶችን የጫኑ የፌደራል መኪኖች አጣበዋታል; ለሰልፍ የሚወጣውን እያፈኑ ነው

ሰማያዊ ፓርቲን ጨምሮ 9ኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዛሬ በመስቀል አደባባይ የጠሩት የ24 ሰዓት የተቃውሞ ሰልፍን ለማስቆም መንግስት መስቀል አደባባይ ላይ የፌደራል ፖሊስ በጫኑ መኪናዎችን ማስፈሩን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመለከተ::
semayawi
9ኙ ፓርቲዎች መንግስት ተቃውሞውን ለማፈን ከመንገድ ላይ እያስቀረ በመሆኑ በአንድ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ከመሄድ ይልቅ በተለያያ አቅጣጫ እንዲሄድ ከደቂቃዎች በፊት ባወጡት መግለጫ ጥሪ አቅርበዋል::
በመስቀል አደባባይ የተገኙ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እየታፈኑ ወደ ኤግዚቢሽን ማዕከል እየተወሰዱ መሆኑን የገለጹልን የአይን እማኞች ሂጃብ የለበሱ የሙስሊም ሴቶች; የኦሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ህብረት ሊቀመንበርና የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ፀሃፊ አቶ ግርማ በቀለ; አህመድ ሞሃመድ የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ አባል እና ሌሎችም ታፍነው ተወስደዋል::
በአሁኑ ወቅት መስቀል አደባባይ የሚገኘው ፌደራል ፖሊስ ለተቃውሞ የወጣውን ሕዝብ እየበተነ; እያሰረ ይገኛል::
ተጨማሪ መረጃ ይዘን እንመለሳለን::

fredag 5. desember 2014

የሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ በፖሊስ ተከብቦ አደረ

 ምንነቱ የማይታወቅ ወረቀት ሲበተን አድሯል



የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በፖሊስ ተከብቦ ማደሩንና አባላት ከውጭ እንዳይገቡ መደረጋቸውን ለአዳር ሰልፉ ቅስቀሳ ዝግጅት ቢሮ ያደሩ የፓርቲው አመራሮችና አባላት ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ አመራሮችና አባላቱ እራት በልተው ወደ ፓርቲው ጽ/ቤት ሲመለሱ ቢሮው በፖሊስ ተከብቦ እንዳገኙትና ወደ ውስጥ እንዳይገቡ እንደተከለከሉ በቦታው የነበሩት የፓርቲው አመራሮችና አባላት ገልጸዋል፡፡ 

አመራሮችና አባላቱ ፖሊስ ከ200 ሜትር ርቀት ውጭ ወደ ፖለቲካ ፓርቲ ጽ/ቤት መጠጋት እንደማይችል ቢከራከሩም ፖሊሶቹ ‹‹መመሪያ ተሰጥቶናል፤ አንሄድም!›› ማለታቸው ገልጸዋል፡፡ አመራሮቹና አባላቱ ከፖሊስ ጋር ሲከራከሩ የአካባቢው ህዝብ በመውጣቱ ፖሊሶቹ ፓርቲው ጽ/ቤት እንደራቁ ታውቋል፡፡

በሌላ በኩል ከውጭ ወደ ቢሮ ከሚመጡበት ወቅት የፓርቲው ቢሮ አካባቢ ምንነቱ ያልታወቀ ወረቀት ተበትኖ እንዳገኙና እነሱ ሲደርሱ ፖሊሶቹ እንዳነሱት የፓርቲው የምክር ቤት አባል ወጣት እየሩስ ተስፋው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጻለች፡፡

torsdag 4. desember 2014

ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ አመክሮ ተከለከለች

ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ “ሽብርተኛ” ተብላ በእስር ላይ የምትገኝ ሲሆን እንደማንኛውም እስረኛ ልታገኝ የሚገባውን አመክሮ ሳታገኝ ቀርታለች:: በመሰረቱ አመክሮ የሚሰጠው አንድ እስረኛ በ እስር ቤት ቆይታው ወቅት የሚያሳየው መልካም ባህሪ ተገምግሞ ለአንድ እስረኛ ከተፈረደበት አመት ተቀንሶ እንዲወጣ ይደረጋል:: ከቤተሰብ ያገኘነው መረጃ እንደሚያስረዳው ከሆነ ለርዕዮት አለሙ ሊሰጣት የነበረው የአመክሮ ቅፅ “ከጥፋቴ ታርሜያለሁ” የሚል ነው::
Reeyot Alemu
Reeyot Alemu
ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙን በዚህ ጉዳይ ያነጋገራት ከፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኤጀንሲ የመጣ ሰው ነበር:: በውይይታቸው ወቅት “ከጥፋቴ ታርሜያለሁ” የሚለውን አባባል ለመቀበል አልቻለችም:: ምክንያቱም ሃሳቧን በጽሁፍ ስለገለጸች ነው “አሸባሪ” ተብላ የታሰረችው:: ከፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኤጀንሲ የመጣውም ሰው “እንግዲያው አንቺ ከጥፋቴ ታርሜያለሁ” ብለሽ የማትፈርሚ ከሆነ እኛም አመክሮ አንሰጥሽም ብሏታል::
ከዚህ በፊትም “አጥፍቻለሁ ይቅርታ ይደረግልኝ” ተብሎ በፕሬዘዳንቱ አማካኝነት የሚደረገውን ሂደት ሳትቀበለው ቀርታ የይቅርታ ደብዳቤ አለማገባቷ ይታወሳል:: አሁን በቅርቡ ማድረግ የሚቻለውን “አመክሮ” ተቀብላ ቢሆን ኖሮ አሁን ከ እስር የምትወጣበት ወቅት እንደነበር ከቤተሰብ አካባቢ ያገኘነው ምንጭ አረጋግጧል::

onsdag 3. desember 2014

ዞን ዘጠኞች ፍርድ ቤት ቀረቡ

በእነ ሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው እየታየ ያሉት ጦማርያን እና ወዳጅ ጋዜጠኞች ላይ የተመሰረተው ክስ ተሻሽሎ ቀርቧል የተባለው የክስ ዝርዝር ዛሬ በልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ተሰምቷል፡፡ ዛሬ ህዳር 24/2007 ጠዋት በዋለው ችሎት፣ በጦማርያኑ እና ጋዜጠኞች ላይ ተሻሽሎ የቀረበው የክስ ዝርዝር በንባብ የተሰማ ሲሆን በክስ ወረቀቱ ላይ ከተመለከቱት ነጥቦች መካከል ግልጽ ያልሆኑ ነጥቦችን አካትቶ እንዲሰጥ ለአቃቤ ህግ ትዕዛዝ ተሰጥቶታል፡፡ ስለሆነም ሙሉ የክስ ወረቀቱ አርብ ለጠበቆቹ እንደሚደርስ ይጠበቃል፡፡
zone 9በጠቦቆቹ በኩል ክሱ ቀደም ብሎ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት መሻሻሉን ለማረጋገጥ ያለፈው የፍርድ ቤቱ ብይን ግልባጭ እስካሁን እንዳልደረሳቸው በመግለጽ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲደርሳቸው ጠይቀዋል፡፡ በዚህም የተነሳ የብይኑ ግልባጭ ሳይደርሰን ተሻሻለ የተባለው ክስ መሰማት የለበትም ብለው የነበር ቢሆንም፣ ክሱን አይታችሁ መቃወሚያ ካላችሁ አስተያየት እንድትሰጡበት እድል እንሰጣለን ያለው ፍርድ ቤቱ ክሱ እንዲሰማ አድርጓል፡፡ ፍርድ ቤቱ ጠበቆቹ ያላቸውን አስተያየት ይዘው እንዲቀርቡ ለታህሳስ 7 ቀን 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ታውቋል፡፡
 ነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

tirsdag 2. desember 2014

በአዲስ አበባ 7ቱም የሃይማኖት ተቋማት ለመንግስት የደህንነት ስራ እንደሚሰሩ ታወቀ

የፌደራል መንግስቱ የ2006 የጸጥታ አጠባበቅ ግምገማ በሚያደርግበት ስብሰባ ላይ እንደተገለጸው በአዲስ አበባ 7ቱም የሃይማኖት ተቋማት ከመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ጋር በጋራ በመቀናጀት የደህንነት ስራ እየሰሩ ነው።
አጠቃላይ ውይይቱን በተመለከተ ለኢሳት የደረሰው ሚስጥራዊ የድምጽ መረጃ እንደሚያስረዳው በአዲስ አበባ በተቋቋመው መዋቅር ውስጥ የሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች የሚገኙበት ሲሆን፣ መንግስት መኪና፣ ኮምፒዩተር፣ ጽ/ቤትና ሌሎች ቁሳቁሶች ሰጥቷቸው ከመንግስት ጋር በመሆን ጸጥታን ለመከላከል እየሰሩ መሆኑን የአዲስ አበባ የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊው በጉባኤው ላይ ተናግረዋል
ህገመንግስቱ መንግስትና ሃይማኖት የተለያዩ መሆናቸውን ቢደነግግም፣ የመንግስት ባለስልጣናት በሚስጢር በሚያደርጉት ስብሰባ የሃይማኖት ተቋማት የመንግስትን የደህንነት ስራ እንደሚሰሩ መግለጻቸውን ከዚህ ቀደም ኢሳት በድምጽ አስድገፎ ማቅረቡ ይታወቃል።
በዚሁ ስብሰባ ላይ የኦሮምያ የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ በክልሉ የሚታየውን የዋቄ ፈታ እምነት ለማዳከም እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ተናግረዋል። ባለስልጣኑ ለተሰብሳቢው ሲናገሩ፣ ኦነግ በዋቄ ፈታዎች መጠቀም ይፈልጋል፤ የዋቄ ፈታ ድርጅት ተወካዮችን ስትራቴጂ ለመፈተሽ  በስውርም በግልጽም ሰዎችን አሰማርተናል፤ እነሱ በሚያቀርቡት ሪፖርት ላይ ተነስተን እርምጃ እንወስዳለን ብለዋል።
የአዲስ አበባው ተወካይ ከአክራሪነት አንጻር ህዝቡን በአራት ደረጃ በመክፈል ማሰልጠናቸውን የተናገሩ ሲሆን፣ ከ ዲ ወደ ሲ 52 ሰዎች፣ ከቢ ወደ ሲ 4486 ሰዎች ከቢ ወደ ኤ 7980 ሰዎች መለወጣቸውን ተናግረዋል። ሰዎቹ ተለወጡ የተባሉት ቀድሞ ሲከተሉት የነበረውን የሃይማኖት አስተሳሰብ በመተዋቸው ነው።
ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በተሰጡት ስልጠናዎች ላይ ተገንቼ ታዝቢያለሁ ያሉ ሌላ የፌደራል መንግስት ባለስልጣን ደግሞ ከአዲስ አበባ የመጡ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የሚጠይቁዋቸው ጥያቄዎች ፈታኞች መሆናቸውን ገልጸው፣ መንግስት በእነሱ ላይ ትኩረት አድርጎ ሊሰራ እንደሚገባ መክረዋል