mandag 15. desember 2014

ሰኞ ከሰዓትን በቂሊንጦ እስር ቤት

(By: Elias Gebru Godana)
‹‹ሰላም ነን፤ ሰላም ሁኑልን!›› ጦማሪያን አቤል ዋበላ እና ዘላለም ክብረት
‹‹በርቱ፣ በሰላም ለመብታችሁ ታገሉ!›› ኡስታዝ አቡበከር አህመድ
———–
ዛሬ ከነበረን የፍርድ ቤት ውሎ በኋላ ከአሸናፊ አሳምረው ጋር ወደቢሮ አመራን፡፡ ችሎት ቁጭ ብዬ ከችሎት በኋላ ቂሊኒጦ እስር ቤት ሄጂ የምወዳቸውን እና የማከብራውን ወዳጆቼን ለመጠየቅ ዕቅድ ቀይሼ ነበር፡፡ በሀሳብ ብቻ አልቀረም፤ ለአሹ ነገርኩት፡፡ እሱም ለመሄድ ፈቃደኛ ሆነ፡፡ አብነት ረጋሳን ጨምረን ‹‹ምሳ እንብላ፣ ቡና እንጠጣ›› ሳንባባል ጉዞ ወደቂኒንጦ አደረግን!
ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ጎዳና
ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ጎዳና
የፈራረሱ የአዲስ አበባ የተወሰኑ መንገድ አድካሚነታቸው እና አቧራቸውም አይጣም ነበር፡፡ …እስር ቤቱ ደጃፍ 9፡00 ሰዓት ግድም ደረስን፡፡ እኔ ዳንኤል ሺበሺ፣ አቤል ዋበላ፣ ዘላለም ክብረት፣ አቡበከር አህመድ፣ አቡበከር አለሙ …ወዘተ ወዳሉበትና በቅርቡ ታስሬበት ወደነበረው ዞን አንድ ተመዝግቤ እና አስመዝግቤ ገባሁ፡፡ አሸናፊ እነበፍቄ፣ አጥናፍና አብርሃ ደስታ ወዳሉበት ዞን ሁለት አመራ፡፡ አብነት ደግሞ ሀብታሙ አያሌውን ሊጠይቅ ዞን ሶስት ከተመ፡፡
በተለያዩ አጋጣሚዎች መሄድ ሳልችል ቀርቼ ስለነበረ ከእስሬ በኋላ ወደቂኒንጦ ሳመራ የመጀመሪያዬ ነበር፡፡ አልዋሽ ነገር፣ አለመሄዴ የአዕምሮ ዕረፍት ነስቶኛል፡፡ ከእነ አቤሎ፣ ዞላ፣ ዳኒ፣ አብበከር ….ጋር የነበሩኝ ደስ የሚሉ ቆይታዎች በትውስታዬ ውስጥ ብዙ ጊዜ ይመላለሱ ነበር – የእሰራቸው ሁኔታ አሳዛኝነት እንዳለ ሆኖ ማለት ነው፡፡
ዛሬ፣ ሁሉንም አገኘኋቸው፡፡ ባለችን 50 ደቂቃ የቻልነውን ያህል ስለተለያዩ ሀገራዊ ሁነቶች አወጋን፡፡ ቁም ነገርን ተካፈልን፣ በቀልዶችም ዳግም ፈገግ አልን፡፡ የዞላንና የአቤሎን ተረብ አጣታምኩት፡፡ ከምር ደስ የሚሉ ልጆች ናቸው! አምላክ ከሁሉም ጋር ይሁን!
በመጨረሻም የስንብት ደቂቃ ደረሰች፡፡ አቤል እና ዘላለም ‹‹ሰላም ነን፤ ሰላም ሁኑልን!›› የሚል መልዕክትን አድርሰዋኋል፡፡ (በነገራችን ላይ ነገ የፍርድ ቤት ቀጠሮ አላቸው) ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ደግሞ ‹‹በርቱ፣ በሰላም ለመብታችሁ ታገሉ!›› ሲል ቅንና ጠንካራ መልዕክቱን ልባዊ በሆነው ፈገግታ አጅቦ ዘንዝሯል፡፡
እኔ፣ አሹና አብነት ለጥየቃ ከገባንባቸው ዞኖች ስንወጣ በፖሊሶች አመራር ተይዘን ‹‹ለምን ለአንድ ተሳሪ በላይ ጠየቃችሁ?›› በሚል ለ10 ደቂቃ ያህል ደስ የማይል የሃሳብ ልውውጥ ካደረግን በኋላ ስማችን ከመታወቂያችን ላይ ተመዘግቦና ማስጠንቀቂያ መሰል ምላሽ ከሰጠን በኋላ ቂሊንጦን ከነአዋራዋ አቋርጠን ወደሰፈራችን ደርሰናል፡፡

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar